የሰንበት ት/ቤቶች የፀረ ሙስና እና የፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ የሚስፋፋበት እና የሚጠናከርበት ስልት ተቀየሰ፤ አማሳኞች ‹‹የሰንበት ት/ቤቶች በዩኒፎርም ሰልፍ መውጣት እያስጠቃን ነው›› አሉ

aassd4

የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች ሊቃነ መናብርት በግምገማዊ ውይይት ላይ (ፎቶ ፋይል)

 • በሀ/ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተጠራ ጉባኤ፣ የአንድ ወር እንቅስቃሴውን ገምግሟል
 • ንቅናቄውን ከመሪ ዕቅዱ ቁልፍ ጉዳዮች ጋር አስተሳስሮ የሚመራ ራሱን የቻለ አካል ተቋቁሟል
 • ከማኅበረ ካህናት እና ምእመናን፣ የማኅበረሰብ ተቋማት እና የፀረ ሙስና አካላት ጋር ይሠራል
 • ዓላማውን ከቤተሰብ እስከ ኅብረተሰብ በማስተዋወቅ በስፋት ማነሣሣትና ማንቀሳቀስ ተግባሩ ነው
 • የዕቅበተ እምነት የመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ንቅናቄው በገዳማውያን አበው ጸሎት ይታገዛል

*        *        *

 • ከ160 በላይ የሀገረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ኹሉም አመራሮች በተገኙበት ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በተካሔደው የግማሽ ቀን ውይይት፣ የአንድነቱ አመራር ባቀረበው የአንድ ወር የእንቅስቃሴው ሪፖርት ላይ የተመሠረተ ግምገማ እና ቀጣይ ስልቶችን የቀየሰ ውይይት ተካሒዷል፡፡
 • የአንድነቱ አመራር በሀገር አቀፉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ስትራተጅያዊ ዕቅድ አፈጻጸሞች ላይ እንዲያተኩር የተወሰነ ሲኾን ለዕቅበተ እምነት፣ ለመልካም አስተዳደር እና ለፍትሕ መስፈን በንቅናቄ መልክ የተጀመረውን ተጋድሎ ከስትራተጅው ቁልፍ ጉዳዮች ጋር አስተሳስሮ የሚመራ እና ከሰባቱም የክፍላተ ከተማ አንድነት ጉባኤያት የተውጣጣ 35 አባላት ያሉበት አካል ተቋቁሟል፡፡
 • ለንቅናቄው በሚያስፈልጉ ሞያተኞች እና በካር አገልጋዮች የተሟላው ኮር አካል ከማኅበረ ካህናት፣ ከማኅበረ ምእመናን፣ እንደ ዕድር ካሉ የማኅበረሰብ እና እንደ ፀረ ሙስና እና ሥነ ምግባር ኮሚሽን ካሉ ተቋማት ጋር በቅርበት የሚሠራ ሲኾን የንቅናቄውን ዓላማዎች ከአባላት ወላጆች (ቤተሰብ) እስከ ኅብረተሰብ በማስተዋወቅ አገልጋዩንና ምእመኑን በስፋት ማንቀሳቀስ፤ አማሳኞችን እያጋለጡ ለፍርድ ማቅረብ እና መናፍቃንን እየመነጠሩ በቀኖናዊ ውሳኔ እንዲለዩ ማድረግ ዋነኛ ተግባሩ ነው፡፡
 • ‹‹ሰንበት ት/ቤቶች ለሚያነሷቸው በተለይም የአለቆች ይነሡልን ጥያቄ ምላሽ መስጠት መሸነፍ ነው›› የሚሉት ቀንደኛ አማሳኞች እነ ኃይሌ ኣብርሃ፣ ዘካርያስ ሐዲስ፣ ተስፋ ፍሥሓ እና ነአኵቶ ለአብ አያሌው‹‹የሰንበት ት/ቤቶች በዩኒፎርም ለሰልፍ እና ለስብሰባ መውጣት እያስጠቃን ነው›› ብለዋል፡፡
 • የሰንበት ት/ቤቶቹን መለያ ልብስ (ዩኒፎርም) ነጥቆ ወደ ግምጃ ቤት ለመክተት፣ ‹‹ገንዘባቸውን እና ንብረታቸውን ኦዲት ያስደረጉ›› በሚል የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕ እና የዕቅበተ እምነት እንቅስቃሴ አቅሞቻቸውን የሚያዳክሙ የአፈና አሠራሮች ለመዘርጋት እየመከሩ ነው፡፡ ስለ ሰንበት ት/ቤቶች የገንዘብ አጠቃቀም እና የንብረት አጠባበቅ የሚናገሩበት ሞራላዊ ሥልጣን የላቸውም!
 • በስም የተጠቀሱት አለቆች (መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ፣ ሊቀ ብርሃናት ዘካርያስ ሓዲስ፣ መልአከ ገነት ተስፋ ፍሥሓ እና መልአከ ብርሃን ነአኵቶ ለአብ አያሌው) በሰንበት ት/ቤቶች ላይ የአፈና አሠራር ለመዘርጋት በሚያካሒዱት ምክር በጥቅመኝነት የተሳሰሯቸው የሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች የሚያግዟቸው ቢኾንም ብዙኃኑ የአድባራት ሓላፊዎች እና ሠራተኞች እንደማይወክሏቸው በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

5 thoughts on “የሰንበት ት/ቤቶች የፀረ ሙስና እና የፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ የሚስፋፋበት እና የሚጠናከርበት ስልት ተቀየሰ፤ አማሳኞች ‹‹የሰንበት ት/ቤቶች በዩኒፎርም ሰልፍ መውጣት እያስጠቃን ነው›› አሉ

 1. ታዛቢው June 16, 2015 at 8:39 am Reply

  በሰ/ት/ቤቱ አንድነት እንቅስቃሴ ዙሪያ ሆታ የሸፈናቸው አንዳንድ እንከኖች!!
  በተደጋግሚ ተነግሯል፡፡በሰ/ት/ቤቶች በመሰረታዊነት የተነሱት፡- ምዝበራን የመግታት፣ርትእት ሃይማኖትን ሳትበረዝ ሳትከለስ የማስቀጠል፣የፋይናንስ ሥርዓትን ግልጽነት የማስፈን፣ለወጣቶች ትኩረት የመሻት የመሳሰሉ አጀንዳዎች ቅድስና ያላቸው ተገቢ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ይሁን እንጅ….
  1– ገና የግንቦት ቅ/ሲኖዶስ ሲጀመር የሰ/ት/ቤት ተወካይ ነን ያሉ ወንድሞቻችን በሰልፍ ያነሷቸው ነጥቦች በየአድባራት ገዳማቱ የሚነሱ የየዕለት ተጨባጭ ችግሮቻቸውን ሳይሆን ስለ ፓትርያርኩ ሥልጣን፣ስለ አ/አ/ስ/አስኪያጅ አሹዋሹዋም፣ያላንዳች ተጨባጭ ማስረጃ የተወገዙ መናፍቃን ወደ ቅጥር እየተመለሱ ነው የሚል ነው:: ሰልፉ ባጭሩ፡- ‹‹በሕይወት የሌሉት አቡነ ጳውሎስና በመንበሩ ከተሰየሙ 2 አመታትን የቆጠሩት አቡነ ማትያስ በኢኦተቤክ ላይ ለሆነው ሁሉ ለብቻቸው ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ተጣምረው የተከሰሱበት ነበር›› ብንል ማጋነን አይደለም፡፡በሚሊዮን የሚቆጠር አባል በስራችን አቅፈናል የሚሉት ሰ/ተማሪዎች 10 ሚሊዮን ሕዝብ ከቅድስት ተዋሕዶ መንጋ ስለመነጠሉ ሲናገሩ “የእናንተ ሚሊዮነ-ሚሊዮናት አባል ይህ ሁሉ ምዕመን እውቀት ከማጣት የተነሳ በተኩላ ሲነጠቅ ምን እየሰራ ነበር???” የሚባሉ አይመስላቸውም፡፡ምክንያቱም አበሳውን ሁሉ የሚሸከም ሰው አለ–ፓትርያርኩና የቤተክሕነት አስተዳደር!!ስሕተቱ እዚህ ላይ ነው!!ሌላው አካል ያልሰራውን መጠቆም እኛ ያልሰራነውን የሚሸፍን ይመስለናል፡፡እውነት ነው!!ፓትርያርኩም ሆነ ቤተክሕነቱ ከተራ የሰ/ት/ቤት አባላት፣ከካሕናት እና ከምዕመናን ሲነጻጸር ያለባቸው ኃላፊነት የገዘፈ በመሆኑ ተጠያቂነታቸውም መግዘፉ ግድ ነው፡፡ያ ማለት ግን በእያንዳንዱ የቤ/ክ አስተዳደራዊ ድክመት ሌላው አካል ኃላፊነቱን በሚገባ ተወጥቷል ማለት አይደለም፡፡
  2– በየደብሩ ያሉት ችግሮችና ኃላፊዎች አንድ አይነት አይደሉም፡፡የችግሮቹ መነሻ ምክንያትና ቁርሾ-ዘመንም ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡የሰ/ት/ቤቱ አንድነት አንቀሳቃሾች ግን ሁሉንም ብሶቶች አጨቁዋቸው፡፡ለአመታ የዘለቁ ብሶቶችን በሊቀ ማዕምራን የማነ እና በአቡነ ማትያስ ላይ ጭነው ተሰለፉ፡፡አናግሩን ብለው ጮሁ፡፡ሀ/ስብከቱ በክብር ተቀብሎ፤መድረክ ሰጥቶ በአዳራሽ ውይይት ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆኑን በገቢር አሳየ፡፡ያገኘው ምላሽ ግን ጅምሩን ማበረታታት ሳይሆን ‹‹ትግሉ በየአጥቢያው ይቀጥላል›› የሚል ሆነ፡፡ይህ ዛቻ የተሰነዘረበት አካል በዐይኑ ስር መዋቅር ሲፈርስ ቆሞ በመፋዘዝ ይመለከተናል ብሎ የሚያስብ ካለ የራሱን የአስተሳሰብ ደረጃ ይፈትሽ!!የአዳራሹ ስብሰባ ለመልካም ውይይት ጅምር ይሆናል ብሎ የተነሳው የነ የማነ ባለ 2 ወራት እድሜ አስተዳደር በግልባጩ የተሰጠው ምላሽ የኖረ አበሳን ሁሉ የሚያላክክ ዛቻና ማስፈራሪያ መሆኑን ከተገነዘበ በኋላ ይህን የአመጻ ተግባር እንደአመጣጡ ለመመለስ መሰናዳት ግድ ይለው ነበር፡፡ከመመካከር ማካረርን የመረጡትን አውቆ-አበድ እቡያንን ለማስታገስ የራሱን ዝግጅት አደረገ፡፡
  3– እናም ቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ላይ በእለተ ሰንበት ቀድሶ ቀርቦ የወጣ አለቃን አንገት አንቀው በጸያፍ ስድብ እየተሳደቡ ያገቱ “ቀናእያን”፣የመኪና ጎማ አስተንፍሰውና አንዱን አውልቀው ያስቆሙ “ጎበዞች”፣ከጋራዥ ባስመጡት መበየጃ ያለምንም ሥልጣንና ኃላፊነት የሚወስድ ሰው ባልተጠቀሰበት መልኩ ቢሮዎችን በቁጥጥራቸው ስር አድርገው በይደው በማሸግ ደብሩ ማንኛውም አገልግሎት ለአንድ ሳምንት እንዳይሰጥ ያደረጉ “የቤ/ክ የቁርጥ ቀን ልጆች” የተመኙትን “ሰማዕትነት” እንዲያገኙ ሲባል የግድ በሰይፍ የሚያስፈራራ መጠራት ነበረበት፡፡ተደረገ፡፡ጥቂቶት ታሰሩ፡፡የተቀሩት መጥሪያ ሲያዩ ተሰወሩ፡፡
  4– ቤተክሕነቱ 2 ጊዜ እንቅፋት አልመታውም፡፡ቦሌና ሰሚትን ካየ በኋላ በእያንዳንዱ አጥቢያ የሰ/ት/ቤት እንቅስቃሴ ላይ የየእለት ከእለት ወቅታዊ ሁኔታ ለመከታተል ጆሮውን አነቃ፡፡በመሆኑም የብስራተ ገብርኤልን እንቅስቃሴ ለጊዜው ከፍትሕ አካላት ጋር በመሆን አብርዷል፡፡በጣም የሚያሳዝነው ይሕ ዘመቻ እየተካሄደ ያለው በአንድ አጥቢያ ሰ/ተማሪዎች ብቻ አይደለም፡፡ለዚሁ ዐላማ ከአጥቢያ ወደ አጥቢያ እየተዘዋወሩ ዙሩን የሚያካርሩ ወጣቶች አሉ፡፡ምክንያቱም ይሕን ማድረግ በምንም መንገድ ይሁን አቡነ ማትያስንና የሚመሩትን ቤተክሕነት ማጋለጥ እስከቻለ ድረስ ፍጻሜው ‹‹አክሊ-ሰማዕት›› የሚያስገኝ ነው ተብሏል!!
  5– መጥፎው ዜና ይሕ አንድ አመራርን፤በጣም ግልጽ እናድርገው ካልን ደግሞ የአንድ አካባቢ ተወላጅ አመራሮችን በተለየ መልኩ በግልጽና በኅቡዕ ዘመቻ ከፍቶ የማሳደድ ድርጊት ያን ያህል የረባ ለውጥ የማያመጣ መሆኑ ነው፡፡ሐራውያንም በሰሚት እና ቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ላይ ያሉ የቢሮ ሰራተኞችን ስም እንኳ ለመጥራት እየተጉዋደዳችሁ በአጥቢያዎቹ የሌሉትን ኃይሌ አብርሃና ዘካርያስ ሐዲስ ለድርጊቶቹ ተጠያቂ አስመስሎ ማቅረብ ብሎጋችሁን በዘረኝነት የማያስጠረጥር ከመሰላችሁ ለንቀታችሁ ታላቅ ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ–ያውም እስከ ወሬ ነጋሪዎቻችሁ፡፡ዘመንፈስቅዱስ ከብስራተ ገብርኤል ወደ ምስራቀ ገብኤል ካሕን ያስቀየሩት የማነ ከመሾሙ በፊት ያውም በክ/ከተማው ሀ/ስብከት ሥልጣን ነው፡፡ኃይሌ አብርሃ ከብስራተ ገብርኤል ከተቀየሩ አመታት ተቆጠሩ፡፡ሆኖም እሳቸው እንደ ቦሌ ቡልቡላው አለቃ ብሎገሮቻችን የተወለዱበት አገር ስላልተወለዱ በሌሉበት ቦታ እንኳ ስማቸው የሚነሳ መንፈስ ሆነው በትውልዱ አእምሮ እንዲሳሉ ሆነ፡፡ይሁና!!!
  6– የበዙ ሰ/ተማሪዎች የማኅበረቅዱሳን አድናቂች እንደሆኑ አውቃለሁ፡፡ይሁን እንጅ ከማ/ቅ፡- አመራርን በየጊዜው ሥርዓት ባለው መልኩ መተካትን፣የመጻሕፍት ሕትመትን፣መደበኛ የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀምን፣…በሚመለከት የተማሩት ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ከማኅበሩ የኮረጁት፡- የቤ/ክ አመራርን በተዐብዮ መገዳደርን፣ኢመደበኛ በሆኑ ሚዲያዎች የቤተክሕነት የሆነውን ሁሉ እንደ እንጀራ አባት ማሳቀልን፣የጳጳሳትንና የካሕናትን ኃጢኣት መቁጠርን፣ጳጳሳትን ጻድቅና ኃጥዕ አድርጎ መከፋፈልን፣በትልቅ ትንሽ ያልተጣራ አሉባልታ መነዳትን፣በሺኖዳ ፍቅር አቅልን ስቶ የሚያወላዳ መደበኛ መንፈሳዊ እውቀት ሳይጨብጡ ‹‹የሰ/ተማሪ ፓትርያርክና ጳጳስ ካልሆነ›› ብሎ በየአደባባዩ መታጀርን ጌጥ አድርገውታል፡፡
  7– እስከምናውቀው ሰ/ተማሪዎች መሰረታዊ ኮርሶችን ይሰጣሉ፡፡ከዚህ ውጭ ግን የዚህና የዚያ ጉባኤ መምህር ሊሰኝ የሚችል ብቁና ለፓትርያርክ ሊታጭ የሚችል ምሁር ይቅርና ዲቁናው እንኳ በስንት ምጥ ነው፡፡ሲጀመር ሰ/ተማሪ ስሙ ራሱ ሁልጊዜ የሚማር ግን የማይመረቅ የሚል መልእክት ያለው ነው የሚመስለው፡፡ሰ/ተ…ማ…ሪ!!የሚነግራእሁ ጠፍቶ እንጅ እውቀታችሁ ከኮርስ የሚያሻግረው ጠፍቶ አብዛኞቹ አመራሮች ጉዟቸው ከኮርስ ወደ ክስ ሆኗል፡፡እውቀቱ ከኮርስ ሳያልፍ እድሜው ግን 40ዎቹ የተሻገረበት አመራር ለቤ/ክ ሊሆን የሚገባውን ከማመልከት ይልቅ ሕንጻ ሲጀመር ‹‹እነ እከሌ ሊዘርፉ ነው››፣ሂደቱ ላይ ‹‹የንብረት ግዢው እንዲህ ተጭበረበረ››፣ሲያልቅ ‹‹ድንጋይ መቆለል ሙያ አይደለም››፣ሲከራይ ‹‹አማሳኞች መዘበሩት››፡፡ሁልጊዜ ገንዘብ-ተኮር ክስና ስሞታ ብቻ!!ምናለበት አንዳንድ ጊዜ እንኳ ተሳስታችሁ ደብራችን ይልማልን የሚል አቤቱታ ብታቀርቡ፣ምናለበት የልዩ-ልዩ ልማት ፕሮፖዛሎች አቅርበን ተቀባይነት አጣን ብትሉ!!በክስ እና በኮርስ ማርጀት!!አለመታደል!!
  8– በሰበብ አስባቡ የምትከሱትንና እሱን ካላወገዘ ሲኖዶስ ቅድስና የለውም በሚል መንፈስ የምተዘምቱበትን በጋሻውን ጨምሮ በተቆርቋሪነትም በነቃፊነትም ሽፋን ቅድስት ቤተክርሰቲያንን እና ብፁዐን አባቶችን ለማነወር ሲነሱ ልሳናቸውን የማያነቅፋቸው አብዛኞቹ አማተር ሰባክያን፣ዘማርያን፣በስመ ታዋቂ የሚነግዱ ፌዝቡከሮችና ብሎገሮች(እነ አሸናፊ መኮነን፣አቤኔዘር ተክሉ፣ኒቆዲሞስ፣ሐዋዝ….) የኋላ የመደብ ጀርባቸው ሲጠና ብዙ ጊዜ ሰ/ት/ቤት ሆኖ ነው የሚገኘው፡፡ከፕሮቴስታንት ፓስተርነት እስከ ኳየር ዘማሪነት የደረሱ ሰ/ተማሪዎች ቁጥር ቀላል የሚባል አለመሆኑ የሚነግረንም የእኛ ሰ/ት/ቤት ት/ት ደረጃ ፓትርያርክ ሊያወጣ የሚችል ሊሆን ቀርቶ ራሱን ከተሐድሶ ዘመነኛ ወጀብ ለመጠበቅ እንኳ ችግር ያለበት መሆኑን ነው፡፡አረጋውያን የሰ/ት/ቤት አመራሮቻችን ሚሉት ግን ሌላ ነው!!
  9– ወመሾች ለእናንተ ሚሆን አደረጃጀት ቅ/ሲኖዶስ እስከፈጥር ድረስ 30 አመት የእድሜ ገደቡን አክብራችሁ ለአዲሱ ትውልድ መድረኩት ብተተውት መልካም ነው!!ምክንያቱም ሰ/ት/ቤት እንደ 50 አመት ተቋምነቱ ለሚያመረቃ እድገት ከማብቃት ይልቅ ባለበት የማደንበሽ፣ከቤተክሕነት የማራራቅ፣የማኅበረቅዱሳን ተለጣፊ የማድረግ፣ቅሬታዎችን በሰ/ጉባኤ ባለው ተወካያችሁ ከማቅረብ ይልቅ በጋዜጣና በብሎግ እያራገቡ የመናፍቃን መዘባበቻ የማድረግ ጉዟችሁ ስለማይጠቅም!!
  10– ስለዚህ ነጽሩ ርእሰክሙ!!አእትቱ እከየ እምአልባቢክሙ!!ባይሆን ከዚያ በኋላ….

  • tekure sew June 16, 2015 at 12:08 pm Reply

   ውድ ሙሴ(ወይ ዘንድሮ)
   ቃለ ህይወት ያሰማልን
   እብሪተኞች፣ ለራሳቸውና ጥቅም አሳቢዎች በሞሉበት በዚህ ዘመን በፈርኦን ቤት እንደ ሙሴ ሆነው ለቤተ ክርስቲያን የተነሱ ከአባታቸው ከክረስቶስ ተምረው ቤተ ክርስቲያን መሸጫና መለወጫ ቤት እንዳትሆን ለሚጥሩ ወጣቶች ዋጋን የሚከፍል እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይክፈል፡፡ ልቦና ለእያንዳንዱ ያድል፡፡

 2. Anonymous June 16, 2015 at 9:17 am Reply

  weye zendero

  ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር

  ሙሴ

  ዕብ. 11፡32
  ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ፤
  የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ የግብፅን አገር የተወ በእምነት ነበር፤ የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአልና።
  ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።
  ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ከፈርዖን፡፡
  ይህ ነው እምነት ከራስ ይልቅ ለሕዝቡ መራራት ያለሕዝብ መሪና ተመሪ የለምና ዛሬ ዛሬ ደግሞ የሙሴን ወንበር የያዙት በጎችን ከማሰማራት ፋንታ ወደመከራ እና በእንግልት መንደር እየገፉአቸው ይስተዋላል፡፡

  ዘፀአ 3፡7

  እግዚአብሔርም አለ፦ በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ
  አሁንም እነሆ የእስራኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ወጣ ግብፃውያንም የሚያደርጉባቸውን ግፍ ደግሞ አየሁ። ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ። አሁንም ና፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ታወጣ ዘንድ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ።
  ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ሙሴም፦ ዛሬ በረከትን እንዲያወርድላችሁ እያንዳንዳችሁ በልጃችሁና በወንድማችሁ ላይ ዛሬ እጃችሁን ለእግዚአብሔር ቅዱስ አድርጉ አለ።
  ከመከራና ከጥፋት የፈርዖን ግቢ ማውጣት ባትችሉ እንኳ መራራት ስትችሉ ይልቁንም አሳልፋችው ልጆቻችውን የምትሰጡ ምን ብልን እንጥራችሁ እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ፡፤

  ዘፀአ፡ 32፡29
  አሁን ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ አለ።
  እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የበደለኝን እርሱን ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ።
  ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፦ ወዮ! እኒህ ሕዝብ ታላቅ ኃጢአት ሠርተዋል፥ ለራሳቸውም የወርቅ አማልክት አድርገዋል በነጋውም ሙሴ ለሕዝቡ። እናንተ ታላቅ ኃጢአት ሠርታችኋል አሁንም ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ ምናልባት ኃጢአታችሁን አስተሰርይላችኋለሁ አላቸው።
  ይገርማል ሕዝቡ ከሚጠፉ እኔ ልጥፋ ጌታየ፤ የሙሴ ወንበር ዛሬ ደግሞ ግፋቸው፤ እሰራቸው፤ ደብድባቸው የሚል ግፈኛ እና ቀማኛ ሰው ሲቀመጥበት አያሳዝንም፡፡

  እውነተኛ ጠባቂ /ቸር ጠባቂ/ ስለ በጎቹ ተላልፎ ይሰጣል የሚለውም ከዚህ አንጻር ነው፡፡ ቸር ጠባቂ በጎቹን ከምንም በላይ ይንከባከባል፡፡ ከተኩላ የሚድኑበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡ ቸር ጠባቂ ስለ አንድ በግ ይገደዋል፡፡ የአንድ ሰው ነፍስ በኃጢአት ተይዛ እንድትሞት አይፈልግም፡፡
  ዮሐ. 10፡15 የራሴን በጎች አውቃለሁ፡፡ የራሴም በጎች ያውቁኛል፡፡ ነፍሴንም ስለ በጎቼ አኖራለሁ እሜጡ ነፍስየ ቤዛ አባግዕየ ለበጎች ለምዕመናን ሰውነቴን ለሞት አሳልፌ እሰጣለሁ፡፡ በጎችን የምንንከባከባቸው ፀጉራቸውን ሸልተን ስለተጠቀምንባቸው፣ አርደን ስለተመገብናቸው፣ እንደሚመቸን ሁሉ ስላደረግናቸው ከሆነ የበጎች ጠባቂ ነን ለማለት አያስደፍርም ጥፋትም ነው፡፡

  ሕዝ. 34፡1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፡፡ የሰው ልጅ ሆይ ትንቢት ተናገር፡፡ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፤ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡፡ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው፡፡ እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን ጮማውን ትበላላችሁ፡፡ ጠጉሩንም ትለብሳላችሁ፤ የወፈሩትን ታርዳላችሁ፤ በጎቹን ግን አታሰማሩም፤ የደከመውን አላጸናችሁትም፤ የታመመውንም አላከማችሁትም፤ የተሰበረውንም አልጠገናችሁም፤ የባዘነውንም አልመለሳችሁትም፤ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም፤ በጭቆናም ገዛችኋቸው፡፡ እስከ መጨረሻው ድረስ ይገባል፡፡ በፊደል ቃል ለተሰበሩት በማስተማር የተጎዳውንና የተጎሳቆለውን ማንነት እንዲጠገን ማድረግ የጠባቂዎች ፋንታ ነው፡፡ ይህ ሰብራት ሥጋዊ ስብራት ሳይሆን መንፈሳዊ ስብራት ነው፡፡ አንድ ፊደል የሰበረውን ሰው ለመመለስ ሺህ ጊዜ ድካም ያስፈልገው ይሆናል፡፡

  የፊደልን ቅርጽ አውቃለሁ ባዩ ሲሰበር ማን ይጠግነው ታዲያ፤፤ የበጎችን ሥጋ በሉ ጸጉራቸው አለቀ፤ ታሰሩ ፤ ተንገላቱ ወደ ወይኒቤት ተወረወሩ አይበቃም ሆይ

  ለታሰሩት መፈታትን ማወጅ

  ይህ ደግሞ ዋነኛው ተግባራቸው ነበር ነገር ግን ለፖሊስ ሠራዊት አሳልፈው ልጆቻአውን በመስጠት ለሥር እየዳረጉ ያሉ ቤተክርስቲያንን የማያውቋት በጊዜውና በዘመኑ ጊዜ ሰጥቷቸው ለመብልና ለጥፋት የተሰማሩ የጥፋት ልጆች ናቸው፡፡

  ማቴ. 21፡1 ወደ ኢየሩሳሌም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ የን ጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከ /ጴጥሮስና ዮሐንስን/ እንዲህም አላቸው፡፡ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፡፡ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፡፡ ፈትታችሁ አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፡፡ እስከ መጨረሻው ተመልከቱ
  የእኛ ጌታ እስከዚህ ድረስ ነው ለታሰሩት አህዮች እንን የሚገደው አምላክ ፈትታችሁ አምጡልኝ በማለት እርሱ ሊመሰገንባቸውም ወደደ፡፡ ብዙ ጊዜ በኃጢአት፣ በልዩ ልዩ ደዌ አልጋ ላይ የዋሉ ለምንም ነገር የማይጠቅሙ አድርገን እናስብ ይሆናል፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ ቸር ጠባቂው ጌታ ሁሉንም ከእስራቱ ይፈታል፡፡ የእርሱ አገልጋዮች የታሰሩትን ሊፈቱ ተልከው ነበር፡፤

  ዛሬ ደግሞ የታሰሩትን እንዲያስፈቱ የተላኩት ከፖሊስ ሠራዊት ጋር ሆነው የሚያስሩ የሚማቱ ፍቅር የሌላቸው ሆኑ፡፡ ምዕመናን እባካችው ስልእግዚአብሔር ብላችው በጸሎታችው ከታሰሩበት የመከራ ሕይወት እንዲፈቱ እርዱዋቸው፡፡

  ዘጸአ. 14፡14

  ሙሴም ለሕዝቡ። አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
  ግብፃውያንም በፈርዖንና በሰረገሎቹ በፈረሰኞቹም ላይ ክብር ባገኘሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ለምን ትጮኽብኛለህ? እንዲጓዙ ለእስራኤል ልጆች ንገር። አንተም በትርህን አንሣ፥ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፥ ክፈለውም የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ። እነሆም እኔ የግብፃውያንን ልብ አጸናለሁ፥ በኋላቸውም ይገባሉ በፈርዖንና በሠራዊቱም ሁሉ በሰረገሎቹም በፈረሰኞቹም ላይ ክብር አገኛለሁ።
  እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ አላቸው። በእስራኤልም ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ፥ በግብፃውያን ሰፈርና በእስራኤል ሰፈር መካከልም ገባ በዚያም ደመናና ጨለማ ነበረ፥ በዚህ በኩል ግን ሌሊቱን አበራ ሌሊቱንም ሁሉ እርስ በእርሳቸው አልተቃረቡም። ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፥ ባሕሩንም አደረቀው፥ ውኃውም ተከፈለ። የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ መካከል በየብስ ገቡ ውኃውም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆነላቸው። ግብፃውያንም፥ የፈርዖን ፈረሶችና ሰረገሎች ፈረሰኞቹም ሁሉ፥ እያሳደዱ በኋላቸው ወደ ባሕር መካከል ገቡ። እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፥ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፥ በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ፥ ውኃውም በግብፃውያን በሰረገሎቻቸውም በፈረሰኞቻቸውም ላይ ይመለስ አለው።
  ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፥ ባሕሩም ማለዳ ወደ መፍሰሱ ተመለሰ ግብፃውያንም ከእርሱ ሸሹ፥ እግዚአብሔርም ግብፃውያንን በባሕሩ መካከል ጣላቸው። ውኃውም ተመልሶ በኋላቸው ወደ ባሕር የገቡትን ሰረገሎችን ፈረሰኞችንም የፈርዖንንም ሠራዊት ሁሉ ከደነ ከእነርሱም አንድ ስንኳ አልቀረም።
  የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ ውስጥ በየብስ ሄዱ ውኆችም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆኑላችው። እግዚአብሔር በዚያን ቀን እስራኤልን እንደዚህ ከግብፃውያን እጅ አዳነ እስራኤልም የግብፃውያንን ሬሳ በባሕር ዳር አዩ።
  ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፥ የግብፃውያንንም ሠራዊት አወከ። የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አገባቸው ግብፃውያንም። እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ አሉ።

  ይህ ነው ሙሴ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከባርነት ቀንበር ነጻ የሚያወጣ እርሱ መከራን በጾም፤ በጸሎት ተሻግሮ ሕዝቡን የሚያሻግር ሙሴ፤ በአንጻሩ ደግሞ ዛሬ የፈርዖንን ቤት የሚናፍቅ የሕዝብ መሪ ለመሆን ዳዴ ሲል መመልከት ይገርማል፡፡ የአንተ ፍልጎትና መሻት እያሸነፈህ፤ እያስቸገረህ ፤ እያንገዋለለህ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ልምራ ስትል ለህሊናህ ምን ይሰማሀል፡፡ ለነገሩ ጥንቱንም ህሊና ቢኖርህ ኖሮ ይህን በደል ሁሉ አትፈጽምም ነበር፡፡ ነገር ግን ህሊና የሌለው ሥልጣን ፍሬ የሌለው ገለባ ማለት ነው፡፡ ትንቱንስ ከገለባ ምን ፍሬ ይገኛልና ነው ድካሙ መስሎን እንጅ ቃሉማ እንዲህ ይል አልነበር ማቴ. 5፡16 መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡
  እንኳን ልታበሩልን የበራውን አጠፋችሁብን፤፤ ብርሃን የሚበራው እኮ ከብርሃን ውስጥ ተገኝቶ ነው፤፤ ጥንቱንም ብርሃን ከሌላቸው የትያመጡታል እንደገንዘቡ የሚዘረፍ እና የሚሰረቅ እይደለማ?

  ፈሪሳውያን
  እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
  እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።
  እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።
  አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ።
  እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።

  አያሳዝን የሙሴን ወንበር እንዚህ ሰዎች ሲቀመጡበት ወይ ድፍረት እንዲህ እንዳሉ ግን መኖር ይኖር ይሆን የቅዱሳን አምላክ የት ሄዶ፡፤

  ለቤተክርስቲያን ሁሌ የምትቆሙ እግዚአብሔር ከእንተ ጋር ነው አይዞአችሁ ብትሰደዱ ብትታሰሩ ሰርቃችሁ አይደለም እውነትን መስክራችሁ እንጅ እውነት ቀራኒዩ ላይ በዕለተ አርብ ተሰቅሎ ነበር ግን የሀሰት መቃብር አላሸነፈውም፤ ዛሬ በዙሪያችሁ ያሉ የሀሰት መቃብሮች ፖሊስና ፈሪሳውያኖች ያልፋሉ እውነት በሲኦል መቃብር ሆድ ውስጥ የተፀነሱትን ሁሉ ማውጣቱ አይቀሬ ነው፡፡

  ብትሰደዱ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡ ብትታሰሩ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፡፡
  ማቴ. 5፡11
  ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።
  ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።
  እግዚአብሔር በእምነት ያጽናን፡፡

  • ታዛቢው June 16, 2015 at 12:55 pm Reply

   ሊመለስና ሊደመጥ የሚገባውን ሙስናን የመዋጋትና የፋይናንስ ሥርዐትን የማስተካከል እንቅስቃሴ ሳይሞቅ ፈላ በሆነው፣ቡድናዊነት በሚሾፍረው፣ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነትን አፈር ድሜ ባበላው፣ራሱን ከብረት የተሰራ ጅማት ያለው አድርጎ በማሰብ በዐውደ- ምሕረቱ በምዕመን ጀርባ ታዝሎ ተቋሙን ማንገዳገዱን እንደ ትልቅ ስኬት በሚመለከት የሚዲያ ጫጫታ አስጠለፋችሁት፡፡፡አሁን ራሳችሁን በጀብደኝነት ሰማዕት-ዘበከንቱ አድርጎ ከማቅረብ አካሄዳችሁን ዳግም ብታቃኙት መልካም ነው፡፡፡

   የመኪና መስታወት ሰብሮ፣ጎማ አፈንድቶ፣ቢሮዎችን በጉልበት በይዶ አሽጎ፣ስብሰባዎችን ረግጦ ወጥቶ፣አለቃና ጸሐፊ ዘልፎ፣የቢሮ ሰራተኞችን በቡድን ተደራጅቶ በመክበብ ሌባ-ሌባ ብሎ ጨፍሮ፣ጸያፍ እና ሰቅጣጭ ቃላትን በቀናኢነት ሥም ሰንዝሮ….በአጠቃላይ ወደ ኃይልና ጉልበት እርምጃ ተሸጋግሮና እርምጃውን ሲያወድሱ ቆይቶ ለኃይለኛው ኃይለኛ ሲጠራ ‹‹ስለጽድቅና እውነት የሚሳደዱ ብፁዐን ናቸው›› ማለት የሚሆን አይደለም፡፡ሺህ ጥቅስ ቢንጋጋ የተፈጠሩትን የአካሄድ ግድፈቶች መሸፈን አይቻልም፡፡ምናልባት የየዋሐንና የማኅበራዊ ሚዲያውን በሞኖፖል ይዘው በአንድ አይነት ቅኝት ካልተቃኘ ለሚሉ እውነትን በድምጽ ብዛት ለመበየን የሚሹ ሰዎች የይምሰል ማጽናኛ ሊሆን ይችላል፡፡

   ሁሉን አውቃለሁ ብሎ ለቅ/ሲኖዶስ አጀንዳ ለመቅረጽ የሚጥር ትውልድ የተፈጠረለትን መድረክ እያጥላላና ሕጉን በእጁ አድርጎ እስከ ጥግ ከሄደ በኋላ ከአቅሙ በላይ በሆነ ኃይል ኃይሉ ሲገታ እኔን ከሚገቱኝ ለምን አይመክሩኝም ማለት ራስን መቃረን ነው፡፡እንዳትገሰጹማ መገሥጹን መቼ እውቅና ሰጣችሁ!!ንቃችሁና ረግጣችሁ ያለፋችሁትን አካል የያዘ ሲይዛችሁ ሳንገሰጽ ለባዕድ ተሰጠን ማለታችሁ የአዞ እንባ ነው፡፡ምክሩን ከአባቶች ሳይሆን ከመከራ ለማግኘት ስለናፈቃችሁ ከመስመር ባለፈ አካሄዳችሁ የሚደርስባችሁን ተጠያቂነት ሰማዕትነት ማለት በሰማዕትነት ማሾፍ ነው፡፡፡

   ባይሆን ‹‹አንትሙሰ ታጸድቁ ርእሰክሙ፤ወእግዚአብሄር የአምር አልባቢክሙ›› እንላችኋለን፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: