የአ/አበባ ሀ/ስብከት: ከጽ/ቤቱ የሕንጻ ኪራይ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ አልሰበሰበም፤ የሒሳብና በጀት ሓላፊው ኤልያስ ተጫነ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው

 • እስከ 360 ሺሕ ብር ከፍተኛ ውዝፍ ያለባቸው ተከራዮች እንደሚገኙበት ታውቋል
 • በቤተ ዘመድ የተሸፋፈነው የክፍያው አሰባሰብ የአስተዳደር ጉባኤ አባላቱን አወቃቅሷል
 • በፍሳሽ እና በቃጠሎ አደጋ የተጎዳው ሕንጻ ከዕድሳት ዕጦት ደኅንነቱ ለአደጋ ተጋልጧል

*          *          *

 • ሓላፊው፣ በደንቡ መሠረት ለአስተዳደር ጉባኤው የሒሳብ ሪፖርት አቅርበው አያውቁም
 • የበጀት ዓመቱ የኻያ በመቶ የፈሰስ ሪፖርታቸውም በጥንቃቄ እንዲመረመር ተጠይቋል
 • ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ በፓትርያርኩም በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እንዲቀጥሉ ተደርጓል

*          *          *

Addis Ababa Dioseces head office
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ ለተለያዩ አገልግሎቶች ከአከራያቸው የሕንጻው ክፍሎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የኪራይ ክፍያ አለመሰበሰቡ ተገለጸ፤ ጽ/ቤቱ፣ ተከራዮች ውዝፋቸውን ከነመቀጫው አጠናቀው እንዲከፍሉ የቀናት ገደብ በመስጠት ቢያስጠነቅቅም ዕዳውን ለማስከፈል አልቻለም፡፡

የሀገረ ስብከቱን ሕንጻ ለቢሮ፣ ለሕክምና እና ለሱቅ አገልግሎቶች ከተከራዩ ስድስት ተከራዮች ያልተሰበሰበው አጠቃላይ ውዝፍ ክፍያ ብር 675 ሺሕ 244 ከ31 ሳንቲም ያህል እንደኾነ ጽ/ቤቱ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር መጨረሻ ከጻፈው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ማስጠንቀቂያው ከደረሳቸው ተከራዮች መካከል፣ ከሰኔ ወር 2005 ዓ.ም. ወዲህ ኪራያቸውን ሳይከፍሉ የቆዩና እስከ 360 ሺሕ ብር ከፍተኛ ውዝፍ ያለባቸው እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

ተከራዮች ደብዳቤው በደረሳቸው በሦስት ቀናት ውስጥ ውዝፍ ዕዳቸውን ከነመቀጫው ከፍለው ለጽ/ቤቱ ካላሳወቁ ቢሮዎቻቸውና ሱቆቻቸው እንደሚታሸጉ ነሐሴ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ቀነ ገደቡ ካለፈም በኋላ እንደሚጠበቀው ተግባራዊ ሳይኾን ከወር በላይ ማስቆጠሩ ተገልጧል፡፡

በከፍተኛ የክፍያ ዕዳ ከሚታወቁ ተከራዮች መካከል ከአንዳንድ የሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደሚገኙበት ምንጮቹ ጠቁመው፤ አጀንዳው በአስተዳደር ጉባኤው ስብሰባ ላይ ቀርቦ በታየበት ወቅትም “የገቢ አሰባሰቡ በዝምድና የተሸፋፈነ ነው” በሚል ሓላፊዎቹን እርስ በርስ አወቃቅሶ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

“ኪራዩ በወቅቱ ቢሰበሰብ፣ በጊዜው የነበረውን ዋጋ ያህል ቤተ ክርስቲያኒቱ ልትሠራበትና ልታተርፍበት የምትችልበት ገንዘብ ለግለሰቦች መጠቀሚያ ኾኗል፤” የሚሉት የሀገረ ስብከቱ ምንጮች፣ የፋይናንስ እና በጀት ዋና ክፍሉን ቀዳሚ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

Lique Tebebit Elias Techane
ዋና ክፍሉ ከኪራዩ የሚሰበሰበውንና የቀረውን ገቢ በየጊዜው በሪፖርት በማሳወቅ ክፍያው እንዳይወዘፍ ማድረግ የሚገባው ቢኾንም አለማቅረቡ የሓላፊውን የሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነን ድክመት እንደሚያሳይ ምንጮቹ አስረድተዋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ቀንደኛ የሙስና ቴክኒሻን የኾኑት ሊቀ ጠበብት ኤልያስ፣ በደንቡ መሠረት ወቅቱን ጠብቀው ለቁጥጥር ዋና ክፍሉ እና ለአስተዳደር ጉባኤው ማቅረብ የሚገባቸውን የሒሳብ ሪፖርት በታሪክ አቅርበው እንደማያውቁ ምንጮቹ ይናገራሉ፡፡

ሊቀ ጠበብት ኤልያስ፣ ከዐሥር ዓመታት በላይ ባስቆጠሩበት ሓላፊነት፣ ገዳማትና አድባራት ለሀገረ ስብከቱ የሚያደርጉትን የኻያ በመቶ ፈሰስ ከአማሳኞች ጋር አየር ባየር እየተቃረጡ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተጭበረበረ ሪፖርት በማቅረብ ከ120 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ባለዕዳ ያደረጉ ናቸው፡፡

አዲስ ተመድበው የሚመጡ ዋና ሥራ አስኪያጆችን በሙስና በማበሳበስ እንዳስለመዱት፣  አኹንም በጥቅም የተቆራኟቸውና ከሓላፊነታቸው እንዳይወገዱ ሎቢ የሚያያደርጉላቸው ዋና ሥራ አስኪያጁ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ “በታሪክ ከፍተኛ መጠን ያለው” በሚል ሰሞኑን ዲስኩር ያበዙበት የበጀት ዓመቱ የገዳማትና የአድባራት የፈሰስ ሪፖርትም፣ በሥልጣን ለመሰንበት ከመቋመጥ ያለፈ ዓላማ የሌለው በመኾኑ በዚኹ ዐይን በጥንቃቄ መመርመር እንደሚገባው ምንጮቹ ያሳስባሉ፡፡

ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ በፓትርያርኩ ጭምር ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብባቸውም በሎቢ እንዲቀጥሉ የተደረጉት ሊቀ ጠበብት ኤልያስ፣ በአዲስ አበባ – ለቡ እና በመቐለ የፎቆች፣ በተለያዩ ቦታዎችና በተለያዩ ስሞች አራት የኮንዶሚኒየም የንግድ ቤቶችና የደለበ የባንክ ተቀማጭ በምዝበራ ያካበቱበትን ሓላፊነት ለማስጠበቅ የተጭበረበረ ሪፖርት ከማቅረብ አልፈው አስከፊ ወንጀል ከመፈጸም እንደማያመነቱ ይነገርባቸዋል፡፡

በ2003 ዓ.ም. የንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም አስተዳደር ወቅት፣ በብቃት ማነስና በታማኝነት ጉድለት በተነሡበት ወቅት፣ ለአጭር ጊዜ በቦታቸው ተተክተው ከነበሩት ግብረ ገቡና ባሕታዊው ሞያተኛው መሪጌታ ይትባረክ ካሴ ድንገተኛ አሟሟት ጋር በተያያዘ በሚበዙት የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ስማቸው በነፍሰ ገዳይነት የሚነሣውም በዚኹ የግፍ ተግባራቸው ሳቢያ ነው፡፡

እስከ ዛሬ ይፋ ያልወጣው የመሪጌታ ይትባረክ ካሴ ድንገተኛ አሟሟት፣ በሰው እጅ ተመተው በተፈጸመባቸው ግድያ እንደኾነ ወድቀው ከተገኙበት ወደ ሆስፒታል ገብተው በተደረገው ምርመራ መረጋገጡን የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች ይናገራሉ፤ ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ወደ ቦታው የተመለሱበት ኹኔታም ጥርጣሬቸውን እንደሚያጠናክረው ያስረዳሉ፡፡

ጭካኔአቸው በዚኽ ደረጃ የሚገለጸው ሓላፊው፣ ዛሬም ከዋና ሥራ አስኪያጁና ከቁጥጥር ዋና ክፍሉ ጋር በመመሳጠር የሚፈጽሟቸውን ምዝበራዎች ሊያውቁብንና ሊነቁብን ይችላሉ ያሏቸውን የሀ/ስብከቱን ሠራተኞች አግባብነት በሌለው የዘፈቀደ ዝውውር ከጽ/ቤቱ በማራቅ ማንላታቱን ቀጥለውበት ይገኛሉ፡፡


በ2001 ዓ.ም. በወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል አስተዳደር፣ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ ተሠርቶና በቀድሞው ፓትርያርክ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የጽ/ቤቱ ሕንጻ ባለቤት አልባ እስኪሰኝ ድረስ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚታይበት ተመልክቷል፡፡

በምንጮቹ እንደተጠቆመው÷ በ2006 ዓ.ም. በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ግቢ ቃጠሎ በደረሰበት ወቅት በደቡብ ምዕራብ የሚያዋስነው የሕንጻው መስኰትና ኮርኒሱ ተሰነጣጥቀዋል፤ ረግፈዋል፤ ከሊቀ ጳጳሱ ቢሮ ወደ ታች እንዳለ በስብሷል፤ ጣሪያው፣ ኮርኒሱ፣ መስኰቱና በአጠቃላይ የጂፕሰም ሥራዎቹ ላይ ነው ጉዳቱ የሚታየው፤ እንኳን አዲስ ሕንጻ ሊገነቡና ሊያለሙ ቀርቶ ያለውም ወደ መፍረሱ ተቃርቧል፤ ብዙ ወጪ የወጣበት ሕንጻ ባለቤትና ተመልካች አልባ ኾኗል፤ አስቸኳይ ዕድሳት ካልተደረገለትም ደኅንነቱን አስጊ ያደርገዋል::

ምንጭ፡- አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 16 ቁጥር 821፤ መስከረም 29 ቀን 2008 ዓ.ም.

Advertisements

4 thoughts on “የአ/አበባ ሀ/ስብከት: ከጽ/ቤቱ የሕንጻ ኪራይ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ አልሰበሰበም፤ የሒሳብና በጀት ሓላፊው ኤልያስ ተጫነ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው

 1. Shitahun Minwyelet October 13, 2015 at 2:21 pm Reply

  Thank you very much

 2. adis October 13, 2015 at 8:56 pm Reply

  YENANTE LEABATA ALU. SILE ADDIS ABABA HINTSA MECHENKE YEAMATE EGR KETENE NEW KEHONEM YETIGENA KOMITY SIQAQAM HELAFI HONO BGUBAE YETESEYEME YETEKLALA AGLGLOT HALAFIWE MEGABE AELAF MAMUYE NEW YET DERESE BITLUT ADDIS ABABA HAGERE SIBKET KAKERAYACHEW TKIT BETOCH WERHAWI KIFYA BALAMEKFELACHEW HISAB KIFLU RIPORT BALEMADREGU NEW MALETACHIHU EWNET BEMASREJA KASDEGFACHUT TIFAT NEW EYALEN GIN BETESETEW MASTENKEKIYA YETEKERAYUWACHEW LAY YALEW TSIHUF HISAB KIFLU BAKEREBEW RIPORT MALETE WIHA ASCHEBETACHIHU BALKEFELUT SEWOCH LAY ZIMDNA ALE YALACHIHUT YETEKERAYOCH WIL YAZGAJEWNA PARAF YADEREGEW MAMUYEN TERTER NEW BAYHONMA NORO LSUK YETEKERAYE KIFL LELELA SIRA TEZAWRO .L3GNA WEGEN TELALFO EYALE BEKEN BEKEN LEMGIB BET BALTEKERAYE BET MIGB BELTO SAYKFL YEMIWETAWN MAMUYEN ADERA ENDTFETSHUT YERESANEW YNEFAS SILK KIFLE KETEMA SIRA ASKIYAJ BENEBEREBET WEKT YALE HEGERESIBKETU FEKAD BERASUNA BMIMSLEW SEW BANK KEFTO KEFTEGNA GENZEB YEMEZEBERE BIHONM RIPORT LIKERBLET SAYHON YETEBELASHEWN EYAYE RIPORT MADREG YEMIGEBAW YEHEGERESIBKETU KUTITR TEBABROT ESKE AHUN EYETETEKEMEBET.
  GIN HRAWOCH EBAKACHIHU EWNET YEHONEW NIGEERUN ESKE MECHE NEW TIKURUN NECH NECHUN KEY YEMILUT ??? ??????? YECHENEKEW Y9 WERE ERGIZ YAGEBAL

  • Anonymous October 16, 2015 at 3:15 am Reply

   ዩሰውየው ሞት በትክክል ኤልያስ ሌባው እንደሆነ የሰዎች ግምት አለ ነገር ግን ፖሊስ ነፍስን የሚያክል ነገር ጠፍቶ ለምርመራ እንኳን አለመፈለጉ ሰውየው ምን ያክል በሙስና የፖሊስ አባላትን እንደሚጫን ያሳያል፡፡ አሁንም መንግስት በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት የምስኪኑን ዜጋ ገዳይ ሊያጣራ ይገባል፡፡ ጉዳዩ የህዝብም ጉዳይ ነው ቢያንስ ሰውየው ታስሮ መመርመር አለበት፡፡ u stupid guy pls try to be justifiiable it is crime crime crime . z gavt has great responsibility to explore z case strictly ይህ ሰው ሌላም ነፍስ አለበት ጎንደር ቆሎ ት/ቤት ተማሪ ገሎ ተሸፋፍኗል ጥቆማውንና ማስረጃ በማጠናቀር ለፖሊስ ግፊት ማድረግ ዜግነት ግዴታ ነው፡፡ ሀ/ስ በተመለከተ አአሳይማር እንደተማረ እራሱ ሳይሰለጥን አሰልጣኝ ወይ ድራማ ታዩታላችሁ የፈረደበትን ደብል ኢንትሪ በተለየ መልኩ አምጥተናል ጫወታ ምኑ የተለየ እንዴነ አይታወቅም ብጫ ቄሶችን ማታለል ማጭበርበርኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡአኡኡኡኡኡኡዩሰውየው ሞት በትክክል ኤልያስ ሌባው እንደሆነ የሰዎች ግምት አለ ነገር ግን ፖሊስ ነፍስን የሚያክል ነገር ጠፍቶ ለምርመራ እንኳን አለመፈለጉ ሰውየው ምን ያክል በሙስና የፖሊስ አባላትን እንደሚጫን ያሳያል፡፡ አሁንም መንግስት በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት የምስኪኑን ዜጋ ገዳይ ሊያጣራ ይገባል፡፡ ጉዳዩ የህዝብም ጉዳይ ነው ቢያንስ ሰውየው ታስሮ መመርመር አለበት፡፡ u stupid guy pls try to be justifiiable it is crime crime crime . z gavt has great responsibility to explore z case strictly ይህ ሰው ሌላም ነፍስ አለበት ጎንደር ቆሎ ት/ቤት ተማሪ ገሎ ተሸፋፍኗል ጥቆማውንና ማስረጃ በማጠናቀር ለፖሊስ ግፊት ማድረግ ዜግነት ግዴታ ነው፡፡ ሀ/ስ በተመለከተ አአሳይማር እንደተማረ እራሱ ሳይሰለጥን አሰልጣኝ ወይ ድራማ ታዩታላችሁ የፈረደበትን ደብል ኢንትሪ በተለየ መልኩ አምጥተናል ጫወታ ምኑ የተለየ እንዴነ አይታወቅም ብጫ ቄሶችን ማታለል ማጭበርበርኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡአኡኡኡኡኡኡ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: