ፓትርያርኩ: የረዳት ሊቀ ጳጳሱን ሒሳብ የማንቀሳቀስ ሓላፊነት ያለቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ቀየሩ፤‹‹ተጠያቂነትና መከባበር የሌለበት የሥራ ኹኔታ አፋጣኝ መፍትሔ ይሻል››/ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ/

A.A Diosces Head Office

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት

 • አስተዳደሩን፣ የገንዘብ እና ንብረት እንቅስቃሴውን የመቆጣጠር ሕጋዊ ሓላፊነታቸው ተገድቧል
 • በዕቅድ ባልተያዙ ከፍተኛ ግዥዎች እና የወጪ ሰበቦች ምዝበራ ሊፈጸም እንደሚችል ተጠቁሟል
 • በቅ/ሲኖዶስ የተመደቡትን ረዳት ያጣው ሀ/ስብከቱ ከ50 ሚልዮን በላይ ተቀማጩ ለአደጋ ተጋልጧል

*        *        *

 • የሠራተኞች ደመወዝ እና አይቀሬ የኾኑትን ዕለታዊ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች እንዳይወጡ ፈቃደኛ ያልኾንኩበት እና ሥራዎች እንዲጓተቱ ያደረግኹበት ወቅት እስከ ዛሬ ድረስ የለም፡፡
 • በተመደቡት ሥራ አስኪያጅ እና በእኔ መካከል ያለው የሥራ ግንኙነት እና ሓላፊነት ከቃለ ዐዋዲው እና ከሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንጻር ታይቶ እና ተለይቶ በትክክል ባለመተግበሩ ሓላፊነቴን ለመወጣት በእጅጉ እቸገራለኹ፡፡
 • በሀገረ ስብከቱ የተረጋጋ እና ሰላማዊ የሥራ ግንኙነት እንዲሰፍን፤ ሓላፊነት፣ ተጠያቂነት እና መንፈሳዊ መከባበር ባለው ኹኔታ በሕጋዊ አሠራር ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የሥራ መመሪያ እንዲኖር ቅዱስነትዎ ትኩረት ይስጠው፡፡

/ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ/

Advertisements

8 thoughts on “ፓትርያርኩ: የረዳት ሊቀ ጳጳሱን ሒሳብ የማንቀሳቀስ ሓላፊነት ያለቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ቀየሩ፤‹‹ተጠያቂነትና መከባበር የሌለበት የሥራ ኹኔታ አፋጣኝ መፍትሔ ይሻል››/ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ/

 1. Anonymous June 5, 2015 at 6:23 am Reply

  ትልቁን በተለይ ደግሞ በፍቅረ ንዋይ አንዳች የማይጠረጠሩትን አባት አቡነ ቀሌምንጦስን ቃልአቀባይ ሁኑልኝ ሳይሏችሁ በግድ ቃል አቀባይ እንሁንዎ ብላችሁ ከፓትርያርኩ እንዳይስማሙ አደረጋችሁ፡፡የተመኛችሁት ደረሰላችሁ፡፡አንድ ወገን ለይታችሁ ለማሳደድ ስትሮጡ ያልጠበቃችሁት ሆነ፡፡የጫራችሁት እሳት መልሶ ፈጃችሁ፡፡የወረወራችሁት ድንጋይ ተመልሶ ራሳችሁን አደማ፡፡ስትጽፉ አማትባችሁ ጀምሩ፡፡አምታትታችሁ ሳይሆን፡፡ያሳዝናል፡፡የእውነት ነው ያዘንኩት፡፡
  አቡነ ቀሌምንጦስና አቡነ ማትያስ ከከበቧቸው ሰዎች ተገልለው ለብቻ ቢወያዩ ላይስማሙበት የሚችሉበት ነጥብ እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ፡፡ችግሩ በሁለቱም አባቶች ጎን ያሉ አማካሪዎች ብፁዐኑን አባቶች እንደ ተወለዱበት አካባቢ ወኪል እንጅ እንደ መለዋ የኢኦተቤክ አባት አይመለከቷቸውም፡፡አማካሪዎቹ የተመኙት ደረሰ፡፡በአቡነ ቀሌምንጦስ በኩል ያሉት አቡነ ማትያስን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማሳቀል ሰማዕትነት እንደሆነ ለማሳመን ዘመቱ፡፡በአቡነ ማትያስ በኩል ያሉትም ጉዳዩ ፓትርያርክ የመፈንቀል አመጻን ማዳን እንደሆነ አድርገው ተሰለፉ፡፡ከዘመቻው ሰልፍ ቤተክርስቲያን አንዳች አላተረፈችም፡፡
  ሚያሳዝነው ይህን ሁሉ ሚያውቁት እነ ሐራ እና የመሳሰሉ ብሎጎች ጉዳዩን በስክነት መርምሮ የተሻለ አስታራቂ ሐሳብ ማቅረቢያ መድረክ መሆን ሲገባቸው ጉዳዩን ያላግባብና ከሚገባው በላይ ወደ አንድ ወገን ባጋደለ መልኩ ለጥጠው አፍራሽ ሚና ተጫወቱ፡፡በአባቶች መካከል መተማመን እንዳይኖርና ጉዳዩ አስተዳደራዊ ሳይሆን ቀኖናዊ እንደሆነ በማስመሰል ወሬ መንዛትን ሙያ አደረጉት፡፡ለእያንዳንዱ ሐራ ለሚያወጣት ዘገባ በፓትርያርኩ በኩል ከተሰለፉት ሰዎች ሚመጣው አጸፋ መንበርና ሥልጣን የሚያሳጣ ባለማኅተም ደብዳቤ መሆኑን እያወቁ አካሄዳቸውን አላለዘቡም፡፡ተሐድሶዎቹስ መቼም አባቶች መካከል ክፍተት ያለ ከመሰላቸው አጀንዳውን ጠልፈው ለስሑት መንገዳቸው ለመጠቀም መሞከራቸው የለመድነው ምውት ጎዳና ነው፡፡የእናንተ እንዲህ ቅጥ ማጣትና ሚዛን ማዛባት ግን ያሳዝናል፡፡
  አምላከ ቤተክርስቲያን ለቤቱ የሚበጀውን ያምጣ!

  • ኀይለገብርኤል June 5, 2015 at 1:22 pm Reply

   አንተ የማነ መናፍቅ ነህ?የበሰበስክ ካድሬ ዘረኛ

  • Anonymous June 5, 2015 at 3:27 pm Reply

   ልጅ ኃይለገብርኤል በቃ ሳትማር መቅረትህ ነው??ስድብህ ራሱ ሁልጊዜ አንድ አይነት ናት፡፡መናፍቅ፣ደደብ፣ዘረኛ፣ካድሬ…አይ ኃይልሾ!!እውቀትሽ አስገራሚ ነው፡፡አሁን እንዳንተ አይነቱ ቢታሰር እንግዲህ ‹‹ሰማዕት›› ተብሎ ሊጠራ ነው፡፡ወይ ይቺ ‹‹ቀናኢነት›› የሚሏት ቃል የስንቱን አላዋቂነት ጋርዳዋለች፡፡
   እስኪ ወንድምዬ ጊዜ ካለህ አካባቢህ ወደሚገኝ ሰ/ት/ቤት ጎራ ብለህ ኮርሷን ከልሳት፡፡ጎሽ!!አይዟህ! አለማወቅ ኃጢኣት አይደለም፡፡አለመማርህ አይደል የሚያስቀባጥርህ!!
   የሰ/ት/ቤት ኮርስ ስትጨርስ ደግሞ ስለ መብትና ግዴታህ ራሱ፡- የሕግ፣የፖለቲካ ሳይንስና የጆርናሊዝም ምሁሩ ቀሲስ የማነ ዘመንፈስቅዱስ ቀነቀጠሮ ይዞ ገለጻ ያደርግልሃል፡፡እውቀት በማጣት ደንቁረህ እንደ መንደር ልጅ በየብሎጉ ወጭ ወራጁን ስትሰድብ እያየንማ ዝም አንልም፡፡
   ወይኔ ወንድሜን!ሥምህ ኃይለ ገብርኤል ሆና ሳለ ምግባርህ ሀጉለ ሳጥናኤል ይሁን!አይይ!ተቆጪ ማጣት!

  • Anonymous May 14, 2016 at 8:36 pm Reply

   Ftary lbetkrstyan ymebjwun yaderg

 2. Anonymous June 5, 2015 at 6:18 pm Reply

  Hailgebreail why you use bad word

 3. nehmiashishay June 6, 2015 at 5:11 am Reply

  እኔም እላለሁ አንተ ራስህ ብቻ ነህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሪ እንዳልሆኑ ምታስበው እንጂ እኛስ አባታችን እንላቸዋለን አካሄዳቸው ግን በጣም ያሳዝናል ሰለዚህ ከአካሄዳቸው ይታረሙ ዘንድ ሁሉ የየዓቅሙ መሰራት ይኖርበታል እምቢ ሚሉ ከሆነም በግድ ከቅዱስ መንበሩ መውረድ ነው ካልሆነ ከእሳቸው ይልቅ እኛ መእምናኑ መነፈሳዊ ጥንካሬ ለቤተክርስትያናችን ከማንም ግዜ በላይ በርትቶዋል

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: