በደብረ ብርሃን በሊቀ ጳጳሱ መኖርያ ቤት ቦምብ ፈነዳ፤ “በሊቀ ጳጳሱ እና በአስተዳደራቸው ላይ ጫና የመፍጠር ዓላማ ያለው ነው”/የሀገረ ስብከቱ ምንጮች/

 • ፖሊስ አምስት ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያካሔደ ነው
 • ከደረጃቸው ዝቅ የተደረጉት የሀገረ ስብከቱ ሓላፊ ይገኙበታል
 • አማሳኞች፣ ጠንቋይ አስጠንቋዮችና መናፍቃን ፈተና ኾነዋል

(ሰንደቅ፤ ረቡዕ፤ ጥር ፲፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

His Grace Abune Ephrem

ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፤ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የደብረ ብርሃን መኖርያ ቤታቸው፣ ታኅሣሥ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ምሽት ቦምብ መፈንዳቱ ተገለጸ፡፡

በመንበረ ጵጵስናው የሊቀ ጳጳሱ መኖርያ በሚገኘው ዕቃ ቤት አጠገብ የፈነዳው ቦምቡ፣ በብፁዕ አቡነ ኤፍሬምም ኾነ በሌላ ሰው ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም፡፡

ከፍተኛ ድምፅ የተሰማበት የፍንዳታው ስፍራ ጉድጓድ ፈጥሮ የሚታይ ሲኾን የዕቃ ቤቱ መስኮቶች ረግፈዋል፤ በመንበረ ጵጵስናው አጠገብ በሚገኘው የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የሊቀ ጳጳሱ ቢሮ መስተዋቶችም ተሰነጣጥቀዋል፡፡

የከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት፣ አምስት የሀገረ ስብከቱን ሓላፊዎች እና ሠራተኞች ታኅሣሥ 27 እና ጥር 3 ቀን በቁጥጥር አውሎ ምርመራ እያካሔደ መኾኑ ተጠቅሷል፡፡

የሰው ኃይል አስተዳደር ክፍል ሓላፊው ቀሲስ አስቻለው ፍቅረ፣ የሕግ ክፍሉ መምህር አክሊል ዳምጠው፣ ኹለት የጥበቃ ሠራተኞች እና አንድ የሊቀ ጳጳሱ የቅርብ ዘመድ በአስተዳደሩ ፍ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት በፖሊስ ቀርበው ከ7 እስከ 10 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡

ፍንዳታው በተከሠተበት ወቅት፣ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የልደትን በዓል ለማክበር በመርሐ ቤቴ እንደ ነበሩ የሀገረ ስብከቱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ድርጊቱ “የማስፈራራት ዓላማ ያለው ነው፤” ያሉት ምንጮቹ፥ ከክሥተቱ ኹለት ሳምንት በፊት በሊቀ ጳጳሱ የዝውውር ርምጃ የተወሰደባቸው የአስተዳደር ክፍሉ ሓላፊና ሌሎች የጥቅም ግብረ አበሮቻቸው በብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ እና በአስተዳደራቸው ላይ ጫና ለመፍጠር ያቀዱበት ሳይኾን እንደማይቀር ጠቁመዋል፡፡

በአስተዳደር ጉባኤ ታይቶ በሊቀ ጳጳሱ የጸደቀ ነው በተባለው ውሳኔ÷ በሙስና፣ በባለጉዳዮች እንግልት እና በጠንቋይ አስጠንቋይነት ክፉኛ የሚተቹት የሀገረ ስብከቱ የሰው ኃይል አስተዳደር ክፍል ሓላፊ ቀሲስ አስቻለው ፍቅረ ከደረጃቸው ዝቅ ተደርገው ወደ ስታቲስቲክስ ክፍል ባለሞያነት መዘዋወራቸው ታውቋል፡፡

በሙስና፣ በመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ አስተምህሮንና ሥርዓትን በሚፃረሩ የኑፋቄ አካሔዶች ገዳማቱን በማተራመስ እና በጠንቋይ አስጠንቋዮች ሳቢያ ከወረዳ ቤተ ክህነት፣ ከአገልጋዮች እና ከምእመናን በርካታ ምሬቶች እና አቤቱታዎች ለብፁዕነታቸው እና ለጽ/ቤታቸው ሲቀርቡ የቆዩ ሲኾን ከሰላም አኳያም አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው የዞኑ አስተዳደር ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጧል፡፡

Abune_Ephrem
በጸሎተኛነታቸው እና በአባትነታቸው ተወዳጅ የኾኑት የዕድሜ ባዕለጸጋው ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፣ ሀገረ ስብከቱን በሊቀ ጳጳስነት ሲመሩ ከ፳ ዓመታት በላይ ማስቆጠራቸውን ያስረዱት ምንጮቹ፣ የተቃጣባቸው አደጋ፣ “በግል ጥቅም ኅሊናቸው ከታወረና ለመናፍቃን ውስጣዊ መዋቅራዊ ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ህልውና አሳልፎ ከመስጠት ወደ ኋላ ከማይሉ አካላት በቀር በሌላ በማንም ሊታሰብ አይችልም፤”  በማለት በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዐዋዲ ደንቡ መሠረት፣ የሀገረ ስብከት ዋና ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ለሚገኘው የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚ አካል ነው፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሾመው ሊቀ ጳጳሱ፣ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት መሪና ተጠሪ ሲኾን ለአስተዳደሩም የበላይ ሓላፊ ነው፡፡ የሰው ኃይል ቅጥር፣ ዕድገት፣ የሥራ ዝውውር፣ ደመወዝ መጨመር እና ሠራተኛ ማሰናበት ሊፈጸምና በሥራ ላይ ሊውል የሚችለው በአስተዳደር ጉባኤው ታይቶ እና ተጠንቶ በሊቀ ጳጳሱ ጸድቆ መመሪያ ሲሰጥበት ነው፡፡

13 thoughts on “በደብረ ብርሃን በሊቀ ጳጳሱ መኖርያ ቤት ቦምብ ፈነዳ፤ “በሊቀ ጳጳሱ እና በአስተዳደራቸው ላይ ጫና የመፍጠር ዓላማ ያለው ነው”/የሀገረ ስብከቱ ምንጮች/

 1. Anonymous January 21, 2016 at 2:36 pm Reply

  ወይ ጉድ የነዚህ የመናፍቃን ዘመቻ እስከምን ድረስ እንደሆነ በጣም የሚያሳስብ ጉዳይ ነው::በያካባቢው ያለው ምዕመን በእግዚአብሔር ቸርነት ጠንክሮ መስራት አለበት ::እግዚአብሔር መናፍቃንን ያስታግስልን::

 2. Anonymous January 21, 2016 at 2:47 pm Reply

  ነገም እንዲሁ ነው የቤተክርስቲያኗ ህልውና አሳሳቢ እየሆነ መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን ያደቆነ……ሳያቀስስ …….አይቀርም የተባለው ለይስሙላ እንጂ ለእምነት የቆመ የለም ለነገሩ ሙት ወቃሽ አያድርገኝ ልተወውና ያሳደጉት ውሻ …….. ነው አሁንም ጥንቃቄ ካልተደረገ….

 3. Muluget Enawegaw January 21, 2016 at 5:47 pm Reply

  እንኳን አባታችንንና ሌሎች ሰዎችም ቢሆን እግዚአብሔር ክፉአቸውን አላሰማን፡፡ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንንና ምእመኖቿን አገልጋየቿን ይጠብቅልን፡፡ ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን፡፡ በአሁን ሰዓት ተግተን የምንጸልይበትና በፊቱ የምንማልድበት ዘመን እንደሆነ ነው እኔ በበኩሌ የተገነዘብኩት፡፡ ይህንን ዘመን በቃልኪዳን የሚረከብ ጻድቅ እንደጠፋ ነው ይህ የሚያሳየውና እግዚአብሔር ቅዱሳኑን ያስነሳልን፡፡ እኛንም ያበርታን፡፡

 4. ዳሞት January 21, 2016 at 5:59 pm Reply

  የዘመኑ መጨረሻ ምልክቶች
  እግዚአብሔርን የሚፈራና ለቤተክርስቲያን ህግና ሥርዓት የሚገዛ ሲጠፋ ይህንና ከዚህም የከፋ አሥጨናቂና ዘግናኝ የጠላት ተግባራት መፈፀማቸው የማይቀር ነው። ለራስህና ለመንጋው ተጠንቀቅ የተባለው እረኛው አባት በጎችን እያባረረ ተኩላዎቹን በበጎች በረት ሊያጎር ቃልኪዳንን ከተኩላዎች ጋር አደረገ። እሥክሞት እዋጋዋለሁ እያሉ ከመንፈሳዊ አባት በማይጠበቅ ቃላት ተኩላዎችን አሥፈነደቁ። ታዲያ ተኩላዎችም ሆኑ የዚህ አለም ተድላና ውበት አማሏቸው ህልም ተስፋቸው ሁሉ ገንዘብ የሆኑት አይደለም ቦንብ ሚሳኤል ቢተኩሱ ምን ያስደንቃል። ማንን መፈርተው! እግዚአብሔርን አይፈሩ። ነውርና ሐፍረት አይሰማቸው። እግዚአብሔርን ሥለ ማይፈሩ እምነት የላቸውም። እምነት አለን የሚሉ ቢሆን እንሿን ምናልባት አፋቸውና ላያቸው ይመሥል ከሆነ እንጂ ውስጠ ሌላ ናቸው። አባት ለእውነትና ከእውነተኞች ጋር ቆሞ ክፉዎችን አይገስፅ አያወገል አይዟችሁ አለ እንጂ። ታዲያ ይች ቤተክርስቲያ፣ ይች እምነት፣ የዚች ቤተክርስቲያን እምነት አማኞች በነዚህ ለመዳን ሳይሆን ለፍር በተጠበቁት ከኀዲያንና ገንዘብ ወዳጆች በቦንብ መፍረስ መገደላቸው ምን ያስደንቃል። ማንን ፈርተውና አፍረው? ፍሬያቸው ጥፋትና ገንዘብን መውደድ እኮ ነው።
  በድረ-ገፆቻቸው ከጳጳስ እሥከ ሰንበት ተማሪ ና ምዕመን ነገር እየሰሩ ታሪክ እየፈጠሩ ባለ ብዙ ሚስት ዘማዊ፣ ነፍስ ገዳይ ደም አፍሳሽ፣ አድር ባይ ተላላኪ፣ መሸተኛ ሰካራም፣ ያልተማረ የሰው ጭንቅላት ሰራቂ፣ እረ አይነገር ይብቃኝ ሥም የሚያጠፉባቸው ፀያፍ ቃላቶቻቸውና ስድቦቻቸው አይነት ተዘርዝረው አያልቁምና። ለማረጋገጥ ግን በተለይ “አባ ሰላማ” የተባለውን ድረ- ገፅ ተመልከቱ። እና ይህን ሁሉ ሥም ማጥፋትና ሥድብ ሲያደርጉ አይዟችሁ የተባሉ እሥኪመሥል ዝም ሲባሉ፤
  አሁን ብሶ ወደ ቦንብ ማፈንዳት።
  ክርስትና በቀለኝነት እንዳልሆነ አምናለሁ። ግና ጠላት በቤተክርስቲያንና በአማኞቿ ሲዘብትና መርዝ ሲረጭ ግን ክርስትና ጠላትን መውደድና መታገስ ነው እያሉ የክርስቶስን ቤተክርስቲያንንና ህብን በተኩላ ማስበላት ግን ለኔ ትክክል አይመሥለኝም። ሊታረሙ ፣ሊገሰፁ፣ ሊወገዙና በህግ ተጠይቀው ከክፉ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማድረግ ይገባል ባይነኝ።
  መምህር፣ መጋቢ፣ ዲያቆን፣ ዘማሪ ወዘተ እየተባሉና እራሳቸውንም እያደረጉ በቤተክርስቲያኗ ማላገጣቸውና የጥፋት ተልሿቸውን በቃ ማለት ይገባል። ጌታ የአዳምን ዘር ሁሉ ለማዳን መጥቶ ሳለ ቤተ መቅደሱን ከሸቃጮች፣ ከሌቦች፣ ከማያምኑት ወዘተ ማጽዳቱን መዘንጋት የለበትም። “አላዓዛርን ከሞት ያስነሳው ማን ነው?” ብሎ ጠይቆ እግዚአብሔር ነው ሲባል እግዚአብሔር፣ ስላሴ ወደ ዛ ወደዚህ አትበሉ ” ኢየሱስ” በሉ እያለ ሥቶ የሚያስት፣ ግራ ተጋብቶ ግራ የሚያጋባ በመጋቢነት ማዕረግ ተኮፍሶ ወንጌልን የሚያወላግድ አይነቱ በቃህ ሊባል ይገባል። የኢየሱስን እግዚአብሔርነት የማያውቅ ኢየሱስ ኢየሱስ ባይ። የሳራን እርጂና የማያውቅ ሳራ ወለደችኝ ባይ። እኛ ባንኖር ይህ ህዝ ወድቆ ነበር እያለ እራሱን በአምላክ ቦታ ያስቀመጠ የሾመ።
  እና እነዚህ ሁሉ አይዟችሁ እየተባሉ ከቦንብ ሌላ ማድረጋቸው አይቀሬ ነው።
  አምላክ ሆይ አድነን!

  • Anonymous January 22, 2016 at 2:31 am Reply

   አባታችንን እንኳን አተረፈልን። ነገን አይውል ሁሉም የጁን ያገኘዋል። እኛ ግን እንህን የመሰሉትን አባት ከጎናቸው እንሁን። ወስብሀት ለእግዚአብሔር።

  • Anonymous January 22, 2016 at 5:53 am Reply

   Amlaka kidusan hoy yebetekrstiyanen yehagaren tifat atasayen becherenetih takulawen awtitah betihin atsida abetu EgziAbher hoy!!!

  • Anonymous January 22, 2016 at 6:30 am Reply

   AMEN,ADNEN GETA HOY!

 5. anonymously January 22, 2016 at 10:18 am Reply

  Yehama zemecha eko 127 ageroch beminoru ayhud lay neber ! Ended Aster subae enyaz!

 6. ቆሽቱ የበገነው/TheAngryEthiopian January 22, 2016 at 3:09 pm Reply

  ሐራ ተዋህዶች እስቲ ሰሜን ሸዋ ውስጥ ስላለው አዲስ የካቶሊክ የምልመላ ዘመቻ በዝርዝር ዘግቡልን። በአዲስ እቅድና መንገድ እየተስፋፉ ነው የሚል ወሬ ከዚህ በፊት ተሰምቶ ነበረ ። ነገር ግን ማንም በዚህ ሁኔታ ላይ የዘገበ የለም።

 7. Anonymous January 23, 2016 at 6:28 pm Reply

  Ibakachiw iwunet leketitegna Hayimanotachin betikikilegna tekorkarinet hulachin dirshachin iniweta .Hayalu Igziabiher Hagerachin, Hayimanotachin, Betekiristiyanachinina Agelgawochiwan yitebikilin.

 8. Anonymous May 10, 2017 at 12:54 pm Reply

  በጣማ አሳዛኝ ነዉ ባገራችን ተሰምቶ የማይታወቅ ነገር ነዉ እግዝሃብሄር ይመስገን አባታችንን በይወት ስላተረፈልን

 9. […] ቡድናዊ ጥቅምን ለማግኘትና ለማስጠበቅ፣ ሀገረ ስብከቱን እስከ ነፍስ ግድያ ያደረሰ “የትግል መስክ” በማድረግ አጠቃላይ ሰላማዊ አሠራሩን […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: