ኢ.ቢ.ኤስ: በቤተ ክርስቲያን ስም የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን በጊዜያዊነት አገደ፤በስም አለመጠቀሳቸው የአፈጻጸም ችግር ፈጥሮበታል

• በቅ/ሲኖዶስ በጸደቀ ደንብ የሚመራው የማኅበረ ቅዱሳን ፕሮግራምም መታገዱ እያነጋገረ ነው
• የመንፈሳዊ ዝግጅቶቹ የአየር ሰዓት በፕሮቴስታንታዊ ፕሮግራሞች ተጽዕኖ ሥር ሊገባ ይችላል
• ጉዳዩ ለምእመናን እና ለቤተ ክርስቲያኒቱ ግርታና ክፍተት እንዳይፈጥር ማኔጅመንቱ ጠይቋል
• የተወገዘው ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶው “ከሣቴ ብርሃን”የቴሌቪዥን ቅሠጣውን ሊጀምር ነው!!

*                *                *

ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ የመጀመሪያ መደበኛ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባው፣ በቤተ ክርስቲያን ስም ሽፋን እያደረጉ ያለዕውቅና እና ያለፈቃድ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት የሚያዛቡ መልእክቶችን በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን የሚያስተላልፉ አካላት፣ በሕገ ወጥ ድርጊታቸው እንዳይቀጥሉ በመወሰን ለጣቢያው እና ለሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤ እንዲጻፍ፤ በሕግም ክትትል እንዲደረግባቸው ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

የጎልማሶች እና ወጣቶች ማኅበራት ኅብረትን ጨምሮ ቀናዒ አገልጋዮች እና ማኅበረ ምእመናን በተጨባጭ ማስረጃ በማስደገፍ ሲያቀርቧቸው ከቆዩት አቤቱታዎች ለመረዳት እንደሚቻለው፣ ጉዳዩ የሚመለከተው ታዖሎጎስ እና ቃለ ዐዋዲ በሚል ስያሜ የሚጠሩ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ምንደኞች አቀንቃኝነት የሚመሩ ፕሮግራሞችን ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳው ላይ በተወያየበት ወቅትም በስም ተለይተው በአጽንዖት ሲጠቀሱ የነበሩት እኒኽ ኹለቱ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡

ከምልዓተ ጉባኤው መጠናቀቅ በኋላም ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አንዱ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዓማኑኤል ካቴድራል እና በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ሺሕ ምእመናን ባስተላለፉት አባታዊ ምክር፡- ቅዱስ ሲኖዶስ ሥራውን እየሠራ ነው፤ በተሐድሶዎችም ላይ ጠንካራ ውሳኔ አስተላልፏል፤ በኢ.ቢ.ኤስ የሚተላለፉ፣ ቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ያልሰጠቻቸው፤ ምእመኑን ለማታለል የእመቤታችንን ሥዕል ከአትሮንስ ሥር አድርገው ስለ እርሷ ግን አንዲትም ቃል የማይናገሩ፤ ፍጹም ፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ የሚያስተምሩ የተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆችን ተጠንቀቁ፤በማለት በግልጽ ተናግረዋል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በራሷም ኾነ በሌሎች የብዙኃን መገናኛዎች ስለምትገለገልበት ኹኔታ ዝርዝር መመሪያ የማውጣት ተግባርና ሓላፊነት የቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ከዚኹ ጋር ብፁዕነታቸው በወቅቱ አያይዘው እንደጠቆሙት፣ “አንድን የተበላሸ ነገር ለማስተካከል ጊዜ ይፈልጋል፤ ቤተ ክርስቲያንም የራሷን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን ስርጭት ልትጀምር በዝግጅት ላይ ናት፤”  ሲሉ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚዲያ ጉዳዮች ያሳለፈውን ሌላውን ዐቢይ ውሳኔ በማስታወቅ ምእመኑ የበኩሉን ጥንቃቄና እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

mahibere-kidusan-logo
ይህ ኹሉ መልካም ኾኖ ሳለ፣ ቅ/ሲኖዶሱ ስለ ሕገ ወጥ የሚዲያ ፕሮግራሞችና ኅትመቶች ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲኾን ለሚመለከታቸው አካላት የተጻፈው የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ደብዳቤ፣ ችግር ፈጣሪዎቹን በስም ለይቶ አለመጥቀሱ የአፈጻጸም እክል እንደፈጠረ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዚኽም ሳቢያ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ በጸደቀለት መተዳደርያ ደንብ፣ ትምህርተ ወንጌልን ከኅትመት ሚዲያዎች ባሻገር በኤሌክትሮኒክስ እና በመሳሰሉት የብዙኃን መገናኛዎች የማስፋፋት እና ወጣት ሰባክያንን የማበረታታት ዓላማና ተግባር የተሰጠው ማኅበረ ቅዱሳን፣ በየሳምንቱ እሑድ የሚያቀርበው ፕሮግራም ከኅዳር 19 ቀን ጀምሮ አብሮ በጊዜያዊነት እንደሚቋረጥ ታውቋል፡፡

የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ለፕሮግራሞቹ አዘጋጆች በጻፈው ደብዳቤ፣ ማኔጅመንቱ የፕሮግራሞቹን የአየር ሰዓት ሲያነሣ ርምጃውን “ጊዜያዊ” ያደረገበት አንዱ ምክንያት፣ በጣቢያው ከሚተላለፉት ፕሮግራሞች ውስጥ የትኞቹን እንደሚመለከት በዝርዝር አለመጠቀሱ ሲኾን ሌላው ደግሞ ከጣቢያው ጋር የአየር ሥርጭት የሰዓት ግዥ ውል በተፈጸመበት ወቅት “የቤተ ክርስቲያኒቱ ዕውቅናና ውክልና አለን” በሚል የቀረቡትን ማስረጃዎች አግባብነትና በቂነት በመፈተሽ ለማስተካከል እንዲቻል ዕድል ለመስጠት እንደኾነ ተገልጧል፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት በዚህ የጣቢያው የተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄዎች ላይ የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልና እና ውሳኔ የሚያስከብር፣ የቀናዒ አገልጋዮችንና ማኅበረ ምእመናን አቤቱታ ያገናዘበ አፋጣኝና አግባብነት ያለው ምላሽ እንደሚሰጥ የሚጠበቅ ሲኾን እስከዚያው ድረስ የተቋረጠውን የአየር ሰዓት ክፍት አድርጎ እንደሚጠበቅ ጣቢያው አስታውቋል፡፡ ይህ ካልኾነ ግን ጣቢያው ከፕሮግራሞቹ ያነሣውን የአየር ሰዓት ለሌሎች ጠያቂዎች ለመስጠት እንደሚገደድና ይህም በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በምእመናን ዘንድ ክፍተትንና ግርታን የሚፈጠር አጋጣሚ እንዳይኾን ሰንደቅ ጋዜጣ በዛሬ ረቡዕ፣ ኅዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም. እትሙ ዘግቧል፡፡

በጣቢያው ደብዳቤ “ክፍተት እና ግርታ” በሚል የተጠቀሱት ቃላት፣ ከጣቢያው የአየር ሰዓት ጠይቀው እየተጠባበቁ ካሉት የሚበዙት አካላት ወንጌላውያን ነን ባይ ፕሮቴስታንቶች እንዳይኾኑና ይህም ክፍተቱን በመጠቀምና ኦርቶዶክሳውያን ድምፆችን ከጣቢያው በማስወጣት ተጽዕኗቸውን የሚያሳዩበት እንዳይኾን ከወዲኹ እየተጠቆመ ነው፡፡

መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በግንቦት 2004 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ በቀዳሚነት ካወገዛቸውና በፕሮቴስታንት ድርጅቶች ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ከሚደረግላቸው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራት አንዱና ራሱን “ከሣቴ ብርሃን” ብሎ የሚጠራው ማኅበር ቅሠጣውን በቴሌቪዥን ፕሮግራም ለማስፋፋት ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡

በመኾኑም ቤተ ክርስቲያናችን ሕገ ወጥ የሚዲያ ፕሮግራሞች በስሟ እንዳይጠቀሙ ያሳለፈችውን ውሳኔ በሙሉ መንፈሱ(ንዋያተ ማሕሌቷን፣ ንዋያተ ቅድሳቷንና አልባሳቷን ጭምር በመገልገል እንዳያጭበረበሩበት የሕግ ክትትሉን በማጥበቅ) ከማስከበር ጋር በመዋቅር የተሰገሰጉ ተንኰለኞች የውሳኔ አፈጻጸሙን ክፍተት በመጠቀም ሕጋውያኑን አካላት ለማዳከምና ለማጥቃት እንዳጠይቀሙበት ሊታሰብበት ይገባል፡፡


(ሰንደቅ፤ ኅዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም.)

logo_final
ሕጋዊነቱና ተቀማጭነቱ በአሜሪካ የኾነው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(ኢ.ቢ.ኤስ) ቴሌቪዥን ሜኔጅመንት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም መንፈሳዊ ዝግጅት የሚያስተላልፉ ሦስት ፕሮግራሞችን ከመጪው እሑድ ጀምሮ ለጊዜው ከአየር ላይ ለማንሣት መወሰኑን አስታወቀ፤ የአየር ሰዓቱ ለሌሎች ጠያቂዎች ተሰጥቶ በቤተ ክርስቲያኒቱና በምእመናኑ ዘንድ ክፍተትና ግርታ እንዳይፈጠር በተቋማቱ ላይ ማስተካከያ ተደርጎ አገልግሎቱ በስፋት እንዲቀጥልም ጠይቋል፡፡

የጣቢያው ማኔጅመንት፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ፣ ላለፉት አምስት ዓመታት በየሳምንቱ እሑድ ለግማሽ ቀን በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም መንፈሳዊ ዝግጅት ሲያቀርቡ የቆዩትን፤ የታዖሎጎስ፣ የቃለ ዓዋዲ እና የማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ ፕሮግራሞችን ከኅዳር 19 ቀን ጀምሮ ከአየር ሰዓታቸው እንደሚያነሣ አስታውቋል፡፡

የሁለቱን ድርጅቶችና የማኅበሩን የአየር ሰዓት ለማንሣት በጣቢያው የተላለፈው ውሳኔ፣ ያለፈቃድ እና ያለዕውቅና በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የሚያስተምሩ ተቋማትን ለማስቆም በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በኩል የሚደረገውን እንቅስቃሴ ከመረዳት፤ ለቤተ ክርስቲያኒቱም ካለው አክብሮትና የመግባባት መንፈስ እንደሆነ ማኔጅመንቱ በደብዳቤው ገልጧል፡፡

ከጣቢያው ጋር ውል በመግባት በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ሦስት መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ሲቀርቡ መቆየታቸውን ያስታወሰው ማኔጅመንቱ፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ የተጻፈለት ደብዳቤ የትኞቹን መንፈሳዊ ፕሮግራሞች የሚመለከት እንደሆነ በዝርዝር ባይጠቅስም ማኅበራቱና ተቋማቱ እንዲሁም መምህራኑ ሕጋዊ የድጋፍና የዕውቅና ሰነዶች እንዲያስገቡ እንደጠየቃቸው አውስቷል፤ ብዙዎቹም ከጣቢያው የአየር ሰዓት ግዥ በጠየቁበት ወቅት ያቀረቡትንና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ዕውቅና ያገኙባቸውን ሰነዶች አያይዘው አቅርበዋል፤ ብሏል፤ የሰነዶቹንም ቅጅ በአባሪነት ማያያዙን ጠቁሟል፡፡

በቤተ ክርስቲያኒቱ ምዘናና የዕውቅና አሰጣጥ ሰነዶቹ በቂ ሆነው ካልተገኙ፣ ፕሮግራሞቹ ከቴሌቪዥኑ ጋር የነበራቸውን የአየር ሰዓት ውል በማፍረስ ለሌሎች የአየር ሰዓት ጠያቂዎች ለመስጠት እንደሚገደድ አስረድቷል፡፡ ይህ ደግሞ፣ በፕሮግራሞቹ ሥር መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለሚከታተሉ ምእመናንና ለቤተ ክርስቲያኒቱ ግርታንና ክፍተትን እንዳይፈጥር የአየር ሰዓቱን የማንሣቱ ውሳኔ በጊዜያዊነት የተላለፈ ርምጃ እንደሆነ ገልጧል፡፡

ቀጥተኛ ውል ከጣቢያው ጋር የሚያስሩ አካላት፣ ከሚመለከታቸው አካላት ሕጋዊ ዕውቅና ሲያገኙና ይህም በሀገር ውስጥ በሚገኘው ብቸኛው ወኪሉ ኢንኮም ትሬዲንግ አማካይነት ሲረጋገጥ መሆኑን ማኔጅመንቱ ጠቅሶ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱም የማስተካከያ፣ የእርምትና የመግባቢያ ጊዜ በማግኘት ዕውቅና በምትሰጣቸው ተቋማት አገልግሎቱን በስፋት ለመቀጠል ትችል ዘንድ ለጊዜው የተቋረጠውን የአየር ሰዓት ክፍት አድርጎ እንደሚጠብቅ አስታውቋል፡፡

Abune Elias
አንድን የተበላሸ ነገር ለማስተካከል ጊዜ ይፈልጋል፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሥራውን እየሠራ ነው፤ በተሐድሶዎችም ላይ ጠንካራ ውሳኔ አስተላልፏል፤ በኢ.ቢ.ኤስ የሚተላለፉ ቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ያልሰጠቻቸው፤ ምእመኑን ለማታለል የእመቤታችንን ሥዕል ከአትሮንስ ሥር አድርገው ስለ እርሷ ግን አንዲትም ቃል የማይናገሩ፤ ፍጹም ፕሮቴስታንታዊ ትምህርት የሚያስተምሩ፤ የተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆችን ተጠንቀቁ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው በመንፈስ ቅዱስ ቢኾንም የእናንተ አስተዋፅኦ ያስፈልጋል፤ እናንተ ከበረታችኹ ካገዛችኹን በፍጥነት ውጤት ማምጣት ይቻላል፤ ስለዚህም ማንንም ተከትላችሁ በየአዳራሹ መሔዳችኹን አቁሙ፤ በዐውደ ምሕረት ላይም ኦርቶዶክሳዊ ያልኾነ ባዕድ ትምህርት ሲሰጥ ከተመለከታችኹ፣ መምህራችን ይህን ከየት አመጣኸው፣ በሉ፤ እንዲህ ዓይነት ትምህርት የቤተ ክርስቲያን አይደለም፣ በሉ፤ የቅዱስ ዓማኑኤል የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ከምእመናኑ ጋር በመተባበር በዐውደ ምሕረቱ ላይ የተሐድሶን ስብከት ያስተምር የነበረውን መምህር፣ ይህ ትምህርት የቤተ ክርስቲያናችን ስላልሆነ ይቅርብን፤ ብለው እንዳስቆሙት ሰምቻለኹ፤ እንዲህ ዓይነት ጥንካሬና ኅብረት ነው የሚያስፈልገው፡፡

ስለዚህም በርቱ፤ ቤተ ክርስቲያንም የራሷን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን ሥርጭት ልትጀምር በዝግጅት ላይ ናት፡፡ (ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፤ የጋሞጎፋ እና ደቡብ ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከተናገሩት)


የማኔጅመንቱ የአየር ሰዓት የማንሣት ጊዜያዊ ውሳኔ ለሦስቱም ፕሮግራሞች አዘጋጆች በደብዳቤ የተገለጸ ሲሆን፤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ምላሽ ሲገኝም እንዲያውቁት እንደሚደረግ ተጠቅሷል፤ አዘጋጆቹም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር በመግባባት የበኩላቸውን መፍትሔ እንዲያገኙ አሳስቧል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ጥቅምት 17 ቀን ባካሔደው የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባው፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ሽፋን እያደረጉ የሚዘጋጁ የዝማሬና መንፈሳዊ ጉባኤያት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና ሥርዓቷንም ጭምር የሚያዛቡ መልእክቶችን እያስተላለፉ በመሆናቸው በርካታ ተከታዮቿን እያደናገሩ እንደሚገኙ በመጥቀስ ሕገ ወጥ ተግባራቸው ወደፊት እንዳይቀጥል ኢ.ቢ.ኤስን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ እንዲገለጽ፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሕግ አገልግሎት በኩልም የሕግ ክትትል እንዲደረግባቸው መወሰኑ ይታወሳል፡፡

Begashaw and Assegidtao logos and kale awadi
በምልዓተ ጉባኤው ስብሰባ ወቅት በስም መጠቀሳቸው ከተጠቆሙት ፕሮግራሞች መካከል፣ ታዖሎጎስ እና ቃለ ዓዋዲ የሚወክሉትን የሃይማኖት ተቋም በተመለከተ ለጣቢያው ያቀረቧቸው ሰነዶች÷ አዘጋጆቹ ከቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ኮሌጆች ያገኟቸውን የዲፕሎማና የዲግሪ ምስክር ወረቀቶች እንዲሁም የድጋፍ ደብዳቤ እንደነበር ተገልጧል፤ ማኅበረ ቅዱሳንም ትምህርተ ወንጌልን በተለያዩ ዘዴዎች/በመጽሔት፣ በጋዜጣ፣ በበራሪ ጽሑፎች፣ በካሴት፣ በኤሌክትሮኒክስ መገናኛዎችና በመሳሰሉት እንዲያስፋፋ እንደተፈቀደለት በመጥቀስ ለሦስተኛ ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ የተሰጠውን መተዳደርያ ደንብ እና ሕጋዊ የኅትመት ሚዲያ ውጤቶቹን ማቅረቡ ታውቋል፡፡

 

Advertisements

16 thoughts on “ኢ.ቢ.ኤስ: በቤተ ክርስቲያን ስም የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን በጊዜያዊነት አገደ፤በስም አለመጠቀሳቸው የአፈጻጸም ችግር ፈጥሮበታል

 1. Anonymous November 25, 2015 at 2:54 pm Reply

  አናለባብስ፡፡ደብዳቤውን በደንብ እዩት፡፡የቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ ‹‹ግለሰቦች፣ማኅበራትና ድርጅቶች›› ነው ሚለው፡፡‹‹ግለሰብ›› ሚለው ቃል አሰግድን ይልጻል፣‹‹ድርጅት›› የሚለው እነበጋሻውን፣‹‹ማኅበር›› ሚለው ማኅበረቅዱሳንን ያመለክታል፡፡ማኅበረቅዱሳን በሲኖዶስ ከተሰጡት መብቶች ውስጥ በኢ.ቢ.ኤስ ስብከት ማሰራጨት አብሮ ስላልተካተተ ነው የተቋረጠው፡፡የቤተክርስቲያን ህግ ለሁሉን ነው ሚሰራው፡፡ልጅና እንጀራ ልጅ ያለ አናስመስል፡፡
  ደብዳቤው ግልጽ ነው፡፡ማኅበረቅዱሳን የታገደው ኢ.ቢ.ኤስ የጠየቀውን የቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ስላላቀረበ ነው፡፡ይሄ ግልጽ የማኅበረቅዱሳን ስህተት ነው፡፡ለወደፊቱ የተጠየቀውን አሟልቶ ስርጭቱን እንዲቀጥል ግን የእኔም ምኞት ነው፡፡ሀተታ አያስፈልግም፡፡ሁልጊዜ ጣት ከመተቆም አንዳንድ ጊዜ ራስንም መፈተሽ ይሻላል፡፡ህግ በማውራትና ህግ በመተግበር መካከል ያለው ልዩነት ግልጽ ነው፡፡ስህተት ተሰርቷል፡፡ያጋጥማል፡፡ለወደፊቱ አርሞ መቀጠል ነው፡፡

  • ዳሞት November 29, 2015 at 8:33 pm Reply

   ለanonymous November 25,2015 at2:54pm
   አናለባብስ ነው ያልከው? ይገርማል! አንተስ ምነው አንተነትህን ባትደብቀው። ለመሆኑ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ማህበራት ሥም የላቸውም? የአያያዝኸው ደብዳቤ ትክክለኛነቱን ባልቀበለዉም ደብዳቤው ለምን በግልጽ በሥም ጠቅሶ ለመጻፍ ፈራ? አንተ ምናልባት ከቤተክርስቲያን ጠላቶች አንዱ ሆነህ ይሆናልና ከሁለት አስርት አመታት በላይ ቤተ ክርስቲያን እውቅናና መተዳደሪያ ሰጥታ ኦርቶዶክ ተዋህዶነታቸው በተግባር የሚታየውን ማህበረ ቅዱሳንን ከጋጠወጥነታቸውና መናፍቅነታቸው በግልፅ በአመፀኝነት ከሚያራምዱት ጋር ማቆራኘትህ አይ የእምነት ሰው እንድል አደረገኝ። ለነገሩ አይደለም እንደኔና አንተ እንዲሁም መሰሎቻችን ቀርቶ አንዳንድ አባቶችንም አይ እረኛ መስቀሉን ተሸካሚ የእምነት አባት ብያለሁ! የእውነትና የእውነተኞች መንገድ ምንም እንሿን ውጣውረድ የበዛበት በሾህ መካከል ቢሆንም በጨለማ ውሥጥም ማብራታቸው አይቀርም።

 2. hazen hazen November 25, 2015 at 3:01 pm Reply

  It is better the church should identify the programs to continue and closed as soon as possible before the air time taken away from the church services.

 3. Anonymous November 25, 2015 at 5:06 pm Reply

  yehe yemiyasayew bete kehenetu

 4. Anonymous November 25, 2015 at 10:38 pm Reply

  this is what I was saying. the game is in the betekihinet!

 5. Anonymous November 26, 2015 at 8:08 am Reply

  ያው ሁሉም ህገወጦች ናቸው።ግለሰቦችም ድርጅቶችም ማኅበራትም እንዲሁም አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም አንዳንድ የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችም ለምሳሌ የመቀሌ ቅ/ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ ከተመረጠ 10 ዓመት ለሆነው ነው ያለ ጠያቂ ም/ቱም የሀገረ ስብከቱ ሥረ አስኪያጅ የደብሩ አለቃ ስለሆነ ለምን ብሎ የጠየቀው የለም

 6. Anonymous November 28, 2015 at 6:18 am Reply

  ስትብላሉ ለሌሎች በር ከፈታችሁ

 7. Anonymous November 28, 2015 at 10:19 am Reply

  Enkan Des Alachihu Des Bilonal YiH MAK yemibalew Yemafya MABER KASET ENA METSIHET NEGADE YALTEFEKEDELTIN YEMIBELA zewd Nafaki mahber Afu Tetameme kemiemnanan bezerefew genze Abalutin balesherna Balemekina yaderegena EKUY TEGBARUN ABZTO BEMECHOH TEAMANINET LEMAGNET YADEREGENA MUKERA BKIDUS SINODOS WISANE BE BEBITSUE ABUNE MATEWOS FIRMANA TITER AFU TEZEGA TSEBL TSEDIK YELELEW WENBEDE MAHBER NEWNA ACSIYONOCHUN SHOTO YEMILEFELFBET MIDIA ESKIYAGEN GENA YEMEDHANEALM FIRD YITEBEKAL HAYMANOTE YALACHEW YMAHBER UN ABALAT BEMAGLEL DURIYEWOCHIN KUTARAWOCHI YEMANEGMENT ABALAT ADRGO YEMISERAW BRABA MATEWOS TEKLAY SIRAASKIYG AFUTEMATA

 8. Anonymous November 30, 2015 at 2:46 pm Reply

  በአመት ሁለት ጊዜ ብቻ የሚሰበሰበው ሲኖዶስ የማኅበረቅዱሳንን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሊከታተል አይችልም፡፡ስለዚህ ሀላፊነቱን ቤተክህነት ወስዶ እንደማንኛውም የቤተክርቲያን ክፍል ማኅበሩን ያዝዘዋል፡፡ይህም የቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ የተለየ አይደለም፡፡ቤተክህነቱ ካልፈቀደ ሊተላለፍ አይችልም፡፡የሲኖዶሱ ህግ አስፈጻሚ ጠቅላይ ቤተክህነቱ ሲኖዶሱን ወክሎ ህጎቹን ያስፈጽማል፡፡ፓትርያርኩም ከበላይ ሆነው ይቆጣጠራሉ፡፡እነዚህ ልጆች ግን እያወቁ ሕጉን መከተል ሲገባቸው በእውቀታቸው እየተኩራሩ የህጉን ቀዳዳ ለማስፋት ይፈልጋሉ፡፡ስለህግ መከበር ይጮሀሉ፡፡ለማኅበረቅዱሳን ሲሆን ግን ህጉ ሁሉ እንዲለጠጥና ከድርጊት በኋላ ስህተቱ ትክክል እንዲባል ይፈልጋሉ፡፡

  በትክክል ይሰራ ከተባለ ማኅበሩ የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮፖዛሉን፣ኤዲቶሪያሉን፣መርሐግብሩ በምን መልኩ ቤተክህነት ሀላፊነት በሚወስድበትና ሊቃውንት መርምረውት እንደሚሰራጭ፣የትኩረት አቅጣጫዎቹን፣አበው ተሳትፎ የሚያደርጉበትን እድል ወዘተርፈ በግልጽ አስቀምጦና አስጸድቆ መግባት ነበረበት፡፡ይሄ ሚኒሚዲያ አይደለም፡፡በቲፎዞና በአባላት ብዛትም አይደለም፡፡ሕግ ምንጊዜም ሕግ ነው፡፡በብልጣብልጥነትና ሁሉን ሰው አፍኖና አሸማቅቆ በመጮህ ህጉን መጣስ ተገቢ አይደለም፡፡የማኅበሩ ራዕይና ዐላማ መተርጎም ካለበትም ፈቃድ በሰጠው አካል እንጅ ሁልጊዜ የቤተክህነትን ሰው በመወንጀል በተካኑት አዛውንት የፌስቡክ ዲያቆናት አይደለም፡፡

  አሁንም ነገሩ ቀላል ነው፡፡ስህተትን አርሞና አሳማኝ ምክንያት አቅርቦ ፈቃዱን ማስመለስ ከባድ አይመስለኝም፡፡ባይሆን ልምድ ያላችሁ ነባር አመራሮች ለትውልዱ ቤተክህነትን ዘለፋ ከማስተማር ተፈቃቅሮ የሚሰራበትን መንገድ አሳዩ፡፡ለስድቡ የተሐድሶዎቹ ከበቂ በላይ ነው፡፡

 9. Anonymous December 1, 2015 at 9:22 am Reply

  ከማኅበረቅዱሳን ሰዎች ከባቢ ኣራት አሳአሳች ነገሮች እየተባሉ ነው፡፡
  ኣንደኛ
  ሰንበት ተማሪዎችን ጨምሮ እያንዳንዱ አጥቢያ እስከ ፓትርያርኩ ድረስ በቃለኣዋዲ ነው የተመሰረቱት፡፡ለቃለአዋዲው አውጭ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ስለሆነም በቁዱስ ሲኖዱስ የተመሰረተው ማኅበረቅዱሳን እና ጥቂት በጣት የሚቆጠሩ ተቅዋማት ብቻ አይደሉም፡፡እንዲያውም እውነት ይነገር ከተባለ ማኅበረቅዱሳን በቃለአዋዲ ሳይሆን በመመሪያ የተቁዋቁዋመ በመሆኑ ደረጃው በቃለአዋዲ ከተጠቀሱት ያነሰ ነው፡፡አሁን ባለው ሀቅ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተክሕነት ነው፡፡ብኣመት ሁለት ጊዜ ብቻ በሚሰበሰበው ሲኖዶስ አመካኝተህ ማኅበረቅዱሳንን ከሁሉም የላቀና የፓትርያርኩና የጠቅላይ ቤተክህነቱ መመሪያና ትእዛዝ የማይመለከተው አድርገህ ልታቀርቦ አትችልም፡፡በሲኖዶስ የተቁዋቁዋመ ለጠቅላይ ቤተክህነትና ፓትርያርኩ ኣይታዘዝም የሚል ቀኖና የለም፡፡ስለሌም ነው ደብዳቤው የማኅበረቅዱሳንና የሌሎችንም ስርጭት ለማስቆም የቻለው፡፡
  ሁለተኛ
  ማኅበሩ በተደጋጋሚ ደብዳቤ መጻጻፉና ስርጭቱን ማከናወኑም ለህጋዊነት መነሻ ሊሆን አይችልም፡፡ደብዳቤና ምስጋና ለብዙ ኣመት መፈጸም እውቅና ቢያሰጥ ኖሮ ‹‹አባ›› ግርማ አይታሰርም ነበር፡፡ድሮ ስንሳሳት ዝም ስለተባልን አሁንም በስህተቱ እንቀጥል ብሎ ነገር የለን፡፡እንዲያውም ካለፈው ኣመት የኣብነት መማህራን ጥሪ በቤተክህነት ትእዛዝ ከታገደ ጀምሮ ማኅበረቅዱሳን ያለቤተክህነት ፈቃድ ከሀገረስቡከቶች ጋራ ደብዳቤ በስሙ እንዳይጻጻፍ ታግዱዋል፡፡ድሮ በአውነ ጳውሎስ ስለሰራን አሁን በአውነ ማትያስም እንቀጥል የሚል ክርክር አምናም ቀርቦ ውድቅ ተደርጉዋል፡፡ኣሁንም እንዲህ ኣይነት ክርክር አቁርቦ መሞገት አዋጭን አይደለም፡፡
  ሥወስተኛ
  ሌላው የሚቀርበው ደካማ መከራከሪያ ‹‹ኤሌክትሮኒክስ መጠቀም›› የሚል ቃል በማቁዋቁዋሚያችን ስላለ ቴሌቪዥንም መብታችን ነው የሚል ነው፡፡ኤሌክትሮኒክስ የሚለው ቃል ለካሴትና ለሲዲ ሽያጭ ያገለግላል ተብሎ በጠባቡ ይቶረጎማል፡፡እንደፈለክ ቴሌቪዥን ለማሰራጨትም፣እንደ አስፈላጊነቱ ኤሌክትሮኒክ የሚል ቃል ባለባቸው ነገሮች ሁሉ ያለምንም ገደብ መጠቀም ማለት አይደለም፡፡ገደብ ስላለው ነው ቤተክህነቱ ያገደው፡፡ሲጀመር ስርጭቱ ያለው ኤዲቶሪያል ፖሊሲ፣ፖሊሲው በሲኖዶስም ወይም በቤተክህነት ስለመጽደቁ፣ለስርጭቱ ማስፈጸሚያ የሚውለው የገንዘብ ምንጭ፣ስርጭቱ ያስቀመጠው ግብና ራእይ ማኅበሩን ለሚቆጣጠረው አካል ቆርቦ አልጸደቀም፡፡ስለዚህ መታገድ ነበረበት፤ታገደ፡፡
  ኣራተኛ
  ከማኅበረቅዱሳን ውጭ ያሉ ሌሎች ኣካላት ሊቀፈቀድላቸው አይገባም የሚለው መከራከሪያም ራስን ከማሳበጥ የመጣ ነው፡፡ለፕሮግራሞቹ ስህተት እንዳላገኙባቸው የሚናገሩ አሉ፡፡በሌላ በኩል የፕሮግራሞቹ ይዘት ግድፈት እንዳለበት ቀላል የማይባል ሰው ይናገራል፡፡ነገር ግን እስካሁን ሲኖዶሱን የሚያሳምን ማስረጃ ያቀረበ የለም፡፡ቤተክህነትና ሲኖዶስ ደግሞ ማኅበረቅዱሳን የጠላውን ሁሉ ተከትለው ሲያወግዙ የሚኖሩ የማኅበር ተለላኪዎች አይደሉም፡፡አባትነታቸው ለሁሉም ነው፡፡ስለሆነም ሁሉንም እኩል እና ባለማግለል የሚዳኝ ህግ አውጥተው ከህጉ የወጣ ሲገኝ ፕሮግራሞቹን በደብዳቤ ማሳገድ ነው የሚሻል፡፡ቤተክህነቱ ሲፈቅድ የሚዳኛቸውን መንፈሳዊ መመሪያም ያሥቀምጣል፤ለአሳራጩም ያሳውቃል፡፡ከዚያ ቡሁዋላ ለቁጥጥርም ኣመቺ ይሆናል፡፡ማኅበረቅዱሳን በውስጥና በውጭ እያስተባበረ ግፊት ስለፈጠረ ብቻ ለሌላውን ሁሉ መግፋት ፍትሀዊ አይሆንም፡፡ሁሉም በድለዋል፡፡በደላቸውም ሳያስፈቅዱ መጀመራቸው ነው፡፡መፍትሄውም ሲጥሱት የሚታረሙበትና ካስፈለገም የሚታገዱበት መመሪያ አዘጋጅቶ እስካሁን ለነበሩት ሁሉ ጥሪ አቅርቦ መፍቀድ፤ለወደፊት ለሚመጡትም ማጣሪያ እያደረጉ ይሁንታ መስጠት ነው፡፡ሁሉን ገፍቶ የቤተክርስቲያን ልሳን በማኅበረቅዱሳን ቦኩል ብቻ ይሰማ ማለት ግና አምባገነንነት ነው፡፡ሰውን ወደቡድንና ቲፎዞ መስመር ይጎትታል፡፡ባይሆን ማኅበረቅዱሳንም ሆነ ሌሎች ወንድሞቻችን የቤተክሕነቱን መምሪያ ተቀብለው ለመስራት ዝግጁ ካልሆኑና ካልቀረቡ በግልጽ አሳውቆ በቤተክርስቲያኒቱ ህግ መሰረት እርምጃ መውሰድ ኣስታራቂ ሀሳብ ይመስለኛል፡፡ካጠፋሁ ይቅራታ፤ከተሳሳትኩ አርሙኝ፡፡

 10. Anonymous December 5, 2015 at 8:27 am Reply

  Ewnetegnawa Tewahedo Meseretwa Kirestos iyesus Newena Amra Demka Kef Telalech, Seitanem Bezuriawa Yanzabebal Egnam Lejochwa Ej Le Ej teyayezen Be Dengel Amalagenet Del Enadergalen

 11. Emu December 5, 2015 at 1:14 pm Reply

  መፀሐፍቅድስን መማር የሚኖርብንለምንድን ነው

 12. Anonymous December 15, 2015 at 6:21 am Reply

  -አሳ ጎረጓሪ ዘነዶ ወጣል አሉ ፣
  -ዝንጀሮ ራስዋን ሳታይ—-፣ ጉድጓድ ስትቆፍር አታርቀው ማን እነደሚግባበት አይታወቅም አሉ፤
  -የሰባኪያኑ እነዲዘጋ ቅስቀሳ ፒቲሽን ስታሰፈርሙ ከርማቸሁ ለራሳችሁ በወጥመዱ እራሳችሁም ገባችሁበት አያችሁ

 13. Yigrem eguale December 24, 2015 at 9:45 am Reply

  እንበርታ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: