ማኅበረ ቅዱሳንን የወለደው፥“እኔ ለቤተ ክርስቲያኔ ምን ማድረግ እችላለኹ” የሚለው ሐሳብ ነው፤ይጥፋ የሚሉት የጥቅም ጋብቻ የፈጸሙ አማሳኞችና የተሐድሶ መናፍቃን ናቸው/ሰብሳቢው/

Kesis Dr. Semu Mitiku

ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ

  • በማኅበሩ የመጀመሪያው ደንብ ፥ የማኅበሩ ወሰን በሚለው፣ ‹‹ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም›› የሚል ነበረበት፤ ነገር ግን በ1994 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ተመልክቶ፣ የማኅበሩ በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ አለመግባት ትክክል ነው፤ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ አንገባም ማለት ግን፣ እኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ናችሁ ብለን እያጸደቀን ስንፈልጋችሁ እምቢ ልትሉን ነው ወይ? ስለዚህ ይህ “ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም” የሚለው ንኡስ አንቀጽ መውጣት አለበት አሉን፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ ነው መተዳደሪያ ደንቡን፣ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይበጃል ባሉት መንገድ አሻሽለው ኹሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፈርመውበት ያጸደቁት፡፡
  • ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ቀኖና የመከተል ግዴታ አለበት፡፡ የቤተ ክርስቲያን የበላይ ውሳኔ ሰጭ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ፥ አይ ይበቃል፤ የማኅበሩ አገልግሎት አያስፈልገኝም ካለ ሊዘጋው ይችላል፡፡ አገልግሎት የምንሰጠው ቤተ ክርስቲያናችንን ለመደገፍ ነው፡፡ ስለዚኽ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነው ነው ተፈጻሚ ሊኾን የሚችለው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔም የማክበር ሓላፊነት አለብን፤ ነገር ግን ፓትርያርኩ ብቻቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን ሊዘጉት አይችሉም፡፡
  • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸውና ከቀዬአቸው ርቀው ወደ ተመደቡበት ግቢ ሲሔዱ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤቶችና ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ጋር የማገናኘት ሥራ እንሠራለን፤ ለተማሪዎቹም አመች ጊዜና ቦታ በማስተካከል ትምህርት እንዲሰጥ እናደርጋለን፡፡ ይህ ጠንካራ መሠረት ይዞና እንደ ባህልም ኾኖ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ቦታ ሁሉ ግቢ ጉባኤያት መኖራቸው ትልቅ ነገር ነው፡፡
  • የተማረው ኅብረተሰብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመጣ፣ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እየተማረና ቤተ ክርስቲያንንም በተሻለ ኹኔታ እያወቃት ነው፡፡ ይህም ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ አቅም ይፈጥራል፡፡ ምንም እንኳ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች የነበረ ቢኾንም፣ የተማረው ኅብረተሰብ ለቤተ ክርስቲያን በበጎ ፈቃድ የማገልገል ልምዱ እምብዛም ነበር፡፡ ይህ የኅብረተሰብ ክፍል ቤተ ክርስቲያንን በበጎ ፈቃድ እንዲያገለግልማኅበረ ቅዱሳን አርኣያ ኾኖታል ብለን እናምናለን፡፡ 
  • ቤተ ክርስቲያን በርካታ የአገልግሎት ዘርፎች አሏት፤ አገልግሎቷንም በትሩፋት ለመደገፍ ብዙ ማኅበራት ያስፈልጓታል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን አንድ ማኅበር ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ከሚያስፈልገው አንድ ሺሕኛውን እንኳ አገልግሎት ሰጥቷል ብለን አናምንም፡፡ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉም የሚበልጡም ብዙ የፈቃድ ማኅበራት ለቤተ ክርስቲያናችን ያስፈልጓታል፡፡ እርግጥ በአገር ውስጥም ኾነ በውጭም አገር ያሉ በርካታ ማኅበራት የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት በተለያየ መንገድ ያግዛሉ፡፡ በተለይ የገዳማትንና የአድባራትን የልማት ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ከበርካታ ማኅበራት ጋር አብረን እየሠራን እንገኛለን፡፡
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዲስ አወቃቀር እንዲሠራ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መርጠው ያቀረቧቸውና ቅዱስነታቸው መመሪያ የሰጧቸው የኮሚቴ አባላት ወደ ጥናት ሥራው እንዲገቡ ሲደረግ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የኾኑም በማኅበሩ ተወክለው ባይኾንም እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸው አባል ኾነው ገብተዋል፤ ጥናቱንም በሚገባ አጥንተው አቅርበዋል፤ ጥናቱም የቅዱስ ሲኖዶስ እንጅ የማኅበረ ቅዱሳን አይደለም፤ የቀረበውም ለቅዱስነታቸው ነው፤ ባለሞያዎቹም መመሪያ የተቀበሉት ከቅዱስነታቸው ነው፡፡ 
  • የጥናቱ ትግበራ፣ የግል ጥቅማችንን ይነካብናል ያሉ ጥቂት አለቆች ተቃውሞ አሥነሱ፡፡ ከባለሞያዎቹ የማኅበሩ አባላት መኖራቸው እንደ ጥፋት ተቆጥሮ በቀጥታ ክሣቸውን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ አቀረቡ፡፡ ለጥናቱ መተግበር በይፋ ሲሰጥ የነበረውን የኅብረተሰቡን ድጋፍም አፍነው ለመሔድ ሞከሩ፡፡ ቅዱስታቸውም በመጀመሪያ የነበረው አቋማቸው ተሸርሽሮ የእነዚኽ አካላት ደጋፊ እየኾኑ መጡ፡፡ ለእኛ ግን፣ ችግራችኹ ይህ ነው ብለው በቀጥታ ሊነግሩን ወይም በችግሩ ዙሪያ ሊያወያዩን አልፈለጉም፡፡ 
  • ቤተ ክርስቲያናችን ደጋፊዎቿ አባላቷ ብቻ ናቸው፤ ጥንካሬዋ በሊቃውንቷ የእምነት ጽናት ላይ፣ በምእመናኗ መተማመንና መደጋገፍ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህ ግን ሰርገው በሚገቡ አካላት እየተቦረቦረ ነው፡፡ የተሐድሶ መናፍቃኑ እንቅስቃሴ ሲያዩት ቀላል ይመስላል እንጂ በብዙ አጥቢያዎቻችን ብጥብጥና መከፋፈል እንዲፈጠር ምክንያት እየኾኑ ነው፡፡ መረጋጋት በቤተ ክርስቲያን እንዳይኖር ተግተው እየሠሩ ነው፡፡ የሥነ ምግባር አለመኖር ኃጢአት እንዳልኾነ የሚያሳይ ልዩ ትምህርት እያስተማሩም ነው፡፡ አንድ ጊዜ በሠራኸው ሥራ ጸድቀሃል በማለት ሰዎች ጥፋትን እንዲለማመዱ ለማድረግ እየሠሩ ነው፡፡ በዚኽም በቤተ ክርስቲያን ገንዘብ የፈለጋቸውን ለሚያደርጉ ጥቅመኞች ሽፋን እየሰጡ ነው፡፡ 
  • የሃይማኖት ችግርና የምግባር ችግር ያለባቸው አካላት ጋብቻ ፈጽመዋል፡፡ ይህ ለቤተ ክርስቲያናችን ከባድ ፈተና ነው፤ ለአገልግሎቷም ትልቅ ዕንቅፋት ፈጥሯል፡፡ በካህናቷ ላይ ጫና ፈጥሯል፡፡ ካህናቱ ተበደልን ብለው የሚጠይቁት እነዚኽኑ በጥቅም የተሳሰሩትን ሰዎች ነው፡፡ ከሥራችን ያባርሩናል ብለው ስለሚሰጉ፣ ደግሞም እያባረሯቸው ስለኾነ ካህናቱ ድምፃቸውን አጥፍተው በስጋት ነው የሚኖሩት፡፡ ይህ እየኾነ በሔደ ቁጥር ምእመናን ስለ ሃይማኖታቸው እየተቆረቆሩ መጥተዋል፡፡ የምእመናን ቁጣ ሌላ አለመረጋጋትና ችግር ፈጥሮ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሔድ የሚመለከተው አካል ኹሉ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል፡፡

*          *           *

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ፣ በአዲስ አበባ ከሚታተመው የቀለም ቀንድ ሳምንታዊ ጋዜጣ ጋር በማኅበሩ አገልግሎት፤ በቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታና ተያያዥ ጉዳዮች ቃለ ምልልስ አድርገዋል፤ እንደሚከተለው ተስተናግዷል፡፡


(የቀለም ቀንድ፤ ቅፅ ፫ ቁጥር ፳፰፤ ማክሰኞ፤ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት ኹለት ዐሥርት ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራት በጋዜጣ ደረጃ መዘርዝር ከባድ እንደ ኾነ ይገባናል፡፡ እስኪ ዝርዝር ጉዳዮችን ለጊዜው እናቆያቸውና፣ ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን በማገልገል በኩል ሠራቸው የሚባሉትን አንኳር ተግባራት ጠቅለል ባለ መልኩ ይግልጹልን?

በመጀመሪያ ልትጠይቁን በመምጣታችሁ አመሰግናለሁ፤ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሊቋቋም የቻለው፣ መጀመሪያ የተለያዩ አካላት በየአካባቢው ቤተ ክርስቲያንን ሲወቅሱ እንሰማ ነበር፡፡ እኛም በቤተ ክርስቲያናችን የምናያቸውና አንዳንዴ እንዲህ ባይኾኑ ኖሮ የምንላቸው ነገሮች አሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ እንዲህ ቢደረጉ ብለን የምንመኛቸው ነገሮችም ነበሩ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እነዚህን ነገሮች ማን ነው የሚሠራቸው ሲባል ኹሉንም ጠቅልሎ ቤተ ክህነቱ ብቻ ይሥራቸው ብሎ ማሰብ ተገቢ ስላልኾነ ቤተ ክርስቲያን የኹላችንም በመኾኗ ማድረግ የሚገባን ምንድን ነው? ብለን አስበን እነ እገሌ ለምን ያን አይሠሩም ከምንል ለምን እኛስ አንሠራም? እንዴትስ ነው የምንሠራው? የሚል መነሻ ነው ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲወለድ ያደረገው፤ አስተሳሰቡንም ጨምሮ “እኔ ለቤተ ክርስቲያኔ ምን ማድረግ እችላለሁ፤” የሚለው ነው፡፡

ምን ማድረግ እንችላለን ብለን ስናስብ፣ በጊዜው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ስለነበርን የሰንበት ትምህርት ቤቶች እኛ ፈልገናቸው ካልሔድን በስተቀር ቀጥታ እኛን የሚደርሱበት ዕድል አልነበረም፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት ለማግኘት እኛ መፈለግ ነበረብን፡፡ በሌላ መልኩ ግን የሌሎች እምነት ተቋማትን ስናይ ግን እዚያው ቀጥታ ከአካባቢው የእምነት ተከታዮቻቸው ጋር የሚገናኙበት ኹኔታ ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነት ቁጭቶች ናቸው ማኅበረ ቅዱሳን እንዲጀመር ያደረገው፡፡

ስለዚህ በመጀመሪያው ጊዜ እንደነበረው፣ ዓላማችን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያውቁ፤ ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁ፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንዲረዱ ማስቻል ከዚያም ባለፈ ካወቁ በኋላ ራሳቸው በሕይወታቸው እንዲወስኑ ማድረግ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ስለ ቤተ ክርስቲያን ሳያውቁ ቤተ ክርስቲያንን ስለሚተቹ ዐውቀው እንዲወስኑ ማስቻል ነው፡፡

ብዙዎቹ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸውና ከቀዬአቸው ርቀው ወደ ተመደቡበት የትምህርት ቦታ/ግቢ ሲሔዱ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤቶችና ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ጋር የማገናኘት ሥራ እንሠራለን፤ ለተማሪዎቹም አመች ጊዜና ቦታ በማስተካከል ትምህርት እንዲሰጥ እናደርጋለን፡፡ አኹን አኹን ግን ይህ ጠንካራ መሠረት ይዞና እንደ ባህልም ኾኖ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ቦታ ሁሉ ግቢ ጉባኤ መኖሩ ትልቅ ነገር ነው፡፡ የተማረው ኅብረተሰብ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመጣ ከፍተኛ ሥራ ተሠርቷል፡፡ ይህም ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ አቅም ይፈጥራል፡፡

ኹለተኛው ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት ነው፡፡ ይህ የብዙዎችን ድጋፍ የሚጠይቅ፣ ሁሉም በያለበት ሊሠራው የሚገባ ተግባር ነው፡፡ አንድ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተቋቋመ የስብከተ ወንጌል መምሪያ፣ አልያም በአጥቢያ ያለ አንድ የስብከተ ወንጌል ክፍል ብቻ የሚፈጽመው አገልግሎት አይደለም፡፡ ኹሉም የቤተ ክርስቲያናችን አባላት ተደጋግፈው የሚሠሩት ሥራ ነውና ከዚህ አንጻር ማኅበሩም በተለያዩ ቦታዎች የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲዳረስ አድርጓል፤ እያደረገም ነው፡፡

ለምሳሌ ብዙዎች የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎቻችን በሚመደቡበት የገጠር አጥቢያ ሒደው በሚችሉት ኹሉ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በብዙ ቦታዎች እንኳን ሰባኬ ወንጌል ማግኘት ቀርቶ የሚቀድስ ካህን እንኳን ማግኘት የተቸገሩ አጥቢያዎች ብዙ ነበሩ፤ አሁንም ወደ ገጠሩ ክፍል እንዲኹ ዓይነት ችግር ያለባቸው ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ከየግቢ ጉባኤያቱ የተመረቁ ወጣቶች የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱና ሰባካ ጉባኤ እንዲመሠረት አድርገው በራሳቸው ገንዘብ ካህን ቀጥረው የአካባቢው ምእመን አገልግሎት እንዲያገኝ ያስቻሉባቸው ቦታዎች ብዙ ናቸው፡፡ ይህ እንግዲህ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አካል ነው፡፡

ቀደም ሲል በየገጠሩ ባሉ የሰንበት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምር መምህርና የማስተማሪያ መሣሪያ እጥረት ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር ችግሩን ለመፍታት ከየግቢ ጉባኤው ተመርቀው ወደ የሰንበት ት/ቤቶቹ ሲሔዱ ለማስተማር የሚረዳቸውና የዘመኑ ሰው ለሚጠይቃቸው ጥያቄ መልስ ሊሰጡ የሚችሉ ጽሑፎችን በማባዛት ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቶች መላክ ጀመርን፡፡ ይህን ለምን ወደ መጽሔት እና ጋዜጣ አናሳድገውም በማለት የሐመር መጽሔት እና የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ኅትመቶችን ማሳተም ጀመርን፡፡ ከዚያም አልፈን ዘመናዊውን ቴክኖሎጂ ተጠቅመን በድምፅ እና በምስል ስብከተ ወንጌል እና መዝሙር እያዘጋጀን እናሰራጫለን፡፡ በድረ ገጾችም የተለያዩ ትምህርቶች ይለቃቃሉ፡፡ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችንም ጀምረን ነበር፤ ወደፊትም እግዚአብሔር ቢፈቅድ እንቀጥልበታለን፡፡

ከዚኽ በተጨማሪም በጠረፍ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎችን እያስተማርን ራሳቸውን እንዲደግፉ እያስቻልን ነው፡፡ ከእንዲህ ዓይነት አካባቢዎች ፈቃደኛ የኾኑ ወጣቶችን መሠረታዊ በኾኑ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች ላይ ሥልጠና እየሰጠን በአካባቢያቸው፣ በባህላቸውና በቋንቋቸው ሒደው እንዲያስተምሩና ስብከተ ወንጌልን እንዲያስፋፉ እያደረግን እንገኛለን፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ኢአማንያን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ተጨምረዋል፡፡

የተማረው ኅብረተሰብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመጣ፣ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እየተማረና ቤተ ክርስቲያንንም በተሻለ ኹኔታ እያወቃት ነው ያለው፡፡ ይህ ሁሉ እንግዲህ በስብከተ ወንጌል በኩል እየተሠራ ያለው ነው፡፡

ሌላው የቤተ ክርስቲያናችን ገዳማት የነበሩበትን ኹኔታ ለመቃኘት የዳሰሳ ጥናት ስናካሒድ ያወቅነው፣ አብዛኛዎቹ ገዳማት ራሳቸውን ችለው የሚኖሩበት ገቢ እንደሌላቸው ነው፡፡ ጥናቱ በተዘጋጀበት ወቅት፣ አብዛኛዎቹ ጥንታውያንና ከእይታ ራቅ ብለው የተገደሙ ገዳማት ውስጥ እንዲሁ ከዚኹ እንሙት ያሉ ታላላቅ አባቶች ብቻ የቀሩባቸው ነበሩ፡፡ ለእነርሱም ቢኾን ጾም ውለው በሰዓት እንኳ የሚመገቡት ማግኘት አዳጋች ነበር፡፡ ብዙ ምእመናን ለገዳማት ርዳታ ቢሰጡም የሚሰጡት ግን መረጃው ላላቸው ገዳማት ወይም ችግራቸውን ለሰሙት ቦታ ብቻ ነበር፡፡ ችግሩ፣ ለቤተ ክርስቲያን የሚጥቅሙ ብዙ መናንያን ያሉባቸው ቦታዎች እየከሰሙ እንዲሔዱ የሚያደርግ በመኾኑ አሳሰበን፤ ከዚህም አንጻር የተለየ መርሐ ግብር መንደፍ ነበረብን፡፡

ብዙ ጊዜ በእኛ አገር ልማት ሲባል በበለጸጉ ሀገሮች ያሉ አካላትን ጠይቆ መሥራት ነው የተለመደው፡፡ እኛ ግን በራሳችን ምእመናን ዐቅምና አስተዋፅኦ ላይ ተመሥርተን መሥራትን ነው የመረጥነው፡፡ ርግጥ የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድ የአገልግሎት ዘርፍ ኾኖ የተቋቋመው የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን አለ፤ ይህ ኮሚሽን አብዛኛውን ገንዘቡን የሚያገኘው ከውጭ በጎ አድራጊዎች ከሚላክ ገንዘብ ነው፡፡ የውጭ ረጅዎች ደግሞ ለአጠቃላይ ማኅበረሰባዊ ጥቅም የሚውል እንጅ ለገዳማት ብቻ ተብሎ የሚሠራ ሥራን ለመርዳት ይውል ዘንድ ብዙም አይፈቅዱም፡፡ በመኾኑም ለገዳማቱና ለአድባራቱ በኮሚሽኑ በኩል የሚደረጉ የልማት ሥራዎች ቢኖሩም ችግሩን ለመፍታት ግን በቂ አልነበሩም፡፡

በዚኽ ምክንያት በአገር ውስጥም በውጭም ያሉ ምእመናን በጋራ በመተባበር ገዳማቱ ራሳቸውን እንዲችሉና በውጤታቸውም ምርታማ እንዲኾኑ መሬት ያላቸው መሬታቸውን አርሰው እህልና ፍራፍሬ እንዲያመርቱ፣ ወይም ንብ እንዲያንቡ፣ አልያም ከብት እንዲያደልቡ፤ የመሬት እጥረት ላለባቸው ደግሞ የእህል ወፍጮ እንዲኖራቸው  እንዲሁም የሽመናና የጥልፍ ሥራዎችን እንዲሠሩ የማመቻቸት ለአንዳንዶቹም የከተማ ቦታ ላላቸው የሚከራይ ቤት ተሠርቶላቸው እንዲጠቀሙ የሚያደርግ ፕሮጀክት ነደፍን፡፡ ይህን እውን ለማድረግ ማኅበረ ቅዱሳን ላለፉት ዐሥራ ስምንት ዓመታት በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡

የአብነት ትምህርት ቤቶችን ስንመለከት ደግሞ፤ ቀደም ባለው ጊዜ ለአብነት ተማሪዎች በነዋሪው ኅብረተሰብ የትምህርት ዕድል (Scholarship) እየተሰጠ ነው ሲማሩ የነበሩት፡፡ ቀደም ባሉት ዘመናት በምዕራባውያኑም ይደረግ እንደነበረው ኹሉ የትምህርት ድጋፍ ይሰጥ የነበረው ለተማሪዎችም ለመምህራንም ሲኾን ኅብረተሰቡ የእህል መዋጮ እያደረገ ኹሉንም ያኖር ነበር፡፡ ተማሪዎቹ እህሉን አስፈጭተውና አብስለው መመገቡ አስቸጋሪ ስለሚኾንባቸው የበሰለ እህል እየተሰጣቸው ነው ሲማሩ የነበሩት፡፡ ተማሪዎቹ በተመደቡበት ሠፈር በመሔድ በእንተ ስማ ለማርያም ብለው ይጠይቃሉ፤ ባለቤቶቹም ወላጆች ባይኖሩ እንኳ ቀሪዎቹ የቤተሰቡ አካላት ተማሪ ሲመጣ ስጡ ስለሚባሉ ለተማሪዎቹ ምግቡ ይሰጣል፡፡

በዚያ መልኩ ትምህርቱ ሲከናወን ቢቆይም አኹን ግን ዘመናችን እየተቀየረ በመምጣቱ፤ ከአንዳንድ አካባቢዎችም ሕዝቡ በተፈጥሮ አደጋዎች እና በሰፈራ ምክንያት አካባቢውን ሲለቅ የገንዘብ አቅማቸው የተሻለ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎችም በአብዛኛው ወደ ከተማ እየገቡ ሲመጡ፣ ትምህርት ቤቶቹ ግን እዚያው ቀደም ሲል የነበሩበት አካባቢ ቀሩ፡፡ በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ያለው ኅብረተሰብም ትምህርት ቤቶችን ለመርዳት ያለው አቅም እየተዳከመ መጣ፡፡ በተቀሩት የሀገራችን ክፍሎች ደግሞ የነበሩት ትምህርት ቤቶች እየከሰሙ ካህን ለማገኘት እንኳ አስቸጋሪ ኹኔታ እየተፈጠረ መጣ፡፡

ይህ ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን ስጋት በመኾኑና በሀገር ደረጃም ቢኾን ለሀገር በቀል ዕውቀቶች ማሸጋገሪያና ማበልጸጊያ የኾኑት እነዚሁ የትምህርት ማዕከላት ስለነበሩ “የባህል ትምህርቶች ናቸው” ብለን ሳንተዋቸው የትምህርቱንም ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ነገር መሥራት ግዴታችን ነበር፡፡ ስለዚኽ ኹለት ነገሮችን መሥራት ነበረብን፡፡

አንደኛው፡- በሰሜን በኩል ያሉና ብዙ ደቀ መዛሙርት ሲያፈሩ የኖሩ ትምህርት ቤቶች መምህራን ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም ከሀገረ ስብከታቸው የምትመደብላቸው በጣም አነስተኛ መደጎሚያ ነበረች፡፡ እኛ ጥናቱን ስናካሒድ እንዲያውም በወር 50 ብር ብቻ የሚሰጣቸው መምህራን ነበሩ፡፡ 50 ብር ለቤተሰብ ማስተዳደሪያ፣ ለልብስ፣ ለቀለብና ለማናቸውንም ወጪ መሸፍኛ ኾና ኑሮን ለመግፋት በፍጹም አታስችልም፡፡ ስለኾነም መምህራኑ የሚኖሩት ተማሪዎች ለልመና ወጥተው በሚያመጡት ነገር ተደጉመው ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህን የኑሮ ኹኔታ ለማሻሻል ለመምህራን መጠነኛ ድጎማ ማድረግ እንዲኹም ለተማሪዎች ለምግባቸውና ለልብሳቸው የሚኾነውን መደጎም የእኛ ድርሻ ነው ብለን ስላሰብን ፕሮጀክት ነድፈን ለኅብረተሰቡ አስተዋወቅን፡፡ ኅብረተሰቡም ደስተኛ ኾኖ የአብነት ትምህርት ቤቶች እንደገና እንዲቋቋሙ አድርጓል፡፡

ኹለተኛው፥ በምሥራቅ፣ በምዕራብና በደቡብ የአገራችን ክፍል ክፍሎች ስንሄድ ግን፤ እምብዛም ያልነበረ ተቋምን እንደገና መመሥረት ይጠበቅብን ነበር፡፡ ስለዚህ በእንተ ስማ ለማርያም ብሎ መጠየቅ ኹሉ የተለመደ ስላልኾነ ለመምህራንም ለተማሪዎችም መኖሪያ እና መማሪያ የሚኾኑ ግንባታዎችን መሥራት አስፈላጊ ነው፡፡ ምግብ ከዚያው መሠራት አለበት፤ መምህራንም በአዲስ ተቀጥረው መሔድ ነበረባቸው፡፡ ከየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳትና ሓላፊዎች ጋር በመነጋገርና አብረን በመሥራት አዲስ የአብነት ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ሥራ እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡ የአካባቢው ወጣቶች በቅርባቸው ባለ አጥቢያ የአብነት ትምህርት ቤት በመማር የቤተ ክርስቲያናቸውን አገልግሎት በብቃት እንዲረከቡ ለማድረግ በሞከርነው አነስተኛ ጥረት ትልቅ ፍሬ እያየንበት ነው፡፡

ከዚኽ ኹሉ በተጨማሪ፣ ምንም እንኳ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች የነበረ ቢኾንም፣ ለቤተ ክርስቲያን የተማረው ኅብረተሰብ በበጎ ፈቃድ የማገልገል ልምዱ እምብዛም ነበር፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ይህ የኅብረተሰብ ክፍል ቤተ ክርስቲያንን በበጎ ፈቃድ እንዲያገለግል አርኣያ ኾኖታል ብለን እናምናለን፡፡ ለአንዳንዶችም ማኅበሩ የበጎ ፈቃደኛ አገልግሎትን በማስተዋወቅ አርኣያ ኾኗል ብለን እናምናለን፡፡

በአጠቃላይ የተማረው ኅብረተሰብ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያገለግል፣ የአብነት ትምህርት የመማር ፍላጎት እንዲያዳብር፣ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲጎለብቱ፣ አጥቢያዎች ራሳቸውን እንዲችሉ፣ ስብከተ ወንጌል በኹሉም እንዲስፋፋ ለማስቻል በአቅማችን የምንችለውን እያደረግን ነው፡፡

እንግዲህ ይህን ኹሉ ሥራ ስንሠራ፣ ማኅበሩ ምን ያህል ኣባላት አሉት? ለተባለው፣ ባለፉት 23 ዓመታት አገልግሎታችንን ስናከናውን በየዓመቱ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ተማሪዎች ስንት ናቸው ብሎ ማስላት ነው? ነው፡፡ በዚኽ ዓመት ብቻ በግቢ ጉባኤ በመማር ላይ ያሉ ወደ 250 ሺሕ ተማሪዎች አሉ፡፡ በርግጥ ከተመረቁት ውስጥ ኹሉም ወደ አገልግሎቱ አልመጡም፡፡ አንዳንዶቹ የማኅበሩን የአባልነት ፎርም ባይሞሉም በአገልግሎት ግን ደጋፊዎች ናቸው፡፡ በማኅበሩ በቀጥታ በመዝገብ የያዝናቸውና በአገልግሎት የሚሠማሩ ከ500 ሺሕ በላይ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ግን የማኅበሩ አባላት እነዚኽ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ አኹን ቁጥራቸውን ይህን ያክል ነው ብሎ ለመናገር ቢያዳግትም የአገልግሎታችን ደጋፊዎቻችን እጅግ ብዙ ናቸው፡፡

ማኅበሩ በመጀመሪያዎቹ ዘመናቱ የነበረው እንቅስቃሴው በጣም ከፍተኛ ነበር፡፡ ብዙ ወጣቶች በግቢ ጉባኤ አማካይነት የማኅበሩ አባላት እየኾኑ ራሳቸውን ማነፅና በኅብረተሰቡ ዘንድ ሳይቀር በዕውቀታቸውና በምግባራቸው የተመሰገኑ መኾን የቻሉ ቢኾንም፣ ቀጣይነት ያለው አይመስልም፡፡ አኹንም ጎልተው የሚታዩት የመጀመሪያው ትውልድ ሊባሉ የሚችሉት አባላት ይመስላሉ፡፡ ማኅበሩ ዕድገቱ ተገትቷል፤ ባለበት እየረገጠ ነው ወይስ እያደገ ነው?

ይኽን ጉዳይ ለማዬት በጨለማ ውስጥ መጀመሪያ አንድ ሻማ ለመለኮስ ክብሪት ስትጭር የምታየው የብርሃን መጠንና ሻማውን ከለኮስከው በኋላ ያለው የመብራቱ የድምቀት መጠን አንድ አይደለም፤ የመጀመሪያው፣ ብርሃን ካልነበረበት ኹኔታ መውጣት ስለነበር ትንሹም ደምቆ ይታያል፤ ቆይቶ ግን ያን ስንለምደው የደበዘዘ ይመስለናል፡፡ ለእኔ ይህ ጥያቄ ከዚኽ ኹኔታ ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡

መጀመሪያ ጊዜ ማንም በሌለበት የተሰባሰቡትን ሰዎች ኹሉም ሰው እንደ አዲስ ያያቸዋል፤ ኹሉም ክብር ይሰጣቸዋል፤ የተለየ አድርጎም ይገምታቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ያሉትን በተጫረው ብርሃን ምክንያት የመጣ ስለኾነ አዲስም ስላይደለ ይለመዳል፡፡ የአባላቱም መጠን ስለሚጨምር ለይቶ እገሌ ለማለት አይቻል ይኾናል እንጅ የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎትም፣ ሰው የማፍራት ሒደቱም እንደቀጠለ ነው፡፡ በቁጥር ብናየው እንኳ አባላቱ እጅግ እየጨመሩ እንጅ እየቀነሱ አልመጡም፡፡ እንዲያውም ለማኅበራችን ፈታኝ የነበረው የመጀመሪያዎቹ የምሥረታ ጊዜያችን ላይ የነበሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥርና ተማሪዎች ትንሽ ነበሩ፤ በኋላ ግን የተማሪዎችም፣ የትምህርት ተቋማቱም ሥርጭትና ብዛት በአንድ ጊዜ ሲመነደግ ኹሉንም ቦታ የመድረስ ሓላፊነት የማኅበረ ቅዱሳን ነበር፡፡ ስለዚኽ በአንድ ጊዜ ሲመነደግ ቁጥሩና ሥርጭቱ ሲያድግ ማኅበራችንም በዚያው ልክ ዐቅሙንም ማሳደግ ነበረበት፡፡

ማኅበሩ ያለው የሰው ኃይልና ሀብት በዚኽ ልክ ዕድገት ስላልነበረው እጅግ ፈታኝ ነበር፡፡ የግቢ ጉባኤያቱንና የሰንበት ትምህርት ቤቶችን የማስተሳሰር ሥራውን የሠሩት አባሎቻችን ናቸው እንጅ ሌላ ከየትም የመጣ አካል አይደለም፡፡ አኹን በአንድ ግቢ ጉባኤ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ50 እስከ 100 መርሐ ግብር አለ፤ በአጠቃላይ ወደ 390 የሚጠጉ የግቢ ጉባኤያት አሉ፡፡ እንግዲህ አባሎቻችን ይህን ኹሉ መሸፈን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ የማኅበሩ አባላትና አገልግሎት ምን ያህል እንደጨመረ ያሳያል፡፡ ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን ቀጣይት ያለው ሥራ እያከናወነ ነው፡፡

ምናልባት መጀመሪያ የነበሩት አባላት አገልግሎት በእይታ ደረጃ አኹን ያሉትን አባላት አገልግሎት ወጥቶ እንዳይታይ ሸፈነው ካላልን በስተቀር አገልግሎታችን እየሰፋ እንደኾነ በርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ የማኅበሩ አገልግሎት ዘርፍም እንዲኹ ሰፍቷል፡፡ ለዚህ ለሰፋው አገልግሎቱ ደግሞ ብዙ ሰው ያስፈልጋል፡፡ ስብከተ ወንጌልን ለመፈጸም በሚቻላቸው ሁሉ ገጠር እየገቡ ያገለግላሉ፡፡ በሞያቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉት አባሎቻችን ኹሉ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ አገልግሎቱም ሰፍቷል፤ ዕድገቱም አልተገታም፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ከእርሱ ውጪ ሌሎች ማኅበራትና ስብስቦች እንዳይገቡ ይከላከላል፤ የሌሎችን ማኅበራት መኖር አይደግፍም የሚል አስተያየት አለ፡፡ አስተያየቱ በእናንተ በኩል እንዴት ይታያል?

እውነት ለመናገር ይህ ትክክለኛ መረጃ ነው ብለን አናምንም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን አንድ ማኅበር ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ከሚያስፈልገው አንድ ሺሕኛውን እንኳ አገልግሎት ሰጥቷል ብለን አናምንም፡፡ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉም የሚበልጡም ብዙ የፈቃድ ማኅበራት ለቤተ ክርስቲያናችን ያስፈልጓታል፡፡ እርግጥ ነው ካህናቱም በፈቃድ ነው ሲያገለግሏት የኖሩት፤ ግን በማኅበር ደረጃ ተደራጅቶ አገልግሎት የሚሰጡ ማኅበራት ቁጥር ውስን ነበሩ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሕግና ደንብ ወጥቶለት በቅዱስ ሲኖዶስም ተፈቅዶለት ተቋቁሟል፡፡ ሌሎችም ማኅበራት የእኛን አርኣያ እንዲከተሉ እንፈልጋለን፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚወቅሱ አካላት ለምን ማኅበረ ቅዱሳን ያልሠራውን ክፍተት ሞልተው አያሳዩንም? ማኅበረ ቅዱሳን የሚያስፈልጓትን ለማሟላትና ክፍተቶች ካሉ ለቤተ ክርስቲያናችን አካላት እገዛ ለማድረግ ኹልጊዜ ይጥራል፤ የሚቻለውንም ያደርጋል፤ ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳን በማኅበር እንዲያደራጃቸው፣ ገንዘብና ለአገልግሎት የሚኾን ቦታም እንዲሰጣቸው የሚሹ አንዳንድ ሰዎች ያሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ ለማድረግ ማኅበሩ ሓላፊነትም ኾነ ዐቅም የለውም፡፡ ይህን ለማድረግ አለመቻላችን ግን አለመደገፍ ተደርጎ ሲወሰድ እንሰማለን፤ ይኼ ያሳዝነናል፡፡

ኹለተኛው፡- በማኅበራት ስም ተደራጅቶና የቤተ ክርስቲያን አካል መስሎ የሚፈልጉትን የቅሰጣ ሥራ ለመሥራት እንዲያመቻቸው ተሐድሶዎቹ የጀመሩት አንዱ ስልታቸው ነበር፡፡ በመኾኑም ማኅበር መሥርተው ብዙ የሔዱ እንዲህ ያሉ ወገኖች መኖራቸውን ባለን መረጃ መሠረት ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ማሳወቃችን እንደ አሉታዊ ኹኔታ ተቆጥሮ ተሐድሶዎቹ ያስወሩትን ሌሎች ወገኖችም በማስተጋባት አሉታዊ ምስል ለመፍጠር ሞክረዋል፡፡ መጀመሪያ ያስወሩት ተሐድሶዎቹ ናቸው፡፡

በዚህም ምክንያት “ማኅበሩ የሌሎች ማኅበራትን መመስረትም ሆነ ማደግ አይፈልግም”  እየተባለ ትክክል ባልኾነ መልኩ መወራት ጀመረ፡፡ ይህ በእውነቱ ያሳዝነኛል፡፡ ከዚያ ውጭ ግን የቤተ ክርስቲያናችንን ሕግና ደንብ ተከትለው ከተቋቋሙ ማኅበራት ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የዐቅማችንንም ያኸል ለመደገፍ ኹልጊዜም ዝግጁ ነን፤ እንዲያውም ለምንድን ነው የተለያዩ ማኅበራት ቢኖሩም ለአንድ ዓላማ እስከተቋቋምን ድረስ የጋራ የውይይት መድረክ የማይኖረን እያልን እንጠይቃለን፡፡

በ1980ዎቹ በበጎ ፈቃድ ተነሣሥተው የተጀመሩ ብዙ የኅትመት ውጤቶች ነበሩ፡፡ በጣም ጥሩ ነበሩ፡፡ እነዚያ ጥረቶች ግን በጥቂት ሰዎች ድካም ላይ የተመሠረቱ ስለነበሩ ሰዎቹ የሚችሉትን አደረጉ፤ የሚያግዛቸው በቂ ሰው ባለመኖሩ አገልግሎታቸው እየከሰመ ሔደ፤ ኋላም ቆመ፡፡ ለረጅም ጊዜ መዝለቅ የቻለው የጽርሐ ጽዮን አንድነት የኑሮ ማኅበር ነው፡፡ እነርሱም አሁን ድረስ መለከት መጽሔትንና የተለያዩ በራሪ ጽሑፎችን በማሳተም፣ ከየጠረፉ የሚመጡትን ወጣቶች ለማሠልጠን የሚያስችል የስብከተ ወንጌል ማሠልጠኛ ማእከል በመክፈትና ሥልጠናውንም ለተከታታይ ዓመታት በማከናወን ለቤተ ክርስቲያን በርካታ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፤ እኛም ከእነርሱ ጋር በጋራ በመተጋገዝ እንሠራለን፡፡

ቤተ ክርስቲያን በርካታ የአገልግሎት ዘርፎች አሏት፤ አገልግሎቷንም በትሩፋት ለመደገፍ ብዙ ማኅበራትም ያስፈልጓታል፡፡ እርግጥ በአገር ውስጥም ኾነ በውጭም አገር ያሉ በርካታ ማኅበራት የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት በተለያየ መንገድ ያግዛሉ፡፡ በተለይ የገዳማትንና የአድባራትን የልማት ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ከበርካታ ማኅበራት ጋር አብረን እየሠራን እንገኛለን፡፡

ማኅበሩ ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋር የሠመረ ግንኙነት የለውም ይባላል፡፡ ምክንያቱ ምን ይኾን?

ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር የተደራጀ የበጎ ፈቃድ ማኅበር ነው፡፡ ፈቃድም የሰጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን መነሻው የማኅበሩ አባላት በፈቃዳቸው በዚህ መልክ ልናገለግል እንፈልጋለን ብለው መቅረባቸው ነው፡፡ አገልግሎታችን የተሻለና የሠመረ የሚኾነው በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ብንኾን ነው ብለን ስላመንን የራሳችን መተዳደሪያ የሚኾን ሕገ ደንብ አውጥተን፣ ዕወቁን ብለን የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር ጠየቅን፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱም አስተዳደር በየደረጃው እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ ያቀረብነውን መነሻ አይቶና መርምሮ ግንቦት 1 ቀን 1984 ዓ.ም. ዕውቅና ሰጥቶናል፡፡ ኾኖም ግን የማኅበሩ ምሥረታ ሒደት ከ1970ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ ነው፡፡

በኋላም የማኅበሩ አግልግሎት እየሰፋና እየሠመረ ሲሔድ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በ1991 ዓ.ም. አይተው ሕገ ደንቡም ዳግመኛ ተሻሽሎ የበለጠ የሚያሠራ እንዲኾን ኾኖ እንዲቀርብ ተደረገ፡፡ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተመራው ኮሚቴ አይቶ መርምሮ ይህን ጨምሩ ይህን ቀንሱ ብሎ በ1992 ዓ.ም. በቋሚ ሲኖዶስ ታይቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ደረጃ የጸደቀ ደንብ ተሰጠን፡፡

በኋላም ሊቃነ ጳጳሳት ይህ የማኅበሩ አገልግሎት እኮ በየሀገረ ስብከቱ እየሰፋ ስለኾነ በአጠቃላይ ደረጃ ሊታይ ይገባዋል በማለታቸው በአምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ፣ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና የሕግ ባለሞያዎች ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ መርምሮ ነው የደንቡን ማሻሻያ ያጸደቀው፡፡ ለምሳሌ ማኅበሩ ባረቀቀው የመጀመሪያው ደንብ ላይ፥ የማኅበሩ ወሰን በሚለው ውስጥ፣ ‹‹ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም›› የሚል ነበረበት፤ ነገር ግን በ1994 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ተመልክቶ፣ የማኅበሩ በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ አለመግባት ትክክል ነው፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ አንገባም ማለት እኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ናችሁ ብለን እያጸደቀን ስንፈልጋችሁ እምቢ ልትሉን ነው ወይ? ስለዚህ ይህ “ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም” የሚለው ንኡስ አንቀጽ መውጣት አለበት አሉን፡፡

በዚኽ ዓይነት መንገድ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይበጃል ባሉት መንገድ አሻሽለው ኹሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፈርመውበት ነው ያጸደቁት፡፡ ርግጥ ነው እንደየትኛውም ዓለም አሠራር መጀመሪያ መነሻ የኾነውን መተዳደሪያ ደንብን አዘጋጅቶ ያቀረበው ማኅበሩ ነው፡፡ ስለዚኽ በማኅበሩ እና በቅዱስ ሲኖዶስ መካከል መቼም ቢኾን ችግር ተፈጥሮ አያውቅም፡፡ ኹልጊዜም እንደ ልጅነታችን የመታዘዝ ግንኙነታችን የሠመረ ነው፡፡ ፈቃዱን የሰጠን ቅዱስ ሲኖዶስ እስከ ኾነ ድረስ ከዚህ በኋላም የማኅበሩ አገልግሎት አያስፈልገኝም ካለም ቅዱስ ሲኖዶስ ማኅበሩን እንዲከስም ሊያደርገው ይችላል፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር የሠመረ ግንኙነት ባይኖረንማ ማኅበሩን ወዲያውኑ ሊሰርዘው ይችል ነበር፡፡

ነገር ግን በአኹኑ ወቅት በሚያሳዝን ኹኔታ ግንኙነታችን የሠመረ ሊኾን ያልቻለው ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ነው፡፡ ቅዱስነታቸው ገና ወደ መንበሩ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ቡራኬ ለመቀበል፣ እየታዘዝን አብረናቸው ለመሥራት ዝግጁ እንደኾን አሳውቀናል፤ ጠይቀናልም፡፡ በደብዳቤም፣ በአባቶችም፣ በአካልም ሔደን ብዙ ጊዜ ጠይቀናቸዋል፡፡ ግን ጊዜ ሰጥተው ሊያናግሩን አልቻሉም፡፡ ምክንያቱም ምን እንደኾነ እስካኹን ሊገባን አልቻለም፡፡ በአንጻሩ ቤተ ክርስቲያን የነበረችበት የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር የከፋ በመኾኑ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ለቤተ ክርስቲያን ባለድርሻ አካላት ኹላችኁም ርዱኝ ብለው ጥሪ ሲያቀርቡ እኛም ለመርዳት፣ ለመታዘዝ ዝግጁ እንደነበርን አሳውቀናል፡፡ ኾኖም ግን በዚያ ደረጃ ስላልተጠየቀ ማኅበሩ በቀጥታ ሠርቶ ያቀረበው ነገር አልነበረም፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዲስ አወቃቀር እንዲሠራ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መርጠው ያቀረቧቸውና ቅዱስነታቸው መመሪያ የሰጧቸው የኮሚቴ አባላት ወደ ጥናት ሥራው እንዲገቡ ሲደረግ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የኾኑ ሰዎችም በማኅበሩ ተወክለው ባይኾንም እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸው የኮሚቴው አባል ኾነው ገብተዋል፡፡ ጥናቱንም በሚገባ አጥንተው አቅርበዋል፡፡ ይህ ጥናትም የቅዱስ ሲኖዶስ እንጅ የማኅበረ ቅዱሳን አይደለም፤ የቀረበውም ለቅዱስነታቸው ነው፡፡ ጥናቱንም የሠሩት ባለሞያዎች መመሪያ የተቀበሉት ከቅዱስነታቸው ነው፡፡

ነገር ግን የጥናቱ ግኝት በተለይ በአዲስ አበባ አድባራት ያሉ አንዳንድ አለቆች የግል ጥቅማችንን ይነካብናል ብለው በማሰባቸው ይመስለናል ተቃውሞ አሥነሱ፡፡ ጥናቱን ከሠሩት ባለሞያዎች መካከል የማኅበሩ አባላት መኖራቸው እንደ ጥፋት ተቆጥሮ በቀጥታ ክሣቸውን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ አቀረቡ፡፡ ለጥናቱ መተግበር በይፋ ሲሰጥ የነበረውን የኅብረተሰቡን ድጋፍም አፍነው ለመሔድ ሞከሩ፡፡ ቅዱስታቸውም በመጀመሪያ የነበረው አቋማቸው ተሸርሽሮ የእነዚኽ አካላት ደጋፊ እየኾኑ መጡ፡፡ ለእኛ ግን፣ ችግራችኹ ይህ ነው ብለው በቀጥታ ሊነግሩን ወይም በችግሩ ዙሪያ ሊያወያዩን አልፈለጉም፡፡

ይህም ቢኾን እንኳ እኛ አባታችን ናቸውና ከቅዱስነታቸው ፊት ቀርበን መመሪያ ለመቀበልና ጉዳዮቻችንንም ለማስረዳት በደብዳቤ ብቻ እንኳ ለስድስት ጊዜ ያክል ጠይቀናቸዋል፤ መልስ እንኳ አልሰጡንም፡፡ በአካል እየሔድን፣ ተራ እየጠበቅን ቀጠሮ እንዲያዝልን ብዙ ሞክረናል፤ ብፁዓን አባቶችንና የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትንም እንዲኹም የተለያዩ አካላትን እንደ ሽማግሌ እየላክን አቅርበው ያነጋግሩን ዘንድ አስጠይቀናል፤ ግን ሊያገኙን አልፈለጉም፡፡ 

በአዲስ አበባ አንዳንድ አለቆች እንዲሁም ከነዚህ ላይ ተጨምሮ በተሐድሶ ኑፋቄ ተከታይነታቸው የሚጠረጠሩ አንዳንድ ግለሰቦች በሚሰጧቸው መረጃ ብቻ፣ ማኅበሩ መጥፋት አለበት የሚሉት አካላትን የሚደግፉ የሚመስሉበት ጊዜ አለ፡፡ ከዚያ ውጭ ግን ከቅዱስነታቸው ጋር ከዚኽ የተለየ የማያግባባ ነገር አለን ብለን አናምንም፡፡ ኹላችንም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ነው የምንተጋው፤ የምንሠራውን የምናውቅ ሰዎች ነን፡፡ ያጠፋነው ጥፋት ካለ እንኳ ጠርተውን ሊጠይቁንና ሊመክሩን ይገባል ነው የምንለው፡፡ ቅዱስነታቸው፣ የቤተ ክርስቲያን ርእሰ መንበር እንደመኾናቸውና የኹሉም አባት ስለኾኑ እንዲህ ዓይነት አመራር ቢከተሉ ነው የሚሻለው፡፡ ከዚያ ውጭ ግን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋርም ኾነ ከየትኛውም የቤተ ክርስቲያን አካል ጋር ምንም ዓይነት የጎላ ችግር የለብንም፡፡

የቅዱስነታቸውን ደብዳቤ እንዳየነው፣ ፓትርያርኩ ማኅበሩ እንዲፈርስ ይፈልጋሉ፡፡ የፓትርያርኩ ሐሳብ (ውሳኔ)ና እምነት ተፈጻሚ ቢኾን የማኅበሩ ዕጣ ፈንታ ምን ይኾናል?

ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ቀኖና የመከተል ግዴታ አለበት፡፡ የቤተ ክርስቲያን የበላይ ውሳኔ ሰጭ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ፥ አይ ይበቃል፤ የማኅበረ ቅዱሳን አግልግሎት አያስፈልገኝም ካለ ሊዘጋው ይችላል፡፡ አታስፈልገኝም ካለው ማኅበሩም በግዴታ አስፈልግሃለሁ አይልም፡፡ ያሉትን ክፍተቶች በትሕትና ከማስረዳት አልፎ ለምንድን ነው የማላስፈልገው ብሎ መከራከር ተገቢ ነው ብሎ አያምንም፡፡ አገልግሎት የምንሰጠው ቤተ ክርስቲያናችንን ለመደገፍ ነው፡፡ ስለዚኽ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነው ነው ተፈጻሚ ሊኾን የሚችለው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔም የማክበር ሓላፊነት አለብን፤ ነገር ግን፣ ፓትርያርኩ ብቻቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን ሊዘጉት አይችሉም፡፡ ቅዱስነታቸው ቅዱስ ሲኖዶሱን በርእሰ መንበርነት የሚመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ መንበር ናቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ብቻቸውን ሊሽሩ አይችሉም፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአኹኑ ወቅት የገጠማት ፈተና ምንድን ነው? ፈተናውን ለመጋፈጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ልታደርገው ይገባል የሚባለውስ ምንድን ነው?

ቤተ ክርስቲያን የተቋቋመችው ዛሬ በኛ ዘመን አይደለም፡፡ ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷን ሲኖዶስ አቋቁማ በራሷ ፓትርያርክ መመራት ከጀመረች ገና የአንድ ሰው ዕድሜ ያክል እንኳ ባይኾንም ብዙ ተመክሮዎች ግን አሏት፡፡ እንግዲህ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሲኖዶስ ተቋቁሞ፣ በራሷ ፓትርያርኮች እየተመራች መሔድ ከጀመረች አጭር ጊዜ ቢኾንም በነዚህ አጭር ዓመታት ውስጥ በሀገራችን የተለያዩ ማኅበረሰብ አቀፍ ለውጦች ተካሒደዋል፡፡ መንግሥት ተቀይሯል፤ የፖለቲካ ፍልስፍና ተለዋውጧል፤ አስተሳሰብ ተለውጧል፡፡ ይህ በቤተ ክርስቲያንም ላይ በበጎም ኾነ በአሉታዊ መልኩ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ 

በነዚኽ ዓመታት ውስጥ በሊቃውንቱ እና በአባቶች ያላሰለሰ ጥረት በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ብዙ ለውጥ የታየባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ፥ ብዙ አህጉረ ስብከት ተቋቁመዋል፤ ደረጃቸውን የጠበቁ መንበረ ጵጵስናዎች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፤ ከሌላውም ጊዜ በተሻለ መልኩ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጥር በመጨመሩ በየአካባቢው ያሉ ምእመናን አገልግሎቱን በቅርብ እያገኙ መጥተዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያናችንን የነገረ መለኰት ትምህርት የሚያስተምሩ መንፈሳዊ ኮሌጆች ተቋቁመዋል፡፡ በየአጥቢያው የሰበካ ጉባኤ በመቋቋሙ ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን ዐውቀው ለማገልገልና የቅርብ ተሳታፊ እንዲኾኑ ለማድረግ ተችሏል፤ በስብከተ ወንጌል አገልግሎቱ ዘርፍም ዕንቅፋቶች ቢያጋጥሙም የተሻለ ለውጥ ይታያል፡፡ በበጎ ጎን የሚታዩ ሌሎችም እጅግ ብዙ ለውጦች ተከናውነዋል፡፡  

ይህም ኾኖ ግን ፈተናዎች ከውስጥም ከውጭም መምጣታቸው አልቀረም፡፡ አኹን ግን የውጩን ብቻ እያየን ከውስጣችን ያለውን ፈተና ከዘነጋን ችግሯን መቅረፍና አደጋውን መቋቋም አንችልም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊያፈርሱ የሚተጉ አካላት ውስጥ ለውስጥ ያለውን ክፍፍል ነው የሚጠቀሙት፡፡ በተለይ በመካከለኛው ዘመን የካቶሊክ መልእክተኞች በጊዜው በነበረው ዓለም አቀፋዊ ወዳጅነት መጥተው አገራችን ውስጥ ፈጠሩት ከሚባሉት ችግሮች መካከል የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ዋና ሥራቸው የሆነውን ስብከተ ወንጌልን ትተው እርስ በርሳቸው እንዲከራከሩና እንዲጨቃጨቁ፣ እርስ በርስም እንዳይተማመኑ ማድረግ ነበር፡፡ በዚያ መሃል ነው፣ እነርሱ ውስጥ ገብተው ነገሥታትን ጭምር በሃይማኖት መቀየር የቻሉት፤ በዚህም ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት በርካታ ምእመናን በእርስ በርስ ጦርነት እንዲያልቁ ምክንያት ኾኑ፡፡

አኹንም ቢኾን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ዓይነት ነገር እንዲገባ ተግተው የሚሠሩና የዋሃንንም በማታለል የክፉ ተግባራቸው ሰለባ የሚያደርጉ አሉ፡፡ የቀድሞዎቹ መናፍቃን ሐሳባቸውን በይፋ ስለሚናገሩ ኹሉም ያውቃቸው፣ መከራከርም ሲያስፈልግ ሐሳቤ ይህ ነው ብለው ለመቅረብ የሚችሉ ነበሩ፡፡ በአኹኑ ዘመን ያሉት እናድሳለን ባዮች ግን እኔ ብለው በይፋ ወጥተው መናገር የማይደፍሩ፣ ሲጠየቁ እኔ አላልኩም ብለው ዓይኔን ግንባር ያድርገው ብለው የሚምሉ በመኾናቸው እንቅስቃሴያቸው በአብዛኛው በሰርጎ ገብ መልኩ ነው፡፡

በተለያዩ የብዕር ስሞች በሚጽፏቸው መጻሕፍት፣ አሳታሚያቸው በውል በማይታወቁ መጽሔቶችና ጋዜጦች፣ በራሪ ጽሑፎች፣ እንዲኹም በድረ ገጾች እና የማኅበራዊ መገናኛዎች የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ያብጠለጥላሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን የውስጥ አገልግሎት ኹሉ በእጅጉ ይነቅፋሉ፡፡ ጽሑፋቸውን ሲጽፉም ግእዝ ስለሚጠቅሱ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች መስለው አንዳንድ የዋሃንን ለማታለል ይሞክራሉ፡፡ ራሳቸውን ደብቀው ስለሚንቀሳቀሱም በሊቃውንቱም ኾነ በምእመናኑ መካከል ጥርጣሬና መለያየትን እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

ኹለተኛው፡- ቤተ ክርስቲያን የምንኖርበትን ዘመን ባገናዘበ መልኩ አደረጃጀቷ የተሻለ መኾን ነበረበት፡፡ ስሕተትን ቶሎ ማረም የሚያስችልና ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችል አስተዳደር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ያስፈልጋታል፡፡ የአመራር ሥርዓቷ በደንብ የተሰናሰለና ለሌውም በአርኣያነት የሚጠቀስ መኾን አለበት፡፡ ይህን ስንል ግን ቀኖናዊ ሥርዓቷ ቀርቶ ዘመናዊ የአስተዳደር ዘይቤ ብቻ የምትከተል ትኹን እያልን አይደለም፡፡ የካህናት አስተዳደርና በውስጧ ያሉትን ኹሉ በሥርዓት የምታስተዳድርበት የአስተዳደር መርሕ በውስጧ አለ፡፡ የካህናት አስተዳደር፣ አባቶቻችን ከሐዋርያት ተቀብለው እስከ አኹን በትውፊት ይዘነው የነበረው ወደፊትም የሚቀጥለው የአስተዳደር ሥርዓታችን ነው፡፡ ኾኖም ግን በሐዋርያትም ዘመን ቢኾን የአስተዳደሩ ጉዳይ ዋናውን ተልእኮአቸውን እንዳያስተጓጉልባቸው አስተዳደሩን የሚያግዙ ሰዎችን ከተመሰከረላቸው አማንያን መካከል መርጠው ሾመው ነበር፤ ይኸው አጠቃላይ ሥርዓት አኹንም አለ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ፣ የዘመኑን ትውልድ አሳምኖ ለመምራት የሚያስችል፣ አርቆ የሚያይና ዘመኑን የሚዋጅ ዘመናዊ አስተዳደር ለቤተ ክርስቲያናችን ያስፈልጋታል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ለኹሉም ነገር ጠንቃቃ የኾነ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አስተዳደራዊ ሥርዓት ያስፈልጋት ነበር፤ ግን ገና የለንም፡፡ ሦስተኛው በፕላን የመመራት ችግር አለባት፡፡ ዘመኑ በጣም በፍጥነት የሚጓዝ ነው፡፡ የጥፋት ተልኳቸውን ለማሳካት ተፈታታኝ የኾኑ አካላት እኩል ነው እየተጉ ያሉት፡፡ ይህን መመከት የሚችል የረጅም ዘመን ዕቅድ ያስፈልጋታል፡፡ ቀድሞ ማሰብ የሚችልና ዘመናዊውን መሥመር የሚያሳይ ዕቅድ ያስፈልጋል፡፡

አኹን ግን፣ በየዓመቱ በሚታቀድ፣ ከእጅ ወደ አፍ በኾነ ባልተሰናሰለ ዕቅድ እየተመራች ነው፡፡ በዚህ ላይ የእናድሳለን ባዮቹ ተጽዕኖ እየጨመረ ነው የመጣው፡፡ ሌሎች ተቀናቃኞቿ የውጭ ደጋፊ አካላት አሏቸው ማለት ይቻል ይኾናል፤ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ግን ደጋፊዎቿ አባላቷ ብቻ ናቸው፡፡ ጥንካሬዋ በሊቃውንቷ የእምነት ጽናት ላይ፣ በምእመናኗ መተማመንና መደጋገፍ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

ይህም ግን ሰርገው በሚገቡ አካላት እየተቦረቦረ ነው፡፡ የተሐድሶ መናፍቃኑ እንቅስቃሴ ሲያዩት ቀላል ይመስላል እንጅ በብዙ አጥቢያዎቻችን ብጥብጥና መከፋፈል እንዲፈጠር ምክንያት እየኾኑ ነው፡፡ መረጋጋት በቤተ ክርስቲያን እንዳይኖር ተግተው እየሠሩ ነው፡፡ የጥሩ ሥነ ምግባር አለመኖር ኃጢአት እንዳልኾነ የሚያሳይ ልዩ ትምህርት እያስተማሩም ነው፡፡ አንድ ጊዜ በሠራኸው ሥራ ጸድቀሃል በማለት ሰዎች የበለጠ ጥፋትን እንዲለማመዱ የማድረግ ሥራ እየሠሩ ነው፡፡ በዚኽም በቤተ ክርስቲያኒቱ ገንዘብ የፈለጋቸውን ለሚያደርጉ ጥቅመኞች ሽፋን እየሰጡ ነው፡፡

የሃይማኖት ችግር ያለባቸውና የምግባር ችግር ያለባቸው አካላት ኹለቱ የጥቅም ትስስር ያለበት ትልቅ ጋብቻ ፈጽመዋል፡፡ ይህ ለቤተ ክርስቲያናችን ከባድ ፈተና ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም ትልቅ ዕንቅፋት ፈጥሯል፡፡ ይህ ደግሞ ታች አግልግሎት ላይ ያሉ ካህናት ላይ ጫና ፈጥሯል፡፡ ካህናቱ ተበደልን ብለው የሚጠይቁት እነዚኽኑ በጥቅም የተሳሰሩትን ሰዎች ነው፡፡ ይህ በመኾኑ፣ ስለኑሯቸውና ከሥራችን ያባርሩናል ብለው ስለሚሰጉ፣ ደግሞም እያባረሯቸው ስለኾነ ካህናቱ ድምፃቸውን አጥፍተው በስጋት ነው የሚኖሩት፡፡ ይህ እየኾነ በሔደ ቁጥር ምእመናን ስለ ሃይማኖታቸው እየተቆረቆሩ መጥተዋል፡፡ የምእመናን ቁጣ ሌላ አለመረጋጋትና ችግር ፈጥሮ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሔድ የሚመለከተው አካል ኹሉ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ብለን እናምናለን፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ፣ ለኹለት ጊዜ ያክል በዚኽ ጉዳይ ላይ በሰፊው ተወያይቶ ውሳኔ ሰጥቷል፤ ግን ውሳኔውን ማስፈጸም አልተቻለም፡፡ ያ የሚያሳየው ጥቅመኞቹ ሰዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ እንደ ኾነ ነው፡፡ ይህን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተፈጻሚ ለማድረግ ኹላችንም ሓላፊነት አለብን፡፡ እንደየድርሻችንም የቤተ ክርስቲያን አንድነት ይመጣ ዘንድና ዕድገቷ ምእመናኗን ኹሉ ለበለጠ አገልግሎት በሚያሳትፍ መልኩ ይኾን ዘንድ ልንደግፋት፤ የበኩላችንን ድርሻም ልንወጣ ይገባል፤ እላለኹ፡፡

 

 

25 thoughts on “ማኅበረ ቅዱሳንን የወለደው፥“እኔ ለቤተ ክርስቲያኔ ምን ማድረግ እችላለኹ” የሚለው ሐሳብ ነው፤ይጥፋ የሚሉት የጥቅም ጋብቻ የፈጸሙ አማሳኞችና የተሐድሶ መናፍቃን ናቸው/ሰብሳቢው/

  1. Anonymous February 9, 2016 at 6:47 pm Reply

    ፓትርያርኩ ብቻቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን ሊዘጉት አይችሉም፡፡

    • right February 10, 2016 at 2:10 am Reply

      Ok

  2. Miressa Kebede February 10, 2016 at 5:32 am Reply

    Mahiberun yakuwakuwamewu Egziabher new silezih Egziabher yemeseretew manim ayafersim lemafresim yemitagel kale tigilu kesewoch gar sayihon ke Egziabher gar new ke Egziabher gar yemitagel degmo mechem ayashenifim.

  3. Anonymous February 10, 2016 at 7:17 am Reply

    minewu patriarku mengist new yemeretachewu weis miemenan weis degimo tehadiso bewun yebetekirstian atir kitir yehonewun mahiber afirso betekirstianin badowan kaskeru buhala endefelegu lemehon new yetefelegewu bewun yateratiral mechem yetignawum maereg lay binhon kekihidet ena kelebinet wedehuala yemil yelem endewu eski kom bilen enasib satinaelim eko yemelaekit aleka neber ena egnih sewu min lemehon endefelegu gize yemifetawu neger new patriarc enkuan lenefisu yaladerebet zemen aye lesilitan yasazinal mastewalun yistachewu

  4. Anonymous February 10, 2016 at 7:21 am Reply

    በቃለመጠየቁ ቀርበው ተቀባይነት ለማግኘት ከሚከብዱ ጉዳዮች ውስጥ
    – ማኅበረቅዱሳን የተመሠረተው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይደለም፡፡ብላቴን ማሰልጠኛ ነው፡፡የኤፍሬም እሸቴን ‹‹አደባባይ ብሎግ›› ማየት ይቻላል፡፡ቀሲስ ዶ/ር ምስረታውን ብላቴ ማለት ለምን እንደፈሩት ግልጽ አይደለም፡፡

    – የአባላቱ ብዛት 500ሺ መባሉ አጠራጣሪ ነው፡፡ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ የገባ ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ የማኅበሩ አባል እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡በግቢ ጉባኤ ሳይታቀፍ የግሉን ጸሎት በቤ.ክ እየጸለየና እያስቀደሰ የሚመለስ አለ፡፡በለዘብተኛነት የሚኖር ኦርቶዶክሳዊም አለ፡፡በግቢ ጉባኤ የሚታቀፈው የኮሌጅና የዩነቨርሲቲ ኦርቶዶክሳዊ ከ3 ተማሪ ምናልባት 1 ቢሆን ነው፡፡ለእሱም ውስጥ ከምርቃት በኋላ ከማኅበሩ ጋር ያለው ግንኙነት የሚቋረጥ ብዙ ነው፡፡ከማኅበሩ መራቅ ማለት ግን ከቤ.ክ መራቅ ማለት አይደለም፡፡ምክንያቱም ማኅበረቅዱሳን ማለት ቤ.ክ ማለት አይደለም፡፡ማኅበር ነው፡፡ስለዚህ የአባል ቁጥሩን ኦዲተር የለውም ብሎ ማጋነን ያስተዛዝባል፡፡

    – ፓትርያርኩ ማኅበሩ ይታረም ነው ያሉት፡፡እርማቱም በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲከናወን እንጥራለን ነው ያሉት፡፡ይፍረስ አላሉም፡፡ይፍረስ አሉ ተብሎ የሚናፈሰው ቲፎዞ ለማንቀሳቀስ እንዲያ መዓት ጨምሮ ማውራት እንደ ልምድ ስለተያዘ ነው፡፡ደብዳቤያቸው ይመስክር፡፡የጋዜጣው ጠያቂ ፓትርያርኩ ማኅበሩ ይፍረስ ያሉ አስመስሎ በመጠየቅ የሠራውን ስሕተት ሰብሳቢው ማረም ሲገባቸው ጭራሽ አጽድቀውት ሄዱ፡፡ይገርማል፤ያሳዝናል፡፡

    – የማኅበሩን አመራር አንድ ጊዜ በጥናቱ ጉዳይ አነጋግረዋል፡፡ጥያቄያችሁ በይደር ይታያል ሲባሉ አሁኑኑ ያጠናነው መዋቅራዊ ጥናት ካልተተገበረ አሉ፡፡በዚህ አለመግባባት ሲወጡ ‹‹ያኛውን ተገላገልን ስንል የባሰ መጣ፤አምላክ ሆይ ይሄንንም ውሰድልን›› ሲሉ ተሰሙ፡፡ከዛ ቀን ጀምሮ ፓትርያርኩ ተቀየሙ፡፡ማኅበሩ ላይ ያላቸው አመለካከት በአመራሮቹ ግብዝነት የተነሳ ተዛባ፡፡

    – ስለቤተክሕነትና ስለፓትርያርኩ ድክመት በስፋት የሚተነትኑት ቀሲስ ዶ/ር በማኅበራቸው ደረጃ ይቅርና አንዳንድ አባላቶቻቸው ስለሚያሳዩት ኢ-ሥነምግባራዊ ባሕርይ ትንፍሽ ማለት አይፈልጉም፡፡መቼም የማኅበሩ የበላይም ሆነ የበታች አመራር አባላት ስለማኅበራቸው ያላቸው ግምት አስደናቂ ነው፡፡መመጻደቁ ወደር የለውም፡፡ስሕተትን በማመን ከማኅበሩ ቤተክሕነቱ ሺ ጊዜ ይሻላል፡፡የፓትርያርኩ ደብዳቤ መነሻ ስለሆነው የኮሌጆች ቅሬታ የጠየቀም የመለሰም የለም፡፡ከዚያ ይልቅ ጉዳዩን የተሐድሶና የኦርቶዶክስ ፍልሚያ አድርጎ ማኅበሩ አስተዳደራዊ ህፀፁን ያለባብሳል፡፡

    – የቤተክርስቲያኗ መዋቅር በልማት፣በስብከተ ወንጌል፣በአብያተ ክርስቲያናት ግንባታ፣በሰብአዊ ልማት፣በማሰልጠኛና በኮሌጅ ግንባታዎች ስላደረገው በጎ እንቅስቃሴ ከተናገሩ የሚቀሰፉ ስለሚመስላቸው አንዳች አይናገሩም፡፡

    – ማኅበሩ ላይ ቅሬታ የሚያቀርብ ወይ ተሐድሶ ነው አልያም ጥቅሙ የተነካበት ነው የሚል ጠባብ አፋኝ አመለካከት ያስተዛዝባል፡፡ንጹሕ ኦርቶዶክሳዊ ሆነው በማኅበሩ አባላት ትምክህተኛ እና በቲፎዞ የታጀለ ቡድናዊ የጫጫታ ጉዞ ቅሬታ ያላቸው አሉ፡፡ይሄን ለማረጋገጥ እኮ በጣም ቀላል ነው፡፡የማኅበሩ ወዳጅ ነን በሚሉ የብሎግና የፌስቡክ ገጾች የሚዘንበውን የማኅበር ውዳሴና የቤተክሕነትን ከነመሪዎቹ እያናጠሉ አራካሽ ዘገባ ለማየት ደግሞ እድሉ ያለን ዘወትር የምናየው ነው፡፡

    ስለሁሉም አባትና ልጅ ተቀራርበው ለሁለንተናዊ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እንዲሠሩ አምላክ ይጨመርበት፡፡

    • anonymously February 10, 2016 at 8:23 am Reply

      Me Tehadsona kene Hama gar honew college tegentew baderegut diskur mahiberun mewires alebin eridugn eskimot aletewewim yalutin alisemahim ???!!? Besachew dereja yemaybal yemiweresew Genet menigite Egizihabiher new!! Yewah??!!

      • Anonymous February 10, 2016 at 9:11 am

        የብሎግና የፌስቡክ መረጃ ይዛችሁ ከነፈሰው ጋር ትነፍሳላችሁ፡፡ፓትርያርኩ ማኅበሩ በሕግና በመዋቅር ደንብ ይመራ ነው ያሉት፡፡ይፍረስ አላሉም፡፡ይፍረስ አሉ የምትሉት ለጫጫታና ለቲፎዞ ማንቀሳቀሻ እንዲመቻችሁ ነው፡፡ሲቀጥል ማኅበሩ በአፉ ለአባቶች ታዛዥ ነኝ ቢልም ውዳሴ ካልሆነ በቀር ተግሳጽ ለመቀበል ምንም ዝግጅት ስለሌለው በተገሰጸ ቁጥር ልፈርስ ነው አገር ይያዝ ማለት ይወዳል፡፡ማኅበሩን ማንም አያፈርሰውም፡፡ሥርዓት መያዝ እንዳለበት ግን አያጠራጥርም፡፡

        ማኅበሩ ሁለንተናቸውን ሰጥተው በትሕትና የሚያገለግሉ አባላት ያሉትን ያህል በየሚዲያው በማኅበር ደጋፊነት ሽፋን አንደበታቸውን በአስጸያፊ ቃላት ሲያላቅቁ የሚውሉ በሺህ የሚቆጠሩ ያልተገሩ አባላት አሉ፡፡ከአመራርም ውስጥ ዘርፈ ብዙ የምግባርና የአመለካከት እንከን የተጠናወታቸው እቡያን አሉ፡፡እነሱ መስመር እንዲይዙ ጠንካራ የመተዳደሪያና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ያስፈልጋል፤ቁርጠኛና የማያወላውል አባት ከነመዋቅሩም እንዲሁ፡፡

        ሕጎች ሁሉ ለሌላው እንጂ ለእነሱ የሚሠሩ አይመስላቸውም፡፡ግን ብዙ ቅንና የዋሀን የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዳሉበት ስለሚታወቅ መመለሱን እንጂ ጥፋቱን የሚመኝ የለም፡፡አቡነ ማትያስም እንደሱ ነው ያሉት፡፡በስሚ ስሚ ወሬ አንሸውድ፤አንሸወድ፡፡

    • Anonymous February 10, 2016 at 2:30 pm Reply

      እውነት አርነት ያወጣዎታል! በቃሉ ካመኑበትና ከኖኑበት። ህሊናዎና ልብዎ በጎውን የሚከተል ከሆነ በጽሑፉ ላይ የሰጡት አስተያየት ሚዛናዊነት የጎደለው ነው። እንዲሁም በሙያዊ የጽሑፍ አተናተንም ሆነ የቀረበውን ጽሑፍ በመሬት ካለው እውነተኛ መረጃ ጋር የማገናኘት አቅም ወይም ፍላጎት ያጣ ነው። አልያም ጭፍን ጥላቻን በእኔ ብቻነት ተስቦ በተጠቃ ህሊናና ልብ የሚያንፀባርቅ ነው። ማኅበሩ የመላእክት ህብረት ነው ስህተት አይሰራም እያልኩ አይደለም፣ የሰው ህብረት ነው ያውም ከተለያየ ቦታ፣ የእድገት ሁኔታ፣ ባህል፣ የትምህርት ደረጃና ሙያና ከመሳሰሉት የመጡ ሰዎች ያሉበት ነው። ነገር ግን የቀረበውን ጉዳይ ሌላ መስመር ማስያዝና እውነትን መቃወም መዘዙ ሁሉን ያለ አድልዎ ከሚያይና ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ማስቀየም ነው። አመኑም አላመኑም እውነት ትዘገይ ይሆናል እንጂ እንደተሸፈነች አትቀርም፣ ደግሞ የመልካም ህሊና ወይም አስተሳሰብ ውጤት ከመልካም ዋጋ ጋር ትጠብቀናለች በክፉ ህሊና የተሰራች ክፉ ሥራ ከክፉ ዋጋ ትጠብቀናለች።/For every action there is Reaction። በጎ ህሊና ያድለን። በደላችንንም አያስብብን።

    • Anonymous February 10, 2016 at 3:00 pm Reply

      የህ በግልፅ በቀን ብረሀን በቪድዬ ያየነውና የሰማነው ነው። ምንም ማስተባበል አትችሉም። ለማፋረስ ብዙ እየለፈችሁ ነው ምንም ጥያቄ የለውም። ምነውስ ፈራችሁ በተቀሙ አባላት ብዛት ለይስ። ት/ቤ ሳለን በመንፈስ የደገፈን ማንስ ነው? ለሁሉም ነገር ፈጣሪ ያውቃል።

    • Anonymous February 10, 2016 at 4:17 pm Reply

      የምን ቱልቱላ መንፋት ነው ኮተታም ካድሬ።

    • Anonymous February 10, 2016 at 5:31 pm Reply

      እቺ የአብዬን ወደ እምዬ ትመስላለች።
      እግዚአብሔር ልብ ይስጥህ።

  5. Anonymous February 10, 2016 at 8:56 am Reply

    ውድ “Anonymous February 10, 2016 at 7:21 am” እውነተኛ የተዋሕዶ ልጅ ከሆንክ የግድ የማኅበሩ ደጋፊ እንድትሆን ባይጠበቅብህም ፀሐይ የሞቀውን አገር ያወቀውን እውነታ ግን መካድ የለብህም፡፡ ማኅበሩ ምንም ያጋነነው ወይም ራሱን ከፍ ያደረገበት ሁኔታ የለም፡፡ እውነቱን ለማወቅ ፍላጎት ካለህ አእምሮሮን ከፍተህ ከጽንፈኛነት ነጻ ወጥተህ ቀርበህ አጥናው፣ ምረምረው፣ ፈትነው፣ በግልጽ ውቀሰው፣ አስተምረው፡፡ አለበለዚያ ግን ጉንጭ ማልፋት ብቻ ይሆንብሃል፡፡

  6. Anonymous February 10, 2016 at 9:23 am Reply

    ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ቀኖና የመከተል ግዴታ አለበት፡፡ የቤተ ክርስቲያን የበላይ ውሳኔ ሰጭ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ፥ አይ ይበቃል፤ የማኅበረ ቅዱሳን አግልግሎት አያስፈልገኝም ካለ ሊዘጋው ይችላል፡፡ አታስፈልገኝም ካለው ማኅበሩም በግዴታ አስፈልግሃለሁ አይልም፡፡ ያሉትን ክፍተቶች በትሕትና ከማስረዳት አልፎ ለምንድን ነው የማላስፈልገው ብሎ መከራከር ተገቢ ነው ብሎ አያምንም፡፡ አገልግሎት የምንሰጠው ቤተ ክርስቲያናችንን ለመደገፍ ነው፡፡ ስለዚኽ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነው ነው ተፈጻሚ ሊኾን የሚችለው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔም የማክበር ሓላፊነት አለብን፤ ነገር ግን፣ ፓትርያርኩ ብቻቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን ሊዘጉት አይችሉም፡፡ ቅዱስነታቸው ቅዱስ ሲኖዶሱን በርእሰ መንበርነት የሚመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ መንበር ናቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ብቻቸውን ሊሽሩ አይችሉም፡፡

  7. Bitweded February 10, 2016 at 9:24 am Reply

    ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ቀኖና የመከተል ግዴታ አለበት፡፡ የቤተ ክርስቲያን የበላይ ውሳኔ ሰጭ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ፥ አይ ይበቃል፤ የማኅበረ ቅዱሳን አግልግሎት አያስፈልገኝም ካለ ሊዘጋው ይችላል፡፡ አታስፈልገኝም ካለው ማኅበሩም በግዴታ አስፈልግሃለሁ አይልም፡፡ ያሉትን ክፍተቶች በትሕትና ከማስረዳት አልፎ ለምንድን ነው የማላስፈልገው ብሎ መከራከር ተገቢ ነው ብሎ አያምንም፡፡ አገልግሎት የምንሰጠው ቤተ ክርስቲያናችንን ለመደገፍ ነው፡፡ ስለዚኽ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነው ነው ተፈጻሚ ሊኾን የሚችለው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔም የማክበር ሓላፊነት አለብን፤ ነገር ግን፣ ፓትርያርኩ ብቻቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን ሊዘጉት አይችሉም፡፡ ቅዱስነታቸው ቅዱስ ሲኖዶሱን በርእሰ መንበርነት የሚመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ መንበር ናቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ብቻቸውን ሊሽሩ አይችሉም፡፡

  8. Anonymous February 10, 2016 at 10:53 am Reply

    Not only 5000 Members It Will be > 5000 Members

  9. Anonymous February 10, 2016 at 2:04 pm Reply

    ከጀማል ሀሰን አሊ (የአሁኑ ገ/ሥላሴ)
    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
    አሜን!
    ምክንያተ ጽሕፈት፡- ከሙስሊም ወገኖች ጋር በተገናኘ
    አንዳንድ ጠለቅ ያሉ የጽሑፍ ሥራዎችን ስለምሠራና
    ንጹሕ ልቡና ላላቸው ሙስሊም ወገኖቻችን ወንጌልን
    በዘዴ እየሰበኩ ወደ እውነተኛው ክርስትና እንዲመጡ
    ስለማደርግ በዚሁ አገልግሎቴ ምክንያት የሊቃውንት
    ጉባዔ አባል ከሆኑ አባቶችና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
    ከሆኑ ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በቅርበት
    የመገናኘትና በአንዳንድ ነገሮች ላይ መረጃ የማግኘት
    አጋጣሚው አለኝ፡፡ እናም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይና በቤተ
    ክህነቱ ውስጥ ስለሚከናወኑ ነገሮች ከምንጫቸው
    መረጃውን በቀላሉ አገኛለሁ፡፡ ከአሕዛብ ጋር በተገናኘ
    በምሰጠው አገልግሎት ምክንያት በቅርቡ መሐመድ
    የሚባል አንድ ወንድሜ ወደ እውነተኛው ክርስትና
    እንዲገባ ምክንያት ሆኜው ነበር፡፡ እሁድ ጥቅምት 16 ቀን
    2007 ዓ.ም ደወለልኝና በቀጠሮ ተገናኘን፣ ነገር ግን
    ስንገናኝ የቀድሞው መሐመድ የአሁኑ ወልደ ሚካኤል
    የጠየቀኝ ጥያቄ እንደቀድሞው ስለ ክርስትና እምነት
    መሠረታዊ ነገር ወይም ስለ አሕዛብ ከንቱነት አልነበረም፡፡
    በተናደደ ስሜት ውስጥ ሆኖ ‹‹በአሁኑ ወቅት ከአንዳንድ
    የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይልቅ የመስጊድ ሸሆች
    ይሻላሉ›› አለኝ፡፡ በጣም በድንጋጤ የተዋጥኩ ቢሆንም
    ምክንያቱን በተረጋጋ ስሜት እንዲነግረኝ ጠየኩት፡፡
    በኢንተርኔት ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችን
    የሚከታተልበትን የሞባይል ስልኩን አውጥቶ ያነበባቸውን
    ድረ ገጾችና የፌስ ቡክ ገጾችን በሙሉ እያወጣ አሳየኝ፡፡
    ‹‹ይሄኮ በጣም ቀላል ነው ታዲያ›› በማለት በፈገግታ
    ነገሩን አቅልዬ ላስረዳው ሞከርኩ፡፡ ነገር ግን መሐመድን
    (የአሁኑን ወልደ ሚካኤልን) እንዲህ በቀላሉ ለማሳመን
    አቅም አነሰኝ፡፡ ‹‹…መናፍቃንና የቤተ ክርስቲያን የውስጥ
    ጠላቶች ፓርያርኩን አግባብተው በእጃቸው አስገብተው
    ማኅበሩን ሊያፈርሱት ነው…›› ‹‹ፓትርያርኩምኮ
    እየተወያዩና እየወገኑ ያሉት ከሲኖዶሱ ጋር ሳይሆን
    ከእነዚህ አካላት ጋር ነው…››፣ ‹‹በአሁኑ ወቅት ከአንዳንድ
    የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይልቅ የመስጊድ ሸሆች ይሻላሉ
    ምክንያቱም ሸሆቹ ቢያንስ ሙስሊሙን ለጠላት አሳልፈው
    አይሰጡም…›› እያለ የምሬት ንግግሮቹን አወረደብኝ፡፡
    ክርስትና ማለት የፈተናና የመከራ ሕይወት መሆኑን፣
    ፈተናውም ከእርኩሳን ረቂቅ አጋንንት የሚመጣ መሆኑንና
    ይኸውም ፈተና በጸሎትና በትእግስት የሚታለፍ እንደሆነ
    ከዚህ በፊት ያስተማርኩትን መርሳት እንደሌለበት
    በማስታወስ ትንሽ ካረጋጋሁት በኋላ ሌሎችም ብዙ
    ነገሮችን አውርተን በሌላ ጊዜ ለመገናኘት በሰላም
    ተለያየን፡፡
    ማታ እቤቴ ገብቼ አረፍ ካልኩ በኋላ ግን የዚህ ወንድሜ
    አነጋገር ውስጤን እረብሾታል፡፡ ለመሆኑ የአሕዛብን ሸሆች
    የሚያስመሰግን ክፉ ነገር በእኛ አባቶች ዘንድ አለ እንዴ?
    እውነትም ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ለጠላት አሳልፈው
    የማይሰጡ ሸሆች ባሉበት ወቅት የቤተ ክርስቲያንን ልጆች
    ለጠላት አሳልፈው የሰጡ ‹‹አንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን
    አባቶች›› አሉን እንዴ? በተናገሩት ነገር ወይም በሠሩት
    እኩይ ተግባር ‹‹አንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች››
    ይሄን ያህል ከአሕዛብ አባቶች ያልተሻሉ ሆነዋልን? ብዬ
    ራሴን ጠየኩ፡፡ እርግጥ ነው እኔም ወደ ክርስትናው
    ከመጣሁ ጥቂት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆኑም በአሕዛብ
    አባቶች ዘንድ ያለውን ታማኝነት አውቀዋለሁ፡፡ ምንም
    እንኳን ከላይ ከገዥው አካላት በኩል የሚመጣባቸውን
    ከባድ ጫና መቋቋም ቢያቅታቸውም የትኛውም የእምነቱ
    መሪ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ አሳልፎ ለጠላት ሲሰጥ
    አልተመለከትኩ፣ አልሰማሁም፡፡ ስለአሕዛብ መሪዎች
    ጥንካሬና ታማኝነት ምስክርነት እየሰጠሁ አይደለም
    ያለሁት-ይልቁንም እነርሱን (የአሕዛብን መሪዎች)
    እያስመሰገኑ ስላሉት ስለእኛው አባቶች አንዳንድ ነገሮችን
    ማለት ስለፈለኩ ነው፡፡
    በዓለም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እጅግ ዘግናኝ የነበረው
    ዘመን የወርቅ ምስልን አምላኩ ያደረገው የከሃዲው
    የዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ነው፡፡ የሚወለዱ ልጆችን
    ክርስትና ለማስነሣት ቤተ ክርስቲያንና አጥማቂ ካህን
    ከመጥፋቱ የተነሣ እንደ ቅድስት ሣራ ያሉ እናቶች
    ከአንጾኪያ ግብጽ ድረስ እስከመጓዝና ጡቶቻቸውን
    እየቆረጡ በደማቸው ልጆቻቸውን እስከማጥመቅ
    የደረሱበት ዘመን ነው-የዲዮቅልጥያኖስ ዘመን፡፡ በዓለም
    ላይ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን ከማቃጠሉም በላይ ከ9
    ሺህ በላይ የሚሆኑትን ደግሞ በማሠር፣ ከ47 ሺህ በላይ
    የሚሆኑ ክርስቲያኖችን በእሳት በማቃጠልና አንገታቸውን
    በመሰየፍ ምድርን በክርስቲያኖች ደም እንድትጨቀይ
    ያደረገው ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ቢሆንም ለዚህ ጥፋቱ
    መነሻ የሆነው ግን አንድ የቤተ ክርስቲያን መነኩሴ ነው፡፡
    ዲዮቅልጥያኖስ በክርስትና እያመነ ያለ አዲስ ክርስቲያን
    ነበር፣ እርሱም የቍዝ ንጉሥን ወንድ ልጅ ኒጎሚዶስን
    በቅዱስ ቴዎድሮስ በናድልዮስ አማካኝነት ከማረከው በኋላ
    የንጉሡን ልጅ ከአባ አጋግዮስ ዘንድ በአደራ ቢያኖረውም
    አባ አጋግዮስ ግን በኒጎሚዶስ ክብደት ልክ ወርቅ
    አስመዝኖ ከአባቱ ከቍዝ ንጉሥ ተቀብሎ ልጁን መልሶ
    ለአባቱ አሳልፎ ሰጠውና ዲዮቅልጥያኖስን ‹‹የማረከው
    የንጉሡ ልጅ ሞቷል›› ብሎ ዋሸው፡፡ ንጉሡ ግን እውነቱን
    ያውቅ ነበር፡፡ መነኩሴው መጽሐፍ ቅዱስንም መትቶ
    በመማል የውሸት መቃብር አሳየው፡፡ ንጉሡም መነኩሴው
    በውሸት መጽሐፍ ቅዱስ መትቶ ሲምል ተሰንጥቆ የሚሞት
    መስሎት ነበርና ምንም ሳይሆን ቢቀር ወርቅ አቅልጦ
    አምጥቶ ቢያጠጣው ተሰንጥቆ ሞተ፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም
    በክርስቶስ ማመኑን ተወና ‹‹አምላክ ማለት እንዲህ
    ሰንጥቆ የሚገድል ወርቅ ነው›› በማለት ክርስያኖችን
    መግደል ጀመረ፡፡ የነገሥታት ልጆች የነበሩት ታላላቆቹ
    ሰማዕታት እነ ቅዱስ ፋሲለደስ፣ እነ ቅዱስ ፊቅጦር፣ እነ
    ቅዱስ ገላውዲዮስ፣ እነ ቅዱስ ቴድሮስ በናድልዮስ፣ እነ
    ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት፣ እነ ቅዱስ ዮስጦስ፣ እነ
    ቅዱስ አቦሊና ሌሎቹም የከበሩ ኃያላን ሁሉ
    በዲዮቅልጥያኖስ ትእዛዝ እጅግ አሠቃቂ መከራዎችን
    እየተቀበሉ በክብር ሰማዕትታቸውን በመፈጸም ለ49ሺህ
    ሰማዕታት መሪ ሆነው እንዳለፉ ስንክሳሩ መጽሐፍ
    ይናገራል፡፡
    በሀገራችንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 40 የመከራና
    የሥቃይ ዘመን በዮዲት ጉዲት ብታሳልፍም ከዮዲት
    ከጀርባ ግን የአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶች እኩይ
    ተግባር ነበረበት፡፡ ይኸውም የእኛው አባቶች ሁለት
    ጡቶቿን በግፍ ቆርጠዋት ስለነበር በበቀል ተነሥታ ነው
    ያን ሁሉ መከራ ያጸናችው፡፡ ግራኝ መሐመድም አንዳንድ
    የቤተ ክርስያናችን አባቶች የግራኝን ወላጅ አባቱን በግፍ
    ገድለውበት በበቀል ተነሥቶ ነው 15 ዓመት ሙሉ በቤተ
    ክርስቲያን ላይ ያን ሁሉ መከራና ግፍ የፈጸመው፡፡
    የማይካድ ሐቅ ነው ከእያንዳንዱ አስከፊ የቤተ ክርስቲያን
    ታሪክ ጀርባ የእኛው የቤተ ክርስቲያን አባቶች መነሻ ሆነው
    አገልግለዋል፡፡ በዘመናችንም ለትውልዱ ጥፋት መነሻ
    የሚሆን ድርጊት ለመፈጸም ‹‹አንዳንድ አባቶቻችን››
    ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ደፋ ቀና ሲሉ ኖረዋል፡፡ ‹‹አባቶች››
    ስል እንዲሁ በደፈናው አይደለም-የእኛው አባቶች የመሰሉ
    አንዳንድ አባቶችን ማለቴ ነው፡፡ ይድረስ ብዬ መልእክቴን
    የጀመርኩት ለፓትርያርኩ ለአቡነ ማትያስ ስለሆነ የዚህ
    ጽሑፍ መዳረሻ አድራሻው እሳቸው ናቸው፡፡
    ‹‹በይድረስ አድራሻ ለፓትርያርክ የሚጽፍ ይኽ ደግሞ
    የማነው ደፋር!?›› ትሉኝ እንደሆነ እኔም ‹‹አዎን ሺህ ጊዜ
    ደፋር ነኝ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ሺህ ጊዜ ብቻ
    ያይደለ እልፍ አእላፍ ወትእልፊት ጊዜ ደፋር ነኝ›› እላለሁ፡፡
    ከዚያ ከአሕዛብ የእርኩሰት ሕይወት ወጥቼ የቅድስና
    ልጅነትን ባገኘሁባት በቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ስለሚያገባኝ
    አዎን ደፋር ነኝ እላለሁ፡፡ ዕለት ዕለት ንስሓ እየገባሁ
    የአምላኬን የመድኃኔዓለም ክርስቶስን ክቡር ሥጋና ደም
    በምቀበልባት በቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ አዎን ደፋር ነኝ
    እላለሁ፡፡ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስያቲያንን
    መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቃሉ ‹‹አካሌ›› ያላት ሲሆን
    ሐዋርያቱም ‹‹አካሉና ሙላቱ›› መሆኗን ነግረውናል፡፡ ኤፌ
    1፡23፡፡ የተለየ የወንጌል መልእክት ይዞ ይህችን
    የክርስቶስን አካል የሚያደማ (ሕጓንና ሥርዓቷን የሚጥስ)
    ካለ የሰማይ መልአክም ቢሆን እርጉም እንዲሆን
    ሐዋርያት በሕጋቸው አጽንተው የለ! ራሳቸው ሐዋርያትም
    እንኳ ቢሆኑ ፊት ካስተማሩት ትምህርትና ከሠሩት ሥርዓት
    የተለየ ትምህርትና ሥርዓት መልሰው ራሳቸው ሐዋርያቱ
    እንኳ ቢያመጡ እነርሱም ራሳቸው ርጉማን እንዲሆኑ
    በራሳቸው ላይ እርግማንን አውጀዋል፡፡ ገላ 1፡8፡፡ እውነት
    ነው የክርስቶስን አካል ከማድማት (የቅድስት ቤተ
    ክርስቲያንን ሕጓንና ሥርዓቷን ከመጣስ) ይልቅ በራስ ላይ
    እርግማንን ማወጅ የተሻለ ነው፡፡
    በእነዚያ ዓመታት ውስጥ ስንቱ ሕዝበ ክርስቲያን ነው
    ከክርስቶስ መንጋነት የተለየው? እንደ ሰደድ እሳት
    በተስፋፋ መልኩ ከ18 ሚሊዮን በላይ የሆነ ሕዝበ
    ክርስቲያን ነውኮ በ‹ኢየሱሴ› የስም ሽፋን አምላክ የለሽ
    የሆነው! እናንተዬ የድሮው ዘመን ሰማዕትነት ይሻል ነበርኮ!
    ድሮ ድሮ ‹‹ክርስቶስን አምላክ አትበል እርሱን አምላክ ነው
    ካልክ ግን ሰውነትህን ለእሳት አንገትህን ለሰይፍ›› ነበር
    የሚባለው፡፡ በዘመናችን ግን ስንቱ ነው በቃል ሰይፍ
    እየታረደ በተዘዋዋሪ መንገድ አምላኩን ያጣው? ስንት
    የገሃነም ደጅ የሆኑ የእምነት ድርጅቶች ናቸው
    የተመሠረቱልን? ከፍትሕ ሚኒስቴር ፍቃድ አግኝተው
    ሕጋዊ ሆነው የተመዘገቡ ከ350 በላይ የተለያዩ የእምነት
    ድርጅቶች በሀገራችን መኖራቸውን ራሱ ሚኒስቴር መሥሪያ
    ቤቱ ነግሮልና፡፡ ቅሉ መድኅን ዓለም ክርስቶስ አንድና አንድ
    ብቻ ቢሆንም ስንት ክርስቶሶች ናቸው የተፈበረኩልን?
    እንደማር የሚጣፍጠው ቃለ እግዚአብሔር 365ቱንም
    ቀናት በሚጎርፍባት ቅድስት ሀገር ላይ ይህን ሁሉ
    ምንፍቅና ያመጣባት ያ የዲዮቅልጥያኖስ አጋንንት
    አይደለምን? በቅድስት ቤተ ክርስተያን ያለነውንስ በዘርና
    በጎጥ እየከፋፈለ የጽድቅ ፍሬን ከምናፈራ ይልቅ
    በጠላትነት እንድንተያይ የሚያደርገን ያ የዲዮቅልጥያኖስ
    አጋንንት አይደለምን? ከላይ እስከ ታች ያሉትን አንዳንድ
    የቤተ ክርስቲያናችንን መሪዎቻችንስ እግዚአብሔርንና
    ቤቱን ከማገልገል ይልቅ ምድራዊ መንግስትን በማገልገል
    ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳ ተግባር እንዲፈጽሙ
    የሚያደርጋቸው ያ የዲዮቅልጥያኖስ አጋንንት አይደለምን?
    እኔ ግን አዎን በትክክልም እርሱ ነው እላለሁ፡፡
    በዘመናችን የነበሩ አንድ ታላቅ አባት ጵጵስና እንዲሾሙ
    ሰዎች ሲያግባቧቸው እኚያ ታላቅ አባት ሹመቱን
    ለመቃወም የተጠቀሙበት ቃል ‹‹ሹመት በአግባቡ
    ካልሠሩበት ሺህ ሞት ነው›› የሚል ነበር፡፡ እኔም
    ወደተነሣሁበት የይድረስ መልእክቴ ልመለስና ይህንኑ
    መልእክት ማስተላለፍ ፈለግኹ፡፡ ብፁዕ አባታችን አባ
    ማትያስ ሆይ ሹመትዎ ሺህ ሞት እንዳይሆንብዎ ስፈራሁ
    ነው ይህን መልእክት ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡ ምክንያቱም
    አባት ብቻ አይደለም ለልጁ የሚስያስበው ልጅም ለአባቱ
    ያስባልና ነው፡፡ ለምን ይህን እንዳልኩ በዝርዝር አንዳንድ
    ነጥቦችን ለማንሳት እሞክራለሁ፡፡ በቅርቡ መስከረም 27
    እና 29 እንዲሁም ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም በጠቅላይ
    ቤተ ክህነትና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ውስጥ
    በተካሄዱ ጉባዔያት ውስጥ ብፁዕነትዎ የመክፈቻ ንግግር
    ማድረግዎን አይተናል፣ ሰምተናል፣ አንብበናል፡፡ አሁንም
    በዚህ ሰዓት በቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ብዙ
    ደስ የማይሉ ነገሮችን እየተናገሩ መሆንዎን በአካል
    ካገኘኋቸው ከሁለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አንደበት
    ሰምቻለሁ፡፡ ስለዚህ የእርስዎ ዓላማ ምን እንደሆነ ሊገባኝ
    ስላልቻለ እስካሁንም ሲናገሯቸው የነበሩትን ነገሮች
    ለመመልከት ተገደድኩ፡፡ ብፁዕነትዎ እርስዎ እስካሁን
    ከተናገሯቸው ንግግሮች ውስጥ ‹‹የሚሰማኝ ስላጣሁ
    ከበታች የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ጋር መወያየት
    አስፈለገኝ››፤ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ
    ነው የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ሃብት ቀምቷል››፤ ‹‹ይህ
    ማኅበር በቁጥጥር ሥር እንዲውል አሳስባለሁ››፣ ‹‹ቤተ
    ክርስቲያን ከቅኝ ተገዥነት ትውጣ››፣ ‹‹እኔ ብቻዬን ሆኛለሁ
    እኔ ብቻዬን የምሠራው ነገር የለም፤ በዚኽ መግለጫ
    እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ››፣ ‹‹በህግና በሥርዓት
    የማይመራ ማኅበር አሸባሪ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው›› ‹‹አባ
    ማትያስ አላበደም፤ መልእክቴን እያስተላለፍኹ ነው
    ያለኹት፤ መልእክቴን በጸጋ ተቀበሉ ብዬ
    እማፀናችኋለኹ…›› በማለት ብፁዕነትዎ በተናገሯቸው
    ንግግሮችዎ ብዙዎቻችን ስንነጋገርባቸው ከርመናል፡፡
    በዚህ በፓትርያርኩ ንግግሮችና በያዙትም አቋም ምክንያት
    ማኅበረ ቅዱሳን ሊፈርስ መሆኑም ሲነገር ሰንብቷል፡፡
    ‹‹ፓትርያርኩኮ እንዲህ አሉ…››፣ ማኅበረ ቅዱሳንን
    ሊያፈርሱት ነው…›› እየተባለ ሲነገር ነበር፡፡ ይህንንም
    የሰሙ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በድንጋጤም ሆነ
    በንዴት ብዙ እንደጻፉ አንብቤያለሁ፡፡ እኔ ግን ማወቅ
    የፈለኩት ብፁዕነትዎ እርስዎ ለምን እንዲህ ሊሉ እንደቻሉ
    ሳይሆን ይህንን አቋም እንዴት ሊይዙ እንደቻሉና እንዲህስ
    ብለው እንዲናገሩ ያደረገዎት ምክንያት ምንድነው
    የሚለውን ነው፡፡ ግን ብፁዕነትዎ እርስዎና ከጎንዎ ያሉ
    ጆቢራ አማካሪዎችዎ በጋራ ሆናችሁ እናንተ
    እንዳሰባችሁት ማኅበሩን አፈረሳችሁት እንበልና እሺ ከዚያ
    በኋላ ምንድነው ማድረግ የፈለጋችሁት? እኔን አሁን
    ያሳሰበኝ ጉዳይ የማኅበሩ መፍረስ አለመፍረስ ጉዳይ
    ሳይሆን የዚህ ጥያቄዬ መልስ ነው፡፡ ሲጀመር ማኅበሩን
    ማፍረስም ፈጽሞ እንደማትችሉ ስለማውቅ ነው መፍረስ
    አለመፍረሱ አላሳሰበኝም ያልኩት፡፡ ግን ለቤተ ክርስቲያኒቷ
    ምን አስባችሁላት ነው በቅድሚያ ማኅበሩን ማፍረስ
    የፈለጋችሁት? ከማኅበሩ ቀጥሎስ የምታፈርሷቸው
    በየአጥቢያው ጠንካራ ድርሻ ያላቸውን ሰንበት ት/ቤቶችን
    ነው? ነው ወይስ እንዳለፈው ሁሉ የቅዱስ ሲኖዶሱንም
    ልዕልና በተጻረረ መልኩ በማን አለብኝነት እየተንቀሳቀሱ
    ቅዱስ ሲኖዶሱን ጥርስ የሌለው አንበሳ በማድረግ የቤተ
    ክርስቲያንን መከራዎች እንደገና ለሁለት ዐሥርት ዓመታት
    ሊያራዝሙልን ይሆን እንዴ? በመሠረቱ እኔ የማኅበሩ አባል
    አይደለሁም ነገር ግን ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር
    የሰጠውን፣ እየሰጠ ያለውንና የሚሰጠውን እጅግ ከፍተኛ
    አገልግሎት ጠንቅቄ ዐውቃለሁ፤ በተግባርም እየታየ ያለ
    እውነታ ነው፡፡ እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱንም ሐሰት ማለት
    ተገቢና ክርስቲያናዊም ግዴታ ነው፡፡
    ብፁዕነትዎ ሆይ የጥያቄዬን መልስ ከእርስዎ
    አልጠብቅም፡፡ ማኅበሩን ካፈረሳችሁ በኋላ ቅድስት ቤተ
    ክርስቲያንን ምን ልታደርጓት እንዳሰባችሁ ምላሹን እኔው
    እነግርዎታለሁ፡፡ እናም መልሴን እንዲህ ብዬ እጀምራለሁ፡-
    ብፁዕነትዎ ሆይ እርስዎንኮ በሥውር ሥራውን
    እንዲሠሩለት ገዥው መንግሥት ነው አምጥቶ በቤተ
    ክርስቲያናችን ላይ ያስቀመጠዎት እንጂ እውነተኛ
    አባትነትዎን አምናበት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
    አልሾመችዎትም፡፡ ይህንን ደግሞ ከማንም በላይ
    እግዚአብሔር ያውቀዋል፣ እርስዎም ጠንቅቀው
    ያውቁታል፣ በአቅማችን እኛም ዕናውቀዋለን፡፡ ይሄ
    ‹‹የ6ኛው የፓትርያርክ ምርጫ›› ምናምን እያላችሁ
    ሳትሸውዱን በፊት ገና መርጫው ከመካሄዱ ከሁለት ወር
    በፊት እርስዎ (አቡነ ማትያስ) 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው
    እንደሚሾሙ በእርግጠኝነት ዕናውቅ ነበር፡፡ ገዥው
    መንግሥት በ‹‹ከፋፍለህ ግዛው›› ፖለቲካዊ አስተሳሰብ
    የሚመራ ስለሆነ ቅድስት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
    ደግሞ ‹‹በፍጹም አንድነትና ፍቅር›› መኖርን
    ስለምንትሰብክ ለገዥው መንግሥት ቤተ ክርስያኒቷ
    ‹‹እንቅፋት›› እንደሆነችበትና ወደፊትም እንደምትሆንበት
    ገና በጫካ ውስጥ በትግል ላይ ሳለ ነው የተናገረው፡፡
    የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላትም ይህንን አምነዋል፡፡
    ገዥው መንግሥት በባሕርይው ከፋፍሎና ገነጣጥሎ
    መግዛትን እንደመርህ ስለሚከተል ‹‹እንቅፋት››
    የሆነችበትን ቤተ ክርስቲያንን በተዘዋዋሪ መንገድ
    በመቆጣጠር በእጁ ስለማድረጉ ፀሐይ የሞቀው አገር
    ያወቀው እውነት ነው፡፡ ‹‹እንቅፋት›› ደግሞ ከመንገድ
    መወገድ ስላለበት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎቷን
    ከማካሄድ ይልቅ በተዘዋዋሪ መንገድ ያላትን ነገር እያጣች
    እንደ ካሮት ሥር ቁልቁል እንድትጓዝ ተደርጋለች፡፡
    ለዘመናት በአንድነቷ ጸንታ የኖረችው ቅድስት ቤተ
    ክርስቲያን በካድሬዎች በኩል እንደራሴ ተደርገው
    በተሾሙት በ5ኛው ፓትርያርክ በአባ ጳውሎስ አማካኝነት
    ለሁለት ተከፍላ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በሚገኙ
    ምዕመናን መካከል ከፍተኛ ልዩነት በመፍጠር በአባቶችም
    መካከል ጥላቻና መወጋገዝ የመጣው ባለፉት 22
    ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ ፍጹም አንድነትንና ፍቅርን
    የምትሰብከውን ቤተክርስቲያን በዚህ መልኩ አንድነቷን
    እንድታጣና ልጆቿም በጠላትነት እንዲተያዩ በማድረግ
    አቅሟን አሳጧት፡፡ በእምነት ነጻነት ሰበብ መንጋዎቿን
    ከተቀደሰው ደጅ እያወጡ የገሃነም ደጅ የሆኑ የመናፍቃንን
    አዳራሽ እንዲሞሉ አደረጓቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ
    ያሉትንም በመከፋፈል በፍጹም የጥፋት ጎዳና ላይ
    እያስጓዙን መሆኑን ብዙዎቻችን ጠንቅቀን እናውቀዋለን፡፡
    ነገር ግን ሁሉም ነገር ረቂቅ በሆነ ሥልታዊ መንገድ
    እየተፈጸመ ስለሆነ አብዛኛው ምእመን ገና አልነቃም፡፡
    ሕግና ሥርዓቱን በመጣስ የቅዱስ ሲኖዶሱንም ልዕልና
    በመጻረር ብሎም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ዋና ሥራ
    አስኪያጅ ስልጣን በመጋፋት አባ ጳውሎስ በካድሬዎቻቸው
    እየተመሩ በማን አለብኝነት የወደዱትን ለመጥቀም ሲሉ
    አላግባብ በመሾምና በመሻር፣ በመቅጠር በማዛወር የቤተ
    ክርስቲያኒቱን ገንዘብ ለከፍተኛ ብክነት ሲዳርጉ እንደኖሩት
    ሁሉ እንዲሁም በብዙ መከራዎች ውስጥ አልፈው የቤተ
    ክርስቲያኒቱን ትምህርት ለተማሩት ተገቢ የሥራ መደብ
    ከመስጠት ይልቅ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደግል ድርጅት
    በመቁጠር በዘመድ አዝማድ ወይዘሮዎችና አቶዎች ወሳኝ
    የቤተ ክርስቲያኒቱን ቦታዎች እንዲይዙ በማድረግ ቤተ
    ክርስቲያንን ለከፍተኛ ምዝበራና ውርደት ብሎም
    ለተሃድሶዎች መናኸሪያ ያደረጓት አባ ጳውሎስ ቤተ
    ክርስቲያንን የማይነቀል ነቀርሳ ተክለውባት አለፉ፡፡ ቅድስት
    ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በ5ኛው ፓትርያርክ
    በአባ ጳውሎስ አማካኝነት ባለፉት 22 ዓመታት
    ያሳለፈቻቸውን በርካታ አሠቃቂ መከራዎች በግልጽ
    ይታወቃሉ፡፡ ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ ስእንደማያጣፍጥ
    ይታወቃል፡፡ ብፁዕነትዎ አባ ማትያስ ሆይ እርስዎም ወደ
    ፕትርክናው መንበር የመጡት በመንግሥት ካድሬዎች
    አጋዥነትና ግፊት የአባ ጳውሎስን ራእይ ለማስቀጠል
    መሆኑን እናውቃለን፡፡ አባ ጳውሎስም በሕይወት ሳሉ
    ‹‹ተተኪዬ›› በማለት ከካድሬዎች ጋር እንዳስተዋወቁዎትም
    እናውቃለን፡፡ ለዚያውም እርስዎም ከካደሬዎችና ከቤተ
    ክህነቱ ጆቢራዎች ጋር ተደራድረውና ተስማምተው ሹመቱን
    እንደተቀበሉት ያወቅነው ምርጫው ሳይካሄድ ከሁለት
    ወራት በፊት ነበር፡፡ ስለዚህ እርስዎ አሁን አያደረጉ ያሉትን
    ነገር ሁሉ ፓትርያርኩኮ እንዲህ… አሉ? ለምን እንዲህ
    አሉ? እንዴት እንዲህ ያደርጋሉ?… ምናምን እያልን ጉልጭ
    አልፋ በሆነ መልኩ በከንቱ መድከሙ ፋይዳ የለውም፡፡
    ምክንያቱም አባ ማትያስ እርስዎ እየፈጸሙ ያሉትና
    ወደፊትም የሚፈጽሙት የታዘዙትንና ቀድመው
    የተዋዋሉበትን ነገር ነው፡፡ አብዛኛው ሰው የሚያየው አሁን
    እርስዎ ማኅበሩን ስለማፍረስ የተናገሩትን ነገር ይሁን
    እንጂ አባ ማትያስ እርስዎኮ ከተሾሙ በኋላ
    የመጀመሪያውን የታሪክ ጠባሳዎትን በማኅበሩና በቤተ
    ክርስቲያን ላይ ያሳረፉት ባለፈው ዓመት ነበር፡፡ ባለፈው
    ዓመት በ2006 ዓ.ም ከ200 በላይ ለሚሆኑ ለሊቃውንቱ
    አብነት መምህራን ትልቅ ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ
    አዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም እርስዎ ግን በቀጭን ፊርማዎና
    በፌዴደራል ፖሊስ ማስፈራሪያነት ጉባኤውን ሲያግዱት
    ብዙዎቻችን በሀፍረት ተሸማቀን በግርምት እጃችንን
    በአፋችን ላይ ጭነን ነበር፡፡ በማኅበሩና በቤተ ክርስቲያን
    ላይ ያሳረፉትን የታሪክ ጠባሳዎትንም አንድ ብለን
    ቆጠርን፡፡ በወቅቱ በአባ ሰረቀ አቀናባሪነትና በፓትርያርኩ
    ቀጭን ትእዛዝና ፊርማ የታገደውን የጋራ የምክክር ጉባኤ
    የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ
    ማቴዎስ በፓትርያርኩ የተጻፈውን የእግድ ርምጃ
    አልተቀበሉትም ነበር፡፡
    የጉባኤውም አላማ በኹለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን ዕድገት
    ሊቃውንቱ የአብነት መምህራን ድርሻ ጎልቶ እንዲወጣ
    በማድረግ የአብነት መምህራንን የቀለብና የአልባሳት
    ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም ሊቃውንቱ መምህራን
    ከ300 ብር ያለፈ በቂ ደመወዝ ስለማይከፈላቸው ድጋፍ
    ለማድረግ ነበር፡፡
    ጉባኤያቸውን አጥፈው ለሀገር አቀፉ ስብሰባ ከሁሉም
    አህጉረ ስብከት የመጡ አካል ጉዳተኛና አቅመ ደካማ
    የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ምሰሶዎችና ዐይኖች የሆኑ
    ሊቃውንት በማኅበሩ ዋናው ማእከል ጽ/ቤት ለ3 ቀናት
    ተሰብስበው በመቆየት የተወያዩ ቢሆንም በኢትዮጵያ
    ስብሰባ ማዕከል ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ሳይገናኙና
    ሕዝቡም በረከታቸውን ሳያገኝ በመቅረቱ በእጅጉ
    ተቆጭተናል፡፡ ‹‹ጵጵስና መሾምን እንኳን አልፈልግም››
    ብለው በበዓታቸው ተወስነው ተማሪዎችን ብቻ
    በማስተማር ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ሌት ተቀን የሚተጉ
    ባለ ጸጋ አባቶች እዚህ እኛው ያለንበት ከተማ ድረስ
    መጥተው እነርሱን ሕዝቡ ሳያገኛቸውና በረከታቸውን
    ሳይቀበል በመቅረቱ ብዙዎቻችን በወቅቱ የጨጓራ
    በሽተኞችም ሆነን ነበር፡፡ በተጨማሪም የቤተ
    ክርስቲያናቸን ዐይን የሆኑትን ሊቃውነቶቻችን የዐይህን
    ችግር አለባቸው ይኸውም ከጤና አጠባበቅ ጋር በተገናኘ
    የተፈጠረ ችግር መሆኑ ስለሚታወቅ ማኅበረ ቅዱሳን
    ሊቃውንቱን የአብነት መምህራኑ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው
    ምሁራን፣ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ከዓለም
    ባንክ የወተር ኤይድ እና ከዩኒሴፍ ተወካዮች ጋር በግዮን
    ሆቴል ስለ ጤና አጠባበቅ ሀገር አቀፉ የምክክር ጉባኤ
    ሊያካሂድ ነበር የታሰበው፡፡ እነ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራንና
    ሌሎቹንም ከ200 በላይ የሆኑ ብርቅዬ የሀገራችንን
    ሊቃውንት የአብነት መምህራንን ስለ ህልውናችሁ
    አትወያዩ፣ ስለ ጉባኤያችሁ አትምከሩ፣ ልምዳችሁን
    አትለዋወጡ፣ በሁሉም የማስመስከሪያ ቤቶች ወጥ
    አሠራር አትዘርጉ፣ የቤተ ክርስቲያኒቷ ምሰሶዎች እናትነተ
    መሆናችሁን ዐውቆ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለአብነት ት/ቤቶች
    የበኩሉን አይርዳችሁ…. በማለት ሊቃውንቱን አትሰብሰቡ፣
    አትመካከሩ፣ ችግር አትፍቱ ብሎ ማገድ እምቢ ካላችሁ
    ግን ‹‹ለመንግሥት እነግርባችኋለ›› ብሎ መንግሥትን
    ማስፈራሪያ በማድረግ ዐይናቸው እንኳን ማየትም
    ለማይችሉ ሊቃውነት አባቶቻችን ጉዳኤያቸውን ከልክሎ
    በእነርሱም ላይ የግልባጭ ደብዳቤ ለፌዴራል ፖሊስና
    ለብሔራዊ ደህንነት መጻፍ ይሄ የሰይጣን ሥራ እንጂ
    ‹‹ቅዱስ›› ተብሎ ከሚጠራ ሰው የሚጠበቅ አልነበረም፡፡
    ጉባኤውም ባለመካሄዱ ምናልባት ሰይጣን ተጠቅሞ
    ይሆናል እንጂ የተጎዳችው ግን ቤተ ክርስያናችን ናት፡፡
    የማኅበሩ ጥናትና ምርምር ማዕከል ባለፈው ስለብራና
    መጻሕፍት አያያዝና መጻሕፍቱም እየተሰረቁ ከሀገር
    ስለሚወጡበት ሁኔታ እንዲሁም የመጻሕፍቱን ሕልውና
    በተመለከተ ምሁራንንና የሚመለከታቸውን አካላት
    በመጋበዝ የውይይት መርሀ ግብር አዘጋጅቶ የነበረ
    ቢሆንም አሁንም በፓትርያርኩ ቀጭን የእገዳ ደብዳቤ
    ምክንያት መርሀ ግብሩ ሳይካሄድ መቅረቱም የቅርብ ጊዜ
    ትዝታችን ነው፡፡
    ብፁዕነትዎ እርስዎ የቅርብ አማካሪዎችዎ ያደረጓቸውና
    በዙሪያዎ የሚያንዣብቡ በርካታ ጆቢራዎች እንዳሉ
    በግልጽ ይታወቃል፡፡ የቤተ ክርስያን የውስጥ ጠላቶች
    የሆኑ ‹‹የጨለማው ቡድን አባላት›› እንዲሁም ‹‹ከሙዳየ
    ምጽዋት ገልባጮች›› ተብለው በሚታወቁት በእነዚህን
    ጆቢራዎች ምክርና በመንግሥት ካድሬዎች ትእዛዝ
    አማካኝነት ነው ቅዱስ ሲኖዶሱ የማያውቀውን ሕገ ወጥ
    ስብስባ መስከረም 27 እና 29 ቀን 2007 ዓ.ም አድገው
    ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ ሲዶልቱ የሰነበቱት፡፡ ሕገ
    ወጦቹን ስብሰባዎች ያካሄዱት ቅዱስ ሲኖዶሱ ሳያውቀው
    ብቻም ሳይሆን መዋቅሩንም ባልጠበቀና ከሥርዓተ ቤተ
    ክርስቲያን ባፈነገጠ መልኩ መሆኑን የመንበረ ፓትርያርክ
    ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ
    አቡነ ማቴዎስ በግልጽ በሚዲያ ተናረዋል፡፡ ( አዲስ
    አድማስ፤ ቅፅ 13 ቁጥር 769፣ ጥቅምት 1 ቀን 2007
    ዓ.ም ) ስብሰባው በወቅቱ ‹‹የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ
    ቤተ ክህነቱን ወቅታዊ ኹኔታ የማይገልጽ፣ መዋቅሩን
    ያልጠበቀና ጽሕፈት ቤታቸው የማያውቀው›› መሆኑን
    በመግለጽ ዋና ሥራ አስኪያጁ በግልጽ ተቃውሞዎታል፡፡
    በወቅቱ አቡነ ማቴዎስ ‹‹መዋቅሩን ሳይከተሉና
    ከሚመለከተው አካል ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋራ ሳይመክሩ
    የሚሠሩት ሥራ ቤተ ክርስቲያኒቱን አደጋ ላይ የሚጥል
    ነው›› እያሉ ቢመክሩዎትም ብፁዕነትዎ እርስዎ ግን
    ‹‹የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት አስተዳዳሪዎችን››
    ሰብስበው እጅግ ዘግናኝና አፀያፊ የሆኑ የስድብ ቃላትን
    ጭምር ሲያደምጡ መዋልዎን ስንሰማ በሀፍረት
    አንገታችንን ደፋን፡፡
    ከምንም በላይ ደግሞ እነዚያ አፀያፊ የስድም ቃላት
    ለማኅበሩ ቅርብ ናቸው በተባሉና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል
    በሆኑ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችን ላይ የተነገሩ
    መሆናቸው የበለጠ ኅሊናን ያማል፡፡ በብልግና አፋቸው
    ከተሳደቡ አይቀር ማኅበሩን ብቻውን ቢሰድቡት ምን ነበረ!
    ግና እነዚህ ‹‹አስተዳዳሪዎች›› የተባሉ አካላትኮ እነማን
    እንደሆኑ በሥራቸው በግልጽ እናውቃቸዋለን፡፡ አንድ ወዳጄ
    እንዳለው እነዚህ አካላት በመንግስት ካድሬዎች ታዘው
    አይዞአችሁ የተባሉ ሲሆኑ በሥነ ምግባርም የዘቀጡ፣
    በሙስናና በስርቆት የደለቡ፣ ሙዳዬ ምጽዋት
    በመገልበጥና በልማት ስም የተሠሩ የአድባራቱን ሕንፃዎች
    እያከራዩ ኪሳቸውን የሞሉ፣ ባዶ እጃቸውን መጥተው ቤተ
    ክርስቲያኒቱን ዘርፈው ቪላ ቤትና መኪና ገዝተው
    ተንደላቀው የሚኖሩ፣ እነርሱ ውስኪ እየተራጩ
    በእውነተኞቹ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ላይ የሚያሾፉ፣
    በእነ ቅዱስ እንጦንስና በእነ ቅዱስ መቃርስ ቆብ
    የሚያላግጡ፣ እግዚአብሔርን የማያውቁ የእግዚአብሔር
    ሰዎች የሚመስሉ የውስጥ ጠላቶች ለመሆናቸው
    ሥራቸው ከበቂ በላይ ምስክር ነው፡፡
    እጅግ የሚገርመውና ኅሊናን የሚያደማው ነገር እነዚህ
    አካላት በቤተ ክርስቲያን ላይ እንደ መዥገር ተጣብው
    ገንዘቧን እንደ ደም በመምጠጥ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋዊ
    ጥቅማቸው ብቻ መጠቀማቸው ሳያንስ የቤተ ክርስቲያን
    መጎዳት የሚያስደስታቸው መሆኑ ነው፤ ማለትም
    የዶግማዋና የቀኖናዋ መፋለስ፣ በመናፍቃንና
    በተሐድሶዎች ዘመቻ ምክንያት የክርስቶስ መንጋ መበተን
    የሚያስደስታቸው መሆኑ ነው፡

    • a February 25, 2016 at 10:23 am Reply

      k.h. yasemalin.

  10. Anonymous February 10, 2016 at 8:55 pm Reply

    Amazing! i can call you Dr Semu but i can not call Kesis Semu. Let me tell dr. don’t you know the right and obligation of the Patriarch? for get about MK, he has a right to dismantle bishops and archbishops who are standing against the church. will see it soon. i am sure. you are now running but near future, will get your wage

  11. Anonymous February 11, 2016 at 7:19 am Reply

    Chigir kalm terto yemikota inji akurfo yemikemetna sera yemidolit abat ………………….?

  12. Anonymous February 11, 2016 at 8:57 am Reply

    ከቻላችሁ እንዳባትና ልጅ ሁኑ፤ መዘላለፉ ግን ማንንም ሊያስተምር አይችልም፤ ሁሉም የቻለውን ይሰራል፤ አርኣያነቱን ግን መልካም ሆኖ እና የተሻለ ሆኖ የሚያሳይ ፍጡር ያስፈልገናል፤ የትኛውንም ያህል አባት ቢያጠፋና ልጅ ለዘለፋ፣ ስድብና ድብድብ ቢነሳሳ በአባት የሚፈርድ የዚህ ዓለም ሰው ፈጽሞ አላየሁም፤ እይታው ከፍቅር ስለሚሆን፤ እናም ደም እንባ ማልቀስ፣ መጮህ፣ ብዙ ሆኖ መሰለፍ ወይም ሃምሳ መቶ ገጽ ደብዳቤ መፃፍ የትክክለኛነት ምልክት አይሆንም ፤ ምናልባትም በመሰረቱ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በሐዋርያት፣ በጻድቃን፣ በሰማዕታት ምሳሌነት እና በእምነታችን አስተምህሮ ቢታይ ፍሬው ምን ያህል እንደሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ምናልባትም የአባትና ልጅ መዘላለፍና መሰዳደብ ለጎረቤት ቡና መጠጫ እና ልብወለዳዊ መዝናኛ ከመሆን በስተቀር፡፡ ስለዚህ የፓትርያርኩም ሆናችሁ የማህበር ተወካዮችና አዋቂ ነን ባዮች እባካችሁ የተለያየ የፖለቲካ አመለካት ይዘው የሚኖሩባትን አገር አንድ አይነት እምነት አለን በሚባሉ ተከታዮች በምታሳዩት ግብረገብነት የጎደለው ስድድባችሁ እኔንና መሰል ደካሞችን ለፈተና አትጣዱን፤ ምዕመኑንም ለመከፋፈል የሰይጣን አጋር ባትሆኑ እጅግ ደስታየ የበዛ ነው፡፡

  13. Anonymous February 12, 2016 at 1:22 pm Reply

    enkuan zare tilaninam alifoal enes geremegn bemebirhan lemin eyegebu ayayutim lebetechirtian bicha sayhon almawi sirayen bikininet endisera yadera meskel yaserelgn mk new

  14. Anonymous February 20, 2016 at 7:34 pm Reply

    Amlakachin hoy yabatochachinin Yne Abune Gorgoriosn Zemenina agelglot amitaln!!!

  15. May 15, 2018 at 6:44 am Reply

    የማህበረ ቅዱሳን ኣባል ለመሆን ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርስቲ የተማረ መሆን ኣለበት የሚለውን ኣልስማማበትንኝም. በኣንድ ቦታ የማህበረ ቅዱሳን ስብሰባ ተገኝቼ የማህበሩን ኣባል ለመሆን ስጠይቅ የኮሌጅ ተማሪ ወይም ተመርቆ ስራ የያዘ መሆን ኣለበት የሚል መልስ ተሰጠኝ… የተማረው ሀይል ለምንድነው ያስፈለገው? ቤተክርስትያንን ጠብቀው ያቆይሉን የኣለማው ትምህርት ተምረው ነው ወይ? የሚቀጥለው የማህበሩ ደንብ ማሻሻያ ማህበሩ በፓለቲካ ጉዳይ መግባት ይችላል የሚል ይሆናል? ዋናው ኣላማስ ሊቀየር ይችላል ወይ? እንዴት ነው ይህ ነገር

Leave a reply to Anonymous Cancel reply