ጠቅላይ ቤተ ክህነት: በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሕንፃዎች ግንባታና በጀት ላይ ጥያቄዎች አነሣ

 • ጽ/ቤቱ÷ መመሪያ ያልተሰጠበት የደብሩ የሚሊዮን ብሮች የበጀት ጥያቄ እንዲዘገይ አዟል
 • ሥራ አስኪያጁ÷ የሀ/ስብከቱን የአስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ በማፈን ግንባታና በጀቱን ፈቅደዋል
 • ሊ/ማ የማነ÷ የደብር ጸሐፊም የሀ/ስብከትም ሥራ አስኪያጅ ኾነው ለተጠያቂነት አስቸግረዋል
 • በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በምክትላቸው መካከል የውዝግብ መንሥኤ ኾኗል

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፲፰፤ ቅዳሜ መስከረም ፰ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

St. George church and bld
የአራዳው መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር፣ እያሠራው የሚገኘው የሁለገብ ሕንፃ ግንባታ፣ ተደርጎለታል ባለው የዲዛይን ማሻሻያ ሰበብ በልዩነት የሚያስፈልገው ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እና ከባለሀብቶች ጋር በመተባበር ለማስገንባት ያቀዳቸው የሌሎች ሁለት ሕንፃዎች ግንባታ እና በጀት እንዲጸድቁለት ያቀረባቸው ጥያቄዎች፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መመሪያ ያልተሰጠባቸው በመሆናቸው “በአሉበት ሁኔታ እንዲቆዩ” የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አዘዘ፡፡

pat head off on Arada St. George Churchየአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባኤ፣ በደብሩ ግንባታዎች እና የበጀት ይጸደቅልኝ ጥያቄዎቹ ላይ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር መጨረሻ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች፣ ለአፈጻጸም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሳይላኩለት የቆዩበት ምክንያት እንዲብራረለትም ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከትላንት በስቲያ፣ መስከረም ፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ለሀገረ ስብከቱ በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል፡፡

የደብሩ ሰበካ ጉባኤ የልማት ዕቅዶች በሀገረ ስብከቱ በኩል እንዲጸድቁለት ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. መጠየቁን ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ባስታወሰበት ደብዳቤው፤ ዲዛይኑ ለተሻሻለው ሁለገብ ሕንፃ ማሠሪያ እንዲሁም በስተምሥራቅ የሚገኙት ሱቆች ፈርሰው በምትካቸው ባለሁለት ፎቅ ሕንፃ መሥራት ይቻል ዘንድ የብር 6 ሚሊዮን በጀት በደብሩ እንደተመደበ፣ በጥያቄው ላይ ለመወሰን ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከተሰበሰበው የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ቃለ ጉባኤ መረዳቱን ጠቅሷል፡፡

በዕለቱ፣ በምክትል ሥራ አስኪያጁ መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር በተመራው የአስተዳደር ጉባኤው ስብሰባ፣ በደብሩ የቀረበው የበጀት ይጸድቅልኝ ጥያቄ፣ “ከባድና ከሀገረ ስብከቱ አቅም በላይ” ኾኖ እንደተወሰደ ተጠቁሟል፤ ወጪው ከ61 ሚሊዮን ወደ 171 ሚሊዮን ያደገው የዲዛይን ክለሳ ጥናት በገለልተኛ ባለሞያዎች ተገምግሞ፣ ውጤቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዲላክ እና በዚያው በኩል እንዲጸድቅ፤ የሁለት ተጨማሪ ሕንፃዎች ግንባታ ውሎችም ለአስተዳደር ጉባኤው ቀርበው እንዲታዩና የውሳኔው ቃለ ጉባኤም በምክትል ሥራ አስኪያጁ ሸኚ ደብዳቤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እንዲላክ ከስምምነት ተደርሶበት እንደነበር ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አውስቷል፡፡


ከሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ

A.A Dio Admin council on St. George blds

በተለይ የኹለገብ ሕንፃ ግንባታው ከ61 ሚሊዮን ወደ 152 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍ ያለበትን ምክንያት፤ ገለልተኛ ባለሞያ በጨረታ ወይም ለሀገረ ስብከቱ አመቺ በኾነ ሌላ መንገድ ተመድቦ በደብሩ መሐንዲሶች የቀረቡትን ኹለት ጥናቶች ገምግሞ ውጤቱን ካቀረበ በኋላ በጥናቱ ላይ በመመሥረት ፕሮጀክቱ በጉባኤው ተገምግሞ ውጤቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲላክና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል እንዲጸድቅ፤ በኹለገብ ሕንጻ ግንባታው ተጫርተው የተሸነፉ፣ ያሸነፉና ቀጥታ ተሳትፎ ያላቸው የምሕንድስና ባለሞያዎች ወይም ድርጅቶች በገለልተኛ የባለሞያ ጨረታው ላይ እንዳይሳተፉ፤ የገለልተኛ ባለሞያዎቹን ክፍያ ደብሩ እንዲሸፍን በደብዳቤ እንዲገለጽለት፤ የአስተዳደር ጉባኤው አባላት በሙሉ እየተገነባ ያለውን ኹለገብ ሕንፃ ቦታው ድረስ በመገኘት እንዲመለከቱ /እንዲጎበኙ/ ይህም በተቻለ ፍጥነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተከናውኖ ጥናቱ እንዲጸድቅ፤ /ከውሳኔው ቃለ ጉባኤ/


ይኹንና ውሳኔዎቹም ኾኑ የውሳኔዎቹ ቃለ ጉባኤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ እንዳልተላከ ጠቅሶ፣ ለሦስት ወራት ሳይላክ የዘገየበት ምክንያት ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር እንዲብራራለት የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት አዟል፤ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ደብርን ጨምሮ የ48 አድባራትን የመሬትና የገቢ ማስገኛ ተቋማት አጠቃቀምና የኪራይ አፈጻጸም ያጣራው አጥኚ ኮሚቴም፣ ጉዳዩን ተከታትሎ እንዲያስፈጽም በደብዳቤው ግልባጭ መታዘዙን ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

በቤተ ክርስቲያኒቱ የቃለ ዐዋዲ ድንጋጌ አንቀጽ ፲፪ ንኡስ አንቀጽ ፰፣ ቋሚ ንብረትንና ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቁ ጉዳዮች በሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉት ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ቀርበው ፈቃድ ሲያገኙ ብቻ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ አልፎ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት እንደመኾኑ፣ በአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያቱ ለሀገረ ስብከቱ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አማካይነት ለፓትርያርኩ እየቀረቡ አመራር ሲሰጥባቸው፣ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በመመሪያው መሠረት ማስፈጸም ይኖርበታል፡፡

በዚኹ አግባብ፣ በሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት የተላለፈው ውሳኔ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አማካይነት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀርቦ አባታዊ መመሪያ እስከሚሰጥበት ድረስ የደብሩ የግንባታና የበጀት ይጸድቁልኝ ጥያቄዎች በአሉበት ኹኔታ እንዲቆዩ ይደረግ ዘንድ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሀገረ ስብከቱን አዟል፡፡

ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ይህን ይበል እንጂ፤ ደብሩ በጥያቄው መሠረት ግንባታውን እንዲቀጥል የሚገልጽ ነው የተባለ ደብዳቤ በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ለደብሩ አስተዳደር አስቀድሞ መጻፉን የሀገረ ስብከቱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ የደብሩም ዋና ጸሐፊ እንደኾኑ የጠቀሱት ምንጮቹ፣ በአንድ በኩል ጥያቄ አቅራቢ በሌላ በኩል ፈቃጅ በመኾን የፈጸሙት ተግባር የተጠያቂነት መርሖዎችንና የአስተዳደር ጉባኤውን ውሳኔ ከመፃረሩም በላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከምክትል ሥራ አስኪያጁ ጋር እየተካረሩ ለመጡበት አለመግባባቶችም አንድ መንሥኤ መኾኑን አስረድተዋል፡፡

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር÷ በሕንፃዎች፣ በሱቆች እና በባዶ መሬት አጠቃቀምና የኪራይ አፈጻጸም፣ የአሠራር ችግር እንዳለባቸው ከተዘረዘሩት 15 ገዳማት እና አድባራት አንዱ እንደኾነ፣ በፓትርያርኩ ትእዛዝ የተሠየመው ኮሚቴ ባካሔደውና በጠቅላይ ጽ/ቤቱ አማካይነት ለቋሚ ሲኖዶስ በቀረበው ጥናታዊ ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡

እንደ ሪፖርቱ፣ የደብሩ ኹለገብ ሕንፃ፣ የዲዛይን ማሻሻያ በሚል ሰበብ ወጪው ከ61 ወደ 171 ሚሊዮን ብር ያደገ ሲኾን አዲስ ተቆጣጣሪ መሐንዲስም በደብሩ ዋና ጸሐፊ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጠቋሚነት ያለጨረታ ተቀጥሯል፡፡ ሀገረ ስብከቱና ሊቀ ጳጳሱ ለአዲሱ የዲዛይን ጥናትና ከብር 110 ሚሊዮን በላይ ላሳየው የዋጋ ጭማሪው ዕውቅናና ፈቃድ ባልሰጡበት ኹኔታ ግንባታው በልማደኛው እና ቀንደኛው አማሳኝ ኃይሌ ኣብርሃ አስተዳደር ፍላጎት መቀጠሉም አግባብነት እንደሌለው በሪፖርቱ ተገልጧል፡፡

YeYemane sost tatoch

ምዝበራንና ኑፋቄን በመቃወምና በማጋለጥ በበጎ ፈቃድ የሚያገለግሉ ሰበካ ጉባኤያትንና የሰንበት ት/ቤቶችን ያግዳሉ፤ መንፈሳውያን ማኅበራትንና አባሎቻቸውን በአክራሪነት ይከሣሉ፤ በሌባ ጣትዎ ወደ ሌላው ሲቀስሩ ሦስት ጣቶችዎ ግን ወደ ራስዎ ያመለክታሉ! የተቃወሟቸው የተቋማዊ ለውጥ ጥናቶች፣ ጥናታዊ ሪፖርቶችና በዋና ሥራ አስኪያጅነት የሚመሩት የሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ ሳይቀር በተደጋጋሚ ያረጋገጡትም ይህንኑ ሐቅና አዝማሚያ ነው፡፡

 

 

 

ቋሚ ሲኖዶስ፣ ጥናታዊ ሪፖርቱን ሙሉ በሙሉ በመቀበል ውሳኔዎችን ማሳለፉን ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በደብዳቤው ገልጾ÷ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብርን ጨምሮ በተዘረዘሩት 15 ገዳማት እና አድባራት የ‘ልማት አርበኞች’ በሚባሉ አማሳኝ ሓላፊዎች በተፈጸመው ኢ-ፍትሐዊ አሠራር፡-

 • በተናጠልም ኾነ በጣምራ ተጠያቂ የሚኾኑ የአመራር አካላት ከተሰበሰቡት ማስረጃዎች ጋር በንጽጽር እንዲቀርቡለት፤
 • የሕንፃዎቹ፣ የሱቆቹ እና የባዶ መሬቶቹ የኪራይ አፈጻጸም እና የመካናተ መቃብሩ አጠቃቀም የሚመሩበት መተዳደርያ ደንብ፤ የጨረታ ደንብ፤ የአከራይ እና ተከራይ የውል ሰነድ በማእከላዊነት በባለሞያዎች ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ፤
 • ጥናቱ ባልሸፈናቸው ሌሎች ገዳማት እና አድባራት ላይም እንዲቀጥል መታዘዙንም አስታውቋል፡፡
Advertisements

6 thoughts on “ጠቅላይ ቤተ ክህነት: በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሕንፃዎች ግንባታና በጀት ላይ ጥያቄዎች አነሣ

 1. Anonymous September 21, 2015 at 1:41 pm Reply

  ምክትሉን በሃይማኖት ህጸጽ እንዳልተቃወማችሁ ዛሬ የማነን ለመቃወም እምነተ ቢሱን ደግፋችሁ ስትጽፉ ትንሽ አታፍሩም፡፡ ምነው ምክትሉ የሀገረ ስብከቱን ኮሪደር ጎጃም በረንዳ ሲያደርገው አፋችሁን ያዘው፤ የአስተዳደር ጉባዔው ውሳኔን ስናነበው እኮ የ6 ሚሊየን ብሩ ህንጻ ይሠራ ነው የሚለው፤ ያኛው ደግሞ ይጠና፡፡ ታዲያ ጉባዔው የፈቀደውን እንፈጸም ደብዳቤ ቢጽፍ ምን ቸገራችሁ፡፡ ይብላኝ እናንተን ተቆርቋሪ ብሎ ለሚሰማ

  • Anonymous September 21, 2015 at 9:09 pm Reply

   የአራዳው አኖኒመስ፣ የለመደብህን ማጭበርበር እዚያው ቦሌና ሃያ ሁለት ሺሻ ቤት አድርገው! አንተስ ለፕሮፓጋንዳህ ሊቁ አእመረ ስትለውማ አልነበር? እምነተ ቢስነቱና ጎጠኛነቱ ዛሬ ነው የታየህ?

   በዜናው የተጠቀሰው ስለ ብልሹ አሠራርና ሙስና በአጠቃላይ ስለ አስተዳደር ጉዳይ ስለሆነ ዝም ብለህ አትወሻክት! የአስተዳደር ጉባኤውም ውሳኔ፣ ‹‹ውሉ ለጉባኤው ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ የግንባታው ጥያቄ እንዲጸድቅ››፤ ‹‹የሥራ ተቋራጩ ያለጨረታ እንዲሠራው ውሉ ቀርቦ ይታይ›› ነው የሚለው፤ አንተ ግን ውሎቹ በጉባኤው ሳይገመገሙ፣ ቀርበውም ሳይታዩ እግርህን እዚህና እዚያ አንፈራጠህ በሁለት ቢላ እየበላህ ወንጀለህን ለማድበስበስ በሌለ ስልጣንህ ህገ ወጥ ትእዛዝ ሰጠህ! ደሞ አላዋጣህም መሰል ቆይተህ ሰበሰብከው አሉ… ሃሃሃ

   እስኪ በቅጡ ቃለ ጉባኤውን አንብበው! አልያ ሂድ እዛው የለመድክበት አጭበርብር! ወዮልህ ላንተ! ወዮላቸው ያንተን ማናለብኝነት ሽፋን አድርገው ለሚሞስኑት!

 2. Anonymous September 22, 2015 at 10:30 pm Reply

  MELIKAMIN MADIRAGIN KA LIKAWONIT MINIMAR YIMASLALI SITAT GINI K HULUM SAW HAND AYITAFEM GIN KIRISTINAN GANZAB AND AYIDELUM BA MIKINATI ISATI ATWUXU KALI HONAMI ISAT INDAYIBAL WUXU YE SAWUN SIM DAGIMO ATAXIFU

 3. rahel2002 September 25, 2015 at 5:53 am Reply

  በቶሮንቶ ቅድሥት ማርያም ቤተከርስቲያን የተነሳው የሃይማኖት ውዝገብ ና መንስኤው

  የውዝገቡ መንስኤው የሆነው የቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ትምሀርት የተሰጠው

  በሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች 13ኛ ዓመታዊ አንድነት ጉባኤ ላይ ሲሆን የትምህርቱ ርእስ “ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው” የሚል ሲሆን በዚህም ትምህርታቸው ላይ “ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና”በሚል ንኡስ ርእስ “ዝማሬ ለአምላክ ብቻ ሊቀርብ እንደሚገባ በመናግራቸው ክቶሮንቶ በቦታው ከተገኙት ምአመናን በቦታው ከፍተ ተቃወሞ አስምተዋል

  የቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ትምሀርት እንዳበቃ በጉባኤው በተደረገው ውይይትም ላይ ““ድጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምሕረትን ተጽናናሁኝ ረሳሁ ሐዘኔን” ብሎ መናገር በራሱ ምመጽሐፍ ቅዱስ የማይደገፍ ነው ተብሎ በድፍረት በጉባኤው በስፋት ተነግሮአል የዚህን ጉባኤ ዝርዝር በበለጠ ለመረዳት ክዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይመልከቱ

  http://www.abaselama.org/2015/09/13.html#more

  እነዚሁ የእመ ቤታችን እና የቅዱሳን ፍቅር የአንገበገባቸው ምአመናን በአንድነት ጉባኤው ላይ በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ የተስጠውን የስህተት ትምህርት እርምት እንዲደርግበት በመጠየቃቸውና ትምሀርቱ ምንም ስህተት የለውም ተብሎ ከካቲድራሉ አስተዳዳሪ ጉዳዩን ለማስተባበል በመሞከሩ ክፍተ አልመግባባት አስነስቶአል አስትዳዳሪወ ቀሲስ ምሳሊ እንግዳ ለብዙ ዘመናት የደክሙበት ቤተከርስቲያን የመናፍቃንና የተሃድሶ መ ታጎሪያ እንዲሆን ይፈልጋሉ ብሎ ማመን ቢክብድም ” ኪዳነ ምሕረትን ድጅ ጠናሁ” ማለት ስህተት ነው የተባልበትን ትምሀርት በእመ ቤታችን መንበር ፊት ቆመው ትምሀርቱ ስህተት የለውም ማለታቸው ለምን ይሆን?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: