ሰበር ዜና – የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ምእመናን አማሳኙን አለቃ አባረሩ! “ሊያስተዳድሩን ስለማይችሉ እንዳይደርሱብን”

 • የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኙ የስብከተ ወንጌል ሠራተኛ፣ በጠብ አጫሪነቱ በወጣቶች ተጎሽሟል
 • አስተዳዳሪው በሕግ እንዲጠየቁ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ የቀረበው ሰነድ ለሕግ አገልግሎቱ ተመርቷል
EgzeabhareAb parish head

በምእመናኑ የተባረሩት አስተዳዳሪ፤ መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሚካኤል ወልደ ሳሙኤል

ለደብራቸው የምዝበራ መንሰራፋት እና የሰላም ዕጦት አፋጣኝ ምላሽ በመሻት ሀገረ ስብከቱን ላለፉት ኹለት ወራት ሲጠይቁ የቆዩት የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፤ አማሳኙንና ምግባረ ብልሹውን አለቃ መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሚካኤል ወልደ ሳሙኤልን ከአጥቢያቸው አባረሩ፡፡

ከዛሬው፣ ነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.፣ የጸሎተ ቅዳሴ ፍጻሜ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር መጠናቀቅ በኋላ ታላላቅ ሽማግሌዎች፤ አስተዳዳሪው የቃለ ዐዋዲውን ድንጋጌ በመፃረር በግልጽ እና በገሐድ ስለሚያካሒዷቸው ሕገ ወጥ ተግባራት ለመጠየቅ ወደ ዐውደ ምሕረቱ ሲቀርቡ ሸሽተው ወደ መቅደስ በመግባት ተደብቀዋል፤ ቆይቶም የምእመኑን ጥያቄ አዳምጠው ከጥፋታቸው የማይታረሙ ከኾነ ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ ለቀው እንዲወጡ በቀረበው ጥያቄ፣ በፖሊስ ታጅበው ወደ አካባቢው ፖሊስ ጽ/ቤት መወሰዳቸውን በስፍራው የተገኙ ምእመናን ተናግረዋል፡፡

ካለፈው ግንቦት አጋማሽ አንሥቶ ስለ ጉዳዩ ሀገረ ስብከቱን ሲያሳስቡ የቆዩት ምእመናኑ፤ ከዛሬው የጋራ አቋም ያደረሳቸው፣ አስተዳዳሪው፣ በማኅበረ ካህናት እና በማኅበረ ምእመናን ምልአተ ጉባኤ የተመረጠውን ሕጋዊውን ሰበካ ጉባኤ በማገድ ሌላ ሰበካ ጉባኤ ለማስመረጥ በድብቅ በመንቀሳቀሳቸው እንደኾነ ተገልጧል፡፡

በአንዲት በጎ አድራጊ ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ የተሰጠ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ በትክክል ገቢ ካለመደረጉ ጋር ተያይዞ የቆጠራ ቃለ ጉባኤ እንዲቀርብለት ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የአስተዳደር ጽ/ቤቱን በመጠየቁ፣ ካለፈው ግንቦት አጋማሽ ጀምሮ በአማሳኙ እና ምግባረ ብልሹ አለቃ ታግዶ ቆይቷል፤ ለምክትል ሊቀ መንበሩም ሕገ ወጥ የስንብት ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት እና የሰበካ ጉባኤው ማደራጃ ዋና ክፍል ለችግሩ እልባት እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ከአማሳኙ አለቃ ጋር ካላቸው የጥቅም ግንኙነት የተነሣ ለይስሙላ እየተመላለሱ ችግሩን ከማባባስ በቀር ሐቀኛ መፍትሔ ለማስገኘት እንዳልቻሉ ታውቋል፡፡

በምትኩ የአጥቢያው ሽማግሌ ምእመናን እና የክፍለ ከተማው ፖሊስ ውዝግቡን በጋራ መድረክ ለመፍታት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ባለፈው ሐምሌ 30 በተካሔደው ውይይት ሕገ ወጡ እገዳ ተነሥቶ ሰበካ ጉባኤው እንዲመለስ ከአስተዳደሩ ጋር ዝርዝር ስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ይኹንና የሀገረ ስብከቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ትምክህታቸው ያደረጉት አስተዳዳሪው፣ ወደ ኋላ ተመልሰው ስምምነቱን በመጣስ እና ምእመኑን በመናቅ ቃለ ዐዋዲውን የሚፃረር ተግባር በድብቅ ሲፈጽሙ ተገኝተዋል፤ በጉዳዩም ላይ በሰላማዊው ምእመን ፊት ቀርበው ለመጠየቅ የሞራል ልዕልናውን በማጣታቸው መሸሽን ቢመርጡም የአጥቢያውን ዘላቂ ሰላም እና የተረጋጋ መንፈሳዊ አገልግሎት ለማስጠበቅ ሲባል እንዲባረሩ መደረጉን ምእመናኑ አስረድተዋል፡፡

Debra Sina EgzeabhareAb Church
ከአንድ ወር በፊት “የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ምእመናን አስተዳዳሪውን አስጠነቀቁ፤ በሀገረ ስብከቱ ዳተኛነት ተመርረዋል” በሚል ርእስ ስለ ጉዳዩ ሰንደቅ ጋዜጣ ባወጣው ዜና፣ የአጥቢያው ምእመናን ባስቀመጡት ቀነ ገደብ ጥያቄአቸው በበጎ ታይቶ ምላሽ ካልተሰጠው፣ የደብሩ ችግር አኹን ካለበት ወደባሰ ደረጃ ሊሸጋገር እንደሚችል አበክረው ሲያሳስቡ እንደቆዩ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

*           *           *

የዐይን እማኞች ምስክርነት

ከጸሎተ ቅዳሴው በኋላ ተኣምረ ማርያም ተነበበ፤ የዕለቱ ስብከት ተሰጠ፤ ስብከቱ ተጠናቆ አለቃው ለማሳረግ ሲዘጋጁ የአጥቢያው አዛውንት እና ወጣት ምእመናን ወደ ዐውደ ምሕረቱ ተጠግተው ጥያቄ አለን አሉ፤ ጥያቄውን ያቀረቡት በርከት ያሉ ታላላቅ አዛውንት ምእመናን ናቸው፡፡

ጥያቄአቸውን አሰምተው ለማቅረብ ድምፅ ማጉያውን ሲጠይቁ፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝነት የሚጠረጠረው የስብከተ ወንጌል ሠራተኛ (በአለቃው ግፊት እና ውሳኔ ከዕለት ገንዘብ ተቀባይነት እና ጉዳይ አስፈጻሚነት ወደ ስብከተ ወንጌል የዞረ) አልሰጥም አለ፤ ጥያቄ አለን እየተባለ በመሀል አለቃው ሹልክ ብለው እየሮጡ ቤተ መቅደስ ገብተው ተቆለፈባቸው – በቄሰ ገበዙ፡፡

ምእመናኑ በካህናት በር ዞረው እየጠበቋቸው ሳለ ከመጠለያው አካባቢ የጩኸት ድምፅ ተሰማ፡፡ በሁኔታው የተበሳጨች አንዲት እኅት፣ ከአለቃው ጋር የሰበካ ጉባኤውንና የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላቱን ስም የሚያጠፋውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ የሆነውን የስብከተ ወንጌል ክፍል አባል፣ “አንተ መናፍቅ፤ ጴንጤ፤ አንተ አታስተምረንም” በማለት በጩኽት እየተናገረች ነበር፤ እርሱም መበጥበጥ ስለፈለገ ተጠግቶ በጥፊ መታት፤ አስተምርበታለሁ በሚለው ወርኃዊ ጉባኤ የሚያጅቡትና ግርግር የሚፈጥሩ ተከታዮቹ ድንጋይ ይዘው ለጠብ ተዘጋጅተው ነበር፡፡

ይሁንና በልጅቷ መመታት የተቆጡ በስፍራው የነበሩ ወጣቶች ወዲያው ደርሰው ሲጎሽሙት አግዳሚ ወንበር ላይ በጀርባው ተዘረረ፡፡ ልጅቷ ተመትቻለሁ ብላ፤ እርሱም መናፍቅ ተብዬ ተሰድቤአለሁ ብሎ እየተካሠሡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሲሔዱ የንስሐ ልጆቹ ናቸው የተባሉ ተከታዮቹ ደግሞ ከቅጽሩ እንዲወጡ ተደረገ፡፡ አለቃው ግን እስከ አሁን ቢጠበቁም ባለመውጣታቸው ምእመናኑ ተሰብሰቡ ተብለው በሁለት አዛውንቶች መሪነት በቀጣይ አካሔዶች ላይ ውይይቱ ቀጠለ፡፡

በውይይቱ እንደተነሣው፣ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በአለቃው በመታገዱ ምክንያት ከአስተዳደሩ ጋር የተቀሰቀሰው ውዝግብ፣ ሐምሌ 30 ቀን የአካባቢው ሽማግሌዎች እና የክፍለ ከተማው ፖሊስ ባለበት ተነጋግረን የሰበካ ጉባኤው እንዲመለስ ተስማምተን ዕርቅ ተፈጥሮ፣ በዐውደ ምሕረትም ሰላም ይሆናል ብለን እንደፈታነው ከተናገርን በኋላ፣ ያለሕጉ ሌላ ሰበካ ጉባኤ ለማስመረጥ በድብቅ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ለምክትል ሊቀ መንበሩም “የሙዳየ ምጽዋት ቁልፍ አስረክበን፤ አለዚያ በሕግ እንጠይቃለን” የሚል ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡ ስለዚህ ምእመኑን ንቀውታል!

ዕርቅ ተፈጥሯል ብለን በዐውደ ምሕረት የተናገርነውንም ሐሰተኛ አድርገውናል፡፡ ሱባኤውን ሙሉ በስብከት እያስታከኩ እኛን “ገለባ” እያሉ ለዐሥራ ስድስት ቀን ሲሰድቡን ከርመዋል፡፡ ስለዚህ እኚህ አለቃ እኛን ሊመሩን አይችሉም፡፡ ከዚህ በኋላ እዚህ ግቢ እንዲመጡ አንፈልግም፡፡ አቋማችን ይኸው ነው፡፡ አንድ ላይ ኾነን ከዚህ በኋላ እርሳቸውን አንቀበልም፡፡ ቤተ ክህነቱ ደኅና አባት እና አለቃ ከላከልን፣ ይላክልን፡፡ ይህንኑ ለሚመለከተው የቤተ ክህነት አካል ማኅተማችንን አድርገን በጽሑፍ አሳውቀናል፤ ጉዳዩም ለሕግ አገልግሎት መምሪያው ተመርቷል፡፡

እኚህ አለቃ ግን ይኼን ሕዝብ ለማስተዳደር አይችሉም፤ ንቀውታል፤ ዋሽተውታል፤ ዳግም አይምጡብን፤ አንፈልጋቸውም!!! ከእኛም ተነሥተው ወደ ሌላ ቢሔዱ ለቤተ ክርስቲያን የማይመጥኑና የማይጠቅሙ ናቸው፡፡

በምእመኑ የጋራ አቋም ከተያዘ በኋላ፣ አብዛኛው ምእመን ወደ ቤቱ ሲሔድ አንዳንዶች፣ አለቃው ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ ሲወጡ ካላየን አንሔድም አሉ፡፡ ከሁለት ሰዓት በላይ አልወጣም ብለው በመቅደስ የቆዩት አለቃው፣ የአካባቢው የፖሊስ ኃይሎች ሲመጡ ወጡ፤ ፈርተው ተንቀጥቅጠው እየሮጡ ወደ ቢሯቸው ገቡና ጓዛቸውን በችኮላ ሸክፈው በፖሊስ መኪና ሆነው ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑን ለቀው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰዱ፡፡

*           *           *

Advertisements

5 thoughts on “ሰበር ዜና – የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ምእመናን አማሳኙን አለቃ አባረሩ! “ሊያስተዳድሩን ስለማይችሉ እንዳይደርሱብን”

 1. ኀይለገብርኤል August 30, 2015 at 10:11 pm Reply

  ቤተክርስትያኗን የመናፍቅ መፈንጫ አደረጓት

 2. G.Michael Zekidus Yared August 31, 2015 at 1:18 am Reply

  Ene Betam Aznalew.Tewahido nisihit emnetachin; menfsawinet (spritual life) tirgumu min endehone enkua mawek betesanachew , enkuan meimeunun rasachewun enkua memrat bemachilu gileseboch memolatua.

 3. Anonymous August 31, 2015 at 7:01 pm Reply

  gobeze betkerestiyane abate yelatem be ahunu seate. egnea lejochua yemiayasefelegewen meswaetenet bemkefele ke menafeqane werera lenetebeqate yegebale. zare abatochachen negede laye nachew enji tselote laye aydelume. yehnenen lemawaqe be yegizew yemiwetuten merejawoche mayete beqi yemeselegneale. lemesale be qerebu yewetawe ye 1.5 billion bire be amete wesete metefate mene malet endehone megemet yechalale.

 4. Zelalem Gudeta September 3, 2015 at 12:18 pm Reply

  በእርግጠኝነት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ነው ብሎ መጻፍ ተገቢ ነውን? ምን ማስረጃስ አላችሁ? ዜና ብላችሁ
  ስታወጡ ግን ሌላውን አንባቢ የሚያወዛግብ መሆን የለበትም፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: