ፓትርያርኩ ለሕክምና ወደ አሜሪካ አመሩ

 • ከፍተኛ አካላዊ ድካም እና የሰውነት መዛል ታይቶባቸዋል
 • የበዓታ ለማርያምን በዓል በዲሲ መድኃኔዓለም ያከብራሉ

(ሰንደቅ፤ ረቡዕ፤ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

Abune-Mathias

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ አሜሪካ ማምራታቸውን የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች ገለጹ።

ከትላንት በስቲያ፣ ሰኞ ማምሻውን ከምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እና ሌላ ረዳታቸው ጋር የተጓዙት ፓትርያርኩ፣ ከኹለት ሳምንት ላላነሰ ጊዜ በሕክምና እንደሚሰነብቱ ተገልጧል።

ፓትርያርኩ በሀገር ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል የጤና ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን የጠቀሱት የዜናው ምንጮች፤ የሕመማቸው መንሥኤ ከከፍተኛ የደም ግፊት ጋር የተያያዘ መኾኑን ጠቁመዋል።

ባለፈው ሳምንት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አኲስም ጽዮን ማርያም ካቴድራል ተገኝተው የክብረ በዓሉን ጸሎተ ቅዳሴ በመሩበት ወቅት ከባድ የሰውነት መዛል እንደታየባቸው የዜናው ምንጮች ተናግረዋል፤ ከዚያም በኋላ የሚሰማቸው ከፍተኛ አካላዊ ድካም የዕለት ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ እክል እንደፈጠረባቸውና የተሻለ ሕክምና በማስፈለጉ ወደ አሜሪካ መጓዛቸውን አስረድተዋል።

የፓትርያርኩ የጤንነት ኹኔታ አሳሳቢ የሚባል እንዳልኾነ የገለጹ ሌሎች ምንጮች በበኩላቸው፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አጠቃላይ የጤና ምርመራቸውንና መደበኛ ክትትላቸውን እስከ ታኅሣሥ 13 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ አጠናቀው እንደሚመለሱ አስታውቀዋል።

[ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ሕክምናቸውን የሚከታተሉበት ግዛት አልያም የጤና ተቋም ተለይቶ ባይጠቀስም፤ ታኅሣሥ ሦስት ቀን የሚታሰበውን የቅድስት በዓታ ለማርያምን ዓመታዊ ክብረ በዓል በዋሽንግተን ዲሲ መካነ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው እንደሚያከብሩ ተመልክቷል፡፡]

Advertisements

11 thoughts on “ፓትርያርኩ ለሕክምና ወደ አሜሪካ አመሩ

 1. […] Source:: haratewahido […]

 2. […] Source:: haratewahido […]

 3. ዳሞት December 10, 2015 at 12:00 pm Reply

  እግዚአብሔር ይማራቸው ። ለቤተክርስቲያንና ለበጎች እውነተኛ እረኛና አባት ያድርጋቸው። ከዘረኛ አባትነት አላቆ ለእውነትና ለእውነተኞች የሚቆሙ ይሁኑ።

 4. Anonymous December 10, 2015 at 6:55 pm Reply

  redatachew man new?

  • ዳሞት December 10, 2015 at 11:18 pm Reply

   ንቡረ ዕብድ ኤልያስ ዘሙስና!

   • ዳሞት December 11, 2015 at 2:56 pm

    ዳሞት የሚለው የብዕር ሥም እኔ እየተጠቀምኩበት ያለ ነው። ለምን በዚህ ሥም የራሥህን አመለካከት ትፅፋለህ። እናም ፈቃድህ ከሆነ ሌላ ሥም ተጠቀም።

 5. ገ/ህይወት December 11, 2015 at 2:14 pm Reply

  E/r kesachew gar yihun.

 6. Anonymous December 11, 2015 at 3:04 pm Reply

  ante Ginbot 7 who are you!!!

 7. Anonymous December 13, 2015 at 2:23 am Reply

  እባካችሁ! የልባችሁን ከፃፋችሁ በኋላ አትፍሩ!!! “ለዳሞት”

 8. Anonymous December 25, 2015 at 7:46 am Reply

  DAMOT, ESKE MECHE TWASHALEH

  • ዳሞት December 25, 2015 at 10:17 pm Reply

   ለanonymous December 25,2015 at 7:46am

   ሥም የለህ ለአቶ ወይም ለወ/ሮ ብዬ አልመልስልህ። እንዲሁ “anonymous” እያልህ በተለያዩ ጊዜያት እውነት ሳይሆን ሐሰትን፤ ነገርን ገልጦ መናገርን ሳይሆን ክስና ሥድብን ጽፈሃል። አንተ በዚህ ድረገጽ ብቻ ሳይሆን የሰይጣን መልእክትና የእንክርዳድ መርጫ በነው እራሱን “አባ ሰላማ” ብሎ በሚጠራ ድረገጽም እኔን ለመተቸት፣ ለመክሰስ፣ ለመሳሰድ ጽፈሃል።
   ወዳጄ፦ በመጀመሪያ እራስህ ለማወቅና ለመሆን ሞክር። በድረገጽ ስድብና ሐሰተኛ ክስ አይጠቅምህም። ለእውነትና ለህሊናህ እንጂ የእንስሳት መገለጫ ለሆነው ዘረኝነትና ለክስ ለዛውም በሐሰት ከሳሽ ከመሆን እራስህን ነፃ አውጣ።
   ወዳጄ፦ የአመንኩበትን አስተያየት ጽፌያለሁ። ውሸት ጻፍክ ካልክ ውሸቱ የቱ እንደሆነ ግለጠው። ከዛ ውጭ የጻፍኩትን ጻፍኩ፤ ያልጻፍኩትን አልጻፍኩም የማለትና የብዕር ስሜን አትጠቀም ማለት ተገቢ ነው። የልባችሁን ከተናገራችሁ በኋላ፣ ፈሪና ሌላ አሉባልታህ ከተለመደው የሐሰት ክስነትና ስድብ ያለፈ አንድም እውነትና ፍሬ የለውም።
   ወዳጄ፦ ከከንቱ ክስና ስድብ እርቀህ የእግዚአብሔርን ቃል ተማር እንደ ቃሉም ኑር። ህይወት የሚሆንህና አርነት የሚያወጣህ እሱ ነውና። ውሸት አለ ካልህ ውሸቱ የቱ እንደሆን ጽፈህ አሳየኝ እንቶ ፈንቶውን ተወውና።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: