የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በግንቦት ይፈጸማል፤ “ጥንት ተለምኖ ነበር፤ አኹን ግን ሹሙኝ እያሉ የሚመጡ ናቸው ያሉት”/ፓትርያርኩ/

 • በዕጩዎቹ ምርጫ የገዳማት ጥቆማ ቅድሚያ ትኩረት ይሰጠዋል
 • ምርጫውንና ውድድሩን ከሲሞናዊነት ለመጠበቅ ይረዳል፤ ተብሏል
 • የካህናቱ እና የሕዝቡ ምርጫ እና ምስክርነትስ?

Holy Synod Tik2008

የዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እና ሹመት፣ በመጪው ግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንደሚፈጸም ተጠቆመ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ በትላንት ስምንተኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው፣ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ጥናት በሚል በያዘው አጀንዳ÷ ዕጩዎቹ፣ ምልአተ ጉባኤው በወቅቱ በሚሠይመው አስመራጭ ኮሚቴ ተገምግመውና ተመዝነው ለውድድር እንዲቀርቡ ወስኗል፡፡

በዕጩዎቹ ምርጫ፣ በገዳማት ለሚጠቆሙ መነኰሳት እና ቆሞሳት የቅድሚያ ትኩረት እንደሚሰጠው ተገልጧል፡፡ ይህም የዕጩዎችን ሥርዐተ ምንኵስና ለመፈተሽ እና ለኤጲስ ቆጶስነት በሚያበቃው መስፈርት መሠረት ተቀባይነት ያለው ምርጫ በማካሔድ ምርጫውንና ሹመቱን ከሲሞናዊነት ለመጠበቅ እንደሚረዳ ታምኖበታል፡፡

በሞተ ዕረፍት የተለዩትና በዕርግና የሚገኙት ብፁዓን አባቶች ቁጥር፣ በበርካታ አህጉረ ስብከት እና ተቋማት ከፈጠረው የአስተዳደር ክፍተት አንጻር የኤጶስ ቆጶሳት ሹመት አስፈላጊነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ቢታመንበትም፣ በስደት ካሉት አባቶች ጋር በተጀመረው ዕርቀ ሰላምና የምርጫ ሥርዐቱን ከማሻሻል ጋር ተያይዞ ሳይፈጸም ቆይቷል፡፡

ምርጫው በአኹኑ ምልዓተ ጉባኤ ተከናውኖ ሹመቱ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሢመት እንዲፈጸም ሐሳብ ቀርቦ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ይኹንና “ማንን ነው የምንሾመው? በዚኽ ጊዜ እንዴት ነው የምንሾመው” የሚለው የርእሰ መንበሩ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጥያቄ፣ ሒደቱ ለሹመት ባሰፈሰፉና ከሹመቱ ለመጠቀም በቋመጡ ሲሞናውያን ፈተና ውስጥ መግባቱን ያረጋገጠ ኾኗል፡፡

የጥቅምት እና የግንቦት ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባዎች በተቃረቡ ቁጥር ሹመቱን ለኖላዊነት እና ለአገልግሎት ሳይኾን ለድሎት እና ለፍትፍት የሚሹ ተስፈኞች ደጅ ጥናት እና ግርግር በገሃድ ይታያል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም፣ “በጥንት ዘመን ተፈልጎ፣ ና ጳጳስ ኹን ተብሎ ተለምኖ ነበረ፤ አኹን ግን ሹሙኝ እያሉ የሚመጡ ሰዎች ናቸው ያሉት፤” ሲሉ ነው ኹኔታውን የገለጹት፡፡

እንደ ፍትሐ ነገሥቱ ሥርዐተ ሢመተ ክህነት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ እና ውሳኔ በአንብሮተ እድ በሚሾመው ኤጲስ ቆጶስ ምርጫ፣ የካህናት እና የሕዝቡ ምስክርነት የራሱ ሚና አለው፡፡ ኤጲስ ቆጶስ ሲሾም ካህናቱም ሕዝቡም በሙሉ ተገኝተው እየመሰከሩለት ነው የሚሾመው = “ወኵሉ ሰብአ ይኅበሩ በእንተ ተሠይሞቱ ሕዝበ ወካህናት እንዘ ስምዐ ይከውን ሎቱ” /ፍት. መን. አንቀጽ ፭/

ካህናት እና ሕዝቡ እንዲሾምላቸው ኤጲስ ቆጶስ የሚኾነውን ቆሞስ መርጠው ሲያቀርቡ ስለ ደግነቱና ትሩፋቱ፤ ስለንጽሕናውና ከነውር የራቀ ስለመኾኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሦስት ጊዜ እየመላለሰ ማረጋገጫ ይጠይቃቸዋል፡፡ ሕዝቡም አረጋግጠው “የሚባለው ነው” ብለው ሦስት ጊዜ መልስ ይሰጣሉ፡፡ በሦስተኛው ሕዝቡ መልስ ሲሰጡ እጃቸውን አንሥተው “ይገባዋል” እያሉ ያጨበጭባሉ ወይም አመልጥነው “አማን በአማን” እያሉ ያሸበሽባሉ፡፡ ካጨበጨቡ በኋላ ተቃውሞ ቢነሣ ያስታርቃሉ እንጂ ተቀባይነት የለውም፡፡ /ፍት. ነገ. አንቀጽ ፭ ረስጠብ ፶፪/

Advertisements

11 thoughts on “የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በግንቦት ይፈጸማል፤ “ጥንት ተለምኖ ነበር፤ አኹን ግን ሹሙኝ እያሉ የሚመጡ ናቸው ያሉት”/ፓትርያርኩ/

 1. Anonymous October 30, 2015 at 9:59 am Reply

  ይህችን ቤተክርስቲያን አስተዳደሯን ለመቀራመት የሚመኙ በብዙ እስትራቴጂና በጀት የሚንቀሳቀሱ የውስጥም የውጭም አካላት እንዳሉ ለማንም ያልተደበቀ ሀቅ ነው፡፡ ስለዚህ በዘመኑ ከሚገኙት የቤተክርስቲያኒቷ አባቶች፣ ቀናኢ የአስተዳደር አካላት፣ የገዳማት አበምኔቶች፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ምዕማናን ከፍተኛ የሆነ ሥራ ይጠበቃል፡፡
  ለዚህ ሹመት ሲሉ በእጅ መንሻ ጉቦ፣ በዘረኝነት፣ በፓለቲካው … ለመጠቀም የሚንቀሳቀሱ እንዳሉ ሁሉ፡፡ የተህድሶው ጉዳይ አስፈጻሚው ደግሞ በልዩ ስልትና ዕቅድ ይህን ዕድል ሊጠቀም ሲሞሆክር ይታያል፤ አሁንም የሞት ሽረት ትግሉን ከማድረግ ወደ ኋላ አይለም፡፡
  በዘመናችን ምንፍቅና ሙስና በየአጥቢያቸው፣ በየአህጉረ ስብከታቸው፣ በየሰበካውና ልማት ኮሚቴው ሲንሰራፋ እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ አንዳንዴም ልዩ ድጋፍና እገዛ የሚያደርጉ የዘመናችን የቤ/ክ አመራሮች እኮ የፈለቁት በዚህ አጋጣሚ ነው፡፡
  ስለዚህ ሁሉም አካል እንደየ ድርሻው ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡ እነ አርዮስ፣ ንስጥሮስን …. ምሳሌ ማድረግ በቂ ነው፡፡

 2. Buruk October 30, 2015 at 11:30 am Reply

  Hatiyat zeran….selasa silsa metom afera…..machedun gin feran.

 3. Anonymous October 30, 2015 at 3:32 pm Reply

  በእውነት ወጣት አባቶች ባይሾሙጥሩነው ገና የሥጋ ፈተና የሃይማኖት ህፀፅ ፈተናንአላለፉዋትም መንፈሳዊነት እናማስታዋሉ በእድሜ የሸመገሉ አባቶች ስለሚሻሉ ምርጫው ከ60 እድሜ በላይ ቢሆን ለቤተክርስትያናችን የተሻለ ነው

  • Anonymous October 31, 2015 at 12:29 am Reply

   ምነው ጃል? ጡረታ እኮ አይደለም።

 4. መለሠ October 30, 2015 at 9:21 pm Reply

  ይህ ስራ ከታች ከአጥብያ በምሾሙ ዲየቁን ጀምሮ ማሰራት አለበት ምክንየቱም ወደ ገጠረ አከባብና ከእትዩጲያ ውጭ ከእጥረት አንፀረ ዬምሾሙትም ቤተ ክሪስትየን ህልና ለይ አደጋ ነው

 5. Gebre mariam October 31, 2015 at 7:02 am Reply

  እግዚአብሔር አምላክ ዳግማዊ ተክለኃይማትን፣ አቡነ ጴጥሮስን ያስነሳልን ይሆናል፡፡ እመ አምላክን ካለ ግንባሩን ለመትረየስ ሲሰጥ እንኳን ስቅቅ የማይለው አባት፡፡ ምዕመናን የእኛ ኃጠያት በዝቶ ሲፈስ ቤተክርስስያን ያልተማሩ አባቶች፣ የስግብግብነት፣የፍቅረ ነዋይ እና ምንፍቅና መነሃሪያ ሆነች፡፡
  አምላክ እስራኤል የአባቶቻችን አምላክ ሆይ ቤትህን በንጽህና የሚጠብቁ የሕዝብን እንባ የሚያብሱ እና እንደ እነ አባ ኤፍሬም ማሪያም ሆይ በምን በምን እመስልሻለሁ የሚሉ አባቶችን አንተ ላክልን!!!!!!!!
  አሜን!!!!!

 6. Anonymous November 2, 2015 at 5:04 pm Reply

  “ጥንት ተለምኖ ነበር፤ አኹን ግን ሹሙኝ እያሉ የሚመጡ ናቸው”

 7. Anonymous June 2, 2016 at 8:13 am Reply

  ይህችን ቤተክርስቲያን አስተዳደሯን ለመቀራመት የሚመኙ በብዙ እስትራቴጂና በጀት የሚንቀሳቀሱ የውስጥም የውጭም አካላት እንዳሉ ለማንም ያልተደበቀ ሀቅ ነው፡፡ ስለዚህ በዘመኑ ከሚገኙት የቤተክርስቲያኒቷ አባቶች፣ ቀናኢ የአስተዳደር አካላት፣ የገዳማት አበምኔቶች፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ምዕማናን ከፍተኛ የሆነ ሥራ ይጠበቃል፡፡
  ለዚህ ሹመት ሲሉ በእጅ መንሻ ጉቦ፣ በዘረኝነት፣ በፓለቲካው … ለመጠቀም የሚንቀሳቀሱ እንዳሉ ሁሉ፡፡ የተህድሶው ጉዳይ አስፈጻሚው ደግሞ በልዩ ስልትና ዕቅድ ይህን ዕድል ሊጠቀም ሲሞሆክር ይታያል፤ አሁንም የሞት ሽረት ትግሉን ከማድረግ ወደ ኋላ አይለም፡፡
  በዘመናችን ምንፍቅና ሙስና በየአጥቢያቸው፣ በየአህጉረ ስብከታቸው፣ በየሰበካውና ልማት ኮሚቴው ሲንሰራፋ እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ አንዳንዴም ልዩ ድጋፍና እገዛ የሚያደርጉ የዘመናችን የቤ/ክ አመራሮች እኮ የፈለቁት በዚህ አጋጣሚ ነው፡፡
  ስለዚህ ሁሉም አካል እንደየ ድርሻው ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡ እነ አርዮስ፣ ንስጥሮስን …. ምሳሌ ማድረግ በቂ ነው፡፡

 8. Anonymous June 25, 2016 at 8:29 pm Reply

  Aba hailemelkot malet Egzio

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: