በአ/አበባ ሀ/ስብከት: ከብር 113 ሚልዮን በላይ የፈሰስ ዕዳ እንዲሰረዝ መጠየቁ እርምት ያስፈልገዋል፤ ‹‹የአየር ባየር የዘረፋ ስልቱን ለመሸፈን የተቀመረ ነው›› /ሠራተኞች/

Lique Tebebit Elias Techane

የአጥቢያዎች ፈሰስ፣ የሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪዎች እና የአበል ክፍያዎች ቀበኛ የጥንቆላ እስረኛሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ: ከግሮሰሪ(አ.አ) እስከ ባለአምስት ፎቅ ሕንፃ(መቐለ) ባለቤት

 • የቁጥጥር እና የፋይናንስ ሓላፊዎች የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ዝቅተኛ ነው
 • በቆጠራዎች የሚዘረፈው የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቢሯቸው ድረስ ይመጣላቸዋል
 • የቤተሰብ ጉባኤ በሚመስለው የቁጥጥር ክፍሉ ስብሰባ የዘረፋ ስልቶች ይቀመራሉ
 • ትኩረቱን ወደ ከፍተኛ ግዥዎችና ፕሮጀክቶች ለማዞር እስከ መምከር ተደርሷል
 • እነኃይሌ ኣብርሃ እንዳሉት፣ ‹‹ንቡረ እድ ኤልያስን የተማመነ ምን ይኾናል!››

/ከሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች/

‹‹ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች›› እንዲሉ በአኹኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሒሳብ እና በጀት እንዲኹም በቁጥጥር አገልግሎት ዋና ክፍሎች በኩል ከሕግ፣ ከመርሕ እና ከሥነ አመክንዮ ውጭ ብዙ ሕገ ወጥ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በአድባራት የደመወዝ እና የአበል ክፍያ ጭማሪ፤ በክብረ በዓል እና በወርኃዊ የአብያተ ክርስቲያን የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እና የንብረት ሽያጭ ጨረታ ወቅት የሚሠሩ ሙስናዎች ልክ እንደ ሕጋዊ መብት በግልጽ እተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ ለዛሬው፣ ለቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ወሳኝ ስለኾነው የፈሰስ(ፐርሰንት) ጉዳይ እንመልከት፡፡

የሀገረ ስብከቱ የፐርሰንት አሰባሰብ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገቢ መጠን ከሌሎች አህጉረ ስብከት በተለየ ኹኔታ ከፍተኛ ነው፡፡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትም ከፍተኛውን ገቢ የሚያገኘው ከአ/አበባ ሀ/ስብከት ነው፤ ነገር ግን የገቢ አሰባሰቡንና የሒሳብ አያያዙን የሚመሩት ሰዎች ከዘመናዊው የሒሳብ ዕውቀትና ልምድ አንጻር ያላቸው ሞያ እጅግ ዝቅተኛ ከመኾኑም በላይ ከገዳማትና ከአድባራት ሓላፊዎች ጋር በተለያዩ የዘረፋ ስልቶች የሚመመሳጠሩ እና በሌብነት የተደራጁ ናቸው፡፡

የሒሳብና በጀት ዋና ክፍሉ እና የቁጥጥር አገልግሎት ዋና ክፍሉ ከነባለቤታቸው በገቢያቸው ከፍተኛ ከኾኑ ከዐሥር የሚበልጡ ገዳማት እና አድባራት በሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ ወቅት ከሚዘረፈው ገንዘብ ላይ ቢሯቸው ድረስ ድርሻቸው የሚመጣላቸው ናቸው፡፡ ከ15 ጊዜ በላይ በተለያዩ አድባራት እየተዘዋወረ ለ17 ዓመት የሠራው ዋና ሥራ አስኪያጁ የማነ፣ የቆጠራ ወቅት ዘረፋውን በውል የሚያውቀው ከመኾኑም በላይ ‹‹የተነቃበት›› እንደኾነና ወደ ከፍተኛ ግዥዎች እና ልማት የሚል ቅጽል ወደተለጠፈባቸው ፕሮጀክቶች ትኩረት መደረግ እንዳለበት እስከ መምከር ደርሷል፡፡

የሒሳብና በጀት እንዲኹም የቁጥጥር አገልግሎት ሓላፊዎች በሥራቸው ዕውቀት ብቻ ሳይኾን ፍጹም ታማኝነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ በአኹኑ ወቅት ሀገረ ስብከቱ ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በወቅቱ መሰብሰብ ሲገባው ያልተሰበሰበ ከ113 ሚልዮን ብር በላይ በገዳማትና አድባራት የተከማቸ የፈሰስ ዕዳ ስለመኖሩ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትም ኾነ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጽ/ቤት በማስረጃ ይታወቃል፡፡ ለምን በወቅቱ አልተሰበሰበም? እንዴት ይህን ያክል ብር ሊከማች ቻለ? ተሰብሳቢዎች (receivables) ከሚሰበሰቡበት ስሌት አንጻርስ ምን የተነደፈ ስልት አለ? የሚሉትን መመዘኛ እና መፈተሻ ጥያቄዎችን እናነሣለን፡፡

የሀገረ ስብከቱ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊነት የተሰጣቸው ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ፣ ገዳማቱ እና አድባራቱ የመክፈል አቅም እና ፍላጎት ስለሌላቸው ያልተሰበሰበው 113 ሚልዮን ብር ይሰረዝላቸው የሚል ምክረ ሐሳብ(ፕሮፖዛል) ይዘው መቅረባቸው አሳዛኝና የእርሳቸውን የአየር በአየር የዘረፋ ስልት ለመሸፈን የተቀመረ መንገድ ነው፡፡

ለምን እንዳልተሰበሰበ የቁጥጥር አገልግሎቱ ሲመልሱ፣ ‹‹እኔ ሥራዬን ሠርቼ ሪፖርት አድርጌአለኹ፤ መከታተል እና መሰብሰብ የሒሳብ ክፍሉ የሥራ ድርሻ ነው›› ብለዋል፤ ከተጠያቂነት የመሸሻ ምላሽ ነው፡፡ ይህን የታዘቡ ሌሎች የሀገረ ስብከቱ የሥራ ሓላፊዎችም በወቅቱ፣ ‹‹ኤልያስ መች ሥራ ይሠራል፤ የእርሱ ሥራ ሌላ ነው›› በማለት የፈሰስ ዕዳው እንዲሰረዝ በቀረበው ፕሮፖዛል አዝነዋል፡፡

Lique Tiguhan GebreMeskel Dirar

ሊቀ ትጉሃን ገብረ መስቀል ድራር: በገንዘብ እና ገንዘብ ነክ ሥራዎች እና ሓላፊነቶች እንዳይመደቡ በቋሚ ሲኖዶስ ተወስኖባቸው ነበር፤ ንቡረ እድ ኤልያስ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ግን የቁጥጥር አገልግሎት ሓላፊ አድርገዋቸዋል፤ ለትንሣኤ በዓል የክፍል ሓላፊ ለኾኑት ባለቤታቸው ወ/ሮ ባሕረ ሙዝ ገብረ ሚካኤል የብር 450‚000 ያሪስ መኪና በስጦታ አበርክተዋል

የአየር በአየር ዘረፋ

የአየር በአየር ዘረፋ የቁጥጥር አገልግሎቱ ሓላፊ ለረጅም ጊዜ ያካበተው የአዘራረፍ ስልት ነው፡፡ በክብረ በዓላት እና በወርኃዊ ገቢዎች ወቅት በቁጥጥር አገልግሎቱ የተመረጡ ሰዎች ከሀገረ ስብከቱ ይላካሉ፡፡ ለዚኽም የቁጥጥር ክፍል ሓላፊው ባለቤት የኾኑት ወ/ሮ የባሕር ሙዝ ገብረ ሚካኤል ተመራጯ ሚሽን አስፈጻሚ ናቸው፡፡ መቼስ ከክፍለ ከተማ ወደ ዋናው ጽ/ቤት በዝውውር የመጡት በተለየ የሞያ ብቃት ሀገረ ስብከቱን ይረዳሉ ተብሎ ሳይኾን ለዚኹ ተግባር ተመልምለው እንደኾነ ይታመናል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በሀገረ ስብከቱ ሦስት ባልና ሚስት፣ ሦስት የአጎት እና የአክስትማማቾች ልጆች፣ ኹለት በጋብቻ የተሳሰሩ ቡድኖች በተቀናጀው የዘረፋ ስልት አሉበት፤ በክፍለ ከተማም እንዲኹ ማጣራት ይቻላል፡፡ አንዳንድ ጊዜም በቁጥጥር አገልግሎቱ ቢሮ የሚደረገው ስብሰባ፣ የቤተሰብ ጉባኤ የሚመስል ሲኾን አዲስ የአዘራረፍ ስልቶች ቅመራና ዕቅድ፣ አስተያየት እና አካሔድ በሚል ስም ይቀየሳል፤ ሌሎችም አሉ፡፡

የቁጥጥር ልኡካኑ በወቅቱ ገንዘብ እና ንብረት አስቆጥረው፣ በሞዴል 64 ገንዘቡን በ19 ንብረቱን አስገብተውና ደረሰኝ አስቆርጠው የሀገረ ስብከቱም ድርሻ 20 ፐርሰንት ታውቆና ለባንክ ገቢ ኾኗል ተብለው ይመጣሉ፡፡ እዚኽ ጋር ነው እንግዲኽ የቁጥጥር አገልግሎቱ እና የሒሳብ ክፍሉ ጫዎታውን የሚጫወቱት፡፡

20 ፐርሰንት ፈሰስ በወቅቱ ለሀገረ ስብከቱ አይገባም

የቁጥጥር አገልግሎቱ ክፍሉ እያወቀ እና እንደገባ በማስመሰል ዝም ይላል፡፡ የበጀት እና ሒሳብ ክፍሉም እያወቀ የቀረበለትን የውሸት የገቢ ሰነድ ደብቆ ይይዘዋል፤ ነገር ግን በገቢ አይመዘገብም፤ ምናልባት ኦዲተር በድንገት ከመጣ ለመጠባበቂያ መኾኑ ነው፡፡ ገንዘቡን ራሳቸውና ወዳጆቻቸው/የሥራ ተባባሪዎቻቸው ይነግዱበታል፡፡ በገዳማትና በአድባራት ያሉ የሚመለከታቸው ክፍሎችና እኒኽ የረጅም ጊዜ የዘረፋ ጓደኛሞች አለአግባብ በሕገ ወጥ መንገድ ይበለጽጉበታል፡፡

ሰኔ ሲመጣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚላኩት ኦዲተሮችም ሌሎች ጉዳዮችን የመመርመርና እውነቱን የማሳወቅ አቅም ያንሳቸዋል፤ የሚያስመድቧቸውም እነርሱ ናቸውና የቀረቡትን ሰነዶች በፈረደበት ካልኩሌተር ደምረውና ቀንሰው ይሔዳሉ፡፡

the-heavily-corrupt-haile-abreha

በአኹኑ ወቅት ዋና ሥራ አስኪያጁ በገፍ በሚያካሒዷቸው ዝውውሮችና ቅጥሮች፤ በልማታዊ ጉብኝት ስም በሚዘዋወሩባቸው አጥቢያዎች ዋነኛው ባለሟልእስከ 8 ሚልዮን የባንክ ተቀማጭ፣ ቤቶችና ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች ያካበተው ኃይሌ ኣብርሃ፤ የሰንበት ት/ቤቶችን የዕቅበተ እምነት፣ የመልካም አስተዳደር እና የፍትሕ ንቅናቄ የአንድነቱን አመራሮች በመክሠሥ ለማክሸፍ በመቶ ሺሕዎች ብር መድቦ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል

ልብ ሊባል የሚገባው ነገር፣ በወቅቱ ከሀገረ ስብከት በሚላኩ የቁጥጥር ልኡካን የሀገረ ስብከቱ ድርሻ 20 ፐርሰንት በእነ ወ/ሮ የባሕር ሙዝ ከገባ፤ የገቢው ኹኔታም የቁጥጥር አገልግሎቱ ሚስት እና ሌሎች አጋሮቹ ያመጡለትን ሪፖርት ለበጀት እና ሒሳብ ዋና ክፍሉ ሪፖርት ካደረጉ ገንዘቡ የት ገባ? ምክንያቱም ገንዘቡ ለቁጥጥር ለሚሔዱ ልኡካን አበል ተከፍሎ ቁጥጥር ተደርጎበታል፡፡ ስለዚኽ በወቅቱና በጊዜው ገቢ እንደሚደረግ ከታወቀ ይህን ያኽል ውዝፍ የቤተ ክርስቲያን ሀብት እንዴት ሊከማች ቻለ? አየርባየር ማለት ይህ ነው፡፡ ይህን የውጭ ኦዲተሮች ቢመለከቱት በቢሊዮን ደረጃ ጉድለት እንደሚገኝ አያጠራጥርም፡፡ የአራዳ ጊዮርጊሶቹ እነኃይሌ ኣብርሃ፣ ‹‹ንቡረ እድ ኤልያስን የተማመነ ምን ይኾናል›› እንዳሉት እኛም በመግቢያችን ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች የሚለውን የአበው ብሂል አውስተናል፡፡

ሊቀ ጠባቡ ኤልያስ ተጫነ እና ሊቀ መሠሪው ገብረ መስቀል ድራር በአኹኑ ወቅት ሚልየነር የኾኑት፣ ያለተቆጪና ቀጪ እንደልባቸው የሚዝናኑት ሃይ ባይና ጠያቂ በሌለው በዚኽ ዓይነቱ መዋቅርና አሠራር ነው፡፡ ዘረፋው በሕዝብ ሀብት ላይ የሚፈጸም ወንጀል እስከኾነ ድረስ መንግሥትስ ለምን ጣልቃ አይገባም? መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም የሚለው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ኦርጂናል የትርጉም ፅንሰ ሐሳብ በዶግማው/በመሠረታዊው የሃይማኖት አስተምህሮ ነው፡፡

ዕዳ ይሰረዝ የሚለው ፕሮፖዛልም ብዙ ሕገ ወጥ ሰነዶችን ለማጥፋት እና በአየር ላይ የተበላው ገንዘብ እንዲወራረድ የተነደፈ መንገድ ነው እንጂ በዘመናዊው የሒሳብ አሠራር ስልት ያልተሰበሰቡ(receivables) የሚሰበሰቡበት መንገድ እኮ አለ፡፡ ለምን አይታይም? አይመረመርም? እኒኽ ልሙድ ቀሳጥያን ለ17 ዓመታት አብረው ሲሠሩ ከኖሩት ሥራ አስኪያጅ ጋር ዶልተው በሞያዊነትም በሥነ ምግባርም ከእነርሱ የተሻሉ ሓላፊዎችን በሕገ ወጥ ዝውውር እና በእግድ ከሀገረ ስብከቱ ያገለሏቸው፣ ይህን የሌብነት ተግባር ከሕግ እና ከአስተዳደር አግባብነት አኳያ በመመርመር ሊያጋልጡብን ይችላሉ ብለው በመገመት ሊኾን እንደሚችል ይታመናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ይፈርዳል ብለን እናምናለን፡፡

የሚመለከተው ክፍል፣ ተሰደብን ወይም ተዘለፍን በሚል እልክ ከመወጠር እና በቤተ ክርስቲያን ንብረትና ሀብት ላይ ቸልተኝነት ከማሳየት የጉዳዩን ትክክለኛነት መርምሮ በፍጥነት ሞያዊ እርማት መስጠት ይገባዋል እንላለን፡፡ ቸር ይግጠመን፡፡

ይቆየን፡፡

Advertisements

23 thoughts on “በአ/አበባ ሀ/ስብከት: ከብር 113 ሚልዮን በላይ የፈሰስ ዕዳ እንዲሰረዝ መጠየቁ እርምት ያስፈልገዋል፤ ‹‹የአየር ባየር የዘረፋ ስልቱን ለመሸፈን የተቀመረ ነው›› /ሠራተኞች/

 1. ታዛቢው June 11, 2015 at 7:59 am Reply

  (1)ምነው ከሀ/ስብከቱ መምሪያዎች ውስጥ 11ዱን አንድ አካባቢ ተወላጆች በተቆጣጠሩበት ወቅት ይሄን ጉድ ሳታወጡት? ወይስ ለምን ሳንጠግብ ተዘዋወርን ነው?

  (2)ሽግሽግ እንጅ ማግለል ስላልተካሄደ አሁንም አብዛኛዎቻችሁ በአስተዳደር ጉባኤ የመቀመጥ መብት ስላላችሁ ለምን በጉባኤው አንስታችሁ በማፍረጥረጥ የቤ/ክ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናችሁን አታሳዩንም??

  (3) እንዳላችሁት ይሰረዝ ተብሎ ቢሆን እንኳ የሚሰረዘው ለግለሰቦች ነው ወይስ ለአጥቢያ ቤ/ክ???

  (4)የጠቅላይ ቤተክሕነቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ይህን እዳ ለማስለመስ ኃላፊነት የለባቸውምን????

  (5)የየአጥቢያዎቹ ኃላፊዎች ኃላፊነትስ እስከ ምን ድረስ ነው?????የሰበካ ጉባኤ አባላትስ?????

  (6)የእነ ሊቀ አእላፍ ራቫ 4፣ የነዮናስ ሊፋን፣ የእነ ዳዊት ያሪስ አብሮ ይካተትልን እንጅ?????? የሣህለማርያም ግልባጭ የሌለውና መዝገብ ቤት የማያውቀው የአየር-ባየር ቅጥርስ??????

  (7)እውነት ይሄ ተሰብሳቢ እዳ(ፐርሰንት) የተከማቸው ትናንት የማነ ሥ/አስኪያጅ ሲሆን ነው???????

  (8)ከ1990ዎቹ ጀምሮ በአ/አ/ሀ/ስብከት በሊቀ ጳጳስ ደረጃ ስ/አስኪያጅነቱን የተፈራረቁበት እነ አቡነ ቄርሎስ፣ማትያስ ዘካናዳ፣እስጢፋኖስ(ሁለት ጊዜ)፣ቀውስጦስ፣ሕዝቅኤል፣ሳሙኤል፣ቀሌምንጦስ የሚሉት ይኖር ይሆን????????ተጠያቂነታቸውስ እስከምን ድረስ????????

  (9)ቤ/ክ ከሙዳየ-ምጽዋት ጥገኝነት ወጥታ ለምዕመናኖቿም የሚተርፉ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በኢኮኖሚ ራሷን ትቻል ብሎ መንቀሳቀስን ገና ለገና ‹‹ገንዘቡ ስለሚበላ ምንም ባይሰራ ይሻላል›› ወደሚል አዝማሚያ ማዘንበል ከእኛ ወገን ያልሆነ ሰው ለምን ስሙን በበጎ ያስነሳል አያስመስልባችሁም????????? ሌብነት ተፈርቶ ልማት ይታጎል?????????

  (10)በመንበሩ ባሳለፋችሁበት ጊዜ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለፈጸማችኋቸው ካሕናትን ያስለቀሱ እግድና ዝውውሮች፣ምዕመናን እና ሰ/ት/ቤቶችን እስካሁን ድረስ ላስሰለፉ ምዝበራዎች፣ተሸንሽነው ያላግባብ ለተከራዩ የቅድስት ቤ/ክ ይዞታዎች፣በጋዜጣና በብሎግ ላናፈሳችኋቸው ወገናዊና ፍጹም ዘረኛ አሉባልታዎች ንስሐ ገባችሁ ይሆን??????????

  ስለ እዳ ስረዛ ሌክቸር ልትሰጡን ሞከራችሁ፤ጣልቃ ገባብን እያላችሁ በየሰበቡ የምትከሱትንም መንግሥት ያለ ወትሮአችሁ ርዳታ ጠራችሁ፡፡ጥሩ ነው፡፡ግን የራሱን የመንግሥት ሚዲያም ተከታተሉ እስኪ፡፡የፌደራል ዋና ኦዲተር በየአመቱ ከሚያነሳቸውና አስፈጻሚውን ከሚያሸብሩ ሪፖርቶች አንዱ በብዛት ያልተወራረዱ ተሰብሳቢ ሂሳቦች መከማቸት ነው፡፡ስለዚህ እርዳታ የጠየቃችሁት አካል ችግሩ ሀገራዊ ጭምር መሆኑን ገልጾ ከማለፍ በቀር የምታዳንቁትን ያህል ጆሮ መስጠቱን እንጃ፡፡

  ደግሞም መንግሥትም ቢሆን ተሰብሳቢ ሂሳቦችን፣ግዴታዎችንና የይገባኛል ጥያቄዎችን(write-offs of receivables, obligations and claims) ከመ/ቤት የበላይ ኃላፊዎች እስከ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ድረስ በየደረጃው የሚሰርዝበት የሕግ አግባብ አለው እኮ፡፡

  እስኪ እናንተ ሁሉን አወቅ ናችሁና ባያሻችሁም ለአንባቢ ሕጉን እንጠቁም፡-(1)የኢፌዲሪ የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 648/200፣(2)የሚኒስተሮች ምክር ቤት ፋይናንስ አስተዳደር ደንብ ቁጥር 191/2002፣(3)በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ስለ ፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች የሂሳብ አያያዝ የወጣ መመሪያ ቁጥር 5/2003 ዝርዝር የእዳ ስረዛ ሥርዓታቱን ይነግራችኋልና ተወዳጅ ሐራውያን አንብቡት፡፡

  በተረፈ ሕሊናን ስለመጠቀም፣ሥራና ሰራተኛን ስለማገናኘት፣ከቸልተኝነት፣ከእልህ እና ከመወጣጠር ታቅቦ እርምት መውሰድ እንደሚገባ ያነሳችኋቸው ነጥቦች ተናጋሪውን ሳይሆን ንግግሩን አይቶ መወሰንም ስለሚገባ በእለት ተእለት አሰራር ተግባራዊ ቢደረጉ መልካም ነው፡፡‹‹ቄስ የሚናገረውን አድርግ፣ቄስ የሚሰራውን ግን አትስራ›› ይባል የለ ከነተረቱስ፡፡‹‹ሞረድ ለራሱ ቢዶለዱምም የዶለዶመ ቢላዋ ይስላል››፡፡ስለዚህ ምክራችሁ መልካም ነው ቢባል ችግር የለውም፡፡ እንዲህ የንስሐ ጊዜ ካገኘ ሰው የምትወጣ ምክር ታንጻለች!! ልብ ያለው ልብ ይበላት!!

  • ዳሞት June 11, 2015 at 3:54 pm Reply

   ለታዛቢው
   አቶ ታዛቢው፦ አንተም ውሻ በበላበት ይጮሃል ነውና ከዘራፊዎቹና አዘራፊዎች አንዱ ነህና ወገብህን ታጥቀህ ፤ ሽንጥህን ገትረህ መከራከርህና ዘጠኝ አይነት ዝርዝሮችን በመደርደር በማይሆን አካሔድና የመንግስት ህግ እንዲህ ይላል በማለት ማምለጫ መንገድ መፈለግ የሚጠበቅ ነው። ዘረፋው ትናንትም ተጀመረ ዛሬ ለዘረፋው መንሰራፋትና በቤተክርስቲያን የተጠላ አለማዊ አስተሳሰብና ተግባር የተንሰራፋው በዘረኝነት በሊቀ ጳጳስነት እየተሾሙ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንበር የተቀመጡት ለእምነት ሳይሆን ለፓለቲካ ትግበራ እንዲሁም ለእግዚአብሔር መንግስት ክብር ሳይሆን ለምድራዊና ዘረኛ ክብር የቆሙና የሚሰሩ በመሆናቸው ነው።

   እነዚህ ሳይገባቸው እስከ ወጨጌ ዘአክሱም በማዕረግ የተኮፈሱ ጳጳስ ተብየዎች የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከት የእነሱ ልዩ ሀገረ ስብከት አድርገው በጉልበት የያዙት ዘርፈው ለማዘረፍና መሰሎቻቸውን በሰማያዊ ሀብት የፅድቅ አክሊል ለማስዋብ ሳይሆን በምድራዊ ተድላና ደስታ በሀብት ማማ ሰቅለው ቁንጮ ቱጃር ለማድረግ ነው። ለዚህም ነው በቤተክርስቲያ ከልዩ ፀሐፊ ተብያቸው ጀምሮ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኗ ተቋማት ውስጥ መሰሎቻቸውን እያጨቁ ያሉት።

   ዘረፋው ዛሬ አይደለም ለምትለው ትናንትናም አባ ጳውሎስ ነበሩ የነበሩት እናንተም ነበራችሁ። እነንትናም ሥራ አሥኪያጅ ነበሩ ለምትለው የነበሩ ቢሆንም እንዳይሰሩ እንቅፋት እየሆናችሁና ጊዜ የሰጣችሁን በዘር የተደራጀ አባትና ልዩ ፀሐፊ ተብየዎችን ተጠቅማችሁ አሥለቀቃችሁት። ምን ይህ ብቻ ባለ መሳሪያዎችንም ተገን አድርጋችሁ እናሳስራችኋለን፣ እናስገርፋችኋለን እያላችሁም በማስፈራራት እንደፈለጋች በእግዚአብሔር ቤት ትፈነጫላችሁ።

   ስለህግ ተናግረሃል፤ ህጉ ለናንተ ዘረፋ ይከላከል እንደሆነ እንጂ ወረቀት ላይ ከመቀመጡ ውጭ ለፍትህና ወንጀለኞችን ለመቅጣት አይሰራም። ደግሞ በህጉም ስተቀልዱበት የናንተን አመፀኛነት ስታስፈፅሙበት አይተናል። እናም ታዛቢው ምናለ ትንሽ በሃይማኖት፣ በእግዚአብሔር መንግስት ዘረኝነት ቦታ የለውም ያስፈርዳልም ብለህ ትንሽ ወደ ህሊናህ ብታዘነብል። በውጭ ያሉት አባቶች ትናንት እናንተ ባላችሁበት ምድር ነበሩ። ነገ የናንተም ተራ ማንም ሳይነካችሁ በሰራችሁት ክፉ ስራችሁና ዘረፋችሁ ተደናግጣችሁ በስደት መቅበዝበዝ ይሆናል። ለዛውም በተሰደዳችሁበትም ከተጠያቂነት ከተረሳችሁ ነው።

   • ታዛቢው June 12, 2015 at 8:22 am

    ወንድም ዳሞት ላነሳሳሀቸው ነጥቦች በስሱ ልመልስልህ!በቅድሚያ ግን ከአነጋገርህ የተነሳ ስሜትህን ባልተገባ መንገድ በመግለጽህ ባልደሰትብህም ግዴለም ስለ ርትእት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ያለህን ቀናኢነት ላድንቅልህ!!አሁን ወደ ነጥቦችህ…

    (1)በአስተያየቴ የተነሳ የፈጠርክልኝን ቅጽሎች ልለፋቸው፡፡በሊቃነ ጳጳሳቱና በነፍሰ-ኄር አቡነ ጳውሎስ ላይ የሰነዝርካቸውን ነቀፌታዎችም ‹‹ኮናኒ ዘበጽድቅ–እውነተኛ ዳኛ›› የምንለው ክርስቶስ ፍርዱን ይስጥ ብየ ልተወው፡፡እሱ እንደ ብሎግና ፌስቡክ ያለተጨባጭ ማስረጃ በቡድን ሆታ አስቀድሞ ከወነጀለ በኋላ ስለንጹህነታችሁ ማስረጃ ካላቀረባችሁ የሚል ሳይሆን ‹‹አይቴ ነበርከ፤ምንተ ገበርከ›› ብሎ የፍጡሩን ድምጽና ማስረጃ ከሰማ በኋላ የሚፈርድ እውነተኛ ፈራጅ እንደሆነ አምናለሁ–በድንግል ልጅ አላፍርበትም!!

    (2)ወደ ሐሜታዎችህ ልለፍ፡-(ሀ)113 ሚሊዮን ብር ከየአጥቢያ አድባራትና ገዳማት ሊሰበሰብ የሚገባው ውዝፍ ፐርሰንት አለ ተባለ እንጅ ካሹ ገንዘብ በተጠቀሱት ግለሰቦች እጅ ስለመግባቱ ዘገባውም ያቀረበልን ነገር የለም፡፡(ለ)ይህ ብር ያልተሰበሰበው በኃላፊዎች ችግር ብቻ አይደለም–አሁን ከሳሽ መስለው ብቅ ያሉትን ጨምሮ የእነሱ ጥቅመኛነትና ቸልተኝነት ስለመኖሩ ጠቋሚ ማስረጃዎች ቢኖሩንም!ማለቴ፡- (1)ህንጻ-ቤ/ክ የጀመሩ አድባራት፣ገቢያቸው አነስተኛ የሆነ አድባራት፣በልዩ ልዩ ልማት የተጠመዱ አድባራትና ገዳማት ፐርሰንት ገቢ ለማድረግ የሚቸገሩበት አጋጣሚ ተደጋግሞ የሚታይ መሆኑን ቢያንስ በክሕነቱ የምንሳተፈው እና የሰበካ ጉባኤ ተወካይ ምዕመናን ያውቁታል፡፡(2)አሁን ይሰረዝ ሲባል የሚሰረዘው በማንና ለማን እንደሆነ የቀረበ ዝርዝር ነገር የለም፡፡(3)ፕሮፖዛሉ እውነት ከሆነ ግን ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 15 አመታት የተጠራቀመን የፐርሰንት እዳ አጥቢያዎች ካላወራረዱ ማለት የአድባራትን የስ/ማስኬጃና የካሕናትን ደመወዝ የመክፈል አቅም ሊፈታተን እንደሚችል ግልጽ ነው፡፡ከሕግ አንጻርም 10 አመት ያለፈው እዳ ብዙ ጊዜ በምሕረት ይታለፋል፡፡ስለዚህ እንደኔ ከ1997 ዓ.ም በፊት ያሉ የፐርሰንት እዳዎች ግልጽ በሆነ መልኩ በቋሚ ሲኖዶስ ወይም በቅ/ሲኖዶስ አቅጣጫ ተሰጥቶባቸው፣እንዲሁም በተደጋጋሚ ውዝፍ ፐርሰንት በማስቀረት የሚታሙ የአድባራት አለቆችና የቢሮ ሰራተኞች እርምጃ ተወስዶባቸው እዳው ለአድባራቱ ቢሰረዝ ደስታየ ነው!!አስተውል!!እዳው የደብሩ እንጅ የአስተዳደሪዎቹ አይደለም!!

    (3)አዲስ አበባ ሀ/ስብከት አንድ ብሔር ብቻ መፈንጫ እንደሆነ ማስመሰል አንድም ክፋት ነው፣አንድም ማስረጃ ማጣት ነው፣አንድም ማስረጃ ለማመሳከር ሰንፎ አእምሮን በፕሮፖጋንዳ የማሳጠብ(brainwash) ውጤት ነው፡፡ባለፉት 7 አመታ ውስጥ ጎጃሜው ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጨ(በጊዜው ምክትል የነበረውን የማነ እስከማገድ የደረሰ ገናና ሥልጣን ነበረው)፣ከትግራይ ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ(ባይዋጥላችሁም ሰይፍ ዘክልኤ የምንለው ጭርስ ያለ ሊቅ መሆኑን ልናገር)፣ከሸዋ አማራ መጋቤሐዲስ ይልማ፣ከኦሮሞ ሊቀ አእላፍ በላይ መኮነን አ/አ/ሀ/ስብከትን በስ/አስኪያጅነት መርተዋል፡፡የጳጳሳት ተዋጽኦም ቢሆን ምስጋና ለአቡነ ጳውሎስ ይሁንና በተቻለ መጠን የፌደራሊዝሙን አወቃቀር ተከትሎ የመጣውን ‹‹ኦርቶዶክስ የነፍጠኛ ሃይማኖት›› የሚል መርዘኛ ቅስቀሳ ለመቋቋም ከየብሔረሰቡ የአካባቢውን ቋንቋ ተናጋሪ ቆሞሳትን ለመዐርገ-ጵጵስና ለማብቃት አስመስጋኝ ጥረት ተደርጓል፡፡ዘፈተወ ይርዐይ!!እሱ አካሄድ ትክክል አልነበረም ካላችሁ የእናንተን የተሻለ ፕሮፖዛል አሳዩን፡፡

    (4)ዘመናዊ ትምህርት የተማረ ሲሾም ‹‹መንፈሳዊ አያውቅም››፤መንፈሳዊ የተማረ ሲቀመጥ ‹‹ኤቢሲዲ አልቆጠረም›› እያላችሁ ስብጥሩን እንደማገዝና የተሻለ ተቋም እንዲኖረን ከመስራት ይልቅ ጅምሩን ሁሉ በግብፅ ሚዛን እያነሱ ማጣጣል ‹‹አባቱን አያውቅ፤አያቱን ይናፍቅ!!›› ያስተርታል፡፡አባታችን አቡነ ሺኖዳ ከሰ/ት/ቤት ተነስተው ፓ/ክ ስለሆኑ እኛም የግድ መሆን አለብን እያሉ መፈክር ከማስቀደም አቡነ ሺኖዳ ያለፉበትን መንገድ፣ዛሬ የእኛ ሰ/ት/ቤቶች ያሉበትን አቋም፣በኢኦተቤክ የሚሰጡ የአብነት የት/ት አይነቶች ከግብጻውያን የሚለዩበትን ባሕርይ መመርመር ይቅደም!!መመዘኛው 20 እና 30 አመት በሰ/ት/ቤት አገልግሎት አሳለፍን የሚለው ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዷ የአገልግሎት አመት ምን እውቀት፣ግብረ-ገብነት እና ለቤ/ክ የተቃና አስተዳደር አበረከትን የሚለው ጭምር ነው፡፡

    (5) ‹‹ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማት›› የሚለውን መዐርግ በሚመለከት እባክህን ከ1960ዎቹ ጀምሮ ያሉትንና በተከታታይ በየዘመናቱ የተሸሻሉትን ቃለ-ዓዋዲዎች እያቸው!!ሁሉም የፓትርያርኩ መዐርግ ወዕጨጌ ዘመንበ ተክለሃይማኖት የሚል ቅጽል ያለበት መሆኑን ይነግሩሀል፡፡ቃለ-ዓዋዲ አንቀጽ 52 ተመልከት!!የአ/አ/ሀ/ስብከት ከቀደምት ፓትርያርኮች ጀምሮ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሀ/ስብከት ነው፡፡ዛሬ ማትያስ ሲሰየሙ፣ወይም ትናንት ለአቡነ ጳውሎስ ተብሎ የተደነገገ አይደለም፡፡ቅ/ሲኖዶሱ ባለፈው ጥቅምት ባደረገው ጉባኤም በግልጽ የአ/አ/ሀ/ስብከት የቅዱስ ፓትርያርኩ ሀ/ስብከት እንደሆነ ደንግጓል፡፡

    (6)በአጠቃላይ በቤ/ክ አስተዳደር ዙሪያ ችግር መኖሩን ሁላችንም እናምናለን፡፡ችግሩ የአንድ ወገን፣የአንድ ፖለቲካ ቡድንና የአንድ አካባቢ ተወላጆች ብቻ እንደሆነ ማስመሰል ግን ትክክል አይመስለኝም፡፡ይብዛም ያነስም፣በማወቅም ባለማወቅም፣በአውቆ አጥፊነትም በቸልተኝነትም ሁላችንም ድርሻ አለን፡፡የችግሩን መኖርና የየራሳችንን ድክመት አጥርተን መነሳቱ ነው የሚበጀን፡፡የተደረገውን አመስግነን፣የተጓደለውን ነቅፈን፣መሆን ያለበትን አመላክተን እርስ በርሳችን ካሕን ከምዕመን ተባብረን ብንነሳ መልካም ነው፡፡እስካሁን እየሆነ እንዳለው የየራሳችንን ቡድናዊነት ሸፍነን አበሳውን ሁሉ አንድ አካል ላይ ጭነን የምንዘምት ከሆነ ግን ‹‹ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ›› ተረቱ ይቀጥላል!!በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙኃንን ወደ ‹‹መለያያ ብዙኃንነት›› ባንቀይራቸው ጥሩ ነው!!

    ስንንዛዛባት ለምትችለኝ ሐራ ይሄው–ምስጋና!!!

  • Anonymous June 12, 2015 at 6:09 am Reply

   (1)ምነው ከሀ/ስብከቱ መምሪያዎች ውስጥ 11ዱን አንድ አካባቢ ተወላጆች በተቆጣጠሩበት ወቅት ይሄን ጉድ ሳታወጡት? ወይስ ለምን ሳንጠግብ ተዘዋወርን ነው? መልስ እባክህ አንተ ሰው አሁንም ቀልዱን ተውና ለእናት ቤተክርስቲያናችን እናስብ፡፡

   (2)ሽግሽግ እንጅ ማግለል ስላልተካሄደ አሁንም አብዛኛዎቻችሁ በአስተዳደር ጉባኤ የመቀመጥ መብት ስላላችሁ ለምን በጉባኤው አንስታችሁ በማፍረጥረጥ የቤ/ክ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናችሁን አታሳዩንም? መልስ አየህ ይህ ነው የአንተ አለማወቅ የተገለጸበት አስተያየትህ ንቡረ ዕድ ኤልያስ ባለበት አቶ የማነ በተቀመጠበት ልባው መናፍቅ አዕመረ አድፍጦ ለመብላጥ በሚጠባበቅበት ጉባኤ ማን ሊሰማ ማን ሊበላ ?

   (3) እንዳላችሁት ይሰረዝ ተብሎ ቢሆን እንኳ የሚሰረዘው ለግለሰቦች ነው ወይስ ለአጥቢያ ቤ/ክ? መልስ መች ለቤ/ክ ሆነና አብያተ ክርስቲያናቱ እኮ ከፍለናል ነው እያሉ ያሉት እዳ የለብንም ብለዋል ለቅዱስ ፓትርያርክ ጽ/ቤትም አስታውቀዋል ብሩ ግን ስላልገባ ይሰረዝ የሚለው ጥያቄ እኮ ሰነድ ላማጥፋት ነው ብሩማ በአየር ላይ ተበልቶአል አይገባህም እንዴ?

   (4)የጠቅላይ ቤተክሕነቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ይህን እዳ ለማስለመስ ኃላፊነት የለባቸውምን???? መልስ እንተ ሰውዬ ታመሃል ፓትርያርኩ እኮ የኔ የግል ካንፓኒዬ ነው ብለዋል በአሁኑ ወቅት የአ.አ ሀ/ስ ከጠቅላይ ቤተክህነት ጋር ያለው መዋቅራዊ አደረጃጀት ተበጥሶአል አቶ የማነም እራሱን በማደራጀት የሀ/ስቱን የብዝበዛ ስልት ከጅቡ ንቡረ ዕድ ጋር ዕያዋከቡት ነው ስለዚህ አቡነ ማቴዎስ ምን አቅም አላቸው ሲኖዶሱም ዝም አለ ይገርማል በትንሹ ተግባብተናል አይዶዶል

   (5)የየአጥቢያዎቹ ኃላፊዎች ኃላፊነትስ እስከ ምን ድረስ ነው?????የሰበካ ጉባኤ አባላትስ????? መልስ እዚህ ጋር ልናገር አንድ የሰበካ ጉባኤ አባል 8 ሚሊን ብር እዳ አለባችሁ ሲባል ጠየቀ ደብሩም ከፍለናል አለ ስለዚህ የወጣብን የእዳ ሰነድ ትክክል ስላልሆነ ሊቀ ጠባቡን ማረጋገጫ ሰነድ ይሰጠን ከፍለናል አለ ምን አይነት ብሎ ሊ ጠባቡ ጠየቀው በዙ ቀን ዕዳ አለባቸው ተብሎ የቀረበው ሪፖርት በስህተት ስለሆነ እነሱ ሰነዳቸው ሲመረመር መክፈላቸው ተረጋግጧል የሚል ነዋ አለው በዚህ ወቅት ሊቀ ጠባቡ አፉን ልክ እንደ አህያ አፍ ድስት በማስመሰል ፉፉፉ ካለው በኃላ ፍ/በት ክሰስ አለው ምዕመኑም አዝኖ እንግዲህ ጠያቂ ካለ በሰነድ እናስረዳለን ብሎ ተመለሰ ጠያቂም የለ……… ገባህ?

   (6)የእነ ሊቀ አእላፍ ራቫ 4፣ የነዮናስ ሊፋን፣ የእነ ዳዊት ያሪስ አብሮ ይካተትልን እንጅ?????? የሣህለማርያም ግልባጭ የሌለውና መዝገብ ቤት የማያውቀው የአየር-ባየር ቅጥርስ?????? መልስ ከሰነፍ ጋር ማውራት ልብ ድካም ያመጣል አሉ ፕሮ. አስራት የማታውቀውን ተናገርኽ ምሁር አይደለህ እንዴ?? በመረጃ አስደግፈው ያወሩልህን ነገር እንደ ጨዋ አትናገር እንጂ አንተ ስታወራ ልቅ አፍ ይሉሀል እኮ እራሳቸው የነገሩህ ይስቁብሃል እራሳቸው ነገሩ……….

   (7)እውነት ይሄ ተሰብሳቢ እዳ(ፐርሰንት) የተከማቸው ትናንት የማነ ሥ/አስኪያጅ ሲሆን ነው???????መልስ ምን ማለትህ ነው አራዳ ጊዮርጊስን አታውቀውም እንዴ 175 ሚሊን ብር እኮ ተበልቶአል ይህንን እኮ ገ/መስቀል በቁጥጥር ስም ለማድበስበስ ትዝዛዝ ተሰጥቶታል የለውጡ ነጻ አውጪ ደግሞ በደንብ ያውቀዋል፡፡ ይህ እኮ በነገሬ ላይ ላሳስብህ የምወደው ነገር አለኝ ይህ ተጨባጭ መረጃ ነው መረጃ እንደተገኘ ደግሞ ማጣራትና መስራት ነው ምሁሩ የማነ በሙህራን ተከቦ የለ እራሱም ጊዮርጊስ እዳውን ከፍሏል ብሎ በዛ ልክ በሌለው የአስተዳደር ጉባኤ ላይ ደንፍቶኣል ይቅርታ የማነ እነዛስ በአንተ ህገወጥ ድርጊት የተዘዋወሩት ተገላግለዋል እና የፈረደብን አልቻልንህም እባክህ ሸምቀቅ በል ታወራለህ ይዘትህን ትለቃለህ ጆሮአችንን አታምግለው በጥቂት ተናገር ሊቀ ጉባኤ የሚባሉት አንድ አባል ይህ ሰው እንዴት ያወራል አይደክመውም የተቀረጸ ቴፕ ነው እኮ የሚመስለው ነጠብ የለውም አሉ ኡኡኡ…. አታውራ..

   (8)ከ1990ዎቹ ጀምሮ በአ/አ/ሀ/ስብከት በሊቀ ጳጳስ ደረጃ ስ/አስኪያጅነቱን የተፈራረቁበት እነ አቡነ ቄርሎስ፣ማትያስ ዘካናዳ፣እስጢፋኖስ(ሁለት ጊዜ)፣ቀውስጦስ፣ሕዝቅኤል፣ሳሙኤል፣ቀሌምንጦስ የሚሉት ይኖር ይሆን????????ተጠያቂነታቸውስ እስከምን ድረስ????????መልስ በዚህ ላይ ትንሽ የዋህ ትመስላለህ ጽድቁን ትቶ በቅጡ በኮነነኝ አለ ያገ….ሰው አሁን ያለውን ይስሩ እስኪ ተወው…..

   (9)ቤ/ክ ከሙዳየ-ምጽዋት ጥገኝነት ወጥታ ለምዕመናኖቿም የሚተርፉ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በኢኮኖሚ ራሷን ትቻል ብሎ መንቀሳቀስን ገና ለገና ‹‹ገንዘቡ ስለሚበላ ምንም ባይሰራ ይሻላል›› ወደሚል አዝማሚያ ማዘንበል ከእኛ ወገን ያልሆነ ሰው ለምን ስሙን በበጎ ያስነሳል አያስመስልባችሁም????????? ሌብነት ተፈርቶ ልማት ይታጎል?????????መልስ ልማት በትክክል በተጠናና በታወቀ እንዲሁም ደረጃውን ጠብቆ በተፈቀደ ጉዳይ ላይ ነው ለምን ትንቁታላችሁ አባቶቻችን ቃለ አዋዲ ሕገ ቤተክ/ያን ሰርተዋል አንብበው በአሁኑ ወቅት እኮ ከቃለ አዋዲውና ከሕገ ቤተክ/ያኑ ይልቅ ንቡረ ዕድ ኤልያስ እስክንድር ደስታ የማነ ክፍት አፉ ሃይሌ መንክራት የሚፈሩት ሲኖዶሱ ውስጥ ያሉት አባላትም የሚፈሩአቸው እነዚን ነው ገባህ ጊዜው ልቅ ሆኖአል ተቆጣጣሪና ተቆጪ አቷል አታድክመኝ እባክህ.

   (10)በመንበሩ ባሳለፋችሁበት ጊዜ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለፈጸማችኋቸው ካሕናትን ያስለቀሱ እግድና ዝውውሮች፣ምዕመናን እና ሰ/ት/ቤቶችን እስካሁን ድረስ ላስሰለፉ ምዝበራዎች፣ተሸንሽነው ያላግባብ ለተከራዩ የቅድስት ቤ/ክ ይዞታዎች፣በጋዜጣና በብሎግ ላናፈሳችኋቸው ወገናዊና ፍጹም ዘረኛ አሉባልታዎች ንስሐ ገባችሁ ይሆን??????????መልስ በቃ ደካማ ነህ ጥቁር ድንጋይ አታናደኝ እንዲህ ከሆነ አልነግርህም

   ስለ እዳ ስረዛ ሌክቸር ልትሰጡን ሞከራችሁ፤ጣልቃ ገባብን እያላችሁ በየሰበቡ የምትከሱትንም መንግሥት ያለ ወትሮአችሁ ርዳታ ጠራችሁ፡፡ጥሩ ነው፡፡ግን የራሱን የመንግሥት ሚዲያም ተከታተሉ እስኪ፡፡የፌደራል ዋና ኦዲተር በየአመቱ ከሚያነሳቸውና አስፈጻሚውን ከሚያሸብሩ ሪፖርቶች አንዱ በብዛት ያልተወራረዱ ተሰብሳቢ ሂሳቦች መከማቸት ነው፡፡ስለዚህ እርዳታ የጠየቃችሁት አካል ችግሩ ሀገራዊ ጭምር መሆኑን ገልጾ ከማለፍ በቀር የምታዳንቁትን ያህል ጆሮ መስጠቱን እንጃ፡፡ መልስ ይህ እኮ ልተሰበሰበ ነው ደንቆሮ ይቅርታ ደደብ እያልን ያለነው እኮ ተሰብስቦ በአየር ላይ ተበልቷል ነው ገንዘቡ ከተሰበሰበ የት ገባ ነው ምክንያቱም ደብሮቱ ከፍለናል ያታይልን እያሉ ነው እባክህ እያወቅክ እንደዚህ አትሁን

   ደግሞም መንግሥትም ቢሆን ተሰብሳቢ ሂሳቦችን፣ግዴታዎችንና የይገባኛል ጥያቄዎችን(write-offs of receivables, obligations and claims) ከመ/ቤት የበላይ ኃላፊዎች እስከ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ድረስ በየደረጃው የሚሰርዝበት የሕግ አግባብ አለው እኮ፡፡ መልስ አሁን ገና ማን እንደሆንህ አወቁኽ አንተ እኮ ቅዱስ ፓትርያሪኩ በአለ ሲመታቸውን እያከበሩ ባለበት ወቅት ቢሮህን ከፍተህ አንድ ሹሮ ቤት እራስ መኮንን ድልድይ ጋር ያላትን ሴት ይዘህ ስታደርግ የነበረውን ነገር ተደርሶብሃል ለመንግስት የቀረብክ ትመስላለህ ነገር ግን ከኣላው እርቀሃል ዱሮም የጋዜታ እውቀት መለቃቀም ነው፡፡ በል ተወው ያ እኮ ሌላ ዳይሜንሽን/ማእዘን ነው ዱሮም የመጣሁት የመንግስትን ዓላማ ለማስፈጸም ነው በማለት እጭቸርብረሃል በእኔ ጉዳይ ወንድ ከሆኑ ሲኖዶስም ያንሳ አሳፍሳለው ያልክ ጀግና እኔ እኮ ቁም ነገረኛ መስለኸኝ….. ለማን ነው የሚሰረዘው ለኤልያስና ለአንተ ወይም የሌብነት ሼሮቻቸው ..ቂቂቂ…

   እስኪ እናንተ ሁሉን አወቅ ናችሁና ባያሻችሁም ለአንባቢ ሕጉን እንጠቁም፡-(1)የኢፌዲሪ የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 648/200፣(2)የሚኒስተሮች ምክር ቤት ፋይናንስ አስተዳደር ደንብ ቁጥር 191/2002፣(3)በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ስለ ፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች የሂሳብ አያያዝ የወጣ መመሪያ ቁጥር 5/2003 ዝርዝር የእዳ ስረዛ ሥርዓታቱን ይነግራችኋልና ተወዳጅ ሐራውያን አንብቡት፡፡ መልስ ኸረ በሕግ አምላክ ይበቃሃል ደንቆሮ ነህ ይቅርታ አብደሃል ለካ

   በተረፈ ሕሊናን ስለመጠቀም፣ሥራና ሰራተኛን ስለማገናኘት፣ከቸልተኝነት፣ከእልህ እና ከመወጣጠር ታቅቦ እርምት መውሰድ እንደሚገባ ያነሳችኋቸው ነጥቦች ተናጋሪውን ሳይሆን ንግግሩን አይቶ መወሰንም ስለሚገባ በእለት ተእለት አሰራር ተግባራዊ ቢደረጉ መልካም ነው፡፡‹‹ቄስ የሚናገረውን አድርግ፣ቄስ የሚሰራውን ግን አትስራ›› ይባል የለ ከነተረቱስ፡፡‹‹ሞረድ ለራሱ ቢዶለዱምም የዶለዶመ ቢላዋ ይስላል››፡፡ስለዚህ ምክራችሁ መልካም ነው ቢባል ችግር የለውም፡፡ እንዲህ የንስሐ ጊዜ ካገኘ ሰው የምትወጣ ምክር ታንጻለች!! ልብ ያለው ልብ ይበላት!!

 2. Anonymous June 11, 2015 at 9:22 am Reply

  ለዚኽም የቁጥጥር ክፍል ሓላፊው ባለቤት የኾኑት ወ/ሮ የባሕር ሙዝ ገብረ ሚካኤል ተመራጯ ሚሽን አስፈጻሚ ናቸው፡፡ መቼስ ከክፍለ ከተማ ወደ ዋናው ጽ/ቤት በዝውውር የመጡት በተለየ የሞያ ብቃት ሀገረ ስብከቱን ይረዳሉ ተብሎ ሳይኾን ለዚኹ ተግባር ተመልምለው እንደኾነ ይታመናል፡፡

 3. sim June 11, 2015 at 9:59 am Reply

  የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከት ከፓትርያሪኩ ልዩ ሀገረ ስብከትነት ማንሳት እና ተጠያቂነት ባለበት መልኩ
  ሊደራጅ ያስፈልጋል፡፡ እሳቸዉ ናቸዉ ዘመዶቻቸዉን ሰብስበዉ ከለላ በመስጠትና በመሾም ኀፍረት እና ትንሽ እነኩዋ መንፈሳዊነት በሌላቸዉ ማፈያዎች የቤተክርስቲያናችንን ሀብት የሚያዘርፉት፤ ቅዱስ ሲኖዶስም ለዚህ ዝርፊያ አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጥ ያስፈልጋል፡፡ ቤተክርስቲያናችንን ከእንደዚህ አይነት መንፈሳዊ ዝቅጠት እንታደጋት! ሀራዎችም በርቱ

 4. sim June 11, 2015 at 10:01 am Reply

  ‹‹ንቡረ እድ ኤልያስን የተማመነ ምን ይኾናል››iiiiii

 5. Anonymous June 11, 2015 at 12:26 pm Reply

  የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ የማነ በ02/10/2007ዓ.ም ከደመዛቸው ጋር የማይመጣጠን ሀብት ስላላቸው የደብር አስተዳዳሪዎች የሀብት ምንጫቸው እንዲጣራ በሰ/ት/ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ የሚከተለውን ተናገሩ፡፡ እኔ በግሌ ካህን ሌባ ነው ብዬ አላምንም ደግሞም ሁሉም ካህናት መኪና ቢኖራቸው ደስ ይለኛል፡፡ የተሰረቀም ካለ ከአሁን በኃላ ተጨማሪ እንዳይዘረፍ ተከታተሉ ሲሉ መልሰዋል፡፡ ይህ ምላሻቸው እንዴት ይታያል ሃራ ተዋህዶ

 6. mimi semiret June 11, 2015 at 2:11 pm Reply

  ምዕመኑ ለእግዚአብሔር ሰጥቷል እግዚአብሔርም ተቀብሏል!!!!!እነ……. ግን እግዚአብሔር ይፋረዳቸዋል ደግሞ ሩቅ አይደለም።

 7. Anonymous June 11, 2015 at 2:47 pm Reply

  Geta woye erdan!

 8. danawit June 11, 2015 at 3:01 pm Reply

  የዚህ ድህረ ገፅ ተከታታይ ነኝ ይህን አስገራሚ ፅሁፍ ጨምሮ ሌሎች አስደንጋጭ መረጃዎችን ከዚህ ድህረ ገፅ አንብቢያለው። የኔ መሠረታዊ ጥያቄ ግን መረጃዎችን ብቻ ማወቅ ምንድን ነው የሚፈይደው? ከላይ የተገለፁት ግለሠብ ከገንዘብ ምዝበራ ባለፍ የሚተገብሩት ባድ አምልኮ ከቤተክርስቲያኒቱ ክብር እና አስተምሮ በጅጉ የተቃረነ ነው። ለዚህ ሁሉ አሣፍሪ ክስተት ጠየቂስ አለው?ተጠያቂውስ ማን ሊሆን ነው?ይህን ተከትሎ ሀገረ ስብከቱ እንዲሁም ጠቅላይ ቤተክነቱ የት ነው?የዚህ ሁሉ ብልሹ እና ወራዳ አሠራር ተሳታፊ ነው?አሳቢ አካል ነኝ ባይስ አለ?ወይስ በሀገረ ስብከቱ እና በጠቅላይ ቤተክነት ያለው ሠው ሁሉ እንደ ህንፃው ግውዝ ነው።

 9. dagi June 11, 2015 at 3:09 pm Reply

  there will be a time for justice. ..

 10. ዳና June 11, 2015 at 4:10 pm Reply

  የድህረ ገፁ ተከታታይ ነኝ ይህን አስገራሚ ፅሁፍ ጨምሮ ሌሎች አስደንጋጭ መረጃዎችን ከዚህ ድህረ ገፅ አንብቢያለው። የኔ መሠረታዊ ጥያቄ ግን መረጃዎችን ብቻ ማወቅ ምንድን ነው የሚፈይደው? ከላይ የተገለፁት ግለሠብ ከገንዘብ ምዝበራ ባለፍ የሚተገብሩት ባድ አምልኮ ከቤተክርስቲያኒቱ ክብር እና አስተምሮ በጅጉ የተቃረነ ነው። ለዚህ ሁሉ አሣፍሪ ክስተት ጠየቂስ አለው?ተጠያቂውስ ማን ሊሆን ነው?ይህን ተከትሎ ሀገረ ስብከቱ እንዲሁም ጠቅላይ ቤተክነቱ የት ነው?የዚህ ሁሉ ብልሹ እና ወራዳ አሠራር ተሳታፊ ነው?አሳቢ አካል ነኝ ባይስ አለ?ወይስ በሀገረ ስብከቱ እና በጠቅላይ ቤተክነት ያለው ሠው ሁሉ እንደ ህንፃው ግውዝ ነው።

 11. anonymous June 11, 2015 at 7:26 pm Reply

  Dear Mr, Elias
  We knew you very well . You are utterly stupid and you have stolen so much money from our mother church! I haven’t seen Such a corrupted man like you! You are a racist & a magician! You don’t believe in God. You are an instrument Of Devil. MODERN thief Yemane I have a question for you how much money you stole from Mela hospital? You don’t represent TPLF or Tigray! ! Hello Gebremeskel who bought a car for your wife/Yebahermuz /? ?? Are you a business man? Hahaha
  Please stop stealing money from the church!

 12. biruk June 12, 2015 at 6:17 am Reply

  Berekete Egeziahehre kenante gare yehune yemetesetunene merega eyetetekemenebache new

 13. Anonymous June 12, 2015 at 10:29 am Reply

  ER YGRMAL !!!! LKE TEBABU. LKE MESRI ! BETE KIRSTYAN NESA YMTWTABT KEN MECH YON GTA ?

 14. a met. addis June 12, 2015 at 11:19 am Reply

  It is good fun but why you forget the best courapted workers of the diocese so if forgot them God forgot you for ever ,Tadewos. Dawit. mamuye. Yemadogow lij Besime Asadagiwe Dawit yaraed 1 yenigdina 1 yegir mekinoch ZEMENAWI BET BBOLE KETEMA. ZEMENAWI CONDOMINIYEM BBIR 800000.OO Yegezazebet misitir Ende Abatu Enchet we is Ende Enatu kubet shito new ? mamuye bad is ababa ketema for yeseraw keye am tito new gin Yelebochu yen anten mahbere degafi Yehone hull Leba bihonm leba aybalm menafik honom menaifik aybalm Drones bihon Le poetics enj mech lekirstina temeseretachihuna Timotaleh inji webber aygegm Levan Lebanon biserkew minyidenkew? kkkkk kenante belay Levana zeregna yelem.

  Tsehafewum, yalekew kale Egziabhr Endayferdibih gin beegziabhr atamnim enj Thegurihn asadigeh yehatiat tsihuf kemitsif made never big gin MAK Keketerach Yewedefitu Tesfegnoch ante silhonk min yidereg .kkkkk
  ya

 15. Anonymous June 12, 2015 at 5:51 pm Reply

  የሀገረ ስብከቱ የሂሳብ ክፍል ቦታ እኮ “ሰው ተገሎበት” በድጋሚ የተገኘ ነው፣ ግሮሰሪ እና ባለ አምስት ፎቅ ህንፃ ሲያንስ ነው፣ ገና ምን አይታችሁ……ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ

 16. ዳሞት June 13, 2015 at 10:38 pm Reply

  ለታዛቢው
  የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ! እኔም ታዘብኩህ።

  በመጀመሪያ ስሜቴን አይደለም ያንፀባረቅሁት እውነታውን እንጂ። አንተ የራስህ የሆነ ተልኮ ስላለህ አገር ያወቀውን ፀሐይ የሞቀውን እውነታ ለመካድ እንዲሁም ለመሸፋፈንና ላለመቀበል መፈለግ ስሜታዊነት ሊሆን ይችላል።

  በቤተክርስቲያኗ መንበር ላይ የነበሩትና በህይወት የሌሉትን ሊቀ ጳጳስ በተመለከተ የድንግል ልጅ ይፈርዳል እኔ አላፍርበትም ትላለህ። አዎ! ፍርዱ በቀኝ በግራ ማቆሙ የእግዚአብሔር ነው። እኔም ፍርድ የተናገርኩ አይመስለኝም ። በህይወት በነበሩበት ጊዜ የሰሩትን ስህተት መደበቅ ግን አይቻልም። ድሀ ሲበደል ፍርድ ሲጓደል፤ ሀይማኖት ሲበረዝ፤ አባቶች ሲደበደቡ፤ ቤተክርስቲያን ቅጥሯ በልማት ሰበብ ሲፈርስ፤ ካህናትና ምእመናን በሰይፍ ሲመተሩ፤ በአውደምህረትና በበዓላት ንግስ ብዙ ግፍ ሲሰራ ለምን ያላሉ እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የብዙ ግፎች ተባባሪ መሆናቸውን ምነው ዘነጋኸው። የቅዱስ ሲኖዶስ ክብርና ህግጋት እየተረገጡ አምባገነናዊነትና ነውረኛ
  አስተሳሰቦች ስጋ ለባሽን ጋሻ በማድረግ መፈፀማቸውን ይዘነጋል እንዴ።
  አሁን ያሉትስ አባት የተናገሩትን የዘነጉ ለፓለቲካ ፍጆታና ለዘረኝነት የተጠቁ አይደሉምን?የቤተክርስቲያኗን ቅዱስ ሲኖዶስ ያዋረዱ በዘፈቀደ ከቋንቋ ተጋሪዎቻቸው የመጣላቸውን የሚሰሙና ሹም ሽረት የሚያደርጉ አይደሉምን? ትናንት እኮ ነው አባቶችን እየሰደቡ የደረቡት ካባና የጫኑትን ቆብ እንሿን በመንፈሳዊ ቦታ መሆናቸውን ሊደብቅላቸው በማይችል ሁኔታ አልሸባብ አልቃይዳ እያሉ
  ንፁሐንን ለማሳረድ የተናገሩት በቀኖና መቀጣታቸውን ተግባራዊ እንዳይሆን ያገዱት? እረ ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ነው ብለዋልም። ይህ ሐሰተኛ ክስና ስድብ እንዲሁም አባቶች ጳጳሳትን ከፈለጉ መሄድ ይችላሉ እያሉ መዝለፍ ዲሞክራሲያዊ መብት ከተባለ ነገ ደግሞ የቤተክርስቲያኗ እምነትና አስተምሮ እንዲሁም ስረርዓት ያልሆነም ቢንፀባረቅ ዲሞክራሲ ነው እንዳይባል ያስፈራል።
  ትናንት የእምነታቸው ስርዓት መፈፀሚያ እንዳይነካ ብለው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የባህር ዳር ከተማ ክርስቲያኖች የተፈፀመው አይዘነጋም። ታዲያ የነሱስ
  ዲሞክራሲያዊ መብት የላቸውምን? ብዙ አሳዛኝ ነገሮችን
  አይተናል ሰምተናል ግን እንተወውና አንተን ወደ ታዘብኩበት ልሂድ።
  አንተ ገንዘብ ተዘርፏል መባሉና የተዘረፈውን ገንዘብ ተጠያቂነትን ለማጥፋት ነው ለአድባራቱ ያልከፈሉት ይሰረዝ የተባለው መባሉ ለምን አስከፋህ?ለቤተክርስቲያንና ለንብረት ገንዘቧ የምትቆረቆር ቢሆን ኖሮ የአንድባራቱ ገንዘብ የት እንደገባ ሳይታወቅና አጥፊና ዘራፊዎች
  ሳይታወቁ በአቋራጭ እዳው ይሰረዝ መባሉን በተቃወምህ ነበር።
  እዳው ይሰረዝ ቢባልም የሚሰረዘው ለአድባራቱ ነው ትላለህ። አድባራቱ በሉት አባከነቱ? አድባራቱ እዳው ካልተሰረዘላቸውስ ሊሸጡ ይሆንን? ካህን ነኝ ብለሃል፤ ካህንነትህ በጨለምተኛነትና በዘር አድሎ ሐሰተኛ ፍርድ መስጠት ነውን?የብሉይ ኪዳኖቹ እነ ቀያፋስ ካደረጉት ምን ተለያችሁ?
  በህንፃ በልማት ተጠምደው ትላለህ። ቤተክርስቲያንን ግን ከልመና አላወጣትም። ምክንያቱም የህንፃውንም የልማቱንም ገቢ የሚበላው በይሁዳ አይምሮ የሚያስቡት ሆዳቸው አምላካቸው ሀሳባቸው ምድራዊ የሆኑት አማሳኞች ናቸው። ታዲያ እንዴት በልማትና ህንፃ
  ግንባታ ስም ይህ ሁሉ ዘረፋ? ለመንግስተሰማየ
  ለእግዚአብሔር ክብር ነውን? መልሱን ለአንተው ትቻለሁ።
  ሌላው የአንድ ዘር ችግር አይደለም ለማለት ይመስላል ከጎጃም እንትና፣ ከኦሮሞ እንትና፣ ከሽዋ እንትና መርተዋል ትላለህ። አይ ካህን ዛሬ እኮ አይደለም ወጣት አዛውንት ህፃናትኔም ማታለል በዚህ መንገድ አይቻልም። መሾማቸውን አወራህ እንጂ ሥራቸውን ተገቢው መንገድ እንዳይሰሩ የተደረጉባቸውን ቢሮክራሲና ዛቻዎች አልጠቀስክም።
  በቤተክርስቲያን የዘር ተዋጽኦ የተናገርከው ምናልባት ለኔ ከስጋ አስተሳሰብ አንፃር ትክክል ልትሆን ትችላለህ ተጣጥሞ ከሆነ። ከመንፈሳዊ እይታ በወንጌልም በአውደ ምህረት እንደተማርነው ከሆነ ትክክል ነው ለማለት በግሌ ይቸግረኛል። በክርስቶስ ቤት የሮም የግሪክ ወይም ባሪያ ጭዋ የሚባል ነገር የለም። ምክንያቱም መንፈሳዊነቱና ለእግዚአብሔር ያለው አገልግሎቱ እንጂ መመዘኛው የዘር ተዋፅኦ ከሆነ ምድራዊ ስጋዊ አስተሳሰብ ሰማያዊ ዋጋ የሌለው ነው። ገና ለገና የዘር ተዋፅኦ አሟላለሁና የክፉዎችን ክስና ትችት ሽሽት በእምነት ስርዓቷ ያልጠነከሩና ለሹመት ያልበቁትን ሁሉ መሾም ቤተክርስቲያንን ማዳከምና እንዲህ አሁን ለሚታየው ዘረኛነትና ዘርን ተገን አድርጎ ታላላቆችን ሳይቀር በዛቻ ማስፈራራትና በዋልጌዎች ቋንቋ ለመሳደብ ይዳርጋል፣ ሆኗልም እየሆነም ነው። መቸም ክፉ ምክንያተኛ ነውና ይህ ድሮ የመጣ ጣጣ ነው እንዳትል። እኔ እንዲህ አይን ያወጣ ያውም የሁሉም አባት ተብለው ከተሾሙት ሳይቀር የተጨማለቀ ዘረኝነት ከዚህ ዘመን ውጭ ሰምቸ
  አላውቅም። ደግሞ የሚገርመው ሀይማኖት እንድትፀናና እንድትሰፋ ቢሰሩ ባስደሰተን ነበር ። እነሱ መዝረፍንና ዘራፊዎችን፤ እብሪተኛና ፓለቲከኞችን፤ ዘርንና ዘረኞችን ነው ያፀኑ ያስፋፉት።
  የፓትሪያርክ የማእረግ ስም ወእጨጌ ተክለሐይማኖት አሁን የተደነገገ አለመሆኑን እገነዘባለሁ። እኔ ያልሁት ማእረገ ስም ብቻ ሆነ መንፈሳዊ አባትነታቸው ለሁሉም አይደለም። ወደ ዘረኝነትና ፓለቲከኝነት አድልተው ፤የእግዚአብሔርን ቤት በር ዘግተዋል ፤በማእረገ ስም ተኮፍሰው ቅዱስ ሲኖዶሱን አዋርደው አባቶችን አሳዝነዋል፤ ክህደት እንክርዳድ ምንፍቅና ሲንሰራፋ የበጎች እረኝነታቸውን ዘንግተዋል ፤ የፖለቲካ አስተሳሰብና መርሆ በእግዚአብሔር ቤት የቤተክርስቲያንን ህግ ሲያፈርስና ሲጥስ ዝም ብለዋል ነው የምለው።
  ችግር መኖሩንም ታምናለህ። ነገር ግን የችግሩን መነሳትና ምንጩ ከየት መሆኑ ሲነገር ትቃወማለህ። ታዲያ ነገርህ ሁሉ የሌባ አይነደረቅ እንደሚባለው ነው የሆነብኝና ከምታብራራልኝ ዝም ብትል በተሻለ ነበር።
  በመጨረሻ እኔ አንድ ተራ ግለሰብ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የማምን ነኝ። እናም ሁሉም የተናገርኩት የራሴው እንጂ የማንም አይደለምና ከምንም ከማንም ጋር እንዳታቆራኘኝ። መጥፎም ሆነ ጥሩ የምትለው ሁሉ የኔ ግሌ ነው።

 17. Anonymous June 15, 2015 at 2:06 pm Reply

  አይ አባ ማቲያስ ዘኢጨጌ ዘአክሱም ከእንደተሸሙ ማግስት የቤተክርስቲያን ችግር አጠራለሁ ሙስናን አጠፋለሁ ባሉት አንደበት አንድም ስራ ሳይሰሩ ይባሱኑ ቤተክርስቲያን ለከፋ መከራና ስቃይ ዳርገዋት እደአጎታቸው መጠራታቸው አይቀርም! በአሁኑ ወክት ክፍት የስራ ቦታና ገንዘብ ያለጠያቂ የሚዘረፍበት ቦታ ቤተክርስቲያ ሁናለች፡፡ በጣም አስገብግቧቸዋል፡፡ ልቦና ይስጣቸው ! እየሱስ ክርስቶስ ለሁለት ጌታ አትገዙም ቢልም በአሁኑ ወቅት ማምለኪያው ገንዘብ ሆኗል. ይቅር ይበላችሁ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: