የሃይማኖት አባቶች የሰላም ጥሪ እንዲያቀርቡ ተጠየቁ

 • “የሽምግልና ሸንጎ”  እንዲቋቋም ሐሳብ ቀረበ

(አዲስ አድማስ፤ ዓለማየሁ አንበሴ፤ ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

በሀገሪቱ የሚታየው የእርስ በእርስ ግጭት እና ሕዝባዊ ዓመፅ ሀገር ከመበታተኑ በፊት የሃይማኖት አባቶች ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው የሰላም ጥሪ እንዲያቀርቡ ተጠየቁ፡፡

የመግባባት አንድነት እና ሰላም ማኅበር (ሰላም) ባወጣው መግለጫ፤ በሌሎች አገሮች የሚታየው የእርስ በርስ ግጭት ያስከተለው ጉዳት እና ቀውስ በአገራችን እንዳይፈጠር የሃይማኖት አባቶች የሽምግልና ሸንጎ በማቋቋም፣ በሀገሪቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪ እንዲያቀርቡ ተማፅኗል፡፡

ሀገር እና ዜጎች ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ጭንቀት ውስጥ የገቡበት አጋጣሚ አለመከሠቱን የጠቆመው ማኅበሩ፤ የሃይማኖት አባቶች በሀገሪቱ የሚታየው በዘር፣ በጎሣ፣ በሃይማኖት እና በቀዬ የመከፋፈል አባዜ፤ እስራት እና ስደት እንዲሁም፣ ግጭት እና ጦርነት መፍትሔ ይበጅለት ዘንድ እንዲተጉ ጠይቋል፡፡ በሃይማኖት አባቶች መካከል ያለው ግጭትም እልባት እንዲያገኝ ማኅበሩ ተማፅኗል፡፡

ኢትዮጵያ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖባት መቆየቷ ባይካድም ያልተቋረጠ ግጭት እያስተናገደች ባለችበት በአኹኑ ሰዓት “ፍጹም ሰላም የሰፈነባት አገር ናት፤” በሚል ከእውነታው መሸሽ ተገቢ አይደለም ያለው ማኅበሩ፤ “በሀገሪቱ የበቀል ርምጃ እየሰፋና እየከፋ በመምጣቱ ምክንያት ማብቂያ ወደሌለው የጥፋት ጎዳና እያመራን እንገኛለን፤” ብሏል፡፡

“አስከፊ የእርስ በርስ ግጭትና ሕዝባዊ ዓመፅ እንደሚመጣ አስቀድመን ስጋታችንን ተናግረን ነበር፤” ያለው ማኅበሩ፤ ኾኖም ለዕርቀ ሰላም ስንማፀን “በሀገሪቱ ፍጹም ሰላም ሰፍኗል” በሚል ሰሚ ጆሮ ሳናገኝ ቀርተናል፤ ብሏል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት በመተባበር ሀገሪቱ አኹን ከገባችበት አስጊ ኹኔታ ትወጣ ዘንድ እንዲጸልዩና የሀገር ሽማግሌዎች ሸንጎ ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረትም እገዛ እንዲያደርጉ ማኅበሩ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Advertisements

5 thoughts on “የሃይማኖት አባቶች የሰላም ጥሪ እንዲያቀርቡ ተጠየቁ

 1. Anonymous December 19, 2015 at 7:35 pm Reply

  sigemer yehaymanot abat yetebalut yeweyane kadrewoch nachew manem aysemachewem eskezare gazetenga sitaser sewe lay gef sisera yet hedew neber

 2. ዳሞት December 19, 2015 at 8:25 pm Reply

  የትኞቹ የሀይማኖት አባቶች ይሆኑ ስለሰላም ጥሪ የሚያደርጉት? ለሰላም፣ ለእውነትና ለፍትህ የሚጨነቁ በለበጣ ሳይሆን ከልብ የሆኑ አባቶች አሉ ብለን ብናስብ እንሿን እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀልና እኔ የዘራሁት ከሆነ ውጭ አይበቅልም ከሚል ትምክተኛና አመፀኛ አገዛዝ ተቀባይነትና መልካም ነገር ይጠብቃቸዋል ወይ?
  ሌላው መታወቅና መታወስ ያለበት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀጳጳስ የሆኑት በአንድ ወቅት ከአድባራት አለቆች ጋር አደረጉት በተባለው ውይይት ወይም ምክክር በሉት የሆነውን ማስታወስ ተገቢ ይመስለኛል። በተለይ መድረኩን ተቆጣጥረው ህሊና ቢስና ሐፍረት የለሽ ሆነው ምን እያሉ በህብሪት ይዘላብዱ እንደነበር መዘንጋት የለበትም። ይነገር የነበረው የንግግር ይዘትና የቤተክርስቲያኗ ተልኮ በእጅጉ የሚቃረኑ ሆነው አማኙን ማሳዘናቸው ሳያንስ መንበሩ ላይ ተኮፍሰው ግራና ቀኝ ቁልጭ ቁልጭ ይሉ የነበሩት እኔ ከእናንተ ጋ ነኝ በማለት ለዛ ትምክተኝነት፣ ጥላቻ፣ ዘለፋ፣ ሐሰት፣ እብሪተኝነትና በእርኩስ መንፈስ ለተሞላ ድንፋታ ድጋፍ በመስጠታቸው የብዙ አማኞችን ልብ የሰበረና አገት ያስደፋ ሆኖ አልፏል። ውይይቱም ሲኖዱሱ የማያውቀውና ያልጠራው በማናለብኝነት ህግ ተላልፈው በመንበሩ የተቀመጡት የጠሩት እንደነበርም ተሰምቷል።
  እና እንዲህ አይነት አባት በኢትዮጵያ ህዝብ የሆነውንና እየሆነ ያለውን ግፍ አውግዘው ለሰላም ከልብና ከእውነት ጥሪ ያደርጋሉ ማለት ለኔ አሉ ለመባል ይሉ ከሆነ እንጂ እነሱም በፕላን ተነድፎ በእቅድ ተቀምሮ እየተከናወነ ላለው ደጋፊና አስፈጻሚ ናቸው ባይ ነኝ።
  የእምነት ቦታችን አይነካ እውነት ለልማት ከተጨነቃችሁ ዳዋ የዋጠው ቦታ አለ ያሉትን ከፈራጆች ጋር ተደምረው ፀረ-ልማት ሽብርተኛ እያሉ ንፁሃንን ይፈርጁ የነበሩና ያሉ አባት እንዴት ነው ለአገርና ለህዝብ ተጨንቀው ለእርቀ ሰላም የሚነሱት!

 3. Anonymous December 20, 2015 at 5:41 am Reply

  Yehaymanot abat ale enida?

 4. Anonymous December 21, 2015 at 10:54 am Reply

  `በበረሃ ላይ ያሉት አባቶች ጸሎት ይርዳን፡፡ ሰዎች እባካችሁ ብልጥ እንሁን ወያኔ እንደሆነ በጥሩ አማርኛው እያማለለ ይህችን አገር ዳግም ወደ ማታንሰራራበት አዘቅት ውስጥ በመክተት የስልጣን ግዜውን ማራዘም ነው እባካችሁ ቀድሞ እንደነበርነው ተከባብረን መኖር አለብን፡፡ እደድሪቶ እየበጣጠሰ ህዝቡን አስፈጀው፡፡ አይ ዲሞክራሲ አላየንም ዲሞክራሲ ሲያወሩ ሰምተው ካወራን ይበቃን ነው መሰለኝ አስተዋይ ልቦና ይስጣቸው

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: