ሰበር ዜና – በሰሚት መድኃኔዓለም የሰንበት ት/ቤት አባላት እስር ወደ ምእመናን ተሸጋገረ፤ በአንድ ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው

 • ‹‹ጉዳዩን በፌስቡክ እያጋጋላችኹ ነው›› የተባሉ 16 የሰንበት ት/ቤት አባላትና ምእመናን ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል
 • በሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ፣ ያለው ፈርሶ በአዲስ ምዝገባ በሚቋቋመው ሰንበት ት/ቤት ዕድሜአቸው ከ30 በላይ የኾኑ ይባረራሉ
 • ‹‹አዲስ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም ያዘዝኹት እኔ ነኝ፤ ዑራኤል ጸሐፊ ኾኜ 700 ሰንበት ተማሪ በትጥቅ ድጋፍ አስበትኛለኹ››/ሥ/አስኪ. ሊ/ማእ. የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ/
Aba Gebre Sellassie Amare of Summit

የፖሊስ ጣቢያውን እንዳሻቸው የሚያዙበት አለቃው መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ አማረ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመካነ ሰላም ሰሚት መድኃኔዓለም ፍኖተ ሰላም ሰንበት ት/ቤት አመራር እና አባላት ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ፣ እስር እና እንግልት ወደ አባላቱ ወላጆች ተሸጋገሮ እየከፋ መሔዱ ተገለጸ፡፡

የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ አማረ ዛሬ፣ ግንቦት ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ፣ በአገልግሎት ላይ የነበረውን ሰንበት ት/ቤት በማፍረስ ሌላ እንደሚቋቋም እና የአባላት ምዝገባ እንደሚያካሒዱ ሲገልጹ የሰንበት ት/ቤቱ አባላትና ምእመናኑ በአንድ ድምፅ ተቃውመዋቸዋል፡፡

‹‹ያለው ሰንበት ት/ቤት ምን ኾኖ ነው አዲስ ምዝገባ የሚካሔደው?›› ብለው በአንድ ድምፅ በመጠየቅ ተቃውሟቸውን በብርቱ ካሰሙት መካከል፣ ዘጠኝ ምእመናንና ሰባት የሰንበት ት/ቤት አባላት በስም እየተጠሩ ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎሮ ፖሊስ ጣቢያ በአስተዳዳሪው ትእዛዝ ተይዘው ተወስደዋል፡፡

ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ደብሩ የመጡት አለቃው መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ፣ በቃለ ዐዋዲው ለሰንበት ት/ቤቱ የተደነገገውን ወጣቶችንና ሕፃናትን የማደራጀት እና የማቋቋም ሓላፊነት በመጣስ በየአጥቢያው የምእመኑን ልጆች በሀብት መደብ እየከፋፈሉ የሀብታም ልጆችን እናስተምራለን ለሚሉ ግለሰቦች አስተዳደራዊ ድጋፍ በመስጠታቸው የተጀመረው ውዝግብ፣ ለሰንበት ት/ቤቱ አመራሮች እና አባላት መታሰር፣ መከሠሥ እና መታገድ፤ ለጽ/ቤቱና ለአዳራሹም መታሸግ ምክንያት ኾኗል፡፡

ከሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት መታሸግ ወዲኽ የአባላት ወላጆች የኾኑ ምእመናንንም ጭምር በማካተት ዛሬ የተፈጸመው እስር፣ ወከባ እና እንግልት በአንድ ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ የደረሰ ነው፡፡ ትላንት ጠዋት ሰባት አባላት ‹‹ለምን ጥያቄ ትጠይቃላችኹ›› በሚል ታስረው ወዲያው የተለቀቁ ሲኾን ባለፈው ረቡዕ ደግሞ ‹‹የአዲስ ምዝገባውን ማስታወቂያ ገንጥላችኋል›› በሚል አምስት አባላት ከ5፡00 – 8፡00 በጎሮ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው መለቀቃቸው ታውቋል፡፡

ምእመናኑንና የሰንበት ት/ቤት አባላቱን በተደጋጋሚ በማሰር የአለቃው ፈቃድ ፈጻሚ የኾነው የጎሮ ፖሊስ ጣቢያ ለቀረበለት የዘፈቀደ እስር እና የጣልቃ ገብነት ጥያቄ፣ ‹‹አባ ገብረ ሥላሴ አዝዘውኛል፤ እርሳቸው ያዘዙኝን ብቻ ነው የምፈጽመው›› ቢልም ከቀትር በኋላ ከአቅሜ በላይ ነው በሚል ምእመናኑንና የሰንበት ት/ቤት አባላቱን አምቼ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዳቸው ተገልጧል፡፡

በምእመናን የተመረጠውን ሰበካ ጉባኤ በማዳከም ደብሩን በዓምባገነንነት የሚመሩት አለቃው መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ፣ በማስታወቂያ በሚያቋቁሙት አዲስ የሰንበት ት/ቤት የሚመዘገቡት ዕድሜአቸው እስከ ሠላሳ ያሉትን ብቻ ሲኾን ይኸውም በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የተላለፈላቸው መመሪያ እንደኾነ ተጠቅሷል፡፡

ይህንኑ መመሪያ በኹሉም የሀገረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በማስፈጸም ከሠላሳ ዓመት በላይ ያሉትን ወጣቶች እና ጎልማሶች ከሰንበት ት/ቤቶች እንደሚያባርሩ የዛቱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ከፓትርያርኩ ዘንድም ይኹንታ እንዳገኙበት ተመልክቷል፡፡

Locked Finot Selam Sunday school gates
የሰሚት መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ፍኖተ ሰላም ሰንበት ት/ቤት÷ አባላቱ በሀብታም እና ድኻ መከፋፈላቸውንና በማስተማርያ ቦታ የሚደረገውን አድልዎ በመቃወሙ አመራሩ እንዲታገድ እና ጽ/ቤቱ እንዲታሸግ በማዘዝ በአዲስ ምዝገባ ሌላ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም መመሪያ የሰጡት ዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ፣ በጸሐፊነት በሠሩበት የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያንም ሰንበት ት/ቤቱን በመሣርያ ኃይል በማፍረስ 700 አባላትን መበተናቸውን በጀብደኝነት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

፬ኛው የሰንበት ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ፣ ከጥቅመኛ ግለሰቦች ጋራ በዓላማ የተሳሰሩ አማሳኝ አለቆች እና እነርሱን የሚተባበሩ አካላት በሰንበት ት/ቤት አባላት ላይ ከሚያደርሱት እስር፣ ወከባ እና እንግልት እንዲቆጠቡ በአቋም መግለጫው አሳስቧል፡፡

በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ሥር የሚገኘው ሀገር አቀፍ አንድነቱ በጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም. በጸደቀለት የውስጥ መመሪያሰንበት ት/ቤቶች ከሕፃናት እና ወጣቶች በተጨማሪ ጎልማሶችንም እንዲያደራጁ የተፈቀደላቸው ሲኾን የቅ/ሲኖዶሱን መምሪያ ኹሉም የበታች መዋቅሮች የመፈጸምና የማስፈጸም ግዴታ እንዳለባቸው ግልጽ ነው፡፡

በሌላ በኩል ሰንበት ት/ቤት፣ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋን ለተረካቢው ትውልድ የምታስተላልፍበትና የምታስጠብቅበት የትምህርት እና የልማት ማእከል በመኾኑ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. በተወሰነው የቃለ ዐዋዲው ማሻሻያ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጀት እና ማቋቋም ድንጋጌ፣ ከ4-30 በሚል ለሕፃናት እና ወጣቶች የተቀመጠው የዕድሜ ገደብ እንዲጤን በሀገር አቀፍ አንድነቱ የአምና እና የዘንድሮ የአቋም መግለጫዎች ተደጋጋሚ ጥያቁ የቀረበበት ጉዳይ መኾኑ ይታወሳል፡፡

Advertisements

8 thoughts on “ሰበር ዜና – በሰሚት መድኃኔዓለም የሰንበት ት/ቤት አባላት እስር ወደ ምእመናን ተሸጋገረ፤ በአንድ ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው

 1. mindnew yemiweraw June 7, 2015 at 5:24 pm Reply

  what kind of religion is that limits ages. over 30 unwanted less than 30 accepted. what a nonsense shitty priest. he must be weyane.

 2. ኀይለገብርኤል June 7, 2015 at 7:51 pm Reply

  የወያኔ አሽከር እንዲሁም አስማተኛነቱ ሳይታለም የተፈታ ነው

 3. Anonymous June 8, 2015 at 8:32 am Reply

  ከአለቃው ወገን ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ በዘገባው ቢካተት መረጃው የበለጠ ምሉዕ ይሆን ነበር፡፡ያም ካልተቻለ ችግሩን ለመቅረፍ ከቅሬታ አቅራቢዎቹ ወገን የቀረበው አማራጭ ምን እንደሆነ ማመላከት አይከፋም ነበር፡፡መቼም ምንም ቢባል አንድ ወገን ብቻ ነው ጥፋተኛ ብሎ መደምደም ብዙ ጊዜ እንዳየነው መቋጫው ትክክል አይደለም፡፡
  የሰ/ት/ቤቶች በዋናነት የሕጻናትና የወጣቶች ክፍል እንዳላቸው አውቃለሁ፡፡በተጨማሪነት እንደየ እድሜ እርከናችን ያለብን መንፈሳዊ ፈተና፣ብስለት፣አስተዋጽኦ፣ብቃትና ድክመት ስለሚለያይ የጎልማሶች ተብሎ ከ30 አመት በላይ ያሉትንና ባለትዳሮችን የሚያቅፍ ራሱን የቻለ አደረጃጀት በውስጣቸው ቢኖራቸው መልካም ነው፡፡
  እስከዚያው ደግሞ ሰ/ት/ቤቶችና አባላቱ ከሌሎች የቤ/ክ ክፍሎች በተሻለ መልኩ ቴክኖሎጅ በላቀ ብቃት የመጠቀም አቅማቸውን ቅሬታን በየአደባባዩ ለማቅረቢያና አንድን ወገን ብቻ የችግሮች ሁሉ ምንጭ አድርሎ ለማሳደጃ ከማዋል ይልቅ ወደ ራስም መመልከቻ፣አማራጭ መፍትሄ መጠቆሚያ፣ገንቢና ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ያልተለየው ሂስ መስጫ፣የእያንዳንዱን ኦርቶዶክሳዊ ካሕንና ምዕመን መብትና ግዴታ ማሳወቂያ ለማድረግ መጣር ገንቢና ከቤተክሕነቱ አስተዳደር ጋር መተማመን የሰፈነበት ግንኙነትን ለማስቀጠል የሚረዳ አካሄድ ይመስለኛል፡፡

 4. Abraham June 8, 2015 at 11:01 am Reply

  May be they think that the youth under 30 do not have initiation and power to oppose. I think they have to refer the Bible as God can do whatever He likes either using children or animals.

  • Anonymous June 8, 2015 at 11:31 am Reply

   @ Abraham :- no need of assumption. the church law(canon) is clear.when QALEAWADI was formulated in 1964 e.c, 30yr stipulated as a maximum age limit to participate in Sunday school.As u know in 1964 e.c neither this Aleqa nor Aba Mathias existed on the law making position.BTW if your aim is opposing, children under 30 r more suitable than those adults above 30.Any way don’t use ‘WE’ & ‘THEY’ terminologies.Blaming & shifting responsibility towards one-side did’t help,and will not.stay blessed.

 5. Anonymous June 8, 2015 at 4:09 pm Reply

  እባካችሁ አንዳንዴ እንኳን ዘገባችሁን እውነተኛ እና ሚዛናዊ አድርጉት !? እንጂ
   የሰሚት መድኃኒ ዓለም ሰንበት ትምህርት ቤት እኮ፡- በተደጋጋሚ ተለምኖ ፣ ማስጠንቀቂያና ውሳኔ ቢሰጠውም አካሄዱን አርሞ ለመሄድ እንቢ ያለ ነው፡፡
   እናንተ የሃብታምና ደኃ የሚል የክስና የነቀፌታ ስም የሰጣችሁት ትምህርት በሐገረ ስብከቱ ክፍለ ከተማ አውቅና አግኝቶ ፣ በቃለ አዋዲው አንቀጽ 19 መሰረት የተቋቋመ ነው፡፡
   ሰበካ ጉባዔው በቃለ አዋዲው አንቀጽ 19 እና 21 መሠረት ሊያደራጀው የፈለገውን የሰንበት ትምህርት ቤት እና መንፈሳዊ ትምህርት ክፍል አልቀበልም ያለው እኮ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አመራር ነው፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የሀገረ ስብከቱ ክፍለ ከተማ የተወሰነውንም አሻፈረኝ ብሏል፡፡
   በመሆኑም በጥቂት ምዕመናንና በሊቀ አዕላፍ በላይ ግፊት የተሳሳቱት እና ጉዳዩን በጥልቀት ያልሰሙት አቡነ ቀሌምንጦስ ከቃለ አዋዲው በተጻራሪ የቆመ አፍራሽ ውሳኔ አስተላልፈዋል ፤
   ቋሚ ሲኖዶስ የዕርምት ውሳኔ በመስጠት የሀገረ ስብከቱን ውሳኔ ሽሮ የደብሩን ሰበካ ጉባዔና የክፍለ ከተማውን ውሳኔ የሚያጸና ውሳኔ አሳልፏል፡፡
   ቋሚ ሲኖዶስ ሑለቱም ትምህርቶች (ማለትም በቃለ አዋዲው አንቀጽ 19 እና 21 የተጠቀሱት መንፈሳዊ ትምህርት እና ሰንበት ትምህርት ቤት) እየተረዳዱና በደብሩ ሰበካ ጉባዔ ሥር ይቀጥሉ ፤ የሚል ውሳኔ አሳልፎዋል፡፡
   ሆኖም የሰንበት ትምህርት ቤቱ አመራር ከውጭ በሚገፋፉት ኃይሎች ታውሮና በማን አለብኝነት የቤተ ክርስቲያንን ውሳኔ አልቀበልም! በማለት ታቦት ማጀብና ሌሎች የአደባባይ አገልግሎቶችን በራሱ ጊዜ አቆመ ፣ በጸያፍ ስድቦችና ሁከት እናነሳለን በሚል ዛቻ ቀጠለ፡፡
   አሁን ሐገረ ስብከቱ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እንደ አዲስ የማደራጀት ውሳኔ ያሳለፈውም ሰንበት ትምህርት ቤቱ የቋሚ ሲኖዶስን ውሳኔ በዚህ መንገድ ባለመቀበሉ ነው፡፡
   የዕድሜ ገደብም የሊቀ ማዕምራን ውሳኔ ሳይሆን የቃለ አዋዲው አንቀጽ 21 ሕጋዊ ውሳኔ ነው፡፡ እድሜያቸው ከ30 በላይ የሆኑ ሰንበት ተማሪዎች፡- በሰበካ ጉባዔ የምዕመናን ተወካይነት ፣ በምግባረ ሰናይ ክፍል ፣ በስብከተ ወንጌል ክፍል ፣ በልማት ክፍል ……….. ሊያገለግሉ እንደሚችሉ ቃለ ዐዋዲ ይፈቅዳል፡፡
   ከዚህ ከፍ ሲልም፡- በሰንበት ትምህርት ቤት ቆይታቸው በጸጋ ፣ በክህነት ፣ በሕይወትና በእውቀት ያደጉና ለማገልገል የሚፈልጉ የሚያገለግሉባቸው አሉላቸው፡፡ ለመሆኑ እኛ ሰንበት ተማሪዎች በክህነት ፣ በመሪጌትነት ወይም በሌሎች የውስጥና የአደባባይ አገልግሎቶች በሙያ ብቃትና በጸጋ ለምን የለንም ? ? የምንከብራቸው ዓመታዊ በዓላት ቑጥር እኮ ከዚህ በላይም ያበቁን ነበር፡፡ የየግል የአገልግሎት ዘመናችንን ያህል ለምን አላደግንም ብለንስ ለምን ??? ወደ ውስጥ አንጠይቅም፡፡
   ወንድሞች እኛ እኅቶቼ፡- እኛ ማደግ ስላቃተን ፣ ቤተ ክርስቲያን ልታሳድገን የሠራችውን ሕግ ማጣመም የለብንም ፤ ቃለ አዋዲውን ስላልተረዳንም ሰዎችን መንቀፍና ሕጉ ይቀየር ማለት አግባብ አይደለም፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: