ሰበር ዜና – ለመልካም አስተዳደር፣ ለፍትሕ እና ለዕቅበተ እምነት የተጀመረው ንቅናቄ ወደ ሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ቀጥሏል፤ ሰንበት ት/ቤቶች በአ/አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ተሰልፈዋል

 • አባላትን በኑሮ ደረጃ በመከፋፈል የሚደርሰውን አስተዳደራዊ አድልዎ በመቃወማቸው ለተደጋጋሚ እስር የተዳረጉት የሰሚት መድኃኔዓለም ምእመናን ጉዳይ ቀዳሚ አጀንዳቸው ነው
 • በፖሊቲካ ሳይንስ እና በጋዜጠኝነት ከመማራቸው በቀር ጥልቅ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሌላቸው ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹የዕውቀት ማነስ እንጂ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ የለም›› ባይ ናቸው
 • ስለ ሕግ የበላይነት፣ ግልጽነት እና መተማመን በቃል ቢተነትኑም በትላንትናው ዕለት የፈጸሙት የ20 የአጥቢያ ሠራተኞች ዝውውር አግባብነትና ፋይዳ ብዙዎችን እያጠያየቀ ነው
 • የሀ/ስብከቱ በር ለተመረጡት ሳይኾን ለኹሉም ባለጉዳዮች ክፍት ነው በሚል ስለ መልካም አስተዳደር ከመናገር የማይቦዝኑት ሥ/አስኪያጁ፣ በቢሯቸው ቢኾኑም በተሰላፊ ሰንበት ት/ቤቶች ላይ ዘግተዋል
 • የጽ/ቤቱ ግቢ በር እንዲከፈትላቸው በትዕግሥት ሲጠባበቁ የቆዩት ፍትሕ ጠያቂ የሰንበት ት/ቤቶች ተሰላፊዎችለመኪና መግቢያ ሲከፈት በርግደው ወደ ቅጽሩ ዘልቀዋል
 • መላው የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ሠራተኞች ከቢሯቸው በመውጣት ለዕቅበተ እምነት፣ ለመልካም አስተዳደር፣ ለፍትሕ የተሰለፉ የሰንበት ት/ቤቶች አባላትን እየተመለከቱ ነው
 • የአ/አ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ያስተባበረው የዛሬው የዕቅበተ እምነት፣ የመልካም አስተዳደር እና የፍትሕ ጥያቄ በሀገር አቀፉ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የጋለ ድጋፍ የተቸረው ነው
 • በ፬ኛው የሀገር አቀፍ አንድነቱ ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ከሠላሳ ዓመት ዕድሜ በላይ ያሉ አባላትን ከየአጥቢያ ሰንበት ት/ቤት ለማባረር የወሰኑት ሥ/አስኪያጁ የፓትርያርኩን ይኹንታ አግኝተዋል
 • ማኅበረ ምእመናን እና ሰንበት ት/ቤቶች በአየጥቢያው ያቀጣጠሉት ንቅናቄ÷ ቤተ ክርስቲያን የምእመናነ ክርስቶስ ጉባኤ መኾኗን በመዘንጋት፣ በማኅበረ ካህናት እና ምእመናን ተደራጅታ በሰበካ ጉባኤ እንድትመራ የተደነገገውን በመተላለፍ ለምእመኑ ሚና ከልክ ያለፈ ንቀት ለሚያሳዩት ለሥራ አስኪያጁ እና ለመሰሎቻቸው ትምህርት እንደሚሰጥ ይታመናል
በክንውን ላይ፤ ከረፋዱ 4፡50፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
addis ababa sunday schools demo to the dioseces HOaddis ababa sunday schools demo to the dioseces HOከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ከተለያዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በመንቀሳቀስ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተሰለፉ የዕቅበተ እምነት፣ የመልካም አስተዳደር እና ፍትሕ ጠያቂ ሰንበት ት/ቤቶች
Advertisements

3 thoughts on “ሰበር ዜና – ለመልካም አስተዳደር፣ ለፍትሕ እና ለዕቅበተ እምነት የተጀመረው ንቅናቄ ወደ ሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ቀጥሏል፤ ሰንበት ት/ቤቶች በአ/አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ተሰልፈዋል

 1. Anonymous June 9, 2015 at 11:56 am Reply

  ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ ዘመናዊ ትምህርት መማሩን ስላመናችሁ ምስጋና ይገባችኋል፡፡ በመንፈሳዊው ደግሞ ቢያንስ የቀሲስነት ማዕረግና የብዙ አመታት ልምድ ስላለው የመንፈሳዊ እውቀቱን ክፍተት በልምዱ ይሞላዋል፡፡ ደግሞም ከየማነ በፊት የነበሩት ሊቀ አእላፍ በላይም እኮ የጉባኤ መምህር አልነበሩም፡፡ምነው ለየማነ ሲሆን ልዩ መመዘኛ አመጣችሁ???

  መልካም አስተዳደር ጠፋ ስትሉ ከርማችሁ ችግሩን በማስጠንቀቂያና በዝውውወር ለመፍታት ሲሞክሩ፣ያላግባብ የታገዱ ሰዎችን ወደ ቀድሞ ስራቸው ሲመልሱ፣የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራን የምዕመናንና የካሕናት ተወካዮች ባሉበት በባንክ በማድረግ ሂደት አመርቂ ውጤት እየተገኘ ባለበት ወቅት እኛ ያልነው ካልሆነ ብሎ ሁሉንም ነገር ማጠልሸት ነውር ነው፡፡

  የምትዘረዝሩት ችግር ሁሉ ዛሬ የማነ ሲሾም የተከሰተ አይደለም፡፡ትናንተ እነ ሊቀ አእላፍ በላይ እያሉም ነበረ፡፡እናንተ ግን አበሳውን ሁሉ ጠቅልላችሁ የማነ ላይ ለመጫን የምታደርጉት ኢሚዛናዊ ዘመቻ አሳዛኝ ነው፡፡ምክንያታዊ አይደለም፡፡

  ስለ ሰ/ት/ቤቶች ጩኸትም ቢሆን በትክክል ስለ ቤ/ክ ቅናት ሲሉ የሚሰለፉ እንዳሉ ሆነው የሱቅ ኦዲትና የመንፈሳዊ ጉዞ ገቢና ወጭ ለምን አሳውቁን ተባልን በሚል የራሳቸውን ድክመት በአስተዳደሩ ላይ ለማላከክ የሚጥሩ የ40 አመት ጎልማሳ የሰ/ት/ቤቶች አመራሮች መኖራቸው ሊካድ የሚችል ሀቅ አይደለም፡፡ጎልማሶቹ ከ4 አመት ጀምሮ በቤ/ክ አድገናል ይበሉ እንጅ ከአድማና አሉባልታ በዘለለ ከሚቆጥሩት አመት ጋር የተመጣጠኘ የረባ መንፈሳዊ እውቀት እንደሌላቸው ብንናገር ሊያኮርፉ አይገባም፡፡ሀቅ ነው!!አመታትን በመቁጠር ሊቅነት አይገኝም!! ፌስቡክና ብሎግ የመጠቀም እድል እና ችሎታ ያለው ሰ/ተማሪ ስለራሱ ጻድቅነት አብዝቶ ስላወራ ሀቁ አይሸፈንም፡፡

  ስለዚህ ምዕመናንን ሆድ ለማስባስ ከመሞከር በየ/ሰ/ት/ቤቱ ያለውን አመራርም መፈተሸ ያስፈልጋል፡፡ ግዴላችሁም ሚዛናዊ ሁኑ!!የቤ/ክ ጥንካሬ ካንድ አካል እንደማይመነጨው ሁሉ ችግሯም ከአንድ አካል አይመነጭም!!

 2. Anonymous June 10, 2015 at 7:53 am Reply

  nice view brother, thank you and God bless you more!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: