የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እና ኤልያስ ተጫነ: በሥልጠና ስም፣ የመዋቅርና የአሠራር መመሪያዎችን ባጠኑ ባለሞያዎችና በየሰንበት ት/ቤቶች ላይ የጥላቻ ቅስቀሳ እያካሔዱ ነው

 • በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መመሪያ የመዋቅር፣ የአደረጃጀትና የአሠራር ጥናቶችንና መመሪያዎችን ያዘጋጁ የበጎ ፈቃድ ባለሞያዎችን ‹‹በማያገባቸው የገቡ ደንቆሮዎች›› ብለዋቸዋል
 • መንግሥት ብድር እየሰጠ በጥቃቅን እና አነስተኛ በማኅበር ተደራጁ ሲል ኮብልስቶን ከመሥራት ይልቅ ‹‹ከአፋችን ሙዳይ ምጽዋቱን ሊነጥቁ እና ሊቆጣጠሩ የሚፈልጉ ናቸው›› ሲሉ የሰንበት ት/ቤቶቹን ዘልፈዋቸዋል
 • ዘመናዊ የፋይናንስ አያያዝና የባንክ አጠቃቀም፤ የሰብአዊ መብቶች አያያዝና ቤተ ክርስቲያን በፀረ ሙስና ትግል ያላት ሚና፤ ቤተ ክርስቲያንና መልካም አስተዳደር በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጥቷል
 • ያለበቂ ዝግጅት የተካሔደውና ሓሳብን ለማንሸራሸር የሚያስችል በቂ ማብራሪያ አልተሰጠበት የተባለው ሥልጠናው፣ ንጹሐንን በማሸማቀቅ ቲፎዞ ለማብዛት ያለመ እና ከወሬ ያላለፈ በሚል በተሳታፊዎች ተተችቷል
 • የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርትንና ቁጥጥሮችን በማግለል ከአራት መቶ ያላነሱ አለቆች፣ ጸሐፊዎች እና ሒሳብ ሹሞች፤ የክፍላተ ከተማ ሥራ አስኪያጆች እና የአስተዳደር ሓላፊዎች፤ የሀገረ ስብከቱ የዋና እና የክፍል ሓላፊዎች የተሳተፉበትን ሥልጠና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብር 157‚000 ስፖንሰር አድር ጎታል
 • የሥልጠናው የለብ ለብ ዝግጅት እና ከቁም ነገሩ ይልቅ በዋና ሥራ አስኪያጁ ዲስኩር፣ ፉከራ እና ውግዘት መርሐ ግብሩ መገባደዱ ገንዘቡ መመዝበሩን ያመላክታል ተብሏል

Lique Maemeran Yemane ZeMenfes Kidusዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፡-

ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም. ውሳኔው፣ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እስከ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ድረስ እንዲሠራበት ይኹንታ እና የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበት የመዋቅር የአደረጃጀት እና የአሠራር ጥናት ወደ ታች ወርዶ በማኅበረ ካህናት፣ በማኅበረ ምእመናን እና በየሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች በውይይት ዳብሮ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲቀርብ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

የመዋቅር የአደረጃጀት እና የአሠራር ጥናቱ፣ ከ96 በመቶ በላይ የማኅበረ ካህናት፣ የማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶችን ድጋፍ ባረጋገጠበት የኹለት ቀናት ውይይት፣ የዛሬው የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተሳተፉት በመጀመሪያው ግማሽ ቀን ብቻ እንደነበር በወቅቱ የተያዘው የመከታተያ ቅጽ ያስረዳል፡፡

ዛሬ በአንድ በኩል፣ የበጎ ፈቃድ ባለሞያዎቹ በብዙ ድካም እና በትሩፋት የሠሯቸውን የጥናቱን ክፍሎች እየወሰዱ የተቋማዊ ለውጥ ጀማሪ እና አብነት መስለው ሲመጻደቁበት በሌላ በኩል ደግሞ ባለሞያዎቹን ‹‹በማያገባቸው የገቡ ደንቆሮዎች›› እያሉ ሲዘልፏቸው ተሰምተዋል፡፡ ለሥልጠና በተጠራው መርሐ ግብር÷ ‹‹ምንድን ነው ነገሩ? ሐሳብ ለማንሸራሸር የሚያስችል በቂ ማብራሪያ አልተሰጠንም፤ ስለምትሠሩት ሥራ ምን ግልጽ ራእይ አላችኹ፤ ግልጽ የኾነ ምን ዕቅድ አላችኹ፤ እንዲኽ ኾነ እንዲኽ ተባለ እያላችኹ ከምታባብሉን ይህን ልንሠራ ዐቅደናል ብላችኹ ንገሩን፤ አለዚያ ከወሬ ያለፈ ትርጉም አይኖረውም፤›› የሚል የተሳታፊዎች አስተያየት ቢሰነዘርም ሰሚ ጆሮ አላገኘም፡፡

የተማረ ከሚባል ሰው በማይጠበቅና የተስፋ መቁረጥ ነው በተባለው የትላንቱ የፉከራና የውግዘት መድረክም በቤተ ክርስቲያን ጥሪ ተደርጎላቸው በበጎ ፈቃድ መመሪያውን ያጠኑ ባለሞያዎችን እንዲኹም ለዕቅበተ እምነት፣ ለመልካም አስተዳደር እና ለፍትሕ መስፈን በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ የሰንበት ት/ቤቶችን በጥላቻ ቅስቀሳዎች ሲያኳስሱ እና ሲያሳንሱ ውለዋል፡፡ እንዲኽ እያሉ…

 • ከዚኽ በፊት እናሠለጥናችኋለን ብለው የመጡ ሰዎች እናውቅላችኋለን ብለው ነበር የመጡት፤ ባለፉት ጊዜያት እኔ ታች ኾኜ ሥልጠና ሲደረግ አንዱ ማስተርስ ዲግሪ አለኝ፤ ከበቂ በላይ ዝግጅት አለኝ ብሎኛል፡፡ ይኼ ስድብ አለበት፤ ምን ማለት መሰላችኹ… እናንተ አትመጥኑኝም፤ ከእናንተ በላይ ነው ዕውቀቴ ማለት ነው፡፡ እንዲኽ ዐይነት ሰዎች ደንቆሮዎች ናቸው፡፡
 • ደብል ኢንትሪ በማለት ግራ ሲያጋቡን ነበር፤ እኛ ደብል ኢንትሪ ስለምንጠቀም ኦዲት አንደረግም ሲሉ ነበር፤ እኛ ባለዲግሪዎች ባለማስትሬቶች ነን ሲሉን አልነበር፤ እኛ በራሳችን ተምረን ልናስደምማቸው ይገባል፤ አኹን ሙሉ ብቁ ሰዎች አግኝተናል፤ እነርሱ ሲያሠለጥኑን አልገባንም ነበር፤ እኔ ራሴ ቁጭ ብዬ የተማርኩባት ቦታ ትታየኛለች፤ አኹን ግን በእኛው እየሠለጠንን ስለኾነ እየገባን ነው፡፡
 • ሒሳብ ሹሞቻችንና የተማሩትን የቤተ ክርስቲያንን ልጆች ከሥራ አፈናቅለው በእነርሱ ቦታ ሊተኩ ነበር፤ እንቀይራለን ብለው ነበር እነርሱ ያሰቡት፤ እኛ ደግሞ በምንም ተኣምር አንቀይራችኹም፤ ይኼ አይደረግም፤ እናንተ ራሳችኹ ናችኹ የምትሠሩት፤ እኛ ግን በመተካት ሳይኾን በማብቃት ላይ የተመሠረተ ፖሊሲ ነው የምናራምደው፤ በቀጣይም ጊዜያት ላይ እንደዚኽ ያሉትን በማያገባቸው እየገቡ እናውቅላችኋለን የሚሉትን አያገባችኁም ልንላቸው ያስፈልጋል፤ እኛ በበቂ መንገድ ዕውቀቱ እና ሞያው ያለን ሰዎች ነን፡፡
 • በአድማ አለቃ አይነሣም፤ ራሳችኹን አስከብሩ፤ ራሳችኹን አስንቃችኹ ከተባረራችኹ ምን እናድርግ፤ ቢሮ የሚያሽጉትን አንታገሥም፤ ጎበዞቹ በራቸውንና ቢሯቸውን ዘግተው እየጠበቁ ነው፤ ተከላክለዋል፤ ሰነፎቹ ደግሞ እያሳሻጉ እየመጡ ምን እንኹን ይሉናል እኛ ፖሊስ የለንም፤ ካህናት ናቸው ያሉን፤ ልትታገሏቸው ይገባል፤ እንደዚኽ ዐይነት ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ሊወገዱ ይገባል፤ አያገባችኹም በሏቸው፤ ለቤተ ክርሰቲያኒቷ እኛ ነን ልንቆምላትና ልንደርስላት የሚገባው፡፡

Lique Tebebit Elias Techaneየበጀት እና ፋይናንስ ዋና ክፍል ሓላፊ ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ (የሀገረ ስብከቱን የመዋቅር የአደረጃጀት እና የአሠራር ጥናት ውይይት በወቅቱ ባያጠናቅቁም አሞግሰዋል፤ ‹‹ማንም የፈለገውን ይበል፤ ጊዜው የኛ ነው›› ባሉበት የትላንት ንግግራቸው ደግሞ እጃቸው ክፉኛ እየተንቀጠቀጠ የሚከተለውን ተናግረዋል)፡-

 • እናሠለጥናኋለን ብለው መጡ፤ አሰይጥነውን ሔዱ፤ ሊያሠለጥኑን ሳይኾን ሊያሰየጥኑን ነው የመጡት፤ እኛ ብቻ እናሠልጥናችኹ የሚሉትን እነዚኽን ነው የማንፈልገው፤ እንደዚኽ ዓይነት ሰዎችን ነገም ተነገ ወዲያውም አንፈልግም፤ በምንም ዐይነት ተኣምር! … እኛ የተቸገርነው ባንክ ሔደን መብራት የለም በሚለው ሳይኾን የባንክ ሒሳብ አንፈርምም በሚሉት ነው፤ እኛ የተቸገርነው መቀየር ባለመቻላችን እኛ እንቀይራችኹ የሚሉ መጥተዋል፤ ኹሉን ነገር ወስደው ይህች ሙዳይ ምጽዋት ነው የቀረችን፤ ማንም ምንም የፈለገውን ይበል፤ አኹን ጊዜው የኛው ነው፤ ማኅበር ምን አገባው፡፡
Advertisements

10 thoughts on “የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እና ኤልያስ ተጫነ: በሥልጠና ስም፣ የመዋቅርና የአሠራር መመሪያዎችን ባጠኑ ባለሞያዎችና በየሰንበት ት/ቤቶች ላይ የጥላቻ ቅስቀሳ እያካሔዱ ነው

 1. Anonymous June 18, 2015 at 7:38 am Reply

  hodam

 2. haratewahido June 18, 2015 at 8:06 am Reply

  Reblogged this on ሐራ ዘተዋሕዶ.

 3. ታዛቢው June 18, 2015 at 10:02 am Reply

  1 የሀ/ስብከቱን ሹማምንት መኃይምናን እንዳትሏቸው 2ቱም ባለማስተርሶች ሆነው ተገኙ፡፡መንፈሳዊ እውቀት የላቸውም እንዳይባል ምክትሉ ወዲህ የ2 ጉባኤ ባለቤት፣እንደገና ወዲህ በቴዎሎጅ ማስተርሱን የያዘ፣እንደገና ወዲህ መቐለ አባ ሰላማ ፍሬምናጦስ ኮሌጅ ውስጥ ወንበር ዘርግቶ ብሉያትን ያንበለበለ ነበልባል–ያውም 2 ስለት ያለው የተሳለ ሾተል፡፡የየማነ ማስተርሶችና 17 አመታት ልምድም እንዲህ እንደዋዛ ሊታይና የአቅም ጥያቄ እንዲነሳበት በር ሊከፍት አይችልም!!

  2 በአሰራር እንዳትወቅሷቸው በግፍ የምንዱባን ካሕናትን ጉረሮ እየዘጉና ለፍ/ቤት ጠበቃ ሳይቀር ፈሰስ እያደረጉ ሲያሳድዱና ሲያፈናቅሉ የነበሩ አለቆችን በጥብቅ ደብዳቤ እያስጨነቁ ግፉዐኑን ወደ ስራቸው በመመለስ ባጭር ጊዜ ካሕኑ ልብ ውስጥ ተጎዘጎዙ፡፡እርግጥ የእነሱ ሀ/ስብከቱን ተደራጅቶ መጠርነፍ ዘረኝነት ሳይሆን የጽድቅ ስራ እንደሆነ የሚያስመስሉ ሰዎች የተወለዱበት አካባቢ በእንደነሱ ዐይነት ኢ-ሥነምግባራዊ ሰብእና ይወከል ይመስል ዘመቻ ተከፈተብን ብለው ጥቂት የዋሐን ካሕናትን በተለይ ደግሞ አለቆችን ለማነሳሳት ሞክረው እርስ በርስ በተፈጠረ የአካሄድ ልዩነት አድማቸው ከጓዳቸው ሳይወጣ መክሸፉን ታዝበናል፡፡

  3 የፐርሰንት ክፍያን በሚመለከት ሊቀ አእላፍ በላይ ምርጥ ስራ ሰርተው ነው የወረዱት፡፡ስኬታማ ነበሩ፡፡ለሊቀ አእላፍ የሚገባቸውን ምስጋና አናጓድልባቸውም!!እነ የማነም አድባራቱንና ገዳማቱን በፐርሰንት ጉዳይ ድርድር እንደሌለ በጥብቅ እያስታወቁ ነው፡፡ስለዚህ ከሊቀ አእላፍ የተሻለ እንጅ ያነሰ ሪከርድ ያስመዘግባሉ ብለን አንገምትም፡፡

  4 የካሽ ሬጅስተርና ሙዳየ-ምጽዋት በባንክ ማስቆጠሩን በሚመለከት እነ የማነ እናንተ ከምታንቆለጳጵሱት የአጥኚ ኮሚቴም ሆነ ከራሳቸው ያመንጩት ዋናው መተግበሩ ነው፡፡እስኪ ለዚች ጅምራቸው እንኳ አጨብጭቡላቸው!! ‹‹የኛ ጥናት በኛ ሰው ካልተተገበረ›› ካላችሁ ደግሞ እ/ሄር መንበሩን እስከፈቅድላችሁ ጠብቁ!!እስከዚያው ግን እናንተ በኩራት ስትጠቅሱት የነበረውን ጥቅስ እንዋስ ‹‹…የስልጠናው ሰነድ ወድቆም ይገኝ፣መሐመድም ያጥናው፣እስከጠቀመን ድረስ ተግባራዊ እናደርገዋለን›› አራት ነጥብ!!እናንተም ሰራችሁት ተግባራዊ እናደርገዋለን.. እንደገና አራት ነጥብ፡፡እንዲህ አይነት እውቀት ማፍለቅ የሚችለው የኛ ማስተር ብቻ ነው ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ ግን ከእእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት ቢያሻችሁ ፓተንት፣ቢያሻችሁ ኮፒ ራይት ጠይቁበት!!

  5 በነገራችን ላይ በ96 ከመቶ ካሕናት ተደግፏል የምትሉት ጥናት ሲጠና ለክፉም ለደጉም ከካሕናትና ከአስተዳደር ሰራተኞች በአጥኚው ክፍል አለመካተቱ እና በጥቅምት 2007 ዓ.ም የፀደቀውን ሕገ-ቤተክርስቲያን ቀድሞ የበታች ሊሰኝ የሚችለው የእናነተ ጥናት መምጣቱ ልክ እንዳልሆነ በመግለጽ ቅሬታ በብዙ ሲቀርብ የምትሰጡት መልስ የተለመደው ፍረጃና ንቀት ነበር፡፡እ/ሔር ግን ያን የተናቀ ድምጽ እየሰማ ነበር፡፡ይሄው ዛሬ ከሳሽና ተከሳሽ ቦታ ሲለዋወጡ አየን፡፡‹‹ጋርቤጅ ውደቁ›› የሚሉ ያልተገሩ ልሳናት የነበሩበት መድረክ ዛሬ ለተሳዳጂዎቹ ሆነ፡፡ዛሬ ያሉት መድረኩን ለእልህና አሉባልታ ነዛብን በሚሉት ላይ ሁሉ የሰይፍ በቀል ማቀባበያ ካደረጉት ደግሞ የድንግል ልጅ መንበሩን እንደገና ይነሳቸዋል፡፡

  6 ክቡራን አኃው፡- የማነ፣አእመረ፣ኤልያስ፣ታጋይ፣ብርሃኑ/ጌጡ፣አባ ኅሩይ፣ወልደ ሰንበት እና ሌሎችም ስማችሁንና መዐርጋችሁን ያልጠራነው!! በመንፈሳዊና ዘመናዊ ትምህርታችሁ፣በእድሜ ትኩስነታችሁ፣በርትእት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖታችሁ፣እስካሁን ባለው የ2 ወራት አስተዳደራችሁ ቅር አላለንም፡፡በውጥናችሁ ደስተኛ ነን፡፡ነገር ግን የኢኦተቤክ ልትከተለው በሚገባት ዘመኑን የዋጀ አስተዳደር ረገድ ወደ ኋላ መቅረቷን አናለባብሰው፡፡እናንተም እንደምትሉን ስር የሰደደ የፋይናንስና የአስተዳደር ጉድለት አለ፡፡ይሄ ችግር በእናንተ መልካም ፈቃድ ብቻ ይቀረፋል ብለን አናምንም፡፡ነገር ግን መንገድ መሪ፤ፋና ወጊ ሁኑን፡፡ይሕን የመሰለ በዘመናዊና በመንፈሳዊ እውቀት የበለጸገ አመራር ተጨባጭ እርምጃ ካላሳየ ‹‹ለካ እውቀት የችግር መድኃኒት አይሆንም››–እውቀት በግለኛ ጥቅም ተሸነፈ ልንል ነው!!ስለዚህ መነሻ የሚሆኑ መፍትሔዎችን ከራሳችሁም፣በቡድንተኛነት ማጥ ካልዘቀጡ ከቅን አሳቢ የቤ/ክ ልጆችም፣ከዓለማዊ ምሑራንም፣ከሊቃውንትም፣ከማኅበረ-ካሕናት ወ ምዕመናንም እየወሰዳችሁ በቅዱስ አባታችንና በቋሚ ሲኖዶሱ ቡራኬ ቀጥታ ወደ ተግባር ግቡ፡፡በውሳኔያችሁና በተግባራችሁ መካከል ያለው ጊዜ ይጠር፡፡ተግብሩ!!

  የእኛ ቤት መንበር እንደሆነ ነባሪውና መጻኢው አይተነበይም!!የሚሻለው በየብሎጉና ፌስቡኩ ከመስመር በወጣ መልኩ ለሚሰነዙ አሉባልታዎች አጸፋ ለመስጠት ጊዜን ማጥፋ ሳይሆን ተገቢነት ያላቸወን ቅሬታዎች እየለዩ በእለት በእለት የሚከሰቱ የካሕናትንና የምዕመናንን ችግሮች ለመፍታት ስራ ተከፋፍሎ መትጋት፣ተቋሙ ተቋማዊ ቅርጽ እንዲይዝ መጣር፣በየአድባራት ገዳማቱ በሙዳየ-ምጽዋት ቆጠራ፣በቦታ ኪራይ፣በሱቅና ፉካ ግንባታና ኪራይ ያሉ ሐሜታዎችን የሚያስቀር ግልጽ መመሪያ ቢያንስ በሰርኩላር መልክ ማሰራጨት፣በተጓዳኝ ደግሞ ጅምር ልማቶች እንዲቀጥሉና አዳዲሶችም እንዲጀመሩ ጥብቅ መመሪያ መስጠትና ክትትል ማድረግ ከእናንተ የሚጠበቁ ስራዎች ናቸው፡፡

  7 ክቡራን አኃው!!በተረፈ የፌስቡክና ብሎግ ወጭ ወራጅ ሐሜታዎችን ‹‹አፍ ስለማይመከት›› ፍርዱን ለእግዚአብሄርና ለቅን አንባብያን ብትተውት መልካም ነው፡፡ ባይሆን ጫን እያለና መስመር እየዘለለ ሲመጣ እኛም ያቅማችንን እንመክትላችኋለን፡፡ ልክ ሰሞኑን ለዘመናት የተጠራቀመውን ብሶት በእናንተ አስተዳደር ላይ ደፍድፈው የአ/አበባን ሰ/ተማሪዎች እንደ ኪስ ቦርሳ ‹‹25 ሺሕውን አባላችንን እንመዛለን›› የሚሉ ከሕሊናቸው ልሳናቸው የፈጠነ አዛውንት ሰ/ተማሪዎች ላይ ምከታችንን እንዳቀረብነው፡፡ ለእናንተ ያለን ድጋፍ ያለፈ ሕይወታችሁ ከአደፍ-ጉድፍ የጸዳና የስኬት ብቻ ነው ብለን አምነን አይደለም፡፡‹‹ለዘኃለፈ እቅበት›› ብለን መሆኑን አስምሩበት!! አደራ!! ይቺ እንደ ሱራፊ ሰይፍ ተገለባባጭ የሆነች መንበር ስትገለባበጥ እንዳትፈጃችሁ ነገን እያሰባችሁ ዛሬን ትጉባት–ባለቤቱ እስከፈቀደ!!

  8 ቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስና እሳቸው የሚመሩት ቋሚ ሲኖዶስም የእኔን የትሑቱን ካሕን ድምጽ እንዲሰማኝ እግረ መስቀሉ ስር ወድቄ እንዲህ እላለሁ፡-አባታችን አቡነ ጳውሎስ ከፋም ለማም በየአመቱ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን እያስጀመሩ ለጊዜው አጥቢያዎችን በመዋጮ ቢያስጨንቁንም ፍጻሜያቸውን እያየን እናመሰግናቸው ነበር፡፡ አቡነ ማትያስ ከመጡ ወዲህ ግን በየአድባራቱና በየአህጉረ ስብከቱ ልማቱ ቢቀጥልም በማዕከላዊው ቤተ ክሕነት ደረጃ ልማት የተቀዛቀዘ ይመስላል፡፡ የተያዘው ፕሮጀክትም የደረሰበትን ደረጃም ማወቅ አልቻልንም፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ አንዲት ክብርት ተቋም የራሷ የተጠናከረ የሚዲያ ተቋም እንደሚኖራት ተስፋ ቢሰጠንም ተስፋው በገቢር አልታየም፡፡ በመሆኑም ይሕ ነው የሚባል ባለቤትና ኃላፊነት የሚወስድ አካል በሌላቸው ማኅበራዊ ሚዲያዎች ብቻ ለመታመን ተገደናል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳትና ቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ የልማቱን መፋዘዝና የሚዲያውን በእቅድ መቅረት አስቡበት እላለሁ–በታላቅ ትሕትና!!

  ታዛቢው ካሕን፡እምነ አሐቲ ደብር፡እምትዕይንተ-ጣይቱ፡እንተ ይዕቲ አዲስ አበባ!!

  • ኀይለገብርኤል June 18, 2015 at 3:42 pm Reply

   መናፍቅ አስመሳይ ነህ

  • ዳሞት June 18, 2015 at 4:06 pm Reply

   ለታዛቢው
   ብዙ ታወራለህ፤ ካህን ነኝ እያልክም እንደ ሌዋውያኑ ራስህን ታስተዋውቃለህ። ግን በመቅደሱ የሚሰራውን ርኩሰት፣ ግፍ፣ ዘረፋ፣ ሙስና፣ ትእቢትና እብሪት፣ ዘረኝነት፣ ኑፋቄ፣ ምግባር አልበኝነትና ተዘርዝረው ተነገረው የማያልቁ ግፎችና ስርዓት አልበኝነቶች እንደ አንድ የእምነት ስነምግባር ስታንቆለጳጵሳቸው ሥመለከት እውነትም ካህን ሌዋዊ ካህን አልኩኝ።

   ግለሰቦችን የካብክበት ካም አስገራሚ ነው። እንዲህም ብየ እንድጠይቅ አደረገኝ፦ ይህ ነው በካህኑ በዘካሪያስ የአገልግሎት ቤት ካህን ሆኖ የቆመውን? ብየ። አዎ ባለማስተር እና ባለሁለት ሰይፈ ነበልባል ናቸው እያልክ ሰማያዊውን አክሊል አያሰጥም እንጅ በሙገሳ ማማ ላይ የሰቀልካቸው። አይ ካህን! እውነት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርት የተማር ካህን ነህን? ለኔ ግን በጭራሽ!

   ታዛቢው፦ የትኛውም እውቀት እግዚአብሔርን መፍራት ከሌለበትና መልካም ነገር ካልሰሩበት ከንቱ ነው። የትኛውም መንፈሳዊ እውቀት በመንፈስ ቅዱስ ካልተቃኘና ትሕትና ከሌለው ብሎም በእምነት ካልፀኑበት ከንቱ ነው። እነ ንስጥሮስ እንዲሁም ለሐዋሪያነት ጌታ በናዝሬት ሳይጠራው በፊት ሳዖል የነበረው ቅዱስ ጳውሎስ የተማሩ አዋቂዎች ነበሩ። ግና በጊዜው ከክፋትና ሐጢያት ሌላ ምንም ፅድቅ አላደረጉም። ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ከሆነ በኋላ ስለነበረው እውቀት ሲናገር ስለ ህግ ብትጠይቁኝ ከገማልያ እግር ስር ቁጭ ብየ የተማርኩ ነኝ አያለ ስለ ነበረው እውቀት ተርሿል። ታዲያ አንተ እንትና ባለማስተርስ እንትና ባለሁለት መንፈሳዊ ማስተርስ እያልክ የምታመፃድቃቸው ለመልካም ሥራ ካልሆነና በሀይማኖት ካልተተገበር ምን ዋጋ አለው።

   ባለማስተርስ እያልክ የምታሞካሸው በዘሩ ከቤተክርስቲያኗ መዋቅርና ህግ ውጭ የተሾመ መሆኑን መዘንጋት የለብህም። በተጨማሪም በነ ገማልያ መንገድ የሚጓዝ ባለጠመንጃን መከታ የሚያደርግ መሆኑን እራሱ መሥክሯል። እንዲሁም የቤተክርስቲያን ህግና ስርዓት ይከበር፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይጠበቅ ይበር፤ የማይገባ ነውረኛ ንግግር የሚናገሩ አማሳኞችና ሙሰኛ ሌቦች ይታረሙ በህግ ይጠየቁ፤ ቅጥረኛና ለሆዳቸው ያደሩ የቤተክርስቲያኗን እምነት የካዱ መናፍቃን ላይ እርምጃ ይወሰድ ባሉት ቤተክርስቲያኗ ልጆን የሰንበት ተማሪዎችን ከመዘመርና አድርጉ የተባሉትን ብቻ እንጅ ሌላ አይመለከታችሁም ፣ ምእመናኑን ደግሞ ምንነታቸው የማይታወቀ ብሎ በእብሪት የዘለፈ አመፀኛ የእምነት ስነምግባር የጎደለው መሆኑን አሥመሥክሯል። ግን ለመሆኑ የሚዘርፈው ገንዘብ የሚሰድባቸው ገንዘብ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ብለው የሰጡትን መሆኑን ያውቅ ይሆን? መልሱ ለእሱና ለአንተ ለታዛቢው ይሁን።

   ታዛቢ። ሥለ ማንነትህም ውብ አድርገህ ነው የገለፅኸው። እኔ ትሁቱ ካህን አይደል ያልከው። ይገርማል የቤተ ክርስቲያኗ ድምፅ ያልሆነ በእግዚአብሔር ክህነት እንዲህ አይነት ተመፃዳቂነትና እራስን ማጽደቅ ሲሰማ። ነገ ደግሞ እኔ ሰማይ ተከፍታ የእግዚአብሔርን መንበር የተመለከትሁ ፍፁሙ ካህን ነኝ ላለማለት ምን
   ያግድሃል?
   ሌላው ብዙ ጊዜ ልማት ልማት ይባላል። ለማ በተባለውም የምትጠቀመው ቤተ ክርስቲያን ሳትሆን በዘር የተደራጁ አካላቶች ናቸው። ለቤተ ክርስቲያን ገቢ ማስገኛ የሚሆን ልማት መሠራቱ ተገቢ ቢሆንም በልማት ሰበብ ቤተ ክርስቲያን ሀብቷ ተዘርፎ እርቃኗን ከመቅረቷ በተጨማሪ የመናፍቃኑ መፈንጫና አስተምሮቷ ያልሆነ ሐሰተኛ ትምህርት በአውደ ምህረቷ እንዲተረክ መንገድ ከፍቷል። ይኸውም አንተ የምታሞግሳቸው አካላቶች ሀይማኖት እንድትቀናና ሥርዓት እንዲፀና ሳይሆን የሚሠሩት ዘረፋ፣ ስርዓት አልበኝነት፣ ሙሥና፣ ምንፍቅናና ሌሎች ህገወጥ ተግባሮች እንዲሰራፉ የሚሰሩ መሆኑ ነው። ለምሳሌ መናፍቅና ምንፍቅናን የሚያራምዱት አለቆች የተባሎ ምድረኞችን በጥቅም ሸብበው ይዙና ምንፍቅናቸውን እንደፈለጉ ያራምዳሉ። ይህን የሚያደርጉት በወንጀል የሚያስጠይቃቸውና ዘብጥያ የሚከታቸው ስለሆነ ጨው ካላሷቸው በጓላ ይህ ትምህርታችሁ ትክክል አይደለም ቢሏቸው በሌብነትና በሙስና እስጠይቃችጓለ ብለው ለማሥፈራራትና ትንፍሽ እንዳይሉ ለማድረግ ነው።

   ለሁሉም አቶ ታዛቢው ዘረኝነትም የተዘረፈው ሀብትም ምድራዊ ነው። ጊዜው የኛነው ምን ታመጣላችሁ እንዘርፍ እንወነብዳለን፤ ምንፍቅናንም እናራምዳለን እብሪት ፉከራው የዲያቢሎስ የዚህ አለም ገዠ እንጂ የሰማያዊው የእግዚአብሔር ቃልና ተግባር አይደለም። ስለዚህ ይህን ህይወት የማያሰጥ ቲፎዞነትህንና ከንቱ መታበይህን አሥወግድ።

   • Senait June 19, 2015 at 7:39 am

    Tebarek Damot….yihe Beaman Netsere letebalew zeregna ferisawi ewunetun negerkilign!!!

 4. An June 19, 2015 at 4:05 am Reply

  ብዙ ታወራለህ፤ ካህን ነኝ እያልክም እንደ ሌዋውያኑ ራስህን ታስተዋውቃለህ። ግን በመቅደሱ የሚሰራውን ርኩሰት፣ ግፍ፣ ዘረፋ፣ ሙስና፣ ትእቢትና እብሪት፣ ዘረኝነት፣ ኑፋቄ፣ ምግባር አልበኝነትና ተዘርዝረው ተነገረው የማያልቁ ግፎችና ስርዓት አልበኝነቶች እንደ አንድ የእምነት ስነምግባር ስታንቆለጳጵሳቸው ሥመለከት እውነትም ካህን ሌዋዊ ካህን አልኩኝ።

  ግለሰቦችን የካብክበት ካም አስገራሚ ነው። እንዲህም ብየ እንድጠይቅ አደረገኝ፦ ይህ ነው በካህኑ በዘካሪያስ የአገልግሎት ቤት ካህን ሆኖ የቆመውን? ብየ። አዎ ባለማስተር እና ባለሁለት ሰይፈ ነበልባል ናቸው እያልክ ሰማያዊውን አክሊል አያሰጥም እንጅ በሙገሳ ማማ ላይ የሰቀልካቸው። አይ ካህን! እውነት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርት የተማር ካህን ነህን? ለኔ ግን በጭራሽ!

  ታዛቢው፦ የትኛውም እውቀት እግዚአብሔርን መፍራት ከሌለበትና መልካም ነገር ካልሰሩበት ከንቱ ነው። የትኛውም መንፈሳዊ እውቀት በመንፈስ ቅዱስ ካልተቃኘና ትሕትና ከሌለው ብሎም በእምነት ካልፀኑበት ከንቱ ነው። እነ ንስጥሮስ እንዲሁም ለሐዋሪያነት ጌታ በናዝሬት ሳይጠራው በፊት ሳዖል የነበረው ቅዱስ ጳውሎስ የተማሩ አዋቂዎች ነበሩ። ግና በጊዜው ከክፋትና ሐጢያት ሌላ ምንም ፅድቅ አላደረጉም። ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ከሆነ በኋላ ስለነበረው እውቀት ሲናገር ስለ ህግ ብትጠይቁኝ ከገማልያ እግር ስር ቁጭ ብየ የተማርኩ ነኝ አያለ ስለ ነበረው እውቀት ተርሿል። ታዲያ አንተ እንትና ባለማስተርስ እንትና ባለሁለት መንፈሳዊ ማስተርስ እያልክ የምታመፃድቃቸው ለመልካም ሥራ ካልሆነና በሀይማኖት ካልተተገበር ምን ዋጋ አለው።

  ባለማስተርስ እያልክ የምታሞካሸው በዘሩ ከቤተክርስቲያኗ መዋቅርና ህግ ውጭ የተሾመ መሆኑን መዘንጋት የለብህም። በተጨማሪም በነ ገማልያ መንገድ የሚጓዝ ባለጠመንጃን መከታ የሚያደርግ መሆኑን እራሱ መሥክሯል። እንዲሁም የቤተክርስቲያን ህግና ስርዓት ይከበር፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይጠበቅ ይበር፤ የማይገባ ነውረኛ ንግግር የሚናገሩ አማሳኞችና ሙሰኛ ሌቦች ይታረሙ በህግ ይጠየቁ፤ ቅጥረኛና ለሆዳቸው ያደሩ የቤተክርስቲያኗን እምነት የካዱ መናፍቃን ላይ እርምጃ ይወሰድ ባሉት ቤተክርስቲያኗ ልጆን የሰንበት ተማሪዎችን ከመዘመርና አድርጉ የተባሉትን ብቻ እንጅ ሌላ አይመለከታችሁም ፣ ምእመናኑን ደግሞ ምንነታቸው የማይታወቀ ብሎ በእብሪት የዘለፈ አመፀኛ የእምነት ስነምግባር የጎደለው መሆኑን አሥመሥክሯል። ግን ለመሆኑ የሚዘርፈው ገንዘብ የሚሰድባቸው ገንዘብ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ብለው የሰጡትን መሆኑን ያውቅ ይሆን? መልሱ ለእሱና ለአንተ ለታዛቢው ይሁን።

  ታዛቢ። ሥለ ማንነትህም ውብ አድርገህ ነው የገለፅኸው። እኔ ትሁቱ ካህን አይደል ያልከው። ይገርማል የቤተ ክርስቲያኗ ድምፅ ያልሆነ በእግዚአብሔር ክህነት እንዲህ አይነት ተመፃዳቂነትና እራስን ማጽደቅ ሲሰማ። ነገ ደግሞ እኔ ሰማይ ተከፍታ የእግዚአብሔርን መንበር የተመለከትሁ ፍፁሙ ካህን ነኝ ላለማለት ምን
  ያግድሃል?
  ሌላው ብዙ ጊዜ ልማት ልማት ይባላል። ለማ በተባለውም የምትጠቀመው ቤተ ክርስቲያን ሳትሆን በዘር የተደራጁ አካላቶች ናቸው። ለቤተ ክርስቲያን ገቢ ማስገኛ የሚሆን ልማት መሠራቱ ተገቢ ቢሆንም በልማት ሰበብ ቤተ ክርስቲያን ሀብቷ ተዘርፎ እርቃኗን ከመቅረቷ በተጨማሪ የመናፍቃኑ መፈንጫና አስተምሮቷ ያልሆነ ሐሰተኛ ትምህርት በአውደ ምህረቷ እንዲተረክ መንገድ ከፍቷል። ይኸውም አንተ የምታሞግሳቸው አካላቶች ሀይማኖት እንድትቀናና ሥርዓት እንዲፀና ሳይሆን የሚሠሩት ዘረፋ፣ ስርዓት አልበኝነት፣ ሙሥና፣ ምንፍቅናና ሌሎች ህገወጥ ተግባሮች እንዲሰራፉ የሚሰሩ መሆኑ ነው። ለምሳሌ መናፍቅና ምንፍቅናን የሚያራምዱት አለቆች የተባሎ ምድረኞችን በጥቅም ሸብበው ይዙና ምንፍቅናቸውን እንደፈለጉ ያራምዳሉ። ይህን የሚያደርጉት በወንጀል የሚያስጠይቃቸውና ዘብጥያ የሚከታቸው ስለሆነ ጨው ካላሷቸው በጓላ ይህ ትምህርታችሁ ትክክል አይደለም ቢሏቸው በሌብነትና በሙስና እስጠይቃችጓለ ብለው ለማሥፈራራትና ትንፍሽ እንዳይሉ ለማድረግ ነው።

  ለሁሉም አቶ ታዛቢው ዘረኝነትም የተዘረፈው ሀብትም ምድራዊ ነው። ጊዜው የኛነው ምን ታመጣላችሁ እንዘርፍ እንወነብዳለን፤ ምንፍቅናንም እናራምዳለን እብሪት ፉከራው የዲያቢሎስ የዚህ አለም ገዠ እንጂ የሰማያዊው የእግዚአብሔር ቃልና ተግባር አይደለም። ስለዚህ ይህን ህይወት የማያሰጥ ቲፎዞነትህንና ከንቱ መታበይህን አሥወግድ

 5. Andu June 19, 2015 at 8:53 am Reply

  ዛሬ ዛሬ ይህች መከራዋ የበዛ ቤተክርስቲያን ከዉጭ ካለዉ ችግር ይልቅ ዉስጣዊ ችግሮች ይበልጥ እየተፈታተናት ይገኛል፡፡ የጌታችንን ስለጣነ ክህነት ይዘዉ በመቅደሱ ግን እጅግ ዘግናኝ ስራ ሲሰሩ ለተመለከተ አማኒ፤ እንዴ ምነዉ ሃይማኖት ቀይሬ ምንም ብጥብጥም ሆነ ችግር ባላይስ የሚሉ በርካታ ናቸዉ እንዴ እግዚአብሔር በመንበሩ የለም እንዴ ፡፡ ጥቂት ካህን ተብዩዎች ምን ያህል ሙሰኞች እንደሆኑ ዛሬ ዛሬ በኣዲስ አበባ ከተማችን እጅግ የፈረጠሙ መነኮሳት ተብዬዎች በፉክክር የሚያሽከረክሩት ኮድ 2 የቤት አዉቶሞቢል ላየ እንዴ ወይ ዘመን ያስብላል የሚይዙት ዘመናዊ ሞባይሎች ልክ የፉክክር መድረክ ያሰመስላል፡፤ ዛሬ ዛሬ አንድ ካህን የደብር አለቃ ሆኖ ለመመደብ የሚከፍለዉ የጉቦ መጠን እሱ ባለቤቱ ነዉ የሚያዉቀዉ፡፡ ብቻ ገንዘብ ካለ …….. በምድር መንገድ አለ ….. የሚሰራዉ በዚሁ ቤተክህደት ዉስጥ ነዉ፡፡

  የሂሳቡን ነገርማ አይነሳ እንጂ ከተነሳማ ስንቱ የሂሳብ ሰራተኛ ተብዬ ነዉ በአግባቡ ወጪና ገቢዉን የሚያውቀው መሰረታዊ የሂሳብ ስሌትስ የሚያዉቀዉ፤ በኦዲት ግዜኮ ድርድሩ ምንያህል (ጉቦ) ታመጣላችሁ እንጂ ትክክል ነዉ አይደለም ሳይሆን ጨዋታዉ ሌላ ነዉ፡፡ ያም ቢሆን የነ የሃገረ ስበከት ቡድን እኮ “አጣሪ” ሆኖ ሲመጣ ሌላ የጉቦ መስመር ተከፈተ ማለት ነዉ፡፡ እና መሰረታዊ ለዉጥ ካልመጣ እንዲሁ ስንባላ ለነፍስም ለስጋም ሳንሆን መጠራት ይመጣል፡፡ ያኔ ፍትሃዊ ዳኛ መልሱን ይሰጠዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱም ሰዎች ቢሆኑም እኮ ምን ያህል ገንዘብ … እያሉ በገንዘብ ከሚቀልዱ በደሙ ለዋጃት ቤተክርስቲያን ምንያህል ክርስቲያን ብለዉ ቢቆጥሩኮ ይህ የዋህ ክርስቲያን በቁጥሩ ልክ ገንዘብ በሰጠ ነበር፡፡ ግንግን ይህ ሁሉ በዚህ ዘመን ሊሆን ግድኮነዉ፡፡ ስለዚህ የዚህ ሁሉ ምንጭ ወቅታዊ አፋጣኝ ምላሽ ካልተሰጠ ችግሩ ወደ ሌላ ይሄዳል፡፡ሆነ ተብሎ የሚሰራ ጉዳይነዉና ሕዝብ ያዳኝ፡፡
  ሁሌ ልቤ እየደማ በዉስጡ ከሚቃጠለዉ ምእመን፡፡

 6. Anonymous June 19, 2015 at 5:57 pm Reply

  In the name of the Father , the Son and Holy Sprit!

  I am an active member of Mahibre Menemenan in last 24years in one EOTC Debere in Eastern Addis Ababa and was following actively what is going in EOTC.

  In the first place, a christian does not have enemies although he might be in contradiction with individuals, association, political leaders what so ever who are ready astray by Satan the great liar! Hence, such problems will have solution only if you have patience, are polite to what ever people are against you and pray and fast so that our Lord and Our Saviour will bring solution according to His will!

  When we with this balance
  What Hara and similar blogs is pinpointing on persons is unholy and emotional. it seems like political fight than spiritual. This will not have possible result as the other side will will be agitated by satan for revenge! The same evil spirit that made you to act with emotions and pin point on individuals will succeed in creating long lasting enmity. Do not go ahead of God.

  When i look the other side, they claim to be supporter of Government and consider others as opposition! What a great lie! if such was true, how can the ruling party have land side victory in the election! It is a fact tat some political leaders might not have good option about EOTC as some might have protestant religion ( it is thier right unless they work to impose it on others ) and others consider her as conservative. Instead of standing against this sectarian point of view together, these people pin point on Mahibre Kidusan as the last fortress of conservatism in EOTC and work to destroy it and now the same is true in Sunady School students. How can you be considered as spiritual if you are not defending your faith and insualt others! First of all Mahibre Kidusan and Sunday Schools are forces change in EOTC that are recognized by mahibre menmenan. At least they contributes to decelerate zemecha filipos and Tehdiso conspiracy and spread of the Gospel among the youth, diasapora and nationalities living in borderlands, and contributing too Abnet schools. They have also waged struggle against corruption and modernization of administration. They can make errors, can be emotional and have to be corrected through proper EOTC channel.

  The voice of menemena has to be heard. You do not have to call us only to collect money! You do not have to create division in EOTC! As leadership you are expected to resolve conflicts and make peace with every one not to lead by emotion. You do not have to be defenders of corrupt and heretic individuals!.

  Let us break down this madness by forgiving each other as we all have sinned and create peace, create proper organs through which conflict shall be resolved (Mahibre Erek) and ask the corrupts and heretic individuals to repent!

  Amen

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: