ጠቅላይ ቤተ ክህነት: ዘመናዊውን የኹለትዮሽ የሒሳብ ሥርዐት ተግባራዊ አደረገ፤ “ቤተ ክርስቲያን ስትተችበት የነበረውን የነጠላ ሒሳብ አሠራር አስቀርቷል” /ጽ/ቤቱ/

head-of-eotc-patriarchate

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት

 • የሥርዐት ለውጡ÷ ጽ/ቤቱ፣ ከሐምሌ 2002 – ሰኔ 2005 ዓ.ም. ያለውን የሒሳብ አሠራሩን በውጭ ኦዲተሮች ካስመረመረ በኋላ የተሰጠውን አስተያየት ተከትሎ የተካሔደ ነው
 • የፋይናንስ ፖሊሲው እና ማኑዋሉ፣ የቤተ ክርስቲያንን የምጣኔ ሀብት እና የሙዓለ ንዋይ አስተዳደር መመሪያዎች በሚያወጣው በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርምሮ የተወሰነ ነው
 • ከኹለትዮሽ የአመዘጋገብ ሥርዐት ጋር ጽ/ቤቱ በተከተለው የሒሳብ ማእከላዊነት(account centralization)፤ ወጪ ቆጣቢ፣ ውጤታማ እና ቀልጣፋ ሥራ መከናወኑ ተገልጧል
 • ትግበራው÷ የሠራተኞችን ሞያዊ ብቃት ከማሻሻሉም በላይ በሕግ ተቀባይነት ያለውና ለቁጥጥር አመቺ የኾነ የሒሳብ አሠራር ለመዘርጋት እንዳስቻለ ተጠቁሟል 
 • ከትግበራው በፊት፣ የጽ/ቤቱ ሒሳብ በውጭ ኦዲተር ሲመረመር፣ “የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት ያልተዘረጋለትና በተለመደው የሒሳብ መርሕ መሠረት ያልተሠራ በመኾኑ ሞያዊ አስተያየት ለመስጠት አይቻልም”(disclaimer) ሲባልበት ቆይቷል 
 • ነገ የሚጀመረው የሰበካ አስተዳደር አጠቃላይ ጉባኤ 34ኛ ዓመታዊ ስብሰባ፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዘመናዊ አሠራር በኹሉም አህጉረ ስብከት እንዲተገበር የጋራ አቋም እንደሚያወጣ ይጠበቃል

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት

 • “ዘመናዊ ማኑዋል አዘጋጅቼ የሒሳብ ሠራተኞችን አሠልጥኛለኹ” ቢልም፣ ማኑዋሉ የተመሠረተበትን የፋይናንስ ፖሊሲ በቅድሚያ ለጠቅ/ቤተ ክህነቱ አቅርቦ በቋሚ ሲኖዶሱ አላጸደቀም
 • “ዘመናዊ ሞዴላሞዴሎች ያስፈልጉኛል” በሚል ደረሰኞች እና ቅጾች እንዲታተሙለት ለቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ያቀረበበት አካሔድም፣ መዋቅሩን የጣሰና ጠቅ/ቤተ ክህነቱ የማያውቀው ነው 
 • ሀ/ስብከቱ ለአንድ ጊዜ ብቻ እንዲያሳትም ተወስኖ ቢፈቀድለትም፤ የሰነዶቹን ዐይነት፣ ጥራትና ብዛት ለጠቅ/ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ባለማሳወቁ ቁጥጥሩንና ክትትሉን አዳጋች አድርጎታል 
 • የሥልጠናው ተሳታፊዎች፣ “ምን እንደሚያወራ ለራሱም የገባው አይመስለንም” በሚል የአሠልጣኙን የሒሳብና በጀት ዋና ሓላፊ የኤልያስ ተጫነን ብቃት ክፉኛ ተችተዋል 
 • ትችቱ፣ የሰው ኃይል ዝግጅቱን አጠራጣሪ አድርጎታል፤ ከተጨባጭ ርምጃ ይልቅ የየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ዲስኩር የበዛበት “የለውጥ ሒደት”ም ከተጠያቂነት የማምለጫ እና በሥልጣን የመሰንበቻ ከንቱ ፕሮፓጋንዳ እንደኾነ አሳይቷል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን፡-

 • ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሒሳብ እና በጀት መምሪያ እንዲሁም ከቁጥጥር አገልግሎቱ ጋር በመግባባት የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረጉ ተገልጧል
 • Modified Cash Base” እና “Accrual Base” የተሰኙ የኹለትዮሽ የአሠራር መርሖዎችን የሚከተለው ማኅበሩ፣ ካለፈው በጀት ዓመት አንሥቶ በጽ/ቤቱ ሞዴላሞዴሎች እየተጠቀመ ነው
 • ከዋናው ማእከል እስከ ማእከላት ድረስ የሚጠቀምባቸው የገቢ እና ወጪ ሞዴላሞዴሎች፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዕውቅና ያላቸውና ለቁጥጥርም አመቺ ኾነው እንዲታተሙ ተደርጓል 
 • “ማኅበሩ በ2007 ዓ.ም. የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት በታተመ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በመጠቀም ላይ ነው፤ በበጀት ዓመቱ ከአባላት ወርኃዊ አስተዋፅኦ፣ ከቅዱሳት መካናት ልማት፣ ከማኅበራዊ አገልግሎትና ከስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራሞች የተገኘ ገቢ ብር 21,914,349.31፤ ለልማት አገልግሎትና ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት የወጣ ወጪ ብር 21,726,982.17 ኾኖ ከወጪ ቀሪ ብር 187,367.14 በልዩነት አስመዝግቧል፡፡” /የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሪፖርት/

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 16 ቁጥር 822፤ ቅዳሜ ጥቅምት 6 ቀን 2008 ዓ.ም.)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ማእከል የኾነው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ የኹለትዮሽ የሒሳብ አመዘጋገብ ሥርዐትን በመከተል አሠራሩን ዘመናዊ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

His grace abune mathewos, gen sec of the patriarchate

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው የምጣኔ ሀብትና የሙዓለ ንዋይ አስተዳደር መመሪያዎች (ፖሊሲዎች) መሠረት፣ የቤተ ክርስቲያን ንብረት፣ የገንዘብ ገቢና ወጪ በፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደንቡ መሠረት መከናወኑን የመከታተልና የመቆጣጠር ሓላፊነት አለባቸው፡፡

ቤተ ክርስቲያን፣ ዘመናዊውን የኹለትዮሽ የሒሳብ አሠራር ሥርዐት/Double entry accounting system/ እንድትከተል የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት በባለሞያዎች ያካሔደውን የፋይናንስ ፖሊሲ እና ማኑዋል ጥናት በቋሚ ሲኖዶስ በማስወሰን ባሳለፍነው የ2007 ዓ.ም. በጀት ዓመት ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ታውቋል፡፡ በዚኽም “ቤተ ክርስቲያኒቱ ዘወትር ስትወቀስበትና ስትተችበት የነበረውን፣ ለቁጥጥር የማያመቸውንና በሕግም ተቀባይነት የሌለውን የነጠላ ሒሳብ አሠራር” ጽ/ቤቱ ማስቀረቱ ተገልጧል፡፡

በፖሊሲው ላይ የተመሠረቱ እና ከማኑዋሉ ጋር የሚስማሙ የሒሳብ ሰነዶች እና ቅጻቅጾች ተዘጋጅተው ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን የጽ/ቤቱ የሒሳብና በጀት መመሪያ ሠራተኞችም ለትግበራው የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

የተቋሙን አጠቃላይ ሀብት እና ዕዳ በማወቅ የፋይናንስ እና የንብረት አጠቃላይ አስተዳደሩንና እንቅስቃሴውን ለቁጥጥር ግልጽ ለማድረግ፤ ተፈላጊውን መረጃ በሪፖርት በማውጣት እና በመተንተን ተገቢ ውሳኔ ለመስጠት ምቹ የሆነውን የሁለትዮሽ አመዘጋገብ ተግባራዊነት ተከትሎ፣ ጽ/ቤቱ ማእከላዊ የሒሳብ አሠራር ሥርዐት በመከተሉ ወጪ ቆጣቢ እና ውጤታማ ሥራ ለማከናወን መቻሉ ተገልጧል፡፡

ከ16 የጽ/ቤቱ መምሪያዎች እና ድርጅቶች፣ በጀታቸውን በራሳቸው እያንቀሳቀሱ ሲሠሩ የነበሩ የሰባት መምሪያዎች እና ድርጅቶች የገቢ እና ወጪ ሒሳብ፣ በአንድ ቋት ተጠቃልሎ በኹለትዮሽ አመዘጋገብ ዘዴ በመሠራቱ ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ የተሠራው ሒሳብ ተመርምሮ ተዘግቷል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ በየጊዜው በሚታየው የዋጋ ግሽበት ተጎጂ ኾና የቆየች ሲኾን በሕጋዊ እና አስተማማኝ የግዢ ሥርዐት ዓመታዊ ግዥ በመፈጸም ዕቃዎች በመጋዘን እንዲቀመጡ በማድረግ ከጉዳቱ ለመዳን መቻሉ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ፣ የቤቶች እና ሕንጻዎች ኪራይ አሰባሰብ በባንክ በኩል በማስፈጸም ሒደቱን ቀልጣፋ በማድረግ ውጤታማ ሥራ መሠራቱ ተመልክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ እና በውጭ ለተቋቋሙት 50 አህጉረ ስብከት የበላይ ሓላፊ እና አመራር ሰጪ የኾነው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋነኛ የፋይናንስ ምንጭ፣ ቤተ ክርስቲያን በየአጥቢያው ባቋቋመቻቸው ሰበካ ጉባኤያት ከምእመናንና ከበጎ አድራጊዎች በአስተዋፅኦ ክፍያ፣ በስጦታ፣ በስእለት እና በሙዳየ ምጽዋት የሚሰበሰበው የገንዘብ ፈሰስ ነው፡፡

ከ34 ዓመታት በፊት በሳንቲም ደረጃ የተጀመረውና ከየአህጉረ ስብከቱ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ፈሰስ የሚደረገው የ35 በመቶ(ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የ65 በመቶ) የሰበካ ጉባኤያት ገቢ፣ በበጀት ዓመቱ ከብር 125 ሚሊዮን በላይ/125,785,279.95/ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ካለፈው ዓመትም ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው ተመዝግቧል፡፡ ከአጠቃላይ ገቢው ውስጥ ከብር አምስት ሚሊዮን በላይ/5,381,655.29/ በልማት ገቢ የተደረገ ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ ከ66,668,379.25 ገቢ ማድረጉ የተገለጸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት 16,432,074.68 ብልጫ ማስመዝገቡ ተጠቅሷል፡፡

የገቢዋ ዕድገት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ልማታዊ አገልግሎቶቿን በራስዋ አቅም ለማከናወን የሚያስችላት ሲኾን ለዚኽም ጠቅላይ ጽ/ቤቱ መከተል የጀመረው ዘመናዊው የኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ እንዲኹም የበጀት ማእከላዊነት በተዋረድ በኹሉም አህጉረ ስብከት እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ተግባራዊ እንዲኾን ሲጠየቅ ቆይቷል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን የገንዘብ አያያዝ እና አጠቃቀም ሥርዐት÷ ዘመናዊ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ማደራጀት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ሦስት ዐበይት ሥር ነቀል የለውጥ ርምጃዎች አንዱ ሲኾን በየዓመቱ በሚካሔደው የሰበካ አስተዳደር አጠቃላይ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባዎችም፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ በተገቢው የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት በጥንቃቄ ተመዝግቦ ለሚገባው አገልግሎት እና ልማት እንዲውል፤ ቤተ ክርስቲያን በራሷ ምእመናንና ልማት ላይ የተመሠረተ ሉዓላዊ ክብሯ እንዲጠበቅ በጋራ አቋሞችና ውሳኔዎች ሲጠየቅ ቆይቷል፡፡

በቀጣዩ ሰኞ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ የሚጀመረውና ከ800 ያላነሱ የመላው አህጉረ ስብከት ልኡካን የሚሳተፉበት 34ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባም፤ ትግበራውና ተሞክሮው በኹሉም አህጉረ ስብከት እና አጥቢያዎች ተስፋፍቶ ቤተ ክርስቲያናችን ለዓለም ተቋማት የመልካም ምሳሌ መነሻና መድረሻ የኾነ አሠራር የምታስፋፋበትና የምታጠናክርበት የጋራ አቋምና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

Advertisements

4 thoughts on “ጠቅላይ ቤተ ክህነት: ዘመናዊውን የኹለትዮሽ የሒሳብ ሥርዐት ተግባራዊ አደረገ፤ “ቤተ ክርስቲያን ስትተችበት የነበረውን የነጠላ ሒሳብ አሠራር አስቀርቷል” /ጽ/ቤቱ/

 1. adis October 21, 2015 at 5:11 am Reply

  IT IS FULLY FALSE OR INTENTIONAL WRONG EOTC MAIN HEAD NOT CHANG IT’S ACCOUNTING METHODS STILL IF WHY NOT PREPARE BALANCE SHEET .DO YOU THINK BUDGET CENTRALISE MEANS DOUBLE INTREY ? WHY YOU BE LIER THINK AS HUMAN BEING NEVER DENAY YOURSELVES PLEAS NO COUNTRY OR CHURCH DEVELOP B/C OF UNTRUTH TALK AS CHRISTIAN THINK CHRISTIANITY LET ME TEL YOU IN AMHARIC (MELKE TIFU BESIM YIDEGFU ) LEZEMENAT YEHISAB AYAYAZU NETELA QWAT OR SINGLE OR PRIMITIVE HONO YEMEQOYETU TETEYAKIW BETEKHINET NEW MIKNIYATUM ESU KEFEKEDACHEW SENEDOCH WICH METEKEM BEKALE AWADI ASRO SIL AS KEMETEW ) STILL NOT MAKE TRUTH FULL PREPARATION BUT YOU GIVE FALSE STATEMENT DON’T BE LIE BROTHERS IN CHRISTIAN LET ME ASK YOU FREINDLY
  1,DO YOU SEE THEIR BALANCE SHEET?
  2,DO YOU SEE THEIR P/L STATEMENT?
  3,DO U YOU SEE THEIR OUNERS EQUITY ?STATEMENT OR CASH FLOW DIRECTION?
  4.DO YOU SEE HOW MONY VENDORS ,CUSTOMERS,INVENTORIES SO ON THEY HAVE?
  RELAPSING LONG STAY FEW DEPARTMENTS BUDGET OR BUDGET CENTRALIZATION Never be CALLED DOUL ENTRY BROTHERS UNLES WE TALL FACE TO FACE TALKING BEHIND OF THE SCREEN NEVER BRING CHANG TO OUR CHURCH !!!!@@

  • Anonymous October 21, 2015 at 11:40 am Reply

   የሥልጠናው ተሳታፊዎች፣ “ምን እንደሚያወራ ለራሱም የገባው አይመስለንም” በሚል የአሠልጣኙን የሒሳብና በጀት ዋና ሓላፊ የኤልያስ ተጫነን ብቃት ክፉኛ ተችተዋል
   + ገና በጠዋት የአዲስ አበባ ምክትል ስራ ዘስኪያጅ ኢያጎ(ታጋይ) በሕገወጥ መንገድ እንዲጠቀምበት የተፈቀደለትን የሀ/ስ አዲስ መኪና እያሽከረከረ ከዛሬው ስብሰባ በፊት ሪፖርቱ ሲቀርብ በጭብጨባና በፉጨት ጭምር ሊያግዙ የተመለመሉትን ባንዳዎች ለመሰብሰብና የመጨረሻ ማስጨንቀቂያና ማሳሰቢያ ለመስጠት ተጣድፋል
   የማነ ከመጀመሪያውም የሪፒርቱ ነገር አልተዋጠለትም ምክንያቱም ሪፖርት የሚጥመውና የሚያምረው ልብ አምኖበት በትክክል በአፍ ሲነገር ነው፡፡ እንደጠበቀውም ደረቅ እንጨት ሆኖበታል የፉገራና የውሸት መአቱን ቢያዘንበውም ከአለቆቱ ጀምሮ እስከነ ጆሮዎቱ ለማጨብጨብ ተስኖአቸው አርፍዷል ታጋይ እንኳን ለማጨብጨብ አፈረ፡፡ ኤልያስ ስራውን ሰርቷል ማሳጣት ነው የሱ ስራ አሳጣው አስጣጣው መሰሪው ገ/መስቀል አፉ እንዳይሸት ይሁን ለምን እንደሆነ በማይታወቅ መልኩ አፉን ያዘ ይገርማል በውሸት ጋጋታ ተአምረኛው ደብል ኢንትሪ እስገጥግ በድፍረት ተተረተረ አባቶች ይህንን ውሸት ፈርተው ይሁን አውቀው ሳይታወቅ ይስቁበት ነበር ይገርማል……. ደኩሌ ከሰላሌና ከቡሬ
   .

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: