ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የመምሪያ እና የኮሌጅ ሓላፊዎችን አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ

 • ማኅበሩ ሚዲያዎች ታግደው ክሥ እንዲመሠረትበት አቋም ለማስያዝ እየተቀሰቀሰ ነው
 • ልዩ ጸሐፊአቸው ንቡረ እድ ኤልያስ እና አባ ሰረቀ ብርሃን ግንባር ቀደም ቀስቃሾች ናቸው
 • ቋሚ ሲኖዶስ እና ብፁዓን አባቶች፣ ፓትርያርኩን ሲመክሩ እና ሲያስጠነቅቁ ሰንብተዋል
 • ፓትርያርኩ፥“ምን ሲኖዶስ አለና” በሚል የጠሩት ስብሰባ፣ ሕጋዊም መዋቅራዊም አይደለም
pat mathias and Nebured

ፓትርያርኩ እና ልዩ ጸሐፊአቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ

ፓትርያርክ አባ ማትያስ፥ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎችን ዋና እና ምክትል ሓላፊዎችን እንዲኹም የሦስቱን መንፈሳውያን ኮሌጆች የአስተዳደር ሓላፊዎችን፣ ዛሬ፣ የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸው ተሰማ፡፡

በመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባው÷ ማኅበሩ በኮሌጆች ውስጥ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ስለሚገኝበት አሳሳቢ ኹኔታ በሚዲያዎቹ ማስነበቡን ተከትሎ፣ ፓትርያርኩ በክሥ እና በቅስቀሳ መልክ ያሳለፉትን መመሪያ የማጠናከር ዓላማ እንዳለው ተገልጧል፡፡

መመሪያው፣ የተሐድሶዎችን ክሥ የሚያስተጋባና የእውነት ጠብታ እንደሌለው በመተቸት ማኅበሩ ባለፈው ሳምንት በሰጠው የጽሑፍ ምላሽ ክፉኛ ተበሳጭተዋል የተባሉት ፓትርያርኩ፣ በተለይም ከማኅበሩ አገልግሎት ጋር የሚገናኙ የሥራ ዘርፎችን በሚመሩ ሓላፊዎች በኩል ተጽዕኗቸውን ለማጠናክር የሚያስችል ‘የጋራ አቋም’ እንዲያዝ ማሰባቸው ተጠቅሷል፡፡

በክትትል እና በቁጥጥር ስም ለአገልግሎቱ አካሔድ ቢሮክራሲዊ ጫናዎችንና ዕንቅፋቶችን ከመፍጠር በተጨማሪ የማኅበሩ መጽሔት እና ጋዜጣ/ሐመር እና ስምዐ ጽድቅ/ ታግደው ማኅበሩ በኮሌጆቹ የስም ማጥፋት ወንጀል ክሥ እንዲመሠረትበት ለማድረግ መታሰቡም ታውቋል፡፡

በዚኹ ዓላማ አንፃር አቋም እንዲያዝ፣ ቅስቀሳውን በተሰብሳቢዎች ላይ በዋናነት ከሚያካሒዱት የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋር፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል እና የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ ዲን ተስፋዬ ሃደራ ይገኙበታል፡፡


በአባ ሰረቀ ብርሃን የሚመራው የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ፥ የአብነት ት/ቤቶች፣ መንፈሳዊ ኮሌጆች፣ የማሠልጠኛ ማእከላት፣ የአዳሪ ትምህርት ቤቶችና ዘመናዊ ት/ቤቶች፥ በወጥ የትምህርት ፖሊሲና ሥርዐተ ትምህርት ተልእኳቸውን በብቃት እንዲወጡ የማስተባበር ሓላፊነት ያለበት ነው፡፡ በራሳቸው በዋና ሓላፊው በቀረበ የመንፈቅ ዓመት ሪፖርት ግን፣ “ምንም አቅም የሌለው፤ በሞት እና በሕይወት መካከል እያጣጣረ የሚገኝ” በሚል ተብጠልጥሏል፡፡

የመንፈሳዊ ኮሌጆቹም፥ የትምህርት ጥራት፣ የትምህርት ፖሊሲ፣ የመምህራን አመዳደብ…ወዘተ እንዲስተካከል ኮሚቴ ቢዋቀርም በሥራ ላይ አለመዋሉን፤ የደቀ መዛሙርት የመግቢያ መስፈርትና የአቀባበል ሒደት መምሪያው ሳያውቀው እንደነበረው መቀጠሉን፤ ተመርቀው ከወጡት የሚበዙት ደቀ መዛሙርትም በየተመደቡበት እንደማይገኙ በሪፖርታቸው አረጋግጠው ነበር፡፡

ዛሬ፣ እኒኽ ድክመቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ለደረሰው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ የራሳቸው አስተዋፅኦ እንዳላቸው ግልጽ ኾኖ ሳለ፤ አባ ሰረቀ ግን ለመፍትሔው ከመትጋት ይልቅ ሓላፊነታቸውን ተገን አድርገው ከልዩ ጸሐፊው ንቡረ እድ ኤልያስ እና ከኮሌጆቹ አንዳንድ ሓላፊዎች ጋር ዋና ከሣሽና የተቃውሞው አስተባባሪ ኾነው ተሰልፈዋል፡፡


ከተሰብሳቢዎቹ የአብዛኞቹ ሓላፊዎች ተጠሪነት፣ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ አስፈጻሚውን አካል በበላይነት ለሚያስተዳድረው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ነው፤ የተወሰኑትም በተሻሻለው ሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ተጠሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ የኾኑ አካላትን የሚመሩ እንደ መኾናቸው፣ በፓትርያርኩ የተላለፈው የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ መዋቅራዊ አግባብነት የለውም፤ ውሳኔዎቹም ሕጋዊ ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

ይልቁንም ስብሰባው፣ ፓትርያርኩ፣ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔና አሠራር ከመፃረር አልፈው መሠረተ ህልውናውንም እስከ መጠየቅ ለደረሱበት ሰሞናዊ ዓምባገነናዊ እና ኢፍትሐዊ አካሔዳቸው ተጨማሪ ግልጽ ማሳያ ነው የሚኾነው፡፡ 

ፓትርያርኩ ለኮሌጆቹ ያስተላለፉት መመሪያ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አደጋ አኳያ የደቀ መዛሙርቱ ምልመላና ቅበላ፤ የመምህራኑ ሃይማኖትና ክህሎት፤ ሥርዐተ ትምህርቱ እና የማስተማርያ መጻሕፍቱ እንዲፈተሹ በተደጋጋሚ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መንፈስ ጋር እንደማይስማማ በመጥቀስ፣ በቋሚ ሲኖዶስ ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባ ላይ እንዲኹም ብፁዓን አባቶች በተናጠል እና በጋራ በመኾን አካሔዳቸውን እንዲያጤኑት ሲመክሯቸውና ሲያስጠነቅቋቸው መሰንበታቸው ታውቋል፡፡

ምክር እና ማስጠንቀቂያውን ተቀብለው ከመታረም ይልቅ፣ “ይህን ማኅበር አንድ ነገር አናደርገውም ወይ?” በማለት የተወሰኑትና የሚወተውቱት ፓትርያርኩ፣ አስፈላጊ ከኾነም ቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራና ጉዳዩ በምልዓተ ጉባኤ እንዲታይ ሐሳብ ሲቀርብላቸው፣ “ምን ሲኖዶስ አለና!” እስከማለት ነው የደረሱት፡፡

Advertisements

64 thoughts on “ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የመምሪያ እና የኮሌጅ ሓላፊዎችን አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ

 1. yohannes February 11, 2016 at 6:08 am Reply

  yigermal betam mn ayenet gezie new yederesenew?

 2. Anonymous February 11, 2016 at 6:54 am Reply

  ማኅበሩ ራሱን አተልቆና በአባላቱ ብዛት ተመክቶ ያን የመሰለ አንጓጣጭ ደብዳቤ ሲጽፍ የሚመጣውን መገመት ነበረበት፡፡ኮሌጁ የሚመሩት በሊቃነ ጳጳሳት ነው፡፡ቅያሜው ከእነሱ የመነጨ ነው፡፡ለእነሱ ቅያሜ ቢቻል የይቅርታ መንፈስ የተላበሰ ደብዳቤ፣ያም ካልሆነ የማኅበሩ ልሳናት በኮሌጆቹ ላይ ያወጡት ዘገባ በማስረጃ የተደገፈ መሆኑን በሰነድ አስደግፎ ምላሽ መስጠት ቀላል ነበር፡፡ያን ማድረግ አልፈለጋችሁም፡፡ዐላማችሁ ፓትርያርኩንና የተወሰኑ ግለሰቦችን ማጥቃት ስለሆነ የኮሌጁን ቅሬታ ዘላችሁ አባል ለማስጮኽ 12 ገጽ የሽሙጥ ድርሰት ደረሳችሁ፡፡የጋዜጣና የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ጀመራችሁ፡፡ለዚህ ዘመቻ አጸፋ እንደማይመጣ ከገመታችሁ የቦርዳችሁን የመተንበይ አቅም ፈትሹ፡፡የእናንተ ዘመቻ በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ አልነበረም፡፡ለነውር መደበቂያ የሲኖዶስ ስም እየጠሩ ማስፈራራት አዋጭ አይደለም፡፡በጠቅላይ ቤተክሕነት ቀሚስ ስር መሹለክለክም አያዋጣም፡፡የሚያዋጣው አንደበትን መቆጣጠርና በመንበሩ የተሰየሙ አበውን አክብሮ መጓዝ ነው፡፡የዲፕሎማቱ አቡነ ጳውሎስ ዘመን አልፏል፡፡የጫጉላ ሽርሽር ጊዜያችሁ አልቋል፡፡አሁን ሕጉና መዋቅሩ ነቁጥ ሳትጎል ይተገበራል፡፡በተቆርቋሪነት ስም አኩኩሉ እየተጫወቱ ጥሰት አለፈበት፡፡ይሄንን ሀቅ በሦስት ዓመት የፓትርያርኩ ቆይታ ካልተረዳችሁ ችግሩ የእሳቸው አይደለም፤የእናንተ ነው፡፡

  • Anonymous February 11, 2016 at 11:16 am Reply

   ማህበሩ እራሱን ያተለቀበት ቀን ሳይሆነ የነበረው ትላልቅ ስራዎችን የሰራበት ቀናት ሳይሆን አመታት ነበር የነበሩት፡፡ መናፍቃን ማህበሩ እንዳይኖር ምንም ቢተጉም ምንም አይሆንም፡፡ ማንም ሲያጠፋ መገሰጽ አለበት እንጂ እያሞጋገሰ ከኖረ ክርስትና አይደለም፡፡ ፓትርያሪኩ የጻፉት ደብዳቤ ልክ አይደለም ማለት እሳቸውን መገዳደር መስሎ ከታየህ ችግሩ ያንተ ነው፡፡ ሰው ሲከሰስ ትክክል ካልሆነ ክሱ መቃወም ያለ ነገር ነው፡፡ ጠርተው አለማናገራቸው ችግሩ የራሳቸው ነው ማህበሩን የከሰሱበት ነገር ሁሉም መናፍቃን ያራግቡት የነበረ መሆኑን ቃል በቃል ሳይለወጥ ያየነው በመሆኑ ከዌብሳይት ሰብስበው የሰጡዋቸው በመሆኑ ማህበሩ ይህንን መቃወሙ ተገቢ ነው ያስብለዋል እንጂ ለምን እንዲህ ተናገርክ አያሰኘውም፡፡ ማህበሩ መቸም ቢሆን በማህበሩ ብዛት ተማምኖ አያውቅም ምን አልባት ለሚሰራው ስራ አዎን ይተማመንባቸዋል፡፡ ጳጳሳትንም ቢሆን መሹለኪያ አያደርግም ይልቁንም የምክር አገልግሎት ይሰጠዋል እንጂ፡፡ ኮሌጆች ችግር እንዳለባቸው ቅዱስ ሲኖዶስ በስብሰባው ሲነጋገር የኮሌጆቹም የበላይ ጠባቂ ጳጳሳት ጉዳዩን አምነውበት እነሱም የተቀበሉት ነው በማህበሩ በዝርዝር መታየቱ ምን ችግር አለው፡፡ ስለዚህ ለማህበሩ ውድቀት የምትተጉ ታፍራላችሁ አለቀለት ስትሉ ስንት ዘመን አለፋችሁ አሁንም ታፍራላችሁ ገና፡፡

  • Anonymous February 11, 2016 at 11:47 am Reply

   እንቶ ፈኝቶና ባዶ ዘራፍነት የተሞላ አስተያየት፡፡ባዶ ጩኸት፡፡ ፓትርያርኩም ቢሆኑ ከሕጻን ልጅ ማይጠበቅ ስራ ነው የሚሰሩት፡፡ እንደተለመደው የቁራ ጩኸት ጮኸው ይወጣሉ፡፡ የአቋም መግለጫ ያወጣሉ፡፡ ይፎክራሉ፣ ያጨበጭባሉ፡፡ ከአዳራሽ ውጪ ግን ሁሉም በነበረበት ይቀጥላል፡፡…

   • Anonymous February 12, 2016 at 11:44 pm

    Amlak hoiy bemengistih sitimeta asbegn. Ariya yemihon teftual ena ante tebiken!

  • ዳሞት February 11, 2016 at 2:59 pm Reply

   ለanonymousFebruary 11, 2016 at 6:54am
   ዘባተሎና የፕሮፖጋንዳ አስተያየትህን ለመለጠፍ በቁራ ክንፍህ ማንም ሳይቀድምህ ትበራለህ። ሥትፈልግ አንድ ጳጳስን ጳጳሳት በማለት ጳጳስና ጳጳሳት የሚለውን ታድበሰብሳለህ። በቀሚስ መሹለክለክ እያልክም የቤተክርስቲያኗን አባቶች(ጳጳሳቱን) እንዲሁም ልታመልካቸውና አምላክ ብለህ ልታውጅላቸው እየከነፍህላቸው ያሉትን ፓትራርኩንም ትወርፋለህ። ነው ፓትራርኩ የሚለብሱት ጥብቆ ቁምጣ ወይስ ፍርኪ ጂንስ ነው? ነው ሱፍ በከረባት ነው። ነጠላችሁ እስኪበን እያልክ የተሳደብህ ትሁት ካህን አይደለህ። እንግዲህ ፓትራርክ ማቲያስ ጊታር ሳክነስፎን፣ ፒያኖ አርሞሪካ የመሳሰሎት ማወጅና እኔ አምላክ ነኝ ማለት ነው የቀራቸውና የሚሆነውን ለማየት እንጓጓለን። ሲኖዶሱ ኤኔነኝ ካሉ ድምፀቱ ከመንፈስቅዱስ አይደለምና ከሳቸው መልካም ለመስማት አሥቸጋሪ ነው። እናም አንተም ባለሱፉ በክፉ መሰልጠን ደስታህን አጣጥም።

  • Anonymous February 11, 2016 at 3:01 pm Reply

   “አፍ ሲከፈት ቅንጭላት ይታያል” አሉ አበዉ: የሆንህ ክፍት አፍ ነገር ነህ እሽ ደደብ፡፡ ለመሆኑ ደብዳቤውን ሙሉ በሙሉ ያነበነብኸው አትመስልም ! የሀራጥቃወች መጫኛ መሆንህን ለማረጋገጥ ብዙም ዶሴ ማገላበጥ አያሻኝም፡ ምክኒቱም የተከፈተው አፍህ ከዛ በላይ ምስክር ሰለሚሆን፡፡ በአንተ ቤት አማረኛን ተጠቅመህ ሞተሃል ባክህ!

   “Million idolates have no power to himmulate MK! Because; if you know that, God is with us. Your vomit haven’t matter on us because it was already done on our healer God (Jesus) by the person’s just like you when he was in this terrible world.”

   በነገራችን ላይ የቅዱሱ ማህበር አባል አልነበርሁም ካሁን በሁዋላ ግን ነኝ! ከቤተ ክርስቲያን ልጆች ጋ አብሬ መሞት ሳይሻለኝ አይቀርም!!!

   • Anonymous February 12, 2016 at 10:59 am

    ይሄን አንደበት ይዘህ ታዲያ የት ልትገባ ነበር?በል በፍጥነት ተቀላቀላቸውና የስድቡን ሰልፍ አድምቁት፤አሳምሩት፡፡ለቤተክርስቲያን ያላችሁን ፍቅር የምትገልጹት ከእናንተ ጋር ያልገጠመ አስተያየት የተናገረውን ሁሉ በስድብ በማጥረግረግ ነው፡፡መቼም የኮርሰኛ መጨረሻ ይኽው ነው፤ጥቂት የግቢ ጉባኤ ኮርስ ትወስዱና የቀረውን በስድብና በፍረጃ ትሞልታላችሁ፡፡

  • Anonymous February 12, 2016 at 1:28 am Reply

   ቱልቱላ

  • Tadesse February 15, 2017 at 11:59 am Reply

   ወዳጄ ማኅበሩን በማታውቅበት ደረጃ ከመዘባረቅ ብትቆጠብስ!
   እንደለመድከው ለተሀድሶ አራግብ።

 3. Anonymous February 11, 2016 at 7:02 am Reply

  we are T.K.P with our patriaric Matiys the strong father of Ethiopian orthodox church!!!!! with out any pre_ condition mhaber kidusan is not orthodox but the other church( dinomination )
  b/c he declar fasting and other dogmatic things!!! till agnist the church fathers and the colleges but now aday the members and leaders of the mahiber kidusan learn in the three colleges specally in trinity college so why do you learn first if the college is protstant/ tehadiso look
  the memebrs of orthodox church? why the Mk meet with colleges face to face? why do you come
  behaind of the scrine ( pls come with evidence to our colleges b/c l know our colleges are
  agnist ant tehadiso! now open door in three colleges. I Fill so mach in mhiber kiduan mission!!! BY BY BY !!!!!!!

  • Anonymous February 11, 2016 at 9:59 am Reply

   yalegabahen batawera melekam new. Yebkahal.
   .

   • Zeyo Gch February 11, 2016 at 11:57 am

    የኖህ መርከብ የዋሁንም አውሬውንም ጭኖ እንደነበረው ሁሉ ዛሬም በመርከብ የተመሰለችው ቅድስት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን እንደ እናንተ አይነቱን ሰው መሰል አውሬ በውስጧ ተሸክማ ይዛለች፡፡ ጥቅም የሌላችሁ የመናፍቃን ተላላኪ ሆዳሞች አትልፉ በክርስቶስ ደም የተመሰረተችውን ቤተ ክርስቲያን ማንም አይችላትም፡፡ ለእንደ እናንተ አይነቱ አላዋቂ ቀርቶ ለሌሎችም አልተንበረከከችም፡፡

  • Anonymous February 11, 2016 at 2:34 pm Reply

   You are evil. Setan nahi awurtah motahal. Mehiberu beyinor nuro zare hulechinim aderesh nebern. Zaragnoch Gubegnoch. Dagmo tewarelechiwu. Betakirisitiyan yehulechinim nati inente menafikanoch titafelechiw Isua hulem tinoralech

  • Anonymous February 11, 2016 at 3:02 pm Reply

   Million idolates have no power to himmulate MK! Because; if you know that, God is with us. Your vomit haven’t matter on us because it was already done on our healer God (Jesus) by the person’s just like you when he was in this terrible world.

 4. Anonymous February 11, 2016 at 7:41 am Reply

  Mk Egziabher yagizzewal be ewunet ye abatocachin amlak ayetewonm

 5. Goytom February 11, 2016 at 7:55 am Reply

  ENIH SEWYE MEKARI ALSEMA ALU KISEFEGN KISEFEGN EYALU NEW
  ELIAS ABUNE PAULOSN DEFA DEGMO ENIHIN LIDEFA DEFA KENA EYALE NEW.

 6. Abera February 11, 2016 at 8:03 am Reply

  yigermal patriariku eko enkuan talakuwan tarikawituan EOTC kerto and atbiya bete kristian memrat yemayichilu nachew. sinodosu ersachewin zewer adrgo lela abat yaskemitilin.
  bete kristianin awaredwat. eliasina aba sereke kezia gibi kalwetu bete kristian selam atagegnim. huletu hager selam sitihon ena bete kristian selam sitihon aywedum. mikniatum eyateramesu meblat lemdewal ena.

 7. ገነተማርያም February 11, 2016 at 9:11 am Reply

  “እግዚአብሔር ምን አለ?”። እግዚአብሔር ትዕግስትና ማስተዋል ይስጣቸው። “ለቤተክርስቲያናችን ምን እናድርግ? ምዕመኑን እንዴት ወደእግዚአብሔር እናቅርብ? ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ህልውናቸው እንደተጠበቀ፥ቤተክርስቲያናችን ስርዓቷ፥ቀኖናዋ ተጠብቆ፥ ሳይበረዝ ሳይከለስ ለተተኪ ትውልድ እናስተላልፍ……ስንቱን ልዘርዝረው? ሚሊዮኖችን ከነጣቂ ተኩላ የታደገን ማህበር እንቅልፍ የነሳቸው በሚመስል መልኩ ለማፍረስ መቋመጥ የጤና አይመስለኝም። ማህበረ ቅዱሳን ስራችሁ ሕያውና ምስክር ነው!!! ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ቅዱሳኑ፥ቢያንስ በግቢ ጉባዔ ያለፈ ትውልድ ስራችሁን ያውቃል፥ የገዳም አባቶችና እናቶች የአብነት ትምህርት ቤቶች፡ተዘግተው የነበሩ አብያተ ክርስቲያን ራሱም ቅዱስ ሲኖዶስ እውነት ካለች ምስክሮች ናቸው።

 8. Anonymous February 11, 2016 at 9:19 am Reply

  labatachin libona ystilin sint misera eyale geta hoy sman selotachinn

  • anonymously February 11, 2016 at 10:19 am Reply

   Ye Ayhud Shengo ; tsehafit Ferisawiyan ; ye kahinat alekoch; ye Sedukawyan legizew tebabirewina teteraritew Kirstos lay endeferedubet!! Eske Arib( Friday) dires new !! Besenibete Kristian Ehud( Sunday) hulu yitawekal!! Tsinu!!

 9. Anonymous February 11, 2016 at 9:57 am Reply

  Leuel Egziaberher hoye? Seyetanina serawitune fetinehe eser! Betekertiyanena miemenoch lejochan awitalen; tebekenem. Fekadih bihon ahunun feredlen?

 10. Anonymous February 11, 2016 at 10:19 am Reply

  Tseliyu Be Ente Selam!

 11. tewodros February 11, 2016 at 10:26 am Reply

  አወይ አባ ማትያስ አረ እባክዎት ወደ ልቡናዎ ይመለሱ፣የዘመናችን አኪላስ አይሁኑ

 12. Rahel February 11, 2016 at 10:37 am Reply

  ይህንን የተቀደሰ ስራችሁን ለማደናቀፍና ለማስቆም እንደማይችል ያወቀው ዲያብሎስ አገልግሎታችሁን ለማዘግየት በተለያየ መንገድ እየፈተናችሁ መሆኑን እኔ ለእናንተ ልናገር አይገባኝም በየደረሳችሁባቸው ገዳማት ሁሉ ያሉት የቅዱሳን አባቶቻችን ፀሎት ይርዳችሁ ድንግል ወላዲተ አምላክ ከለላ ትሁናችሁ

 13. Anonymous February 11, 2016 at 10:40 am Reply

  ant abra ye mahibre kidusan telalaki arefeh betkemet yehalal ! yeh yant abat seytan new b/c tesdabi sew orthodox aydelemna ante teraz netek leba!!!!!

 14. Getaneh Kassie February 11, 2016 at 10:42 am Reply

  ?እረኞች? በጎችን ከጋጥ ሲያባርሩ፣
  በጎችም በረግገው ሲሉ ይብላኝ ዱሩ፣
  ተኩላዎች በደስታ አቅራሩ ፎከሩ።

 15. Anonymous February 11, 2016 at 11:04 am Reply

  ፓትርያሪኩ ለነገር ሰዎችን ከሚሰበስቡ ምን አለበት ከጸደቀ ስንት አመት የሆነውን የሰው ሃይልና የፋይናስ ስርዓቱ ዘመናዊ ሆኖ እንዲሰራ ገዳማትንና አድባራትን ቢሰበስቡና መመሪያ ቢሰጡ፡፡ ምን አለበት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ካህናትን ጠርተው ስለ ችግሮቻቸው ቢያወያዩዋቸው፡፡ ምን አለበት ገዳማትን የአብነት ትምህርት ቤቶችን ችግር ለመቅረፍ ጠርተው ቢያወያዩዋቸው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስን የሚንቅ ፓትርያሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እኝህን አየን፡፡ ማህበሩ ምንም አይሆንም ምክንያቱም ምንም ይበሉ ወሳኙ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ወሮ በላ ሰብስበው ቢያናግሩ ወደ ህግም ቢወስዱት ሕግ ያለበት ሀገር ስላለን ማህበሩም እስካሁን ህግን ማእከል ባደረገ መልኩ ነውና ሲንቀሳቀስ ሲሰራ የነበረው ምንም ችግር የለውም፡፡ ይልቁንም ስለህግ ምንም የማያውቁ ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ በዙሪያቸው ያሉ መናፍቅና ጉበኞች ዘራፊዎች የሚመክሩዋቸውን ትተው ሳይዋረዱ አርፈው ቢቀመጡ የተመረጠ ነው፡፡

  ይህቺ ቤተክርስቲያን በሕገ እግዚአብሔር በቃለ አዋዲ እንዲሁም በፍትሀ ነገስት የምትተዳደር እንደመሆኑ የዘመናችን አዋቂ ነን ባዮች በፍትህ መንፈሳዊ መዳኘት ሲችሉ ዓለም ያውራልን በሚል ከንቱ ክስ ይዘው ወደ ዓለም መሄድን መረጡ ያሳፍራል፡፡ ፓትርያርክ ሆይ የምትሰሩትን እያጤኑ ያድርጉት፡፡ ሃሳቡ የእርሶ ካልሆነ የሰዎችን አስተሳሰብ ማራገብ አይገባዎትም፡፡ ማህበሩ የሚገባውን መልስ ሰጥቶዋል የሰጠው መልስ ካልጣመ ጠርቶ ማናገር ይህ ከመንፈሳዊ ያውም የበላይ አባት ከሚባሉ የሚጠበቅ ሲሆን አሁን ግን ከአህዛብ የሚጠበቅ ስራ እያየን ነው፡፡ የሚያወሩሎት ሰዎች ስለማህበሩ ተቃራኒ ነገር ሁሌም የሚናገሩ ከሆነ ሰውየውን ሊመረምሩት ከአጠገብዎ ሊያርቁት ይገባል፡፡ የእርስዎ ትልቅ ችግር በኔ ዘመን ለምን እንዲህ ሆነ ይባላል የሚልም አንድምታ አለው፡፡ ዘመኑ እየከፋ የሚሄድ በመሆኑ ነገሮች እየከፉ ቢሄዱም መደነቅ የለቦትም ይልቁንም በክስተቶች ላይ አጽንኦት ሰጥተው ቤተክርስቲያኒቱን ለማዳን መጣር ይገባዎታል እንጂ፡፡

  ለቤተክርስቲያ በነጻ አገልግሎት ልስጥ ያለን፤ ቤተክርስቲያኒቱ በመናፍቃን መከበቡዋን ውስጥዋም ገብተው ሲንቀሳቀሱ በጠቆመ፤ ህግና ስርዓት ይከበር ባለ፤ እናንተ መስራት ያለባችሁን ለመስራት በታገለ፤ ዶግማና ቀኖና ይከበር ባለ፤ ቤተክርስቲያን ህልውናዋ ይከበር ባለ፤ ገዳማትንና አድባራትን ምዕመናንን አስተባብሮ በረዳ የምን ማሳደድ ነው፡፡ ባይሆን ስደት የሚገባቸው ከስርዎት ያሉት ሙሰኞችና በዝባዦች ናቸው፡፡ አሁንም ደግመን ደጋግመን የምንለው ማህበሩን በፈቃድዎ ምንም ሊያደርጉ እንደማይችሉ ይወቁ፡፡ ማህበሩን የመሰረተው እግዚአብሔር እንጂ ሰዎች አይደሉም፡፡ ክስ ለማህበሩ አዲስ አይደለም ምን አልባት በርስዎ ዘመን ማህበሩን በመክሰስ ሪከርድ ሊሰብሩ ፈልገውም ከሆነም አያዋጣዎትም እንጂ ሊሰብሩ ይችላሉ፡፡ እንደተከበሩ ቢቀጥሉ ይሻሎታል፡፡

  የተሸሙት ማህበርን ለማፍረስ ሳይሆን ማህበርን ለማጠንከር ሊሆን ይገባል፡፡ ከቀደሙ አባቶች ብዙ ተማሩ ለምሳሌ ከቀደሙት አቡነ ጎርጎርዮስ ከግብጹ አቡነ ሺኖዳ፡፡ ምን አለበት በህይወትዎ እንደ አቡነ ሺኖዳ መጻህፍትን እየጻፉ ለልጆችዎ ቢያበረክቱ የሚያምርቦት እንዲህ ቢያደርጉ ነበር፡፡ ገዳማት መሄድ መጸለይ እራስን በስራ መወጠር አይሻልም ፡፡ የሚበጅዎትን ያውቁት ነበር ግን በማይበጅዎት ተወጠሩ ፡፡ ስለዚህ አስር ጊዜ ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ ነውና ለሚያስተላልፉት ነገር ሁሉ በአይምሮ ሆነው ይወስኑ፡፡ ስልጣኖት ለወንበዴዎች ሳይሆን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ነውና የተሰጠዎት ያስተውሉ፡፡ ልቦና ይስጥዎት ፡፡

  • Anonymous February 11, 2016 at 3:51 pm Reply

   እኝህ አባት ግን በጤናቸው ነው? ያናድዱኝ ነበር አሁን ግን እያሳዘኑኝ መጡ ምክንያቱም ሰ80 እና ከዛ በላይ እድሜያቸው የሞቱላትን የቤተክርስቲያን እንደዚእ ማወክ እግዚአብሔር ይወድላቸዋል በእውነት በጣም ያሳዝናሉ ዘረኝነት ፈተና ሆነባቸው ምንም ደካማ ብንሆን እስቲ ሁላችን በፀሎት እናስባቸው

   አባታችን ማህበረ ቅዱሳን እኮ በደጋግ አባቶች ፀሎት አልፎ ተርፎም በእግዚአብሔር ፈቃድ የተመሰረተ ማህበር ነው እርሶ እንደሚሉት በአንድ ጊዜ ማፍረስ አይቻልም ቅዱሳን ለምን ቅዱሳን እንደተሰኙ ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው።በእልልታና በጭብጨባ ቅድስና አይገኝም እንደውም መልካም እየሰሩ መገፋታቸው የበለጠ ትሩፋት ነው የሚያበቃቸው

   ይብላኝ ለእርሶ እንዴት ያሳዝናሉ ድሮም ሳጥናኤል ስራው ሰውን ከገነት ማባረር ነው አባታችን እባክዎን ወደ ልብዎ ይመለሱ የቅዱሳን አምላክ ይርዳዎ አሜን።

 16. Anonymous February 11, 2016 at 11:12 am Reply

  mechetelemdena ke tekula zemdnaa…………EGZIABHER EKO BEZUFANU ALEEEE,ANFERAM

 17. getachew February 11, 2016 at 11:18 am Reply

  ጸልዩ በእንተ ቤተ ክርስቲያን
  በስርዓተ ቅዳሴያችን ዘወትር እንደምንሰማዉ እንደምናሰማዉ፤ ቀድሰን እንደምናስቀድሰዉ ጸሎት የችግሮች ሁሉ መልስ የያዘ ቁልፍ መንፈሳዊ በትር ነዉ፡፡ በየጊዜዉ ማለትም ከአዉሬ ዲያብሎስ ክህደት እና ከሰማይ መላእክት ጦርነት ቀጥሎ እስከ አሁን ባለዉ የጠሀድሶ መናፍቃንና ሌሎች የዉስጥ እና የዉጭ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እየተዋጉ ነዉ፡፡ ይህ ጦርነት ለጊዜዉ ቀዝቃዘዉ ጦርነት ቢባልም የመስቀል ጦርነት በመሆኑ መጨረሻዉ የዓመለም ፍጻሜ መሆኑ ግልጽ ነዉ፡፡
  የጦርነቱ አይነት መንፈሳዊ፤ የጦርነቱ ሜዳ፤ ክርስቶስ እግዚአብሔር በደሙ የመሰረታት ቅድስት፤ ሐዋርያዊት፤ ኩላዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን (በሶስቱም ትርጉም ማለትም በምእመናን፤ በማህበር እና በህንጻ ቤ/ክን አፈታት ትርጉም ማለተ ነዉ)፤ የጦርነቱ ምክኒያት መንፈሳዊ ፍትህ እና እዉነት ብሎም ሰማየዊ ርስት፤ የጦርነቱ ቀስቃሽ እና ጠላት ዲያብሎስ እና ፈረሶቹ (የተሀድሶ መንፈስ አቀንቃኞች፤ ፖለቲከኞች፤ አህዛብ ነገስታት እና ለምድ የከለበሱ ተኩላዎች ከዲያቁና-ጵጵስና ማእረግ የገዙ ሲሞናዉያን)፤ በጦርነቱ ሊገደሉ የሚፈለጉ የተዋህዶ ምእመናን፤ ማህበራት እና እዉነተኞች አባቶች በሙሉ እንድሁም ቅዱሳን በሙሉ ናቸዉ፡፡
  ግን ለምን እንደት? ቤተክስርቲያን ድል የነሳች (በሰማይ ያሉ ቅዱሳን ህብረት) እና በጦርነት ላይ ያለች እና ተጋድሎዋን ያልጨረሰችዉ ይህችዉ ምድራዊት የእግዚአብሔር ኤምባሲ ቤተከርስቲያን በመሆኗ ይህም በወንጌል ጠላት የዘራዉ እንክርዳድ እና ፈጣሪ የዘራዉ ንጽህ ስንዴ ዘር አብረዉ እስከ መከር እንደሚቆዩ ስለተነገረን አንደነቅም፤ ግን ዲያብሎስ የእናን ብልቶች መሳሪያ አድርጎ ሲመጣ ስናይ ከራሳችን ብልቶች ጋር ዉጊያ እንገጥማለን፡፡ እነዚህ ብልቶች በህክምና በንስሀ የማይዱ ከሆነ ሌሎችን ጤነኛ አካላትን በሽታ እንዳያስተላልፉብን ስለምንፈልግ እያዘንም ቢሆን ቆርጠን ወደ እሳት እንጥላቸዋል፤ ፈጣሪ በቸርነቱ የንስሃ ልብ ሰጥቶ እንዲመልሳችዉ ግን እንጸልይላቸዋልን፤ ዳግም ከሞቱበት ከተነሱ እንቀበላቸዋል፤ ይህን የመወሰን ስልጣን በመንፈስ ቅዱስ የሚመራዉ የቅድስት ቤ/ክን አባቶች ጉባኤ ቅዱስ ሲኖድዮስ ብቻ ነዉ፡፡
  ሰለዚህ አዉሬወ ለምን ይጮሃል?
  1. ምላስ እንጅ እዉነተኛ መንፈሳዊ መልስ ስሌለለዉ
  2. እምነት እንጅ ሃይማኖት እና ምግባር የለመዉምና
  3. ድፍረት እንጅ መንፈሳዊ እዉቀት የለዉምና
  4. ወሸት እና የዉሸት አባት ነፍሰ ገዳይ በመሆኑ የእርሱ ሰላም ጦርነት ብቻ በመሆኑ
  5. ግብዓተ መሬቱ መጨረሻዉ ጊዜ እንደደረሰ ስላወቀ
  6. መምሰል እንጅ መሆን ስለማይችል፤ ሳይሆን የብርሃን መላእክ መስሎ በእኛዉ ሰዎች እኛን በድብቅ እና ስጋ ለብሶ በገሃድ ይዋጋል፤
  ስለዚህ ምን እናድርግ?
  1. መጀመሪያ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ስለ አንድት ሃይማኖት አስተምሮ ጠንቅቀን እንወቅ ለዚህም እንጸልይ
  2. የቤተ ክርስቲያን ባህርያት በመረዳት ሌሎች ድምጾችን በመለየት በመረጃ ተደገፈ መፍትሔ እንያዝ፤ ለእዉነተኛ የቤ/ክን ምእመናንና አባቶች እናስረዳ
  3. በቤተ ክረስቲያን አስተዳደር ከአጥቢያ እስከ መንበረ ጳትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያሉ የተሰገሰጉ ተኩላዎችን ከእዉነተኛች በጎች እንለይ፤ በመቀጠል ከእነርሱም እርሾ እንጠበቅ
  4. ለመወሰን አንቸኩል፤ ለመጸለይ ለስጋችን እረፍት አንስጥ
  5. ቅዱስ ፓትርያሪኩ አሁን የያዙት የግለሰብ እንጅ የቤተ ክረስቲያን አቋም እና ድምፅ ባለመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስን ዉሳኔ ከእግዚአብሔር እንጠብቃለን፡፡ እርሳቸዉ ሀሳባቸዉም አካሄዳቸዉም ለቤተ ክርስቲያን የማይጠቅም ኔቶርካቸዉ የተጠለፈ ነዉ፡፡ እዉነታዉ ይህ ነዉ፤ አንደ አባትነታቸዉ አክብሬ ስህተታቸዉን ግን እኮንናለሁና፡፡
  6. የሜዲያ ጦርነቱ ወደ እዉነት እንጅ ወደ ሞት እንዳይወስድን ሁላችንም እናስብ፤ እንጸልይ፤
  7. የተሀድሶ እና ድብቅ አላማዉን ለማወቅ ለምትፈልጉ በሙሉ የመረጃ ችግር የለም ፤ በዚህም ቅዱስ ሲኖዶስ ዉሳዎችና የማኅበረ ቅዱሳን ትኩስ እና ነባር መረጃዎች ከበቂ በላይ ናቸዉ፤ ስለዚህ የጸረ ተሀድሶ ዉጊያዉን ይቀጥላል፤ ድል ለተዋህዶ ልጆች፡፡
  ባጠቃላይ አባ ማትያስ ሆይ ወደ ገዳም ገብተዉ ከሰዉ ተለይተዉ፤ ከተሀድሶ እና ጥቅመኛ ጅቦች ድምፅ ርቀዉ ስለ ጉዳዩ ይጸልዩበት ዘንድ የልጅነት ሀሳቤ ነዉ፤ ይህ ካልሆነ ግን ሁሉም የራሱን ገመድ ያሰጥራል፡፡ ቸር ያሰማን፡፡

  • Anonymous February 24, 2016 at 5:39 am Reply

   K.H. YASEMALIN

 18. ile tinebiru February 11, 2016 at 11:29 am Reply

  alarif yalech…ale yahegere sew. Ine and neger astawisalehu, kezih befir awasa lay beneberew huneta, abune fanuael bekahinatuna begziabher teteltew neber. imama akbetebetachew, manim saynagerachew sidibun meatun azigodegodut, bemecheresha… isachewuna leke melaku layteyayu tesenebabetu… izaw teblew teshegnu. Ignih fiyel yimesil tsim bicha yehono bado chikilat shimagle biyarfu ayshalachewum gin???

 19. Anonymous February 11, 2016 at 11:45 am Reply

  ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው አትታወኩ ይህ ሊሆን ግድ ነው ማህበረ ቅዱሳንን ፈጣሪ ይጠብቅልን

 20. Anonymous February 11, 2016 at 11:49 am Reply

  ፓትርያርካችን፣ እብድ ውሻ መስለዋል፡፡ ልቦና ይስጣቸው፡፡

 21. Asnake February 11, 2016 at 12:12 pm Reply

  አሁንም ደግመን ደጋግመን የምንለው ማህበሩን በፈቃድዎ ምንም ሊያደርጉ እንደማይችሉ ይወቁ፡፡ ማህበሩን የመሰረተው እግዚአብሔር እንጂ ሰዎች አይደሉም፡፡ ክስ ለማህበሩ አዲስ አይደለም ምን አልባት በርስዎ ዘመን ማህበሩን በመክሰስ ሪከርድ ሊሰብሩ ፈልገውም ከሆነም አያዋጣዎትም እንጂ ሊሰብሩ ይችላሉ፡፡ እንደተከበሩ ቢቀጥሉ ይሻሎታል፡፡

  የተሸሙት ማህበርን ለማፍረስ ሳይሆን ማህበርን ለማጠንከር ሊሆን ይገባል፡፡ ከቀደሙ አባቶች ብዙ ተማሩ ለምሳሌ ከቀደሙት አቡነ ጎርጎርዮስ ከግብጹ አቡነ ሺኖዳ፡፡ ምን አለበት በህይወትዎ እንደ አቡነ ሺኖዳ መጻህፍትን እየጻፉ ለልጆችዎ ቢያበረክቱ የሚያምርቦት እንዲህ ቢያደርጉ ነበር፡፡ ገዳማት መሄድ መጸለይ እራስን በስራ መወጠር አይሻልም ፡፡ የሚበጅዎትን ያውቁት ነበር ግን በማይበጅዎት ተወጠሩ ፡፡ ስለዚህ አስር ጊዜ ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ ነውና ለሚያስተላልፉት ነገር ሁሉ በአይምሮ ሆነው ይወስኑ፡፡ ስልጣኖት ለወንበዴዎች ሳይሆን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ነውና የተሰጠዎት ያስተውሉ፡፡ ልቦና ይስጥዎት ፡፡

 22. Asnake February 11, 2016 at 12:13 pm Reply

  “እግዚአብሔር ምን አለ?”።

 23. Zeyo Gch February 11, 2016 at 12:15 pm Reply

  የኖህ መርከብ የዋሁንም አውሬውንም ጭኖ እንደነበረው ሁሉ ዛሬም በመርከብ የተመሰለችው ቅድስት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን እንደ እናንተ አይነቱን ሰው መሰል አውሬ በውስጧ ተሸክማ ይዛለች፡፡ ጥቅም የሌላችሁ የመናፍቃን ተላላኪ ሆዳሞች አትልፉ በክርስቶስ ደም የተመሰረተችውን ቤተ ክርስቲያን ማንም አይችላትም፡፡ ለእንደ እናንተ አይነቱ አላዋቂ ቀርቶ ለሌሎችም አልተንበረከከችም፡፡

 24. Anonymous February 11, 2016 at 12:21 pm Reply

  ይህንን የተቀደሰ ስራችሁን ለማደናቀፍና ለማስቆም እንደማይችል ያወቀው ዲያብሎስ አገልግሎታችሁን ለማዘግየት በተለያየ መንገድ እየፈተናችሁ መሆኑን እኔ ለእናንተ ልናገር አይገባኝም በየደረሳችሁባቸው ገዳማት ሁሉ ያሉት የቅዱሳን አባቶቻችን ፀሎት ይርዳችሁ ድንግል ወላዲተ አምላክ ከለላ ትሁናችሁ

 25. Anonymous February 11, 2016 at 1:23 pm Reply

  Lets see who wins! you will see on your eyes too.ፓትርያሪኩ ለነገር ሰዎችን ከሚሰበስቡ ምን አለበት ከጸደቀ ስንት አመት የሆነውን የሰው ሃይልና የፋይናስ ስርዓቱ ዘመናዊ ሆኖ እንዲሰራ ገዳማትንና አድባራትን ቢሰበስቡና መመሪያ ቢሰጡ፡፡ ምን አለበት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ካህናትን ጠርተው ስለ ችግሮቻቸው ቢያወያዩዋቸው፡፡ ምን አለበት ገዳማትን የአብነት ትምህርት ቤቶችን ችግር ለመቅረፍ ጠርተው ቢያወያዩዋቸው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስን የሚንቅ ፓትርያሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እኝህን አየን፡፡ ማህበሩ ምንም አይሆንም ምክንያቱም ምንም ይበሉ ወሳኙ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ወሮ በላ ሰብስበው ቢያናግሩ ወደ ህግም ቢወስዱት ሕግ ያለበት ሀገር ስላለን ማህበሩም እስካሁን ህግን ማእከል ባደረገ መልኩ ነውና ሲንቀሳቀስ ሲሰራ የነበረው ምንም ችግር የለውም፡፡ ይልቁንም ስለህግ ምንም የማያውቁ ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ በዙሪያቸው ያሉ መናፍቅና ጉበኞች ዘራፊዎች የሚመክሩዋቸውን ትተው ሳይዋረዱ አርፈው ቢቀመጡ የተመረጠ ነው፡፡

  ይህቺ ቤተክርስቲያን በሕገ እግዚአብሔር በቃለ አዋዲ እንዲሁም በፍትሀ ነገስት የምትተዳደር እንደመሆኑ የዘመናችን አዋቂ ነን ባዮች በፍትህ መንፈሳዊ መዳኘት ሲችሉ ዓለም ያውራልን በሚል ከንቱ ክስ ይዘው ወደ ዓለም መሄድን መረጡ ያሳፍራል፡፡ ፓትርያርክ ሆይ የምትሰሩትን እያጤኑ ያድርጉት፡፡ ሃሳቡ የእርሶ ካልሆነ የሰዎችን አስተሳሰብ ማራገብ አይገባዎትም፡፡ ማህበሩ የሚገባውን መልስ ሰጥቶዋል የሰጠው መልስ ካልጣመ ጠርቶ ማናገር ይህ ከመንፈሳዊ ያውም የበላይ አባት ከሚባሉ የሚጠበቅ ሲሆን አሁን ግን ከአህዛብ የሚጠበቅ ስራ እያየን ነው፡፡ የሚያወሩሎት ሰዎች ስለማህበሩ ተቃራኒ ነገር ሁሌም የሚናገሩ ከሆነ ሰውየውን ሊመረምሩት ከአጠገብዎ ሊያርቁት ይገባል፡፡ የእርስዎ ትልቅ ችግር በኔ ዘመን ለምን እንዲህ ሆነ ይባላል የሚልም አንድምታ አለው፡፡ ዘመኑ እየከፋ የሚሄድ በመሆኑ ነገሮች እየከፉ ቢሄዱም መደነቅ የለቦትም ይልቁንም በክስተቶች ላይ አጽንኦት ሰጥተው ቤተክርስቲያኒቱን ለማዳን መጣር ይገባዎታል እንጂ፡፡

  ለቤተክርስቲያ በነጻ አገልግሎት ልስጥ ያለን፤ ቤተክርስቲያኒቱ በመናፍቃን መከበቡዋን ውስጥዋም ገብተው ሲንቀሳቀሱ በጠቆመ፤ ህግና ስርዓት ይከበር ባለ፤ እናንተ መስራት ያለባችሁን ለመስራት በታገለ፤ ዶግማና ቀኖና ይከበር ባለ፤ ቤተክርስቲያን ህልውናዋ ይከበር ባለ፤ ገዳማትንና አድባራትን ምዕመናንን አስተባብሮ በረዳ የምን ማሳደድ ነው፡፡ ባይሆን ስደት የሚገባቸው ከስርዎት ያሉት ሙሰኞችና በዝባዦች ናቸው፡፡ አሁንም ደግመን ደጋግመን የምንለው ማህበሩን በፈቃድዎ ምንም ሊያደርጉ እንደማይችሉ ይወቁ፡፡ ማህበሩን የመሰረተው እግዚአብሔር እንጂ ሰዎች አይደሉም፡፡ ክስ ለማህበሩ አዲስ አይደለም ምን አልባት በርስዎ ዘመን ማህበሩን በመክሰስ ሪከርድ ሊሰብሩ ፈልገውም ከሆነም አያዋጣዎትም እንጂ ሊሰብሩ ይችላሉ፡፡ እንደተከበሩ ቢቀጥሉ ይሻሎታል፡፡

  የተሸሙት ማህበርን ለማፍረስ ሳይሆን ማህበርን ለማጠንከር ሊሆን ይገባል፡፡ ከቀደሙ አባቶች ብዙ ተማሩ ለምሳሌ ከቀደሙት አቡነ ጎርጎርዮስ ከግብጹ አቡነ ሺኖዳ፡፡ ምን አለበት በህይወትዎ እንደ አቡነ ሺኖዳ መጻህፍትን እየጻፉ ለልጆችዎ ቢያበረክቱ የሚያምርቦት እንዲህ ቢያደርጉ ነበር፡፡ ገዳማት መሄድ መጸለይ እራስን በስራ መወጠር አይሻልም ፡፡ የሚበጅዎትን ያውቁት ነበር ግን በማይበጅዎት ተወጠሩ ፡፡ ስለዚህ አስር ጊዜ ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ ነውና ለሚያስተላልፉት ነገር ሁሉ በአይምሮ ሆነው ይወስኑ፡፡ ስልጣኖት ለወንበዴዎች ሳይሆን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ነውና የተሰጠዎት ያስተውሉ፡፡ ልቦና ይስጥዎት ፡፡

 26. Anonymous February 11, 2016 at 3:01 pm Reply

  በጎ እንዳትሰሩ እንዳታስቡ የከለከላችሁ ማንም የለምና በጎውን ሰርታችሁ እኛንም አሰሩን
  January 28, 2016 · by temesgenz · in ልዩ ልዩ, ወቅታዊ ጉዳዮች. ·
  ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፡
  ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፡
  አቡነ ማትያስ ሰሞኑን አሜሪካ ሄደው በሰው ሀገር ያሉትን ምእመናን አስለቅሰው መጡ ብዙም ሳይቆዩ
  ሀገር ቤት መጥተው ማኀበረ ቅዱሳንን እስከምሞት እዋጋዋለሁ እጅ እግሩን አስረዋለሁ ማለታቸው ነው በጣም ብዙ ሰዎችን አሳዝኗል፡

  ማኅበረ ቅዱሳን
  ማኅበረ ቅዱሳን
  የሕንድ ቤተክርስቲያን በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ስብከት እና ሰማዕትነት ላይ የተመሰረተችና በተለያዩ ጊዜያት በብዙ ፈተና ተፈትና ለዛሬ የደረሰች ሐዋርያዊትና ከእኀት አብያተክርስጺያናት አንዷ ናት፡፡
  እነሱ ጥቂት ሆነው እየሰሩ ያለዉን ጥቂቱን ነገር እንኳን ባነሳ ገዳማቶቻቸውና አብያተክርቲያናቶቻቸው የራሳቸው የሆነ ሆስፒታሎች÷ ከመጀመርያ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ የደረሱ የትምህርት ተቋማት ያላቸው÷ የሕጻናት ማሳደጊያ÷ በሱስ የተጠቁ ሰዎች ማገገሚያ ማዕከላት የመሳሰሉት ያሏቸው÷ከከተማ እስከ ገጠር ያሉ ቤተክርስቲያኖች ያላቸው ውበትና ጥራት (በየዓመቱ ቢያንስ ቀለም ይቀባሉ) የሰንበት ትምህርት ቤቶቻቸው በዕድሜ ደረጃ የተከፋፈለ የሥርዓተ ትምህርት ያላቸውና የተደራጁ መንፈሳዊ ኮሌጆቻቸው ብዙና ዕድሜ ጠገብ የሆኑና ከዚያም ገብቶ ለመማር ቢያንስ የመጀመርያ ዲግሪ መያዝና ስለ መልካምና በጎ ስነምግባር ማረጋገጫ እንዲሆናቸው አንድ ደቀ መዝሙር ሊቃነ ጳጳሳቱን ከ6 እስከ 8 ወር ማገልገልና ከአባቶች ይሁኝታ ሲያገኝ ነው የመግቢያ ፈተና እንኳን የሚፈተነው፡፡
  የእኛን ሳስበው 50 ሚሊዮኖችን ነው ምንመራው እያሉ ነገር ግን አብዛኞቹ ነገን እያሰብ ብዙ ከመስራት ይልቅ በጥቂቱ ሥራ የሚረኩ ሲተቹ በፍጹም የሚከፋቸው አንቱ አንቱን ብቻ የሚወዱ መሆኑን ሳስበው አዝናለሁም፡፡
  እስቲ የትኛው ሰንበት ትምህርት ቤታችን ነው በመዋቅር የወረደ በሥርዓት የተደራጀ እና በየደረጃው የተከፋፈለ ሥርዓተ ትምህርት ያለው እዉን እስከአሁን ድረስ ሦስት መንፈሳው ኮሌጅ ብቻ ነበር ሊኖረን የሚገባው የትኛው መንፈሳው ኮሌጅ ነው ተማሪዎቹን ከታች ጀምር በሥርዓት መልምሎ እየተቀበለ ያለና በመልካም ማንነት ታንጸው እንዲወጡ እያደረገ ያለው÷ ጥቂት አድባራትና ገዳማት በልማት ራሳቸውን ለመቻል ሕንጻ ቢገነቡ ለሱቅ ሥራ አከራዩት እንጂ ለትውልድ መፍለቂያ ለታመሙት ማገገሚያ ማዕከል መቼ አደረጉት (የሰው ልማት ይቀድማልና) በእውነት እስኪ ግልፅ ግልፁን እንነጋገርና ምኑ ነው የሚያኮራን አብነት ትምህርት ቤቶቻችን ገዳማቶቻችን ዘመኑን እንዲዋጁ ትውልዱን እንዲታደጉት እየተደረገ ነውን ? አቡነ ማትያስ ያስተማሩት መምህራኖቻቸውና ልጆቻቸው ኑሯቸው ተስተካከለላቸው? ይህን ትውልድ ዓለም እንዳይነጥቀው ደረሳችሁለት ወይስ ጥዋት አስቀድሶ ማታ ይጨፍራል ? በሰንበት ትምህርት ቤት ከሚማረው ወጣት ይልቅ የማይሳተፈው እንደሚበልጥ ጠፍቷቹ ነውን? ሰበካ ጉባኤያትስ በእውነት ታች ምእመኑ ጋር እንዲደርሱ በአግባቡ እየመራቹአቸው ነውን ?ሁሉም ምእመን ቅዳሴ ተስጦ እንዲመልስ እንደ ግብፅና ሕንድ ቤተክርስቲያን አስተምራቹ ለንስሓ ለሥጋ ወደሙ አበቃችሁትን ?

  ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፡
  ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፡
  ታዲያ ከሠራችሁት ጥቂት ሥራ ይልቅ ያልሰራችሁት ብዙ ሥራዎች እያለባችሁ ከበረቱ ያልገቡትን መሰብሰብ (መፈለግ) ትታችሁ እንዴት በበረት ያሉትን የተሰበሰቡትን ወጣቶች መበተኑ ታያቹ ? ይህ በእዉነት የበጎ ህሊና ውጤት አይመስለኝም፡፡
  መማር ካለባችሁ ከህሕንድ ቤተክርስቲያን ተማሩ፡፡በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ማር ጎርጎርዮስ የክርስቲያን ተማሪዎች ማኀበር (Mar Gregorios Orthodox Christian Student Movement) የሚባል ልክ እንደ ማኀበረ ቅዱሳን ያለ ማኅበር አላቸው፡፡ ከተመሰረተ 107ኛውን ዓመት ዘንድሮ ያከበረ ሲሆን የማኅበሩ ፕረዘዳንት ማር ቄርሎስ የሙንባይ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (His Grace Geevarghese Mar Coorilos Metropolitan of Bombay Diocese and Presedant of Mar Gregorios Orthodox Christian Student Movement) ናቸው ፡፡ የዚህን ማኀበር ዋና ጽ/ቤት ሕንፃን ግዙፍነት የሰራቸውን የተለያዩ ሰማይ ጠቀስ አፓርትመንቶችን የንግድ ማዕከላት ሕንፃዎቹን÷ የማተሚያ ድርጅቶቹን ያሉትን ምሁራን ስብስብ እየሰራ ያለሁን ዘርፈ ብዙ ሥራ ብታዩና ከዛም ብትማሩ በማኀበረ ቅዱሳን በአባለት ደም በተገነባ አንድ ትንሽ ሕንፃና መልካም ሥራን በሚሰሩ ምእመናን ላይ ዐይናችሁ ባልቀላና ልባችሁም ባልከፋ ነበር፡፡በጎ እንዳትሰሩ እንዳታስቡ የከለከላችሁ ማንም የለምና በጎውን ሰርታችሁ እኛንም አሰሩን፡፡
  “በእዉነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ኹሉ ይሰደዳሉ፡፡” 2ኛ ጢሞ

 27. Anonymous February 11, 2016 at 5:35 pm Reply

  yegemal!! under the blog hono fekera men yregal mhiber kidusan not church but NGO AND poltica parti subaia gibu !! patiaric matyas is our father!!!!!!

 28. Anonymous February 11, 2016 at 5:44 pm Reply

  የአባቶች መንገድ የሚከተሉትን ለማፈራረሰ ከመሮጥ ከ 3 የተከፈለችውን ቤተክርስቲያን አንድ ለማረግ ቢሮጡ አይሻልም ነበር

 29. Anonymous February 11, 2016 at 6:01 pm Reply

  ፀልዩ በእንተ ፓትርያርክነ ማትያስ

 30. Anonymous February 11, 2016 at 6:09 pm Reply

  ere tewu dem bedem ayteram teregagu mindinew akaki zeraf malet betekirstian ke mahibere kidusan bejuwala yetemeseretech aderegachihu eko ere tewu begom aydel mindinew endih megenfel yetemarachihu aydelem ende.
  Eshi endalachihu patriariku ke siltan tenesu Aba Samuel weyim Aba Mathewos teteku enibel ahun balew mewaqir ena betekirstiyanin bemigedader kumena tizelqalachihu?
  asteyayet yesetewun hulu bemenakes tizelqalachihu?
  Aba Matiyas sishomu man neber guday asfetsamiw ersachew endimeretu ene bayabil ene W/ro Mekdelawit … yiseru yeneberut sira aytaweqim ende
  tewu lemenfesqidus bota yiset sibal begirgir alsema bilachihu alneber ende midnew ahun endih mehon seken rega belu
  chigrochun adebabay mawtat enantem degafi endalachihu ersachewum degafi ayatum mechereshaw esti mindinew
  ere sile betekirstiayan amlak esti enante beltachihu tegegnu
  bechuhet betifozo bizat atimeku yihichi saygebat bemedafachihu ej yewedeqech betekirstiayan tasazinachihu
  amlake yebekirsiyanen wurdet kemiyasayegn biwesdegn yishalal

 31. Anonymous February 11, 2016 at 7:54 pm Reply

  MK now you see? you are frustrated enough, commenters of this blog! think twice before you speak.. you are cutting the rob of your nick . And check the spirit of your heart and mind.
  we pray for you. but you have to understand our beloved patriarch is working hard to protect the church the enemy according to the rule of the Orthodox Church
  please repent and say sorry because time is running out

 32. Anonymous February 11, 2016 at 7:54 pm Reply

  Aye zenedero feyele kemdersewa kelele mebetasewa alu Abbtochachen wntchewn newu Abbu matyse menfiken lemtafate newu almchewu wyse Le msefafate?????

 33. Damtew Tilahun February 11, 2016 at 8:22 pm Reply

  you should think as a religious man.

 34. Damtew Tilahun February 11, 2016 at 8:24 pm Reply

  አንዳንድ የዋሃን ፍጥረታት ማህበረ ቅዱሳን ማለት በማህበር ስም የተሰበሰቡ ግለሰቦች ጥርቅም ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ማህበረ ቅዱሳን ማለት የኦርቶዶክሰ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ልቦና ስብስብ ማለት ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳን የሚጠፋው ሁሉም አማኝ ሙሉ በሙሉ ከዚህ ዓለም ሲጠፋ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የማህበሩ አባላት የሚባሉት በአባቶች እግር ስር ቁጭ ብለው ዶግማውንና ቀኖናውን ጠንቅቀው የተማሩ፤ ክርስትና ማለት መስዋዕትነት መሆኑን በመለማመድ ላይ ያሉ ሁሉም በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ምዕመናን ናቸው፡፡ ስለሆነም ማህበሩን ለማጥፋት ከመሞከር ይልቅ እያንዳንዱን ምዕመን ማጥፋት የሚቀል ይመስለኛል፡፡

 35. Anonymous February 11, 2016 at 11:00 pm Reply
 36. Anonymous February 11, 2016 at 11:01 pm Reply

  Who was supposed to do this…..
  በሐዋሳ ማረሚያ ቤት አዲስ አማንያን ተጠመቁ….
  http://eotcmk.org/site/-mainmenu-18/2071-2016-02-10-12-44-21

  • Anonymous February 12, 2016 at 10:51 am Reply

   የዲላ ወረዳ ቤተክሕነት ጋዜጣም ሆነ ዌብሳይት የለውም፤ሰ/ት/ቤቱም እንዲሁ ጋዜጣና ዌብሳይት የለውም፡፡ዜናው ጋዜጣና ዌብሳይት ባለው ማኅበረቅዱሳን ወጣ፡፡እንደዚያ ማለት ግን ተጠማቂዎቹን በማሳመን ሂደት የተሳተፈው ማኅበረቅዱሳን ብቻ ነው ማለት አይደለም፡፡አጥቢያዎች፣የወረዳው ቤተክህነትና ሰ/ተማሪዎች ተሳታፊ ናቸው፡፡ስለዚህ የትሩፋቱን ዋጋ ሁሉ ጠቅልለሎ ዜናውን ላወጣው ማኅበር መስጠት ልክ አይደለም፡፡ዘገባውንም ካነበብከው በማኅበረ ቅዱሳን ጥረት ‹‹ብቻ›› ተጠመቁ አይልም፡፡እየተስተዋለ፤ሁሉም አንደ ትሩፋቱ እውቅና እና ክብር ይሰጠው፡፡ላምጪው እንዲከፈል ሕግ ያስገድዳል በሚል መርህ ትሩፋቱን ሁሉ ለዜናው አቅራቢ ጠቅልሎ መስጠት ደስ አይልም፤ሁሉም እንደየድርሻው፡፡

 37. Anonymous February 11, 2016 at 11:39 pm Reply

  እናንተ ሰዎች እንዲህ አይነት መወራፍና መገፋፋት ለቤተክርስቲያን የሚጠቅመው ምንድነዉ?

 38. Anonymous February 12, 2016 at 4:24 am Reply

  Ere ebakachihu abatochi minew 1 mahber. tcheger ala chihu srachin lebete k/ n yemaytekm kehone beyegizew lemin tkefafel alachhihu lehaymanota hin yemitekmen yeabatochi andinet enaselam new andi hunachihu asawkun ebakachihu andi hunu yemahberun melkam sra mezerzer ayasfelgm lemanm gls slehone

 39. Anonymous February 12, 2016 at 5:16 am Reply

  እንዲህ አይነት ሰዎችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ ማየት ምንኛ ልብን የሚያደማ ነገር ነው?”አባ” ማትያስ ግን መጨረሻቸው ምን ይሆን?ይህንን ሁሉ መንጋ ለመበተን መድከም ምን የሚሉት ዘረኝነትና ምንፍቅና ነው?ዋ! አለ!

 40. Anonymous February 12, 2016 at 6:45 am Reply

  ምነው ቅዱስ አባታችን ሌላ የሚሰሩት አጡ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የሚፈልጉ ልጆችወን ለመበታተን ያሰቡ

 41. Anonymous February 12, 2016 at 7:07 am Reply

  ለፌስቡኩና ለብሎጉ ጦር ቤተክርስቲያን ማለት ማኅበረቅዱሳን ነው፤ማኅበረቅዱሳን ማለት ቤተክርስቲያን ነው፡፡ስለዚህ ማኅበሩን መገሰጽ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ጦር መስበቅ ማለት ነው፡፡ስህተቱ ይነገር ከተባለም ‹‹ወጣቶች ናቸው፤ሰዎች ናቸው፤አይሳሳቱም አይባልም›› ተብሎ በደፈናው ተናግሮ ማለፍ እንጂ በዝርዝር እንዲህ ተሳስተዋል፤እንዲህ ተቋማትንና አባቶችን አስከፍተዋል፤ይሄ ጥፋት ስለሆነ ቢስተካከል ከተባለ ያን ያለው ሰው በራሱ ፈረደ፡፡ሁሉም ስሞችይሰጡታል፡፡

  መናፍቅ፣ካድሬ፣ዘረኛ፣ጉቦኛ፣ሐራጥቃ፣ተሐድሶ፣ሆዳም፣ተላላኪ፣መሐይም፣ፕሮቴስታንት፣ካርዲናል፡፡ስድቡ አያልቅም፤ደግነቱ ስድብ ሰው አይገልም፡፡ባጭር አነጋገር ማኅበሩ ከውዳሴ ከንቱ በቀር በፍጹም ለገንቢ ትችት ዝግጁ አይደለም፡፡አባላቱም በተለያየ መድረክ መታዘብ እንደሚቻለው ለማኅበራቸው ያላቸው አመለካከት ከቤተክርስቲያን ፍቅር የመነጨ አይመስልም፡፡በተቃራኒው ነው፡፡ለቤተክርስቲያን ያላቸው ፍቅር ከማኅበረቅዱሳን የመነጨ ነው፡፡ማኅበረቅዱሳን ባይኖር ቤተክርስቲያን አትኖርም ነበር እስከማለት የደረሰ ግብዝነት ላይ የተደረሰው በዚህ ምክንያት ነው፡፡አሁን ባለው ነባራዊ ሀቅ ማኅበረቅዱሳን የቤተክርስቲያን አምባሳደርነቱን ትቶ የራሱ ገጽታ አምባሳደር ሆኖ እየወጣ ነው፡፡ይሄን ለመታዘብ የአባላቱን ጽሑፎችና አስተያየቶች ድምጸት በስክነት አንብቦ ማስተዋል ነው፡፡

  • anonymously February 12, 2016 at 10:29 am Reply

   Min Synodos ale???? Patriarikus ALU?

  • ዳሞት February 12, 2016 at 3:02 pm Reply

   ወንድም ቤተክርስቲያን ማለት ማህበረ ቅዱሳን ማለት ነው ያለ የለም። ማህበረ ቅዱሳን ባይኖር ቤተክርስቲያን አትኖርም ነበርም በማህበሩም ሆነ በሌሎች የቤተክርስቲያኗ ልጆች አልተባለም። ምናልባት እኛ ባንኖር ኖሮ የሚለውን ድምፀት ከሌላ ዐገን ሰምተህ እነሱን ለመከላከል ካልሆነና የራሥህን አመለካከት ለማንፀባረቅ ፈልገህ ከሆነ እንጅ ይህ አልተባለም። ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቶስ አካል የሆነች የክርስቲያኖ( አማኞቿ) የፀሎት ቤት ናት። ቤተክርስቲያን አይደለም ከማህበረ ቅዱሳን ከራሳቸው ከአባ ማትያስ በፊትም ነበረች፤ ነገም በፈተና ውስጥ እያለፈች ትኖራለች።
   ነገር ግን መልካም የሚያደርጉ ሊመሰገኑና ሊደገፉ ይገባልና ማህበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን በሚሰራው ስራ ይወደዳል ፣ ይመሰገናል ፣ ይደገፋል። ለዚህም ነው ማህበሩን ምን አጠፋ ፣ ለቤተክርስቲያን እየሰራ ያለን ማህበር ለማፍረስ አትሩጡ የምንለው። ካመኑትና ለቤተክርስቲያ በቅንነት ከሚሰሩታ ጋር መተባበር ደግሞ ሀይማኖታዊም መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው።
   በቤተክርስቲያን አገልግሎት ደግሞ እምነትን አምኖ ብቻ መሔድ ሳይሆን ሐሰተኞችንና የእምነት ችግር ያለባቸውን ማጋለጥ፣ የቤተክርስቲያኖን ገንዘብ ንብረት የሚዘርፉትንም መቃወምና ክፉ ስራቸውን እዲተው ማጋለጥ ተገቢ ነው።
   የሰከነ ልቦናና ለአንዲቷ ሀይማኖት ብትቆረቆሮ ኖሮ ማስዋል የሚገባህ አንተ ነበርክ። የሚሰራን ለማፍረስ ከመሮጥ ቅጥሯን በሳንቲም ድቃቂ አከራይተው እነሱ በሙስና ያበጡትን ነበር መቅጣት። በጎችን ለማባረር ከመሮጥ ለሶስት የተበተነችውንና በዚህም አምልኮ ሥርዓቷ እየተበከለ ያለችውን ቤተክርስቲያን አንድ ለማድረግና ለማዳን ነበር መትጋት የሚገባ።
   እንግዲህ አባ ማትያስ ሲኖዶስ የለም ብለዋል፤ እራሳቸውንም ለማስመለክ የሚፈልጉ ነው የሚመስሉትና ካመለክህ አምልካቸው እንጂ ሥህተት እየሰሩ ቅዱስ ማለት ተገቢም አይመስለኝም።

  • Anonymous February 13, 2016 at 12:27 am Reply

   Ezih bilog lay asteyayet yemiset hullu ye MK abal weyim tewekay aydelem. Yihin eyegelebetachihu le Patriariku eyesetachihu mekiseft atamtu. Egiziabher libona yistachihu!

 42. Anonymous February 13, 2016 at 10:56 am Reply

  Damot !!! are you orthodox or Mhiber kidusan? first what is Holy means after that you can write any thing before that think your self!! who are you ? aginst patriaric this is the mission of Mhibere kidusan b/c this group is under one departement of sunday school for me mk is
  not wise but arogant devil spirit his father is satan b/c he didn t understand the orthodox church,b/c the members of Mk is in problem? look the leaders is not ethical person, pls come to mother church of orthodox!

 43. Anonymous February 18, 2016 at 3:29 pm Reply

  እግዚኣብሔር ብቻ ይጠብቀን እንጂ ሌላ ሁሉ ስለዘረኝነትና ለራሱና ለወገኑ ብቻ ነው የሚሮጠው፡፡ ከመጀመርያ ጀምረው ከመርዳትና ከመምከር ይልቅ ፈጥኖ ማውገዝና አባቶችን ስሜታዊና እነዲቆጡ መገፋፋት ይመርጣሉ፡፡ ነገር ግን በጊዜ ሂደት አየባሰበት ውስጥ ሲታዩ መላእክት ለመምሰል የሚጥሩ ዘረኝነትና ፖለቲካ በውስጣቸው የተሞሉ በየፌስቡካቸው ና በገኙት አጋጣሚ ሁሉ ክፋት የሚሰብኩ ብዙ ወንድሞች ሳይ እኔ ወደሌላ ውጥንቅጥ ውስጥ ሳልገባ ከቤተክርስቲያን አልጥፋ እንጂ ከሌላ ነፃ ሆኜ መቀጠል አለብኝ ብየ ወሰነኩኘ፡፡
  በአጠቃላይ ግን እግዚአብሔር ቅድስት ተዋህዶ ኦርቶዶክስን ይጠብቅ እንጂ እኔ ማነንም ማመን አልችልም እራሱ የቅድስት ሓይማኖታችን ፈጣሪና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እሰኪፈቱት ድረስ፡፡
  እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከነልጇ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ለዘሩ ዝናና ለፖለቲካ በየፊናው የሚንቀሳቀሰውን ሁሉ በአማላጅነቷ ትገስፅ ልቦና ትስ፡፡
  ቅድስት ተዋህዶ ኦርቶዶክስና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ተጠበቃ ለዘለዓለም ትኑር፡፡ አሜን

 44. በየነ ወርቁ ትስማ June 7, 2016 at 8:43 am Reply

  ማሀበር ቅዱሳን. ለ
  ማነወ.ተጠራ ነቱ?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: