የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን: በልማት ስም ከጥቅመኛ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር የቤተ ክርስቲያንን ሀብት እና ንብረት ለግሉ በማካበት በሚታወቀው የቀድሞው አለቃ ኃይሌ ኣብርሃ፥ የባለቤትነት እና የተጠቃሚነት መብቱን አሳልፈው በሚሰጡ የኪራይ ውሎች ከመመዝበሩም በላይ የሚልዮኖች የባንክ ባለዕዳ አድርጎት ያለተጠያቂነት ለመሰል ዘረፋ ወደ ሌላ ደብር ተዘዋውሯል፡፡
በእግሩ የተተኩት ግብታዊው እና ዐምባገነኑ መልአከ ብርሃን ዘመንፈስ ቅዱስ (የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ አባት)፥ በቃለ ዐዋዲው መሠረት በሰበካ ጉባኤው ሙሉ ተሳታፊ የኾኑትን እና የወሳኝነት ድርሻ ያላቸውን የማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮችን በማሳደድ እና ከልጃቸው ጋር ተማክረው ሥልጣን በሌለው የክፍለ ከተማው የሰው ኃይል አስተዳደር ሓላፊ በኩል አምስት ካህናትን ወደ ሌላ አድባራት በማዘዋወር ሀብቱንና ይዞታውን ከሚነጥቁ ቀማኞች ጋር እየሠሩ ነው፡፡
* * *
- በአለቃው ከሰበካ ጉባኤው የተባረረው የማኅበረ ምእመናን ተወካዩ እና የሰንበት ት/ቤቱ አባሉ ዲ/ን ሰሎሞን የኋላሸት ‹‹ወረቀት በትኗል፤ አድማ አነሣስቷል›› በሚል በአለቃው ጥያቄ ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ ነው
- በጥፋታቸው ስለሚቃወሟቸው፣ በዋና ሥራ አስኪያጁ ልጃቸው ተመክተው በግፍ ያዘዋወሯቸው ካህናት በሳምንት ጊዜ ውስጥ እንዲመለሱ፤ ሰበካ ጉባኤውም እንደ ቃለ ዐዋዲ ደንቡ በተሟሉ ተወካዮች እንዲጠናከር ምእመናኑ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል
- በደብሩ የጠበልተኞች ማደርያ የኾነው ቦታ እንዲከበር የሚጠይቁትን የጠበል ዕድርተኞች ፊት በመንሳት ለግለሰብ ተላልፎ እንዲሰጥ እየተባበሩ ነው
- በሰበካ ጉባኤው የሰንበት ት/ቤቱ ተወካይ በመልቀቁ በሌላ እንዲተካ ሰንበት ት/ቤቱ ለወራት ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም
- ምክትል አስተዳዳሪ በሚል ተቀምጦ ቀድሞ ደብሩን ለመዘበረው ኃይሌ ኣብርሃ መረጃ የሚያቀብለው ግለሰብ ተጨማሪ ምእመናንን በጥቆማ ለማሳሰር እየሠራ ነው
Advertisements
[…] Source:: haratewahido […]
ምነው እናንተ ሁሌ እከሌ ተሾመ እከሌ ተሻረ እከሌ ሊሻር ነው እከሌ ሊሾም ነው በማለት ተራ እና ከንቱ በሆነ ወሬ ተጠምዳችሁ ቀራችሁ ለሕይወት የሚሆን መልዕክት የላችሁም ማለት ነው የተረት አባቶች ሁሌ ተረት የባልቴት ወሬ ርካሽ ወሬ በጣም ያሳዝናል።
የቄስ አደራው ንጉሴ የቀድሞ አስተዳደር ምዝበራ የት ደረሰ ለ10ተ አመታት ተሸፋፍኖ
አሁን በ አትላንታ እንደሚነገኙ መረጃዎች አሉ ደግሞ ጊዜውን ጠብቆ መልአከ ገብርኤል
ያወጣዋል ቤተ ክርስቲያኒቱ የተከበበችው ከፍተነኞ ባለ ሀብቶች ምእመን ጭምር
በመሆኑ ከፍተኞ ነዋይ በቀላሉ ይመዘበራል DX ፠ Lada ፠ vitz ይዘው ሲንቀሳቀሱ
ማየት የተለመደ ነው ፀበል ለመርጨት እንኳ በግር እንደ ጥንቱ ቀርቷል እናም ቃለ
እግዚያብሄር ተሽሮ በሀገረ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው ድረፍረት ተፈጸመ
ፖሣህ ሱፐር ማርኬት ዝሆን የቁሻሻ ማስወገጃ በኚሁ ቄስ ተባባሪነት ኤርትራዊቷ ከወ/ሮ አስቴር
ጋር ያለምንም ጨረታ ሸንቁረዉ ሰጡ ይህን ተከትሎ በዙሪያው ከ20 በላይ ሱቆች ተከፍቶ
እየተመዘበረ ይገኞል እንዲሁም ምእመኑ የደከሙበት የትምህርት ቤት ቦታ 2000ካሬ
ሜትር በላይ በሙስና መሸጡ በጣም አሳዛኝ ክስተቶችን እያስተናገደ የሚገኝ ደብር ነው።
ዛሬ በመንገዱ ቢያልፉ ቤ/ክኑን ሊታያችሁ ቀርቶ የምታማትሙት ሱቆተቹን ነው
ያስለቅሳል የተቀደሰ ስፍራ እንዲህ መሆኑ እባካችሁ ምእመናን እንዴት እንታደግ ?
አዱኛና ማህበረ ሰይጣን መቸም ቢሆን አይሳካላችሁም ፡፡ ምክንያቱ ህብረታቹ ከሰይጣንና ከርኩሰቱ ነውና፡፡ እግዚአብሄር በልጆቻቹ ያሳያቹ፡፡ ቤተክረስቲያንን እንዲሀ በጠበጣችሃት አንድ ቀን ጭሆትዋ ይሰማ ይሆናል፡፡