ቅዱስ ሲኖዶስ: የቴሌቭዥን አገልግሎቱን የ24 ሰዓት የሳተላይት ሥርጭት ለማስጀመር ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

 • የሳተላይት ሥርጭቱ መካከለኛው ምሥራቅን፣ ደቡብ አውሮፓንና ሰሜን አፍሪቃን ያካልላል

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፳፬፤ ቅዳሜ፣ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

Holy Synod2008Tikmit
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አገልጋዮችዋ እና ምእመናንዋ ድምፅዋን የምታሰማበትና መረጃ የምትሰጥበት የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት እንድትጀምር ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡ ከጥቅምት 12 ጀምሮ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በማካሔድ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የቴሌቪዥን አገልግሎቱን ለማስጀመር የሚያስችል የብር 12 ሚሊዮን 22 ሺሕ ዓመታዊ በጀት ከትላንት በስቲያ ማጽደቁ ታውቋል፡፡

በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብዙኃን መገናኛ ድርጅት በሚል ተዋቅሮ ሥራ አስኪያጅ በመሠየምና እስከ 22 ሠራተኞችን በመቅጠር የሚጀምረው አገልግሎቱ፤ ዝግጅቱንና ቀረጻውን በሀገር ውስጥ በማከናወን በሳተላይት እንደሚሠራጭ ተገልጧል፡፡

his-grace-abune-markos-zedebre-markosበስብከተ ወንጌልና ሐዋርያ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የሚመራውና ዘጠኝ አባላት ያሉት የብዙኃን መገናኛ ቦርድ፤ የሳተላይት ሥርጭት አገልግሎት የሚሰጠውን የኮሚዩኒኬሽን ኩባንያ በመምረጥ ሥራውን ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

ባለፈው ማክሰኞ በሚዲያ ጥቅም፣ አሠራርና የወደፊት አቅጣጫ ዙሪያ ለምልአተ ጉባኤው አባላት ማብራሪያ የሰጡት የቦርዱ አመራሮች፤ የሳተላይት ሥርጭቱ ለጊዜው መካከለኛው ምሥራቅን፣ ደቡብ አውሮፓን፣ ሰሜንና ምሥራቅ አፍሪቃን የሚያካልል እንደኾነና ለተቀረው ዓለም ዝግጅቱን በኢንተርኔት በመጫን እንደሚያስተላልፍ አስረድተዋል፡፡

መምሪያው፣ የብዙኃን መገናኛ ባለሞያዎችን በማስተባበር ያስጠናውን የአገልግሎቱን መተዳደርያ ደንብ፣ ኤዲቶሪያል ፖሊሲና የቴሌቪዥን ሥርጭት መመሪያ ባለፈው ዓመት ግንቦት በቅዱስ ሲኖዶሱ አጸድቋል፤ በቀጣይም የሬዲዮ ሥርጭት ለመጀመር መታቀዱ ተጠቁሟል፡፡ ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችል መሠረታዊ የኦዲዮ ስቱዲዮ በመንበረ ፓትርያርኩ የሚገኝ ሲኾን አገልግሎቱ የሚፈጥረው የፋይናንስ አቅም ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡

የቴሌቭዥን አገልግሎቱን የ24 ሰዓት ሥርጭት ለማስጀመር ያኽል የጸደቀው የአንድ ዓመት በጀት በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሚሸፈን ሲኾን ለዘለቄታው ከማስታወቂያ፣ ከአየር ሰዓት ሽያጭና ከበጎ አድራጊዎች በሚገኘው ድጋፍ አገልግሎቱን ያጠናክራል፤ ተብሏል፡፡ በአሌክሳንደርያ ተዘጋጅቶ ቆጵሮስ እና ሰሜን አሜሪካ በሚገኙ የሳተላይት ኩባንያዎች የሚሠራጨው የግብጹ ኮፕቲክ ቴሌቭዥን ወጪ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመን በኾኑ ባዕለጸጋ መሸፈኑም አገልግሎቱን በፋይናንስ ከመደገፍ አኳያ ለኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን ባለሀብቶች የሚያስገነዝበው ትልቅ ቁም ነገር አለው፡፡

Abune samuel22በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ከ50 ሚሊዮን በላይ አገልጋዮችና ምእመናን ያሏት ቤተ ክርስቲያን፤ ከሬዲዮና ከቴሌቭዥን ነባር ሚዲያዎች በተጨማሪ ዘመኑ የሚጠይቀውን የመገናኛ ቴክኖሎጂ ተጠቅማ ምእመናንዋን መጠበቅና ማስተማር ካልቻለች በተለይም ተተኪውን ወጣት ትውልድ ለመድረስ እንደሚያስቸግራት፣ የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ይናገራሉ፡፡

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ የብዙኃን መገናኛ ሥርጭት ጥናቱ ሲጀመር ከተመደቡት ሦስት ብፁዓን አባቶች ጋር የሚዲያ ጥናት እና የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴውን በማስተባበር፤ በግብጽና በእስራኤል ያሉ ተሞክሮዎችን በመዳሰስ፤ የሚዲያ ባለሞያዎችን በማትጋት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ብፁዕነታቸው፣ “ሚዲያ እና ዓለምአቀፋዊ አስተሳሰብ” በሚል ርእስ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ የ24 ሰዓት የሳተላይት ሥርጭት የሚጀምረው የቴሌቪዥን አገልግሎቱ÷ ቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረተ እምነቷን፣ ሥርዐተ እምነቷን፣ ክርስቲያናዊ ትውፊቷንና ታሪኳን ለማስተማር፤ ቅዱሳት መካናቷንና ቅርሶቿን ለማስተዋወቅ፤ ተማሪዎችንና ምሁራኑን ለጥናትና ምርምር ለማነሣሣት፤ በየአህጉረ ስብከቱ የተሠሩ መልካም ሥራዎችን በማስፋፋትና ተቀራርቦ በመሥራት የምእመኑን ጠንካራ ድጋፍ ለማግኘት የግድ ያስፈልጋታል፤ ብለዋል፡፡

Advertisements

18 thoughts on “ቅዱስ ሲኖዶስ: የቴሌቭዥን አገልግሎቱን የ24 ሰዓት የሳተላይት ሥርጭት ለማስጀመር ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

  • Anonymous November 1, 2015 at 2:09 am Reply

   Le ethiopia hzeb teru nger atsrum
   Yaw ywyanen sera lemsrat engy

 1. haile October 31, 2015 at 11:09 am Reply

  Great

  • Bee October 31, 2015 at 11:52 pm Reply

   መጀመሪያ የተራቡ ወገኖች ስላሉ ፣ክርስቲያንነትን ለነዚህ ወገኖቻችሁ ስሩ ።እግዚህአብሄርን ብለው ቅጠል ሸጠው የሚያዋጡትን ገንዘብ እስቲ ለወገናችሁ ድረሱበት ። በአንፃሩ ወገንን ለመርዳት በመንግስት ደረጃ በውጪ አገር የሚኖሩ ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ክርስቲያኖች እንዲረዱ ሲለመን ፣እናንተ የማትኖሩበትን ኦርቶዶክሳዊ እምነት አማኝ በሰበካ የምትኖሩበት ለማሰመሰል መስበኪያ ማዘጋጀት ።ከኮፍያ በቀር ርህራሄ ያልፈጠረበት ጭንቅላት

   • Alemineh yeshiwas November 1, 2015 at 2:00 pm

    It is nice

   • Kaleabe November 2, 2015 at 4:44 am

    Absolutely right!!!

   • Anonymous November 2, 2015 at 7:20 am

    ወልደ ኃጎል!!!! ወንጌል መሰሰበኩ እጅግ ያሳመመህ ይመስላል፡፡ ነው ወይስ ቦታ አጣለሁ ብለህ ሰጋህ ? ለፍፃሜ ይድረስልን እንጂ ሀሳቡን ከዲያብሎስ ውጪ የሚቃወም የለም፡፡

   • Anonymous November 2, 2015 at 7:47 pm

    yemecheresha dedeb neh rhirahe yante bicha ybekal ahiya

 2. haile October 31, 2015 at 11:11 am Reply

  I m happy ,thanks God

 3. Anonymous October 31, 2015 at 12:07 pm Reply

  Egziabher melkam sirawochin besinodosachin yasfalin kibru yigelets zend.

 4. Anonymous October 31, 2015 at 5:08 pm Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን።

 5. Anonymous October 31, 2015 at 5:22 pm Reply

  ENDAT DES YELALE E/R YEMSGEN

 6. Dawit November 1, 2015 at 12:39 am Reply

  Good

 7. Eskinder November 1, 2015 at 12:52 am Reply

  Wow very nice plan i will be with you
  GOD BLESS us!

 8. mamush solomon November 2, 2015 at 5:17 am Reply

  a great move towards apostolic mission. bo gize lkulu !!!

 9. Yonas Mekonnen November 2, 2015 at 8:10 am Reply

  ይድረስ ለ ቅዱስ ስኖዶስ:በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን እኔ ዲያቆን ዮናስ ሞኮንን እባላለው ቅዱስ ስኖዶስ በከፈቴው በቴለቪዢን መ/ግብር የተለያዩ መ/ዝግጅቶች ስላሉኝ ተሰጦም ሲላለኝ ብቀጥረኝ ባይ ነኝ ስልክ 0916079430 አሜን።

  • Anonymous November 2, 2015 at 1:52 pm Reply

   Enameseginalen!!! min enakerbalen bilen techegiren neber. enkuan dereskilin yegna tija tolo feten bileh ene welde hagolin teyikachew kikikiki tigermaleh tija!!!! embua bel eshi tija af

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: