የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ ያሰጋው ማኅበረ ቅዱሳን: የፓትርያርኩ የክሥ መመሪያ የእውነት ጠብታ የሌለበት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለው ገለጸ

 • ቅዱስ ሲኖዶስ እርምትና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ተማፅኗል
 • ከኑፋቄ፣ ከአስተዳደር በደል እና ከዝርፊያ የተነሣ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ አስግቶታል
 • በማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ የፓትርያርኩ አካሔድ “እንግዳ እና አስገራሚ ነው” ብሏል
 • በአካልና በግለሰቦች በኩል እንዲኹም በደብዳቤ 6 ጊዜ ውይይት ቢጠየቁም ፈቃደኛ አልኾኑም
 • በፓትርያርኩ ስም የሚጻፉ ደብዳቤዎች ክብርና ተኣማኒነት ያላቸው ይኾኑ ዘንድ አመልክቷል
 • አግባብነት ያለው ወቅታዊ እርምትና መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እንዲኾን ጠይቋል

*                        *                        *

(ሰንደቅ፤ ረቡዕ፤ ጥር ፳፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)(የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ከዜናው በታች ይመልከቱ)

mahibere-kidusan-head-office

የማኅበረ ቅዱሳን የዋናው ማእከል ጽ/ቤት

የማኅበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፣ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ በስውር የሚካሔደውና ለቤተ ክርስቲያንን የህልውና ስጋት የኾነው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ አሳሳቢ ደረጃ ስለ መድረሱ በተከታታይ መዘገቡን ተከትሎ፣ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የማያቋርጥ ትግል እንዲካሔድ ለኮሌጆቹ ያስተላለፉት የክሥና የቅስቀሳ መመሪያ፣ አንዳችም የእውነት ጠብታ በሌለው መረጃ ላይ የተመረኮዘና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆቹን ክሥ የሚያስተጋባ እንደኾነና እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለው ማኅበሩ ገለጸ፡፡

ማኅበሩ፥ ትላንት ጥር 24 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በቁጥር ማቅሥአመ/239/02/ለ/08 ለፓትርያርኩ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአድራሻ በጻፈውና ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱና ለተለያዩ መንግሥታዊ አካላት ደግሞ በግልባጭ ባሳወቀው ደብዳቤ፤ ለፓትርያርኩ የክሥና የቅስቀሳ መመሪያ ሰፊ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ማኅበሩ በዚኹ ምላሹ፣ ፓትርያርኩ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 2007 ዓ.ም. ምልዓተ ጉባኤው÷ ከኑፋቄው ሤራ አንጻር፣ የመምህራን ክህሎትና የሃይማኖታቸው ጉዳይ፣ የትምህርት ካሪኩለም አቀራረጽ፣ የመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት ምን እንደሚመስል እንዲታይና እንዲፈተሽ ያሳለፈውን ውሳኔ መሠረት አድርገው፣ መናፍቃንና የተሐድሶ አራማጆች በቤተ ክርስቲያናችን ኮሌጆች ተምረው ስውር ዓላማቸውን በማካሔድ ሕዝበ ክርስቲያኑን በመከፋፈል ላይ ስለሚገኙ ከኮሌጆቻችን ጀምሮ…በማስረጃ የተደገፈ ጥናት እንድታቀርቡ በሚል አጽንዖት፣ ችግሩን እንዲያጠና ለተቋቋመው ኮሚቴ ኅዳር 4 እና 11 ቀን 2007 ዓ.ም የጻፉትን ደብዳቤ ለትውስታ ጠቅሷል፡፡

ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ መረጃም፣ የሊቃውንት መፍለቂያ በኾኑት ኮሌጆች ላይ፣ ስለ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ እንቅስቃሴ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ላይ የተመሠረተና ችግሩም በአጠቃላይ አሠራር ደረጃ እንዲፈታ የኹሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት የነቃ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ለማስገንዘብ የተዘጋጀ እንጂ ከሣሾቹ እንደሚሉት፣ ኮሌጆቹን በጅምላ በሃይማኖት ሕጸጽ የመወንጀል አልያም የግለሰቦችን ስም እየጠቀሱ የማውጣት ዓላማ እንደሌለው፣ ለዚኽም ሲባል እንዳልቀረበ አስረድቷል፡፡

“እንደ እውነቱ ከኾነ፣ በጋዜጣው ላይ የወጣው አጠቃላይ የጽሑፉ ጭብጥ ሲታይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከወሰነው ውሳኔ የተለየ ስምዐ ጽድቅ የጻፈችው ምን አለ?” ሲል የጠየቀው ማኅበሩ፣ በኮሌጆቹ አስተዳደር፣ ሠራተኞች፣ መምህራንና ደቀ መዛሙርት ስም የቀረበው አቤቱታ፣ ጋዜጣው በይፋ ያወጣው መረጃ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በእውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አካላት ዘንድ ትኩረት በማግኘቱ የተደናገጡት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች የሰርጎ ገብ እንቅስቃሴያቸው እንዳይገታባቸው የፈጠሩት የማዘናጊያ ውንጀላ እንደኾነ አብራርቷል፡፡

“ከየኮሌጆቹ ከሚማሩ ደቀ መዛሙርት መካከል በውድም ኾነ በግድ እንዲፈርሙ ተደርገው ለቅዱስነትዎ የቀረበልዎት ጥያቄ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ውሳኔ መኾኑ ተዘንግቶና የማኅበረ ቅዱሳን አንድ ተወካይ እንኳ ተገኝቶ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሳይደረግ እንዲኽ ዓይነት ብያኔ በእርስዎ በቅዱስ አባታችን መሰጠቱ አሳዝኖናል፤” ሲል ቅሬታውን ገልጧል፡፡ አያይዞም፣“ጥቂት የተሐድሶ እምነት አራማጆችን በርቱ፣ ተቃውሟችሁንና ማደናገራችሁን ቀጥሉበት የሚል የሚመስል መልእክት የያዘ ሐሳብ በቅዱስነትዎ ፊት መሰጠቱም እጅግ አስደንቆናል፡፡ በጥሞና ከታየ የቀረበውን መረጃ ወስዶ በቅዱስ ሲኖዶስ እንደገና የተቋቋመው ኮሚቴ እንዲያጠናው ማድረግ የሚገባ እንጂ ሊያስከሥሥም ኾነ እንዲኽ ዓይነት ደብዳቤ ሊያስጽፍ የሚችል ነገር ለመኖሩ በፍጹም አልታየንም፤”  ሲል የፓትርያርኩ አካሔድ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔና አሠራር የሚቃረን፣ ማኅበሩን የማይገልጽና ፍትሐዊነት የጎደለው እንደኾነ ተችቷል፡፡

የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን የእምነት መግለጫቸውን አሳትመው በይፋ በማሠራጨት የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖትና ቀኖና በማንአለብኝነት በሚፃረሩበት፤ በአስተዳደራዊ መዋቅራችን ውስጥ ጥቅመኝነት ክብር ተሰጥቶት በግላጭ ዝርፊያ በሚፈጸምበትና አገልጋይ ካህናት በየቦታው በሚበደሉበት በአኹኑ ወቅት፤ በርእሰ መንበሩ ደረጃ ለቤተ ክርስቲያን የማይበጁ እንዲኽ ያሉ የሐሰት ክሥና የቅሰቀሳ መመሪያ ያዘሉ ደብዳቤዎች እየተፈረሙ ሲወጡ ማየት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለውም ማኅበረ ቅዱሳን በደብዳቤው አሳስቧል፡፡

ክሡን በግልባጭ እንኳ እንዲያውቀው አለመደረጉንና የደብዳቤው ዓላማና ተልእኮው ምን እንደኾነ ለመገመት መቸገሩን የገለጸው ማኅበሩ፤ ምንም እንኳ ማኅበሩን፣ አጥጋቢ ሥራ ሠርቷል ወይም አልሠራም፤ ስሕተቶችን ይፈጽማል አይፈጽምም ብሎ መከራከር፣ መውቀስና በሐሳቦቹም መወያየት፣ አስፈላጊም ሲኾንም መገሠጽ እየተቻለ ከአንድ ቅዱስ አባት ቀርቶ ከየትኛውም የተቋም ሓላፊ በማይጠበቁና የሰዎችን ስሜት በሚያስቆጡ ቃላት መሸንቆጥ በእጅጉ አሳዝኖናል፤ ብሏል፤ በተለይም “የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ይገኛል” የሚለው የፓትርያርኩ ጭፍን ብያኔ ለማኅበሩ አመራርና አባላት ቀርቶ ደብዳቤውን በየሚዲያዎቹ ያዩት ኹሉ፣ ትዕግሥትን የሚፈትን እንደኾነ እየገለጹለት እንደሚገኙም ጠቁሟል፡፡

አባታዊ መመሪያና ቡራኬ ለመቀበል፣ ለቤተ ክርስቲያን ቅን የማያስቡ አካላት በሚያነሡበትም ክፉ ጉዳዮች ለመወያየት÷ በአካል በመቅረብ፣ ለስድስት ጊዜያት ደብዳቤ በመጻፍ እንዲኹም ብፁዓን አባቶችን ጨምሮ በተለያዩ ግለሰቦችና አካላት በኩል ፓትርያርኩን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ጊዜ ሰጥተው ሊያወያዩት እንዳልቻሉ ማኅበሩ በጽሑፍ ምላሹ አውስቷል።

በአንጻሩ ማኅበሩን በመክሠሥ ለሚቀርቡ የተለያዩ አካላት ፓትርያርኩ ጊዜ እየሰጡ እንደሚያነጋግሩ የጠቀሰው ደብዳቤው፣ “ለአንድም ቀን እንኳን በተከሠሥንበት ጉዳይ ቀርበን ቃላችንን እንድንሰጥ አለማድረግዎ አስደንቆናል፤” ብሏል።

የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች በሚያዘጋጇቸውና በሚመሯቸው ድረ ገጾችና ብሎጎች ማኅበሩን ለመክሠሥ የሚያወጧቸው ሐሳቦች በፓትርያርኩ መመሪያም ተጠቅሰው መታየታቸው እንዳሳዘነውና እንዳስገረመው ማኅበሩ ገልጾ፣ ከሣሾች ባቀረቡት ቃል ላይ ብቻ ተመሥርቶ ፍርድ መስጠት እውነተኛውን ሕግ በምትተረጉመው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም እንግዳ ሥርዓት ነው፤ ሲል ተችቷል፡፡

እውነታውን ለማወቅና ለሚነሡ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የጉዳዩን ባለቤቶች ጠርቶ ፊት ለፊት በማነጋገርና በመመካከር መፍታት እንጂ አንድ ጩኸት በተሰማ ቁጥር ደብዳቤ መጻፉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንደማይበጅም ማኅበሩ አስገንዝቧል።

በብፁዓን አባቶች ቡራኬና መመሪያ ሰጪነት፣ በገዳማውያን ጸሎትና በምእመናን ከፍተኛ ድጋፍ ቤተ ክርስቲያንን በአገልግሎቱ ለማገዝ ላለፉት 23 ዓመታት የዐቅሙን ያህል ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የጠቀሰው ማኅበሩ፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንንና የአማሳኞችን ውንጀላ የሚያስተጋባው የፓትርያርኩ የክሥና የቅሰቀሳ መመሪያ በቅዱስ ሲኖዶስ በአንክሮ ውይይት ተካሒዶበት እርምት እንዲደረግበትና አስቸኳይ መፍትሔም እንዲሰጠው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ተማፅኗል፡፡

በፓትርያርኩ ስም የሚጻፉ ደብዳቤዎች፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉና ክብርዋን የሚያስጠብቁ፣ በኹሉም አካላት ዘንድ ተኣማኒነት ኖሯቸው ትኩረት ሰጥተው የሚመለከቷቸው እንዲኾኑ ማኅበሩ አስተያየቱን አስፍሮ ለወደፊቱም፣ አግባብነት ያለው ወቅታዊ እርምትና መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እስካልኾነ ድረስ፣ “የሚከተለው አደጋ ትልቅነት ይታየናል፤” ሲል የፓትርያርኩ ወገንተኛና ያልተስተዋለ(እየገነገነ የቀጠለ ኢ-ፍትሐዊና ዓምባገነናዊ አካሔድ) የከፋ መዘዝ እንዳያስከትል በደብዳቤው አስጠንቅቋል፡፡ (በስምንት አርእስተ ጉዳዮች እና በ12 ገጾች የተካተተው የማኅበረ ቅዱሳን ደብዳቤ ሙሉ ቃል ከዚኽ በታች ተያይዟል)

*                        *                        *

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜንmahibere-kidusan-logo

ቁጥር፡- ማቅሥአመ/239/02/ለ/08
ቀን፡- 24/05/2008

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ
በያላችሁበት

 

ጉዳዩ፡- በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ስለተጻፈና የተሳሳተ መረጃ የያዘ ደብዳቤን ይመለከታል፤

ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-

በደብዳቤ ቁጥር ል/ጽ/179/338/2008 ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም ከቅዱስነትዎ የተጻፈና ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ለሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና ለቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በአድራሻ የተጻፈ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን አስመልክቶ ፍጹም እውነትነት የሌለው መረጃ ላይ በመመርኮዝ መመሪያ ያስተላለፉ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ በተለያዩ ሚዲያዎች ተሰራጭቶ ተመልክተናል፡፡ ይህም ጉዳይ እኛን የቤተ ክርስቲያን አካል የሆንን ልጆችዎን እጅግ አሳዝኖናል፡፡ የደብዳቤው ዓላማና ተልእኮም ምን እንደሆነ ለመገመት አስቸግሮናል፡፡ ምንም እንኳ በደብዳቤው የሰፈረው ሃሳብ ፍጹም እኛን የማይገልጸን ቢሆንም ስለተከሰስንበት ጉዳይ በግልባጭ እንኳ እኛ እንድናውቀው አልተደረገም፡፡ ይሁንና እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ እንዳደረግነው እውነቱን ለማስገንዘብ አሁንም ይህንን ደብዳቤ ለመጻፍ ተገደናል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ስር ሕጋዊ በሆነ ሥርዓት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ ዕውቅናና ፈቃድ ተዋቅሮ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ እነሆ 23 ዓመታትን አሳልፏል፡፡ ማኅበሩ የሚመራበትና የሚተዳደርበት ደንብም በመጀመሪያ በማደራጃ መምሪያው በኩል በኋላም በ1992 ዓ.ም በቅዱስ ፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በኩል በዝርዝር የሚያጠኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩት ኮሚቴ ታይቶና ተመርምሮ የጸደቀለት እንዲሁም በ1994 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ደረጃ ቀርቦ የታየ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩት፣ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና የሕግ ባለሙያዎች የተሳተፉበትና ከ6 ወራት በላይ የፈጀ ጥናት የተደረገበት የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ እንደገና ታይቶና ተፈትሾ በምልዓተ ጉባኤው የጸደቀና ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ፊርማቸውን ያስቀመጡበት መሆኑን ቅዱስነትዎ ጠንቅቀው ያውቁታል ብለን እናምናለን፡፡ ይህንንም ማድረጋቸው ብፁዓን አባቶቻችን ዘመኑን በመዋጀት በዘመናዊ ትምህርት የሚመረቁ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ አርቀው በማሰባቸው ነው፡፡ እውነታው ይኽ ሆኖ ሳለ በደብዳቤዎ ላይ ማኅበሩን «ጥቅሙና ጉዳቱ በሚገባ ሳይጠና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር የሚያስከትለው የሃይማኖትና የሥርዓት ተፋልሶ ሳይፈተሽ በአንድ ወቅት ራሱ አርቅቆና አዘጋጅቶ ባቀረበው ደምብ በቅዱስ ሲኖዶስ የተፈቀደልኝ ሕጋዊ ማኅበር ነኝ ይላል›› በማለት መግለጽዎ ለምን እንደሆነ አልገባንም፡፡ ይህ ሀሳብም ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና አሠራር የተቃረነ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በ2004 ዓ.ም የማኅበሩ አገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ እና በወቅቱ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊዎች ጋር የነበረውን አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤ ደረጃ በአጽንኦት ከተመልከተ በኋላ ለጊዜው የማኅበሩ ተጠሪነት ለብፁዕ ዋና ሥራ አሥኪያጅ እንዲሆንና ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ እና ማኅበሩን ከነበረበት ደረጃ የበለጠ ሊያሠራው የሚችል ደንብ እንዲኖረው በማሰብ ቅዱስ ሲኖዶስ እርስዎም በተገኙበት ጉባኤ ደንቡን የሚያሻሽል (የጉዳዩ ባለቤት የሆኑ የማኅበሩ አባላትም የተካተቱበት) ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል፡፡ ይኸው ማሻሻያ ተሠርቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ግን ማኅበሩ በ1994 ዓ.ም ጸድቆ የተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ ሕጋዊ ሆኖ እንደሚቀጥልም አጽንኦት ተሰጥቶበት መታለፉ ግልጽ ነው፡፡ ቅዱስነትዎ በመንበሩ ከተሰየሙ በኋላም ይኽው አጥኚ ኮሚቴ ሥራውን አጠናቅቆ ቢያቀርብም ቅዱስነትዎ በተደጋጋሚ አልቀበልም በማለትዎ መዘግየቱን የሚዘነጉት አይመስለንም፡፡ እንዲያውም ከዚህ አንፃር በርስዎ በኩል የቀረበ እና በየትኛውም አሠራር ቢሆን እንግዳ የሆነ ውሳኔን ማኅበሩ ይሁን ብሎ ተቀብሎታል፡፡ ይኸውም በመንግሥታትም አሠራር ቢሆን አንድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሊሰጥ የሚደራጅን ማኅበር ሊያገለግልበት የፈለገበትን አቅጣጫና የሚመራበትን ውስጠ ደንብ ከተቋሙ ሕግ አንፃር አርቅቆ በማቅረብ በፈቃድ ሰጪው አካል ያስጸድቃል እንጂ ፈቃድ ሰጪው አካል ራሱ ሕገ ደንብ አርቅቄ ካልሰጠኹህ አይልም፡፡ ሆኖም ግን ቀደም ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ የሰየመውና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መሪነት ከአንድ ዓመት በላይ የደንብ ማሻሻያውን ጥናት ሲሠራ የቆየው ኮሚቴ ያዘጋጀውን ጥናት አልቀበልም ብለው እንግዳ በሆነ መልኩ አንድም የማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ የሌለበት ሌላ አዲስ ኮሚቴ እንዲቋቋም መደረጉን ሲሰማ ማኅበሩ በይሁንታ ነው የተቀበለው፡፡ ይህንንም ያደረግንበት ምክንያት በብፁዓን አባቶቻችን ላይ ካለን አመኔታና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታዛዥ ከመሆናችን የተነሣ ነው፡፡ ይሁንና ቅዱስነትዎ ይህንን በአዲስ መልክ የተቋቋመውን ኮሚቴ አባላቱ እነማን እንደሆኑ እንኳ ለኛ ባላሳወቁበት ሁኔታ #በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን የደንብ ማርቀቅ ሥራ ሆን ብሎ በማሰናከል ያለ ደንብ እየሠራ ይገኛል$ በማለት በደብዳቤዎ ላይ ማስቀመጥዎ እጅግ አስገራሚ ነው፡፡

ይህ ሁሉ ቢሆንም ማኅበረ ቅዱሳን በአባቶች ምክር፣ ጸሎት እና ድጋፍ ምንም ዓይነት የሕግም ሆነ የሥርዓት ተፋልሶ ሳያስከትል ለአባቶች እየታዘዘ አሁንም አገልግሎቱን ግልጽ በሆነ አሠራር እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከእርስዎ ከቅዱስ አባታችንም ዘንድ ቀርበን አባታዊ ቡራኬና መመሪያ ለመቀበል፣ እንዲሁም አንዳንድ ለቤተ ክርስቲያናችን ቅን የማያስቡ ወገኖች የማኅበሩን ስም በክፉ ባነሱበት ጊዜ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተደጋጋሚ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት በአካልም እየቀረብን በደብዳቤም ከስድስት ጊዜ በላይ (በቁጥር ማቅሥአመ/80/02/ለ/06 ቀን 21/1/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ /118/02/ለ/06 ቀን 9/5/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ/127/02/ለ/06 ቀን 25/6/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ /138/02/ለ/06 ቀን 24/8/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ/165/02/ለ/07 ቀን 01/02/07 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ /212/02/ለ/07 ቀን 3/13/07 ዓ.ም) ለቅዱስነትዎ በቀጥታ ጽፈን መጠየቃችን ይታወሳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከብፁዓን አባቶች ጀምሮ የተለያዩ አካላትንና ግለሰቦችን ከርስዎ ጋር እንዲያወያዩን በተደጋጋሚ ጠይቀን ነበር፡፡ ነገር ግን እርስዎ ጊዜ ሰጥተው ሊያነግግሩን አልቻሉም፡፡ በአንጻሩ ማኅበሩን ከቅዱስነትዎ ዘንድ ከስሰው የሚቀርቡ የተለያዩ አካላትን ጊዜ እየሰጡ ማነጋገርዎ ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን እንኳን በተከሰስንበት ጉዳይ ቀርበን ቃላችንን እንድንሰጥ እንኳ አለማድረግዎ አስደንቆናል፡፡ ክስ የቀረበበትን አካል አቅርበው ሳይጠይቁ ከርሱም ሳይሰሙ ከሳሾች ባቀረቡት ቃል ላይ ብቻ ተመስርቶ ፍርድ መስጠት በማንኛውም አካል ዘንድ በተለይም እውነተኛውን ሕግ በምትተረጉመው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም እንግዳ የሆነ ሥርዓት ነው፡፡

ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-

የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና የሚያስጠብቀው ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 2007 ዓ.ም ባደረገው ጉባኤ ከተወያየባቸው ጉዳዮች መካከል ተሐድሶን በተመለከተ በቃለ ጉባኤው ያሰፈረው እንደሚከተለው ይነበባል “… የተሐድሶ መናፍቃን መገኛ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ ጉባኤው በመወያየት ደቀ መዛሙርቱ ከየአኅጉረ ስብከቱ ሲላኩ ጤናማ እንደሆኑ ነገር ግን ተመርቀው ሲመለሱ ግን ከነችግራቸው ሌላ ሰው ሆነውና መስለው ይመለሳሉ፡፡ ለዚህ የችግሩ ምንጮች ኮሌጆቹ እንደሆኑ ያመለክታል፡፡ ምክንያቱም መንፈሳዊ ኮሌጆች ተልከው መናፍቃን ሆነው ሲመለሱ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኮሌጆች ሊፈተሹና ሊመረመሩ ይገባል …“  ካለ በኋላ ቃለ ጉባኤው የሚከተለው ውሳኔ መተላለፉን ይገልጻል፡፡ “… የመምህራን ክህሎት እና የሃይማኖታቸው ጉዳይ፣ የኮሌጆች የትምህርት ካሪኩለም አቀራረጽ፣ የመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት ምን እንደሚመስል ታይተውና ተፈትሸው ሊሠራባቸው ይገባል” የሚል ውሳኔ ማስተላለፉና ይህንንም የሚያጠና አንድ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡ ይህንን ውሳኔ ለተቋቋመው ኮሚቴ ለማሳወቅ ቅዱስነትዎ ኅዳር 4 እና 11 ቀን 2007 ዓ.ም በጻፏቸው ደብዳቤዎች ላይ “መናፍቃንና የተሐድሶ አራማጆች በቤተ ክርስቲያናችን ኮሌጆች ተምረው ስውር ዓላማቸውን በማካሄድ ሕዝበ ክርስቲያኑን በመከፋፈል ላይ ስለሚገኙ ከኮሌጆቻችን ጀምሮ … በማስረጃ የተደገፈ ጥናት እንድታቀርቡ” በሚል አጽንኦት ሰጥተው መግለጽዎ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረጉት የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ አኅጉረ ስብከት የቀረቡ ሪፖርቶችና አስተያየቶች ከየመንፈሳዊ ኮሌጆች የተመረቁ አንዳንድ መምህራን የተሐድሶ መንፈስ እያራመዱ እንዳስቸገሯቸውና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ማወካቸውን በግልጽ ማቅረባቸው፣ እነዚህም ሀሳቦች በጉባኤዎቹ ሲቀርቡ በተሰብሳቢዎቹ ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጣቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ የሆነችው ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ጋዜጣም ይህንን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና የአኅጉረ ስብከት ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ ከመስከረም ወር 2008 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ንቁ በሚለው ዓምዷ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ መልኩን እየቀያየረ እና በረቀቀ መልኩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕልውና አደጋ ውስጥ እየከተተ የመጣውን የተሐድሶ መናፍቃኑን አጠቃላይ የኅቡዕ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ዘገባ እየሠራች መረጃ መስጠት ቀጥላለች፡፡ በተለይም በኅዳር እና በታኅሣሥ አጋማሽ እትሞቿ ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያናችን በምትመካባቸው መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ውስጥ በስውር ምን እያደረጉ እንደሆነ እና ለነርሱም መግቢያ ቀዳዳ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን በማሳያነት በመጥቀስ ዘገባ ማቅረቧ እውነት ነው፡፡ ለዚህም ዘገባ የተለያዩ አካላት ያወጧቸውን ሪፖርቶች ጋዜጠኛው ወይም ጸሐፊው በመጠቀም በኮሌጆቹ አካባቢ የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ የሚያመላክት የዳሰሳ ጥናት ማድረጉ ተገልጿል፡፡ በንጹሕ ስንዴ መካከል እንክርዳድ መገኘቱ ፍጹም እንግዳ ባይሆንም ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱ ግን አሳሳቢ መሆኑ በጽሑፉ ተዳስሷል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችን እጅግ የምትኮራባቸው መምህራንና ሊቃውንት ከነዚሁ ኮሌጆች በብዛት መገኘታቸውን እና የየኮሌጆቹ የሥራ ኃላፊዎችም ሆኑ እውነተኞቹ ደቀ መዛሙርት ይህንን የተሐድሶዎችን እንቅስቃሴ ተረድተው ምን ዓይነት ተጋድሎ እያደረጉ መሆኑን፣ ችግሩ ግን ሰፊ ሆኖ ከዐቅማቸው በላይ እንዳይሆን የሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት የነቃ ተሳትፎና ርብርብ እንደሚያስፈልግ በጋዜጣዋ በሰፊው ታትቶ ቀርቧል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም ችግሩን በአጠቃላይ አሠራር ደረጃ እንዲፈታ ማድረግ ላይ ማተኮር እንጂ በቤተ ክርስቲያናችን የሚመለከተው አካል ውሳኔ ሳይሰጥባቸው አንዳንድ የችግሩ መገለጫ የሆኑ ግለሰቦችን በስም እየጠቀሱ በጋዜጣ የማውጣት ዓላማ የለውም፡፡

ሆኖም ግን ይኸው መረጃ በይፋ መውጣቱና ጉዳዩም ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በየደረጃው ባሉ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያናችን አካላት ሁሉ ዘንድ ትኩረት በማግኘቱ የተደናገጡት የተሐድሶ እምነት አራማጆች የሰርጎ ገብ እንቅስቃሴያቸው እንዳይገታባቸው ማዘናጊያ መፍጠር ነበረባቸው፡፡ ለዚህም እንዲረዳቸው ማኅበረ ቅዱሳን በስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ጋዜጣው “መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶቹን በጅምላ በሕፀፀ ሃይማኖት ከሰሰ” በማለት የጋዜጣዋን አንድ እትም አንጠልጥለው ከአንድ ወር በኋላ ወሬውን በአዲስ መልክ በየኮሌጆቹ አካባቢ በስፋት ማናፈስ ጀመሩ፡፡ ይህንን ወሬ የሰሙ አንዳንድ እውነተኛ ሰዎችም ሳይቀር ሙሉውን ተከታታይ ጽሑፍ ሳያነቡት ቅሬታ ተሰምቷቸው ቀርበው አነጋግረውናል ፤ አንዳንዶቹም የተወሰነውን ጥቅስ በማንሳት ለምን እንዲህ እንደተገለጸ እንድናብራራላቸው በደብዳቤ የጠየቁንም አሉ፡፡ ከእነዚህ ጋር ጥሩ ውይይት አድርገን መግባባት ላይ ደርሰናል፡፡ ነገር ግን ይህንን የተሐድሶዎቹን ድብቅ ዐላማ ያልተረዱ አካላት አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ጭምር በማሳሳት የዚህ የስውር እንቅስቃሴያቸው ደጋፊ እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል፡፡ እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከየኮሌጆቹ ከሚማሩ ደቀ መዛሙርት መካከል በውድም ሆነ በግድ እንዲፈርሙ ተደርገው ለቅዱስነትዎ የቀረበልዎትን የቅሬታ ጥያቄ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ውሳኔ መሆኑ ተዘንግቶና የማኅበረ ቅዱሳን አንድ ተወካይ እንኳ ተገኝቶ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሳይደረግ እንዲህ ዓይነት ብያኔ በርስዎ በቅዱስ አባታችን መሰጠቱ በከፍተኛ ሁኔታ አሳዝኖናል፡፡ ጥቂት የተሐድሶ እምነት አራማጆችን “በርቱ፣ ተቃውሟችሁንና ማደናገራችሁን ቀጥሉበት” የሚል የሚመስል መልእክት የያዘ ሐሳብ በቅዱስነትዎ ፊት መሰጠቱም እጅግ አስደንቆናል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ በጋዜጣው ላይ የወጣው አጠቃላይ የጽሑፉ ጭብጥ ሲታይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከወሰነው ውሳኔ የተለየ ስምዐ ጽድቅ የጻፈችው ምን አለ? በጥሞና ከታየ የቀረበውን መረጃ ወስዶ በቅዱስ ሲኖዶስ እንደገና የተቋቋመው ኮሚቴ እንዲያጠናው ማድረግ የሚገባ እንጂ ሊያስከስስም ሆነ እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ ሊያስጽፍ የሚችል ነገር ለመኖሩ በፍጹም አልታየንም፡፡

ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-

የማኅበረ ቅዱሳን አደረጃጀት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የመንፈሳዊ ትምህርት ሥርዓት ለመከታተል፣ አባላቱ በሙያቸውና በበጎ ፈቃዳቸው ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን የትሩፋት አገልግሎት ለማስተባበር ተብሎ በሀገረ ስብከትና በወረዳ ደረጃ ብቻ መዋቅር የተዘረጋለት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአጥቢያ ደረጃ ማኅበሩ ምንም ዓይነት ተቋማዊ አደረጃጀት እንደሌለውም የተገለጠ ነው፡፡ ይኽ አደረጃጀቱም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ የተሰጠው መሆኑ ለሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት ግልጽ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የማኅበሩ አባላት በፍጹም ታዛዥነት ቀርበው በቤተ ክርስቲያን መዋቅር እየተመራንና ብፁዓን አበው መመሪያ እየሠጡን እንሥራ ብለው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት መቅረባቸው የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስወቅስ አልነበረም፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን የአገልግሎት ማኅበር ሲቋቋም ማኅበረ ቅዱሳን የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን እውቅና ሰጥታቸው የተቋቋሙ፣ የራሳቸው ጠቅላላ ጉባኤ ፣ የራሳቸው ውስጠ ደንብ ፣ የራሳቸው አመራር ያላቸው ብዙ ማኅበራት በቤተ ክርስቲያናችን ነበሩ፤ አሁንም አሉ። ሆኖም ግን በእንዲህ ዓይነት መንገድ የተቋቋሙትና የቤተ ክርስቲያን የቅርብ ክትትል ያልተለያቸው ማኅበራት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ሲጠቅሙ እንጂ ጉዳት ሲያደርሱ ታይቶ አይታወቅም። በርግጥ ቤተ ክርስቲያን የማታውቀውና በቤተ ክርስቲያንም ሥርዓት የማይመራ ማኅበር ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለእምነታቸው ቀናዕያን የሆኑ አንዳንድ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ተሰባስበው ሃይማኖታቸውን ለመማር መነሳሳታቸው፣ በተማሩትም ትምህርት መሠረት ስለወንጌል መስፋፋት እገዛ ማድረግና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት መጀመራቸው እንዳሻቸው መሆን ለለመዱት ተሐድሶዎች እና ጥቅመኞች ነገሩ ስላላማራቸው ‹‹ማኅበራት በሌላ ቦታ እንጂ በቤተ ክርስቲያን አመራር ሥር መዋቀራቸው ቀኖና የጣሰ ነው›› የሚል ሐሳብ ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ይህ አባባል እንደ እውነታ ተወስዶ በእርስዎ ደብዳቤም መጻፉ ቅር የሚያሰኝ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያናቸው ቀናዒ ሆነው የድርሻቸውን ለመወጣት የሚደራጁ ማኅበራት ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሳካት እስከሆነ ድረስ ማኅበረ ቅዱሳን ስለነዚህ ማኅበራት መደራጀት በጎ አመለካከት ቢኖረውም ማኅበረ ቅዱሳን ከራሱ ውጪ ለየትኛውም ማኅበር መቋቋምም ሆነ መክሰም ኃላፊነት የለበትም፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ከቀድሞ ጀምሮ የዓመት ዕቅዱንና በየስድስት ወሩ ደግሞ የአፈጻጸም ሪፖርቱን ተጠሪ ለሆነለት አካል በጽሑፍ ሲያስገባ ቆይቷል፡፡ እንዲሁም የፋይናንስ (የገቢና የወጪ) አሠራሩን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በመመዝገብ ገለልተኛ በሆኑና በመንግሥት በተፈቀደላቸው የውጭ ኦዲተሮች ጭምር በየዓመቱ እያስመረመረ ሪፖርቱን ለሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያናችን አካላት እያቀረበ መጓዙ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በ2007 ዓ.ም የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ለቤተ ክርስቲያን ቁጥጥር የተሻለ እንዲሆን በቤተ ክርስቲያን ሥር የተቋቋሙ ማኅበራት ሁሉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተፈቅዶ በሚሰጣቸው የገቢና የወጪ ደረሰኝ እንዲጠቀሙ በተወሰነው መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን የዚህ ውሳኔ አፈጻጸም ፋና ወጊ በመሆን ይህንኑ ካርኒ አሳትሞ መጠቀም መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ይህንኑም በያዝነው ዓመት በቀረበው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓመታዊ ሪፖርት ላይ የቁጥጥር መምሪያውም ማረጋገጡን በግልጽ መስክሯል፡፡ ማኅበሩ የአገልግሎትና የፈቃድ ማኅበር እንደመሆኑ አባላቱ እንደየገቢያቸው መጠን የአባልነት አስተዋጽኦ ይከፍላሉ፡፡ የማኅበሩም ዋናውና ቋሚው የገቢ ምንጭ ይኸው በመሆኑ ማንኛውም የማኅበሩ የሥራ ማስኬጃ የሚሸፈነው በአባላቱ መዋጮ ነው፡፡ የማኅበሩ አመራር አባላትም አገልግሎታቸው የበጎ ፈቃድ በመሆኑ ጊዜአቸውን መስዋዕት አድርገው ከመስጠታቸው በተጨማሪ ለትራንስፖርትም ሆነ ሌሎች ወጫአቸውን ሁሉ የሚሸፍኑት ከኪሳቸው አውጥተው ነው፡፡ እንዲያውም ብዙ ጊዜ ለሥራ ማስኬጃ የሚሆን ገንዘብ ሲያነስ ተጨማሪ መዋጮ እንዲያዋጡ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ማኅበሩ በተለየ ሁኔታ ገንዘብ እየሰበሰበ ለማይታወቅ አገልግሎት ያውላል ተብሎ መገለጹ ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላ ከመሆኑም በላይ ከአንድ ቅዱስ አባት የማይጠበቅ በመሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል፡፡

ማኅበሩ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ በግልጽ በተፈቀደለት መሠረት አባላቱ ሙያቸውንና ዕውቀታቸውን አስተባብረው ገዳማትን በልማት ራሳቸውን እንዲችሉና የአብነት ትምህርት ቤቶች በደጋፊ ማጣት የትምህርት አሰጣጣቸው እንዳይስተጓጎልና እንዳይበተኑ ለማድረግ ፕሮጀክት ቀርፀው ለቤተ ክርስቲያናችን አባላት ለሆኑ በጎ አድራጊዎች በማኅበሩ በኩል ያቀርባሉ፡፡ ለፕሮጅክቱ የሚሆን ገንዘብም ሲገኝ ማኅበሩ በሥራ ላይ አውሎ ለሚመለከተው አካል (ለገዳማቱ ወይም ለአብነት ትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች) ያስረክባል፡፡ ይህም የሚፈጸመው በቅድሚያ በገዳማቱ በደብዳቤ ሲጠየቅ ወይም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወይም በሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ሲታዘዝ (ሲጠየቅ) ነው፡፡ የእነዚህ ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸውንም ሆነ የፋይናንስ አወጣጣቸውን የሚያሳየውን ሪፖርት በየጊዜው እየተዘጋጀ ገንዘቡን ላዋጡት ምእመናን (ወይም ማኅበራት) እንዲሁም ፕሮጀክቱ ለሚተገበርላቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት የሚቀርብላቸው ሲሆን ይህም በየዓመቱ በውጭ ኦዲተሮች እየተመረመረ ሪፖርቱ ለሚመለከታቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አካላት እየቀረበ ይገኛል፡፡ በመሆኑም አገልግሎቱ የየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ ክትትል አይለየውም፡፡ እንግዲህ በዚህ አሠራር መጓዝ የትኛውን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና እንደሚጥስ ለእኛ አልገባንም፡፡ እንዲሁም ‹‹ከቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን አመራር አይቀበልም፣ አባቶችን ይዳፈራል›› ተብሎ በእርስዎ ደብዳቤ መገለጹ አግባብነት አለው ብለን አናምንም፡፡

የማኅበሩ አባላት በአብዛኛው ወጣቶች የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን አማንያን ናቸው፡፡ ከነርሱ መካከልም የመንፈሳዊ አገልግሎት ዝንባሌ ያላቸው የአብነት ትምህርቱን ከትምህርታቸው ጎን ለጎን እየተማሩ፣ በየሊቃነ ጳጳሳቱ እየተፈተሹና መሥፈርቱን እያሟሉ ክህነት ይቀበላሉ፡፡ ቅዱስ አባታችን እርስዎም በአሜሪካ በነበሩ ጊዜ በዚሁ መንገድ ለአንዳንዶቹ ክህነት መስጠትዎን አይዘነጉትም፡፡ ይህ ደግሞ በሁሉም ብፁዓአን አባቶች የታወቀ ጉዳይ ሆኖ ሳለ በደብዳቤዎ ላይ ‹‹ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ … ለአባላቱ በጅምላ ክህነት እያሰጠ …›› ብለው መግለጽዎ በምን ምክንያት እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ መቼም ክህነት የሚሰጠው በእናንተ በብፁዓን አባቶች እንጂ በሌላ አካል እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ታዲያ በዚህ ጉዳይ ቀኖና ተጥሶስ ከሆነ የጣሰው ማን ነው ለማለት ነው; ምናልባት ካሁን ቀደም ብፁዓን አባቶችን ለማንቋሸሽ ሲባል አንዳንድ ሰዎች በየመድረኩ ሲናገሩት የነበረውን ድጋፍ ለመስጠት ታስቦ ካልሆነ በስተቀር ማኅበረ ቅዱሳን የሚከሰስበት አንዳች ምክንያት የለውም፡፡ ደግሞም አሁን ባለው ሁኔታ የዘመናዊውን ትምህርት መስፋፋት ተከትሎ ብዙ ብሩኅ አእምሮ ያላቸው ወጣቶች ከአብነት ትምህርቱና ከቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት ተለይተው እንዳይቀሩ መሥራት የቤተ ክርስቲያናችን ድርሻ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በርከት ያሉ የአብነት ትምህርት የተማሩና በትምህርቱም የገፉ ወጣቶች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየገቡ በመሆኑ ገና ብዙ አብነቱን እና የአስኳላውን ትምህርት ያጣመሩ ምሁራን ቤተ ክርስቲያናችን ይኖሯታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይህም አርቆ ላሰበ ሰው ለቤተ ክርስቲያን አንድ ሰፊ የአገልግሎት አቅጣጫ ነው፡፡

በውጭ ሀገር ስላለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም ምናልባት ያለፉት ሦስት ዓመታት አስረስተዎት ካልሆነ በቀር የማኅበሩ አባላት ስለቤተ ክርስቲያን አንድነት በሚያደርጉት ከፍተኛ ተጋድሎ እንደ ገና ዳቦ ከሁሉም አቅጣጫ እሳት እየነደደባቸው የሚታገሉ መሆኑን በየጊዜው ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከውጪ ሀገር በመጡ ቁጥር ይመሰክሩት የነበረ ነው፡፡ በቅርቡም በአሜሪካ ሄደው በነበረ ጊዜ የተጋበዙባቸው አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እዚያ ደረጃ እንደደረሱና ማን መሥዋዕትነት እንደከፈለባቸው፣ አሁንም ቢሆን በቅዱስነትዎ ጉዞ ወቅት ማን እንዳስከበርዎ ልቡናዎ ያውቀዋል፡፡ ከዚህም በላይ በሀገር ውስጥ ለተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች በሚዘዋወሩበት ጊዜ በየቦታው በደመቁ ሰልፎች ተሰልፈው እየዘመሩ በማጀብ የሚቀበሉዎ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያውቁና አባቶቻቸውን እንዲያከብሩ ስላስተማራቸው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-

በተጨማሪም በደብዳቤዎ ላይ አንዱ ዋና ወንጀል ተደርጎ የተገለጸው «በሌለው ሥልጣን የጾም አዋጅን እስከማወጅ ደርሷል›› የሚል ይገኝበታል፡፡ በአጭር ቋንቋ ለመግለጽ ማኅበረ ቅዱሳን ያወጀው ጾም የለም፡፡ ጾም በቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚታወጅም ጠንቅቆ ያውቃል፤ ያስተምራልም፡፡ ለጾም አድሉ ብላ በምታስተምር ቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ጾም ታውጃላችሁ ተብሎ የቀረበብን ክስ ‹‹በቤተ ክርስቲያን ጾም በዝቷልና ካልተቀነሰ›› እያሉ በከንቱ የሚደክሙትን ተሐድሶዎች ሀሳብ ለምን አትደግፉም የሚል ያስመስለዋል፡፡

በአጠቃላይ ካሁን ቀደም በተለያዩ የተሐድሶ እምነት አራማጆች በሚያዘጋጇቸውና በሚመሯቸው ድረ-ገጾችና ብሎጎች ላይ በተደጋጋሚ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመክሰስ ሲያወጧቸው የነበሩትና አንድም የእውነት ጠብታ እንኳ የሌላቸውን ሀሳቦች በርስዎ ደብዳቤ በአጭር በአጭሩ ተጠቅሰው ማየታችን እጅግ አሳዝኖናል፤ አስገርሞናል፡፡ እነርሱ ሁል ጊዜም እውነት መናገር ልማዳቸው እንዳልሆነ በሁሉም ዘንድ ስለሚታወቅ ንቀን መልስ ሳንሰጣቸው ቆይተናል፡፡ በርስዎ ደረጃ ይህ እንደገና ሲስተጋባ ግን ዝም ማለቱ ተገቢ ስላልሆነ ነው ይህን ምላሽ ለመስጠት የተገደድነው፡፡ ይህ ለመንፈሳውያን ኮሌጆቹ በአድራሻ የተጻፈላቸው ደብዳቤም ዓላማው በእውነት ግልጽ አይደለም፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢሆን እውነታውን ለማወቅና ለሚነሱ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የጉዳዩን ባለቤቶች ጠርቶ ፊት ለፊት በማነጋገር እና በመካከር መፍታት እንጂ አንድ ጩኸት በተሰማ ቁጥር ደብዳቤ መጻፉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚበጅ አይመስለንም፡፡ በርስዎ ስም የሚጻፉ ደብዳቤዎችም ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉና ክብርዋን የሚያስጠብቁ፣ በሁሉም አካላት ተአማኒነት ኖሯቸው ትኩረት ሰጥተው የሚመለከቷቸው እንዲሆኑ ቢደረግ እጅግ ደስ ይለናል፡፡

ክቡራን ንዑዳን ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ፡-

ማኅበረ ቅዱሳን በናንተ ቡራኬና መመሪያ ሰጪነት በብዙ ገዳማውያን አባቶቻችን ጸሎት እና በምእመናን ከፍተኛ ድጋፍ ቤተ ክርስቲያንን በአገልግሎቱ ለመደገፍ ላለፉት 23 ዓመታት የዐቅሙን ያህል ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የነበረው አገልግሎት አልጋ በአልጋ ባይሆንም በተለይ በአሁኑ ወቅት ያለው የቤተ ክርስቲያናችን ሁኔታ እያሰጋን መጥቷል፡፡ የተሐድሶ መናፍቃኑ በማን አለብኝነት የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖት እና ቀኖና በሚጻረር መልኩ የእምነት መግለጫቸውን በይፋ በመጽሐፍ መልክ አሳትመው እያሰራጩ ባሉበት ወቅት፣ ጥቅመኝነት በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ክብር ተሰጥቶት በይፋ ዝርፊያ በሚፈጸምበት እና አገልጋዮች ካህናት በየቦታው በሚበደሉበት በዚህ ጊዜ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ርዕሰ መንበር ደረጃ በቅዱስነታቸው እንዲህ ዓይነት ለቤተ ክርስቲያን የማይበጁ ደብዳቤዎች እየተፈረሙ ሲወጡ ማየት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለው ይሰማናል፡፡ ምንም እንኳ ማኅበሩን አጥጋቢ ሥራ ሠርቷል ወይም አልሠራም፣ ስሕተቶችንም ይፈጽማል አይፈጽምም ብሎ መከራከር መውቀስና በሀሳቦቹም መወያየት፣ አስፈላጊም ሲሆን መገሠጽ እየተቻለ ከአንድ ቅዱስ አባት ቀርቶ ከየትኛውም የተቋም ሓላፊ በማይጠበቁና የሰዎችን ስሜት በሚያስቆጡ ቃላት መሸንቆጥ በእጅጉ የሚያሳዝን ሆኖ ተሰምቶናል፡፡ ለአብነት ያህልም ማኅበሩን ከሳሾቹ እንኳን በማይሉት መንገድ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ይገኛል›› የሚለው ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ይህ አገላለጽ ለማኅበሩ አመራርና አባላት ቀርቶ ደብዳቤውን በየሚዲያዎቹ ያዩት ሁሉ ትዕግሥትን የሚፈትን እንደሆነ እየገለጹልን ይገኛሉ፡፡ የጥቅምቱን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተከትሎም ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያናችንን ስብከተ ወንጌል ለዓለም የሚያሰራጭበት የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ሲቋረጥ ለሚመለከተው የቤተ ክርስቲያናችን አካል ብናመለክትም በቅዱስነታቸው ደብዳቤ እንዲቆም መደረጉም ሌላው አሳዛኝ ተግባር ነው፡፡ ከዚህም በላይ በዘመናችን ባለው ቴክኖሎጂ ምክንያት የትኛውም መረጃ ወይም ጉዳይ በሚዲያ ለሕዝቡ በከፍተኛ ፍጥነት የሚዳረስ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ይህንም ተከትሎ ብዙ ዓይነት ስሜቶችና አጸፋዎች ከምእመናን ይደመጣሉ፡፡ በመሆኑም በወቅቱ አግባብነቱን የጠበቀ ዕርምትና ለወደፊቱም መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እስካልሆነ ድረስ የሚከተለው አደጋ ትልቅነት ይታየናል፡፡

ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ ላይ በአንክሮ እንዲወያይበት እና እርምት እንዲሠጥበት ለእኛም ከዚሁ አንፃር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን እንድታደርጉልን ከእግረ መስቀላችሁ ሥር ወድቀን በፍጹም ትሕትና እንጠይቃለን፡፡

የቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን
የብፁዓን አባቶቻችን የጸሎታችኹ ረድኤት አትለየን

ቀሲስ ሰሙ ምትኩ(ዶ/ር)
የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ
የማይነበብ ፊርማና ማሕተም አለው

ግልባጭ፡-

 • ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
 • ለሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ
 • ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት
 • ለኢ.ፊ.ዲ.ሪ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጽ/ቤት
 • ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ጽ/ቤት
 • ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
 • ለብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት
 • ለውስጥ ደኅንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ
 • ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
  አዲስ አበባ
 • ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
 • ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
 • ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ጽ/ቤት
  መቐለ
 • በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለሚመሩት አህጉረ ስብከት
  በያሉበት፤
 • ለማኅበረ ቅዱሳን ለሁሉም ማእከላት
  በያሉበት

 

 

Advertisements

61 thoughts on “የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ ያሰጋው ማኅበረ ቅዱሳን: የፓትርያርኩ የክሥ መመሪያ የእውነት ጠብታ የሌለበት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለው ገለጸ

 1. Anonymous February 3, 2016 at 3:18 pm Reply

  አጻጻፉ በተቋሙ ስር እንዳለ አካል ሳይሆን በሁለት ተገዳዳሪ ተቋማት መካከል መምሰሉ ይገርማል፡፡በዘገባው ኮሌጆች ላይ ለደረሰው የሞራል ስብራት ምንም ፀፀት የለም፡፡ፈራሚዎች ተሳስተው እንደፈረሙ ነው ታሳቢ የተደረገው፡፡ማኅበሩ ሚዲያውን ሁሉ ተቆጣጥሮ ደብዳቤ በበረረ ቁጥር ጉዳዩን ከተሐድሶ ጋር ማያያዝን ልማድ አደረገው፡፡ደብዳቤው ለመፍትሄ ፍለጋ ሳይሆን ለአባላቱ እኛ እንዲህ ነን ለማለት መጻፉን መገመት ቀላል ነው፡፡የግልባጭ አጻጻፉ የፓትርያርኩን ደብዳቤ ተምሳሌት ያደረገ ነው፡፡ማኅበሩ የፓትርያርኩ ደብዳቤ ይዘት ተሐድሶዎች ከሚሰነዝሩብን ክስ ጋር ይመሳሰላል ሲል የእሱም ደብዳቤ በየብሎጎቹ ከሚንጸባረቀው ጸረ ቤተክህነት አቋም ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆኑ ተዘንግቶታል፡፡ሳምንት የፓትርያርኩን ደብዳቤ በሚመለከት ዜና ሲሰራ የማኅበሩን ሐሳብ በማካተት ሚዛናዊ ለመምሰል የሞከረው ሰንደቅ በዚህኛው ዘገባው የቤተክህነቱን አቋም ለማካተት አለመሞከሩ የሆታ ዘመቻውን ያንጸባርቃል፡፡

  ሌላው ማኅበሩ ላይ ተግሳጽ ከተሰነዘረ በቤተክርስቲያን ላይ ምጽአት እንደቀረበና ሰማይ ሊደፋባት እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ የተለመደ ስለሆነ አይገርምም፡፡ሚዲያው በምንም መልኩ ማኅበሩን ከማወደስ በቀር ራሱን እንዳይመለከት በማድረግ የተካነ ነው፡፡ስለዚህ ክፍተቱን የተሐድሶ ሚዲያዎች እንደፈለጉ ይጠመዝዙታል፡፡ማኅበሩ በበኩሉ ክፍተቱ እንዳይነገር በማፈን እኔን የሚተች ሁሉ ተሐድሶ ነው ለማለት ተመችቶታል፡፡አባላቱም እንዲያ እንዲያስቡ ተደርገው ስለተሰሩ ለእነሱ ማኅበረቅዱሳን ማለት በራሱ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ማለት ነው፡፡የሃይማኖቱ ዶግማና ቀኖና መስፈርት በእነሱ ቤት ማኅበረቅዱሳን ነው፡፡ሀቁ እንደሱ እንዳልሆነና የማኅበሩ ከሲኖዶስ የቀደመ ኮሌጆችንና የቤተክህነት ተቋማትን በተሐድሶነት መፈረጅ አግባብ እንዳልሆነ ሲገለጽ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት መጣ፡፡ጉዳዩ ፓትርያርኩ ዘንድ ከመድረሱ በፊት ሦስቱም ኮሌጆች ማኅበሩ ማስተባበያ እንዲያወጣ ተማጽነዋል፡፡ማኅበሩ ጆሮ ነፈጋቸው፡፡ጭራሽ አቤቱታቸውን ለፓትርያርኩ ሲያቀርቡ እያናጠሉ ስም ማጥፋት ተጀመረ፡፡ከአሜሪካ እስከ አምስት ኪሎ የተቀናጀ ዘመቻ ተከፈተ፡፡በማኅበሩ አስተሳሰብ ቤተክህነቱና ፓትርያርኩ ሰነፎች ስለሆኑ የአባላቱን እንቅስቃሴ አያውቁም፡፡እንዲያው መቃጠል ነው፡፡ ቃላት መደርደር መቼ ረባን፡፡አባትና ልጅ ተጣጥመው ለቤተ ክርስቲያን መከታ የሚሆኑበትን ዘመን ያምጣልን፡፡ሚዲያችን ለወንጌልና ለክብረ ቅዱሳን መስበኪያ ሳይሆን ለሐሜትና ለመፈራረጃ ሆኖ ቀረ፡፡ይሄንን አሳዛኝ የ24 ዓመት ሂደት የአማላጂቱ ልጅ መላ ያብጅለት፡፡

  • anonymously February 3, 2016 at 4:30 pm Reply

   Eshohin Be Eshoh yiluhal endih new!!!

  • Anonymous February 3, 2016 at 8:37 pm Reply

   ወሽካታ መናፍቅ ዝም በል።

  • ዳሞት February 4, 2016 at 7:51 pm Reply

   ለanonymous February 3,2016 at 3:18pm
   የቀድሞው ታዛቢ፤ የአሁኑ አነኒሞስ(anonymous)፦ መቸም አንድ ጊዜ የእውነት ብርሐን በርቶላቸው መልሰው የካዱትን ለንስሃ ማብቃት ከባድ እንደሆነ የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል። አንተም አምነህ የካድ ሆነሃልና ለእውነትና ለሀይማኖት ትቆማለህ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ምክንያቱም እምነትንም እውነትንም አውቀሃት ነበር፤ አሁን ግን ክደሃታልና ነው። የካደና እውነትን የጠላ ደግሞ ትላንት ያለውን ዛሬ አይደግመውም።
   ባለፈው አድርባይ ቲፎዞነትህና ትችትህ ፓትራርኩን ለማነጋገር የጠየቁበትን ደብዳቤ ያሳዩንና አብሬ ልጩህ ስትል መዘላበድህን እረስተህ ለአባቶችና ለሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኗና ሌሎች አካላት የተጻፈውን ለመተቸት አፍህን ከፈትህ። በእርግጥ ከሾህ ወይን አይለቀምምና ከእንዳንተ አይነቱ በዘረኝነት የጠነዛና በምንፍቅና ለሚማስን ምንም አይነት እውነትን መገንዘብና መልካም ነገር አይገኝምና ያንተን ጩኸት ማንም አይሰማም ለሥጋዊ ነገር የቆመ ካልሆነ።
   ያንተ መዘላበድ በአመኑት ዘንድ ምንም የሚያመጣ ነገር ባይኖርም ሰው ሆነህ በክርስቶስ ተዋጅተህ ተመልሰህ ጭቃ ውስጥ ተለውሰህ መማሰንህ ነው የሚያሳስዝነው።
   የሚገርመው ደግሞ ሚዲያውን እያብጠለጠልኸው የሰይጣን መልእክትህንና ትችትህን ለማስፈር ግን ቀዳሚው መሆንህን ነው። በተጨማሪም እንደ ትሁት ካህንነትህ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አማኝ ለመምሰል “የአማላጅቱ ልጅ መላ ያብጅለት” ማለትህ ነው። መምሰልንማ ማን ብሎት ዲያብሎስ፤ መሆን ሆኖ መገኘት የለም እንጂ። የፈጠረውን አምላኩንም ለመገዳደር ጥቅስ ከመጥቀስም አላቆመም። በመመሳሰል አይሆንምና መንገድህን አስተካክል።

  • Anonymous March 21, 2016 at 2:30 am Reply

   YELEBA AYNEDEREK MELSO LIB YADERK

  • Anonymous February 4, 2016 at 11:32 am Reply

   betam yemitasazinew neger binor hasabih endehasab mansatih bego hono sale:”…ከሚንጸባረቀው ጸረ ቤተክህነት አቋም ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆኑ ተዘንግቶታል….”tsere betekihinetinina tsere tehadison lemawek ebakih wendime bebetekihinetu ke abogida eske 4 ayina yekoyutin abatoch teyik.wetatuna melkam bego mahiberat lebetekrstiyanachin min eyeseru endehone asb.bete kihinet(yekahinat meflekiya.bet.megegna,magelgeya …)malet enjii bechifinu abatochachin nitsuhan yalubet malet ayidelem.minim enkuan nitsuhan bifelkubetim bemulu ayibalim.merejaw keleleh yebete krstiyan tarik(3tu abeyit Gubaeyatin anbib….)bebetekihinet endeariyos tetemare lik yelem eskiyasegn dires …..ere sintun bicha anibew. ene kidus diyoskoros, k/Atnatiyos,……(Hayimanot Abew Anbib)…..yalum abatoch eko kebete kihinet yewetu nachew. Neger gin yehonew hono Sile shewa dabo lemenager berulay mashitet beki ayidelem.

   “ማኅበሩ ላይ ተግሳጽ ከተሰነዘረ በቤተክርስቲያን ላይ ምጽአት እንደቀረበና ሰማይ ሊደፋባት እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ የተለመደ ስለሆነ አይገርምም፡፡”waldiba sifers gibiGubaeyat sibetenu….Gebd yetesera kemeseleh?Antenetih sayihon astesasebihin keyir. Nege beye Adbaratu lekalkidanu tabot yeminberekekuna eyewedeku mintaf yemiyanetifu mahiberat sizegu minim yemayimeslih kehone???Abezahubih wendime”Letebibse ahatii kal tibeque

   “….መፈረጅ አግባብ እንዳልሆነ ሲገለጽ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት መጣ…፡”yebat mikir ena tegsatsi min endehone digame meniger alfeligim..begubae….besibseba…bebet…besenbet t/t bet..betsiwa yimekiralu::endezemenum endetintum..enikuan lebetekrstiyan kenae negn lemitil lante ….kerto….Bedelala lemetach serategna enkun Misa ablita sitabeka wuchiii ayibalim .Ahun anten ayadirgewuna kemitagelegilibet(Kehonk?) senbet t/t bet, mahiber,miemeninet minim satineger,satimeker, tagidehal bimetabih…yemiyasagid enkuan bihon enkuan beageligilot sitet yesera.Lotu sibehatina” Weld fitur new “bilo afun molto yetenagerewun Ariyosin bitmeles bilew yekenona seat setut” eskii tewo wendime yih kalhone gin hayimanot endelelew sew chibt ena erbana belelew yawum kesikar yihun kemenfes yet metanetu bemayitawek mereja 1 sew sayihon hulun miemenan mawezageb kehayimanotegna ayitebekim.

 2. Anonymous February 3, 2016 at 4:27 pm Reply

  Kale hiwot yasemaln!!! look the politics of Mk, ante mhiber who is your father? are you Orthodox? patriaric le mengist gelbach debdabi tsafu beleh tikse neber now lemin ant tsafic yegermal!! ahunim and tera mahiber le patriaric metsaf aychilem!!! mahiber kidusan hymanot new
  or derget( politica) look him self again b/c you are not the representative of the church!!
  MAFERYAWOCH!!!!! we will pray for our patriarc Matriays ( our model of Ethiopia orthodox church)

 3. Anonymous February 3, 2016 at 6:02 pm Reply

  ዓይነ ሕሊና በእውነት ተሰውረዋል፡፡ ለመሆኑ እስከመቼ ድረስ ነው እንዲሁ የቤተክርስቲያኒቱን ካባ ለብሰህ በፖለቲካ ጥማትህ ቤተክርስቲያኒቱን እያተራመስክ የምትኖረው ?ለመሆኑ እኒህ ቅዱስ አባት ቤተክርስቲያኒቱን መጠበቅና ማስጠበቅ የለባቸውም? ይረዱኛል ብለህ የምትጮህባቸው አባቶች ምን እንዳደረካቸውና ምን እንዳደረክላቸው ተገንዝበው ይረዱኛል ብለህ ይሆን? ማወቅ ያለብህ ቅዱስ ፓትርያሪኩ በምንም መንግድ ልያዙልህ አልቻሉም፡፡ ችግርህ ይህ ነው፡፡ ሌላው ቅዱስ ፓትርያሪኩ የተመረጡ በመላው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናትና ምእምናን ሁሉ እንደሆነ እወቅ፡ እንተ ምልምለህ አንዳንዱን እንደሾምክ የተሸሙ አይደሉም፡፡ ለምሆኑ ስርዓት ያዝ ፤የምታደርገው ና የምትሄደው መንገድ ሃይማኖታዊ ቀኖናዊ መንገድ አይደለም፡፡ በማነኛውም ጉዳይ በቤተክርስያኒቱ ዙርያ የያዝከውና የምታውቀው መረጃ ካለ እንደ ሕገ ሲኖዶስ ለሚመለከተው አካል አቅርብ እንጂ መግለጫ የመስተጠና የማውገዝ ሲልጣንህ አይደለም መባልህ አስቆጣህ? ይህንን ካልተቀበልክስ ከዚህ የባሰ መናፍቅነትና አጉራዘለልነት አለ?
  ምናው ውስጥህ ብትፈትሽ፡ ምንው ንስሐ ብትገባ፡ ፓለቲካዊ ጥማትህ እንዴት ልብህ አሳወረው? ማቅ. ብፁዓንና ንዑዳን አልክ? ጥሩ ሙገሳ ነው፡፡ ምን እንደምትላቸውና ስለ እነዚህ አባቶች ምን ብለህ እንደምትናገር ቢያስ እስከ አሁን እውነቱ ነው ብለው የደገፉህ የሚታዘቡህ አይመስልህም? አሳፋሪ ነህ፡፡ እውነቱን ልንገርህ አንተም የራስ ምታት ስለሆንክባቸው ንስሐ የምትገባበትን ወይም ካልተመለስክም ዕድሜ እንዲያጥር እንደም ጸልዩ አትጠራጠር፡፡ ልብ ቢኖርህ አይደግመኝም ፡፡እስተካከላለሁ፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝ ብለህ መመለስ ነበረብህ፡፡ ግን በቤተክርስቲያኒቱ ስም የሰበሰብከው ገንዘብና ዕለት ዕለት የምትመኘው ሥልጣንን የማግኘት አባዜ እዕምሮህ ደፈነው፡፡ በል ንስሐ ግባ አለበለዚያ በተሎ ይመጣብሃል፡፡ ስም አጠራርህም ይጠፋል፡፡

  • Anonymous February 3, 2016 at 8:32 pm Reply

   ለደንቆሮ “የሃይማኖት አባት” አግባብ ያለው መልስ ነው፣ግን “አባ” ማቲያስ አይደለም ጆሯቸው ልባቸው ታውሯል ።ይብላኝላቸው።

  • Anonymous February 4, 2016 at 5:45 am Reply

   ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር ስለቻለን እናመሰግነዋለን እንጂማ እንዳንተ ያለ መናፍቅ እምነትን ከክህደት ልማትን ከጥፋት ብርሃንን ከጨለማ እውነትን ከሐሰት ፍቅርን ከጥላቻ መለየት ያቃተህ ድፍን ጥላቻ በውሰጥ የያዝክ ከወንጌል ይልቅ በወንጀል የተካንክ
   ስለበለህ የምትጮህ ላበላህ የምትሞት እምነት ምንማለት እንደሆነ የማይገባ ልብህ በዲያቢሎስ የታሰር የዲያቢሎስ ምረኮኛ እውነት ያልገባህ እንዲገባህም እራስህን ያልገለጥክ ፍጡር በእውነት እናንተ ክርሰቲያን ወንድሞች የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የኦርቶዶክስ አማኞች ስለዚህ አይነት ሰዎች ፀልዩላቸው እንጂ አትዘኑባቸው

   ማስተዋሉን ያድልህ

  • mamush February 4, 2016 at 4:48 pm Reply

   kelay mahberun seteweks yeneberkew,hulu negereh endemestawet fentew belo yitayal.ante manafek neh besew guday min agebah?ene yalgebagne aba matias yanen hula yehaset kes sikesu alayehem?atleast yehone mastewal yemibal aytehew atawkem?yalgebagne patriarch yalew hulu ewnet new yaleh manew?yichi neger patriarchu ye egziabher enderase selehonu aysasatum yaleh manew?yichi neger kecatholicoch tarik lay new yayehuatena.tekekelegna abat eskehonu dres cheger yellewem,patriarch gin kemanafkan gar tebabro lejochun yemiwaga kehone abat mehonu yikerena erasum tekula yihonal,patriarch selehone bicha ketesasatu aynegerachewem yalew manew?

 4. Anonymous February 3, 2016 at 8:19 pm Reply

  I just enjoyed the above comments; good job dudes! I want to forward my appreciation to your comprehension capabilities and I expect some of your friends come forward to do so – “yeleba aynederek. .. . ” endil yagere sew

 5. Anonymous February 3, 2016 at 10:10 pm Reply

  enough is enough! MK please! the time of your repentance is now. stop playing with fire or with a sharp knife .you have to say sorry and follow and respect the conn, rule and regulation of the church. Now we do know you very much you are not part of the Ethiopian Orthodox or any orthodox church. I dare to you are from others. because if you are part of the Church you wouldn’t stand against the holy patriarch. as we know the patriarch is the heard of the entire church and he has a right to protect the church from any enemy. if you are part of the mother church, you have to hear the voice of the patriarch and abide by his leadership otherwise, you have to split and depart from the church and be registered as a politician .
  may God open your internal ear to hear his divine word

  • Anonymous February 5, 2016 at 12:40 pm Reply

   Which rule and regulation is violated? Can’t you understand the content of the letter? If then, you better stop your nonsense. You and your likes are always striving to create political associations with the true fight of the church against anti-orthodox groups. But then, you fail to prove your claim with evidence. You simply bark. That’s what you are hired for. One thing you forgotten is you are fighting with God’s church. If you have some truth, present it parallel to the contents of the letter.

 6. Demeke Alamirew February 3, 2016 at 11:23 pm Reply

  down with aba diabilos(Mathias)!

 7. Anonymous February 4, 2016 at 12:03 am Reply

  “በቅርቡም በአሜሪካ ሄደው በነበረ ጊዜ የተጋበዙባቸው አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እዚያ ደረጃ እንደደረሱና ማን መሥዋዕትነት እንደከፈለባቸው፣ አሁንም ቢሆን በቅዱስነትዎ ጉዞ ወቅት ማን እንዳስከበርዎ ልቡናዎ ያውቀዋል”
  ምን ለማለት ተፈልጎ ነው? የት እንደሄዱ በግልጽ ቦታውን ብትገልጹት ጥሩ ነበረ በግልጽ መልስ መስጠት ይቻል ነበረ፣ በደፈናው ግን በሬ ወለደ ብሎ መዋሸት ያሳፍራል።

 8. Anonymous February 4, 2016 at 4:54 am Reply

  ተሀዲሳውያን ተሀገራችን ይጥፉ

  • ebe February 4, 2016 at 8:03 am Reply

   Mathias: Pente-Tehadiso; YeElias lole!

  • anonymously February 4, 2016 at 8:23 am Reply

   Devils have > 7000 years experience but tehadso & ye betekihinetu werobeloch more than him?!!!?

  • Anonymous February 4, 2016 at 7:13 pm Reply

   ማህበረ ቅዱሳን፣ የቤተ ክርስትያን የቁርጥ ቀን ልጅ፣

 9. Anonymous February 4, 2016 at 5:38 am Reply

  የሚከተለው አደጋ ትልቅነት ይታየናል!!!

 10. Anonymous February 4, 2016 at 6:20 am Reply

  Let us stand against tehadso Protestantism

 11. Anonymous February 4, 2016 at 6:36 am Reply

  በአሽሙር የተሞላና ከፍጹም የታዛዥነት መንፈስ ውጭ በገጽም በይዘትም አጠፌታ ለመስጠት በማኅበረቅዱሳን ተጻፈ ተብሎ የተለጠፈውን ደብዳቤ ለማመን አቃተኝ፡፡ለማመሳከር ብዬ የራሱ ማኅበሩ ዌብሳይት ላይ ብሔድ ‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ ለጻፉት ደብዳቤ ማኅበር ቅዱሳን መልስ ሰጠ›› በሚል ርእስ ይኼው ደብዳቤ በፒ.ዲ.ኤፍ ተሰይሟል፡፡በጣም ገረመኝ፡፡ከማኅበረቅዱሳን ውጭ በቤክርስቲያኗ ስር አያሌ ተቋማት እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ሆኖም በውሳኔዎች ደስተኛ ካልሆኑ የሚጽፉት ደብዳቤ ‹‹መልስ መስጠት›› አይደለም፡፡ቅሬታ ወይም አቤቱታ ማቅረብ ነው፡፡ለምሳሌ መንፈሳውያን ኮሌጆችን ማየት ይቻላል፡፡በማኅበረቅዱሳን ላይ ያላቸውን አቤቱታ ደረጃና መዋቅር ጠብቀው አቀረቡ፡፡የራሳችን የሕግ ሰውነት ያለን ነን ብለው በስማቸው ለየመንግሥት አካሉ ግልባጭ የተደረገ ደብዳቤ ሲበትኑ አላየንም፡፡
  አንድ ማኅበር ቤተክርስቲያኗን አክሎና መስሎ ከላይ በመንበሩ ያሉት አበው ለሚጽፉለት ደብዳቤ በአሽሙርና በፀጉር ስንጠቃ የተሞላ እንካሰላንቲያ ውስጥ ከገባ፣በስሙ ለሊቃነ ጳጳሳትና ለመንግሥት አካላት ደብዳቤ ማብረር ከጀመረ፣በዚህ መጠን የቅሬታ ይዘት ያለው ሳይሆን የተግሳጽና የመልሶ ፍረጃ መልስ የተሞላ ደብዳቤ ማብረር ከቀጠለ ማዕከላዊ መዋቅር ለምን አስፈለገ?‹‹መልስ ሰጠሁ›› ያለ አካል መልሶ መልስ ከሰጠው አካል ዳኝነት አይጠይቅም፡፡መልስ ከተሰጣጡ እኮ በውስጠ ታዋቂ እኩል ቁመና ያላቸው 2 ተፎካካሪ አካላት ናቸው ማለት ስለሆነ እሳቸው እግረ መስቀል ስር በመደፋት ማኅበሩ ጊዜውን ማባከን አይጠበቅበትም፡፡
  ልክ የማኅበሩ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትርያርኩን አክለውና ተገዳድረው መልስ እንደሰጡት ቦርዱ በፊናው ተሰብስቦ ፓትርያርኩን ማውገዝ ይችል ነበር፡፡ካደረጉ አይቀር እንደሱ ነው፡፡ነካክቶ መተው ምን ያደርጋል፡፡ስለቤተክሕነት ባሕርይ ብዙ የምታውቁ ይመስለኝ ነበር፡፡ለካ ፌስቡክና ብሎግ ቋንቋችሁን አጥፍቶባችኋል፡፡ያን ያህል ገጽ በአሽሙርና ፌዝ መሸፈን ከባድ ብቃት ነው፡፡ቅሬታና አቤቱታ የሚጻፍበትን ቋንቋ እና ሥርዓት አለማወቃችሁ አስገረመኝ፡፡ቤተክርስቲያኗን ወክሎ ከመንግሥታዊ የበላይ አካላት ጋር በዋናነት የመጻጻፍ ሉዐላዊ መብት በመንበሩ የተሰየመው ፓትርያርክና የጠቅላይ ቤተክሕነቱ ሥ/አስኪያጅ ሊቀ ጳጳስ መሆኑንም ዘንግታችሁታል፡፡በማኅበሩ ውስጥ ካሉ አካላት ይልቅ የዚህ ብሎግ አዘጋጅ ለመግለጫችሁ የተሻለ ርእስ ሰጥቶታል፡፡እስኪ ለማንኛውም እግዚአብሔር አበሳችሁን አይቁጠርባችሁ፤እሳቸውንም ከእናንተ ጋር ተቀራርበው በስክነት የሚመክሩበትን የይቅርታ መንፈስ ያድልልን፡፡እኛን ዘለዓለም የእናንተን አተካራና ፍትጊያ ከመስማት ይልቅ ትሩፋታችሁን ብቻ ያሳየን፡፡

  • Anonymous February 5, 2016 at 12:56 pm Reply

   መዘንጋት የሌለበት እዉነታ፣ ጉዳዩ በቅዱስ ፓትርያርኩ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የተከሰተ አለመግባባት ሳይሆን የተሀድሶዎችን መሰሪ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ቤተክርስቲያኒቱ እያደረገችሁ ያለችዉን የግንዛቤ ማስጨበት ሥራ ለማወክ ብሎም ለማስቆም ያለመ ነዉ፡፡ ከዚህ አንጻር ካየነዉ እና ቀደም ሲል በፓትርያርኩ የተጻፈዉ ደብዳቤ ይዞት የወጣዉን አደገኛ መረጃ ትክክለኛነት ማገናዘብ ላለባቸዉ አካላት ሁሉ መረጃ ማድረስ ተገቢ ነዉ ከተባለ፤ ከዚህ የተለየ ምን መንገድ ሊኖር ይችላል? አንደኛዉ መንገድ የፓትርያርኩ ደብዳቤ በደረሰበት ቦታ ሁሉ በሌላዉ ወገን ያለዉን እዉነታ ማስገንዘብ ነዉ፡፡ ለዚህም የግልባጮቹን መመሳሰል ያስተዉሏል፡፡ የደብዳቤዉን ይዘት በጥንቃቄ አይተዉት ከሆነ እኮ በዝምታ ለማለፍ የሚከብድ እና ከበስተጀርባዉ የአጽራረ ቤተክርስቲያን እጅ ስለመኖሩ ለመገመት ብዙ መመራመር የማይጠይቅ ነዉ፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ እዉነቱን ማወቅ ለሚገባዉ አካል ሁሉ ተገቢዉን እና እዉነተኛዉን መረጃ ማድረሱ አማራጭ የሌለዉ ነገር ነዉ፡፡ እዉነቱ ተዳፍኖ ቤተክርስቲያኒቱ የጥቃቱ ሰለባ ሆና እንድተቀር ካልተፈለገ በስተቀር፡፡

 12. Anonymous February 4, 2016 at 6:46 am Reply

  እኔ በርግጥ የማህበሩ አባል ለመሆን 2001 ዓ.ም ምዕራብ ሐረርጌ በዴይሳ ከተማ በሚገኙ የማህበሩ አባላት ለመምጣት ብሞክርም በወቅቱ ከአካባቢው በስራ ምክንያት በመቀየሬ ምክንያት ማህበሩን ለመቀላቀል የነበረኝ ጉጉት ቀረ፤በመሆኑም ስለማህበሩ እንቅስቃሴ ስራ ዘወትር ስለማህበሩ ከማገኘው መረጃ አንፃር ማህበሩ ለቤተክርስቲያናችን ያለው ተቆርቋሪነት አንፃር የሚሰሯቸው ስራዎች ግን ይበል የሚያሰኝና የሚበረታታ ሆኖ ሳለ በቅዱስ ሲኖዶሳችን ዛሬ ዛሬ እየቀረበበት ያለው ክስ ግን እጅግ ያሳዝናል ያሳፍራልም፡፡እንደኔ እንደኔ ግን ለነኛ የናት ጡት ነካሽ ተሃድሶና መናፍቃን የቤተክርስቲያናችንን ክብር ዳግም ማስደፈርና የልብ የልብ እንዲሰማቸው ማድረግ ነው የሚሆንባችሁ፡፡

 13. Anonymous February 4, 2016 at 7:16 am Reply

  by this way if tehadiso can’t get away they want to say mk want poletics

 14. Anonymous February 4, 2016 at 7:45 am Reply

  ለማንኛ ዉም መበርታትን አትርሱ።ፈጣሪ ያዉቃል።
  😀

 15. XXXXXXXXXXXX February 4, 2016 at 8:28 am Reply

  እኔ እንደ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመንነቴ ውስጤን ያበገነው ማኅበሩ የፃፈው ምላሽ ሳይሆን ቅዱስነታቸው የፃፉት ድብዳቤ ነበር፡፡ ምክንያቱም የቤተክርስቲያኒቷ ተከታይ እንደመሆኔ መጠን ምን ተሠራ፣ ምን እየታሰበ ነው፣ ወጣቱን በተለይም ወደ ክፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡትን ለቤተክረስቲያን ብሎም ለሀገር በሚጠቅም መልኩ ለመቅረጽ፣ ገዳማት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ በልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ የቤተክርስቲያኒቷ ልጆች ምን ሥራ መሠራት ነበረበት ብዬ ራሴን ስጠይቅም ሆነ ማኅበሩ የሚሠራቸውን ሥራዎች እከታተለው ስለነበር የተሠሩትን ነገሮች ስገመግም በቅዱስነታቸው የተገለፀው ነገር በጣም ይገርመኝ ነበር፡፡ ይህ የኔ ስሜት የአብዛኛው ምንዕመን በተለይም ማኅበሩ በሰጣቸው አገልግሎቶች እምነቱን ያፀና የቤተክርስቲያኒቷ ተከታዮች ስሜት ሊሆን እንደሚችል አምናለሁ፡፡ አሁንም መፍትሔው በቅዱስነታቸው እጅ ያለ ይመስለኛል፡፡
  በቤተክረስቲያን ፍቅር ተነሳስተው ያለምንም ሥጋዊ ጥቅም እያገለገሉ ያሉትን የማኅበሩን አባላት ቀርቦ በማናገር ከዚህ በላይ ቤተክርስቲያኒቷን ሊጠቅም በሚችል መልኩ ማስተናገድ መቻል ይኖርባቸዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡
  በሌላ በኩል ደግሞ በተለይ በተሀድሶ እንቅስቀሴ ላይ የሚደረገውን ክትትል የማህበረ ቅዱሳን ብቻ አድርጎ መውሰድ የሚመሩትን ምዕምን ስሜት አለማወቅ እና ምዕመናንም መናቅ ይመስለኛል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የሚጮኸው በብዕርና መዋቅራዊ ተጠሪነቱን ተከትሎ ለሚመለከታቸው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መረጃ በማድረስ ብቻ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ከዚህ የማኅበሩ የብዕር ገለፃ በዘለለ ምዕመኑ በተግባር ምላሽ መስጠት ሲጀምር ጉዳቱ የከፋ ይሆናል፡፡ እኔ እንደ ምዕመን ስመለከተው የማኅበሩ መኖር እኛን ለዘብተኛ፣ አንድን ነገር ለመጋፈጥ ፈሪ እንድንሆን እና እርሱን እንድን ጠብቅ ያደረገን ይመስለኛል፡፡
  ይህ ነገር መቼም ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ከሚመለከቱ አብቶቻችን የተሰወረ ይሆናል ብዬ አላስብም፡፡
  እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡

 16. Anonymous February 4, 2016 at 8:40 am Reply

  yemehahiberu tekawami hulu chigr alebet fikre EGZIABHER yelelebet sle betekrstian yemayagebaw yemaychenek new!!!!!! libona ysten!!!

 17. Belay kebede February 4, 2016 at 9:05 am Reply

  Ere atawozagebun befeker ennur.

 18. መዝገቡ February 4, 2016 at 9:09 am Reply

  አስገራሚ ነገር አንዳንድ አስተያየት ሳነብ ማህበረ ቅዱሳን አባቶች ምንም ቢያጠፉ መልስ መስጠት የለበትም የሚሉ ናቸው
  በመጀመርያ ማህበረ ቅዱሳን እየታገለ ያለው የትሃድሶ አራማጆችን ነው ይህን ሲያደርግ ለምን ተነኩ ተዋቸው ቤተክርስትያንን ይውረሷት የሚል ካለ አለካ ስለሆነ ብቻ ተቀባይነት የለውም
  የመላይክት አለቃም በክደቱ ወድቋል

 19. Anonymous February 4, 2016 at 9:55 am Reply

  gilibach yetederegew silemin lemengist akale tedereg? tegebi kehon dagimo lemin le tigray kilil bicha kehone lehulum higawi shifan indinorew ketefeleg lehulum sijemer betekrstiyanachin lela astaraki atfeligim ignaw be ignaw

  • Anonymous February 5, 2016 at 1:00 pm Reply

   Bemejemeria Yetetsafew debidabie lederesachew akalat leginizabe endiredachew tasibo yimeslegnal.

 20. Anonymous February 4, 2016 at 11:27 am Reply

  ቅዱስ አባታችን አልልም! ምክንያቱም እንዲህ አይነት ቅድስና የትም ታይቶ አይታወቅምና፡፡
  አስተያየት ለመስጠት አልወድም ፡፡ ምክር ለመስጠትም አቅመቢስ መሆኔን በቅጡ እንኳ የማላዉቅ ደካማነቴ ይታወቀኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ እንዲህ መትጋትዎ ለምን አንደሆነ ምክኒያት ሊሆንዎ ይችላል ብዬ ለማሰብ ሞክሬ ደከመኝና ተውኩት ፡፡ እንዲህ አይነት
  በእሳት የመጫወት ያህል ታሪካዊ ስህተት መፈጸም የጀመሩት ገና ወደ መንበሩ ከመድረስዎ መሆኑ ደግሞ እጅጉን የመዳረሻዎን ውጤት አስቀያሚነት ያጎላዋል ፡፡ እጅግ ብዙ የብዙ ብዙ ለሆንን ለኛ የሃይማኖት ት/ት አስተምህሮ ለዚህ ያበቃንን ምርኩዛችንን ነጥቀው ጅብ ሊያስበሉን በመሆንዎ በአቅማችን እንዋጋዎ ዘንድ አለን፡፡
  እናም ለማስተዋል ጊዜው አልረፈደም እልዎታለሁ ብፁዕነትዎ፡፡

 21. የውብዳር February 4, 2016 at 11:51 am Reply

  ቅዱስ አባታችን አልልም! ምክንያቱም እንዲህ አይነት ቅድስና የትም ታይቶ አይታወቅምና፡፡ ታድያ ከምን ልጀምር ? እንጃ….!!!
  አስተያየት ለመስጠት አልወድም ፡፡ ምክር ለመስጠትም አቅመቢስ መሆኔን በቅጡ እንኳ የማላዉቅ ደካማነቴ ይታወቀኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ እንዲህ መትጋትዎ ለምን አንደሆነ ምክኒያት ሊሆንዎ ይችላል ብዬ ለማሰብ ሞክሬ ደከመኝና ተውኩት ፡፡ እንዲህ አይነት
  በእሳት የመጫወት ያህል ታሪካዊ ስህተት መፈጸም የጀመሩት ገና ወደ መንበሩ ከመድረስዎ መሆኑ ደግሞ እጅጉን የመዳረሻዎን ውጤት አስቀያሚነት ያጎላዋል ፡፡ እጅግ ብዙ የብዙ ብዙ ለሆንን ለኛ የሃይማኖት ት/ት አስተምህሮ ለዚህ ያበቃንን ምርኩዛችንን ነጥቀው ጅብ ሊያስበሉን በመሆንዎ በአቅማችን እንዋጋዎ ዘንድ አለን፡፡
  እናም ለማስተዋል ጊዜው አልረፈደም እልዎታለሁ ብፁዕነትዎ፡፡ አቤቱ ቤተከርስቲያናችንን በጽኑ ጠብቅልን፡፡

 22. Anonymous February 4, 2016 at 12:01 pm Reply

  ክርስቶስ ለሞተላት ለዕውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የደምና የአጥንት ዋጋ የከፈሉ ሰማዕታት እንዲሁም የፃድቃን ድካም ብርታት ስለሚሆነን ድንግልን ይዘን ይህንን በቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የመጣ የዲያብሎስ ፈተና በድል እናልፈዋለን፡፡

 23. yewbdar February 4, 2016 at 12:02 pm Reply

  ቅዱስ አባታችን አልልም! ምክንያቱም እንዲህ አይነት ቅድስና የትም ታይቶ አይታወቅምና፡፡
  አስተያየት ለመስጠት አልወድም ፡፡ ምክር ለመስጠትም አቅመቢስ መሆኔን በቅጡ እንኳ የማላዉቅ ደካማነቴ ይታወቀኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ እንዲህ መትጋትዎ ለምን አንደሆነ ምክኒያት ሊሆንዎ ይችላል ብዬ ለማሰብ ሞክሬ ደከመኝና ተውኩት ፡፡ እንዲህ አይነት
  በእሳት የመጫወት ያህል ታሪካዊ ስህተት መፈጸም የጀመሩት ገና ወደ መንበሩ ከመድረስዎ መሆኑ ደግሞ እጅጉን የመዳረሻዎን ውጤት አስቀያሚነት ያጎላዋል ፡፡ እጅግ ብዙ የብዙ ብዙ ለሆንን ለኛ የሃይማኖት ት/ት አስተምህሮ ለዚህ ያበቃንን ምርኩዛችንን ነጥቀው ጅብ ሊያስበሉን በመሆንዎ በአቅማችን እንዋጋዎ ዘንድ አለን፡፡
  እናም ለማስተዋል ጊዜው አልረፈደም እልዎታለሁ ብፁዕነትዎ፡፡

 24. Anonymous February 4, 2016 at 12:24 pm Reply

  ለደንቆሮ “የሃይማኖት አባት” አግባብ ያለው መልስ ነው፣ግን “አባ” ማቲያስ አይደለም ጆሯቸው ልባቸው ታውሯል ይብላኝላቸው። ?????????????? በጣም በጣም ያሳዝናል፡፡ ወይ አቅምን እና ደረጃን አለማወቅ፡፡ እባካችሁ ከአባቶች ወደ አባትነት የሚወስደውን ትምህርት ተ ማ ሩ!!!! ደግሞስ ማን ለማን በእንዴት አይነት ሁኔታ መጻፍ እንዳለበት ይጥፋብን ያሳዝናል፡፡ ይህን ይጠቅማል ብላችሁ ሼር የምታደርጉስ ዓላማችሁ ምንድን ነው

 25. Anonymous February 4, 2016 at 1:26 pm Reply

  LET US PRAYE FOR OUR BROTHERS AND SISTERS THE MEMBER OF MK WHO ARE BLIND FROM SEEING THE LIGHT OF TRUTH. MEMEBERS OF MK PLEASE BE AWARED AND STOP FROM KILLING YOUR MOTHER CHURCH BY DOING THIS AND PLEASE COME TO THE TRUTH AND DEAL WITH IT. OR PLEASE ADDRESS WHAT YOU WANT ? YOU VERY MUCH KNOW THAT YOU DO KNOW NOTHING ABOUT THE DOGMA AND CONNEN OF THE CHURCH.
  PLEASE SUPPORT YOUR MOTHER CHUCH
  MAY GOG BLESS YOU ALL

 26. Anonymous February 4, 2016 at 3:09 pm Reply

  my brothers, we know who you are and never ever do your Tehadeso on the ancient Ethiopian Orthodox Church. You know why? every problem has its own solution. You create problems because you are traders(negade). As far as you get money you try to sell the church but the church(GOD) is not trader like you and hence try to solve the problem. Mahebere kidusan is established to solve the problems not to sell. Therefore, what ever you shout no body listens rather keep silent and do their jobs.

 27. Anonymous February 4, 2016 at 4:41 pm Reply

  ማህበረ ቅዱሳን ለምን በጽሑፍ ምላሽ ሰጠ? ይህንን በማድረጉ ቤተክርስቲያንን እንደ ተዳፈረ አድርገው የሚያስቡ ካሉ ማኅበሩ የፃፈውን ምላሽ በሚገባ ካለ መረዳት ይመስለኛል፡፡ እኔ ከጽሑፉ መንፈስ እንደተረዳሁት ከፓትሪያርኩ ጋር ለመገናኘት ያለው አማራጭ ይህ ብቻ ይመስለኛል፡፡ ለምን ቢባል ከጽሑፉ እንደ ተረዳሁት እርሳቸውን ለማግኘት እና አባታዊ ቡራኬ ለመቀበል ስድስት ጊዜ ያህል ሞክሮ እንዳልተሳካለት አስፍሯል፡፡ ስለዚህ በዚህ መልኩ ለማስረዳት መሞከሩ ትክክል ነው የሚል አምነት አለኝ፡፡
  እርሳውም ቢሆኑ ትልቅ የቤተክርስቲያንን ጉዳይ ይዞ የሚሠራን ማኅበር ቀርበው አለማናገራቸው፣ መከተል ያለበትን አካሄድ ለማመላከት ፍቃደኛ አለመሆናቸው ክፍተኛ ትዝብት ውስጥ ሊከታቸው የሚችል ነው፡፡ እኔ እስከ ዛሬ ድረስ ለወደፊትም ማህበሩ የሚሠራቸውን ሥራዎች ቤተክርስቲያን እንደሠራች አድርጌ እንጂ የሆነ የተሰባሰበ በጎ አድራጊ ቡድን እንደሠራ አድርጌ አልቆጥርም፡፡
  ስለዚህ ቅዱስነታቸውን እምማጸነው እባኮዎትን ማኅበሩ እየሠራ ያለው ትውልድን የማዳን፣ ታሪክን የማቆየት፣ ቅርስን የመጠበቅ፣ ከሁሉም በላይ ቤተክርስቲያንን ለመርዳት በጎ ፍቃድ ያላቸው ምዕመናን ሊቆጣጠሩት እና ሊመለከቱት በሚችሉት መልኩ አስተባብሮ ለገዳማት እና ለአብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ማድረግ በመቻሉ በመጀመሪያ ደረጃ ቤተክርስቲያን ተጠቃሚ ብትሆንም ከዚያ በሻገር ደግሞ በአገሪቷ ልማት ውስጥ ገዳማት እና አድባራት ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያደረገ በመሆኑ የሚበረታታ እና ማንም ሊደግፈው የሚገባ ጉዳይ ስለሆነ ቀርበው ያማክሩት፣ ይገስፁት፣ ይሄ ይቀራል ለምን ለትሠሩ አልቻላችሁም እንዲሉ ነው፡፡ ይህ መሆን ቢችል ኖሮ ቅዱስነታቸው በርቀት በሚያውቁት፣ ማኅበሩ የሚሠራው ሥራ ፀሐይ የሞቀው በመሆኑ ሕዝብ በሚገባ በሚያቀው ነገር ላይ ተቃራኒውን ጽፈው የሕዝብ አፍ ውስጥ ባልገቡ ነበር፡፡ አሁንም ከትናንት ቢዘገዩም ከነገ መቅደም ስለአለባቸው ልጆቹን አቅርበው ገስፀው ቤተክርስቲያንን ሊጠቅም ወደሚችል ሥራ ውስጥ መግባት መቻል አለባቸው ስል ቡራኬያቸው ይድረሰኝ እያልኩ ነው፡፡
  የሰላም ጊዜ እግዚአብሔር ያምጣልን፡፡

 28. Anonymous February 5, 2016 at 2:02 am Reply

  salelen kedist egzaw mharen yesses crestos !! men mataben abatachen tamwale sabale ymwsdach atwe end ebakecheh eneradan enastamachew btabachew endzh yhnwalew belaw mamen ychegral kadam blew tngerew neber ymsachew ataw new!! egzaw egezabher amlek gatachen ndhanetachen yesses crestos ldengel Mary amen ysthaten yasrat ager khare tk tabkelen amem !!

 29. Anonymous February 5, 2016 at 4:35 am Reply

  ማህበረ ቅዱሳን ለምን በጽሑፍ ምላሽ ሰጠ? ይህንን በማድረጉ ቤተክርስቲያንን እንደ ተዳፈረ አድርገው የሚያስቡ ካሉ ማኅበሩ የፃፈውን ምላሽ በሚገባ ካለ መረዳት ይመስለኛል፡፡ እኔ ከጽሑፉ መንፈስ እንደተረዳሁት ከፓትሪያርኩ ጋር ለመገናኘት ያለው አማራጭ ይህ ብቻ ይመስለኛል፡፡ ለምን ቢባል ከጽሑፉ እንደ ተረዳሁት እርሳቸውን ለማግኘት እና አባታዊ ቡራኬ ለመቀበል ስድስት ጊዜ ያህል ሞክሮ እንዳልተሳካለት አስፍሯል፡፡ ስለዚህ በዚህ መልኩ ለማስረዳት መሞከሩ ትክክል ነው የሚል አምነት አለኝ፡፡
  እርሳውም ቢሆኑ ትልቅ የቤተክርስቲያንን ጉዳይ ይዞ የሚሠራን ማኅበር ቀርበው አለማናገራቸው፣ መከተል ያለበትን አካሄድ ለማመላከት ፍቃደኛ አለመሆናቸው ክፍተኛ ትዝብት ውስጥ ሊከታቸው የሚችል ነው፡፡ እኔ እስከ ዛሬ ድረስ ለወደፊትም ማህበሩ የሚሠራቸውን ሥራዎች ቤተክርስቲያን እንደሠራች አድርጌ እንጂ የሆነ የተሰባሰበ በጎ አድራጊ ቡድን እንደሠራ አድርጌ አልቆጥርም፡፡
  ስለዚህ ቅዱስነታቸውን እምማጸነው እባኮዎትን ማኅበሩ እየሠራ ያለው ትውልድን የማዳን፣ ታሪክን የማቆየት፣ ቅርስን የመጠበቅ፣ ከሁሉም በላይ ቤተክርስቲያንን ለመርዳት በጎ ፍቃድ ያላቸው ምዕመናን ሊቆጣጠሩት እና ሊመለከቱት በሚችሉት መልኩ አስተባብሮ ለገዳማት እና ለአብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ማድረግ በመቻሉ በመጀመሪያ ደረጃ ቤተክርስቲያን ተጠቃሚ ብትሆንም ከዚያ በሻገር ደግሞ በአገሪቷ ልማት ውስጥ ገዳማት እና አድባራት ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያደረገ በመሆኑ የሚበረታታ እና ማንም ሊደግፈው የሚገባ ጉዳይ ስለሆነ ቀርበው ያማክሩት፣ ይገስፁት፣ ይሄ ይቀራል ለምን ለትሠሩ አልቻላችሁም እንዲሉ ነው፡፡ ይህ መሆን ቢችል ኖሮ ቅዱስነታቸው በርቀት በሚያውቁት፣ ማኅበሩ የሚሠራው ሥራ ፀሐይ የሞቀው በመሆኑ ሕዝብ በሚገባ በሚያቀው ነገር ላይ ተቃራኒውን ጽፈው የሕዝብ አፍ ውስጥ ባልገቡ ነበር፡፡ አሁንም ከትናንት ቢዘገዩም ከነገ መቅደም ስለአለባቸው ልጆቹን አቅርበው ገስፀው ቤተክርስቲያንን ሊጠቅም ወደሚችል ሥራ ውስጥ መግባት መቻል አለባቸው ስል ቡራኬያቸው ይድረሰኝ እያልኩ ነው፡፡
  የሰላም ጊዜ እግዚአብሔር ያምጣልን፡፡

 30. Anonymous February 5, 2016 at 4:55 am Reply

  እናንተ ሶስተኛ ፓትርያርክ ለመግደል የምታሴሩ ክፎች

 31. solomon February 5, 2016 at 7:08 am Reply

  ቅዱስ አትናቴዎስ

  ከመንበሩ ከአምስት ጊዜያት በላይ ስደትና ግዞት የደርሰበት አባት።አርዮሳውያንን በጉባኤ ኒቅያ የክህደት ትምህርታቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ የራቀ መሆኑን አጥብቆ በመንገር እንዲረቱ ያደረገው ቅዱስ አትናቴዎስ ነው። ስለዚህ አርዮሳውያን በነፍሰ ገዳይነት፣ ሰው በመደብደብ፣ በፖለቲካ፣ በዝሙት ይኽን በመሳሰለው ነውር ሁሉ በሐሰት ቅዱስ አትናቴዎስን ከስሰውት ነበር። አርሳንዮስ የተባለውን ኤጲስ ቆጶስ ገድሎ ያሟርትበታል.፣መቃርስ የሚባል ካህን ደብድቧል፣ በንጉሡ ላይ ላመፁ ሽፍቶች ስንቅና ትጥቅ ያቀብላል በማለት ወንጅለውታል። ስሙን እንጂ መልኩን አይታ ለይታ ከማታውቀው ከአንዲት ሴት ጋር በገንዘብ ተመሳጥረው በጉባኤ መካከል ቅዱሱን አቁመውት ከክብር አሳንሶኛል በማለት እንድትከሰው አድርገዋል። የሚገርመው ግን ከቅዱስ አትናቴዎስ ጋር ከነበሩት አበው አንዱ ጢሞቴዎስ የተባለው ተነሥቶ “እስቲ እውነቱን ተናገሪ ድንግልናሺን ያጠፋሁት እኔ ነኝ? ከክብር ያሳነስሁሽ እኔ ነኝ? ቤትሽንስ አውቀዋለሁ ቢላት አትናቴዎስን ስሙን እንጂ መልኩን የማታውቀው ስለሆነ አዎን አንተ ነህ አለችው። (አቡነ ጎርጎርዮስ፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ 1978 ዓ.ም)።ቅዱስ አትናቴዎስ

  ከመንበሩ ከአምስት ጊዜያት በላይ ስደትና ግዞት የደርሰበት አባት።አርዮሳውያንን በጉባኤ ኒቅያ የክህደት ትምህርታቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ የራቀ መሆኑን አጥብቆ በመንገር እንዲረቱ ያደረገው ቅዱስ አትናቴዎስ ነው። ስለዚህ አርዮሳውያን በነፍሰ ገዳይነት፣ ሰው በመደብደብ፣ በፖለቲካ፣ በዝሙት ይኽን በመሳሰለው ነውር ሁሉ በሐሰት ቅዱስ አትናቴዎስን ከስሰውት ነበር። አርሳንዮስ የተባለውን ኤጲስ ቆጶስ ገድሎ ያሟርትበታል.፣መቃርስ የሚባል ካህን ደብድቧል፣ በንጉሡ ላይ ላመፁ ሽፍቶች ስንቅና ትጥቅ ያቀብላል በማለት ወንጅለውታል። ስሙን እንጂ መልኩን አይታ ለይታ ከማታውቀው ከአንዲት ሴት ጋር በገንዘብ ተመሳጥረው በጉባኤ መካከል ቅዱሱን አቁመውት ከክብር አሳንሶኛል በማለት እንድትከሰው አድርገዋል። የሚገርመው ግን ከቅዱስ አትናቴዎስ ጋር ከነበሩት አበው አንዱ ጢሞቴዎስ የተባለው ተነሥቶ “እስቲ እውነቱን ተናገሪ ድንግልናሺን ያጠፋሁት እኔ ነኝ? ከክብር ያሳነስሁሽ እኔ ነኝ? ቤትሽንስ አውቀዋለሁ ቢላት አትናቴዎስን ስሙን እንጂ መልኩን የማታውቀው ስለሆነ አዎን አንተ ነህ አለችው። (አቡነ ጎርጎርዮስ፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ 1978 ዓ.ም)።

 32. Anonymous February 5, 2016 at 7:57 am Reply

  Abatachin min nekachew yihon?abedu yihon endetenagerut?

  • anonymously February 5, 2016 at 12:28 pm Reply

   Alabedikum bilum sirachew ye ebidet new!!! Mahiberu Mel’s yesetew lewonbdewochuna le luterawyan tehadso new!!!

  • anonymously February 5, 2016 at 2:10 pm Reply

   Yemiweresew 3 kind tekul afer na Genet Mengiste semayat new ye betekinetu werobeloch na luterawyan tehadso mahiberu yedekemebetin liwerisu??? Kenitu mignot!!!?

 33. Anonymous February 5, 2016 at 10:25 am Reply

  እየሱስ ክርስቶስን ለማሳደድ የተፈጠረ ማህበር ፤ እየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሲሰበክ የሚያቃጥለው ማህበር የዲያቢሎስ ካልሆነ በቀር ። ሰማይ በደረሱ እዉነት መሠል ተረቶቹ ሕዝብን ማሳወሩ፥ የሁሉ ፈጣሪ የሆነው እግዚአብሔር መመለክ ሲገባው ፈጣሪ አማልክት የተባሉ ጣኦታትን በሕዝቡ ልብ ዉስጥ ማስቀመጡ ። በአጠቃላይ ማቅ ነዉረኛ ማህበር ነው።

  • ዳሞት February 6, 2016 at 3:30 pm Reply

   ለanonymous February 5,2016 at 10:25am
   ለመሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስን በስምና በቃላት ሳይሆን በእምነት( ሀይማኖት) ታውቀዋለህን? በእርግጥ ደፋር ነህና ያለ እምነት ሆነህ አዎ! አውቀዋለሁ እንደምትል ነው። ምክንያቱም ክርስቶስንም ጳውሎስንም አውቀዋለሁ ያለው የዲያቢሎስ ልጅ ነህና ነው። ዲያቢሎስና ልጆቹ ደግሞ አይደለም ስሙን መጥራት ጥቅስ(ቃላት) እየመዘዙ መፈታተንና መገዳደር ግብራቸው ነው። ሰይጣንና የግብር ልጆቹ አይደለም የክርስቶስ የሆኑትን ቀርቶ ክርስቶስንም ለመፈተን ወደ ኋላ የማይሉ ደፋር የቃላት ተዋጊዎች ናቸው። ሥለሆነም የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት ሳታውቅ በማስመሰል አሳዳጁ አሳዳጅ እያል ካለቤትህ ገብተህ ትከሳለህ።
   ለመሆኑ ክርስቶስን እያሳደደ ያለው ማን ነው? አንተና አንተን መሰሎች የቤተክርስቲያን እምነት ተፃራሪዎች አይደላችሁምን። ጳውሎስ በሳዖልነቱ ዘመን ያሳድድ የነበረው እኮ እውነተኛውን የክርስቶስ ወንጌልን ያስተምሩ የነበሩትን ነበር እኮ። የክርስቶስ የሆኑትን ቅዱሳን ጻድቃንኑ መጥላት፣ ማዋረድ፣ ጣዖታት ማለት፣ መቃወም ወዘተ እኮ ክርስቶስን መጥላት፣ ማዋረድ፣ መቃወም፣ ጣዖት ነው ማለት ወዘተ ነው። ምነው የቃሎ ትርጉም፣በስሙ ማመንና ስሙን መጥራት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሳይገባህና ሳታምን ኢየሱስ ኢየሱ ትላለህ። ስም በመጥራትና ቃላት በመደርደር ብቻ ማመንና እምነት አይደለም።
   እግዚአብሔር (ኢየሱስ ክርስቶስ) የመረጣቸውን፣ ያከበራቸውን፣ ድንቅ ስራውን የገለፀባቸውን ጣዖታት በማለት ለመሳደብ አፍህንም ከፍተሀል። ጣዖትና ታቦት የማትለይ ማስተዋል የጎደለህ። ምስለ ክርስቶስ፤ ምስለ ቅዱሳንኑን ከምስለ ጣዖት ለይቶ ለማየት የተሳነህ በአዚም የተያዝህ። ለመሆኑ ታቦት በሰማይ አለና ሰማይንም የጣዖት ቦታ ትለው ይሆንን? ሐዋርያቱ በአሥራ ሁለት ወንበር ተቀምጠው በመጨረሻው ዘመን ይፈርዳሎና የእናንተን ፍርድ አልቀበልም ጣዖት ናችሁ ትል ይሆንን? ለነገሩ የዛን ጊዜ ብርክና ፀፀት ያንቀጠቅጥኀል እንጂ በመዳፈር አፍ መክፈት አለና? የጠላሐቸው፣ የነቀፍሐቸው፣ ጣዖታት ብለህ የሰደብካቸው፣ ዝክራቸውን መታሰቢያቸውን የጣዖት ዝክር መታሰቢያ ነው እያልክ ያረከስካቸውን በአባታቸው ቀኝ ቆመው ስታይ ለአንተ ግን ጥርስ ማፏጨትና ለቅሶ ዋይታ ይሆናል። ሁሉን ማድረግ የሚችለውን አማለጅ ፍጡር እያልክ ያቀለልከው፣ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል ያለውን ቅዱሳኑን በማሳደድ ያሳደድኸው፣ ማመንና መዳን ኢየሱስ ኢየሱ በማለት መስሎሎህ ኢየሱስ ኢየሱስ እያልክ በስሙ የተዘባበትህበት፣ በስሙ ድውይ አንካሳ ፈወስን እያልክ ያላገጥህበት በዛች በፍርድ ቀን ሂዱ እናንት አመፀኞች ሲል ሥምህን ጠርተን ፣ በስምህ ታምራት አድርገን ብትል መልሶ አላውቃችሁም ይልሀል።
   እናም ወዳጄ፦ ሲጀመር ካለቤትህ ገብተህ የሌላውን ቤተ መበጥበጥ ትክክል አይደለም። ከዛም ኢየሱስ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ ክርስቶስ በማለት ማመን ፣መታመን ፣ መዳን አይደለም። “አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ ” የሚለው ኀይለ ቃል በመጀመሪያ ይግባህ ተረዳው።

   • Anonymous February 11, 2016 at 2:14 pm

    እግዚአብሔር ይባርክልን! ቃለ ህይወት ያሰማልን!

 34. Anonymous February 5, 2016 at 12:33 pm Reply

  እግዚአብሄር ማህበራችንን ጠብቅልን!!!

 35. Anonymous February 5, 2016 at 7:49 pm Reply

  Amazing!! MK! you have been studying a lesion of Satan for the last 23 years. that’s why have been accusing the leaders of the church. specially, the Patriarchs, bishops and archbishops as well as the scholars of the church. MK, Think your time and your satanic power is determinate. And the blood of the innocent scholars and preachers which was and is shed by you is heard now by the Lamp of God which is the King of kings Jesus Christ.
  MK. Do not afraid when you hear the Holy name of our Lord and you have to know you much bitter than Tehadso and you are the number one enemy of the orthodox Tewahdo Church.

  • Anonymous February 7, 2016 at 5:37 am Reply

   Yasazinal lij abatun yemisadebbet zemen medresachin

   • anonymously February 7, 2016 at 9:49 am

    Debidabew yerekekew be “aba” serekena bene hama new!! Papasu anibew lemechres ye Ginbot Sinodos yidersibachewal!!!?

  • Henock Tamirat February 8, 2016 at 3:26 pm Reply

   Everyone knows who you are and why you write this. Can you mention a single moment where and when MK insults fathers of the church. You lair, father of lies and it is clear where you are from.

 36. Firew k t February 7, 2016 at 4:13 pm Reply

  why does ‘ MK ‘ send copies of the letter to entities outside the church? While ‘MK’ is doing a good job of shepherding our church from the wolf pack it is not advisable to be confrontational ;and why invite outsiders into a domestic dispute ????

 37. Anonymous February 7, 2016 at 9:31 pm Reply

  get out from the church son of the evil one, how you are you dare to say kind of this word to the holy patriarch?

 38. Henock Tamirat February 8, 2016 at 3:04 pm Reply

  ሲጀመር ፓትርያርኩ እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ ለዚህ ሁሉ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጭምር በግልባጭ ማብረራቸው እንዴት ይታያል? ለኔ በጣም ወረዱብኝ፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ እንደመሆናቸው ማህበሩን መገሰጽ ካልሆነም መቆንጠጥ ይችሉ የለም እንዴ?? ከዚህ ሁሉ ዉንጀላቸው ስረዳ ማህበሩን እንደ ባላንጣ ያዩት ይመስላሉ፡፡ ለማህበሩም ተደጋጋሚ የአነጋግሩን ጥያቄ ምላሽ አለመስጠታቸውና ከአንድ ወገን የሚመጣን ክስ ብቻ የሚሰሙ እንዲያውም ….፡፡
  ማህበሩ በፓትርያርኩ ላይ እንዲህ አቻዊ መልስ መስጠቱ ቢከብድም ሲወነጀልና ውንጀላውም ትክክል አለመሆኑን ለማስረዳት እድሉን ሲያጣ ተገቢውን መልስ መስጠቱ ህዝብና በግልባጭ ያወቁ አካላት ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃን እንዲያገኝ ያስችላልና ትክክል ነው እላለሁ፡፡ ማህበረ ቅዱሳንን ለ20 ዓመታት ያህል አውቀዋለሁ፡፡ ከትምህርቱና ከአገልግሎቱም ከተጠቀሙ በመቶ ሽዎች ከሚቆጠሩ በከፍተኛ ትምህርት ካለፉት ወጣቶች (የአሁን ጎልማሳ) አንዱ ነኝ፡፡ በፍጹም የቤተክርስትያን ቀኝ እጅ እንደሆነ ይሰማኛል፤ በተለይም ሰርጎ ገብ አጽራረ ቤተ ክርስትያንን በትምህርተ ወንጌል በመዋጋትና መሠሪ ሥራዎቻቸውን በማጋለጥ፡፡ የምንኩስና ቆብ አድርገው በቤተክርስትያን ውስጥ ሰርገው በመግባት ስንት ደባ የፈጸሙትንና በኋላም በፕሮቴስታንት አደራሾች ተገኝተው እየዘለሉ ሲጨፍሩ የነበሩ የበግ ለምድ ለባሾች የሃሰት መነኮሳትን በቪዲዮ ማስረጃ ጭምር ለቅዱስ ሲኖዶስ በማቅረብ ተወግዘው እንዲለዩ ያደረገ ማን ነው? ማህበረ ቅዱሳን እኮ ነው!!! ማህበረ ቅዱሳን የሰራቸውን በጎ ስራዎችና መንፈሣዊ አገልግሎቶች አሁን ዘርዝሬ አልዘልቅም፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: