ሰበር ዜና – ሊቀ ካህናት መርዓዊ ተበጀ በአጠቃላይ ሰበካ ጉባኤው ተቃውሞ ከመድረክ ወረዱ፤ “የእግዚአብሔር ሥራ ነው”/ብፁዕ አቡነ ሙሴ/

 • ሦስተኛ ሲኖዶስ አቋቁመዋል” በሚል ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱን ለመክሠሥ ተዘጋጅተው ነበር
 • “ቤተ ክርስቲያን ለ30 ዓመት በሰላም ኖራ እየተናወጠች ትገኛለች”/ሊቀ ካህናት መርዓዊ ተበጀ/
 • “መጥነው እንዲያወሩ ዕድል ቢሰጣቸው ተዋረዱ፤ የእግዚአብሔር ሥራ ነው”/ብፁዕነታቸው/

MerawiTebege2

 

ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩትና ከደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡት፣ ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ ተበጀበ34ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በገጠማቸው ጠንካራ ተቃውሞ ንግግራቸው ተቋርጦ ከመድረክ ተገፍተው ወረዱ፡፡

ሊቀ ካህናቱ ዶ/ር መርዓዊ፣ ሦስተኛ ቀኑን በያዘው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የመናገር ዕድል የተሰጣቸው አጠቃላይ ጉባኤው ለምሳ ዕረፍት ለመውጣት በተቃረበበት ሰዓት ላይ ሲኾን የተጋበዙበትም፤ የሀገረ ስብከቱን፣ የደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ዓመታዊ ሪፖርት ቀድመው ለአጠቃላይ ጉባኤው ባሰሙት በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ሙሴ ጋባዥነት ነው፡፡

ሊቀ ካህናቱ፣ በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አመሠራረት ሲያብራሩ ከቆዩ በኋላ፣ ከብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ጋር ተፈጥሯል ስለሚሉት ችግር ለማስረዳት ሲጀምሩ ነበር ከአጠቃላይ ጉባኤው በተሰሙ ድምድምታዎች ንግግራቸውን ለማቋረጥ የተገደዱት፡፡

ከሠላሳ ዓመታት በፊት በጀርመን የተመሠረተችው ቤተ ክርስቲያን፣ ዛሬ 12 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እንዳሏት በንግግራቸው መግቢያ የጠቀሱት ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ “በአውሮፓ፣ የጀርመኗ ቤተ ክርስቲያን እንደ እናት ቤተ ክርስቲያን ናት፤” ብለዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያኑ በቁጥር ይብዙ እንጂ የራሳቸው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ያላቸው ኹለት ብቻ እንደኾኑም ገልጸዋል፡፡

የተቃውሞ ድምፅ እየተሰማ ንግግራቸውን ለመቀጠል ሙከራ ባደረጉበትም ወቅት፣ የጉባኤው የሥነ ሥርዐት ተቆጣጣሪዎች ወረቀታቸውን በመሰብሰብ ከሰጧቸው በኋላ ከመነጋገርያ ሥፍራው እየገፉ አውርደዋቸዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሪፖርት በብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ መቅረቡን የጠቀሱት የአጠቃላይ ጉባኤው ዋና አዘጋጅ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ፣ ሊቀ ካህናቱ ዶ/ር መርዓዊ ለማቅረብ የሞከሩት ጉዳይ ወቅቱንና ቦታውን ያልጠበቀ፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ መታየት ያለበት በመኾኑ እንዲቋረጥ የመደረጉን አግባብነት ለቤቱ አስረድተዋል፡፡

“አገለለኝ ብለው ከሚወቅሱኝና ከሚበጠብጡኝ ከብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ጋር ተመካክረን መጥነው እንዲያወሩ ነበር His grace Abune Musseመድረኩ የተሰጣቸው” ያሉት ብፁዕ አቡነ ሙሴ፣ “ዕድሉ ቢሰጠውም ጉባኤው አዋረደው፤ እኔ ምንም አላልኩትም፤ የእግዚአብሔር ሥራ ነው፤”  ሲሉ የተፈጠረው ነገር ያልጠበቁትና ያስደነቃቸው መኾኑን ተናግረዋል፡፡

ሊቀ ካህናቱ፣ በዛሬው ንግግራቸው፣ ሊቀ ጳጳሱ “ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር ስምምነት በመፈራረም ሦስተኛ  ሲኖዶስ መሥርተዋል” በሚል ለመክሠሥና ያስረዱልኛል ያሏቸውን ዶሴዎች ለማሳየት ተዘጋጅተው እንደነበር ተመልክቷል፡፡ ሀገረ ስብከቱ በበኩሉ፤ ስምምነቱ በጀርመን ባሉት ኹለቱ አኃት አብያተ ክርስቲያናት መካከል ብቻ የተፈረመና ዓላማውም በመረዳዳት መንፈሳዊ አገልግሎትን(ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት፣ ገዳማትን መመሥረት) ለመፈጸም እንደኾነ በመግለጽ መረጃው ከእውነት የራቀና አሉባልታ መኾኑን ነሐሴ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል፡፡

በሆክስተር የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ገዳም ተቀማጭነታቸው ጀርመን ውስጥ በኾነው በኹለቱ አብያተ ክርስቲያናት ሊቃነ ጳጳሳት የተፈረመው ስምምነት እ.አ.አ በ2013 ዓ.ም. (ብፁዕ አቡነ ሙሴ ከመምጣታቸው በፊት) ሙኒክ ከተማ ላይ የተቋቋመው “የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ማኅበር“ መርሐ ግብሮች አንድ አካል ነው፡፡ ይህም በጀርመን ብቻ የሚገኙ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት በመረዳዳት መንፈሳዊ አገልግሎት የሚፈጽሙበት እንጂ የኢትዮጵያን ሲኖዶስ አያጠቃልልም።

Advertisements

8 thoughts on “ሰበር ዜና – ሊቀ ካህናት መርዓዊ ተበጀ በአጠቃላይ ሰበካ ጉባኤው ተቃውሞ ከመድረክ ወረዱ፤ “የእግዚአብሔር ሥራ ነው”/ብፁዕ አቡነ ሙሴ/

 1. Anonymous October 21, 2015 at 3:55 pm Reply

  Liqe Kahinat Dr. Merawi use to rule EOT Churches in German with an iron fist, and finally he is facing the consequences of being arrogantly dictatorial. Lehulum Gizzie Alew !

 2. Anonymous October 22, 2015 at 11:02 am Reply

  ersachew menafq aleqa adrgew shomew kebetekrstiyan yaskobeleluachew nefsat metfat yemayasaznew menalbat endet tedeferu lil yechelal ene bebekule gen aydelem kesbseba medrek bateqalay kebeterstiyan agelglot meweged yalebachew aqorquazz nachew egziabher yetedafene gudachewn yemigeltebet seat dersual meseleng leerasachew amnew yalqorebutn qurban siyaqorbun yenorut leteqmachew becha enji lehaymanot yalqomu ketabot yelq neccochen yemiyakebru yemiyasbeltu zerafi aydelum ende? paletikaws yepatryarkna yeteqlay ministr Foto bemaqatel yepoletika alamachew bewaldba Sem mongoch honenlachew self bemaswetat lematref yemokeru poletikenga nachew lenegeru yetesakalachewm yehew new leqdasena lewdasewma yalesachew sew yelele meslon sentalel norn enji bada mehonachewn ahun ahun yemetutn abatoch senay teredtenewal abet masmesel qemis lebso biznes qof defto poletika! Egziabher yefredbachew ahunm

 3. Anonymous October 23, 2015 at 4:08 pm Reply

  ወገኖቼን አንድ ሰው ብዙ አመት በስልጣን ላይ ከቆየ አምባ ገነን ይሆናል።ሰው ምክር ካልሰማ መጨረሻው ይህ ነው።ምከረው ምከረው ካልሰማ መከራው ይምከረው! ነው እና ለሁለቱም ጊዜ አለው!

 4. Anonymous October 23, 2015 at 4:11 pm Reply

  ወገኖቼን አንድ ሰው ብዙ አመት በስልጣን ላይ ከቆየ አምባ ገነን ይሆናል።ሰው ምክር ካልሰማ መጨረሻው ይህ ነው።ምከረው ምከረው ካልሰማ መከራው ይምከረው! ነው እና ለሁሉም ጊዜ አለው!

 5. Anonymous October 25, 2015 at 2:53 pm Reply

  በውጭ ሲታይ ደብራቸው ሰላም ያለ የመስላል ።ግን በአምባ ገነንነት እና በጉልበት ምእመኑን አፍነው እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን በማለት ሲገዙ የኖሩ ናቸው። አሁንም እዚህ እንደ ጀርመን መስሏቸው ብዙ ሊያወሩ ሲሉ ቀንዳቸውን መባላቸው እይደንቀኝም።የብዙ ሰው እምባ አለባቸው።እንባ እና ደም ደግሞ ….

 6. ወይ ጀርመን October 28, 2015 at 9:22 pm Reply

  ጉደኛ ሁላ!
  ጳጳስ ባዶቤት አፍነው እያስራቡ ምግብ ተርፎ በሚደፋበት ሀገር ነውረኛ ሁላ ደግሞ አፍ አለኝ ብሎ ማውራት ይገርማል ፍርዱን ለፈራጁ ሰጥተናል ይቀጥላል ገና….. አለ…. መች ተነካና ገና…

 7. […] ሳይወሰኑ፣ “ጀርመን ለብቻው ሀገረ ስብከት ይገባዋል፤” እያሉ ከአራት የማይበልጡ አድባራትን በመያዝ […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: