ሰበር ዜና – ፈቃድ የሌላቸው የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ተወሰነ፤ የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ይጀመራል

 • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈቃድ እና ዕውቅና የሌላቸው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ፣ ታዖሎጎስ እናቃለ ዐዋዲ  በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ በስም ተለይተው ተጠቅሰዋል
 • በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት፣ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
  የብዙኃን መገናኛ ቦርድ ሥራውን ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ ነው
 • በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ላይ የቀረቡ ማስረጃዎች የበለጠ ተጠናክረው አጀንዳው በልዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲታይ ተወስኗል

synod tik2008 Edited

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ከማእከል የተሰጠ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(EBS) የቴሌቭዥን ጣቢያ“ሃይማኖታዊ ትምህርት” የሚያስተላልፉ ፕሮግራሞች፣ የቤተ ክርስቲያንን ስም እንዳይጠቀሙ ወሰነ፡፡

ምልአተ ጉባኤው በዛሬ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ስድስተኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲኾን፤ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቭዥን በደብዳቤ እንዲያውቁት ይደረግ ዘንድ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

በውሳኔው÷ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ፣ “ታዖሎጎስ” እና ቃለ ዐዋዲ”  በስም የተጠቀሱ ሲኾን በፕሮግራሞቹ አዘጋጅነት የሚታወቁት በተለይ የ“ታዖሎጎስ” ግንባር ቀደም ምንደኞች፣ ፕሮግራማቸው“ራሱን የቻለ የሚዲያ ተቋም” እንጂ  ከቅዱስ ሲኖዶሱ ይኹን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጋር ተቋማዊ ግንኙነት እንደሌላቸው በይፋ በሰጡት መግለጫ ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡

ምልአተ ጉባኤው ከዚኹ ጋር በማያያዝ፤ በሊቃውንት ጉባኤ ሳይመረመሩ እና በማእከል ሳይፈቀዱ በግለሰቦች እየተዘጋጁ የቤተ ክርስቲያንን ስም ይዘው ስለሚወጡ የስብከት፣ የመዝሙር እና የመጻሕፍት ኅትመቶች እንዲኹም የአዳራሽ ጉባኤያት እና ስብሰባዎች ከተወያየ በኋላ ቀደም ሲል ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በማጽናት ተመሳሳይ ትእዛዝ መስጠቱ ታውቋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ “ስብከተ ወንጌል እና ሚዲያን በተመለከተ” በተራ ቁጥር ሦስት በያዘው አጀንዳ፤ ቤተ ክርስቲያን ማእከላዊነቱን ጠብቆ የራስዋን ድምፅ ለዓለም የምታሰማበት እና ስብከተ ወንጌልን የምታስፋፋበት የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት እንዲጀመርም ወስኗል፡፡

ለቤተ ክርስቲያንየቴሌቭዥን አገልግሎት ስርጭት የሚያስፈልገውና በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ አስተባባሪነት የተጠናው በጀት ባለፈው ዓመት ግንቦት በምልአተ ጉባኤው የጸደቀ ሲኾን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር እንደተመለከተው፤ በዚኽ ዓመት በጀቱ በአፋጣኝ ሥራ ላይ እንዲውል የቀረበውን ጥያቄ በመቀበል የፋይናንስ ምንጮቹን ወስኖ ለነገ የሚያቀርብ ሦስት አባላት ያሉት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት(ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ) ኮሚቴ በምልአተ ጉባኤ ተሠይሟል፡፡

ምልአተ ጉባኤው ባለፈው ዓመት ግንቦት ባጸደቀው የሚዲያዎች (የሬዲዮ እና የቴሌቭዥን አገልግሎት) ሥርጭት ደንብ መሠረት፤ በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የሚመራ ዘጠኝ አባላት ያሉት የብዙኃን መገናኛ የሥራ አመራር ቦርድ የተቋቋመ ሲኾን ተግባሩን ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ እንዳለ ለ34ኛው የመንበረ ፓትርያርክ የሰበካ አስተዳደር አጠቃላይ ጉባኤ የቀረበው የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሪፖርት ያስረዳል፡፡

በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው፤ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌልን ከዐውደ ምሕረት ባሻገር በአጽናፈ ዓለም ለማስፋፋት እና ለማጠናከር ስለሚያስፈልጓት ሚዲያዎች፣ በመምሪያው አስተባባሪነት በብዙኃን መገናኛ ባለሞያዎች የተካሔደውን ጥናት መሠረት አድርጎ መተዳደርያ ደንብ፣ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ እና የቴሌቪዥን ሥርጭት መመሪያ/ማኑዋል ተዘጋጅቷል፡፡

በተያያዘ ዜና፣“የቤተ ክርስቲያኗን ወቅታዊ ኹኔታ በጥልቀት ማየት” በሚል ዐቢይ አጀንዳ ሥር በፊደል ተራ ቁጥር 4/መ፣ “የተሐድሶ እንቅስቃሴን በተመለከተ”፤ የተዘጋጀው ሰነድ በተጨማሪ ማስረጃዎች ተስፋፍቶ እና ተጠናክሮ ራሱን በቻለ ልዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲታይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ወስኗል፡፡

የስብሰባው ምንጮች እንደተናገሩት፤ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ግንባር ቀደም መሪዎች በሚሰጣቸው ተልእኮ እና ድጋፍ በቤተ ክርስቲያናችን የአስተዳደር እና የአገልግሎት መዋቅር ውስጥ በመስረግ የኑፋቄውን አስተሳሰብ እና ድርጊት የሚያራምዱ የ66 አካላት እና ግለሰቦች የሰነድ፣ የምስል እና የድምፅ ማስረጃዎች ከኃምሳ ገጾች ማብራሪያ ጋር ተደግፎ ተዘጋጅቷል፡፡

ከቤተ ክርስቲያናችን ዐውደ ምሕረት እና የአስተዳደር መዋቅር ባሻገር፣ የኑፋቄው ግንባር ቀደም መሪዎች እና ምንደኞቻቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን(መንፈሳዊ ኮሌጆች እና የካህናት ማሠልጠኛዎች) ውስጥ በተለያየ ሽፋን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ትኩረት እንዲደረግበት ምልአተ ጉባኤው ኮሚቴውን አሳስቧል፡፡

Beriyaበመካከለኛው ምሥራቅ አህጉረ ስብከት፣ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ሳያውቁት ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ በተቋቋመው የኑፋቄው መናኸርያ “ዱባይ ሚካኤል” እና “ቤርያ ቲኦሎጂካል ኢንስቲትዩት” በሚል መሪዎቹ የመሠረቱት ሕገ ወጥ ተቋም በከፍተኛ ደረጃ ያነጋገረ ሲኾን በምልአተ ጉባኤው ጥናት ተካቶ እንዲቀርብ መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ ኹኔታ ጉባኤውን ያነጋገረው፣ በመንበረ ፓትርያርኩ የውጭ ጉዳይ መምሪያ በሓላፊነት የተቀመጡት መልአከ ሰላም አባ ቃለ ጽድቅ የተባሉ ግለሰብ፣ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቁ አንጻር ያላቸው ሃይማኖታዊ አቋም እና ሥነ ምግባራዊ ኹኔታ ነበር፡፡ የግለሰቡ አመጣጥ እና አመዳደብም ከፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋር ባላቸው የጥቅም ግንኙነት እንደኾነ መጠቆሙ ደግሞ ችግሩ ከግለሰቡም በላይ ልዩ ጽ/ቤቱ እንደ መዋቅር ያለበትን አስከፊ ደረጃ እና አሳሳቢነቱን ለምልአተ ጉባኤው አለብቧል፡፡ 

ከዚኽ ውስብስብነቱና ከሚያስፈልገው ጠንካራ ቅንጅት አኳያ፤ አጀንዳው ራሱን በቻለ አስቸኳይ እና ልዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲታይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሲወስን ጊዜው በመጪው ወርኃ ጥር ላይ ሊኾን እንደሚችል ከወዲኹ የተጠቆመ ቢኾንም በኮሚቴው ውጤታማ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚመሠረት ነው፣ በብዙኃን የምልአተ ጉባኤው አባላት ዘንድ መግባባት የተደረሰበት፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ሥነ ሥርዐት መሠረት፤ አስቸኳይ እና ድንገተኛ ጉዳይ ሲያጋጥም ቅዱስ ፓትርያርኩ ወይም ቋሚ ሲኖዶሱ ወይም የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ በሚያደርጉት ጥሪ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሊካሔድ ይችላል፤ ከዐራቱ እጅ ሦስቱ እጅ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት ስብሰባም ምልዓተ ጉባኤ ይኾናል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በማናቸውም ስብሰባ ላይ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍም፣ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከት ከኾነ በሙሉ ድምፅ ያልፋል፤ በሃይማኖት እና በቀኖና ጉዳይም ድምፀ ተዓቅቦ ማድረግ አይቻልም፡፡

 

 

Advertisements

49 thoughts on “ሰበር ዜና – ፈቃድ የሌላቸው የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ተወሰነ፤ የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ይጀመራል

 1. Anonymous October 28, 2015 at 12:56 pm Reply

  ቅድስት ቤተክርስቲያን ግራና ቀኛቸውን በማያውቁ ገላግልት መጠራት የለባትም፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከሊቆቹ ጋር ተቀላቅለው የሚያምሱት ልቆች/ሐራጥቃ ተሐድሶዎችም ተጠራርገው ይውጡ፡፡

 2. Zekariyas kefelegn October 28, 2015 at 12:56 pm Reply

  kalehiwet yasemaln

 3. Anonymous October 28, 2015 at 1:27 pm Reply

  ህዝበ ክርስትያኑ የሚፈልገው እንደዚህ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ነው።

 4. Engidawork Deribe October 28, 2015 at 1:29 pm Reply

  በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በጣም ደስ ብሎኛል ፡፡በአንዳንድ አብያተክርስቲያናት ውስጥ የኑፋቄ ትምህርታቸውን እየዘሩ ያሉ ሐራ ጥቃዎች ላይም ተገቢው እርምጃ እንዲሁ በቶሎ ቢወሰድ፡፡ብፁዓን አባቶቻችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡፡

 5. Anonymous October 28, 2015 at 1:33 pm Reply

  Good move…Let it be practical. The most important thing is its implementation. Thanks God

 6. Anonymous October 28, 2015 at 1:42 pm Reply

  የውሳኔውን ተፈፃሚነት አሳውቁን

 7. getu October 28, 2015 at 2:16 pm Reply

  is it truly implemented? if it is, that is so good. anyways we will see

 8. Anonymous October 28, 2015 at 2:27 pm Reply

  Temesgen….

 9. zekeyos October 28, 2015 at 2:43 pm Reply

  እ/ር ይባርካቹ

 10. haftu kalayou October 28, 2015 at 2:47 pm Reply

  good news

 11. Anonymous October 28, 2015 at 3:07 pm Reply

  temesegeane egezihabhire gizea alew

 12. Anonymous October 28, 2015 at 3:12 pm Reply

  አሁንም ቢሆን አልረፈደም አስፈላጊውን እርምጃ ቅዱስ ሲኖዶሱ ይወሰድ፡፡ የማንም መጫወቻ ሆንን እኮ !

 13. getachew October 28, 2015 at 4:05 pm Reply

  ለቅዱስ ሲኖዲዮስ ወሳኔዎች ተፈጻሚነት ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን፡፡ ለእዉነተኛች አባቶቻችን እድሜና ጤና ይስጥል፡፡

 14. Selam October 28, 2015 at 4:31 pm Reply

  Egzeabher yebarkachu

 15. shumu belay October 28, 2015 at 4:39 pm Reply

  at the right time decision be brave we growth our unity will be continue our strength to fight our enemy for ever our life ethiopian orthodox tewahid

  • Anonymous October 28, 2015 at 8:15 pm Reply

   አይ ውሳኔ! ወሳኝ መቼ ጠፋ ያለ ቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና የቆመው የአቡነ ጳውሎስ ሀውልት እንዲፈርስስ ቅ/ሲኖዶስ ወስኖ አልነበረ?

  • Anonymous October 28, 2015 at 9:14 pm Reply

   ዚምታው ይብቃን ውጭ የውጡትን ብቻ አይደለም ትመሳስሎ ያሉት ሌላ እሳት ሳያቀጣጥሉ ይለዩ

 16. Anonymous October 28, 2015 at 4:57 pm Reply

  ይህ ኤልያስ አብርሃ የተባለው የቤተክርስቲያን የውስጥ ጠላት ካልተወገደ ምን ሰላም አለ? ፍጹም ሙሰኛ፣ ዘረኛ፣ ከሀዲ መናፍቅ … የስራውን እግዚአብሔር ይክፈለው፡፡

 17. Anonymous October 28, 2015 at 5:01 pm Reply

  እንደ እውነቱ ከሆነ በአሁን ሰዓት የተሀድሶ መናፍቅ ያለበት ደረጃ እኮ ከቤተክርስቲያኒቷ ቁንጮ ጀምሮ እኮ ነው፡፡ ምዕመኑም ቢሆን አሁንም ገና ጋና በጣም ገና አልገባውም አልተማረም አላወቀም ዘልማዳዊ ነው፡፡ ስለዚህ መፍትሄው ብዙ መሰዋትነት ይጠይቃል፡፡ ውሳኔው በጣም የዘገየ ነው፡፡ ታዖሎጎስ … እኮ በጀቱ ማን እንደሆነ በመረጃና ማስረጃ ይታወቃል፡፡ ግን ተግባር ላይ መዋሉን ሁሉም ሊከታተለው ይገባል፡፡

 18. Anonymous October 28, 2015 at 6:36 pm Reply

  አባቶቻችን ክበሩልን

 19. Andarge getnet October 28, 2015 at 6:45 pm Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን

 20. habtamuamare10@gamil.com October 28, 2015 at 7:59 pm Reply

  በጣም የሚያምር እና ለኦርቶዶክ እምነት መልካም ዜና ነው

 21. ኤፍራታ ቀራንዬ October 28, 2015 at 8:00 pm Reply

  የ“ታዖሎጎስ” ግንባር ቀደም ምንደኞች፣
  ፕሮግራማቸው “ራሱን የቻለ የሚዲያ ተቋም” እንጂ
  ከቅዱስ ሲኖዶሱ ይኹን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጋር ተቋማዊ ግንኙነት እንደሌላቸው በይፋ በሰጡት መግለጫ ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡
  ግዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል አሉ።
  ጉድድድድድድድ
  እቤቱ አድነን።።።።።።

 22. Messeret October 28, 2015 at 9:55 pm Reply

  Meshetuale gene tekite dekikawoche sikerew neqachehu. Bertu gene bezu yetebekebachehuale!

  • Anonymous October 29, 2015 at 4:32 am Reply

   Endih new ahun Demo yemntebkew belegbar mewalun new .ye atmakiwm Hone yetehadso guday tilik yemimenan fetena new Abatoch min eyeseru new yemilewn tyake asnestoal!!!! Ahunm bihon alzegeyem.
   Kalehiwot yeselam

  • Anonymous October 29, 2015 at 6:27 am Reply

   አይ ውሳኔ! ወሳኝ መቼ ጠፋ ያለ ቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና የቆመው የአቡነ ጳውሎስ ሀውልት እንዲፈርስስ ቅ/ሲኖዶስ ወስኖ አልነበረ?

 23. tariku Geremew October 29, 2015 at 5:19 am Reply

  egiziabher alena sile min tichenekalachew lejochun aytilimina

 24. Anonymous October 29, 2015 at 5:41 am Reply

  ከዚህ ሁሉ ወንጌሉን ብታስፋፉት ይበጅ ነበር እየፈለሰ የሚሄደዉን ህዝብ እስቲ ለምንድርነዉ በላችሁ ጠይቁት፡፡ እዚህ በሎግ ላይ አካኪ ዘራፍ የምትሉት ራሳችሁን ጠይቁ፡፡ ለመሆኑ በሳምንት ስንት ጊዜ ነዉ መፅሐፍ ቅዱስ ካለችሁ ከፍታችሁት የምታዉቁት፡፡ ለአዋልድ መጽሐፍትና ለቅዱሳን የምትቀኑትን ያህል ለኢሱስ ክርስቶስ ብትቀኑ የት በደረሳችሁ፡፡ ወንጌል ዋጋ እንደሚያስከፍል ሰለሚታወቅ ክሱና ግርግሩ ለነዚህ የዘመኑ ሐዋሪያት ክብር ነዉ፡፡ በእዉነት ያስቀኑኛል፡፡ የንሰሐ ጊዜ እንዲሰጠንና የኢየሱስን ስም በጋራ ከፍ እንድናደርግ እንፀልይ፡፡

  • Anonymous October 29, 2015 at 2:25 pm Reply

   ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። 2ኛ ቆሮ 3፤ 6 መጽሐፍ ቅዱስ አንብቡ አንብቡ ትላላችሁ፤ እናንተ አነበብን የምትሉት እኮ ቃሉን ባለመረዳት እንደራሳችሁ ትርጓሜ ሄዳችሁ አይሁድና መናፍቃን ከወደቁበት ገደል ወደቃችሁ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አማላጅ በማለት። እርሱ በሥጋዌው ጊዜ ያጠቃለለውን ዛሬም እንደሚያደርገው ማሰብ ከንቱ እውቀት ነው። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ግን ትላንትም ዛሬም እስከ ዘለዓለምም ጌታችንን ይፈርዳል፤ በጌትነቱ ስፍራ ነው ያለው፤ ከአባቱ ጋር ትክክል ነው፤ አምላክ ነው፤ ብላ ታስተምራለች። አማኞቿም ይህን አምነው ይኖራሉ። አሁን እዚህ ጋር የትኛው እምነት እንደሚበልጥ እንይ፤ የእናንተ መጽሐፍ ቅዱስን አንብበናል የምትሉት ጌታችንን በአማላጅነት ማስቀመጥ ወይስ የእኛ እርሱን በፈራጅነት፣ በአምላክነት ማስቀመጥ?

 25. Anonymous October 29, 2015 at 5:42 am Reply

  ቅን አባቶቻችንን ያቆይልን፡፡ቅን የቤተ ክርስቲያን መሪ ምንግዜም እግዚአብሔር እንዲሰጠን በትጋት እንጸልይ፡፡

 26. Abraham October 29, 2015 at 6:03 am Reply

  Wowww tmchitogal ktelubate

 27. Anonymous October 29, 2015 at 6:31 am Reply

  በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከፈተኛ ደስታ ተሰመቶናል
  መጥራት የሚገባቸው በእዙ አሉ

 28. Anonymous October 29, 2015 at 7:06 am Reply

  wusanie bicha sayhon tefetsaminetum tetenakro meketel alebet bay negn yihn semtew, aytew yihin wusanie lewesenu abatochim egziabher tilk edmie ena tsegawun yistachew. Amen

 29. ye-mariam October 29, 2015 at 7:29 am Reply

  wesani aybekam tolo we de tigeberaw EBAKACEHU telemenu mot endehone ayker

 30. Anonymous October 29, 2015 at 7:41 am Reply

  የአባቶቻችን ውሣኔ እንዲተገበር ጸልዪ

 31. Mesfin October 29, 2015 at 8:06 am Reply

  Egziabhier Haymanotachin yibark Orthodox lezelalem tnur (nzelalem tnber).

  • Anonymous October 29, 2015 at 8:42 am Reply

   አቤቱ ጌታ ሆይ አንተ ተናገር ፍቅርን አስተምረን የወጡትን መልስልን ያሉትን ጠብቅልን እውነተኛውን መንገድ አንተ አሳየን አባቶቻችን ጠብቅልን ተዋህዶ እምነታችን ጠብቅልን እውነት ካንተናት ፍረድልን በመምሰልና በማስመሰል መንጋውን ከሚያውኩም ጠብቀን የአለምን ክብር በመሻት በሀሠት በቅናት ከሚመጣ የሰይጣን ሀሣብ ጠብቀን

 32. Anonymous October 29, 2015 at 9:33 am Reply

  I think you don,t know the power of reformers, now we control any of orthodox main basement. but you d,t understand, we will see the vector, we have the true Word of God.

 33. Anonymous October 29, 2015 at 11:09 am Reply

  እግዚአብሄር ውሉደ መርገምን ከቤተክርስትያናችን ጠራርጎ ያውጣልን!!!

 34. haileysus October 29, 2015 at 1:20 pm Reply

  Egziabnier fitsamewen yasamerelen

  • Jesus is Lord♥ October 29, 2015 at 11:25 pm Reply

   በጣም ደስ ይላል….በዚህ በመጨረሻው ዘመን መዘናጋት አያስፈልግም።

 35. Amanueal October 30, 2015 at 3:23 am Reply

  You can’t stop the movement of wongel in our Church, we aren’t leaving our church like others did back in the day. We are everywhere even at papasate heart. Ethiopia is blessing by our movement, we doing basement now , you will see the finishing part very soon.

 36. Anonymous October 30, 2015 at 6:20 am Reply

  You, guys, say that you do not want that people should not mention your church’s, orthodox, or organization’s name, synod, but you mention the name “protestant” in profane. Let me ask you a very important question: Who gave you the right for the EOTC to despise the name “protestant” while you do not want the name “orthodox” mentioned? I think the name “orthodox” belongs not only to the Ethiopian orthodox church alone. Other orthodox churches are called by this name: the Greek orthodox, Russian orthodox, Coptic/Egyptian orthodox, Armenian orthodox, etc.

  In fact, the setting in Ethiopia is different than other countries’. Another question that i want to pose is that “who is manafik?” Well, according to the EOTC, those who do not follow the “doctrines” or the “teachings” of the EOTC are liable to be called “menafik”. The EOTC seems having a privilege of calling others “menafik” for long time. It must be also be true that, according to the Bible [which is protestant, make sure that there are a lot of protestants], any person or group or organization or institution or church which preach or add on other gospel than Jesus Christ and Him crucified is “menafik” because there is no other way to heaven than Christ (John 14:6; Acts 4:12; 1 Timothy 2:5-7; Hebrews 7:19, 25;9:24; Romans 8:34). So, was Jesus “menafik” who preached there is no other way to heaven except through Him (John 14:6)? Was apostle Peter “menafik” who preached that there was/is no other name through whom sinners who believe in Him would be saved (Acts 4:12)? Was Paul “menafik” who preached Christ and Him crucified and the only intercessor in heaven right now (1 Timothy 2:5; Hebrews 7:25)?

  So, are those in among you, or the so-called “tehadiso” preach this truth or against this? If they are preaching/teaching this, hey, guys, I would like to call upon your attention that make sure that you are not opposing the true gospel for the sake of “organization”, but if they are not preaching the gospel but another thing, here is what apostle Paul said: “But even if we, or an angel from heaven, should preach to you a gospel contrary to to what we have preached to you, he is to be accursed” (Galatians 1:8). Otherwise, if you are accusing or persecuting them of preaching/teaching the true gospel, make sure that you are not persecuting them, but you are persecuting Christ Himself for the sake of religiosity as apostle Paul did before his true conversion. To him, this is what Jesus Christ said: “And he said, ‘Who are You, Lord?’ and He said, ‘I am Jesus whom you are persecuting…'” (Acts 9:5).

  Therefore, my greatest advice would be is that you must “think three times before you throw the first stone!” May God help you to do so!!

  • aklil October 30, 2015 at 11:56 am Reply

   The protestants were called menafik because from the beginning Martin Luther was not sure which parts of the bible he should accept. He was saying “only believing without doing is enough”; so he couldn’t accept Book of James because it says “But be the doers of the word, and not hearers only, deceiving your own selves.” James 1-22. He was called “the receiver of bible not the whole but the parts that he calls them true word of God”. His successors accepted this book after a long time. So what I am saying is minfikina(kefilo mamen) means accepting only what you like and ignoring that you don’t like from the bible. Then how could you ask that it is not right to be called menafikan; then what should we call you other than this. You are protestant and helping the tehadiso groups view/ belief; that’s why we also call them menafikan and we want them to know this will be over soon.

  • Anonymous October 30, 2015 at 8:04 pm Reply

   The decision was to stop using the name “Ethiopian Orthodox Tewahido” which belongs only to us. Once up on a time this the person who teaches in this program was Ethiopian Orthodox Tewahido church preach but legally their right is removed because their thought was beyond EOTC(Tewahido) doctrine. Therefore, It is illegal to us the the name with out the permission of EOTC(Tewahido).

   The name Protestant is mentioned because they are the one behind the sine they fund organize and support this action directly. EOTC(Tewahido) have tangible evidence on that that why it mentioned for those to know remind them we know their hand are there despite we have very strong spiritual background, Doctrine especially faith on God.

   “Menafik” is a word stand for those how didn’t believe (ለስም አተራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰዉ እና ጌታችን መድሐኚታችን እየሱስ ክርስቶስ)Jesus Christ as God, or in other word If you call him as prayer for as to God EOTC(Tewahido) designate them as “menafik” who didn’t believe in (ለስም አተራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰዉ እና ጌታችን መድሐኚታችን እየሱስ ክርስቶስ)Jesus Christ.

   Those who didn’t even know Jesus they are called (አህዛብ) non believer.

 37. Anonymous October 31, 2015 at 12:49 pm Reply

  የእናንተንስ ክፋትና ተንኮል በቀልተኝነት አድሎ ሙሰኝነት ማን ያስቁመው?????? የክርስትና መአዛ የሌለው ሰይጣነዊ ተግባራችሁንስ በያዛችሁት የክህንት ስልጣን መገልገል እንደሌለባችሁ እንደ ቴሌቪዠን ፕሮግራሙ አታርጡትም ክርስትና የሌላውን ጉድፍ ብቻ ማውጣት ሳይሆን የራስንም የአይን ውስጥ ግንድ ማስወገድ ነው፡፡

 38. Anonymous November 3, 2015 at 10:17 am Reply

  የተኩላ ቅጥረኞች ሁሉ ከዚህ በኋላ በሊቃውንት ሳያሳርሙ የሚያሠራጩት ትምህርት አበቃለት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤፤

  ከዚህ በኋላ የቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ብቻ ልንሠማ ነው፤ ተመስገን፡፡ የአባቶችን ድምጽ መስማት ናፍቆኝ ነበር፡፡

  ተመሳስለው የገቡ ተኩላዎች ንስሐ እንዲገቡና በእናት ቤተ ክርስቲያን እንዲማሩ ዕድል ይሰጣቸው፡፡

  እስቲ ንስሐ ገብተው እነርሱ ደግሞ ተቀምጠው አበው ያስተምሩ፡፡

 39. Anonymous November 5, 2015 at 3:26 pm Reply

  “በተመሳሳይ ኹኔታ ጉባኤውን ያነጋገረው፣ በመንበረ ፓትርያርኩ የውጭ ጉዳይ መምሪያ በሓላፊነት የተቀመጡት መልአከ ሰላም አባ ቃለ ጽድቅ የተባሉ ግለሰብ፣ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቁ አንጻር ያላቸው ሃይማኖታዊ አቋም እና ሥነ ምግባራዊ ኹኔታ ነበር፡፡ የግለሰቡ አመጣጥ እና አመዳደብም ከፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋር ባላቸው የጥቅም ግንኙነት እንደኾነ መጠቆሙ ደግሞ ችግሩ ከግለሰቡም በላይ ልዩ ጽ/ቤቱ እንደ መዋቅር ያለበትን አስከፊ ደረጃ እና አሳሳቢነቱን ለምልአተ ጉባኤው አለብቧል፡”

  ይሄ የት እንዳለን ያሳየናል:: መናፍቃኑ ቤተ ክህነቱን ለመቆጣጠር ምን ያህል እርምጃ እንደሄዱ ያሳየናል:: እኝህ ሰውዬ አሜሪካ
  ኦክላንድ የነበሩ የውጪው “ሲኖዶስ” የነበሩ በምንፍቅና መረጃ የቀረበባቸው ናቸው::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: