ማኅበረ ቅዱሳን: የኦርቶዶክሳዊነትን ዓለም አቀፋዊነትና በቤተ ክርስቲያን የምእመናንን ድርሻ የሚያስገነዝብ ዐውደ ርእይ ያዘጋጃል

 • ከመቶ ሺሕ በላይ ተመልካቾች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል
 • ኦርቶዶክሳዊ ክውን ጥበባት ልዩ ገጽታዎቹ ይኾናሉ ተብሏል
 • ለአጠቃላይ ዝግጅቱ ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረጋል
 • የዐውደ ርእዩ መሪ ቃልና መለዮ ዛሬ በማዕከሉ ጽ/ቤት ይፋ ይኾናል  

  *               *               *

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፴፰፤ ቅዳሜ፤ ጥር ፳፰ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

logo2
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን፥ የቤተ ክርስቲያንን ዓለም አቀፋዊነት፣ ነባራዊ ኹኔታ እና ተግዳሮቶች ተረድተው የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የሚያስገነዝብ ልዩ ዐውደ ርእይ በመጪው መጋቢት ወር አጋማሽ እንደሚያካሒድ ማኅበረ ቅዱሳን አስታወቀ፡፡

ማኅበሩ፣ ከመጋቢት 15 – 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚያካሒደው ዐውደ ርእይ፣ ለአምስተኛ ጊዜ የሚያዘጋጀው ሲኾን፣ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን: አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ!!” የሚል መርሕ እንዳለው የዝግጅቱ ዐቢይ ኮሚቴ ገልጧል፡፡

በዘንድሮው ዐውደ ርእይ፥ ቤተ ክርስቲያን በአደረጃጀቷ የካህናትና የምእመናን ኅብረት መኾኗን በማስገንዘብ ምእመናን ድርሻቸውን ዐውቀው ሓላፊነታቸውን የሚወጡበትን መንገድ የሚያሳዩ፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የአንድ አካባቢ ወይም ጎሳ ብቻ ሳትኾን በባሕርይዋ ዓለም አቀፋዊት(ኵላዊት) እና አንዲት መኾኗን የሚያስረዱ በአራት ሰፋፊ አርእስተ ጉዳዮች የተከፈሉ ትዕይንቶች፣ ዘመኑ በደረሰበት የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመታገዝ እንደሚቀርቡ ተጠቅሷል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን ማንነትና ከሌሎች የምትለይበትን የመሠረተ እምነት/ነገረ ድኅነት/ አስተምህሮ፤ በዓለም፣ በአፍሪቃ እና በኢትዮጵያ የምታከናውነውን ሐዋርያዊ ተልእኮ፤ ወቅታዊ ተግዳሮቶቿንና መፍትሔውን በመለየት፣ ኹሉንም ጉዳይ ለመዋቅሩና ለጥቂት አካላት ብቻ ከመስጠት ይልቅ ምን መደረግ እንዳለበትና ከምእመናን ምን እንደሚጠበቅ በስፋትና በዝርዝር ከተካተቱበት ዐውደ ርእይ ጎን ለጎን፣ ጭብጦቹ በጥናታዊ ጽሑፍ የሚዳሰሱበት ዐውደ ጉባኤ እንደሚካሔድም ታውቋል፡፡

ዐውደ ርእዩ ለእይታ ክፍት ኾኖ በሚቆይባቸው ሰባት ቀናት፣ የቤተ ክርስቲያንን የጥንታዊ ሥርዐተ ትምህርት የመማር ማስተማር ሒደት በደቀ መዛሙርቱና በመምህራኑ እንቅስቃሴ በተጨባጭ የሚታይበት የአብነት ት/ቤቶች መንደር” የሚገነባ ሲኾን፤ በየዕለቱ ከ10 ሰዓት በኋላም ያሬዳዊ ዜማ እና ቅኔ ከትውፊታዊ ዕሴቶቻቸው ጋር የሚቀርቡበት የመድረክ መሰናዶ እንደሚኖር ተገልጧል፡፡ ኮሚቴው፣ “ኦርቶዶክሳዊ ክውን ጥበባት” /performance arts/ ሲል የገለጻቸው መሰናዶዎቹ፥ የጥበባቱን ሕያውነት፣ ሥነ ውበት፣ ገቢራዊነት እና አሳታፊነት በማስገንዘብ ተመልካቾችን ለዕውቀት በማነሣሣት ረገድ ጉልሕ ድርሻ ይኖራቸዋል፤ ብሏል፡፡

ለዐውደ ርእዩና ተጓዳኝ መሰናዶዎች አስፈላጊው ፈቃድና የድጋፍ ደብዳቤ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጽ/ቤት ተገኝቶ ከኤግዚቢሽን ማእከሉ ጋር በኅዳር ወር ሙሉ ስምምነት መፈጸሙን ዐቢይ ኮሚቴው ገልጦ፤ ከአንድ ሺሕ አባላቱ በዝግጅት፣ በቅስቀሳና በቴክኒክ ምድቦች ተከፋፍለው ቅድመ ዝግጅታቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉና በሒደትም የሰንበት ት/ቤቶችን፣ የሠራተኛ ጉባኤያትንና ሌሎች መንፈሳውያን ማኅበራትን በአጋርነት በመያዝ እንደሚቀጥል ተጠቅሷል፡፡

ለአጠቃላይ ዝግጅቱ ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተያዘለት ሲኾን፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ተቋማት ጨምሮ የተለያዩ አጋር አካላት ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን ለማኅበራዊ ግብይት በማቅረብ እንደሚያስተዋውቁበት ተመልክቷል፡፡

M k
ከመክፈቻው ዕለት ጀምሮ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽቱ 12፡00 ለእይታ ክፍት የሚኾነው ዐውደ ርእዩ፣ ከመቶ ሺሕ በላይ ተመልካቾች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል፤ የመግቢያ ትኬቶች ሽያጭ ካለፈው ታኅሣሥ ወር ጀምሮ በማኅበሩ ሱቆችና በሌሎችም ቦታዎች በመካሔድ ላይ መኾኑን የገለጸው ዐቢይ ኮሚቴው፣ ዓላማውን የሚደግፉ አካላት አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ፣ ሕዝበ ክርስቲያኑም ወዳጅ ዘመዶችን በመጋበዝ ስለ ቤተ ክርስቲያን እንዲያውቅና እንዲያሳውቀው ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በቤተ ክርስቲያንና በምእመኑ መካከል ያለውን መስተጋብር ለማዳበር፣ ማኅበሩ ከ1989 ዓ.ም. ጀምሮ ከዘረጋቸውና በስፋት ከተገበራቸው ሰፊ የማስተማርያና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሮች መካከል ዐውደ ርእይ አንዱ መኾኑን ያስረዳው ዐቢይ ኮሚቴው፤ ያለፉት አራት ዙር ዝግጅቶች፥ ለቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ ታሪክ፣ የቅርስ ባለቤትነትና ባለአደራነት፤ በአካባቢ ጥበቃ፣ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ለሀገሪቱ ዕድገት ላበረከተችው አስተዋፅኦ ሰፊ ሽፋን የሰጡ እንደነበሩ አስታውሷል፡፡

Advertisements

17 thoughts on “ማኅበረ ቅዱሳን: የኦርቶዶክሳዊነትን ዓለም አቀፋዊነትና በቤተ ክርስቲያን የምእመናንን ድርሻ የሚያስገነዝብ ዐውደ ርእይ ያዘጋጃል

 1. mulugeta ayana February 6, 2016 at 11:27 am Reply

  waw this is good idea

 2. Anonymous February 6, 2016 at 12:07 pm Reply

  Amlak hoy ante teradan

 3. Anonymous February 6, 2016 at 2:54 pm Reply

  Wow it is so amazing news we are waiting the day …….

 4. Anonymous February 6, 2016 at 4:21 pm Reply

  አገልግሎታችሁን እግዚአብሔር ይባርክላችሁ ባለን አቅም የቤተክርስቲያናችንን እናገልግል

 5. Tsegaye bekele February 6, 2016 at 5:01 pm Reply

  እግዚአብሔር አምላክ በአገልግሉታቹ ሁሉ ከፊት ይቅደምላቹ!!!

 6. abate February 7, 2016 at 10:13 am Reply

  ከማህበረ ቅዱሳን እጃችሁን እንሱ

  መልካምን በመስራት የተከሰሱት ፣ የተወገዙት ብኖሩ ማህበረ ቅዱሳን ናቸው።
  ለምን ተከሰሱ?
  በቁማቸው ሃውልት አሠሩ?
  ለስልጣናችዉ ስሉ ቀኖና ቤተ ከርስቲያንን ሻሩ?

  አልያም ታባተ ህጉ ፍት ልፍት ሰውን በሽጉጥ ገደሉ?

  ወይስ
  ዋልዲባን የአባቶቻቸውን እምናትና እርስት ሸጡ?

  ወይስ
  ስልጣነ ክህነትን በገንዘብ ቸበቸቡ?
  ወይስ
  ሰውን በዘር እና በጒሳ ከፋፈ?
  ወይስ በመቅደስ ውስጥ ታጣቂ ኮማንዶ ይዘው ገቡ?
  ይህ ሁሉ የማህበረ ቅዱሳን ከሳሾች ወይም የማህበረ ቅዱሳን ከሳሾች ድርግት እና ገፅ ባሕርያት ነው።
  ልጆቹን የምረግም እና የሚከስ የ8ኛ ሺህ ” እበት ” ያውም የቤተክርስቲያን

  ተራ ዱርዩ እንድ ቀን ቤተ ከርስቲያን ደጅ ረግጦ የማያውቅ ሰው የማይናገር ንግግር
  እክራር ሀገርን እና መንግስትን የሚያ ሰጉ፣

  የቤተክርስቲያን ቅኝ ግዛት ተይዛልች
  እስከ እለተ ሞቴ አልተዋቸውም ፤ አለቃቸውም
  እንዴት ይባላል?
  የቤተ ከርስቲያን ህግ መጣስ በእውነት ካንገበግባችው ለምን
  ለቤተክርስቲያን አንድነት መስዋዕት አልሆኑም?
  በእነሱ ለዓለም ክብር ስራኮቱ ቤተ ከርስቲያን
  ለ2 ት ከዝያም ለ3 ከዝያ አልፎ ለ5 ስትከፋል ምንም እልተሰማቸው?
  ምዕመናን በአባቶች ህገ ቤተ ክርስቲያን ማፍረስ ፣ቀኖናዋ፣ሥርዓቷ መናድ ምክንያት ፦ የውጭው ስኖዶስ ተከታይ፣ የወያኔ ስኖዶስ ተከታይ፣ ሁለቱንም ያልተከተለ የራሱን ስሜት የተከተለ ገልተኛ ፣እርቴዶክሳዊነቱን ጠብቆ ከሶስቱ ያልሄ ዝህም አልፎ በእናንተው ምክንይት የተነሳ ከአባቱ ከእግዝእብሔር ቤት አማራችሁ አስወጥታችሁ በመናፍቃን ያስነጠቃችሁ፤ በጎቻችሁን ለጅብ እና ተኩላ ዩዳረጋችሁ ?

  ምን ይሰማችኋ?
  በናንተው ብሶ የበተናችሁትን
  በጎች የምሰበስብ
  ለበጎቻችሁ ምግብ፣ ውሃን የምሰጥ
  በጎቹን ከአውሬ የምጠብቅ መልካም የልጅ
  ይመሰገናል እንጅ የት ሃገር ነው የምረገመው?
  ” “አሸባር የምባልው?
  እምናቱን ያፀና እርስቱን የጠበቅ ትውፍቱን፤ ቤተ ከርስቲያንን ያነፀ ፣ያሳነፅ እንዴት ቤተክርቲያንን ቀኝ ገዥናት ይዘዋል የምባሉት?
  እንግዳውስ እውነቱን መናገር ከተፈለገ ፣ እንደ ወራርዉ የእጣልያን ቀኝ ገዥ 8000 የደብረ ልባኖስን እንደ ገዳሉ ንብረት እንደ ዘረፉ ፦
  እንግዳውስ
  ቤተ ከርስቲያን ከነ ምዕመኗ ስት ቃጠል ዝም ያሉ፣
  አባቶች በታቦተ ህጉ ፍት ለፍት በጥይት ስገዳሉ ዝም ያሉ፣
  ገዳማት ስቃጠል ምንም ያልገዳችው፣
  በገዳማት አባቶች መነኲሳት ስገዳሉ እና ስሰደዱ ዝም ብሎ ማዩት፣
  የገዳማት ንብረታቸውን ስዘረፍ መሬታቸው ስቀማ፣ የአበው ቅዱሳን አባቶች እፅም ተቆፍረው ተጥለው በመቃብረቸው ላይ ሸንኮራ አገዳ ሥዘራ ዝም ንሎ ማዩት፣
  ዓይናቸው በጎሳና በጎጥ ተሸፍኖ ክርስቶስን ማየት ተስኖአቸው ከቤተ መቅደስ ሰውን በጎሳ ለይተው እንተ የዝህ ጎሳ ስለሆንክ እዝህ መሆን አትችልም ያሉ
  የቤተክርስቲያን መርዎች፣
  ከክርስቶስ ፍቅር ይበልጥ ስኳር የጣማቸው
  አባቶች ፣
  ለአንድ እፍታ ቁሙ እስቡ
  ለእግዚአብሔር ብላችሁ እርስ በርስ ተጣላችሁ?
  በእውኑ ለእግዚአብሔር ብላችሁ እርስ በራሳችሁ ተወጋገዛችሁ?
  ሁላችሁ እኮ የተወገዛችሁ ናችሁ
  ክርስቶስ እኮ ጣላታችሁን ውደዱ

  (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5)
  ———-
  44-45፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።

  46፤ የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?

  እግዚአብሔር እንድህ ይላል
  ከማን ተምራችሁ ነው ?
  በእውነት ለእግዚአብሔር እስባችሁ ነው የተወጋገዛችሁ፣ ከአንድ ወደ 5 ምዕመንን የከፋፈላችሁ?

  ለቀስስ መላኩ እና መሳዩቹ
  ፅሁፍዎትን አንብባለሁ ፣ እንደተረዳሁትም ካህን ኖት
  ካህን እግዚአብሔር የሾመው ዳኛ ነው ፤ ይህ በእግዚአብሔር የተሾመ ድኛ ደግሞ መናገር ፣ መመስክርም ያለበት እውነትን ነው። ማንም ብሆን ማን ውሸትን እናገር ዘንድ ቅዱስ መፀሐፋችን አይፍቅድም፣ እውነትን እውነት ሃሰትን ሃሰት በል እንጅ ይላል ለዝህ ነው፣ እውነተኛ አባቶቻችን ማንንም ሣይፈሩ እውንትን ተናግረው፣ እውነትን መስክረው እናንት ካህናት እውነትን ትመሰክሩ ዘንድ ፣ ሀግር ስትፍርስ ለአንድነት ትሟገቱ ዘንድ፣ ደሃ ስብደል ፣ ያለአግባብ ስፈረድብት ያለኣግባብ ተፈርዶበታ ብላችሁ ፍርደገምድሉን ትገስፁ ዘንድ ፣ ድሃን ትፅናኑ ዝንድ፣ ከተገፋው ፣ ጒን ትቆሙ ዝንድ ነበር እንደ መጥምቀ መለኮትን ቅዱስ ዮሐንስ ፣ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ እፈወርቅ እንድ እዉነተኛ እባቶች።
  እናንተ ግን እውነተኛውን የክርስቶስን መስቀል። ይዛችህ እውነት መናገር ተሳናችሁ ቤተ እግዚአብሔር በፅላቱ ፍት አባቶች ስገደሉ ዝምታ መረጣችሁ ከመገሰፅ አሞገሳችሁ፣ የቤተክርስቲያን ቀኖና ስናድ ምንም አልገዳችሁም፤ አባቶቻችን ያቆዩልንን ዶጉማና ህገ የቤተክርስቲያን ለግል ጥቅም ለጉሳ ፖለቲካ አፋረሳችሁ ፣ የእግዚአብሔርን ቀን ከሚጠባበቁ ጥቅት አባቶች በስተቅር ሁላችሁም ከቀያፋ ጋር ተባበራችሁ ፣ እነሱ ክርስቶስን ሰቀሉት ገደሉትም እናንት ዳግሞ እውነትን ሰቀላችኋት፣ ገደላችኋትም።ዱሮ እውነት የሚመነጨው ከቤተክርስቲያን ፣ ከቤተ እግዚእብሔር፣ ከክርስቶስ ሃዋሪያ ነበር ዛሬ እናንተ በእነርሱ እግር ተተክታችሁ፣ ቤተ ከርስቲያን ከዓለማዊው ይልቅ ዘረኝንት የምፋልቅበት፤ የክርስቶስ ፍቅር የማይነገርበት ፤ ስልጣነ ክህነት እንደ ዕቃ በገንዘብ የምሸጥብት የግያዝ ን ዓላማ የምተተገብሩ መሆናቸሁ ።ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን ፈራችሁ ንፀሃን ስገደሉ ፣ያለፍርድ ስገረፉ ስታሰሩ እናንት ከቀያፋና ከጵላጦስ ጋር መሆንን መረጣችሁ ፣ ግብረ ሰዶም በኢትዮጵያው ስነገር አፍ ኣውታችሁ መናገር ፤ መገሰፅ ተሳናችሁ፤ ከእግዚአብሔር ህግ ይልቅ የሰልባጅ እርዳታ መርጣችሁ ዝምታን መረጣችሁ ትጠብቁ ዝንድ የተሰጣዥሁን በጉቻችሁን ለተኩላ ሰጥታችሁ የግል ክብርን እና ድሎትን መረጣችሁ ፣ የእንድ በግ መጥፋት ምንም እልመሰላችሁም ፣ በጒቻችሁን ጥላችሁ በጒቹን ክሚበላ ተኩላ ጋር ተሰላፋችሁ።
  አረ ዋልድባ ስታረስ ፣ አባቶቻችን በግፍ እተኙብት ቦታ ስታረዱ ፤ስገረፍ፣ ስታሰሩ ፣ በቤተ እግዚአብሔር ይህን ጎሳ አንፍልግም በዝህ ገዳም ይውጡ ስባሉ
  ዪት ነበራችሁ? ምእመናን ፣ ካህናት አባቶች ከነ ታቦተ ህጉ በእሳት ስጋዩ የት ነበራችሁ?
  ” ማማለጃን አትቀበል፤ ማማለጃ የዓይናማዎችን ሰዎች ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።”
  (ኦሪት ዘጸአት 23:8)
  የምትል ቤተክርስቲያን ዛሬ መርዎቿ እና ግብረ አበሮቻቸው 4000 የኢትዮጵያ ደሞዝ ይዘው የ10 እና የ20,000,000 ድርጅት የምከፋቱት ቤተክርስቲያን በመዝረፍና በጉቦ ነው
  ምስክር ይሁነን ዝንድ
  Goole the top richest person in Ethiopia ብታዩ 9ኛ ሰው ዘረኛ የቤተክርስቲያን አፍራሽ ይሁዳው አቡነ ጳውሉስ ናቸው።
  እናንተ እባት የተባላችሁ የቤተክርስቲያንን ስትፍርስ ዝም ብላችሁ ስታዩ እግዚአብሔር አምላክ ህፃናትን አነስነሳ ፣ እናንተ የቀበራችሁትን መክልት ሰጣቸው እንሱ ወጣቶች ሆነው እንደ እናንት ፍቅረ ንዋይ ሣይበግራችው የአፍላነ ወጣትነት ሳያሸንፍልቸው ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እናንተ የጣልችሁትን የረሳችሁትን የሸጣችሁትን ፣ በዘረኝነት የባታተናችሁንትን ቤተ እግዚአብሔር ፣ እራሱ የክብር ባለቤት ፣ህያው እግዚአብሔር ማህበረ ቅዱሳን አስነሳ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከሀገር ቤት እስከ ውጭው ዓለም ወንጌልን አስፋፉ ፣ ምዕመንን እገኙ ፣ ሰውን እምነቱን እንድ አውቅ አበቁት ፤ ቤተክርስትያንን አሰሩ፣ ገዳማትን አስተዋወቁ የፈረሱ እብያተ በክርስቲያኖች ጠገኑ የአብነት ት/ቶችን አስፋፍ የካህናት ቁጥር እና የዲያቆናት ጨመረ ፣ጠፍተው የነበሩት እን እምነታቸው አላልተው የነበሩት እምነታቸውን አጠነከሩ እምነቱ ትስፋፋ። በእግራቸው እስክ ጠረፍቷ የሀራችን ተዘው ወንጌልን ሰበኩ ፣ ክርስትናን አስፋፉ ፤ቤተ ክርስእቲያንን እስፋፉ ፣ ከክሳቸው እና እንደ እነሱ ለቤተ ለክርስቲያን ቀናዕ የሆኑትን እባቶችን ፣ምዕመንን ጋራ በመሆን የዝች ቤተ ክርስቲያን ፦ስርዓቷ፣ እንዳይፍርስ ትፍዊቷ፣ ለዘልዓለም ለልጅልጅ እንድተላላፍ ፣ ዘረኝማት እና ጉበኝንት እድቀር ፣ ህገ ቤተ ክርስቲያን እንድጠብቅ፣ ማንነቷ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ተኩላዎች ለመጠበቅ መስራታቸው የሚያስመሰግን እንጅ የሚይስረግም አልይም ።
  ይህ የሰይጠን ክስ ነው፣ ሌላ ሊሆን አይቻልም፣ ቤተ ከርስቲያን አስፋፋህ፤ እምነትን እስፋፋ፣ ገዳማትን ጠገንክ፣ ቤተ ከርስቲያንን ስሠራህ ፤ ምዕመን እምነታቸውን አወቁ፣ አጠበቁ ፣ ወደ ንሰሃ መጡ ስባል የሚከፋውጥንተ ጠላታችን ሰይጠን ብቻ ነው።
  አዎ አንድ እምነት ያለለው ጊዜ የሾመው ይሁዳ
  እንድህ ብሎ ነበር
  “ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እና አማራን አንግት እስደፍተናል” ነበር ያሉት ።
  ቤተ እግዚአብሔር ማንም አያጠፋትም ፣መሠረቷም ፣ ግንቧም ጉልላቷም ክርስቶስ ነው፣ አትነቃነቅም ፣ ስልዝህ ጠላት ሆይ ደስ አይበልህ !
  እግዚአብሔር ሰው አለው በአባቶቻቸው ፋንታ ልጆቹን አስነስቷልና
  እግዚአብሔር ተዋህዶ እምነታችንን
  ኢትዬጵያን ሃገራንን
  ይጠብቅልን
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር
  ወለ ወላዲቱ ድንግል
  ወለ መስቀሉ ክቡር

  • anonymously February 7, 2016 at 3:26 pm Reply

   Abate kalehiwot yasemalin !!! Eskezare yetneberik? “aba” serekena hamawoch seif lay komewal!!!?

 7. Belay February 7, 2016 at 4:28 pm Reply

  አገልግሎታችሁን እግዚአብሔር ይባርክላችሁ ባለን አቅም የቤተክርስቲያናችንን እናገልግል!!

 8. Anonymous February 7, 2016 at 9:36 pm Reply

  Mk you must to have a permeation from the church first before doing this, otherwise it will be stopped. watch out and be carefully and abide by the church

 9. Anonymous February 8, 2016 at 7:02 am Reply

  Ensu yekesesu enanet degemo bqal Egeziabeher nefsachenenn xaesu

 10. Anonymous February 8, 2016 at 7:34 am Reply

  የኮሌጆችንና የፓትርያርኩን ጨረሳችሁና ደግሞ ወደ መዋቅሩ ዞራችሁ፡፡ እድሜ ለ1965 ዓ.ም በአቡነ ቴዎፍሎስ አርቆ አሳቢነት በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ጸድቆ የወጣ ቃለዓዋዲ ይሑንና በእያንዳንዱ አጥቢያ ምዕመን፣ካሕን፣የሰ/ት/ቤት ወጣት ወሳኝ ተሳትፎ የሚያደርግበት የሰበካ ጉባኤ አደረጃጀት አለ፡፡ እርግጥ ማኅበረ ቅዱሳን በአጥቢያ ደረጃ አደረጃጀት ስለሌለው ችላ ብሎት ይሆናል፡፡ እሱ ችላ ስላለውና በአጥቢያ ደረጃ እንዲደራጅ ፈቃድ ስለሌለው ምዕመኑ እንደተገፋ አድርጎ ጩኸት ቀምቶ ለመጮኽ መሞከር ‹‹እኛ ያልወጠወጥነው…›› አባዜ ነው፡፡

  ኤግዚቢሽን መደረጉ ጥፋት የለውም፡፡ኤግዚቢሽኑ የሚደረገው እኛ እንዲህ ነን፤ቤተክሕነቱ ግን አይረባም፣ምዕመናንን የያዝነው እኛ እኛ ብቻ ነው አይነት ልክ መምሪያው ሁሉ በማኅበረቅዱሳን ቡራኬ እንደቆመ፣ከ40ሺህ በላይ የሚገመቱ የቤተክርስቲያን አጥቢያዎች በማኅበረቅዱሳን ዓስራትና ብፅዐት እንደሚኖሩ፣ከ500ሺህ በላይ የሚገመተው ካሕንና መምህር ደሞዝ ከፋይ ማኅበረቅዱሳን እንደሆነ፣ፓትርያርኩን ሲያይ በአክብሮት የሚሳለምና የሚዘምር ሁሉ የማኅበረቅዱሳን አባል ብቻ እንደሆነ፣ካለ ማኅበረቅዱሳን ተሐድሶን የሚዋጋ የቤተክርስቲያን ሰው እንደሌለ፣ወዘተ በማስመሰል ራሳን እያሻሻጡ ቤተክርስቲያኗን ከነመዋቅሯ አክሎና መስሎ ለመታየት ከሆነ ግን የሚካሄደው ሩጫ ስክነት ይታከልበት፡፡

  ድሮ በትሩፋቱ ብቻ የሚታወቀው ማኅበር ዛሬ የአሉባልታና የመመጻደቅ አብነት እየሆነ ነው፡፡ራሳችሁ ከሳሽ፣ምስክር፣ዳኛ እየሆናችሁ ጽድቅ ጽድቁን ለራሳችሁ፣አበሳውን ሁሉ ጠቅልሎ ለቤተክሕነትና በመንበሩ ላሉ አበው የማሸከም ጉዞ ትክክል አይደለም፡፡ማኅበረቅዱሳን ከቤተክሕነት ተገኘ እንጂ ቤተክሕነት ከማኅበረቅዱሳን አልተገኘም፡፡በአንድ በኩል የቤተክሕነቱን መዋቅር መጠለያ አድርጎ በሌላ በኩል ደግሞ ያንኑ እውቅና ሰጥቶ ያስጠለለ መዋቅር መውቀር ያቃቅራል፡፡በቲፎዞ ጫጫታና በውዳሴ ከንቱ ሰክራችሁ ስስ ነጠላችሁ በኖ እስኪድ እየታበያችሁ ነው፡፡ማኅበራዊ ሚዲያውንና ጋዜጦችን በሞኖፖል ተቆጣጥሮ እኔ ብቻ ጻድቅ ይሉት መመጻደቅ ዋጋ ያሥከፍላል፡፡ኮሌጆችንም፣መዋቅሩንም፣ፓትርያርኩንም ስም እየሰጣችሁ ለተቀረው ዓለም ዓለምአቀፋዊነታችንን እናሳያለን ማለት ስላቅ ነው፤ቢሳካ እንኳ የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ የሚያስተርትባችሁ ነው፡፡ነገሮችን ሁሉ ከተሐድሶ ጋር እያያዙ ወግ ከመሰለቅ ተሐድሶውን በእውቀት፣አመራሩን በመመካከር ለመፍታት ጥረት ይደረግ፡፡ጉድለቶችን ሁሉ በተሐድሶ ጠቅልሎ ራስን ለመሸጥ በየሚዲያው መሰየም ትርፉ ውሃ ወቀጣ ነው፡፡ምሁራን ነን ካላችሁ ያልተማረ የምትሉትን ቤተክሕነት ደካማ ጎኑን አውቃችሁ በጥንቃቄ የሚስተካከልበት መነገድ መፈለግ ነው፡፡መማር ለመታበይና ለቲፎዞ ጫጫታ ብቻ ከሆነ ግን ቀስ በቀስ ወደ ማኅበር አምላኪነት መውረዳችሁን እወቁት፡፡

  አሁን ነገረ ሥራችሁ ሁሉ የማኅበር አምልኮ ቅርጽ እየያዘ ነው፡፡የቤ.ክ መለኪያ ለማኅበረቅዱሳን የምታሳየው ፊት ሆኗል፡፡ማኅበረቅዱሳንን ከገሰጸች ልተፈርስ ነው እንባላለን፤ሲበረታታ ደግሞ ያበረታቱት አበው ሰማያውን አበው የሆኑ ያህል በውዳሱ ከንቱ ይንበሸበሻሉ፡፡ተግሻት ሳይሆን ማበረታቻ ብቻ የሚፈልግ ልጅ አይደለም፤እንጀራ ልጅ ነው፡፡በማኅበሩ ስም እልፍ አእላፍ ገጾች ተከፍተው የሙሉ ሰዓት ሥራቸው ማኅበሩን ከሰማይ የወረደ ማስመሰል፣ቤ.ክ ከማኅበረቅዱሳን በፊት ያልኖረች ያህል እኛ ባንኖር አትኖርም ብሎ መደስኮር፣አቡነ ጎርጎርዮስንና አቡነ ሺኖዳን ለማወደስ የኛን አባቶች በጸያፍ ቃላት ማብጠልጠል፣ማኅበረቅዱሳን ላይ ምንም አይነት ትችት ቢሰነዝር ጉዳዩን ከተሐድሶ እና ከኢህአዴግ ጋር ማያያዝ፣ኮሌጆችንና ቤተክሕነታዊ አካላትን ሁሉ የባዕዳን ተቋማት አድርጎ በአምሳለ ጭራቅ ስሎ ማቀረብ፣ሥራቸው ነው፡፡ የተወሰኑ የማኅበሩ ነባር አባላት ይህን አካሄድ ገርቶ ወደመስመር እንደማስገባት በጉዳዩ ላይ በፈሪሳዊነት የታጀለ ጽሑፍ በማከል የእብድ መካሪ ሆነው ራሳቸውን ያሻሽጡበታል፡፡አንዳንዶች ነውራቸውን መሸፈኛ አድርገውታል፡፡ ከዚህ ከጎጻጕጽ መንገድ በጊዜ ተመልሳችሁ ከመዋቅሩ ጋር ለመናበብ ካልጣራችሁ ቀስ በቀስ መሬት እየለቀቃችሁ የማኅበራዊ ሚዲያና የጋዜጣ ተቋም እንዳትሆኑ ያሰጋል፡፡

 11. Anonymous February 8, 2016 at 2:03 pm Reply

  ከላይ … ወደ መወቅሩ ዞራችሁ ያልከው! በውስጡ ምክርም ስድብም አለው፡፡ መምከሩ ጥሩ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ማንም ቢሆን ማህበርን የመከተለል፤ የማግዘፍ አባዜ ካለው ይታረም:፡ ግን ጉዳዩ ይሔ አይመስለኝመም:፡ ይህን የመሰለ መንፈሳዊ አገልገግሎት ለምን ይሰናከላል፤ የ3000 ታርክ ባለቤት ከሆነች ቤ/ክ ርዕሰ መንበር በቤተ ከ/ርስትያኒቱን የማይመጥን፤ በዕውነት ያልበለፀገ ክስ ይቀርባል ነው ጥያቄው፡፡

 12. Anonymous February 9, 2016 at 2:27 am Reply

  God bless you!!

 13. Anonymous February 9, 2016 at 5:50 pm Reply

  mk never and ever represent EOTC.

 14. Anonymous February 9, 2016 at 6:10 pm Reply

  mk is breaking church rules by disobeying our patriarch, his holiness Abune Mathias.So, we will never visit your exhibition.And the church must excommunicate such acts in the name of the church!

 15. Anonymous February 12, 2016 at 4:14 pm Reply

  The so-called mahibrekidusan is ceaselessly humiliating the true church servants at the expense of its financial motifs and ambition to control the EOTC and privatize all what belongs to the church.To this end, this profitable organizations doing its best in scolding church servants and defaming them all the time since its establishment.

  Congregation of Doctors by credential

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: