የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የቤተ ክርስቲያንን የተለያዩ አካላት በወቅታዊ ጉዳዮች እያነጋገረ ነው

 • ማኅበረ ቅዱሳንን በመወንጀል ‹‹ወጣቶቹን ሰብስባችሁ እሰሩልን›› ያሉ አስተዳዳሪዎች የፖሊስ እና የደኅንነት አካላትን በተባባሪነት ወቀሱ
 • ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንን እንደተቋም መወንጀል አትችሉም፤ ፖሊስ የእናንተ ብቻ አይደለም፤ መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ›› /ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም/
 • የቅድመ ውይይት ምክክሩና ውይይቱ፣ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የወሳኝነት ድርሻ ያላቸውን ማኅበረ ካህናትን፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮችን ሊያካትት ይገባል፡፡

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፭ ቁጥር ፰፻፭፤ ቅዳሜ ሰኔ ፲፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

MoFA Logo
በሙስና መንሰራፋት፣ በመልካም አስተዳደር እና በፍትሕ ዕጦት ሳቢያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እየተደረገ ካለው የአገልጋዮች እና የምእመናን መነሣሣት ጋር በተያያዘ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የቤተ ክርስቲያኒቱን አካላት እያነጋገረ ነው፡፡

ብልሹ የሰው ኃይል አስተዳደር እና የፋይናንስ አሠራር በተከታዩ ዘንድ የሚፈጥረው የተከማቸ ቅሬታ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ እምነት እንዲያጡ ምክንያት እየኾነ እንዳለ የሚገልጸው ሚኒስቴሩ፣ በቅርቡም የወሳኝነትና የተሳትፎ ድርሻ ያላቸው የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር እና የአገልግሎት አካላት የሚሳተፉበት ተከታታይ ውይይት እንደሚያካሒድ ተጠቁሟል፡፡

በሚኒስቴሩ ጥያቄ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተመረጡ አድባራት አስተዳዳሪዎች ከትላንት በስቲያ ከቀትር በኋላ ከሚኒስትሩ ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም እና ከሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው ጋር የውይይቱ ቅድመ ዝግጅት ነው የተባለው ምክክር አድርገዋል፡፡

በዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የተመሩ የኻያ አምስት አድባራት አስተዳዳሪዎች በተካፈሉበት በዚኹ ምክክር፣ ‹‹በማኅበራት ሰላማችንን እያጣን ነው፤ ሰንበቴ ሲከበን እናንተም የላችኹም፤ መንግሥትም የለም፤ አልደገፋችኹንም፤ አልረዳችኹንም›› የሚሉ ክሦች እና አቤቱታዎች ከአንዳንድ አለቆች መቅረቡ ተጠቅሷል፡፡

ካለፈው ሚያዝያ መጨረሻ ጀምሮ የሀገረ ስብከቱ ሰንበት ት/ቤቶች ሙስና እንዲወገድ፣ መልካም አስተዳደርና ፍትሕ እንዲሰፍን፣ እምነትና ሥርዐት እንዲጠበቅ በሰልፎችና በስብሰባዎች የሚያካሒዱት እንቅስቃሴም ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ልብሱን ለውጦ የመጣበት ነው›› ብለዋል – አስተዳዳሪዎቹ፡፡

የሰንበት ት/ቤት አባላቱ የመለያ ልብሳቸውን(ዩኒፎርሞቻቸቸውን) ለብሰው በመውጣት በሚያደርጓቸው ሰልፎች እና ስብሰባዎች መንግሥት የጸጥታ ርምጃ ሳይወስድ በዝምታ መመልከቱን የጠቀሱት አለቆቹ፣ የፖሊስ እና የደኅንነት አካላትን በተባባሪነት በመውቀስ ‹‹ወጣቶቹን ሰብስባችኹ እሰሩልን›› ብለው ሲጠይቁ ተሰምተዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን ሀብት ለግላቸው በማካበት ከገቢያቸው በላይ የሚኖሩ አለቆች በሥነ ምግባርና በፀረ ሙስና ኮሚሽን እየተመረመሩ በሀገሪቱ ሕግ እንዲጠየቁ የሰንበት ት/ቤቶቹ የሚያመለክቱ ሲኾን ዋና ሥራ አስኪያጅ እና አንዳንድ አለቆች በአንፃሩ፣ ‹‹ዶልፊን እና ሃይገር የሚያቆሙ ናቸው፤ ቢዝነስ አድርገውታል›› በማለት ይከሷቸዋል፡፡

the-heavily-corrupt-haile-abrehaበምክክሩ ወቅት ቃሉን መጥኖ እንዲናገር ቢመከርም ‹‹ብሶት ነው የሚያስጮኸኝ›› በማለት በከፍተኛ ድምፅ ሲናገር የነበረው መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ብሎ ብሎ አባላቱን የሰንበት ት/ቤት ዩኒፎርም አስለብሶ መውጣት ጀምሯል፤ እርሱስ ሕንፃውን ከየት አምጥቶ ነው ያቆመው?›› ሲል በሰንበት ት/ቤቶቹ መነሣሣት ማኅበሩን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ ‹‹ወጣቱን ዩኒፎርም እያስለበሱ ይልካሉ›› ያሉ ሌላው አስተዳዳሪ፣ ‹‹እንዴት አድርገን መከላከል እንዳለብን አሠልጥኑን እንጂ ስለሰላም ምን ያደርግልናል፤›› በማለት የሚኒስቴሩን ሓላፊዎች አስደምመዋል ይላሉ የስብሰባው ተሳታፊዎች፡፡

ፖሊስ እና የጸጥታ አካላት የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት የሚጠብቁ መኾናቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም፣ ‹‹ፖሊስ ለእናንተ ብቻ ነው እንዴ?›› ሲሉ አለቆቹን ጠይቀዋቸዋል፤ ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና የተሰጠው ሕጋዊ ማኅበር መኾኑን ጠቅሰው፣ ‹‹ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ይኖራሉ እንጂ ማኅበር እያላችሁ በጅምላ መጥራት የለባችኹም፤ ተቋሙን በጅምላ መፈረጅ ወንጀል ነው፤›› ብለዋቸዋል፡፡

ሀገረ ስብከቱን ጨምሮ አስተዳዳሪዎቹ በሚመሯቸው አድባራት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ለምእመናንና ለሰንበት ት/ቤቶቹ ወጣቶች ምሳሌ መኾን እንደሚገባቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ሰው እሰሩ ያላችኹት ሌላ ችግር ነው የሚፈጥረው፤ ጀግና መፍጠር ነው፤ የምናስረው ሰው የለም፤ መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ›› በሚል ለአለቆቹ የእሰሩልን ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

State Minister Ato Mulugeta Wuletaw and Minister Dr Shiferaw

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም እና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉጌታ ውለታው

በሚኒስቴሩ ዕቅድ መሠረት ይካሔዳል የተባለውና በቤተ ክርስቲያኒቱ ከሚታየው የአገልጋዮች እና የምእመናን የዕቅበተ እምነት፣ የመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ጥያቄዎች መነሣሣት ጋር የተገጣጠመው የቅድመ ውይይት ምክክር፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር መዋቅር የወሳኝነት እና የተሳትፎ ድርሻ ያላቸውን ማኅበረ ካህናትን፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮችን ሊያካትት እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡

በሰላም፣ በዘመናዊ አሠራር እና በመልካም አስተዳደር ላይ የሚያተኩረው ዋናው ውይይት በሚቀጥሉት ኹለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር የሚኒስቴሩ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ የውይይቱን አቅጣጫ ለማመቻቸት በሚል ከትላንት በስቲያ በሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች ከተመሩት የአድባራት አለቆች ጋር ከተካሔደው የቅድመ ውይይት ምክክር ፍጻሜ በኋላም ‹‹ዘመናዊ አሠራር ዴሞክራሲዊነት እና ብዝኃነት›› በሚል ርእስ በሚኒስቴሩ የተዘጋጀ የመወያያ ጽሑፍ እንደተሰጣቸውም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

Advertisements

13 thoughts on “የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የቤተ ክርስቲያንን የተለያዩ አካላት በወቅታዊ ጉዳዮች እያነጋገረ ነው

 1. Kebekab June 22, 2015 at 5:57 am Reply

  ፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ውስጥ የማህበረ ቅዱሳn አባላት ወይስ ቃለ አቀባዮች ናቸው ያሉት????

 2. Anonymous June 22, 2015 at 7:46 am Reply

  የድረሱልን ጥሪ ከአቃቂ ቃሊቲ ምዕመናን!!!

  በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን!

  በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ላለፉት ሃምሳ አመታት ከዘጠኝ በላይ ገዳማትና አድባራት ለጥምቀት በዓል ሲገለገሉበት የነበረውን በሀገረ በቀል ዛፎች ያጌጠውን ጥምቀተ ባህር ለልማት በሚል ሰበብ በክፍለ ከተማው የተሰገሰጉት የፕሮቴስታንት መናፍቃን ባለስልጣናት ከቤተክርስቲያኗ ዕውቅና ውጪ ስፍራውን እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ እየታረሰና እየወደመ ሲሆን ይህም ከመንግስትንና ከህዝብ የተሰጣቸውን ሀላፊነትና አደራ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት በከፍተኛ ሁኔታ ያለ እንቅልፍ እየሰሩ ያሉ የፕሮቴስታንት መናፍቃን ጥቃት መሆኑ ግልፅ ሆኗል፡፡

  ከጃንሜዳ ቀጥሎ በአዲስ አበባ በታላቅ ድምቀት በአለጥምቀት የሚከበረው በዚሁ ስፍራ የነበረ መሆኑ ሲታወቅ ይህ ሚሊየኖች በደመቀ ሃይማኖታዊ ስርዓት የሚያከብሩትን በዓል ለማጥፋት የፕሮቴስታንት መናፍቃኑ መንግስታዊ መዋቅሩን እየተጠቀሙበት መሆኑን ለብዙዎች ግልፅ ሆኗል፡፡
  ከዚህ ቀደም የከተማዋን የመስቀል ማክበሪያ ስፍራን ነጥቀው ሌላ ምትክ ስፍራ እንዳይሰጥ በማድረግ በዓሉን የማጥፋት ተልእኮ የተሳካላቸው መናፍቃኑ አሁን ደግሞ ከሃምሳ አመት በላይ የቤተክርስቲያኗን የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ስፍራን ለልማት በመመል ሽፋን የማጥፋት ስራቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ቦታው ሲወድም እስካሁን አንድም የቤተክርስቲያን አባቶችና አስተዳዳሪዎች ለምን ብለው እንኳን ለመጠየቅና ጉዳዩን ለምዕመናን ለማሳወቅ አልፈቀዱም፡፡ ይህም ቦታው ለአንዲት ባለሃብት ተሸጧል አየተባለ በህዝቡ መሃል የሚነገረውን ጭምጭምታ የሚያረጋግጥ ሊሆን ይችላል፡፡
  በመሆኑም፦
  1ኛ. ህዝበ ክርስቲያኑስለጉዳዩ ወደ እግዚአብሔር በፀሎት እንዲያሳስብ
  2ኛ.መንግስትም ስለጉዳዩ በማጤንና በውስጡ ተሰግስገው ሌላ ግላዊ ዓላማቸውን በማራመድ ህዝቡ በመንግስት ላይ እንዲከፋና እንዲመረር እንዲሁም ጥላቻ እንዲያድርበት እየሰሩ ያሉ አካላትን አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድባቸው በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡
  3.ታላቅ ሰማያዊ አደራ የተጣለባችሁ አባቶች ከዝምታ አዚም ወጥታችሁ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግራችሁ አንድ ትውልድ እግዚአብሔርን የሚያመልክበትና ሃይማኖታዊ ስርዓት የሚፈፅምበት የነበረውን ጥምቀተባህራችንን ታስከብሩልን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡

 3. sim June 22, 2015 at 11:11 am Reply

  አይ ስምንተኛዉ ሺህ አባት ልጆቹን ለንስሀ እና ለስጋወደሙ ማብቃት በሚገባበት ወቅት የእሰሩልን ጥያቄ ማቅረብ ምን ይባላል፡፡ በሚናገሩት ሰዉ ፊት እንኩዋ የማይጠነቀቁ እነዚህ መንፈሳዊነት ቀርቶ ሰባዊነት የሌላቸዉ አረመኔ ሰወች ቤተክርስቲያናችንን እንደግል ቤታቸዉ ሲዘርፉዋት ኑረዋል እና በፍርድ አካላት ሊጠየቁ ይገባል፡፡

 4. ገብረ ማርያም June 22, 2015 at 2:17 pm Reply

  “ፈፀምክሙሂ ዘመነክሙ ዘመነ ደናግል እልኩ
  እንዘ ኩልክሙ ከመ አርዌ በበይናቲክሙ ትትናሰኩ”
  ” ባህቱ ለእመ ትትባልኡ ወትትናሰኩ ተሃልቆ ተርፈተክሙ”

 5. ገብረ ማርያም June 22, 2015 at 6:58 pm Reply

  እናንተስ አላችሁ አይደል ያቆረባችሁን ካህን እጅ የምትነክሱ እናንተ የእፉኝት ልጆች ሁሉ ለእርግማን የተፈጠራችሁ እግዚአብሔር ይገስፃችሁ ርጉማን ሁሉ ለሰይጣንና ለመልዕክተኞቹ ወደተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!!!

 6. Libu Yedema June 23, 2015 at 6:22 am Reply

  ዛሬ ዛሬ ይህች መከራዋ የበዛ ቤተክርስቲያን ከዉጭ ካለዉ ችግር ይልቅ ዉስጣዊ ችግሮች ይበልጥ እየተፈታተናት ይገኛል፡፡ የጌታችንን ስለጣነ ክህነት ይዘዉ በመቅደሱ ግን እጅግ ዘግናኝ ስራ ሲሰሩ ለተመለከተ አማኒ፤ እንዴ ምነዉ ሃይማኖት ቀይሬ ምንም ብጥብጥም ሆነ ችግር ባላይስ የሚሉ በርካታ ናቸዉ እንዴ እግዚአብሔር በመንበሩ የለም እንዴ ምነዉ ዝምታው፡፡ ጥቂት “ካህን” ተብዩዎች የበግ ለምድ የለበሱ፤ ምን ያህል ሙሰኞች እንደሆኑ ዛሬ ዛሬ በኣዲስ አበባ ከተማችን እጅግ የፈረጠሙ መነኮሳት ተብዬዎች በፉክክር የሚያሽከረክሩት ኮድ 2 የቤት አዉቶሞቢል ላየ እንዴ ወይ ዘመን ያስብላል የሚይዙት ዘመናዊ ሞባይሎች ልክ የፉክክር መድረክ ያሰመስላል፡፤ ዛሬ ዛሬ አንድ ካህን የደብር አለቃ ሆኖ ለመመደብ የሚከፍለዉ የጉቦ መጠን እሱ ባለቤቱ ነዉ የሚያዉቀዉ፡፡ ብቻ ገንዘብ ካለ …….. በሰማይ መንገድ አለ ….. የሚሰራዉ በዚሁ ቤተክህደት ዉስጥ ነዉ፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህ ሰዎች ስለ ሰማያሚ መንግስት የማይጨነቁ ብምድር ላይ ለወለዱአቸዉ ልጆች መከራን የሚያስቀምጡ ናቸዉና፡፡
  የሂሳቡን ነገርማ አይነሳ እንጂ ከተነሳማ ስንቱ የሂሳብ ሰራተኛ ተብዬ ነዉ በአግባቡ ወጪና ገቢዉን የሚያውቀው መሰረታዊ የሂሳብ ስሌትስ (መደመር መቀነስ) የሚያዉቀዉ እንደዉ ቤት ከሚዉል/ከምትዉል አስገባ እየተባለ የተሰገሰገዉ የዘመድ አዝማድ ሰንሰለት አይነካ እንጂ ወይ ጉድ…….. ፤ በኦዲት ግዜኮ ድርድሩ ምንያህል (ጉቦ) ታመጣላችሁ እንጂ ትክክል ነዉ አይደለም ሳይሆን ጨዋታዉ ሌላ ነዉ፡፡ ያም ቢሆን የነ የሃገረ ስበከት ቡድን እኮ “አጣሪ” ሆኖ ሲመጣ ሌላ የጉቦ መስመር ተከፈተ ማለት ነዉ፡፡ እና መሰረታዊ ለዉጥ ካልመጣ እንዲሁ ስንባላ ለነፍስም ለስጋም ሳንሆን መጠራት ይመጣል፡፡ ያኔ ፍትሃዊ ዳኛ መልሱን ይሰጠዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱም ሰዎች ቢሆኑም እኮ ምን ያህል ገንዘብ … እያሉ በገንዘብ ከሚቀልዱ በደሙ ለዋጃት ቤተክርስቲያን ምንያህል ክርስቲያን ብለዉ ቢቆጥሩኮ ይህ የዋህ ክርስቲያን በቁጥሩ ልክ ገንዘብ በሰጠ ነበር፡፡ ግንግን ይህ ሁሉ በዚህ ዘመን ሊሆን ግድኮነዉ፡፡ ስለዚህ የዚህ ሁሉ ምንጭ ወቅታዊ አፋጣኝ ምላሽ ካልተሰጠ ችግሩ ወደ ሌላ ይሄዳል፡፡ሆነ ተብሎ የሚሰራ ጉዳይነዉና ሕዝብ ይዳኝ፡፡
  ስለዚህ፡-
  1. ሕዝበ ክርስቲያኑ ህገወጥ ድርጊት የፈፀሙት (ጉቦኞች) ከቤተክርስቲያን እስኪሰናበቱ ምንም አይነት የገንዘብ ልገሳ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንዳያደርጉ ማስተባበር፤
  2. ማንኛዉም ሕዝበክርስቲያን የአጥቢያዉን የአስተዳደር ሰበካ ጉባኤ/አስተዳዳሪ ሁኔታ በጥልቀት መከታተል፤
  3. የቤተክህነት ሃላፊ ተብዬዎች ይህንን በህዝብ እንባ የገባ የስለት ብር በጉቦ መልክ እየተቀበላቸሁ ፍርደ ገምድል የምትሰጡ ዋዋዋ….. ደግሞ ይመስላችሁዋል እንጂ አትበሉትም ያዉ ወይ በመድሃኒት ያልቃል ወይ ለሳጥን መግዢያ ነዉ የሚሆነዉ፡፡
  4. ከምንም ነገር በላይ አብዝታቸህ ፀልዩ ….. ፀልዩ……ፀልዩ ጊዜዉ ከመቼዉም በላይ የከፋ ነዉና፤

  ሁሌ ልቤ እየደማ በዉስጡ ከሚቃጠለዉ ምእመን፡፡

  • Anonymus June 25, 2015 at 1:03 pm Reply

   ልቡ መልካም ሀሳቦችን አንስትሀል ያስቀምጥካቸው የመፍትሔ ሀሳቦችም ላይ በሁሉም እስማማለሁ 1ኛውን ግን አካሄዱ ሌሎችን እንዳይጎዳ እፈራለሁ እሱም ምንም አይነት የገንዘን ልገሳ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንዳያደርግ የሚለው ነው እርግጥ ነው እነኚህን ሰዎች ለመቅጣት ትልቁ መሳሪያ ነው በመሀል ግን ንጹሐን ካህናት አሉ በወር ደሞዛቸው ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ የአንድ ደሞዝ ቢታጎል ለጎዳና የቀረበ ህይወት ያላቸው አሉ በላተኞቹማ እስካሁን የበሉትን እየተጠቀሙ እስከ እድሜያቸው ፍጻ ሜ መቆየት ይችላሉ እናም ስጋቴ ገብቶህ ከሆነ ምልእክትህ ሌሎችን ስሜታዊ እንዳታደርግ ሰግቼ ነው፡፡ ባይሆን እንዳማራጭ እንዲህ አይነት ነገሮችን በየአጥቢያው ሚያስተባብሩ ታማኝ ሙዳይ ምጽዋት ሳይደርስ የህዝቡን ገንዘብ ሰብስበው ለካህናቱ ደሞዝ ሚከፍሉበት ስራ ካልተሰራ ከባድ ይመስለኛል

 7. Kuba Adugna June 23, 2015 at 11:44 am Reply

  Igiziabiher Libona Yistachaw. Le Betakiristiyanachinim Selam Yistat…..Amen

 8. Libe dema June 23, 2015 at 11:51 am Reply

  ዛሬ ዛሬ ይህች መከራዋ የበዛ ቤተክርስቲያን ከዉጭ ካለዉ ችግር ይልቅ ዉስጣዊ ችግሮች ይበልጥ እየተፈታተናት ይገኛል፡፡ የጌታችንን ስለጣነ ክህነት ይዘዉ በመቅደሱ ግን እጅግ ዘግናኝ ስራ ሲሰሩ ለተመለከተ አማኒ፤ እንዴ ምነዉ ሃይማኖት ቀይሬ ምንም ብጥብጥም ሆነ ችግር ባላይስ የሚሉ በርካታ ናቸዉ እንዴ እግዚአብሔር በመንበሩ የለም እንዴ ምነዉ ዝምታው፡፡

  ጥቂት “ካህን” ተብዩዎች የበግ ለምድ የለበሱ፤ ምን ያህል ሙሰኞች እንደሆኑ ዛሬ ዛሬ በኣዲስ አበባ ከተማችን እጅግ የፈረጠሙ መነኮሳት ተብዬዎች በፉክክር የሚያሽከረክሩት ኮድ 2 የቤት አዉቶሞቢል ላየ እንዴ ወይ ዘመን ያስብላል የሚይዙት ዘመናዊ ሞባይሎች ልክ የፉክክር መድረክ ያሰመስላል፡፤

  ዛሬ ዛሬ አንድ ካህን የደብር አለቃ ሆኖ ለመመደብ የሚከፍለዉ የጉቦ መጠን እሱ ባለቤቱ ነዉ የሚያዉቀዉ፡፡ ብቻ ገንዘብ ካለ …….. በሰማይ መንገድ አለ ….. የሚሰራዉ በዚሁ ቤተክህደት ዉስጥ ነዉ፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህ ሰዎች ስለ ሰማያሚ መንግስት የማይጨነቁ ብምድር ላይ ለወለዱአቸዉ ልጆች መከራን የሚያስቀምጡ ናቸዉና፡፡

  የሂሳቡን ነገርማ አይነሳ እንጂ ከተነሳማ ስንቱ የሂሳብ ሰራተኛ ተብዬ ነዉ በአግባቡ ወጪና ገቢዉን የሚያውቀው መሰረታዊ የሂሳብ ስሌትስ (መደመር መቀነስ) የሚያዉቀዉ እንደዉ ቤት ከሚዉል/ከምትዉል አስገባ እየተባለ የተሰገሰገዉ የዘመድ አዝማድ ሰንሰለት አይነካ እንጂ ወይ ጉድ…….. ፤ በኦዲት ግዜኮ ድርድሩ ምንያህል (ጉቦ) ታመጣላችሁ እንጂ ትክክል ነዉ አይደለም ሳይሆን ጨዋታዉ ሌላ ነዉ፡፡

  ያም ቢሆን የነ የሃገረ ስበከት ቡድን እኮ “አጣሪ” ሆኖ ሲመጣ ሌላ የጉቦ መስመር ተከፈተ ማለት ነዉ፡፡ እና መሰረታዊ ለዉጥ ካልመጣ እንዲሁ ስንባላ ለነፍስም ለስጋም ሳንሆን መጠራት ይመጣል፡፡ ያኔ ፍትሃዊ ዳኛ መልሱን ይሰጠዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱም ሰዎች ቢሆኑም እኮ ምን ያህል ገንዘብ … እያሉ በገንዘብ ከሚቀልዱ በደሙ ለዋጃት ቤተክርስቲያን ምንያህል ክርስቲያን ብለዉ ቢቆጥሩኮ ይህ የዋህ ክርስቲያን በቁጥሩ ልክ ገንዘብ በሰጠ ነበር፡፡ ግን ግን ይህ ሁሉ በዚህ ዘመን ሊሆን ግድኮነዉ፡፡ ስለዚህ የዚህ ሁሉ ምንጭ ወቅታዊ አፋጣኝ ምላሽ ካልተሰጠ ችግሩ ወደ ሌላ ይሄዳል፡፡ሆነ ተብሎ የሚሰራ ጉዳይነዉና ሕዝብ ይዳኝ፡፡

  ስለዚህ፡-
  1. ሕዝበ ክርስቲያኑ ህገወጥ ድርጊት የፈፀሙት (ጉቦኞች) ከቤተ ክርስቲያን እስኪሰናበቱ ምንም አይነት የገንዘብ ልገሳ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንዳያደርጉ ማስተባበር፤
  2. ማንኛዉም ሕዝበ ክርስቲያን የአጥቢያዉን የአስተዳደር ሰበካ ጉባኤ/አስተዳዳሪ ሁኔታ በጥልቀት መከታተል፤
  3. የቤተክህነት ሃላፊ ተብዬዎች ይህንን በህዝብ እንባ የገባ የስለት ብር በጉቦ መልክ እየተቀበላቸሁ ፍርደ ገምድል የምትሰጡ ዋዋዋ….. ደግሞ ይመስላችሁዋል እንጂ አትበሉትም ያዉ ወይ በመድሃኒት ያልቃል ወይ ለሳጥን መግዢያ ነዉ የሚሆነዉ፡፡
  4. ከምንም ነገር በላይ አብዝታቸህ ፀልዩ ….. ፀልዩ……ፀልዩ ጊዜዉ ከመቼዉም በላይ የከፋ ነዉና፤

  ሁሌ ልቤ እየደማ በዉስጡ ከሚቃጠለዉ ምእመን፡፡

  • ታዛቢው June 26, 2015 at 12:27 pm Reply

   @Libe dema ‹‹የእብድ ገላጋይ›› አንሁን!

   የካቶሊክ መነኩሴ አይተህ ከሆነ እንዳለ ላንድሮቨር አሽከርካሪ ነው፡፡ሼኮችም ጉንጫሞች ናቸው፡፡የፕሮቴስታንት ፓስተሮች በየቀኑ አዳራሻቸውን እየሸነሸኑና ቅርንጫፍ እየከፈቱ ሚሊኒየር ከመሆናቸውም በላይ ዛሬ ፉክክራቸው ከናይጄሪያዎቹ ባለ የግል አውሮፕላን ፓስተሮች ጋር ሆኗል፡፡የሕዝቡን ገንዘብ በትንቢትና ልሳን ሥም ዐይን አስጨፍነው መዝረፍ አልበቃቸው ብሎ በሕጋዊ ጋብቻ የታሰሩ ወይዛዝርትን ማማገጥን ስራየ ብለው ከያዙት ቆዩ፡፡

   በኛ ቤት ሙስናውና ብልሹ አሰራሩ እግር እየተከለ መሆኑ አይካድም፡፡ቢሆንም በእኛ ቤት በአንድ አ/አበባ አጥቢያ ስር ደሞዝ ተከፋዩ አገልጋይ በአማካይ ከመቶ በላይ ሲሆን ዘረፋው የሚካሄደው ለዚህ አገልጋይ ከሚከፈለው ደሞዝ የተረፈውንና በልማት ወጭ ከሚደረጉ ግዥዎች በመቀነጫጨብ ነው፡፡ይሕም የፕሮቴስታንቱ ፓስተር ሙሉውን ሙዳየ-ምጽዋት ገልብጦ ቦርጩን እንደሚያሳብጥበት አይነት አይደለም፡፡በአንጻራዊነት የእኛ አደረጃጀት ተጠያቂትና ኃላፊነት ያለበት ነው፡፡ጨርሶ ተስፋ ማስቆረጥም ደግ አይደለም!

   ስለሆነም እንደተባለው አሰራርን ማዘመን፣ቁጥጥርን ማጥበቅ እንጅ ‹‹የመባዕ እጃችሁን ሰብስቡ›› ብሎ ምክር ደግ አይደለም፡፡መብዐው ሲጀመር ለጥቂት ከምግባር የወጡ ሰዎች ሲባል ሳይሆን ለእግዚአብሔር ተብሎ ነው የሚቀርበው፡፡ቢቋረጥም የሚጎዳው ተራው ደሃ ካሕን እንጅ እነ አጅሬማ የሰበሰቡትን እያወጡ ይበላሉ፡፡አንሳሳት! ‹‹የእብድ ገላጋይ›› አንሁን!እንደሌሎቹ በፈረንጅ እርዳታ ሳይሆን በገዛ ምዕመኖቿ የቆመችን ቤ/ክ <> ብሎ ማወጅ እጅግ ሰቅጣጭና ኃላፊነት የጎደለው አነጋገር ነው!ይታረም!የልብን መድማት ለመከላከል መፍትሄው ይሄ አይደለም፡፡ይሄ የሰነፍ ተግባር ነው!

   እኛ ራሳችን ዘወትር ስለ ንብረትና ገንዘብ ምዝበራ ብቻ እያወራን አለቆችን ስለገንዘብ እንጅ ስለጠፋው ምዕመን የማይጨነቁ ብሎ መክሰስ በራሱ ራስን መቃረን ነው፡፡እስኪ እኛም ሁልጊዜ የተወሰኑ ሰዎችን ገበና ከማዝራት ስለሌሎች አንገብጋቢ የቤ/ክ ጉዳዮች፣መሆን ስላለበት አሰራር፣ሊዘረጋ ስለሚገባው ለቤ/ክ ራስ ማስቻያ ልማት፣የራቁ ምዕመናንን ማቅረቢያ ዘዴ እንወያይ!እንጅ የእብድ ገላጋይ አንሁን!ድንጋይ አናቀብል!ኳስ በመሬት!እርጋታ-ወ- ጥንቃቄ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: