ኢ.ቢ.ኤስ: ሃይማኖታዊ የቲቪ ፕሮግራሞች የታደሰ ፈቃድ እንዲያስገቡ አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 16 ቁጥር 821፤ ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን 2008 ዓ.ም.)

logo_finalየኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(ኢቢኤስ)፤ በሳምንት አንድ ቀን በጣቢያው መንፈሳዊ ዝግጅት የሚያስተላልፉ ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች፣ የታደሰ የፈቃድ ማስረጃዎቻቸውን እንዲያስገቡ አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ፡፡

የቴሌቪዥኑ ፕሮግራሚንግ ኮሚቴ መስከረም 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ለአራት የሃይማኖታዊ ፕሮግራም ክፍሎች በጻፈው ደብዳቤ፤ ከጣቢያው ጋር በገቡት ውል መሠረት ለሚወክሉት የሃይማኖት ተቋም ወይም የሃይማኖት ትምህርት ለመስበክ ያስፈቀዱበትን ወይም እያደረጉ የሚገኙትን አገልግሎት የሚደግፍ የታደሰ ፈቃድ ወይም ደብዳቤ በአስቸኳይ እንዲያቀርቡለት ጠይቋል፡፡

የታደሰ ፈቃድ ወይም ደብዳቤ እንዲያስገቡ የታዘዙት÷ ታዖሎጎስ፣ ቃለ ዐዋዲ፣ ማኅበረ ቅዱሳን እና ኤንሼንት ዊዝደም የተባሉ አራት ፕሮግራሞች ሲኾኑ ተቋሞቻቸው ከሚመለከተው የመንግሥት ይኹን የሃይማኖት አካል ለአገልግሎታቸው ይኹንታ ያገኙበትን የታደሰ ፈቃድ ወይም ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት እትማችን፣ “በታዖሎጎስ እና ቃለ ዐዋዲ የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች ላይ ተቃውሞ ተነሣ” በሚል ርእስ፣ ፕሮግራሞቹ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ እና ክብር የሚጋፉ በመኾናቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እንዳጠቀሙ የሚቀሰቅስ የሕዝባዊ ተቃውሞ ድጋፍ ፊርማ በመሰብሰብ ላይ መኾኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል በስም ተጠቃሾቹ የሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች አዘጋጆች፣ በወጣው ዘገባ ላይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

Advertisements

17 thoughts on “ኢ.ቢ.ኤስ: ሃይማኖታዊ የቲቪ ፕሮግራሞች የታደሰ ፈቃድ እንዲያስገቡ አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ

 1. Yordanos Abebe October 10, 2015 at 10:58 am Reply

  Thank u for ur Info.

 2. Anonymous October 10, 2015 at 12:11 pm Reply

  የቤተክርስቲያናችን የውስጥ ጠላቶች እነ ኑረዲን ኤልያስ አብርሃ፣ ሰረቀ፣ የማነ … የተሀድሶው የውስጥ ጉዳይ አስፈጻሚዎች ናቸው እኮ፡፡ በአደባባይ የሚፈጽሙትን በዓይናችን እያየን በጆሮአችን እየሰማን ያለነው በቤተክርስቲያናችን ላይ የዝርፊያ፣ የውንብድና የምንፍቅና ጀሌሎች ምን የማያደርጉት ነገር አለና፡፡ ለአምላክ እናት ለአማላጂቷ ክብር ይግባትና ሰረቀ እኮ ‹‹የቅድስት ድንግል ማርያም ዘላላማው ድንግልና ከሳይንሳዊ ውጭ የሆነ ፍልስፍና…›› ብሎ ያወጀ ከሃዲ መናፍቅ ነው እኮ፡፡ የዘመናችን ሁኔታ ግን ‹‹እናቱን በገጀራ የገደለ ጎራዴ ተሸለመ›› ስለሆነ በአስተዳደር ቁንቾ ላይ ሆነው እንዳሻቸው ይሆናሉ፡፡ ግን የሚገርመው ነገር EBS የሚባለው ቻናል ነው እንጂ፡፡ ያለ አንድ መረጀና ማስረጃ ማንም በየመንደር አዳራሽ እየተሰበሰበ በዝህች ቤተክርስቲያን ላይ እንዲጨፍርባት ማድረጉ ነው፡፡ ከአሁን በኃላ ግን ይህ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በቤተክርስቲያናችን ላይ ሌላ የውስጥ ተልዕኮ ከሌለው በስተቀር ይህን ያህል የህዝብ ተቃውሞ አቤቱታ እና የአደባባይ መረጃና ማስረጃ እየደረሰው ባያቆም እንደ ክርስቲያን ሁሉም አማኝ ኦርቶዶክሳዊ ዝም ሊለው አይገባም፡፡ ሁሉም የራሱ የሆነ መብትና ግዴታ አለውና፡፡ ለአጸፋው የአጸፋ ምላሽ በተገቢው መንገድ ሊሰጠው ይገባል እንጂ ደብዳቤ አምጡ ንግድ ፍቃድ አውጡ ምናምን … ብሎ አንድን የዕምነት ተቋም ቴሌቪዥን ጣቢያ ከፍቶ ማሰደብ፣ መወንጀል፣ ማስነቀፍ፣ በስሙ ክህደት ማሰራጨት አይችልም፡፡

  • Anonymous October 11, 2015 at 10:46 am Reply

   Although I share the idea that all should get permission from our church. I disagree on your comments ድንግል ማርያም ዘላላማው ድንግልና ከሳይንሳዊ ውጭ የሆነ ፍልስፍና…›› .belo astemare yalkew. I know that is a lie. If you have a proof put it up. It is a technology era and accusing some one without a proof doesn’t work. Nesha geba. But In conclusion all weather on tv, church or anywhere should have a permit to preach from the respected belief authority.

   • Binyam October 14, 2015 at 2:05 pm

    proof is already on facebook videos and audios it is a complete gesture by this guy to his evil employers

 3. Anonymous October 10, 2015 at 1:17 pm Reply

  የገሃነም ደጆች አይችሏትም

 4. Anonymous October 10, 2015 at 2:29 pm Reply

  በጣም አሪፍ ሃሳብ ነው

 5. Anonymous October 10, 2015 at 3:03 pm Reply

  በጣም አረፊ ነው

 6. Tina kinfe October 10, 2015 at 4:41 pm Reply

  ያለ ክርስቶስ ይቅር ባይነት ያለ ድግል ማርያም አማላጅነት አለም አትድንም

  • Anonymous October 10, 2015 at 6:15 pm Reply

   እውነት፡ከሆነ፡መልካም፡ነው።

 7. Anonymous October 10, 2015 at 10:36 pm Reply

  mahibere kidusanin kelikilew leleloch bayisetuwachew min ale belugn..,

 8. drar nguse October 11, 2015 at 2:56 am Reply

  i love u Ethiopian broadcast television

 9. drar nguse October 11, 2015 at 2:58 am Reply

  hii ebs costumers

  hiiiii

 10. Zenaw getahun October 11, 2015 at 5:22 am Reply

  Very good

 11. Anonymous October 11, 2015 at 3:10 pm Reply

  hulum melk meyaz alebet

 12. መለሠ October 12, 2015 at 10:02 pm Reply

  Why anyone who wants things which is not himself

 13. Anonymous April 6, 2016 at 2:27 pm Reply

  HOW THISE IS TRUE

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: