ሰበር ዜና – በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የተመሩ አለቆች: ‹‹ወጣቶቹን ሰብስባችኹ እሰሩልን›› ሲሉ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርን ጠየቁ፤ ‹‹መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ››/ሚኒስቴሩ/

State Minister Ato Mulugeta Wuletaw and Minister Dr Shiferaw

በሥራ አስኪያጁ ፍላጎት ብቻ የተመረጡትንና የተመሩትን ኻያ አምስት ያህል አለቆች የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም እና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉጌታ ውለታው አነጋግረዋቸዋል

 • ወደ ሚኒስቴሩ ካመሩት 25 አለቆች 20 ያኽሎቹ በዋና ሥራ አስኪያጁ በተደረገባቸው ጫና ያለፍላጎታቸው እንዲሔዱ መገደዳቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
 • በየሰንበት ት/ቤቶቹ የዕቅበተ እምነት፣ የመልካም አስተዳደር እና የፍትሕ መነሣሣት ማኅበረ ቅዱሳንን ወንጅለዋል፤ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ልብሱን ለውጦ የመጣበት ነው›› /ኃይሌ ኣብርሃ/
 • ‹‹እንዴት አድርገን መከላከል እንዳለብን አሠልጥኑን እንጂ ስለ ሰላም መወያየት ምን ያደርግልናል?›› /የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ/
 • ሌላው ተናጋሪ፣ የሚነዷቸውን ውድ መኪኖች የሚሰጧቸው የነፍስ ልጆቻቸው መኾናቸውን ሲናገሩ ሌሎች አለቆች በእግራቸው ወለሉን እየተመተሙ ስለተቃወሟቸው አቋርጠዋል፡፡
 • ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ሕጋዊ ዕውቅና ያለው ማኅበር ነው፤ ማኅበር እያላችኹ በጅምላ መወንጀል አትችሉም፤ ሰው እሰሩ የምትሉት ጀግና መፍጠር ነው፤ ይልቁንስ መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ፤ ለምትመሯቸውም ምሳሌ ኹኑ፡፡›› /ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም/

 *           *           *

 • በቀጣዮቹ የኹለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሚኒስቴሩ በዘመናዊ አሠራር፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰላም ጉዳዮች ላይ የቤተ ክርስቲያንን የተለያዩ አካላት እንደሚያወያይ ተጠቁሟል፤ ለውይይቱ ‹‹ዘመናዊ አሠራር፣ ዴሞክራሲያዊነት እና ብዝኃነት›› የሚል የመወያያ ጽሑፍ መሰራጨቱ ተጠቁሟል፡፡
 • ሚኒስቴሩ: በእነ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ኹኔታዎች የሚመቻችላቸውን አማሳኝ አለቆች እና አድባርዮችን ብቻ ሳይኾን በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የወሳኝነት እና የተሳትፎ ድርሻ ያላቸውን ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮችንም ቀርቦ ያነጋግር!!!

ምንጭ፡- አዲስ አድማስ፤ ቅዳሜ ሰኔ ፲፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.
ሙሉ ዘገባውን ይከታተሉ

*          *         *

 • የሃይማኖት ተቋማት የሰው ኃይል አስተዳደር እና የፋይናንስ አሠራር ሥርዐታቸው፤ ለተከታዩ ሕዝብ ያላቸው ግልጸኝነት እና የተጠያቂነት ጉድለት ለኪራይ ሰብሳቢነት ከፍተኛ ተጋላጭነት እየፈጠረ የሚገኝ ጉዳይ ነው፡፡
 • ብልሹ አሠራሮች የሚፈጥሩት የተከማቸ ቅሬታ ተቋማቱ በተከታዩ ሕዝብ ዘንድ እምነት እንዲያጡ እና ከተለያዩ ጫፎች በመነሣት እንዲወገዙ ምክንያት ይኾናሉ፡፡
 • የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ተከታዮች የሚተቹበት እና አስተያየት የሚሰጡበት መንገድ፤ የሃይማኖቶቹ የልማት ሥራም ይኹን ሌላ ለተከታዩ ቀርቦ ግልጽ ውይይት የሚደረግበት የግልጸኝነት እና የተጠያቂነት አሠራር የሚባል ጉዳይ የተተከለ አይደለም፡፡

/ከሚኒስቴሩ የሥልጠና ሰነዶች/

Advertisements

3 thoughts on “ሰበር ዜና – በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የተመሩ አለቆች: ‹‹ወጣቶቹን ሰብስባችኹ እሰሩልን›› ሲሉ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርን ጠየቁ፤ ‹‹መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ››/ሚኒስቴሩ/

 1. matiyas June 20, 2015 at 12:27 pm Reply

  Ere yemigrim new!

 2. ኀይለገብርኤል June 20, 2015 at 3:10 pm Reply

  ግራ የገባው ነገር እኮ ሆነ ፣ይቺ ቤተክርስቲያን በማንም ወንበዴ መመራቷ የሚያቆመው መቼ ይሆን?
  እግዚአብሔር መልካሙን ግዜ ያመጣልን።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: