የአ/አበባ ሀ/ስብከት በቀጣይ ብክነት ላይ – “ፓትርያርኩን ሰርፕራይዝ እናድርጋቸው” በሚል ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ኾነ!

 • የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በዋና ሥራ አስኪያጅነት በመቀጠሉ የምስጋና ሰርፕራይዝነው
 • ያልታቀደው ወጪ፣ የፓትርያኩን የመኖርያ ቤት ዕቃዎች ለመቀየር መዋሉ ተነግሯል
 • ጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩን የማስተዳደር ሓላፊነት ያለው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አያውቀውም
 • የሀ/ስብከቱ ሒሳብ፣ ያለተቆጣጣሪና ያለዕቅድ በየማነ ዓምባገነንነት እንዲባክን ተፈርዶበታል

2007Yek

በወሬ እና በይስሙላ አካሔዶች የተሳሳተ ምስል እየፈጠረ ራሱን እንደ ለውጥ አራማጅ እና መሪ በመስበክ የሥልጣን ወራቱን እያራዘመ የሚገኘው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ “ፓትርያርኩን ሰርፕራይዝ እናድርጋቸው” በሚል ከሀገረ ስብከቱ ሒሳብ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንዲኾን ማድረጉ ተገለጸ፡፡

“የፓትርያርኩን የተጓደሉ የመኖርያ ቤት ዕቃዎች ለማሟላት እና ለመተካት” በሚል ከሀገረ ስብከቱ ተቀማጭ ብር 586‚000 ወጪ የተደረገ ሲኾን ግዥው አስቀድሞ ያልታቀደና በጀትም የተያዘለት እንዳልነበር ታውቋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በተደረገው የሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ ስብሰባ፣ አዲስ አበባ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት መኾኑን በመጥቀስና “ሥራ አስኪያጃችንን ስላስቀጠሉልን ሰርፕራይዝ እናድርጋቸው” በሚል ግፊት አስቀድሞ ተሰብስቧል በተባለው ፕሮፎርማ መሠረት ግዥው በተጠቀሰው ወጪ እንዲካሔድ መወሰኑ ተመልክቷል፡፡

እንደ ቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ፣ እንዲህ ባሉ ግምታቸው ከፍተኛ በኾኑ ወጭዎች የፈራሚው ሊቀ ጳጳሱ አልያም የፓትርያርኩ ፈቃድና መመሪያ ቢያስፈልግም ግዥው በዋናነት በሥራ አስኪያጁ አመንጪነትና በአድርባይ ሓላፊዎች ግፊት በታቀደ “ሰርፕራይዝ” በመከናወኑ፣ የሀገረ ስብከቱ ተቀማጭ ሒሳብ ያለበላይ ተቆጣጣሪ በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ አማሳኝ እና ዓምባገነናዊ አካሔድ እየባከነ ለመኾኑ አረጋግጧል፡፡

“አዲስ አበባ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ስለኾነ” የሚለው የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋጌ በአስተዳደር ጉባኤው ስብሰባ ተነሥቶ ውሳኔውን ሕጋዊ ለማስመሰል ቢጠቀስም ክፋቱ የየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሥልጣን ማራዘሚያ መርፌ መኾኑ ነው፤” ያሉ የመረጃው ምንጮች፣ የቅዱስነታቸውን መኖርያ ጨምሮ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩን በባለቤትነት የማስተዳደር ሓላፊነት ያለው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት እንደኾነና በጉዳዩ እንዳልተማከረ፣ የሚያውቀውም ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

“የፓትርያርኩን መኖርያ ቤት ማሟላት የቤተ ክህነቱ ድርሻ ነው”  በሚል ለተነሣው ሐሳብም “ከእዚያ ጋር መነካካት አያስፈልግም፤ የራሱ ጉዳይ” የሚሉ በእብሪት የተሞሉ ምላሾች ከአድርባዮቹ ሓላፊዎች መሰጠታቸው ታውቋል፡፡

ግዥውን እንዲያከናውን በተቋቋመው ሦስት የሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች ባሉበት ኮሚቴ፣ ለየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ቅርበት እንዳላቸው የሚነገርላቸው የፓትርያርኩ ረዳት የኾኑት መነኮስ እንዲጨመሩ መደረጋቸው፣ ‘ሰርፕራይዝ ነው’ የተባለውን ምስጋና አወሳስቦታል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ከጥቅምት 25 ቀን ጀምሮ ወደ ምሥራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት መጓዛቸውን ተከትሎ፣ “ከዓዲ ግራት መልስ ሳያውቁ ቤታቸው ተቀይሮ ማግኘት አለባቸው” በሚል ከኢትዮ ሴራሚክስ፣ ከግሎሪየስ፣ ከአዲስ ዲኮር፣ ከዋሪት፣ ከዋው፣ ከዴሉክስ ፈርኒቸርስ በርካታ የግል መገልገያ ዕቃዎች ተሸምተው በጨረታ ያሸነፈ ነው በተባለው ድርጅት እንዲገጠሙ ተደርጓል፡፡

በተከናወነው ግዥ÷ የሳሎን፣ የመኝታ እና የመታጠቢያ ቤት እንዲኹም የመመገቢያ አዳራሽ ዕቃዎች የተካተቱ ሲኾን ከእነርሱም መጋረጃ እና የወለል ምንጣፎች፤ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች፤ አልጋ እና ፍራሽ፤ ጃኩዚ እና ቴሌቭዥኖች እንደሚገኙበት ተገልጧል፡፡

የፓትርያርኩ የመኖርያ ቤት መገልገያዎች፣ ከአያያዝ ጉድለት ይኹን ከጊዜ ብዛት “አርጅተዋል፤ ቆሽሸዋል፤ በልዘዋል፤ ተነቃቅለዋል” ቢባል እንኳ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረት፣ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ተጠሪ እንደ መኾኑ መጠን የገንዘብ እንቅስቃሴውን ማወቅና በጉዳዩም መማከር ነበረበት፡፡

ባለመደረጉ፣ የየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ያልታቀደና ያልተፈቀደ የሥልጣን ማራዘሚያ ‘ሰርፕራይዝ’፣ በአወዛጋቢ የሥራ አስኪያጅነት ምደባው ሳቢያ ካለፈው ዓመት የካቲት ወዲኽ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጋር ተቃውሶ የቆየውን መዋቅራዊ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያባብሰው ተጠቁሟል፡፡

በርግጥ፡-

 • ከሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ጋር በዋና ጸሐፊነት ደርቦ በያዘው የገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ደብር፣ ያለሀገረ ስብከቱ ዕውቅና እና ያለሊቀ ጳጳሱ ፈቃድ በሕገ ወጥ የዲዛይን ክለሳ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ የግንባታ ወጪ ልዩነት ያለበትን ሕንፃ በማስቀጠል ባካበተው ዳጎስ ያለ ሀብት የቢዝነስ ፕላኑን እያማተረ ላለው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፤
 • ያለሊቀ ጳጳሱ መመሪያና ያለአስተዳደር ጉባኤው ውሳኔ÷ በአጥቢያ ሠራተኞችና ካህናት ዝውውር፣ ቅጥር እና የ“ጠብቀኝ፣ አትንካኝ” መደበኛ አምኃዎች ምዝበራውን ላጧጧፈው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፤
 • ከአወዛጋቢ ምደባውና ከሙስና ወንጀሉ ጋር በተያያዘ፣ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወቅት የተፈጠረበትየተጠያቂነትና የመወገድ ስጋት አልፎኛል በሚል የበርካታ አድባራት አለቆችን በማዘዋወር ወንጀሉን ለመሸፈንና ምዝበራውን ለመቀጠል ለቋመጠው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፤

የፓትርያርኩ የብር 586‚000 የሥልጣን ማራዘሚያ እና የምስጋና ሰርፕራይዝ ወጪ ላያስደነቅ ይችል ይኾናል፤ ሀገረ ስብከቱ ግን በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ብሎጎች ጭምር በሚታገዘው የየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከተግባር የራቀ የለውጥ አራማጅና መሪ መሳይ ዲስኩሩ ሽፋን፤ እንዲኹም ሕግና ደንብ በማይገዛው አማሳኝና ዓምባገነናዊ አካሔዱ በቀጣይ ብክነትና ምዝበራ ውስጥ እንደሚገኝ ተረጋግጧል!!

Advertisements

16 thoughts on “የአ/አበባ ሀ/ስብከት በቀጣይ ብክነት ላይ – “ፓትርያርኩን ሰርፕራይዝ እናድርጋቸው” በሚል ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ኾነ!

 1. senu November 9, 2015 at 10:31 pm Reply

  lib belu Hizbu be rehab eyaleqe new !!!!

  Gud bel Gonder !

 2. w/Maryam November 10, 2015 at 8:06 am Reply

  ‘surprise’ yeleyelet lulawinet ! er hoy frdih ayzegy, hizibhinm eyyyy!

 3. Anonymous November 10, 2015 at 8:53 am Reply

  betam yegermal tenesh koyeto menbere patryarkum selareje yekeyer maletu aykerm

 4. Anonymous November 10, 2015 at 9:03 am Reply

  ye yemane zemenfes kedus asafari derget enho be kotebe gebreal yemiseraw amachu Abrham maletem ye yemane ehet bal be astdadariew lay shgut mezo lemasferarat mokero beyameltem polis teketatelo le 12 ken ketasere behuala yemane astedadariewn ene keza anesawalehu erso kesun ansu bemalet be amasagnochu bekul chana adrgo kesun kasnesa behuala ena amachu ketefeta behuala eskahun keza yalanesaw sehon seteyek kefelgu astdadariew serawn metew endemichelu geltual begezew kenebrut ena le polis meskerenet kesetut west hisab shumun wedyawnu keyerotal dergitu yetefesamaw pagume 4 sehon eskahun dres kahenatum debrum cheger west nachew huletum beteleyaye seat yemetalu sera kekome 2 wer honotal asafariew yemane eskahun zemetan mertual betekrstiyanachen beze asazage huneta west sthon melse yemiset yebelay akal alemnoru betam yasazenal

 5. getachew November 10, 2015 at 9:52 am Reply

  ቅዱስ ሲኖዶስ በድርቅ ለተጎዱ ወጎኖች እርዳታ እና ድጋፍ እንዲደረግ ለማስቻል በሊቀ ጰጳስ የሚመረዳ የእርዳታ ኮሚቴ በመመስረት እየተዘጋጀ ባለበት ባሁኑ ችግርና የክፉ ቀን ወቅት ፤ በርካታ አካባቢዎች/ገዳማት፤ አድባራት፤ መነኮሳት፤ ምእመናን/ የቤተ ክርስቲያንን አባቶችንና ደጋፊ ምእመናን እጅ እየጠበቁ ነዉ፤ ለምሳሌ ዋልድባ ገዳም በከፍተኛ ችግር ላይ በመሆኑ ሲኖዶስ ባደረገዉ ዉይይት ከ700000/ ሰባት መቶ ሺህ ብር/ በላይ አፋጣኝ እርዳታ ይፈልጋል፤ ለዚህም በተወሰኑ ሀገረ ስብከቶች 100000 ብር ድጋፍ አድርጉ መባሉ ሰሞኑን በነበረ ንግስ ሰምቻለሁ፤ የአቅሜን ድጋፍ አድርጌአለሁ፤ ሌሎች በርካታ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋል፤ አዳድስ አማንያን ቤተ መቅደስ የላቸዉም፤ በገንዘብ ማጣት በርካታ የስብከተ ወንጌል ስራዎች ቀርተዋል፤ በየ ዓዉደ ምህረቱ ልመና ቀኖና ሆኖ እየተለመነ ነዉ፡፡ ስንቱን ላስዉ ሰንቱን ችግር ልተዎዉ ሆዲ ይፍጀዉ፤ የአቶ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ አድስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ግን በሚሊዮን ቁማር ይጫዎታል፤ ቢራ ይረጫል፤ ሰርፕራይዝ እያለ በድሃ ገንዘብ በረሃብ ዘመን በቤተክርስቲያን ላይ ያሾፋል፤ ይሁዳ ገንዘብ ያዥ ስለ ነበር ነዉ፤ ለጌታ ከተደረገዉ ሽቶ ብር 30 ድርሻዉን አስልቶ ለእርሱ እብጅ ለጌታ እንዳይሆን ተቃወመ፤ በብልጠትም አለ፤ ይህ ገንዝብ ለድሆቸ እንጅ ለጌታ ሽቶ መግዣ መሆን የለበትም አለ፡፡ ቤ/ክንን የጌታ መሳሌ ናት ማደሪያዉ ናትና፤ ለእርስዋ ገንዘብ እየከለከሉ ለግለሰቦች ማዋል ይሁዳን መምሰል ነዉ፡፡ ቅዲሚያ ለቤ/ክ/ምእመናን በነፍስ ወከፍ፤ ህንፃ ቤ/ክን፤ የምእመናን ህብረት ቤ/ክን ይባላሉ/ ፡፡ ባለስልጣኑ ይሁዳ ግን ለቤ/ክን ሳይሆን በድሆች /የገንዘብ ሳይሆን የእዉቀት የስልጣን ሳይሆን የትህትና የፍቅር ድሆች/ እያመካኘ ለራሱ ይበላል፤ የስልጣን እድሜዉን ያረዝማል፤ እስከመቼ? ፍርድ ለእግዚአብሔር እንስጥ፡፡

 6. Anonymous November 10, 2015 at 11:31 am Reply

  ke Enate yemaytebek sira min yadergal kefay Egziyabiher minalebet Egna mihimenan behiminet binnor enate endi yehonachu egna endet linhon new geta yemiyastemirew fikir new metrareb min yadergal benante yetenesa haymanoten eyetelahu metahu Pls ebakachu eris berisachu tewadeku. Eris berersachu temamaru engi; ebakachu lelgocachin enasib.

 7. Tadesse November 11, 2015 at 3:39 am Reply

  yeyemanen ena ye patirarikun email ena webisit post yideregilin hasab lemesitet yamechen zend. Yih ariwos kebetekiristiyan menekel alebet. Ke kiristos hawariyat gar mekoyet yelebetem betam asikotitonan. Ewnet lingerachew beahun seat lebetekiristiyan asirat kemaweta asiraten sebisibe nedeyanin babela yishaleyan.

 8. Anonymous November 11, 2015 at 11:18 am Reply

  lela sidib chemru astewayoch

  • Anonymous November 12, 2015 at 10:32 am Reply

   Tekebyenet YELELEW yetera ena small mind sewoch yemiyasbut tera were mefebrekiya midea honachihu eko hizbu berehab eyaleke belela gize lisera yemichl SIRA koito genzebu leterabu wegenoch zare biset tiru neber kohonebohala gin Tiru new maletu yishalal yam hono Abamatewos saywku yemilew gin yawkalu engi memalat yeneberebet mamalat yeneberebachew eko esachew nachwe gin enkan liyadrrgut Alasebutim Berehab gize lemilew leterabu hizb Teklay Siraaskiju mineyaderegu nachew? Harawoch, Tewut Tewut tewet.

 9. Anonymous November 13, 2015 at 5:37 am Reply

  የክፈት ልጆች እንደሆናቹ እናውቃለን ይህ አልተደረገም ቢደረግስ እንካ እድሳትና ለአዲስ ፓትሪያርክ አሮጌ እቃ በአዲስ እቃዎች መቀየር ምንም ብርቅ አይደለም እናንተ ግን ለአንደ ቱልቱላቹ የሆነ ዻዻስ አስተዳዳሪ ወይም ሰባኪ ሌላም ነገር ታረጋላቹ ለምሳሌ በአዲግራት ለአቡነ ዴስቆሮስ የተደረገው . . . . በግብፅም አዲሱ ፖፕ ተደረገው ስታደንቁ አልነበረም።በጣም ታሳዝናላቹ

 10. Anonymous November 13, 2015 at 6:01 am Reply

  yasazenal yegna batkerstyan macha yhone dehuchen ymetrdaw hule gezay lalewena beseltan lay letkmet new yeader bayonet sera ymseraw awene bate kehenet mene atou new hager sebket yenen ymadergew

  • Anonymous November 15, 2015 at 4:01 am Reply

   BETEKHINET MINATITONEW HEGERESIBKET YEMISERAW LALKEW BETEKIHNETU EKO SIRA ASKIYAJ YELEWM TEKLAY SIRA ASKIYAJ U EKO 22 ABYATEKRSTIYANAT AZEGTEW RASACHEW BAZEGAJUT SHILMAT LRASACHEW ABYATEKRSTIYANATIN LAZEGUBET SHILMAT YEWESEDU YILUGNIN YEMAYAWKU NACHEW YET BETEKRSTIYANS SIKEDSU TAYU YEMAYKEDS PAPAS MINYLUTAL. ..BEGEHAD ENNEGAGERBET

  • Anonymous November 15, 2015 at 4:02 am Reply

   BETEKHINET MINATITONEW HEGERESIBKET YEMISERAW LALKEW BETEKIHNETU EKO SIRA ASKIYAJ YELEWM TEKLAY SIRA ASKIYAJ U EKO 22 ABYATEKRSTIYANAT AZEGTEW RASACHEW BAZEGAJUT SHILMAT LRASACHEW YETESHELEMU ABYATEKRSTIYANATIN LAZEGUBET SHILMAT YEWESEDU YILUGNIN YEMAYAWKU NACHEW YET BETEKRSTIYANS SIKEDSU TAYU YEMAYKEDS PAPAS MINYLUTAL. ..BEGEHAD ENNEGAGERBET

 11. Anonymous November 14, 2015 at 2:27 pm Reply

  አባ ማትያስ ከወሬ አቀባይነት በአንድ ሌሊት ይህ ሁሉ ሊቃውንት ያለበትን ቤተ ክርስትያን ስራ አስኪያጅነት ማድረጋቸው፣አጀብ ነው።

 12. Anonymous November 17, 2015 at 3:13 pm Reply

  አቡነ ማትያስ ይህ ሰው የወጣለት አማሳኝ ስለሆነ አውቀው አንተንም ቢሆን አለቅህም ብለውት አልነበር እንዴ ተግባራዊ ያድርጉት እንጂ አባታችን እሱ ይዘገያል እንጂ የእጁን ከእግዚአብሔር ዘንድ ማግኘቱ አይቀሬ ነው ወይ ቤተክርስቲያን ፈተናሽ እጅግ በዛ የገሀነም ደጆች አይችሉሽም!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: