ማኅበረ ቅዱሳን: የግቢ ጉባኤያት አገልግሎቱን የሚያነቃቃ የሺዎች መርሐ ግብር ሊያካሒድ ነው

 • የትውልዱን አመለካከት እና ሥነ ምግባር በበጎ የሚቀርጹ አካላት ይሳተፉበታል
 • በግቢ ጉባኤያት አስተምሮ ያስመረቃቸው አባላቱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ደርሰዋል
Gibi Gubae Abinet Timhiret

ግቢ ጉባኤያት በአብነት ትምህርት

በእምነት ያሉትን የማጽናት እና አዲስ አማንያንን የማብዛት ሐዋርያዊ ተልእኮ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንክሮ ሊሠራበት እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል አጽንዖት በተሰጠበት ዓመት ላይ እንገኛለን፡፡ ከዚኹ ጋር በተያያዘ፣ የቤተ ክርስቲያን የህልውና መሠረት እና የደም ሥር የኾነው የስብከተ ወንጌል አገልግሎታችን ያለበት ውስንነት እና በመዋቅራችን የተንሰራፋው የመልካም አስተዳደር ዕጦት የተልእኮው ዐበይት ችግሮች እንደኾኑ ተጠቅሷል፡፡

ትውልዱ ከሃይማኖት እንዳይናወጽ፣ ከሥርዐት እንዳይወጣ፣ ታሪኩንና ባህሉን እንዳይዘነጋ ማድረግ የቤተ ክርስቲያን ድርሻ በመኾኑና ቤተ ክርስቲያን ያለስብከተ ወንጌል ልትስፋፋ እና ልትጠናከር እንደማትችል በማመን፣ ከማንኛውም ተግባር በማስቀደም የችግሩን ብዛት እና የትውልዱን አካሔድ ያገናዘበ በቂ እና መጠነ ሰፊ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በትጋት ለማዳረስ የጋራ አቋም ተይዟል፡፡ ምእመናንና ልጆቻቸው በዕውቀት እየበለጸጉ ከዘመኑ ጋር ቀድመው እየሔዱ ባሉበት ወቅት፣ ዘመኑን የሚዋጅ እና ቢቻልም ቀድሞ የሚገኝ የበሰለ አመራር የሚሹ በመኾናቸው፣ መልካም አስተዳደርን በቤተ ክርስቲያናችን በማስፈን በተቋማዊ ለውጥ ጎዳና እንድታልፍ የማድረጉ አስፈላጊነት ታምኖበታል፡፡

በተግባርም፣ ከራስ በላይ የቤተ ክርስቲያንንና የሀገርን ክብር እና ጥቅም በማስቀደም ሓላፊነትን በትጋት እና በታማኝነት የሚወጡበት፤ ንጹሐን የማይበደሉበት እና ሙስናን የሚዋጉበት አሠራር እና ቅን አገልጋይ የመፍጠሩ ተጋድሎ በአየጥቢያው በመቀጣጠሉ ብዙኃኑን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚያስደስት ተግባር ኾኖ ተገኝቷል፡፡ በዚኽ ረገድ በዘመኑ ትምህርት የበሰለው የኅብረተሰብ ክፍል ሃይማኖቱን ጠንቅቆ ያወቀ፣ በሥነ ምግባር የታነፀ፣ ሀገሩን የሚወድ እና ቤተ ክርስቲያኑን ለማገልገል በጎ ፈቃድ ያለው እንዲኾን ለማድረግ ማኅበረ ቅዱሳን ከኹለት ዐሥርት ዓመታት በላይ ሲያበረክት የቆየው ትውልዳዊ አስተዋፅኦ ተጠቃሽ ነው፡፡

ማኅበሩ፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን ተቋማቱ በሚገኙበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ባሉ የግቢ ጉባኤያት በማደራጀት የቤተ ክርስቲያንን እምነት እና ትምህርት፣ ሕግ እና ሥርዐት እንዲማሩና ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁም በአበው ቡራኬ በማስመረቅ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥር በሞያቸው፣ በዕውቀታቸው እና በገንዘባቸው እንዲያገለግሉ የማድረግ ተልእኮ በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀ መተዳደርያ ደንብ ተሰጥቶታል፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና በአህጉረ ስብከት ዓመታዊ ሪፖርቶች እንደተዘገበው÷ ማኅበሩ ለገዳማት፣ ለአድባራት እና ለአብነት ት/ቤቶች ያደረገው የሕንፃ ፕላን ሥራ፣ የፕሮጀክት ዝግጅት፣ የሥልጠና፣ የሕግ አገልግሎት እና የገንዘብ ድጋፍ፤ በልዩ ልዩ የብዙኃን መገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሰጠው የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት፤ እኒኽን አባላቱንና ይህንኑ ዓላማውን የሚደግፉ ገባሬ ሠናያትን በማቀናጀት ያስገኘው የመንፈስ ፍሬ ነው፡፡

ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በያዘነው ዓመት ማኅበሩ በሥሩ ያቀፋቸው የግቢ ጉባኤያት ቁጥር እስከ 400 እንደሚደርሱ የተጠቆመ ሲኾን አገልግሎታቸውን በበላይነት የሚያስተባብረው አካልም በዋና ክፍል ደረጃ መቋቋሙ ታውቋል፡፡ ዋና ክፍሉን በሰው ኃይል፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እና በአሠራር ሥርዐት ለማሳደግ ልዩ እገዛ እንደሚያስፈልግ የገለጸው ማኅበሩ፣ ከዛሬ ታኅሣሥ 20 ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀናት የሚቆይ የግቢ ጉባኤያት ሳምንት በማዘጋጀት አገልግሎቱን ለማነቃቃት እና የአባላቱን ትውልዳዊ መንፈስ ለማስተሳሰር የሚረዱ የተለያዩ መርሐ ግብሮችንና የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያካሒድ አስታውቋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ማጠናቀቂያም፣ ትውልዱን በሃይማኖት እና በሥነ ምግባር በማነጽ አስፈላጊነት ላይ ጠንካራ ግንዛቤ በማስጨበጥ እንዲኹም ከተቋማቱ መስፋፋት ጋር በተመጣጠነ መልኩ የተማሪዎቹን የተሳትፎ ቁጥር በማሳደግ÷ የዕውቀት ደረጃቸውን ያገናዘበ ትምህርት እንዲያገኙ ለማስቻል፤ መምህራንን በተሻለ ጥራት እና ቁጥር ለመመደብ፤ በቴክኖሎጂ የታገዘ የምክር አገልግሎት እና የተሞክሮ ልውውጥ ለማድረግ፤ ተማሪዎች የማኅበሩን መንፈሳዊ አገልግሎት ተረድተው ተተኪ እንዲኾኑ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ጠቃሚ ውጤቶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመልክቷል፡፡


(ሰንደቅ፤ ፲፩ኛ ዓመት ቁጥር ፭፻፴፰፤ ረቡዕ ታኅሣሥ ፳ ቀን ፳፻፰)

mahibere-kidusan-logoበከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶችን “በግቢ ጉባኤያት” በማደራጀት የሚያስተምረው ማኅበረ ቅዱሳን፤ አገልግሎቱን በማስፋፋት እና በጥራት በማሳደግ ትውልዱን ባለራእይ ለማድረግ ያለሙ የድጋፍ መርሐ ግብሮችን ከታኅሣሥ 20 – 26 ቀን 2008 ዓ.ም. እንደሚያካሒድ አስታወቀ፡፡

“መሰብሰባችንን አንተው” በሚል መሪ ቃል የግቢ ጉባኤያቱን ጥቅም የሚያስገነዝቡና ተሳትፎን የሚያነቃቁ የአንድ ሳምንት መሰናዶዎች እና የገቢ ማሰባሰቢያዎች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ እና በማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት የሚከናወኑ ሲሆን በውጤቱም አገልግሎቱን በሰው ኃይል፣ በገንዘብ እና በቁሳቁስ የሚያግዝና የሚያጠናክር አቅም ለማጎልበት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

ዛሬ፣ ታኅሣሥ 20 ከቀኑ 11፡30 በማኅበሩ ጽ/ቤት በሚከፈተው የፎቶ ዐውደ ርእይ መርሐ ግብሩ ሲጀመር፤ አባላቱ በሚማሩባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እምነታቸውንና ሥርዐታቸውን ለማወቅ በአቅራቢያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እና የሰንበት ት/ቤቶች መሰባሰብ ከጀመሩባቸው ከ1970ዎቹ መጨረሻ አንሥቶ የግቢ ጉባኤያቱን የአገልግሎት ሒደት እና ውጤት የሚያመለክቱ ትዕይንቶች ለእይታ እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡ ዐውደ ርእዩ ከ10 ሺሕ ባላነሱ ተመልካቾች እንደሚጎበኝ የጠቆመው አዘጋጅ ኮሚቴው፣ ከ2008 – 2010 ዓ.ም. በሚቆይ የሦስት ዓመት የቃል ኪዳን ሰነድ የገንዘብ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሠራበት ገልጿል፡፡

በመጪው ቅዳሜ፣ ግቢ ጉባኤያቱ ያሉበትን ደረጃ እና ተግዳሮት የሚመለከት ጽሑፍ እና ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ ውይይት በማካሔድ በአገልግሎቱ የሚሳተፉ በቂና ብቁ አባላትን ለማፍራት መታሰቡ ተጠቅሷል፡፡ በዕለቱ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ከቀትር ጀምሮ በሚደረገው ውይይት፣ በግቢ ጉባኤያቱ ተምረው ያለፉና ከአገር ውስጥ እና ከውጭ የተጋበዙ ከ2‚000 በላይ የቀድሞ ምሩቃን፣ የግቢ ጉባኤያትን ጅምር እና ሒደት በወቅቱ ከሚገኙበት ኹኔታ ጋር በማነጻጸር የሚመክሩበት ልዩ መርሐ ግብር ያካሒዳሉ፤ ተብሏል፡፡

መርሐ ግብሩ በማግሥቱ እሑድ ጠዋት በዚያው አዳራሽ ቀጥሎ፣ የቀድሞዎቹ ምሩቃን ከወቅቱ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች ጋር በመገናኘት ለሚነሡ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የልምድ ልውውጥ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡ በግቢ ጉባኤያቱ ተምረው በሕይወታቸው ለውጥ ያመጡ፤ ቤተ ክርስቲያንንና ሀገርን በማገልገል ላይ ያሉ የቀድሞዎቹ ምሩቃን ምርጥ ተሞክሯቸውን በአካል እና በፊልም በአርኣያነት የሚያካፍሉ ሲኾን፤ ይህም እስከ 10ሺሕ የሚገመቱ የውይይቱን ተሳታፊዎች የሚያነቃቃ እና ትውልዳዊ የአስተሳሰብ ትስስር የሚፈጥርበት እንደሚኾን ተገልጧል፡፡

በመርሐ ግብሩ ማጠናቀቂያ፣ እስከ 1ሺሕ5 መቶ የሚገመቱ የግቢ ጉባኤያቱን ተማሪዎች ወላጆች፣ የሰንበት ት/ቤቶችን፣ የመንፈሳውያን ማኅበራት ተወካዮችንና እንዲሁም የትውልዱን አመለካከትና ሥነ ምግባር ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ጋር ባልተቃረነ መንገድ የሚቀርፁ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶችን የሚያሳትፍ ውይይት ይካሔዳል፡፡ ሥነ ምግባርንና ሃይማኖትን በመጠበቅ ረገድ ትውልዱ ባሉበት ፈተናዎች ዙሪያ በሚቀርብ ጥናታዊ ጽሑፍና ዘጋቢ ፊልም ላይ የሚያተኩረው ውይይቱ፤ ለግቢ ጉባኤያቱ የሚያስፈልገውን የወላጆችና የአጋር አካላት ማኅበራዊ ድጋፍ ለማስገኘት የሚረዳ የጋራ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያስችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ 

ማኅበሩ ባለፉት 24 ዓመታት በግቢ ጉባኤያት አስተምሮ ያስመረቃቸው ወጣቶች ጠቅላላ ቁጥር ከ500 ሺሕ በላይ እንደሚደርስ የተጠቀሰ ሲኾን፤ በአኹኑ ወቅትም ከ369 በላይ የግቢ ጉባኤያትን በማቀፍ ከ350 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

*           *          *  

የግቢ ጉባኤያት በሰብአዊ ረድኤ ተግባር 

Alemaya Univ Tefenakayoch Eredata

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ: በድርቅ ተፈናቅለው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ለተጠለሉ ወገኖች የቁርሳቸውን ዳቦ ሲለግሱ

 የግቢ ጉባኤያት ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የገቢ ማሰባሰብ

arba mini 1999 tit lekema

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ: የጥጥ ለቀማ ለገቢ ማስገኛ

የግቢ ጉባኤያት ካሠሯቸው አብያተ ክርስቲያን

Gibi Gubae BeteK Sera

ዲላ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ

ከብላቴ ወታደራዊ ማሠልጠኛ የ1983 ዓ.ም. የግንቦት ልደታ ለማርያም አከባበር ትዝታዎች11561224105110651164112710411407የኬስፓኑ የግንቦት ልደታ ለማርያም ዝክር

Advertisements

7 thoughts on “ማኅበረ ቅዱሳን: የግቢ ጉባኤያት አገልግሎቱን የሚያነቃቃ የሺዎች መርሐ ግብር ሊያካሒድ ነው

 1. Anonymous December 31, 2015 at 12:26 pm Reply

  keber ygbaw lmdhnalem !! enantan dagazaw abat abwn gorgers yasrat msaret asyzaw bylfew nwero zare yzhe watat et Fanta men namber? bertw egezabher amlk ldengle Maryam asrat ystat agare Ethiopian slmytel enantan satan bartw ! bertw! ydengle Maryam melgana bereket aylych amen!!

 2. Alebachew Molla December 31, 2015 at 5:15 pm Reply

  እግዚአብሔር ማኅበረ ቅዱሳንን ይባርክ!!!

 3. ዳሞት December 31, 2015 at 5:58 pm Reply

  እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያንና ለምዕመኑ( አማኙ) ያዘጋጀውን ማህበር ማህበረ ቅዱሳንና ሌሎች የቤተክርስቲያኗ እውነተኛ ልጆችና አገልጋይ የሆኑትን ማህበራትና አገልጋዮችን በአባቶቻቸው በረከት እየባረከና እያስባረከ ሥራውን ይሰራልና። ጠላት ዲያቢሎስ መዳንን ጠሎቶ ሞትን ግን መርጦ መንደርተኛ ወሬና ሐሜትን ጨምሮም ሟርትን ያናፍሳል። ለእምነታቸው ለክርስቶስ መንግስ የቀኑት ደግሞ አምላካቸውን አምነው እምነታቸውን ማከናወንና ቤተክርስቲያቸው፣ ትውልዱንም ለማገልገል ይፋጠናሉ። እናም በርቱ በፀሎት ተግታችሁ መልካሙን አገልግሎታችሁን አከናውኑ። እናንተ ለእግዚአብሔር ሥትሰሩ ጠላት ምቀኛ እየተቃጠለ ብዙ ሐሜትና ሥም ማጥፋትን ያጋሳልና በዚህ ደሥ እያላችሁ ለእግዚአብሔር የሆነውን መልካሙን አገልግሎታችሁን በጽናት አከናውኑ።

 4. Anonymous January 1, 2016 at 7:51 am Reply

  ማኅበረቅዱሳን በግቢ ጉባኤያት፣በዋናው ማዕከል፣በየወረዳ ማዕከላት እና በባሕር ማዶ ለሚሠራቸው በጎ ሥራዎች ክብር አለኝ፡፡ለቤተክርስቲያን አስተዳደር ያለው ቅንነት የጎደለው አተያይ፣እኔ ብቻ ነኝ ቀናተኛ ሌላው ሌባና መናፍቅ ብቻ ነው፣እኔ የሌለሁበት ሁሉ ርኩስ ነው፣እኔን የሚተች ሁሉ መናፍቅና ካድሬ ነው ወዘተ አይነት አግላይ አካሄዱ ግን አይመቹኝም፡፡በቤተክርስቲያን ውስጥ በአስተዳደር ረገድ ሁሉም አካል በድክመቱ ይተቻል፡፡ሚዲያዎችም ትችቱን ይቀባበሉታል፡፡ይሄ ትክክል ነው፤የቀና አካሄድ ነው፡፡የማኅበሩ አካላት ግን ይሄ አካሄድ ለቤተክሕነት ብቻ ነው የሚሠራ የሚመስላቸው፡፡ስለዚህ እነሱን መተቸት አይታሰብም፡፡በሁሉም የሚዲያ አይነት ያላቸውን ኃይል ተጠቅመው የተቻቸውን ሁሉ በአንባገነንነት አንገት ያስደፋሉ፡፡ስለሆነም ይሕ በገሐድ እንዳይናገር የሚታፈን ትችት እየቆየ ውስጣዊ የመዋቅር ጥላቻ በማኅበሩ ላይ እየፈጠረ ነው፡፡ይሕ ጥላቻ የሚወገደው ለብቻ እየተፈናጠሩ በመደስኮር ሳይሆን መዋቅሩን ቀርቦ በፍቅር በማነጋገር፤ከነድክመቱ የኔ ነው ብሎ በመቀበል፣የራስንም ድክመት ለመንቀስ ከልብ በመሞከር፣በመዋቅሩ ውስጥ አያሌ የቀና ሃይማኖት ያላቸው ሰዎች እንዳሉ ባለመዘንጋት፣ኃላፊነት ከጎደለው ዘለፋ በመታቀብ፣ ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ዘንግቶ ዘወትር ስለራስ ብቻ እየሰበኩ ሌሎቹ የቤተክርስቲያኒቱ አካላት እንዳያዝኑ በማድረግ፣ ሁልጊዜ ምሬትና እሹሩሩ ከማድረግ በመቆጠብ ወዘተ ነው፡፡ ራሳችሁን ለገንቢ ትችት ድፍን አድርጋችሁ ሌላውን መዋቅር ተደራጅቶ መውቀር አያዋጣም፡፡ ማኅበሩ ጆሮዎቹ ለውዳሴ ብቻ የተቃኙ ወደ ግብዝነት ያጋደለ ማኅበር እየሆነ ነው፡፡ የአባል ብዛትና የከንቱ ውዳሴ ጋጋታ ራሱን እንዳይመለከት እያደረገው ነው፡፡ አስቡበት፡፡

  • Anonymous January 2, 2016 at 3:06 pm Reply

   በማስረጃ
   ሌባ ወይም መናፍቅ ካልሆነ ማኅበረቅዱሳን ማንንም አይተችም

 5. Damtew Ayele January 2, 2016 at 8:20 pm Reply

  It is a very good ldea every one must work hard for the success

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: