ፓትርያርኩ:“እስከምሞት እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ” ሲሉ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዛቱ፤ ኮሌጆች፥ ከተሐድሶ ኑፋቄ አንጻር እንዲፈተሹ በቅ/ሲኖዶስ የተወሰነውን የሚቃወሙትን አበረታቱ

Holy Synod Tik07 On Protestant Reformationቅዱስ ሲኖዶስ፡-

 • በምልመላ፥ የደቀ መዛሙርቱ የሃይማኖት ጥንካሬ እንዲታይ አህጉረ ስብከትን አስጠንቅቋል
 • በቅበላና በትምህርት ዝግጅትም፥ ጥራቱና የመምህራኑ ሃይማኖት እንዲፈተሽ ኮሌጆቹን አሳስቧል
 • አህጉረ ስብከቱ ጤናማ ተማሪ ቢልኩም፣ ተመርቀው ሲወጡ “ሌላ ሰው ኾነውና መስለው ነው”
 • በጤና የተላኩ ልጆች መናፍቃን ኾነው ሲመለሱ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል
 • እነማን እንደሚማሩባቸው፣ መምህራኑ እነማን እንደኾኑና መጻሕፍታቸው ሊመረመሩ ይገባል

*          *           *

ማኅበረ ቅዱሳን፡-

 • በየኮሌጆቹ፥ የተሐድሶ ኑፋቄን አስከፊ ደረጃ የሚያትቱ ጽሑፎችን በሚዲያዎቹ አስነብቧል
 • ከተማሪ ምልመላ ጀምሮ የአመራር፣ የክትትልና አያያዝ ድክመቶች በመንሥኤነት ተጠቅሰዋል
 • የኑፋቄው ተጽዕኖ ስለማየሉ የቀረቡት ገለጻዎች፣ በበቂ ማስረጃ መደገፋቸው ተገልጧል
 • ማስረጃዎቹ፥ በ1991 እና በ2004 በቅ/ሲኖዶስ በተላለፉ ውግዘቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል
 • በመተዳደርያ ደንቡ፣ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ትውፊትን የማስጠበቅ ተልእኮ ተሰጥቶታል

*          *           *

Aba Mathiasፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፡-

 • ማኅበሩን በፀረ ተሐድሶ እንቅስቃሴው ከሚከሡ የኮሌጆቹ ተቃዋሚዎቹጋ ትላንት ተወያይተዋል
 • ማኅበሩ እያስቸገረን ነው፤ በሚል “ከመንግሥት ጋር ተረዳድተን መጣል አለብን” ሲሉ አሳስበዋል
 • በአሜሪካ ጉብኝታቸው፣ ቤተ ክርስቲያንን ሊረከብ ትንሽ እንደቀረው መረዳታቸውን ገልጸዋል
 • “ወይ ማኅበሩ ይረከበናል፤ ወይ እኛ እንወርሳቸዋለን” ሲሉ የኮሌጅ ተቃዋሚዎቹን አበረታተዋል
 • ማኅበሩን፣ ደንብ አልባ እንዳደረጉት ጠቅሰው በቀጣይም፣ “የሚኾነውን እናደርጋለን” ብለዋል
 • ቅ/ሲኖዶሱን ለተጋፉ የኮሌጆቹ አካላት፣ አባቶችን በአድመኝነት በማማት እገዛ ጠይቀዋል

*          *           *

በኮሌጆቹ ስም የሚንቀሳቀሱት ሓላፊዎች እና ደቀ መዛሙርት፡-

 • ማኅበሩን፥ በፖሊቲከኛነት፣ በአሸባሪነት፣ በዘረኝነት፣ በደም አፍሳሽነት እና በኑፋቄም ከሠዋል
 • በቅ/ሲኖዶስ የተሰጠው ዕውቅና ተነስቶት በአሸባሪነትና በስም አጥፊነት እንዲከሠሥ ጠይቀዋል
 • የማኅበሩን፥ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስኮላርሽፕ“ኮሌጆቹን ለማዘጋት ያቀደበት ነው፤” ብለዋል
 • ያስመረቃቸውም ደቀ መዛሙርት፥ “ሙስሊሞች ይኹኑ አሸባሪዎች አይታወቁም” ሲሉ አፊዘዋል
Birhane Gebra tsadikan

ብዙዎች፥ በአካዳሚያዊ አቅሙና በማስተማር ክሂሉ “የኮሌጁ ኀፍረት” ነው፤ ይሉታል፡፡ በሓላፊነት ከተቀመጡ ሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑን እያደራጀ፣ በቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል – በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የማታ መርሐ ግብር ሓላፊው ብርሃኔ ገብረ ፃድቃን

በተለይ፣ አስተምረበታለኹ የሚለውን ማስታወሻ ጭምር በተማሪዎቹ እገዛ የሚያዘጋጀው አቅመ ቢሱ እና ቀንደኛ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑ አስተባባሪ ብርሃኔ ገብረ ፃድቃን፡-

 • “ከማኅበሩ ይከፈላቸዋል፤ ሙዝ ይገባላቸዋል” እያለ ብፁዓን አባቶችን ሲዘልፍ አምሽቷል

በጽሑፍ ባዘጋጀው መግለጫው፥ በአንድ በኩል ማኅበረ ቅዱሳንዕውቅናው ይነሳው እያለ በሌላ በኩል ደግሞ ማኅበሩን በፖሊቲከኛነት እየከሠሠ ለአባላቱ እና ለመንግሥት መልእክት ሲያስተላልፍ የነበረው የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ ዲኑ ተስፋይ ሃደራ፡-

 • “ቅዱስነትዎ፥ በሲኖዶስ ስብሰባዎች አጋዥ እያጡ ነው፤ እኔ 150 ተማሪ ይዤ መምጣት እችላለኹ፤” ብሏል፡፡

*           *           *

የኮሌጆቹ ታዛቢ ሓላፊዎች እና ብዙኃን ደቀ መዛሙርት፡-

 • ካልፈረማችኹና ካልተሰለፋችኹ በሚል በግዴታ ወደ ፓትርያርኩ ቢሮ እንዲገቡ ተደርገዋል፤
 • ለምሩቃን የደመወዝ ጭማሪ እንጠይቅ በሚል የፈረሙበት አቤቱታ ተለውጦ ለሌላ ቀርብዋል፤
 • ፓትርያርኩ ከከሣሾቹ ይልቅ፥ “የዐቅሜን ታግየዋለኹ፤ የሚሰማኝ አጣኹ” ሲሉ አቤቱተኛ ነበሩ፤
 • “በቅ/ሲኖዶስ የወሰኑበትን የተሐድሶ ኑፋቄን አሳሰቢነትና የደመወዙን ጉዳይ እንኳ አልጠየቁም፤”
 • “ሌሎችም አሉ፤ እነርሱንም ላነጋግራቸው አላሉም፤ ውይይት ሳይደረግ በአንድ ጊዜ ዳኛ ኾኑ፤”

 • ማኅበረ ቅዱሳን፥ ለቤተ ክርስቲያን እንደማያስፈልግ፣ ያለጥናት እንደተመሠረተና ዕውቅናም እንደሌለው ተናገሩ፤
 • ሊቃነ ጳጳሳቱንም፥ “በያንዳንዱ ይሔዱበታል፤ ያስጠኗቸዋል፤ አንድ ኹነው አድመው ይመጣሉ፤ እዚኽ አንድ አጀንዳ ሳነሣ ይንጫጫሉ፤ ራሴ ላይ ይወጡብኛል፤” በማለት አምተዋቸዋል፤
 • “አቋም ካላችኹ፣ ቆርጣችኹ ከተነሣችኹ እኔ ማኅበሩን እስከ ሞት ድረስ ነው የምታገለው፤ እስከምሞት ድረስ እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ፤” ሲሉ እነብርሃኔ አስጨበጨቡ፤
 • ትግሉም ከፍተኛ መሥዋዕትነት እንደሚጠይቅና ከፍተኛ ጦርነትም እንደሚከፈት አስገነዘቡ፤
 • “ወሳኝ አካላት ናችኹ፤ የሌላችኹበት አገር የለም” ብለው ከሣሾችን በማበረታታት በቀጣዩ የሲኖዶስ ስብሰባ፣ “ልታስረዱን ትችላላችኹ፤ ከመንግሥት ጋር ተረዳድተን መጣል አለብን፤” ሲሉ አሳሰቡ፤
 • የትግሉ ውጤት እና ፍጻሜም፥ “ወይ እነርሱ ይወርሱናል፤ ወይ እኛ እንወርሳቸዋለን፤ ወይ እርሱ ተረክቦ እንዲመራ ይደረጋል፤ ወይ እኛ እንመራለን፤” መኾኑን አስታወቁ፤
 • ‘ታጥቃችኹ ውጡ፤ እንጋደላለን’ እያሏቸው እኮ ነው፤ ጭፍን ጥላቻ ነው ያላቸው፤ በእውነቱ ለእርሳቸው ይታዘንላቸዋል፤ እኛም ሐሳብ ልንሰጥ ተነጋግረን እንዴት ብለን እንስጥ!
 • ደጋጎች በተቀመጡበት መንበር እንዲኽ ያሉ የወረዱ አባት ስናይ እርሳቸውን ነው፤ ምንም አይጠይቁም፤ አቋም የላቸውም፤ አስቀድሞ የተነገራቸውን ብቻ ነው መልሰው የሚያስተጋቡት፤ ተራ ንግግራቸው መልሶ የሚያስንቃቸው ራሳቸውን ነው፤ ቤተ ክርስቲያኗ፣ ምን ዕዳ ነው የጣለባት??? በጣም አዝነንና ንቀናቸው ነው የወጣነው!!!
Advertisements

71 thoughts on “ፓትርያርኩ:“እስከምሞት እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ” ሲሉ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዛቱ፤ ኮሌጆች፥ ከተሐድሶ ኑፋቄ አንጻር እንዲፈተሹ በቅ/ሲኖዶስ የተወሰነውን የሚቃወሙትን አበረታቱ

 1. Anonymous January 16, 2016 at 3:36 am Reply

  በስመአብ ወወልድ ወመነፈስ ቅዱስ አሀደ አምላክ አሜን
  መቼም እሰካሁን ብዙ መንፈሳዊ ስብሰባዎችን ተመልክቻለሁ አስተያየት ሲሰጠ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አመምላክ ብሎ የሚጀምር የለም ታዲያ ከመሪዎቻችን ተምረነው ነው ወይም ስጋዊነት የተሞላበት ስለሆነ የምናወጣቸው ጽሁፎችና አስተያየቶች ከዚህ የተለዩ አይደሉም ለዚህም ይመስለኛል ሥራችን ሁሉ መንፈሳዊነት እየተለየው ካሃይማኖተኝነት ይልቅ ወደ ፖለቲካው ያደላ የመሰለ ንግግርና ወሬ ብቻ የሆነው ምናለ አርፈን የየራሳችንን ስራ ብንሰራ ምዐመኑም ቢተጋ አባቶችም ምዕመኑን እያሥተማሩ ህዘቡ ወደህግዚአብሔር እንዲቀርብ ብታደርጉ እንደው በጭቅጭቅ ዳግም ምጻት መጥቶ በጠራረገን ያን ግዜ እንደየስራችን አግኝተን እንገላገላለን እንደው አሁንማ ቤተክርስቲያን ውሰጥ ሆናችሁ ህዝቡን ለተኩላ አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ስትሰበሰቡ የምታወሩት ሁሉ ስለወንጌል መስፋፋት ሣይሆን ስለወንጀል እውነት ስለአንደመሀበር እያወራችሁ የተፈቀደላችሁን ግዜ ሳትሰሩበት እንዳትጠሩ ፈራሁላችሁ ስንት የሚሰራ ነገር እያለ ሁል ግዜ ስለ ማህበር ቅዱሳን ማውራት ለመሆኑ ማህበረ ቅዱሳን ማነው አስከሚገባኝ አውቅና የሰጠው ሲነዶስ አይደል ታዲያ ሌላ ስራ የላችሁም ነው ቤተክህነት አካባቢ የተሰበሰቡ ሰዎች ዕቅድ አቅዶ ስራ መስራት የማይችሉ የወርደሞዝ ለማግኘት በሆነም ባልሆነመም ነገር እያወሩ ወር ቆጥሮ ደሞዝ መቀበልና ሙስና እየሰበሰቡ መኖር አር አራሳችሁን ተመልከቱ በተቀደሰ ስፍራ እረኩሰትን አትጠሩ በጣም የሚገርመው ስለማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ከነገረን እናንተ የቤተክህነት ሰዎች ያሰተዋወቃችሁለት ይበልጣል ሥራ ሥሩ ሥራ ወንጌልን ማስተማር አሁንም እላለሁ ወንጌልን ማስተማር አሁንመም እላለሁ ወንጌልን ማስተማር
  የገጠር አብየተክርስቲያናትን በአዲስአበባ ቤተክርስቲያኖች እነዲደገፉ ማስተሳሰር ዝምብሎ ቤተክህነት ውሰጥ ተቀምጦ መኖር መብቃት አለበት የተጠራችሁት ለአገልግሎት ስለሆነ በአገልግሎታችሁ እንጂ በማውራታችሁ ገንዘብ ታገኙበት እንደሁ አትባረኩበትም ለመባረክ እንስራ

  ልቦና የስጠን

 2. እዉነት ተገልጦልናል፡፡ January 16, 2016 at 12:50 pm Reply

  አህጉረ ስብከቱ ጤናማ ተማሪ ቢልኩም፣ ተመርቀው ሲወጡ “ሌላ ሰው ኾነውና መስለው ነው”
  በጤና የተላኩ ልጆች መናፍቃን ኾነው ሲመለሱ፣ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል

  ማንም ሰዉ በተረዳዉ እዉነት የመኖር መብት የለዉም አንዴ አንምነት የህሊና ጉዳይ ነዉ

 3. Anonymous January 16, 2016 at 3:21 pm Reply

  This is the last chance for the M.k group l cant understand the mission and the vision of
  M.K our college H.T.T.C is the proud of orthodox church and the teachers and the leaders are in work!!! that way M.K leaders are against the college!!!! l love you my college and all staff.

 4. Anonymous January 18, 2016 at 6:23 am Reply

  I am one of a proud graduate of Holy trinity theological collage and admirer of Mahibere – Kidusan’s work. Both institutions are established with the purpose of evangelizing the world, stand for faith,cannons and teachings of the apostles. Both are the fruits of Ethiopian orthodox tewahido church. I understand the aim of all this trash propaganda – that is to create antagonism between the two. That way the enemy will have a chance to penetrate and rip-off the believers.

  Dear brothers and sisters, our enemy is not Mahibere – Kidusan nor all disciples of HTTC are not heresies. Think of the first century of christian antiquity. Our church is now being attacked by enemy devil from inside and outside. Let’s stand together start fighting against our ego, corrupted clergy people, heretics teaching and Melekaweyan.

  If there is a problem with in MK let our fathers solved without inviting outsiders. My brothers in HTTC, I believe all of you are pure from all these false accusations, but try to see yourself and make yourself clearer as you should be.

  I am among the first graduates, during our time also there were four brothers /two from Addis and two from Tigray hageresebket/ who were allude to as Heresies/ menafekan. We did not eat for days if not for weeks to get a solution from bishops. Finally the bishops chaired by Abune Gerima concluded by saying, they did not find any wrong teachings.

  After graduation, the next day all of them except one, /that one person was Birhane Gebretsadkan/ disclosed themselves as protestant. By the way Birhane was enrolled for degree program but after two years he failed with all subjects then the administration decided to give him diploma before returning to his diocese. The other person was who failed to proceed but got diploma was his friend Fikre. Fikre was one of the four accused to be Menafek and after graduation he went back to his protestant church, I believe he is now living in Mekele leading local NGO.

  So please don’t be a cover for others which are not from us from the very beginning. Trust me, all of you who are not standing for the true cause of orthodox faces God’s judgement.

  May God bless all of us, May the prayer of saints, martyrs, angels and above all the blessing of our saint Virgin Mary be up on our orthodox tewahido church.

  • Anonymous January 20, 2016 at 10:17 pm Reply

   I am with you, bro. God bless you.

 5. Anonymous January 21, 2016 at 7:13 am Reply

  My friend, l am not with you!!!! l am with college stand!! hara the tehadeso betbalu yeshalal
  b/c patriaric yemetsadebu!!! werbloch mehonachiu ahun geban!!!!

 6. Anonymous January 21, 2016 at 11:43 am Reply

  Yegrmal!!! anti Tigray mehonachihu yasayal mekinaitu His Holiness abba matyas, Mhr. Tesfay and Mhr. Berhane becha nachew ytenagerut????????????? Betam koranbachew!!!! God bless you,Sertse yepawelos Dean men below yehon ????? ———————————————-!!!

 7. Anonymous January 26, 2016 at 10:36 pm Reply

  Egezabher yedefawete
  endeze asafare e ye Ethiopia tewahedo patryarek asafare zeregna

 8. Anonymous January 27, 2016 at 12:11 pm Reply

  Ante (Donkey) Mehayem ye mahbere kiduasan (dog) kinget PARTY zari yewtaw meglecha ye patriaric anbebe ante
  0 class!!! be kerb seat ante tedefaleh!!! boda!!!

 9. Anonymous February 8, 2016 at 2:10 pm Reply

  mahibere kidusan le betekiristiyan kemanim belaye yemidekim mahiber mehonu yeteserut sirawoch yasayalu.Egziabiher kidisit betekiristiyaninina mahibere kidusanini yitebikilin.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: