በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ: “ታዖሎጐስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተጋግሎ ቀጥሏል

 • የአ/አበባ ጎልማሶችና ወጣቶች ማኅበራት ኅብረት ተቃውሞውን ያስተባብራል
 • ለተቃውሞው፣ በሰባት ቀናት ከ100 ሺሕ በላይ የድጋፍ ፊርማዎች ተሰባሰቡ
 • የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንዲወስንበት ለማድረግ ታቅዷል
 • “በማስረጃ ተደግፎ የሚቀርብ ነገር ካለም እርምት እንወስዳለን”/የኢ.ቢ.ኤስ ሥራ አስፈጻሚ/

(ምንጭ: አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፳፤ ቅዳሜ መስከረም ፳፪ ቀን ፳፻፰)

tao logos and kale awadi Begashaw and Assegidኢትዮጵያን ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (EBS) ቴሌቪዥን በሚተላለፉት “ታዖሎጐስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” በተሰኙት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝ ፕሮግራሞች ላይ ሰሞኑን ከፍተኛ ተቃውሞ ተነሣ፡፡ ፕሮግራሞቹ እንዲዘጉና በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ለመጠየቅ የሚያግዝ የሕዝባዊ ተቃውሞ ድጋፍ ፊርማም እየተሰባሰበ ነው፡፡ 

በ7 ቀናት ከ100ሺሕ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች መፈረማቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ጐልማሶች ማኅበራት ኅብረት ሰብሳቢ ፌቨን ዘሪሁን ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡

“ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ ዕውቅና ለሌለው አካል ፈቃድ እየሰጠ ጥንታዊቱንና የተከበረችውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖና እንዲኹም ያሬዳዊ ዝማሬን እያንኳሰሱ ይገኛሉ፤” ያሉት ወ/ሮ ፌቨን፤ “ይህ ትውልድን ከመተካት እና የቀናችውን ሃይማኖት ከማስቀጠል አንጻር ትልቅ አደጋ አለው፤” ብለዋል፡፡

የአገራችን ሕገ መንግሥት ማንኛውም ሰው ወይም ተቋም የፈለገውን ሃይማኖት የመከተልና የሀገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት የእምነቱን አስተምህሮ ማስተማር እና ማስፋፋት እንደሚችል ያስታወሱት ሰብሳቢዋ፤ ነገር ግን የሌሎችን የእምነት ተቋማት ስም በማናለብኝነት በመዝለፍ በሃይማኖቱ ስም ስብከትም ኾነ ትምህርት በብዙኃን መገናኛ ማስተላለፍ ወንጀልም ኃጥያትም ነው፤ ሲሉ ኰንነዋል፡፡

“ታዖሎጐስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የተባሉት የጣቢያው ፕሮግራሞች፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሥርዐት እና ደንብ የተዘጋጁ መኾናቸውን ቢገልጹም የሚተላለፉት መልእክቶች ግን ከኦርቶዶክሳዊ ትምህርት፣ ሥርዐት እና ትውፊት ፈጽሞ የሚቃረኑና የቤተ ክርስቲያኗን ክብር የሚጋፋ በመኾናቸው ፕሮግራሞቹን ለማዘጋት በበርካታ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በመዘዋወር ከ100 ሺሕ በላይ ምእመናንን ማስፈረማቸውን ወ/ሪ ፌቨን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ “በነዚኽ መርሐ ግብሮች አፋቸውን የሚያላቅቁት ጥቂት የማይባሉ ሰባክያን ነን ባዮች ኦርቶዶክሳዊ ያልኾነ ኑፋቄ ሲጽፉና ሲያስተላልፉ የነበሩ ውስጠ ሌላዎች መኾናቸው በግልጽ ይታወቃል፤” ብለዋል ሰብሳቢዋ፡፡

ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋር ግንኙነት አላችኹ ወይ? ፊርማውንስ አስባስባችሁ ስትጨርሱ ለማን ነው የምታቀርቡት? በሚል ላነሣንላቸው ጥያቄ፤ ወ/ሪት ፌቨን ሲመልሱም፤ “አኹን እንቅስቃሴውን እያደረጉ የሚገኙት ከምእመናን ጋር እንደኾነ ገልጸው፤ ውሳኔውን ግን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲቀርብ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ከዚያ በፊት ግን ከቅዱስ ሲኖዶስ በታች በተዋረድ ካሉ ጽ/ቤቶች ጋር እንነጋገራለን፤” ብለዋል፡፡

ለኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ቅሬታ አቅርበው እንደኾን የተጠየቁት ሰብሳቢዋ፤ “የጣቢያው ባለቤቶች ስሕተት እንደሚሠራ በርግጠኝነት ያውቃሉ፤” ካሉ በኋላ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰቡን በ10 ቀናት ውስጥ በአፋጣኝ አጠናቀው ጥቅምት ላይ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ለሚቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ እየተጣደፉ መኾኑን ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም፤ ጣቢያውም ጥያቄ እናቀርባለን፤ ብለዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት በአዲስ አበባ ለሚገኘው የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ተወካይ ኢንኮም ትሬዲንግ ደውለን፤ እነዚህ ፕሮግራሞች ፈቃድ የሚያገኙት አሜሪካ ከሚገኘው ዋናው መሥሪያ ቤት ስለኾነ በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ነግረውናል፡፡

logo_finalአሜሪካ ከሚገኙት የጣቢያው ሥራ አስፈጻሚዎች አንዱ፤ አቶ ነቢዩ ጥዑመ ልሳን፤ ለአዲስ አድማስ በስልክ እንደተናገሩት፤ ከቅዱስ ሲኖዶሱም ኾነ ከሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ ተቋማት በይፋ የደረሳቸውና በአካልም ቀርቦ ያመለከተ ባይኖርም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚካሔደውን እንቅስቃሴ ተረድተነዋል፤ ብለዋል፡፡ በማስረጃ ተደግፎ የሚቀርብ ነገር ካለም አስፈላጊውን እርምት እንደሚወስዱም አስታውቀዋል፡፡

*               *               *

“ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ”የተባሉ የኢ.ቢ.ኤሰ ቲቪ ፕሮግራሞች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ስለ መጠየቅ

Petition Background (Preamble):

የሀገራችን ሕግ መንግሥት ማንም ሰው የፈለገውን ሃይማኖት የመከተል መብት እንዳለው በግልጽ አስቀምጧል:: ስለዚህ ማንም የፈለገውን ሃይማኖት ያለተጽዕኖ እና ግፊት መከተል ይችላል፤ የሚያምንበትንም ሃይማኖት፣ የሀገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ለማስተማርና ለማስፋፋት የሚከለክለው የለም፤ ነገር ግን የሌሎችን የእምነት ተቋማት ስም በማናለብኝነት በመዝለፍ እና በዚያ እምነት ስም ስብከትም ኾነ ትምህርት በብዙኃን መገናኛ ማስተላለፍ ግን ወንጀልም ኃጥአትም ነው::

ለዚኽም መነሻ የኾነን፣ በኢ.ቢ.ኤስ ላይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም የሚተላለፉ “ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የተባሉ የቴሌቪዝን መርሐ ግብሮች ናቸው:: እኒኽ መርሐ ግብሮች፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደንብ መሠረት የተዘጋጁ እንደኾኑ ይገልጻሉ፤ የሚተላለፉት ዝግጅቶች ግን፣ ከኦርቶዶክሳዊ ትምህርት አንጻር ከፍተኛ ጥያቄ የሚያሥነሱና የብዙውን ኦርቶዶክሳዊ ምእመን ግንባር የሚያስቋጥሩ ናቸው:: በነዚኽ መርሐ ግብሮች የሚራቀቁት ጥቂት የማይባሉት ሰባክያንም ኦርቶዶክሳዊ ያልኾነ የኑፋቄ ትምህርት ሲጽፉና ሲያስፋፉ የነበሩ ውስጠ – ሌላ ሰዎች መኾናቸው በተለያዩ ሚዲያዎች በስፋት ተዘግቧል፤ እየተዘገበም ነው::

በቅርቡ በኢ.ቢ.ኤስ በሚተላለፈው የቴሌቪዥን መርሐ ግብርም ላይ በግልጽ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዘመን ጠገብ ያሬዳዊ ዜማዎች እና የተከበሩ ዘማርያንን “መንደርተኛ” ብለው እስከ መዝለፍ ማለት ደርሰዋል:: ይህ በሃይማኖት ነጻነት ስም የሚደረግ ጠብ አጫሪነት በጊዜ ካልተፈታ በኋላ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ እና ሀገራዊ ችግር መፍጠሩ አይቀርም::

ስለዚህ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ጥያቄዎቻችንን ከዚህ በታች አቅርበናል፡-

1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሱን የቻለ ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ መዋቅር አላት:: ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ይዞ የሚወጣ የአየር ፕሮግራም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ ፈቃድ ወይም ይኹንታ ማግኘት አለበት:: የቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር ውስጥ ያለ አካል መኾን ይኖርበታል:: ቤተ ክርስቲያኒቱ ያላከችው ማንም አካል ግን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ስም ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም::

በዚኽም መሠረት “ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የተሰኙት መርሐ ግብሮች ከቤተ ክርስቲያኗ ሕጋዊ ፈቃድ እስካልተሰጣቸው ድረስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያንን ስም መጠቀም አይችሉም:: ስለዚኽም ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ሕጋዊ ማስረጃ ካላመጡ በስተቀር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም መጠቀም እንዲያቆሙ ቴሌቪዝን ጣቢያው አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድልን እንጠይቃለን::

2. በነዚሁ የቴሌቪዝን መርሐ ግብሮች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና በሚጥስ መልኩ የሚተላለፉ መልእክቶች እና ድርጊቶች እየተበራከቱ መጥተዋል:: ይህም የአንድን ሃይማኖት ክብርና ልዕልና የሚነካ ነው:: በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም የሚከናወኑ ኢ – ኦርቶዶክሳዊ የኾኑ ስብከቶች እና ድርጊቶች የሃይማኖቱ ተከታዮች ላይ የሞራልና የሥነ ልቡና ጫና እያስከተለ ነው:: ሕዝቡ ወደ ሕጋዊ ጥያቄ ከመሔዱ በፊት የኢ.ቢ.ኤስ አስተዳደር አስፈላጊውን እርምት እንዲሰጥልን እንጠይቃለን::

3. በነዚኹ ሰባክያን፣ በነዚሁ የቴሌቪዥን መርሐ ግብሮች ላይ በዐደባባይ “መንደርተኛ” በሚል የተዘለፈው የቤተ ክርስትያኒቱ ዘማሪ ይልማ ኃይሉ በይፋ ይቅርታ እንዲጠየቅ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮም ኾነ መምህራን ላይ ተመሳሳይ ዘለፋ እንዳይከናወን አስፈላጊውን መመርያ እንዲሰጥልን የኢ.ቢ.ኤስን አስተዳደር በኢትዮጵያዊ እና ክርስቲያናዊ ትሕትና እንጠይቃለን::

4. በመጨረሻም እነዚሁ ስብስቦች ለቲቪ ፕሮግራሞቻቸው ማስፈጸሚያ ይኾኑ ዘንድ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ስም የሚያደርጓቸው የስፖንሰር ጥያቄዎችና ልመናዎች በአስቸኳይ እንዲታገዱ እንጠይቃለን::

በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርም፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ስለሚተላለፉት መርሐ ግብሮች ግልጽ መግለጫ እንዲሰጥ እንጠይቃለን:: ከኹሉም በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና እና ታሪክ ከመጠበቅ እና ከማስጠበቅ አንጻር በዚኽ ጉዳይ ላይ ሰፊው ምእመን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡

Sign the petition: “ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ”የተባሉ የኢ.ቢ.ኤሰ ቲቪ ፕሮግራሞች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ስለ መጠየቅ

Advertisements

26 thoughts on “በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ: “ታዖሎጐስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተጋግሎ ቀጥሏል

 1. tizita October 3, 2015 at 5:02 pm Reply

  elellllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllll gena tehadiso yitefal

  • Anonymous October 5, 2015 at 11:59 am Reply

   የወንጌል አይሲስ ሆናችሁ ከመቅረብ ሌላ አንዳች ምክንያት የላችሁም። ምናልባት ሕዝቡ ለወንጌል ያለዉን ጥም ሲያረካ ዲያቢሎስ በተለመደዉ መንገድ ሊጠቀምባችሁ ነዉና እባካችሁ ልብ ግዙ። የወንጌሉ ባለቤት ክርስቶስ ለፔቲሽኑ መልስ ይሰጣልና ብዙም የሚያስጨንቅ አይደለም። ይህንን በእዉቀት ማነስ የተበተባችሁትን ሕዝብ ለክፋ ዓላማችሁ ለማዋል ማቀዳችሁ ያስጠይቃችሁዋልና ንሰሐ ግቡ።

   • ዳሞት October 10, 2015 at 8:24 pm

    አቶ ወይም ወይዘሮ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት፣ የወንጌል አሥተምሮ፣ ዝማሬና የመዝሙር ስርዓት፣ የአምልኮ ሥርዓት፣ መጽሐፍ ቅዱስና ቅዱሳት መጽሐፍት እና ለቅዱሳን የሚሰጥ ክብር ካልተቀበልህና ካላሳመነህ ወደ ምትቀበለውና የምታምንበት መሔድ መብትህ ነው። ማንም በሰንሰለት አሥሮ አልያዘህም።
    ሆኖም ቤተክርስቲያንን እየተቃወምህ፣ እየተሳደብህ፣ ከሐዋርያት የተለየ ወንጌል እየሰበክህ፣ ከሀይማኖታዊ ሥርዓት ውጭ እየተመላለሥህ፣ ክርስቶስን ሳታምን እያስመሰልህ ለጥፋት ተግባርህ ማራመጃ የማታምንባት የአኮርቶዶክስ ተዋህዶን ሥም መጠቀም ግን አትችልም።
    ከዛ ውጭ ህዝቡ ለወንጌል አያላችሁ የምታላዝኑት ማላዘን ያው የእባብነት ምልክታችሁ ነው። ወንጌል በሚል ስም ወንጀልና እንክርዳድን ነው የምትበትኑት።

 2. Abraham dujen October 3, 2015 at 7:31 pm Reply

  Egzihabeher amlak yerdach hulem kegonach nen bebetekrstiyan yemtabenen enewagalen tere tehadeso yewedem

 3. Anonymous October 3, 2015 at 8:27 pm Reply

  Bemegemeria patriarku erasun yaswogid yalezia dr shiferaw ha.mariam ena esu maehtemachnin masbetesache aykerim

 4. Anonymous October 4, 2015 at 1:39 am Reply

  I can’t sign the petition can you guys do something???? Please.

  • haratewahido October 4, 2015 at 11:02 am Reply

   Please go to the link: “ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የተባሉ የኢ.ቢ.ኤስ ቲቪ ፕሮግራሞች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ስለ መጠየቅ and sign the petition. Thank you.

 5. yeabneh October 4, 2015 at 10:10 am Reply

  egzihabiher yirdachu beritu bizu hizibina wetat kegonachu ale

 6. semhal October 4, 2015 at 11:45 am Reply

  ስለ እግዚአብሄር ለኔም ፈርሙልኝ

 7. million mulugeta October 4, 2015 at 11:51 am Reply

  እግዚአብሔር ይርዳችሁ አይይይይይይ እነሱ በቤ/ክ ላይ እንደቀለዱና አደንደዘበቱ አይቀሩም

 8. Anonymous October 4, 2015 at 1:14 pm Reply

  ktabiayw maskom beca sayhon k betkrstiyan endiwgzu mesrat yegbal . zare beglth tlalaky eylaku tmhrtacwn ketlwal.
  be saris abo sbkt wnegel yetmdbut 3 hlafiwoc yenersun sra ymisru nacw
  b wreq sefr mariam yalw sbaki wnegel tmsegne blay beglt ythadson sra eyaseru yalu nacew hbert endzi fetren kbetkrstyan marak yegbanal . begza enzebacen eyatfun newna

 9. ታዛቢው October 5, 2015 at 9:24 am Reply

  ጥቂት ለመናገር ያሕል!!
  1. 100ሺህ ፊርማ ተሰበሰበ ተባለ፡፡ማስረጃ ግን የጠየቀም ያቀረበም የለም፡፡በጨበጣ እንተማመን ነው ነገሩ፡፡እንዲያ ባይሆን መልካም ነው፡፡
  2. እኔ ባለኝ መረጃ የፕሮግራሞቹ አዘጋጆች በይፋ ውጉዛን(የተወገዙ)አይደሉም፡፡ስለዚህ መጀመሪያ እነሱን ማናገር ማንን ገደለ!ውግዘት እና መፈክር አይምታታ፡፡ከቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ በፊት ባልተሰጠ ስልጣን ስም መስጠት ጸያፍ ነው!ኢ-ሥርዓታዊ ነው!
  3. ‹‹ዶግማ፣ቀኖና፣ዝማሬ አንኳሰሱ፤የትውልዱን እምነት አናወጹ›› ተባለ፡፡ማስረጃ ግን አልቀረበም፡፡መቼም ፕሮግራሙ በግልጽ የሚተላለፍ ነውና ለዚህ የቪዲዮ ማስረጃ ማቅረብ አይገድም፡፡ስለሆነም አስቦና በማስረጃ ተመርኩዞ መናገር አይከፋም፡፡ወትሮም እንዲህ ተብሎ ተብሎ ተብሎ መጨረሻ ቢታይ የተልፈሰፈሰ ማስረጃና መፈክር ብቻ ሆነ፡፡የሊቃውንት ጉባኤ የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ.ም በጋሻውን በነጻ አሰናበተ፡፡ሌሎችማ ለክስም አልቀረቡ፡፡ታዲያ በውሳኔውና እርቁ ሁሉም ውሳኔ-ሲኖዶስን ዘንግቶ ተንጫጫ፡፡ለአባቶች ስም ሰጠ!የዋህ!ስመ-ክርስትናን ሰርዞ ከቅድስት ቤ/ክ መነጠል እንዲህ የፌስቡክ ፕሮፋይል እንደመቀያየር ቀላል መሰለህ!ተው!መንጋ አንሁን!
  4. ጋዜጣው የፕሮግራሙን አዘጋጆችና የቤተክርስቲያኒቱን የአስተዳደር አካላት ማናገር ሲችል አላናገረም፡፡የተለመደ የአዲስዓድማስ የእወደድባይነት ስሑት አካሄድ!
  5. ‹‹ኑፋቄያቸው በግልጽ ይታወቃል›› ብሎ የልመና ክስና ፍርድ የለም፡፡የከሰሰ አካል ክሱን በማስረጃ ማቅረብ ግዴታው ነው፡፡ያለበለዚያ ራሱ ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡ሰው ክቡር ፍጡር ነው፡፡ክቡርነቱ ከስሙ ይጀምራል፡፡ያለማስረጃ ስም ሰጥቶ ማሳደድ ደግ አይደለም፡፡ሕግና ሥርዓተ-ቤተክርስቲያንም አይደግፉትም፡፡
  6. ልጆቹ የቤ/ክ መድረክ ሲጠይቁ በፍረጃ መድረክ ይዘጋባቸዋል፡፡ለክልከላውም የድል ከበሮ ይመታል፡፡አንዳንድ አጥቢያዎች ሲፈቅዱላቸው ፈቃጆቹ የውግዘት መዓት ይወርድባቸዋል፡፡ሊቃነጳጳሳት ሳይቀሩ ከእነሱ ጋር ከታዩ ዘለፋው ሌላ ነው፡፡ተማርረው ቀረጻቸውን በዓለማዊ አዳራሾች ሲያደርጉ ደግሞ ምዕመኑን አስኮበለሉት ብሎ የክስ ጋጋት ይደረደራል፡፡በሁለት ወገን እንዲህ አድርጎ ወጥሮ ለማስወጣት መሞከር ከቶ ደስ የሚል አይደለም፡፡ያሳዝናል!ቢያንስ የማኅበረቅዱሳን ቀረጻ በቤ/ክ ውስጥ ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነ አውናውቃለን–የማኅበሩ ህንጻ እንደ ቤተመቅደስ ይቆጠራል ካልተባለ በቀር!ማኅበሩ በወመዘክርና በግዮን በ6ኪሎው የስብሰባ ማእከል አያሌ ዝግጅቶችን ሲያደርግም እናውቃለን፡፡እናም እነሱን ብቻ ለይቶ ማጣደፍ ፍትሐዊ አይመስልም፡፡
  7. እርግጥ ነው ልጆቹ ደፈር ብለው ኃይለቃላትን ይወረውራሉ፡፡ሆኖም ከሊቃውንት ጉባኤ ተግሳጽ በኋላ ይሄ አነጋገራቸው የታረመ ይመስለኛል–በተለይ ታኦሎጎሶቹ፡፡ስለክብረ-ቅዱሳን እና ስለሥርዓተ-ቤተክርስቲያን በፕሮግራሞቻቸው እምብዛም አለመነሳቱ ሁላችንንም ያሳስበናል፡፡ሆኖም ደግሞ አስተምህሮውን ነቅፈው ሲሰብኩ አልተሰማም፡፡ስለዚህ በንግግር ነገረ-ቅዱሳንንም እንዲያካትቱ መወትውት ከውግዘቱና ከማሳደዱ በፊት ቢቀድም ክፋቱ አይታየኝም፡፡
  8. በተጓዳኝ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮዎችን የሚያጎለብቱ ፕሮግራሞችን ማስፋት፣ማኅበራዊ ሚዲያዊና ለገንቢ ሚና መጠቀም፣የማታ የስብከተ-ወንጌል መርሐ-ግብሮችን ማጠናከር፣ሰ/ት/ቤቶች ያላቸው የት/ት ስርዓት እንዲጠብቅ መስራት አግባብ ይሆናል፡፡ምክንያቱም ባለፉት ዓመታት እነበጋሻውን ከየመድረኩ ማሳደድ በተለይ በከተሞች አካባቢ እንደስኬት ቢታይም ከእነሱ በኋላ የማታ የስብከተ-ወንጌል መቀዛቀዙ የማይታበል ሀቅ ነው፡፡የማሳደዱን ያህል ለስብከቱም እንበርታ!ከበረታን ብቻ ነው በቀላሉ ልቡ የማይሸፍት ኦርቶዶክሳዊ ማፍራት የሚቻለው፡፡በየደረሰበት ስድብ-ስንቁ የሆነ ትውልድ መኮትኮት ወንዝ አያሻግርም፡፡
  9. እንዲህ አይነት ዘመቻዎች በድንገቴና እንደ ዘመድኩን በቀለ ባሉ አንደበታቸው ያልታረመ፣ንግድና ሃይማኖት የሚቀይጡ፣ቲያንስ እና ሐዋርያዊ ጉዞ የተምታታባቸው፣ሁሉን ከማነወር የማይመለሱ ሰዎች ሳይሆን በእውቀትና በማስተዋል በሚራመዱ የቤተክርስቲያን ልጆች ሊመራ ይገባል፡፡ውግዘት በድምጽ ብልጫ የሚወሰን የቡድን ስራ ሳይሆን በማስረጃ፣በእውቀት፣በእውነት፣በፍትሕ እና በርትዕ በሥልጣነ-ክሕነት የሚፈጸም ተግባር ነው፡፡ስለዚህ ርትዕት ሃይማኖታችንን ከነቅዱስ መጽሐፏና ትውፊቷ አስጠብቆ ለትውልድ የማስተላለፍ የዕቅበተ-ሃይማኖት ተግባር ለዚህ አካሄድ በበቁ ሰዎች ሊመራ ይገባል፡፡
  10. ቅዱስ ሲኖዶስ ከቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና አንጻር ሁሉንም ወገን እኩል የሚገዛ የሚዲያ ሕግና ሥነ-ምግባር ሊቀርጽ ይገባል፡፡ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ለመጀመር ከዚህ በፊት ሁለት ሦስት ጊዜ ያጸደቀውን ውሳኔም ወደ ተግባር ሊያወርድ ይገባል፡፡ሦስት ኮሌጅ፣17 መምሪያ፣ከሦስት በላይ ግዙፍ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ከ10 በላይ የካሕናት ማሰልጠኛ፣ከ40 ሚሊዮን የተሻገረ ምዕመን፣ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁ ካሕናት፣ከ50 በላይ አህጉረ-ስብከቶች፣….ያሏት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በሚዲያ በኩል ያላት ተደራሽነት በዚህ ደረጃ የወረደ መሆኑ ያሳዝናል፡፡የጥቅምቱ ጉባኤ ይሄንንም ቢያስብበት መልካም ነው፡፡በመረጃ እጦት የቤ/ክ ልጆች ዘወትር በብሎግና በፌስቡክ ወሬ ሲታመሱ ማየት ደስ የሚያሰኝ አይደለም፡፡ቸልተኝነቱ ተቋሙንና አባቶችንም ከማሳነሱ በላይ ከማኅበረ-ምዕመናን ጋር ያላቸውን ሥርዓታዊ ግንኙነትም እያስተጓጓለ ነው፡፡ይታሰብበት!ውግዘት ያለማስረጃ በነዘመድኩን በቀለ የጥላቻ ዘመቻ ብቻ ከቀጠለ ግን እንዲህ እንቀኛለን፡-

  ኢይሴፈዎ፡መኑመ፡ለዘሲኖዶስ፡ልዕልና፣
  እስመ-ለወጊዝ፡አልጸቀት፡አማተሪዝም፡ዲቁና፡፡

  • Anonymous October 15, 2015 at 6:29 am Reply

   Really nice comment!!

 10. Anonymous October 5, 2015 at 11:14 am Reply

  አንድ ያልገባኝ ነገር አለ። በእዉነት እነዚህን ጣቢያዎች ለአንድ ቀን አዳምጣችሁ ታዉቃላችሁ?. ምኑጋ ነዉ ቀኖና የተጣሰዉ? ስለቀኖና የተነገረበት ጊዜስ መቸ ነዉ? ጣቢያዎቹ በቀጥታ ወንጌልን ከመሰበክ ዉጪ የማንንም ሃይማኖት ሲፃረሩ አልሰማሁም። ይህንን የምመሰክረዉ ስለ እዉነት ነዉ። ፔቲሽን ፈራሚዎች ሆይ እንዳይቆጫችሁ በመጀመሪያ በጣቢያዎቹ የሚተላለፉትን አዳምጡ። ያለበለዚያ ወንጌል እንዳይሰራጭ እንቅፋት በመሆን ነገ ባለቤቱ ይጠይቃችሁዋል። ይልቁኑ የሌሎቹም ጣቢያዎች ተደማጭ እንዲሆኑ አሁን በአኮቴትና መሰል መስኮቶች ብቅ የሚሉትን ሰባኪዎች ደረጃ ከፍ አድርጉ። ሕዝቡ የተጠማዉ ወንጌል እንጂ ታሪክና ባህል አይደለም። እኔንም ጨምሮ።

 11. fasil October 5, 2015 at 12:32 pm Reply

  from the beginning those TV services were established by some selfish individuals but not by the church.

 12. Anonymous October 6, 2015 at 6:09 pm Reply

  I like tazabiw’s comment!
  bemejemeria eyetewenejelu yalut yemi’erabawuyanin zeye tewahiduwachew tsinfi yizew protestant protestan yemishet nigigirachewun orthodoxawi leza bisetut des yilegnal.yam bayihon gin enede taliyan werera gize beneberu ethiopiawuyan wonew lelela agerachewun letilat asalifew endemisetu bandawoch betarik tewekash tihonalachihu enji be Orthodox tewahido lay kintat lewut yemitametu ayimselachihu.
  le ahimed giragn,le kibat na tsega,lecatholicawuyan ena le yodit guditim alitesaka.silezihim wede libachihu enditimelesu betihut kal be akibrot eteyikalehu.

  tekorkuri nen bemalet bewedeke gind misar yibezal endemibalew besimet bicha ende alemawu neger gedel lemekitet yemititadefit bemastewal adirgut.
  hulet tsinfegnoch atihunubin. andu eyesu bicha lelaw degmo kidusan kidusan bicha endibal yemitifeligu. huletum bemasmamat yemihedu nachew.minim enkuan yesibket hulu maekel kirstos bihonim.

 13. Takele dadi October 7, 2015 at 6:29 am Reply

  እነ በጋሻው ተሐድሶ መሆናቸውን መርምሮ ያረጋገጠው ሲኖዶስ ማህበረ ቅዱሳን ይባላል፡፡ ማህበሩ በኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሲቲየን ጉዳይ ላይ ማንኛውንም ውሳኔ ለመወሰን ሥልጣን ከላይ ከሰማይ የተሰጠው ስለሆነ እሱን የሚቃወም ሁሉ ይቀሰፋልና ጳጳስም ቢሆን ፓትርያርክ ዝም ይበል፡፡ አይቆጣ! አይቅጣ!! ስምንተኛው ሺህ እስኪመጣ ድረስ ያሻውን እንዲናገርና እንዲያዝ፣ የሚበቃውንም ያህል ሀብት ይዞ ቤተ ክርስቲያንን የሚገዛበትና የሚቆጣጠርበት የኒውክለር ጦር መሳሪያ እንዲያመርት ጊዜ ይሰጠው፡፡

 14. birhanu October 7, 2015 at 4:37 pm Reply

  Bemejemeriya benante bekul yalewn neger fetshu. Ye poletica intervention yelem? Anid neger awkalew enante endastemarachihun , Christos hulunim ewnet yawtalin.

 15. Anonymous October 8, 2015 at 4:52 pm Reply

  The teaching on Tao-logos is more or less as per the Dogama of EOTC. However, the songs have derailed from Yardew and some comments given by Begashew are controversial!
  With Regared Kale- awdie it is not as per dogam and canon of EOTC. He did not metion about our Holy Vergin Mary during Felseta. The preaching is is in general protestant style which does not reognize the saintst and angles.

 16. solomon October 28, 2015 at 5:17 pm Reply

  e/r yestachu..,

 17. ወ/ተክለሀይማኖት December 31, 2015 at 4:55 pm Reply

  እግዚአብሔር እንደ ብረት ምሰሶ ያጽናችሁ!!! በሀይማኖታችን ፀንተን ለመኖር እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቀን አሜን!!

 18. hazen hazen February 8, 2016 at 5:05 am Reply

  በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ
  የተሐድሶው ቡድን የስብሰባ ዉሎና ዉሳኔው
  ዛሬ በ22/4/08 ዓ/ም ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፉን አጥቶ ሲመክር
  ያደረው የተሐድሶው ቡድን ከ1ኛ ዓመት እስከ 4ኛ ዓመት ያሉትን
  ደቀመዛሙርት ሰብስቦ የሞኝ ለቅሶውን ሲያስለቅስ ዋለ።
  ከጠዋቱ 3፡15 ሰዓት እስከ 6፡45 ሰዓት የፈጀው የተሐድሶው
  ቡድን ስብሰባ በቀንደኞቹ ተሐድሶዎች ብርሃኔ ፥ ግርማ እና
  ጎይቶም የስብሰባ መሪነት 2 አጀንዳዎችን ያቀረበ ሲሆን
  የቀረቡት አጀንዳዎችንም ስንመለከት ፥- 1ኛ፡ ሁላችንም
  ሳንከፋፈል አንድ ሁነን የማህበረ ቅዱሳንን ህልውና እንዴት
  ማጥፋት አለብን ፥ 2ኛ፡ ንጹህ የሆነውን የኮሌጃችንን ስም
  እያጠፋ ያለውን ድህረ ገጽ ጸሐፊ እንዴት ማግኘት እና ድህረ
  ገጹንስ እንዴት ማዘጋት አለብን ፥ የሚሉ ናቸው። በስብሰባውም
  ላይ ተመላላሽ ተማሪ የሆኑት ቀንደኛ ተሐድሶዎች ታረቀኝ እና
  አበበን ጨምሮ ሌሎች ስም ዝርዝራቸው ይፋ የሆነው መናፍቃን
  ያነሷቸውን ነጥቦች ስንመለከት ፥- 1ኛ፡ ማህበሩን ከመንግስት
  ጉዳይ ጋር በማያያዝ ተሰልፈን ወደ መንግስት አካል በመቅረብ
  ህልውናውን ማጥፋት አለብን ፥ 2ኛ፡ በማህበሩ ላይ ክስ
  መመስረት አለብን ፥ 3ኛ፡ ማህበሩ ሲኖዶሱ ሳይፈቅድለትና
  ኤዲት ሳያስደርግ ላወጣው ጋዜጣ በስህተት መሆኑን ገልጾ
  ማስተባበያ ይስጥልን ፥ 4ኛ፡ ከደቀመዛሙርቱ ውስጥ
  ምስጢራችንን የሚያወጡ የማህበሩ አባላት ከኮሌጁ ይባረሩልን
  ፥ 5ኛ፡ፓትርያርኩ ሲመጡ ኣባ ጢሞቴዎስን ከፊት እኛ ከኋላ
  ጥቁር ለብሰንና ተሰልፈን በመቅረብ ነፃነታችንን ማሳወጅ አለብን
  ፥6ኛ፡ በክፍል ውስጥም ይሁን ከክፍል ውጭ እንዳሻችን
  እንዳንሆን የሚገስጹን መምህራን ላይ እርምጃ ይወሰድልን ፥
  7ኛ፡ ወደፊት ወደየሀገረ ስብከታችን ስንሔድ ተቀባይነትና
  ተአማኒነት እንዲኖረን ፓትርያርኩ ለየግላችን ደብዳቤ እንዲጽፉ
  ይደረግልን ፥ የሚሉት ናቸው። በመጨረሻም የተሐድሶው ቡድን
  በተነሱት ነጥቦች ላይ በመወያየትና ነጥቦቹን ተቀብሎ ውሳኔ
  በማሳለፍ ከቀንደኞቹ የተሐድሶው ቡድን አስተዳደር ሰራተኞች
  ጋር ሆነው ውሳኔውን ሊያስፈጽሙ የሚችሉ ከየባቹ አንዳንድ
  ደቀመዛሙርትን በመምረጥ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ስምምነቱን
  በፊርማው የማያረጋግጥ ደቀመዝሙር ከኮሌጁ እንዲባረር
  በመወሰን ስብሰባውን ( የሞኝ ለቅሶውን ) አጠናቋል። ግን ግን
  የተሐድሶው ቡድን ማንን ይሆን ለማታለል የሚሞክረው ? ጤፍ
  በሚቆላው ምላሱ የቤተክርስቲያኒቱ ነኝ ብሎ ለመምሰል እና
  ለማጃጃል የሚሞክረውስ ማንን ይሆን ? ዛፉ መራራ መሆኑ
  በፍሬው ያልታወቀ መስሎት ይሆን ? በተሐድሶው ቡድን
  አመለካከት ከቤተክርስቲያኒቱ ጎን የቆመ ሁሉ የማህበሩ አባል
  ነው ። በግቢው ውስጥ ስለነገረ ቅዱሳን ያነሳ ሁሉ የማህበሩ
  አባል ነው ። ለእነሱ በህግና በስርዓት እንመራ ያለ ሁሉ
  የማህበሩ አባል ነው ። ለነሱ ከማህበሩ አባላት ውጭ ሌላ
  ኦርቶዶክስ የለም ። አንተ መቃብርህ እየተማሰ ያለኽው
  የተሕድሶው ቡድን ከማህበሩ አባላት ውጭ የሚያሳድድህ
  ቢሊዮን ቁርጠኛ የኦርቶዶክስ ልጅ ስለመኖሩ ወደፊት
  እንደለመድከው ስዘባርቅና ከአውደ ምህረቱ አንቆ ሲያወርድህ
  ትረዳዋለህ ። ይቆየን ፡፡ **** ሼር ሼር ሼር ማድረግዎትን
  አይርሱ፡፡

 19. Anonymous December 21, 2016 at 12:57 pm Reply

  ማን ይሆን ልበ ንፁህ እግዚአብሔርን የሚያይ!

  በእውነት ክርስትና ስለ ወንድማማቶች ምን ትላለች ጥል፣ ጭቅጭቅ፣ ማሳደድ፣ ያልተፈቁዱ ናቸው ይልቁስ ስለወንድሙ አንዱ ለአንዱ እንዲፀልይ ታስገድዳለች እንጂ ፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያን የተሸከመውን ሐዋሪያዊ ተልዕኮ ለመፈፀም ደፋ ቀና ማለት ሲገባው በአዳራሽ ተሰበከ….. በማለት ባገኙት ቦታ ሐዋሪያዊ ተልዕኮ ለመፈጸም የሚታትሩትን ማሳደድ —-ለማን ይሆን የቀናነው፡፡እባካችሁ እነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ፣ — ታላላቅ ሐዋሪያቶች የተሰውት ክርስቶስን በመስበካቸው መሆኑን አንርሳ፣ እነሱ በተደላደለ ቦታ ሆነው አልነበረም የሰበኩት ባገኙት ቦታ ነበር፣ ማህበረ ቅዱሳን ሃይማኖታዊ ተልዕኮ የጨረሳችሁ አይመስለኝም ይልቁንም እሱ ላይ መበርታት አይሻልም፣ ወገኖችን ከማሳደድ ያልተፈቀደውን ከማድረግ፡፡

 20. Haylemeskel Habtegebrel May 25, 2017 at 4:52 pm Reply

  yetekeberachihu wtd yewengel arbejochachin bteley beteley memhir Zebene betam yemnadenkhu sebakiychn Egziabher kerzemenhin ybarklo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: