በአማሳኞች በደል እና በፍትሕ ዕጦት የተመረሩ ምእመናን ርምጃ መውሰድ ጀመሩ፤ በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ሓላፊዎችን በማስወጣት እና መኪኖቻቸውን በማገት ጽ/ቤቱን ተቆጣጠሩ

 • አስተዳደሩ፣ በሕገ ወጥ ኪራይ የደብሩን ጥቅም ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ በመስጠት ይታወቃል
 • ጽ/ቤቱን አስበይደው በማሸግ የተቆጣጠሩት ምእመናኑ የተመሩት በሰንበት ት/ቤቱ አባላት ነው

*      *      *

 • በመ/ፓ ቅ/ቅ ማርያም፣ የሒሳብ ፈራሚነቱን ለቄሰ ገበዙ ለማሳለፍ የተደረገው ጥረት ከሽፏል
 • ሒሳብ ሹሙ ‹‹ጉረሮዬን ዘግተኽ አትኖርም›› እያለ በምእመኑ ተወካይ ላይ ሲዝት ሰንብቷል

*      *      *

 • በደ/ሲና እግዚአብሔር አብ ያለደንቡ የታሰበው የሰ/ት/ቤት አመራር ለውጥ በውጥኑ ታርሟል

*      *      *

 • የታሰሩ የሰ/መድኃኔዓለም ምእመናን በሃይማኖት ሰበብ ሕዝብን ማሳመፅ በሚል ፍ/ቤት ቀረቡ
 • በሊ/ማ የማነ ላነጋግራችኹ አልፈልግም የተባሉት ቤተሰቦች ከጽ/ቤቱ በር በጥበቃ ተመልሰዋል

*      *      *

eotc ssd demoየፀረ ሙስና እና የፀረ ኑፋቄ ንቅናቄው በተቀናጀ ስልት ወደ ተግባራዊ ርምጃ ተሸጋግሯል!

አማሳኞች እንዲጠይቁ፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች እንዲወገዱ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና እንዲከበር እና ውሳኔዎቹ እንዲተገበሩ በየደረጃው ጩኸታቸውን ሲያሰሙ የቆዩት ማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች በየአጥቢያቸው የተቀናጀ ርምጃ መውሰድ ጀምረዋል!

በሙስና፣ በአስተዳደር በደል እና በፍትሕ ዕጦት የተመረሩት ማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች፣ በየአጥቢያቸው በአማሳኝ ሓላፊዎች ላይ የጀመሩት የፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ተግባራዊ ንቅናቄ÷ በእብሪት፣ በጥቅመኝነት እና በጎጠኝነት ለታወረው እና ለደነቆረው የፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር የማንቂያ ደወል ነው!

በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም፣ በደብሩ ይዞታ ውስጥ የሚገኙ ቦታዎችንና ሱቆችን ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅም እና ከቤተ ክርስቲያን አቋም ጋራ በማይስማማ መልኩ በሚፈጽመው ሕገ ወጥ የኪራይ ውል ራሱን ሲጠቅም በቆየው አስተዳደር ላይ የሰንበት ት/ቤቱ አባላት እና ምእመናን የተቀናጀ ርምጃ ወስደውበታል፡፡

በደብሩ የልማት ይዞታ የተሠሩት ልዩ ልዩ ሱቆች የኪራይ ውል፣ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ የተከራዮችን ጥቅም እና መብት የሚያስጠብቁ ሲኾኑ ለሦስተኛ ወገኖችም በከፍተኛ ዋጋ ተላልፈው የተከራዩ ናቸው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ሥርዐት እና አቋም ጋር በማይስማማ አኳኋን በደብሩ መግቢያ ላይ የተከራዩት የመጠጥ ግሮሰሪዎች እና የውበት ሳሎኖች ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተቹና ምእመኑን ሲያስቆጡ ቆይተዋል፡፡

ለመካነ መቃብር አገልግሎት የተለየው የደብሩ ቦታ ከዓላማው ውጭ ስፋቱን በሚያጣብብ መንገድ እየተሸነሸነ ያለጨረታ ተከራይቷል፡፡ አካሔዱ የይዞታ መብቱን የሚያስነጥቅ በመኾኑ አስተዳደሩ ተከራዮችን በአስቸኳይ እንዲያስለቅቅና ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲያውል ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው ቆይቷል፡፡

የኪራይ አገልግሎቱ በዋናነት በቅርቡ የመሠረት ድንጋይ ለተቀመጠለት አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ማሠርያ ገቢ ለማሰባሰብ በሚል በስፋት ቢፈጸምም ሥራው እንደሚጠበቀው እየተከናወነ አይደለም፡፡ ‹‹ከአጠቃላይ የኪራይ ገቢው በወር ከ700‚000 – 800‚000 የሚገኝ ቢኾንም ሥራው እየተንቀሳቀሰ አይደለም›› የሚሉት ምእመናኑ፣ በምትኩ የአስተዳደር ሓላፊዎቹ ግንባታውን በማጓተት ራሳቸውን እየጠቀሙበት እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

የደብሩ አስተዳደር የተጠቀሱትን ችግሮች እንዲያስተካክል በተደጋጋሚ ቢነገረውም ባለማረሙና ባለማስተካከሉ በሰንበት ት/ቤቱ አባላት የተመሩ ምእመናን ትላንት እሑድ ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ በድንገት ለእርምት ተነሣስተውበታል፡፡ በርምጃው የደብሩ አስተዳዳሪ ‹‹ሊመሩን አይችሉም›› ተብለው ከቅጽሩ የተባረሩ ሲኾን በፖሊስ ታጅበው ወጥተዋል፡፡ ርምጃው በፍጥነት ቀጥሎ የጽ/ቤት ሠራተኞችን ቢሮዎች በመቆጣጠር በራቸውን በማስበየድ ወደ ማሸግ ተሸጋግሯል፡፡

እንደ አለቃው ኹሉ ሰኞ ጠዋት ወደ ደብሩ የመጡት ጸሐፊው ከቅጽሩ የተባረሩ ሲኾን ከእርሳቸው ጋር የዋና ተቆጣጣሪው ኹለት መኪኖች በምእመናኑ መታገታቸው ታውቋል፡፡ ሓላፊዎቹ የተሽከርካሪዎቹ ባለቤት የኾኑት እየተመዘበረ ባለው የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ይኹን አይኹን ሳያጣራ እንደማይለቀቁ፣ ምእመናኑ ወደ ቅጽሩ ዘልቆ ለገባው የአካባቢው ፖሊስ አስረድተዋል፡፡

በአኸኑ ወቅት በአጥቢያው ምእመናን ቁጥጥር ሥር የሚገኘው የደብሩ ጽ/ቤት የፈረቃ መርሐ ግብር በማውጣት ጥበቃ እየተደረገለት መኾኑ ታውቋል፡፡ አስተዳደሩ በበኩሉ የአንዳንድ ምእመናንን ስም ይዞ ለሀገረ ስብከቱ እና ለአካባቢው ፖሊስ በማሳወቅ ክሥ ለመመሥረት መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን ሥርዐት ከማስከበር እና ሀብቷን ከማስጠበቅ አኳያ የተወሰደው የቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ምእመናን ርምጃ፣ አማሳኞችን ተጠያቂ ለማድረግ እና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንን ለማስወገድ የተጀመረው የሰንበት ት/ቤቶች ፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ አካል ሲኾን ለአቤቱታው ጆሮ ዳባ ልበስ ላለው የፓትርያርክ አባ ማትያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደርም የማስጠንቀቂያ ደወል ኾኖ ተወስዷል፡፡

Advertisements

5 thoughts on “በአማሳኞች በደል እና በፍትሕ ዕጦት የተመረሩ ምእመናን ርምጃ መውሰድ ጀመሩ፤ በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ሓላፊዎችን በማስወጣት እና መኪኖቻቸውን በማገት ጽ/ቤቱን ተቆጣጠሩ

 1. TIRSIT WUBIE June 9, 2015 at 5:31 am Reply

  ቤተክርስትያን ሆይ በየአቅጣጫው ፈተናሽ በዛ

 2. wondwossen sahlie June 9, 2015 at 8:19 am Reply

  bereget yetederegew negr teru new elalew le lelaw temeheret yehonal gin ke megachet ena ke metalat yelek mesemamat yenorebenal beye new masebew mekniyatum egna feraj adelenem feraj 1 egeziyabeher becha new esu hulunem yayal

 3. Anonymous June 9, 2015 at 5:13 pm Reply

  ሁልጊዜ በገንዘብ እንደተባላን የበታች ሰራተኛ ሲጨቆን ዝም ፣ አባቶች ከሥራ ሲበረሩ ዝም…..ትሉና የገንዘብ ነገር ሲሆን ማሞጥሞጥ ለምን አላካፈላችሁኝም ያስመስላል ፡፡

 4. baneyas June 12, 2015 at 5:18 pm Reply

  bemiyasgerem huneta memenanu be eser lay eyale ye debru astedader zare tewat gebetew yemifelegutn adergew yemifelegutn asaserew wetewal

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: