በደ/ብሥራት ቅ/ገብርኤል በአለቃው ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አይሏል፤ ‹‹ጸሎተ ምሕላ ይዘናል፤ ሕዝብ የሚወደው ኦርቶዶክሳዊ አባት እስክናገኝ ተቃውሟችን ተጠናክሮ ይቀጥላል››/ምእመናን/

 • ትላንት እሑድ ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ለኹለተኛ ጊዜ ደብሩ፣ በአለቃው ‹‹የመንግሥት ያለኽ›› ጩኸት እና በምእመናን ‹‹ኃይል የእግዚአብሔር ነው፤ አንፈራም፤ አንሰጋም›› መዝሙር እና ተቃውሞ ውሏል
 • ‹‹ስለ ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ምሕላ ይዘናል፤ የሀገረ ስብከቱ ነገር አታካች ኾኖብናል፤ መፍትሔ ካልተሰጠን የአካባቢው ሰላም እየታወከ፣ በየሰንበቱ ቅዳሴው በፖሊስ እየተጠበቀ መቀጠል ስሌለበት ሕዝቡ ተወያይቶ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀውን ይወስናል፡፡›› /ምእመናኑ/

*           *           *

Melake Birhan ZeMenfes

በ፸ዎቹ መጨረሻ የሚገመተው ዕድሜአቸው ሊያስከብራቸው ሲገባ የመንፈሳዊነት ምልክት ከማይታይበት ዕርግናቸውና ኦርቶዶክሳዊ ወገናዊነት ከሌለው የቀማኛና የእብሪት አስተዳደራቸው የተነሣ ከሳምንት ሳምንት የፖሊስና የደኅንነት ያለኽ በሚለው ጩኸታቸው እየቀለሉ የሚገኙት አለቃው መልአከ ብርሃን ዘመንፈስ ቅዱስ

 • የቤተ ክርስቲያንን ነገር አደራ ብለው መባረኪያ መስቀላቸውን የሰጡ እንደ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እና ብፁዕ አቡነ መልከ ጸዴቅ ያሉ ደጋግ አባቶችን ያየ ምእመን በምን አእምሮው ይቀበላቸው? በፍቅር የኖረ፣ ክርስትናውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሕዝብ ነው፤ አኹን የመጡበት አስተዳዳሪ ግን የመንፈሳዊነት ምልክት የሌላቸው እብሪተኛ ናቸው፤ ካህናትን ይበትናሉ፤ ምእመናንን ያሳድዳሉ፤ ሰበካ ጉባኤን ያፈርሳሉ፤ ቤተ ክርስቲያንን ይዘርፋሉ፤ እናንተን ልክ ካላስገባኹ እኔ ትግራይ አልተወለድኹም እያሉ ጎጠኝነትን ያስፋፋሉ፤ ቤተ ክርስቲያንን እያጠፉ ስለኾነ ኦርቶዶክሳዊነታቸውንም እንጠራጠራለን፡፡

Bisrate Gabriel Church00

 • በቃለ ዐዋዲው የቤተ ክርስቲያን መተዳደርያ ድንጋጌዎች የወሳኝነት እና የተሳትፎ ድርሻ ያላቸውን የማኅበረ ካህናት፣ የማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮችን በማባረር አስተዳደሩን ለብቻቸው ተቆጣጥረዋል፡፡ የደብሩ የጠበልተኛ ማደርያ በኾነው ይዞታ ሹፌራቸው ከእነቤተሰቡ ይኖርበታል፤ ቦታውን ከልሎ በስሙ ካርታ ሊያወጣበት እየተሯሯጠ ነው፤ በልምድ እንደተገነዘብነው፣ ሰበካ ጉባኤ ሲፈርስ ቤተ ክርስቲያን ይዘረፋል፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመዝረፍ ሲያስቡ ሰበካ ጉባኤውን ነው የሚያፈርሱት፡፡
 • በመጀመሪያ በሰበካ ጉባኤው የሰንበት ት/ቤቱን ተወካይ አልቀበልም ብለው ሰንበት ት/ቤቱን ከአጥቢያው አስተዳደር አገለሉ፤ ቀጥለው የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ ከዝርፊያ ለመጠበቅ በሙዳይ ምጽዋት ቆጠራው ላይ የተገኘውን የምእመኑን ተወካይ ዲ/ን ሰሎሞን የኋላእሸትን በርግጫ መትተው እና ገፍትረው አባረሩ፤ ለቀናትም በፖሊስ ጣቢያ አሳሰሩ፤ ይባሳችኹ ብለው በአገልግሎታቸው የተመሰከረላቸውንና በደብሩ የልማት እንቅስቃሴ ሐሳብ በመስጠታቸውና ጥፋቶችን በመቃወማቸው በጠላትነት ያዩዋቸውን አራት የማኅበረ ካህናት ተወካዮችን ከማይመለከተው የክፍለ ከተማው የሰው ኃይል አስተዳደር ሓላፊ ጋር በመመሳጠር ከደብሩ በዝውውር ስም አባረሩ፡፡ አኹን ሰበካ ጉባኤው በእርሳቸው ብቸኛ ቁጥጥር ሥር ነው፡፡
 • የአለቃውንና የጥቂት እኩያን ግለሰቦችን ፍላጎት ለማሟላት መልአከ ገነት ሙሴ ዘነበ በሚባለው የክፍለ ከተማው የሰው ኃይል አስተዳደር ቲተር እና ፊርማ በዝውውር ስም ግፍ እና በደል የተፈጸመባቸው ካህናትና ሠራተኞች፡- ቀሲስ ኃይለ ገብርኤል ደርብ፣ ሊቀ ጉባኤ ጽጌ አክሊሉ፣ መሪጌታ ሲሳይ ዘመነ እና ወ/ሮ አበባ ተገኘ ናቸው፡፡ ካህናቱ እና ሠራተኞቹ ቤተሰቦቻቸውን ችግር ላይ በሚጥል አኳኋን የተፈጸመውን ዝውውር በመቃወም ቢያመለክቱም፤ ክፍለ ከተማው ዝውውሩን የፈጸምኩት ‹‹የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቀይር ብሎኝ ነው›› ሲል ሀገረ ስብከቱ በበኩሉ ‹‹እኛ እንዲቀየሩ ትእዛዝ አልሰጠንም፤ ይህንንም ዝውውር አናውቅም›› በሚል እየተጉላሉና በቀል እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡
 • በአጠቃላይ፣ በየደረጃው እየተመደቡ የሚላኩ ሓላፊዎች ኦርቶዶክሳውያን ናቸው ወይ የሚል ጥያቄ አለን፤ በማንፈልገው አለቃ አንተዳደርም፤ ሕዝብ የሚወደው አለቃ ነው መሾም ያለበት፤ የሚገባው ክፍል መንፈሳዊ አባት እስኪመድብና መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ ከጸሎት ጋር ተቃውሞው በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል፤ ሰላምን የምንሻ የሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች ነን፤ የሀገረ ስብከቱ ነገር አታካች ኾኖብናል፤ መፍትሔ ካልተሰጠን የአካባቢው ሰላም እየታወከ፣ በየሰንበቱ ቅዳሴው በፖሊስ እየተጠበቀ መቀጠል ስሌለበት ሕዝቡ ተወያይቶ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀውን ይወስናል፤ ተወልደን ያደግንበት፣ አግብተን ልጅ ያሳደግንበት ቤተ ክርስቲያን ነው፤ እነርሱ ልክ እንደ መሥሪያ ቤት በፔይሮል ፈርመው ደመወዝ የሚወስዱበት ቢሮ አድርገው ቢያዩትም ለእኛ በሐዘንና በደስታ ልመናችንንና ምስጋናችንን የምናቀርብበት የሥርዐተ አምልኮ ቦታ ነው፤ ለማንም የምንተወው ጉዳይ አይኾንም፡፡
Advertisements

7 thoughts on “በደ/ብሥራት ቅ/ገብርኤል በአለቃው ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አይሏል፤ ‹‹ጸሎተ ምሕላ ይዘናል፤ ሕዝብ የሚወደው ኦርቶዶክሳዊ አባት እስክናገኝ ተቃውሟችን ተጠናክሮ ይቀጥላል››/ምእመናን/

 1. Anonymous June 29, 2015 at 6:19 am Reply

  ሀራ ማትውጀውን አባት ትሰደቢያለሽ የአንችውን ደጋፊ ታነግሻለሽ

 2. SAMI June 29, 2015 at 6:27 am Reply

  EGIZIABIHER WORTODOCS TEWAHIDO HIMANOTACHININ YITEBIKE LELA TELIEKO YALACHEWN YIGESITSI

 3. ዳሞት June 29, 2015 at 11:15 pm Reply

  ሰላምን የምንሻ የሰላማዊው የኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች ነን

  ከላይ እንደ ርዕስ የተጠቀምኩበት አረፍተ ነገር ልብን የሚነካ ስለእምነታችን ሲባል የሚታለፍበትን መከራ የሚገልፅ ሐይል ያለው ነው። ይህ ሃረግ ክርስትና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችንን ምን እንደምታራምድና ምን እንደምትመሥል የሚገልፅ ነው።

  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን ሰላምን የምትሻ፣ ሰላምን የምታራምድና የምትሰብክ፤ ሰላማዊውን የሰላም ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስን የምታመልክና የምትሰብክ ነ ስለሆነች ልጆቿም ያስተማረቻቸውን ይህን ልብ የሚነካ ንግግር ተናገሩት።

  ምንም እንሿን ቤተ ክርስቲያንና እውነተኛ ልጆቿ ሰላምን ያነገቡ የሰላሙን ባለቤት ክርስቶስን የሚያመልኩ ቢሆንም ጊዜው የኛነው የሚሉ ከክርስትናና ከመንፈሳዊ አስተሳሰብ ይልቅ የአህዛብነትንና የአለማዊነት አሥተሳሰብን ያነገቡ በተግባር የቤተክርስቲያኗ ልጆች ያልሆኑ ነገር ግን የአብርሃም ልጆች ነን እንዳሉት በድርጊት ግን ሌላ እንደነበሩት ያሉ አስመሳዮች ሰላምን እያወኩ ቤተ ክርስቲያንን እረፍት አሳጥተዋታል።
  እኔ ግርም የሚለኝ ሌላው ነገር ደግሞ እንዲህ ካላደረግሁ ከዚህ አልተወለድሁ እየተባለ የሚካሔደው ትምክህትና እብሪት ነው። የአለማውያኑ ሲገርመን የሀይማኖት ካባ የደፉ ሳይቀር በዚህ ክፉና ፀያፍ የደካማ አስተሳሰብን መከናነባቸው በራሱ አካባቢውን ሀይማኖት የለሽና ሰባዊነት ያልነካካቸው ነው ያስመሰሉት። እብሪተኝነትና ክፉ ማድረግ ለማንም አይበጅም እንጅ ለክፋትና ለጥፋት ህፃናትም ይበረታሉ። ስለሆነም ከእምነትና ከሰባዊነት የተነሳ ባይሆን ኖሮ ማንም ከማንም አያንስም ነበር።

  እኔ ዘርንና መሳሪያን በመመካት ትምክትንና ፅንፈኝነትን የማውቀው ክርስቶስንና የሱ የሆኑትን ያሳድዱና ይገሉ የነበሩት በአይሁድ ካህናት ዘንድ እንጂ በክርስትና አላየሁም። ክርስትና ባሪያ ገዠ፤ አይሁድ ግሪካዊ የማትል ሁሉንም በአንድ አይን የምታይ ሚዛኗ የማያጋድል የማያዛባ ነው። እነዚህ ሰዎች ግን በዘራቸው ትምክተኝነት የሚታበዩና የዘራቸውን ስልጣን መሳሪያ በመመካት የፈለጉትን የሚያደርጉ የሚዘርፉ እድሜና ታሪክ እንሿን የማይወቅስ የማያስተምራቸው እጂግ የወረዱ በእንስሳነት አስተሳሰብ የሚኖሩና የሚውሉ ናቸው። ጥንትም ሆነ ዛሬ እንስሳ ብቻ ነው ከዘሩ ተጣብቆ ዘሩን ተገን አድርጎ የሚኖር የሚንቀሳቀስ።

  እኒህ እድሜ የማያስተምራቸው ዘመን የማይወቅሳቸው ባለካባ ሀይማኖተኛ መሳዮች ገንዘብን በመውደድ ቤተክርስቲያንን የሚቦረቡሩ መንፈስ ቅዱስን የሚዋሹ የሚፈታተኑ ናቸው። አዎ! እኒህ ገንዘብን ውሸትን አምላካቸው ያደረጉ ከፅድቅ ይልቅ ሌብነትን የሚያደርጉ ከሐናንያምና ከሰጲራ የማይማሩ ነገ በሃይለኛው በእግዚአብሔር እጅ እንደሚወድቁና ፍርድን እንደሚቀበሉ የዘነጉ ደካሞች ናቸው። የዘረፉት ብልና ዝግ ሆኖ እንደሚቀርና ተልቶ አላስቀርብ እንደሚላቸው የማያውቁ ልስን መቃብሮች ናቸው።

  እነዚህ አካላት ፀያፍ የሆነውን የዘረኝነት ትምክህትና ፅንፈኝነትን፤ የዘራቸውን መሳሪያና ወንበር አምላኪነትን እርኩስ መንፈስ እስካላወለቁና በቤተክርስቲያኗ መንበር እስከቆሙ ድረስ የቤተክርስቲያን ክፉ እንቅርቶችና የፅድቅ እንቅፋቶች ሆነው ይቀጥላሉ።

  እነሱ በዘራቸው ትምክትን እየተናገሩ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ የተኮፈሰውንና መሳሪያን በመመካት ውንብድናን እያከናወኑ ደም ለማፍሰስ፣ ለማሳሰር፣ ለማባረርና ለመዝረፍ ይተጋሉ። የቤተክርስቲያኗ ልጆች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች ደግሞ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ የሚለውንና ሃይል የእግዚአብሔር ነው የሚለውን በእምነት ይዘዋልና እኛ በእግዚአብሔር እንመካለን ሃይላችንም እሱ ነውና ሰይፍና ጎራዴ ወይንም ስጋ ለባሽን አንመካም ሃይልም አናደርጋቸውም በማለት ከኒህ ይርቃሉ። ነገር ግን ለቤተክርስቲያናቸውና ስለመዳናቸው እምነት ለመጋደል የእምነትን ፅሩርና ሰይፍ ይኸውም የእግዚአብሔር ቃል ነው ፣ እሱን ይዘውና ታጥቀው በእምነት ይጋደላሉ።

 4. Anonymous June 30, 2015 at 10:12 am Reply

  abate beande wogen leje belela wogen zerefawen eyatutofute new

 5. Samuel tesfu July 19, 2015 at 12:29 pm Reply

  ቅዱሥ ገብርኤል እሡ ይፍረድ! ይህ ሁሉ ደብሩ ከፍተኛ ገቢ ያለው በመሆኑ ለምዝበራ እንዲያመች ሠበካ ጉባኤውን አፍርሠዋል ምእመኑን በትነዋል የሚሠማን አጣን እሡ ገብርኤል ይዳኘን ታማኝ እረኛ ይሥጠን.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: