የፌዴራል ጉዳዮች የመልካም አስተዳደር ውይይት: ዓላማውንና ሒደቱን በሚቃረኑ ዝብረቃዎች ተጠቃለለ፤ አማሳኞች የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ አጠልሽተውበታል

MoFA Logo

 • የቡድኖች ማጠቃለያዎች፣ ውይይቱን የማያንጸባርቁ እና የጋራ አቋሞችን የማይወክሉ ነበሩ
 • አክራሪነት እና ጽንፈኝነት፣ በሚኒስቴሩ ከተሰጣቸው ትርጉም እና ማብራሪያ ውጭ ውለዋል
 • ለመልካም አስተዳደር የተሰጠው መድረክ በቀማኞች የስመ አሸባሪ ዝባዝንኬዎች ተጠልፏል
 • የሰንበት ት/ቤቶች እና መንፈሳውያን ማኅበራት በአክራሪነት እና በጽንፈኛነት ተፈርጅዋል

*            *            *

 • ጥሪው በአማሳኞቹ በመጠለፉ ከ169 አጥቢያዎች 20 የሰንበት ት/ቤት አባላት ብቻ ተገኝተዋል
 • ሕጋዊው የሰሚት መድኃኔዓለም ሰ/ት/ቤት ልኡክ፣ በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እየተገፈተረ ተባሯል
 • የቡድን ማጠቃለያዎቹ እንደማይወክላቸው ለሚኒስትሩ የተናገሩ ሲኾን ሌላ መድረክም ይዘጋጃል
 • አማሳኞች በሕግ እንዲጠየቁ ለተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚነት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል

…እኛ በቡድን የሰጠነውን ሐሳብ በማጠቃለያ ሪፖርቱ በፍጹም አላስገቡትም፤ ቀልብሰውታል፤ ያወያዩን የሚኒስቴሩ ሰዎች ናቸው፤ የቡድኑን የማጠቃለያ ሪፖርት ያቀረቡት ግን ከሀገረ ስብከቱ የተወከሉት ሰዎች ናቸው፤ ለእያንዳንዱ ቡድን የትኩረት አቅጣጫ ሰጥተውታል፤ በሰንበት ት/ቤቶች፣ በማኅበራት… እያሉ ነው፤ በተለይ ሁለተኛው ተናጋሪ፣ ባሕሩ ተፈራ የተባለው የሀገረ ስብከቱ ሕግ ክፍል፣ ሌላው ደግሞ የየካ ሚካኤል ጸሐፊ ነው፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በተዋቀረው ኮሚቴ ሲያጣሩ የነበሩ ሰዎች ድሮ በሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ኾነው ሙስና ሲሠሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፤ ይህን ለማድረግ ምን ብቃት አላቸው፤ ቅዱስ አባታችን ይህን እንዲመለከቱ እንፈልጋለን፤ እኛም አንቀበለውም፤ አሉ፡፡ ከአጀንዳው ጋር ጨርሶ በማይገናኝ ኹኔታ፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ በሰሞኑ የፀረ ሙስና ንቅናቄ ተጠርጎ እንዳይወገድና የሥልጣን ዕድሜው እንዲራዘምለት የለመኑ አሳፋሪዎችም ነበሩ፡፡

በመጨረሻ አንድ የሀገረ ስብከቱ ተወካይ ንግግር ያደርጋል በሚል ለየማነ ከመድረኩ ዕድል ተሰጠው፤ እርሱ ሲናገር … ተቸግረናል፤ ማኅበሩ ሊቃውንቱን ተሐድሶ እያለ ሥራ እንዳንሠራ እያደረገን ነው፤ በቤተ ክርስቲያናችን አሸባሪ፣ አክራሪ በትክክለኛው ለመኖሩ ማስረጃው ይህ ማኅበር ነው፤ ርምጃ እንዲወሰድልን እንፈልጋለን፤ እኛም እስከ መጨረሻው እንደክማለን፤ ራሱን አግልሎ ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጣ፤ አለ፡፡ የነበረው ነገር በጣም የሚያሳዛን ነው፡፡

እዚያ ላይ እጃችንን አውጥተን መረበሽ አልፈለግንም፤ ሚኒስትሩንም ሚኒስትር ዴኤታውንም በየተራ ከበን ያዝናቸው፤ መጀመሪያ ለሚኒስትር ዴኤታው ስንነግራቸው ደነገጡ፤ አስፈላጊ ከኾነ በየቡድኑ የተወያየነውን ሙሉውን ቀድተነዋል፤ ከቀረበው ማጠቃለያ ሪፖርት ጋር ማነጻጸር ትችላላችሁ ስንላቸው ወስደው ከሚኒስትሩ ጋር አገናኙን፤ ያልነውን ነገሯቸው፤ ደነገጡ፡፡ የተደረገውን ነገር በፍጹም አላውቅም፤ ከእናንተ ብቻ በጎ ነገር ይኑር፤ ለማንኛውም እኔ የማደርግላችኹ ነገር ለብቻችሁ መድረክ አዘጋጅላችኋለኹ፤ ይህን ሐሳባችኹን እንድትገልጹልኝ እፈልጋለሁ፤ አሉን፡፡


*            *            *

 • ዐሥሩንም ቡድኖች ያወያዩት የሚኒስቴሩ ባልደረቦች ቢኾኑም፤ የማጠቃለያ ሪፖርቶቹ በዘባራቂው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በተመረጡ እና ‘ረዳት’ በተባሉ አማሳኞች ተዛብተው መቅረባቸው፣ የጋራ መድረኩ በንቃት እና በባለቤትነት እንዳልተመራ አሳይቷል፡፡
 • በውይይቱ መክፈቻ፣ በቤተ ክርስቲያናችን ከአክራሪነት ይልቅ ያለው ዋነኛ ችግር የመልካም አስተዳደር ነው ያሉት ሚኒስትሩ ዶ/ር ሺፈራው፣ የግልን ችግር ለመሸፈን ሲባል ‘ጽንፈኛ’ እያሉ ማኅበራት ላይ እየጮኹ ማስቀየስ ተገቢ እንዳልኾነ ተናግረው ነበር፡፡
 • የአመራሩ ተሰሚነት እና ተደራሽነት የሌለበት፤ የካህኑና የምእመኑ መብት ያልተለየበት፤ የአሠራር ሒደቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያልተረጋገጠበት ተቋማዊ ችግር በአስቸኳይ ካልተስተካከለ ችግር ፈጣሪውም ተጎጂ እንደሚኾን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
 • በቡድን ውይይቱ፣ ማኅበራትንና ሰንበት ት/ቤቶችን በጽንፈኝነትና በአክራሪነት የወነጀሉት አማሳኞቹ፣ በሚኒስቴሩ የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር፤ እርማት እና ተግሣጽ ተሰጥቷቸዋል“ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ምን እንደኾነ ካልገባችሁ አትናገሩ! ዝም በሉ!”

አንዱ የቡድኑ አባል፣ ማኀበሩ ጽንፈኛ ነው፤ ሰንበት ተማሪውን ዩኒፎርም አስለብሶ ያሰልፋል እያለ ያወራ ነበር፤ በአጋጣሚ ሐጂ የሚሏቸው የሃይማኖት እና እምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬቱ መጥተው ቆሙ፤ ቆይ እስኪ ያቁሙ አሉት፤ ጽንፈኛ ምንድን ነው ትርጉሙ? አክራሪነት ምን ማለት እንደኾነ ታውቁታላችኹ? ብለው ጠየቁ፡፡

እነዚህ ዩኒፎርም ለብሰው ሰልፍ ወጡ የምትሏቸው፣ ጠይቀዋችሁ ሳትመልሱ ስትቀሩና ሲቃወሟችሁ ጽንፈኞች ናቸው፤ አክራሪዎች ናቸው ማለት አትችሉም፤ ወጣት እውነትን ይፈልጋል፤ አሳትፉኝ ይላል፤ ይጠይቃል፤ የሕዝብን ሀብት አላግባብ ስታውሉት ማን ዝም ይላችኋል! ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ምን ማለት እንደኾነ ካልገባችሁ አትናገሩ! ዝም በሉ! ማኅበሩ፣ ማኅበሩ የምትሉት ማኅበሩን እኛ ነን እንዴ ዕውቅና የሰጠነው? የቤተ ክርስቲያን አባቶች ናቸውኮ ዕውቅና የሰጡት፤ ስለዚህ ማኅበሩ አልተማረም ስትሉ አባቶች አልተማሩም እያላችሁ ነው፤ ምንድን ነው እንደዚህ የምትነጋገሩት፤ አትደባበቁ !!!


*            *           *

 • ንጹሕ መስለው ለመታየት የሞከሩት እነኃይሌ ኣብርሃ፣ ዘካርያስ ሐዲስ እና የተወሰኑ ጸሐፊዎች÷ ምዝበራቸው ፊት ለፊት እየተጋለጠ፣ የመከላከል ዐቅም አጥተው፣ ራሳቸውን እያከኩና ወለሉን በእግራቸው እየተመተሙ ቁም ስቅላቸውን አይተዋል፤ የሚኒስቴሩ የቡድን አወያዮች ግን ስለ እነርሱ ይሸማቀቁ ነበር፡፡
 • “ኃይሌ÷ ማኅበሩ እና ሰንበቴዎች በጠበጡን፤ ይላል፤ እኛም፤ መቶ ሚሊዮን ብር የሚዘርፍ አለቃ እኮ ነው ያለው፤ እንላለን፤ በአንዳንድ አጥቢያዎች ዐውደ ምሕረቱን የያዙ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንን እንቃወማለን፤ አወያዮቹም፤ እነዚህ ናቸው ወይ ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩት ይላሉ፡፡”
 • በበርካታ ሱሶች ቀልቡን ያጣውና በቢሮ ውስጥ ሳይቀር አጸያፊ ድርጊት የሚፈጽመው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ሕጋዊውን የሰሚት መድኃኔዓለም የሰንበት ት/ቤት ልኡክ፣ “የሰንበት ት/ቤቱ ተበትኖ የለም እንዴ? በየምናኑም ተሰብሰብ፤ አያገባኝም፤ ቤተ ክርስቲያኗ ግን አታውቅህም” ብሎ ከአዳራሹ እየገፈተረ አባሮታል፡፡
 • በቤተ ክርስቲያኒቱ ይኹን በማኅበራት አክራሪነት እንደሌለና ለመልካም አስተዳደር ትኩረት በተሰጠበት ኹኔታ የሊቅነትን ካባ ለራሱ የደረበው ዘባራቂው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ “አሸባሪው ዒላማ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ፓትርያርኩን፣ ሰንበት ተማሪውንና ስብከተ ወንጌሉን ነው፤ ማን እንደሚያስተምራቸው፣ ገንዘባቸው አይታወቅም፤ ይህን ለሚጠይቅም ስም ይሰጣሉ” ሲል በአድርብዬና በፈጠራ ትንተና ዘባርቋል፡፡
 • በርካታ ሰበካ ጉባኤያት በአማሳኝ አለቆች እየታገዱ አድባራቱ ያለከልካይ ለምዝበራ ሲጋለጡ ሽፋን እየሰጠ በእብሪት የሚያላግጠው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ “በማኅበር ተደራጅተው ይመጣሉ፤ የራሳቸውን አስተሳሰብ በሰው ላይ እየጫኑ ያስፋፋሉ” እያለ ከምክትል ሊቃነ መናብርቱ ጀምሮ የሰበካ ጉባኤ አባላቱን በአክራሪነት ለመፈረጅ ዘባርቋል፡፡
 • እውነታው ግን፣ ዋና ጸሐፊነትን ደርቦ በያዘበት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር፣ ፣ በዲዛይን ክለሳ ስም ያለጨረታ አማካሪ መሐንዲስ በመቅጠር ከብር 100 ሚሊዮን በላይ ገንዘብ እንዲመዘበር ማድረጉ ነው፤ ይህም በነበር – የሰበካ ጉባኤ – የቁጥጥር – የልማት ኮሚቴና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት መጋለጡ ነው፡፡ በትላንቱ ዝብረቃው ታዲያ፣ ይኸው ዘረፋው በማስረጃ የተረጋገጠበትንና በቋሚ ሲኖዶሱ ጸድቆ በሕግ ተጠያቂ የሚኾንበትን ጥናታዊ ሪፖርት ነው በፓትርያርኩ ፊት ለማጠልሸት ሲዘባረቅ የነበረው፡፡
Advertisements

8 thoughts on “የፌዴራል ጉዳዮች የመልካም አስተዳደር ውይይት: ዓላማውንና ሒደቱን በሚቃረኑ ዝብረቃዎች ተጠቃለለ፤ አማሳኞች የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ አጠልሽተውበታል

 1. kjljk September 6, 2015 at 5:35 pm Reply

  ስቀሎ፣ ስቀሎ … አይህድ በአደባባይ ሲናገሩት የነበረውን ከመድገም ባለፍ በእኛም ዘመን ያሉት የአውሬው መንፈስ የደረባቸው ሊናገሩትና ሊያደርጉት የሚችሉት ከዚህ የተለየ ይሆናል ብሎ ማሰብ በእውነቱ ሲበዛ ፍጹም የዋህነት ነው፡፡ የሚያናግራቸውና የሚያደርጉት ነገር ሁሉ በውስጣቸው ባደረው በአውሬው መንፈሳ ነው፡፡ በአደባባይ በቤተክርስቲያን ላይ እነዚህ አካላት እየፈጸሙት ያለው የዝርፊያና የውንብድና ተግባር እኮ በሀገሪቱ በትክክል ለህግ መከበር ቆሚያለው የሚል አካል ቢኖር ኖሮ ዛሬ በፍርድ አደባባይ የሚቆሙ አካላት ነበሩ፤ ነገር ግን ጊዜ ሰጣቸውና እንዲህ እንዲናገሩና እንዲያደርጉ ተፈቀደላቸው፡፡
  ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱስ ቢሆን በጉባኤው ላይ ለምን የሰበካ ጉባኤ አባላት እንዳኙ ፈለገ፣ አንድ አጥቢያ እኮ የሚመራው በአስተዳዳሪው በጎ ፍቃድ ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያኒቷ ቃላዋዲ መሰረት በሰበካ ጉባኤ መሆኑ እየታወቀ ስለዚህ የጉባኤ መነሻውም ቢሆን ዓላማውን በተወሰነ ደረጃ ስቷል ማለት ይቻላል፡፡

 2. Anonymous September 7, 2015 at 2:38 am Reply

  Earlier, u said Yemane is tribal, corrupted, weyane … Now u come with a new tag “addicted” yesew sim tilashet sitkebu enante free from any sin mehonachihu new?!!
  Fetari firdih endesew bihon noro min bewaten neber.

 3. Tesfa Kebere September 7, 2015 at 7:01 am Reply

  አሁን ገና ማህበረ ቅዱሳን አንገቱ የታነቀ ይመስላል!! በተለይ በየአጥቢያው ያው የሰንበት ት/ቤት መዋቅር የገንዘብ አያያዙ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ መሆኑ የማህበሩን አንገት ያደነደነ ነበር፡፡ የየአጥቢያ ሥርዓት ከያዘ በኋላ የ5 ኪሎውንም ባለሕንጻ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓት ማስገባት ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ ግን ምንም ተባለ ምንም አሁን ያለው ማ/ቅ እንደገና ክርስትና ተነስቶ ዐቃቤ ሥርዓት ተመድቦለት በትክክል ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊነትን ካልተማረ ይህቺን ቤተ ክርስቲያን ከማመስ አያርፍም፡፡
  ማ/ቅን በማውገዝ እና በመክሰስ ሰበብ ተሸፍናችሁ ቤተክርስቲያንን የምትቦጠቡጡ አስተዳዳሪዎች፣የቢሮ ሰራተኞችና በየቦታው እውቀትና ችሎታ ሳይሆን ቀን ያስቀመጣችሁ!! ቀን ያስቀመጣችሁ!! ጉዶችም ከማ/ቅ የማትተናነሱ የቤተክርስቲያንን ደጃፎች በስግብግብነታችሁ ያከረፋችሁ ጅቦች ናችሁ፡፡
  ቀን/ጊዜ ሰጠን ብላችሁ፣ ሥልጣን ለእኛ ብቻ!! የምትሉ ዘረኞችም ሌላውን በመናቅና ለቤተክርስቲያን ሀላፊነት እንዳይበቃ፣ ያለእናንት ሌላው ሁል ጊዜ ትንሽ የሚመስላችሁ ገፊዎች ጎጃም ጎንደር ሸዋ ኦሮሞ…. ያስጠላችሁ፣እረ ለመሆኑ ቤቱ የክርስቶስ አይመስላችሁም?? ክርስቶስን ምሰሉ እንጂ ስንት ዘመን ለመኖር እሳት ትበላላችሁ????

 4. Tesfa Kebere September 7, 2015 at 1:44 pm Reply

  «ከማኅበሩና ከሙሰኞቹ የትኛው በመወገድ ሊቀድም ይገባል? የሚለው ካልሆነ በስተቀር በሁለቱም አላስፈላጊነት ላይ አንዳችም ብዥታ የለንም»

 5. Anonymous September 7, 2015 at 3:06 pm Reply

  Dear Tesfa

  This may be impossible, because We know that your comment shows your background; that message is from devil. What I can assure you is that, every orthodox tewahido Christianity follower knows about MK without any additional frekersky, just like your comment.

  We don’t have time to read a meaningless sentence …………

 6. ዳሞት September 7, 2015 at 9:56 pm Reply

  ሁለቱም ለራሳቸው እንጂ ለእውነት ግድ የሌላቸው
  በተደጋጋሚ መልካም አሥተዳደርና ለመልካም አስተዳደር ውይይት ይደረጋል የሚል ነገር ተመልክቻለሁ ሰምቻለሁ። ሰው ሥንት ጊዜ እንደሚታለልና ግራ እንደሚጋባ አይገባኝም። ፌዴራል ጉዳዮችም ሆኑ የቤተክርስቲያን አስተዳደርና አለቆች የተባሉት ተመሳሳይ የሆነ ፍላጎትና አላማ የሚያራምዱ መሆናቸውን ማንም ማወቅ ያለበት ይመሥለኛል።
  ፌዴራ ጉዳዮች ሥለ መልካም አስተዳደር የሚያወራው እውነት ለህዝቦች ሰላምና ፍትሃዊ መብት ተጨንቆ ሳይሆን ለራሱ ስልጣንና ጥቅም እንዳይናጋበት ከማሰብ መሆኑ በዋናነት መሠመር አለበት። ምክንያቱ ከአንድ ቦታ የተነሳው የመብት መጣስ ሰፍቶ እንዳይነቅላቸው ነው።
  በሌላ በኩል የቤተክርስቲያን ችግር መልካም አስተዳደር ብቻ አይደለም። የመናፍቃን አፍራሽ ተግባር፣ ሙስናና ዘረኝነትም ዋነኛዎቹ የቤተክርስቲያኗ ችግሮችና ሰላሟን የነሷት ጉዳዮች ናቸው። ታዲያ የፌዴራል ጉዳዮች የመልካም አስተዳደርን ይፈታል ተብሎ ቢታሰብ እንሿን ሌሎችን ችግሮች ግን ሊፈታቸው እንደማይችል ነው የማምነው። ምክንያቱ አንዳንዶች የመንግስት አካላት የሌላእምነት ተከታይ ሥለሆኑ ለቤተክርስቲያን እምነት፣ ስርዓትና ህግ መጠበቅ ደንታ የማይሰጣቸው በመሆኑ። ሙስናውና ዘረኝነቱ ደግሞ በዋነኝነት የሚዘወረው ጊዜው የኛ ነው ባዮች ስለሆነ የፌዴራ ጉዳዮቹ አቶ ሽፈራው እኒህን ባለጊዜዎች የመንካት አቅማቸው በእኔ አይታ ከዜሮ በታች በመሆኑ ነው።
  ሁለተኞቹ የቤተክርስቲያኗ አስተዳደርና አለቆች ነን ባዮች ሲሆኑ እነዚህ ግለሰቦች ዋነኛ አላማቸው የራሳቸውን ኑሮና ፍላጎት ማሥጠበቅ ነው። ይኸውም በሃብት ራሳቸውን አበልፅገው በተንደላቀቀ ኑሮ መኖር፣ ከሌሎች በላይ ሆኖ በመታየት ሌላውን ማንቋሸሽና ዘራቸውን መንከባከብ ብሎም ለነሱ ጥሩ ታሪክ የመሰላቸውን አሳፋሪ የዘረኝነት ታሪክ መዝገብ መከተብ ነው። እነዚህ ግለሰቦች እምነታቸው በአንገታቸውና በካባቸው ካልሆነ በቀር በልባቸው የለም። የቤተክርስቲያን ስርዓት፣ ህግጋት፣ ወንጌልና የመተዳደሪያ ደንብ(ቀኖና) ምናቸውም አይደለም። የምድራዊ መንግስትን ሥራ ይሰራሉ የክርስቶስን ትእዛዝና ወንጌል ግን በእግራቸው ይደቀድቃሉ። ሀይማኖት ተበረዘ ከተባሉ የእውቀት ችግር ነው በሚል ሰንካላ ምክንያት ሀይማኖት እያጠፉ ያሉትን ከነጥፋታቸው ይንከባከባሉ። የእውቀት ችግር ነው ካሉ ለምን አሥተምረው ምንፍቅናቸውን አሥወልቀው ንፁሁ ሥንዴ በውስጣቸው መኖሩን አያሳዮንም። ነገር ግን የዋሃንን ለማደናገር የእውቀት ችግ ነው እያሉ ያደናግራሉ። ለቤተክርስቲያኗ የሚሰሩትን አሸባሪ እያሉ የእውነተኛ ወንጌል ተናጋሪዎችንና አማኞችን አንገት መክተፊያ ሰይፍን ይመዛሉ።
  በዚህ በሁለት ቀን ስብሰባቸው አሥተዳደርና አለቆች የተባለት አሉት የተባለውን እንመልከት። ሙስናን አጥኝ የሆኑት በፊት በቤተክርስቲያን ሥልጣን የነበሩና ሙሥና የሠሩ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል። እነሱ ንፁሐን ነን ብለ ካሰቡ ለም ይፈራሉ? ጥናቱ ተጠናም አልተጠናም ወንጀል ከሌለባቸው ነፃ ናቸው። ህግ ጉዳዩን ያይና ወይ ይፈርድላቸዋል ወይም ይፈርድባቸዋል። ደግሞ ጥናቱ ተጠንቶ ከፍተኛ ሙስና የተፈፀመባቸው አድባራት አሁን ጥናቱን ሌላ አቅጣጫ ለማስያዝ የሚሞክሩት መሆናቸው ተገልፇል።
  ሌላው አሥገራሚው ሥለየትኛው ማህበር በግል ፅ ባይናገሩም ማህበሩ ጠቅልሎ መውጣት አለበት ሲሉ አሥተዳደር ተብየና አለቆች የተናገሩት ነው። በቡሽ ላይ የሰሩት የቦሌ ቤታቸው ነው ያስመሰሏት ቤተክርስቲያንን። ለነገሩ እነሱ ምዕመኑን ሲያስወጡ እንጂ አህዛብን አጥምቀው ሲያመጡ አልታዩምና ይህን ማለታቸው አይደንቄም። ህንፃ ቤተ መቅደስን ሳይሆን ህንፃ ሙስናን ነው የገነቡት። የክርስቶስ ወንጌልን፣ እምነት ስርዓትን ሳይሆን ያለሙት በማህበረ ምዕመናን ለእምነታቸው በሰጡት ገንዘብ ለከርስ ለስጋቸው ማደለቢያ የሚመቻቸውን ፈራሽ በስባሽ ህንፃ ነው። ታዲያ ክርስቲያኖችን ለማስወጣት በአደባባይ መናገራቸው ማን መሆናቸውን በግልጽ ያሳያል።
  ታዲያ ከኒህ አካላት ለቤተክርስቲያን መልካ መጠበቅ የዋህነት ነው ይመሥለኛል።

 7. Anonymous September 9, 2015 at 5:37 am Reply

  ፈርኦናዊ ልብ ያለው አካል ፍጻሜው መሠጠም ነው፡፡
  እንደ እኔ እምነት ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ወቅት መስቀላዊ መንገድ ላይ ቆማለች፡፡ ምርጫዋም ከሁለቱ አንዱን ነው ፡፡ ይህ ማለት፤
   አሁን እንደጀመረችው በውስጧ እንደመዥገር ደሜን የሚመጠምጡ አስመሳይ ባለ ሥልጣትን መልየትና ሥርዓት ማስያዝ፡
   ይህ ትክክለኛ ስም ያለተገኘለት የንጹሐን ስም ጥላሸት ቀቢና ነፍሰ ገዳይ ፤ የሙሰኞችና የፖለቲከኛች መፈልፈያ ማኅበረ ቅዱስን በሚል የመደናገሪ ስም የሚታወቀው አካል ወደ ትክክለኛ መሥመር ማስገባት፡
   የሙሉ አካልዋ ሞተር የሆነውን ጭንቅላቷን /ሲኖዶስ/ ማከም እና ማስተካከል ይጠበቅባታል፡፡
  ይህን ካልመረጠች ግን ቤተክርስቲያኒቱ ወደ ማያባራና ወደ ደቅድቅ ጨለማ መግባቷ የማይቀር ነው፡፡
  ስለዚህ ፈርኦናዊ ልቡና በማስወገድ ራሳችንንም በመፈተሸ እናት ቤተክርስቲያናችንን ማዳን ይኖርብናል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: