በሚኒስቴሩ የምክክር መድረክ: በመልካም አስተዳደር ላይ የተያዙት የጋራ አቋሞች በአቀራረብ ጫና እንደተደረገባቸው ተገለጸ

  • ተሸራርፈው እና ተገልብጠው ጎልተው እንዳይወጡ መደረጋቸውን ዳይሬክቶሬቱ ገምግሟል
  • “የመልካም አስተዳደር ድምፃችን አልተሰማም፤ ውክልናችንም አንሷል” (ሰንበት ት/ቤቶች)
  • ምክክሩ፣ በሀገረ ስብከቱ የሰባቱ ክፍላተ ከተማ እና በሌሎችም አህጉረ ስብከት ይቀጥላል

(ሰንደቅ፤ ፲፩ኛ ዓመት ፭፻፳፪፤ ረቡዕ፣ ጳጉሜን ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

Ethiopian Ministry of Federal Affairs

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 170 አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና የሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች በተገኙበት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ለኹለት ቀናት የምክክር መድረክ አካሒዷል፤ ተጨማሪ የውይይት መድረኮችም፤ በአዲስ አበባ ሰባቱም የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት እና በአህጉረ ስብከት ለማድረግ ማቀዱንም ገልጿል፡፡

ነሐሴ ፳፱ እና ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ አዳራሽ በተካሔደው የምክክር መድረክ ላይ፤ በሰላም አብሮ መኖርና ዕሴቱን ለትውልድ ከማስተለለፍ አኳያ ቤተ ክርስቲያን በዕቅድ እየተመራች ስለ መኾንዋ፣ ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ጉዳይ እንዲኹም በቤተ ክርስቲያኒቱ ስላለው ውስጣዊ ተቋማዊ ግንኙነት ጤናማነት ተሳታፊ ልኡካን የቡድንና የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡

በመጀመሪያው ነጥብ ላይ፣ ቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ተልእኮዋ ስለኾነው ሰላም እና አብሮ የመኖር ወርቃማ ዕሴቶቻችን አዘውትራ ብታስተምርም ሥራዎች በዕቅድ ተይዘው መከናወን እንደሚገባቸውአክራሪነትንና ጽንፈኝነትን በተመለከተ በ“ዘመናዊ ኪራይ ሰብሳቢነት እና ሙስና” መልኩ ተጋላጭነቱ እንዳለ ድምዳሜ ላይ መደረሱን አቶ ትእዛዙ ደለለኝ፣ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል፣ የሰላም እና መከባበር መስፈን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርሰንደቅ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ሦስተኛውን ነጥብ ማለትም፤ በቤተ ክርስቲያንዋ ጤናማ ያልኾነ ውስጣዊ ግንኙነት መስፈኑን በተመለከተ፣ በቡድን ውይይት ወቅት ከፍተኛ ክርክር እና የሐሳብ ልውውጥ መንጸባረቁን አቶ ትእዛዙ አስረድተዋል፡፡ ከአሳታፊ እና ዘመናዊ አሠራር አኳያበውሳኔ አሰጣጥ ካህናትንና ምእመናንን በማዳመጥ እና በማሳተፍ፤ በቅጥር፣ ዕድገት እና ዝውውር ወቅት ሰዎችን በብቃት በመመዘንና ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛ ቦታ በመመደብ ረገድ ከፍተኛ ጉድለቶች እንዳሉ መግባባት ላይ መደረሱን አረጋግጠዋል፡፡

የምክክር መድረኩ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች “ድምፃችን አልተሰማም፤ ውክልናችንም አንሷል” የሚሉ አቤቱታዎችን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አቅርበዋል፡፡ በጋራ መድረኩ ውይይት ወቅት ከመልካም አስተዳደር አንጻር ያቀረቧቸው ሐሳቦች በቡድን ሪፖርቱ እንዳልተካተቱ ያጋለጡት ተወካዮቹ፣ የተሳትፎ ቁጥራቸውም ጥሪ ከተደረገላቸው 170 አድባራት ውስጥ ከኻያ ያልበለጠ መኾኑን በመጥቀስ ውክልናው በቂ እና ትክክል አለመኾኑን አመልክተዋል፡፡

አቶ ትእዛዙ እንደገለጹት፣ ለመሰል ውይይት ካለው የልምድ ማነስ አኳያ በምክክር መድረኩ ችግሮቹ እንደሚገባው ነጥረው ሊወጡ እንዳልቻሉ፣ ክንውኑን በገመገመው የሚኒስቴሩ የሃይማኖት እና እምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በኩል ታይቷል፡፡ ይህም በአንዳንድ ቡድኖች አቀራረብ ላይ፣ የጋራ አቋሞች በአብዛኛው ተሸራርፈው እና ተገልብጠው፣ ጎልተው እንዳይወጡ በማድረጉ ጫና የደረሰ የሚመስልበት ኹኔታ መታየቱን በሚኒስቴሩ በኩል ግንዛቤ መያዙን አቶ ትእዛዙ አመልክተዋል፡፡

ተጨማሪ የምክክር መድረኮች፣ በሀገረ ስብከቱ ሰባቱም የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት እና በሌሎችም አህጉረ ስብከት ከሚመለከታቸው ሓላፊዎች ጋር በመነጋገር እንደሚዘጋጁ አቶ ትእዛዙ አስታውቀው፤ ከዚኽ በኋላ በሚኖሩ ተመሳሳይ መድረኰች መሻሻሎች ይኖራሉ ብለን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያንዋ በውስጥዋ ያሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በራስዋ እንድትፈታ ፍላጎቱ መኾኑንና ለዚኽም ውጤታማነት አብሮ እንደሚሠራ ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡ የሚኒስቴሩ ቅድሚያ ትኩረት ማስተማር መኾኑንና ወንጀል ከተሠራ ግን የሕግን የበላይነት ለማስከበር የሚያግደው በር እና አጥር የለም፤ ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
His Holiness at Civil service college
በምክክር መድረኩ መዝጊያ ላይ የተገኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ÷ የውስጣዊ ሰላም ጠንቆች፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሌለው አሠራር፣ ሕግንና ሥርዐትን ማእከል ያላደገረ የሥራ አፈጻጸም፣ የቤተ ክርስቲያንን ሳይኾን የራስን ጥቅም ማስቀደም እንደኾኑ ገልጸዋል፡፡

የእኒኽ ውስጣዊ ጠንቆች መፍትሔዎችም፤ የኅሊና መሥዋዕትነትን በመፈጸም መልካም አስተዳደርን ማስፈን፤ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ፤ የቤተ ክርስቲያንንና የሕዝብን ሉዐላዊነት ማስቀደም፤ ብክነትንና ዝርክርክነትን መጠየፍ እንደኾኑና ሓላፊዎች፣ ሠራተኞችና አገልጋዮች በግንባር ቀደምነት ሊተግብሯቸው እንደሚገባ ቅዱስነታቸው በአጽንዖት አሳስበዋል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “በሚኒስቴሩ የምክክር መድረክ: በመልካም አስተዳደር ላይ የተያዙት የጋራ አቋሞች በአቀራረብ ጫና እንደተደረገባቸው ተገለጸ

  1. ዳሞት September 10, 2015 at 4:46 pm Reply

    እንዲህ ተደረገ ለማለት ካልሆነ ሌላ ያመጣው መፍትሔ የለም። ሁሉም ለሥጋው እንጅ ለእግዚአብሔርና ለፍትህ የቀኑና የቆሙ አይደሉም በእኔ እይታ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: