የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር ዛሬ ይወያያል፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ በሚኒስቴሩ እና በሚኒስትሩ ስም ያስፈራራሉ

 

addis ababa sunday schools demo to the dio HQ

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሃይማኖት እንዲጠበቅ፤ ሙስና እና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ፤ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በመጠየቅ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ያደረጉት ሰልፍ (ፎቶ ፋይል)

 • በፀረ ሙስና፣ በመልካም አስተዳደርና በዕቅበተ እምነት ንቅናቄውየአማሳኞች የሕግ ተጠያቂነት እንዲኹም በእስር እና በወከባ የሚያደርሱት እንግልት ዋነኛ ትኩረት እንደሚኾን ተጠቁሟል
 • ዋና ሥራ አስኪያጁ÷ በአለቆች፣ በካህናትና በሰባክያነ ወንጌል ላይ እንዳደረጉት ኹሉችግሮችን ውጫዊ በሚያደርግ ኦሬንቴሽን ትኩረቱን ከወዲኹ ለማስቀየስ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም
 • ‹‹የተሾምኩት በመንግሥት ትእዛዝ ነው የሚሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ጥያቄ እና ተቃውሞ የሚያነሡባቸውን ሠራተኞች በሚኒስቴሩ እና በሚኒስትሩ ስም ያስፈራራሉ
 • ሚኒስቴሩ÷ ‹‹በዘመናዊ የሙስና አደረጃጀት›› በሚሠራው በሊቀ ማእምራን የማነ ብልሹ አመራር ከተማረሩ ሠራተኞች፣ ካህናትና ምእመናን ይልቅ የዋና ሥራ አስኪያጁን ‹ምርጦች› ብቻ ቅድሚያ ሰጥቶ ሲያነጋግር መቆየቱ ሲያስተቸው ቆይቷል፡፡

*        *        *

yemane zemenfes

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በዋና ሥራ አስኪያጅነት እና በመላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ቅዱስ ፓትርያርኩን እንዳማክር በመንግሥት ትእዛዝ የተሾምኩ ነኝ ባዩ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ

 • ‹‹ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ያለምንም መሸማቀቅ በድፍረት እንዲኽ ብለውናል፡- የአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ኾኜ የተሾምኩት በመንግሥት ትእዛዝ ነው፡፡ ሊቀ ጳጳሱ፣ ቋሚ ሲኖዶሱ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሳያውቁት እንድሾም የተደረገው መንግሥት ከቤተ ክርስቲያን የሚፈልገውን ምስጢራዊ ሥራዎች እንዳስፈጽም ነው፡፡ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተጥሶ ነው አላግባብ የተሾምከው እና ብቻህን የምትሠራው የምትሉኝ ምስጢሩን ስለማታውቁ ነው፤…››
 • ‹‹… ኹለቱ ባለሥልጣናት[ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እና በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ] የሸዋ ተወላጆች ስለኾኑ በአኹኑ ሰዓት መንግሥት አይፈልጋቸውም፡፡ ለዚኽም ነው ብቻዬን እንድሠራ የተደረገው፡፡ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የተደረገውም ቀደም ሲል የሥራ መደቡ የነበረ በመኾኑ ብቻውን ፓትርያርኩ ሾሙት እንዳይባል ለሳምፕል ነው፡፡››
 • ‹‹… ቅጥር፣ ዝውውር እና ልዩ ልዩ ፈቃድ ስፈጽም፣ ዕድገት ስሰጥ በምክትል ሥራ አስኪያጁም ኾነ በአስተዳደር ጉባኤው ሳላስወስን እንድሠራ ነው መመሪያ የተሰጠኝ፤ የፋይናንስ መምሪያ ሓላፊውን ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነንና የቁጥጥር መመሪያ ሓላፊውን ሊቀ ሥዩማን ገብረ መስቀል ድራርን ብቻ ነው እያማከርኩ የምሠራው፡፡ አስተዳደር ያደረግኹትንም ታውቁታላችኹ፤ የሰጠኹትን ፓራፍ እንዲያደርግ ብቻ ነው ያስቀመጥኹት፤ በባሕርይው ለሾመው አካል ምንም ዐይነት ጥያቄ አያቀርብም፤ የታዘዘውን ነው የሚጽፈው፤ እኔም በዚኽ ፀባዩ ተመችቶኛል፡፡››

 • ‹‹…ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ስም በድፍረት እየጠሩ፡- ከሀገረ ስብከት፣ ከወረዳ ቤተ ክህነት፣ ከገዳማትና አድባራት የቢሮ ሠራተኞችን እንዳዘዋውር አስቸኳይ ትእዛዝ ተሰጥቶኛል፤ እኔ ግን በአንድ ጊዜ አዘዋውሬ ምእመናን እንዳይበጣበጡ በሳምንት 8 ወይም 10 አድርጌ እያነሣኋቸው እገኛለኹ፤ በአንድ ጊዜ ባለማዘዋወሬ መመሪያችንን ወደ ተግባር አለወጥክም በማለት ከመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ከፍተኛ ወቀሳ እና ማስጠንቀቂያ ደርሶኛል፡፡››
 • ‹‹…በአኹኑ ሰዓት የፈለግኹትን ማድረግ እና መሥራት እችላለኹ፤ ኹሉም በወቅቱ ነው፤ ይኼ ጊዜ ደግሞ የእኔ ነው፤ እኔን የሚቃወም ካለም ሒሳቡን ያገኛል፤ እየሰበሰብኩኝ በየእስር ቤቱ አጉረዋለኹ፤ እያሉ አስፈራርተውናል፤ ዝተውብናል፤ ፎክረውብናል፡፡ እናንተ በእኔ የእጅ መዳፍ ውስጥ ናችሁ፤ በእጁ ወፍ የያዘ ሰው ቢለቃት እንድትበር ያደርጋታል በተቃራኒው ደግሞ ይጨምቃታል፤ ለእናንተ ይኼ ምሳሌ ይበቃችኋል፤ በማለት ሕግ ጥሰው እያስፈራሩ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ እየነገዱ እና በጀመሩትም የንግድ መሥመር ያለማንም ከልካይ ከፍተኛ ተጠቃሚ ኾነው ይገኛሉ፡፡››
 • ‹‹…የየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን በዚኽ ብቻ አያበቃም፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩንም በዚኽ ግቡ በዚኽ ውጡ የምላቸው እኔ ነኝ፤ ቅዱስ ፓትርያርኩንም የፈለገ መንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት መሔድ አይጠበቅበትም፤ እኔ ቢሮ መጥቶ በቀጥታ ስልክ ደውዬ በማገናኘት ጉዳዩን እጨርሳለኹ፤ ለምን ቢባል ከእኔ ውጭ እንዲሠሩ አልተፈቀደላቸውም፤ ሹመቴ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ይባል እንጂ በምስጢር ለመላው ኢትዮጵያ ነው፡፡ ፓትርያርኩ ሀገሩን በደንብ ስለማያውቁ ነው፡፡ የቤተ ክህነቱንም ኾነ የቤተ ክርስቲያኒቱን የሥራ ተዋረድ ስላልኖሩበት እና ስለማያውቁ እኔ እና ሦስት አስተዳዳሪዎች (እንደራሴዎች) ኾነን እኛ በምንላቸው ብቻ እንዲሠሩ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፤ አሉን፡፡››
 • ‹‹የሔዱትን[በቀደሙት ውይይቶች የተሳተፉትን አለቆች፣ ካህናት እና ሰባክያን] ጠይቁ፤ ሰሞኑን ሚኒስትሩ አቅፈውኝ ትከሻዬን እየመቱኝ፣ በርታ፤ እኔ ከጎንህ ነኝ፤ ያለምንም ስጋት መንጥራቸው ብለው መመሪያ ሰጥተውኛልስለዚኽ ወደተመደባችኹበት ደብር ሔዳችኹ ሥሩ፤ የትም ብትሔዱ መፍትሔ አታገኙም፤ እናንተ በእግር ስትሔዱ እኔ እዚኽ ተቀምጬ መመሪያ እሰጣለኹ፤ እኔ ለሸዋ እና ለኦሮሞ ተወላጆች ISIS ነኝ በማለታቸው በጣም አዝነናል፡፡ ስም እየጠሩ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እስካለ ድረስ እጨርሳችኋለኹ ብለዋል፡፡ መንግሥት እርሳቸው እንደሚሉት የእርሳቸው ብቻ አይደለም፡፡ እኛ መንግሥት ከዜጎቹ ጋር ነው ያለው ነው የምንለው፡፡ ስለዚህ በአስቸኳይ ይድረስልን፡፡››

/በጥቅመኝነት እና በጎጠኝነት ትስስር ላይ በተመሠረተው የዋና ሥራ አስኪያጁ የዝውውር አሠራር የተማረሩ የገዳማት እና አድባራት ሠራተኞች ለፓትርያርኩ፣ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ እና ለመንግሥት በጽሑፍ ካቀረቡት አቤቱታ/

Advertisements

5 thoughts on “የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር ዛሬ ይወያያል፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ በሚኒስቴሩ እና በሚኒስትሩ ስም ያስፈራራሉ

 1. Anonymous July 30, 2015 at 3:33 pm Reply

  እሱን አዋረድን ብላችሁ ራሳችሁን ማስገመታችሁ ይገርማል፡፡ይሄን ያለው፡-የት፣መቼ፣ለእነማን፣በምን የተነሳ የሚል ጥያቄ ተነስቶ የጻፋችሁትን የማስረዳት ግዴታ ስለሌለባችሁ ብቻ እንዳሻችሁ ባታወሩ መልካም ነበር፡፡ይልቅስ ሰንበት ት/ቤቶች ጥያቄ ላይ ብታተኮሩ አይሻልም፡፡ካሕኑ በአንጻራዊነት በአሁን ሰዓት ተረጋግቶ ነው ያለው፡፡የጻፋችሁት ጽሑፍ ወቅታዊውንና ነባራዊውን እውነታ የሚያንጸባርቅ አይመስለኝም፡፡

  • Anonymous August 1, 2015 at 3:30 pm Reply

   በእውነት ስለቅዱስ ዑራኤል ቤተክረስቲያን በወ/ሮ መና የቀረበውን አጠቃላይ መግለጫ ቀደም ሲል በኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ በመቀጠለም በዚህ ድሕረ ገጽ ሳነብ ብዙ ነገሮች በህሊናየ ተመላለሰ፤ ጀግንነት ራስን በመግዛት ለእውነት መታገልና እውነትን መጋፈጥ እንደሆነም ተምሬአለሁ፡፡ በትእቢት ከመወጠርና ከመታበይ ጉዳዩ ምን ያክል እውነትነት አለው ብሎ መመርመርና መፍትሄ መስጠት የተሻለ ነው፡፡

   እንደኔ ወ/ሮ መና ካስተላለፉት አሳሳቢ መልእክት ውስጥ አንድም መሬት የሚወድቅ የለውም፡፡ ጉዳዩን እኔም የማነም ስንወያይበት የነበረ በመሆኑና ወደ ኋላ ከተሔደም የየማነ ጉድ አለበት፡፡ መረጃ ለማጥፋት የተሰራ ስራ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የልደታው ጉዳይ ላይ የማነም ተከሳሽና ጉዳዩ ገና ያልተቋጨ ነው፡፡ የአራዳው ጊዮርጊስ 175 ሚሊዮን ብሩን ለማድበስበስና የተዘረፈውን ዘረፋ ሕጋዊ ለማድረግ በድፍረት ያቀረበውን አጀንዳ በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ተጥሎበታል(ውድቅ ተደርጓል)፡፡ እንዴት የአንድን ደብር ጉዳይ ራሱ ጸሃፊ የሀ/ስብከት ስራ አስኪያጅ እራሱ በዘራፊነት ተጠያቂ መሆኑ እየታወቀ መረጃ ለማጥፋት መሞከር በራሱ አስደናቂ ድፍረትና ገራሚ ነው፡፡ ነገሩ ቁማርተኛ ምን ጊዜም ደፋር ነው፡፡ ለማንኛውም ወንዝ ያፈራሽ ዳግማዊት ጣይቱ (ምንም እንኳን የእናት ሆድ ዝጉርጉር ነው ቢባልም) ወ/ሮ መና ጀግና ነሽ፡፡

   ይህ በእንዲህ እያለ በአዕምሮዬ ከሚመላለሱት አሳሳቢ ጥያቄዎች መካከል፡-
   1. እንደዚህ ያሉ ጉዳዮች በቤተ ክርሲቲያኗ ኣስተዳደር ውስጥ እስከ መቼ ድረስ ነው የሚቀጥለው ?
   2. ግለሰቦችስ ቡድናዊ ዘረፋንና የዘረኝነትን አመለካከት ይዘው የሚቀጥሉት እስከመቼ ነው?
   3. መንግስትስ ጣልቃ ገብነቱን በትክክል ሀገራዊ ደህንነትን ባስጠበቀ መልኩ ቤተክርሲቲያኗን የሚጠቅመው መቼ ነው?
   4. የቤተ ክርስቲያኗ የበላይ ኃላፊዎች ከፓትርያርክ እሰከ ስር ያሉ ሰራተኞች ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ፤የእምነት ተቆርቋሪነት ያለው፤ በመንፈሳዊነትና በእውቀት ላይ የተመሰረተ አስተዳደርን የሚያመጡት መቼ ነው?
   5. ፓትርያርክስ ሁሉን አቀፍ የሆነ፤ ከዘረኝነት የጸዳ፤ ለቤተክርስቲያኗ መሰረታዊ ሕግና እምነት ያደላና ተቆርቋሪ የሆነ፤ በስነ ምግባር የታጠረ፤ የሁሉም እኩል አባትና የእምነት አባት የሚሆኑት መቼ ነው?
   6. ቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልናወን አስጠብቆ በግርማ ሞገስ ስለ እውነት የሚመሰክረው፤ ከተራ አሉባልታ ወጥቶ ሕጋዊ መሰረት የሌለውን አጀንዳ ከህጋዊው አጀንዳ እየለየ በእውቀትና በመንፈስ የሚሰራው መቼ ነው
   7. ግለሰቦችስ በመንግስት ስም በመነገድ እያደረጉ ያሉትን የተደራጀ ምዝበራ የሚያቆሙት መቼ ነው?
   8. ምዕመኑና ካህናቱ እየተደረገ ያለውን ግፍ ተቀናጅተው የሚመክቱትና የሚፈቱት መቼ ነው?

   ዞሮ ዞሮ የነአቶ የማነና የአጋሮቹ ተግባር ተራ ውንብድና ነው፡፡ ምክንያቱም መርሃቸው መዝረፍ ፤መዝረፍ፤መዝረፍ ነው፡፡ እያንዳንዱ እርምጃቸውም የጋለሞታይቱን ስርዓት መተግበር ነው፡፡ ባቢሎኖች(ዝሙት የተስፋፋበት ስርቆት የነገሰበት እግዚአብሔር የማይፈራበት አለቆች የረከሱበት ከተማ)፡፡ እኔ በትንሹ የማነን አውቀዋለው፤ አብረንም ሰርተናል፤ አድገናል፤ የቤተ ክርስቲያኑ ትምህርት የማይገባው ሃይ ስኩል እያለንም ለቋንቋ እንጂ ለሌሎች መሰረታዊ ትምህርቶች ቦታ የሌለው(ትግርኛ ለመልመድ ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ነበር)፤ በጣም ስለሚያወራ BBC እንለው ነበር፤ ምክንያቱም ስለ ሚትርዮሎጂ ስለ ጦርነት ስለ ስፖርት ወዘተ. ማሰሪያ ነጥብና ጭብጥ የሌለው ነገር ያወራል፡፡

   በማታው ክፍለ ጊዜ 6ኪሎ ዬኒቭርሲቲ ፖለቲካ ሳይንስ ዲፓርትመንት በኢሀዴግ/ሕወሀት/ የደብዳቤ ድጋፍ ተመዘገበ፤ ምክንያቱም ድርጅቱን አማላይ በሆነ ቃል አሳክሮት ነበር፡፡ እውነታው ግን ሕወሀት ለትግል ጫካ በገባበት ወቅት አባቱ ለትግል ልጄን በረሃ ይወስዱብኛል በማለት በልጅነቱ አሽሽተው ወደ አ.አ አመጡት፡፡ በሌሎች ሰማእትነት ለመክበር ታስቦ፡፡ ሆኖም ይህንን እውነታ በማጣመም ደርግን እየሰለልን መረጃ እንድናቀብል ተብሎ የተላክን ነን ይላል፡፡ አንዳንድ ጊዜም እያመለጠው ጫካ እንደታገለም ያወራል፤ ነገር ግን የትግሉ ዓላማ ምን እንደሆነ መተንተን ያቅተዋል፤ ነገሩ በሚስቱ ታግሏለል፡፡

   ፖለቲካ ሳይንስ ዲፓርትመንት የገባው ሲጨርስ ለትግራይ ክልል ርዕሰ ብሔርነት እንደሚሾም በተደጋጋሚ ያወራ ነበር፡፡ ሕውሀት ሴንጪው ሰርስሮ ገብቶ መረመረውና ከኢቲቪ በፐርፎርማንስ ማነስ አባረረው፡፡ እንኳን ለትልቅ ስልጣን ሊታጭ ለምንጣፍ አንጣፊም ብቁና ታማኝ አለመሆኑን አብጠርጥረው ደረሱበት፡፡ የማን ዘር ጎመን ዘር በአንድ ወቅት አባቱ ከልዋጭ ስራቸው አረፍ ብለው ታማኝ መስለው የአንድ ደብር መገበሪያ አክባሪ ነበሩ፡፡ የመገበሪያ ስንዴ ለግል ጥቅም በማዋላቸው ታግደው ነበር፡፡ በኋላም ምንጣፍ አንጣፊ ተቀጥረው የአንድ ምእመንን የተረሳ ንብረት ወስደው ስለተገኙ ይህም ተደርሶባቸው ለረጅም ጊዜ ታግደው ነበር፡፡ ደፋሮች! ለዚህ ነው ልጁም ያደገበትንና ከአባቱ የወረሰውን ተግባር እያከናወነ ያለው፡፡ ብቻ እንተወው፡፡

   አሁን ደግሞ ለቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ፖለቲካ ሳይንስ አስፈላጊ እንደሆነ በመኩራራትና በድፍረት መንግስትም እሱን መርጦ ከቤተ መንግስት እንደላከው ይናገራል፡፡ እረ መንግስት የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግስት ነው….. በአጠቃላይ ኦና/ባዶ ቤት ሲገኝ እንዲህ ነው፡፡ ትክክል ነው፤ በአሁኑ ወቅት የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ መሪዎች የሆኑ በአጠቃላይ ቆም ብለው ማሰብ ይገባቸዋል፤ በአብሮ መብላትና መጠጣት ይልኙታ ባይጠፈነጉ የተሻለ ነው፡፡ ይሄ ውርደት ነው፤ ነገር ግን ለማስተካከል ቀላል ነው፤ የሀይማኖት ቁርጠኝነቱ ካለ ታራዎችን ዞር በሉ አይመለከታችሁም የከዚህ በፊቱ መጭበርበርና መሸወድ ይበቃል ቢባሉ ይቆማል፡፡ ነገር ግን ማን ይጀግን፤ ማን ሰማእትነት ይቀበል፤ ያሳዝናል ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስም በሕግ የተሰጣቸውን ስልጣንና አደራ ለመተግበር የስነ ልቦና ጥንካሬና የሓይማኖት ቁርጠኝነት አጡ፤ እንዳውም አንድ ጊዜ ማን ይበላል ብለው ተናግረዋል ይባላል፡፡ ለቸልተኝነታቸው ምክንያቱ ፍርሃት ብቻ ነው እሳቸው በትንሹ እንዴት የሐንስን ፈሩ??????፡፡ ሆድ ይፍጀው፡፡

   እነዚህንና ሌሎችን ጉዳዮች ባሰብኩ ጊዜ ህሊናዬ ከአየራት አየራት ወደላይ መጥቆ በመጓዝ እውነትን በመናፈቅና በመሻት ይዋትታል፤ ይፈልጋል ነገር ግን ሁሉ ነገር ተስፋ አስቆራጭና አሳዛኝ ይሆንበትና በመቆዘም ለጥያቄዎቹም መልስ ያጣና ይመለሳል፡፡ አሳዛኝ ነው ቤተ ክርስቲያኗ ባሳለፈችው ዘመን ንጽጽራዊ በሆነ በዓለም እይታ በዘመናዊ ዕውቀትና ጥበብ እንደ አቡነ ጳውሎስ ያለ ፓትርያርክ ተገኝቶ አያውቅም ይላሉ ነገር ግን በዘረኝነት፤ በቤተሰባዊ አስተዳደርና በአንባገነንነት ላይመለሱ በድለው አለፉ፡፡ ለዚህ ነው በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ታላቁን አባት የማስታወስና በሞታቸው እንኳን የማዘን ሁኔታ የሌለው፡፡ ያረፉበት ቀን እንኳን ከመታወስ ይልቅ የጠፋው ምን አልባት የሚያስታውሷቸው ዘመዶቻቸውና ጥቅመኞቹ ናቸው ያሳዝናል፡፡

   ያገሬ ሰው ሆድ ሲብሰው ትሻልን ፈትቼ ትብስን አገባው ይላል፤ በአቡነ ጳውሎስ እረፍት ቤተ ክርሲቲያኗ ታርፋለች ሲባል የባሰውና ቤተ ክርሲቲያኗን ወደ ከፋ ምዝበራና በዘረኝነት ተገን የሌቦች ቡድን የተዋቀረበት ሆነ ሊቃነ ጳጳሳቱም ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀውንባወ ጡት ሕግ መሰረት ከመስራትና ከመቆርቆር ይልቅ የየትኛው ቡድን አባልና ደጋፊ ብሆን ጥቅሜ ይከበርልኛል ዘመዶቼ ያልፍላቸዋል በሚል ከንቱ እሳቤ በመተብተብ በእምነት ዛሉ ለተጠሩበት ዓላማና ለተለዬለት የእምነት ተልእኮ ታማኝ መሆን አቅቶአቸዋል፤ ያሳዝናል ምን ለማግኘት የት ለመድረስ እንደሆነ ግራ ያጋባል፡፡

   ራቁትነት ከዚህ በላይ ምን አለ፤ እግዚአብሔርም ወዴት ናችሁ ብሎ ለመጠየቅና ለመፈለግ በሰሩት ስራ የሚጸጸት የተዘጋጀ ልብ ጠፍቶኣል፡፡ የመንግስትም ሆኔታ ግራ ያጋባል፡፡ የሚገርመው እንዴት ዶ/ር ሽፈራውና ሌሎች አካላት ለቤተ ክርስቲያኗ መፍትሄ ይሰጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ እነሱማ ራቁቷን ስትንከራተት አገኟት፡፡ በጦር ሜዳ መካከል እንደ ተገኘ ጠላት ተረባረቡባት፤ ምክንያቱም እንኳንም እናቴ ሞታ እንዲሁም እልቅስ አልቅስ ይለኛል እንዲሉ አሳፋሪ ስራ እየሰሩ ነው፡፡ ጭራሽ አባበሱት፤ ከመፍትሄው ይልቅ ስልጠና የግንዛቤ ማስጨበጫ በሚል ሰበብ ከዘራፊዎቹና ከተከሳሾች ጋር በመጎዳኘት የተከሰሱበትን ጉዳይ ከማጣራትና መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ አድበሰበሱት አሁንማ ጓደኛ ነን አብረን እንሰራለን እየተባለም ነው መደናነቅ ተጀምሯል፡፡

   ወይ ዶ/ር ሽፈራውና የፌደራል ጉዳዮች ሰራተኞች፤ ከዚህ በፊት በሸዋ ተወላጅነትና በኦሮሞነት ብቻ ለበቂ ምክንያት ከህጋዊ አሰራር ውጪ ተበድለናል ይታይልን የሚሉ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሰራተኞች አቤቱታ ለፌደራል ጉዳዮች ሚንስቴር ማቅረባቸው ይታወቃል፡፡ ምርጫው ይለቅና በጥልቀት ተወያይተን መፍትሔ እንሰጣለን ተባለ፡፡ ወይ ዶ/ር ሽፈራው ታሪክና እውነት ይፍረድ፤ ፍርዱ ይህ ከሆነ የት ይኬድ፤ ስራው ይገርማል(ፍትህ በነዶ/ር ስትከሳና ስትጎሳቆል ትዕቢት በልበ ሙሉነት ሲንጎባለል ተመለከትን) ይሁና…

   ቤተ ክርስቲያኗ የተዋረደችው እኮ በአንድ ተራ ዲያቆን ለዛውም ዲቁናውን እንኳን በቅጥ ያላደራጀና ያላደላደለ ውዳሴ ማርያም መድገም የማይችል በማንኛውም መመዘኛ ለስራ አስኪያጅነት የማይበቃና የማይመጥን በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርጦ በፓትርያሪክ የተሾመን ሊቀ ጳጳስ ከመንበሩ አፈናቅሎ እንደዚያ ያለ ዘግናኝ ስህተት ሲፈጸም ቆሞ መመልከት ትክክል ነው? ጉዳዩስ የግለሰብ ጉዳይ ነው? ዝምታው ምን ያመላክታል? ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያኗ በእምነቱ የቆረጠ ኣባት በማጣቷ ለራቁትነት የተዳረገችው፡፡ ለተራና ለምናምንቴ ሰዎች ተላልፋ የተሰጠችው፡፡ እባካችሁ አባቶች ከዘረኝነትና ከወገንተኝነት ጸድታችሁ ቤተ ክርስቲያንን ነጻ ሊያወጣ በሚችል መልኩ ተቀናጁ ነገሮች ይፈተሹ መበታተንና በተለያየ ጎራ መሮጡ ይቅርባችሁ፡፡ ያለፈው ዘመን ይብቃችሁ፡፡

   በአንድ ወቅት አንድ ሊቀ ጳጳስ ለአንድ የወንዛቸው ልጅ በላኩት መልዕክት ላይ፣ የአካባቢህን ሰውና ያገርህን ሰው እየጠከምክ እራስህን ጥቀም፣ ጥቅምም ከሆነ ከነሱ ተጠቀም፤ በማለት ሰው እየሰማቸው በድፍረት ተናግረዋል፡፡ ይህ ምን ማለት ነው? ምን አልባት አገር ወዳድነት? ቂቂቂ ዝቅጠትና ራቁትነት፡፡ ከዚክ በላይ ምን አለ? ሌሎቹስ ምን እያደረጉ ነው? በእውነት ለእምነታቸው ተለይተው ቆርጠዋል ያሳዝናል…

   …ሞት ላይቀር ምንድነው ማንቋረር እንዲሉ አበው ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ አምባገነንነትና ዘረኝነት ለታላቁ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስም አልበጀ ይልቅስ ታሪክ የጣለብዎትን የቤተ ክርስቲያን ስልጣንና አደራ ሁሉን አቀፋ አባት ሆነው ቢያሳልፉት ይሻላል፡፡ በተለያየ ነገር ተተብትበው ሌትና ቀን ለሚወተውትዎት ጥቅመኞች ብቻ ጆሮዎን ከመስጠት ተቆጥበው በሃይማኖት ከበቁትና አጠገብዎ ካሉት ጳጳሳት ጋር ቆም ብለው ቢያሰላስሉ ይሻላል፡፡ በጸሎት ቢተጉ ይሻላል፡፡

   እነዚህ በዙሪያዎት ለአደን እንዳደባ ተኩላ የሚያንዣብቡትን የተደራጁ ሌቦችና አማካሪዎች ከቤተ ክርስቲያንዎና በመንፈስ ቅዱስ ከተሰጠዎ ስልጣን አይበልጡም፡፡ ሕጉ አለልዎ መንፈሳዊና ቁጥብ የሆኑ ጳጳሳት አሉልዎ በጸሎት የሚያግዙዎ አበው በየገዳሙ አሉልዎ እባክዎ ያስቡበት፤ ቤተ ክርስቲያኗን አያስበሏት፤ በተወራልዎና በተደረገልዎ መጠን ሳይሆን ማሰብ ያለብዎ በህጋዊነት ይመኑ፤ ለሲኖዶሱም ክብር ይስጡ ከሁሉ በላይ እግዚአብሔርን ይፍሩ? ምክር አይደለም የመረረ ማስጠንቀቂያና ላለመፈረካከስ መድሃኒት ነው ብለን ነው አስተዳደርዎ ዘቅጧል ተበላስቷል ዘረኝነት አይኑን አፍጥጦ ተጋኖብዎታል በኃላ የተቋጠረው ውል እንዳይጠፋና መመለሻው እንዳይቸግር ትህትናን በመላበስ ቢያስቡበት ይሻላል እርስዎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክና የሁሉም አባት መሆንዎን አይዘንጉት እኛ አምነናል እስርዎም ይመኑበት

   ሞት ላይቀር .. ካለፉት አባቶች ደጉንና ክፉውን መመርመርና መማር ይበጃል፡፡ ይህ ካልሆነ የመረረው ይመጣል፡፡ አቡነ ማቴዎስም ከተደበቁበት ዋሻ ይውጡና እውነትን ይጋፈጡ!!!

 2. adis July 31, 2015 at 6:02 am Reply

  LEHARA AZEGAJOCH: EBAKACHIHU LEBOCH YAMETULACHIH YEWISHET ALUBALTA TEKEBLACHIHU AIR LAY KEMAWALACHIHU BEFIT DIROTO ALUBALTA YIZO YEMIMETABACHIHU MANNER BITATARU. TEGEMETACHIHU! EBAKACHIHU 100% BAYHONIM 1% EWNETA TSAFU!

  WANA SIRA ASKIYAGU LIKEMAEMRAN YEMANE ZARE EYESERAW YALEW AYZOH YEMIYASBIL ENGI YEMIYSWEKIS AYDELM KITR BETEMELEKETE MIN ALEH MEBAL KERTO MINTAWKALEH EYETEBALE BLIKAWNT FETENA EYETESETE BEFETENAW WTET SIKRBLET KEMFEREM WITH ESUYEMIYAWKEW NEGER YELEME KEFETAGNOCH WISTIM LIKU MIKTIL SIRA ASKIYAGNEW GIN YIH ASERAR YEGODACHE DELALAW ABA HIRUY, DELALAW DAWT YARED, DELALAW HAILU GUTETA YIH AKAHED TEKARTO GENZEB YEMISETU ENDIKETRU EYETATU NEW. HARA MINCHEGERW WEYIS AZEGAJU YALTAWEK YEKITR DELALA NEW?

 3. Getasew May 31, 2016 at 3:32 am Reply

  እውነት የቤተክስስቲያን ችግር ተፈትቶ እናየው ይሆን ?
  ለኣማሳኞቹ ልቦና ይስጣቸው ። አኛም ከሓሜት ወጥተን እንዳቅማችን ቤተክርስቲያንን እናገልግል ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: