ፓትርያርኩ የጠቅላላ ጉባኤውን ተሳታፊዎች ለማነጋገር ፈቃደኛ አልኾኑም፤ መላው ሰንበት ት/ቤቶች የአንድነቱን ቀጣይ የንቅናቄ ጥሪ በንቃት እየተጠባበቁ ነው

eotc ssd pouring out to patriarch palace

ከመሰብሰቢያ አዳራሹ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ያመሩት የጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፊዎች ፓትርያርኩ እንዲያነጋግሯቸው በመጠየቅ ከአርባ ደቂቃዎች በላይ እየዘመሩ ጠብቀው ነበር

 • ፓትርያርኩ ጠቅላላ ጉባኤው በላካቸው ብፁዓን አባቶች እና ተሳታፊዎች ላይ በራቸውን ዘጉ
 • የፓትርያርኩን ዳተኝነት በማጋለጥ ፍትሕን የሚጠይቁ የዐደባባይ ሰላማዊ ሰልፎች ይካሔዳሉ
 • በአማሳኞች እና በተሐድሶ መናፍቃን ላይ የሚደረገው ተጋድሎ በየአጥቢያዎቹ ይቀጣጠላል
 • ማስረጃ የተገኘባቸውን አማሳኞች በአገሪቱ ሕግ ለመጠየቅ የባለሞያዎች ቡድን ተቋቁሟል

*       *       *

፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ባለ18 ነጥቦች የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፤ ከመግለጫው ነጥቦች፡-

 • በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበው ጥያቄ የኹሉም አህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤያት የጋራ አቋም በመኾኑ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው ተጠይቋል፤
 • የቤተ ክርስቲያን ሀብት እና ንብረት ለግል ጥቅማቸው በማዋል የቤተ ክርስቲያንን አቅም የሚያዳክሙ አማሳኞች ማስረጃ ተጠናቅሮ በአገሪቱ ሕግ መሠረት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠይቋል፤
 • አንዳንድ የገዳማት እና አድባራት ሓላፊዎች ‹‹የተሳሳተ አመክንዮ›› ሳቢያ በሰንበት ት/ቤቶች ላይ እየደረሰ ያለው እስር፣ እንግልት እና ወከባ እንዲቆም ተጠይቋል፤
 • የመንግሥት የፍትሕ አካላት ከአጥፊዎች ጋራ በመተባበር የሰንበት ት/ቤት አባላትን ከማሰር እና ከማንገላት እንዲቆጠቡ ይደረግ ዘንድ ተጠይቋል፤
 • በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አፈጻጸም ላይ ተጽዕኖ እየፈጠረ ያለውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ለማጋለጥ ከሀገር አቀፍ አንድነት እስከ አጥቢያ ማስረጃ የማሰባሰቡ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፤
 • ማስረጃ በቀረበባቸው ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥ እና ውሳኔውንም ተግባራዊ ለማድረግ ኹሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ተጠይቋል፤

ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ

Advertisements

9 thoughts on “ፓትርያርኩ የጠቅላላ ጉባኤውን ተሳታፊዎች ለማነጋገር ፈቃደኛ አልኾኑም፤ መላው ሰንበት ት/ቤቶች የአንድነቱን ቀጣይ የንቅናቄ ጥሪ በንቃት እየተጠባበቁ ነው

 1. yismaw snshaw May 31, 2015 at 8:59 pm Reply

  thank you !!!

 2. Anonymous June 1, 2015 at 6:26 am Reply

  you guys are making a fire mixing a gasoline. these Sunday school students know how to sing but they do not have enough matured spiritual life. I do not accept the way you are doing if they pass the red light the government will put jail. I am not pro_ grovenment. Today In Ethiopia No justice Everywhere

 3. ቀፀላወርቅ ዓድማሱ June 1, 2015 at 9:20 am Reply

  የተነሱት ጥያቄዎች ተገቢ ናቸው፡፡ከሞላ ጎደል በፓትርያርኩም እንደ ግለሰብም ሆነ በጠቅላላ የቤተክሕነቱ አስተዳደር የሙስና፣የዘመድ አዝማድ አሰራር፣የኑፋቄ ፈተናዎች፣የመልካም አስተዳደር ጉድለት እንዳለ በገሐድ ይታመናል፡፡ይነገራል፡፡ይሕን ተገንዝቦ በሰ/ት/ቤት ደረጃ የራስን ገንቢ አስተዋጽኦ ለማበርከት መነሳት የተገባ ነው፡፡ክርስቲያናዊ ግዴታም ነው፡፡

  ይሁንና ሰ/ት/ቤቶች አሁን እየሄዱበት ያለው መንገድ ከአስተዳደሩ ተቀራርቦ በልጅና አባት መንፈስ መነጋገርን ሳይሆን በብሎግና በፌስቡክ ችግሩን ለጥጦ ማቅረብን፣የችግሩ አካል እንዳልሆኑ ሁሉ ራስን ለይቶ ማጽደቅን፣ለዘለቄታዊ መፍትሄ በመተማመን መንፈስ ከመስራት ይልቅ በሰልፍና በደብዳቤ ጋጋታ ቲፎዞ ለማስጨብጨብና አጉዋጉል ‹‹በግድ ሰማዕት›› ለመሰኘት መሯሯጥን፣ግለሰቦችን ለይቶ በብሎግ መሪነት ማሳደድን፣በየጋዜጣው ባለቤት የሌለው አሉባልታ ማሰራጨትን፣የወጣቱን የመረጃ ክፍተት ለፀረ-ቤተክሕነት ዐላማ ማዋልን፣ራስን ብቸኛና የተለየ የኦርቶዶክስ ዐርበኛ በማድረግ አባቶች ለቤ/ክ እንደማያስቡ ቆጥሮ ከመስመር የወጣ ዘለፋ መሰንዘርን፣ልማት ይልማ በሚል መንፈስ ሳይሆን ከለማ በኋላ ባለው ኪራይ ላይ አተኩሮ አሉባልታ መንዛትን፣አባቶቻችን ‹ሳንቲም ሲያቃጭል የሚነቁ ቁማርተኞች›› በመባላቸው ሲቆረቆሩ ሰንብተው መልሰው እጅግ በወረደ ቋንቋ በኦርቶዶክስ ተቆርቋሪነት በተሸፈነ ግብዝነት በቤተክሕነቱ ያሉ ካሕናትን መዝለፍን፣ወዘተ ሙያ አድርገው ይዘውታል፡፡ምክራቸው ሁሉ የጎበዝ ምክር እንጅ የሽማግሌ ምክር ስላልሆነ ‹‹ሳይሞቅ ፈላ›› ነው፡፡

  ፓትርያርኩን በውንጀላ ጋጋታ እያሳደዱ መልሶ ለምን አያናግሩንም፣ሰልፍ እንጠራለን፣እናጋልጣላን እያሉ ከጣራ በላይ መጮህ መካር ማጣት ነው፡፡እንደ እውነቱ ሰ/ት/ቤቶች እየሄዱበት ያለው የሰሞኑ ጎዳና ‹‹ብሎግ-አፈራሽ›› ከሚባል በቀር ያን ያህል የተጠና፣በማስረጃ የተደገፈ፣በቤ/ክ ያሉ አከላት በየድርሻቸው ያለባቸውን ድክመት አንጥሮ የለየ፣ከካሕናት እና ምዕመናንን ጋር የተናበበ፣ውስን በብሎግ ተሳዳጅ ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ድክመት ያለበት አካል የለየ፣በአጠቃላይ ከበለው-ፍለጠው-ቁረጠው-አውግዘው-እሰረው-ግረፈው-ክሰሰው-ሌባ-አማሳኝ-ዘረኛ-ሸረኛ ከሚሉ ቅጽሎች ባሻገር ሊታረም የሚገባው ታርሞ፣ሊገሰጽ የሚገባው ተገስጾ፣አርአያ ሊሆን የሚገባው አርአያነቱ ተቀስሞ፣በስተመጨረሻ ጥፋቱ በማስረጃ ተደግፎ ቀርቦ ማስተባበል ያቃተው ተጠርጣሪ እንደ ሁኔታው በተግሳጽም፣ለሕግ በማቅረብም፣ከስራ በማሰናበትም ወይም ደግሞ የሃይማት ህጸጽ ከሆነ በውግዘት በመለየት የቅድስት ቤተክርስቲያንን አንድነት ማጽናት ያሻል በሚል መንፈስ የቀረበ አይደለም፡፡ዝምብሎ በለው-ፍለጠው-ቁረጠው!

  ሰ/ት/ቤቶች እንደ አንድ የቤ/ክ አካል በቤ/ክ ጉዳዮች መሳተፍ መብታቸውም ግዴታቸውም ነው፡፡‹‹ለሁሉም ነገር ታሪካዊና ወቅታዊ አደራ ያለብን እኛ ብቻ ስለሆንን በውድም በግድም ያሰብነውን ዳር እናደርሳለን›› ብሎ በተዐብዮ መፎከር ግን አዋጭነቱን እንጃ፡፡ከብሎግና ከፌስቡክ ስሜት አቀጣጣይ ዘመቻዎች ባሻገር እያንዳንዱ ሰ/ተማሪ የዘመቻ ሂደቱ በማን፣ለምን ዐላማ፣እንዴት ባለ ክርስቲያናዊ መንገድ እየተመራ እንደሆነ መመርመር ይገባዋል፡፡በአካል ስለማያውቁት ሰው ሁሉ ገና ለገና በፌስቡክና በብሎግ ብዙ ስለተወንጀለ ‹‹ኃጢኣተኛነቱ አገር ያወቅ ፀሐይ የሞቀው ነው›› ብሎ በጭፍን መሰለፍ የኋላ ኋላ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ምክንያቱም እውነት በድምጽ ብልጫ ስለማትቆም፡፡አድማ የጋራ ቢሆንም ኃላፊነት የግል ነው፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ሰ/ተማሪ ለክስና ለሰልፍ ሲነሳ በግሉ ተጨባጭ መረጃ ቢኖረው አይከፋም፡፡ያለበለዚያ….

  • Anonymous June 1, 2015 at 7:14 pm Reply

   Dear sister I did not like ur tone at all.

 4. Anonymous June 1, 2015 at 7:12 pm Reply

  What do you think should they have done if the patriarch could not come and talk to them and able to address their concern?

  • Anonymous June 2, 2015 at 6:43 am Reply

   they blatantly accuse his Holiness,sign petition,repeatedly defame him,….doing all that they are shameless to call him to testify his own mis-deed before them.how an accused called for a decision-making on his own case?this guy are victims of per-judgment thanks to unfettered&clandestine hear-says of the so called EOTC defenders,like HARA. it is already an hijacked movement,by some interested groups.So,Abune Mathias was right to remain in his home than attending a meeting driven by emotion&hate-monger of YESENBET T/BETOCH ANDNET leadership. The leadership engulfed by self-exaggeration,undermining church authority,being a mercenary of MK&thereby losing its credibility as an autonomous and confident association under EOTC.It is now in practice an appendix of MK, not BETEKIHINET.It turned itself into messenger-boy of MK.As is known MK is praying for a sudden death of PATRIARIK Mathias.Anyway; Complaining on Abune Mathias for his unwillingness to appear in court & give a judgment over accusations filed in his name does not sound reasonable.B4 trying to change others, change ur bombastic attitude.Change ur bombastic leadership.U r nat o z rt track!!U r just crossin z red line.

  • Anonymous June 2, 2015 at 7:13 am Reply

   Teru asteyayet newe

 5. Anonymous June 3, 2015 at 5:59 am Reply

  አቤት ውሸት ደግሞም አድማ ለውጥ አያመጣም በቤተክርስቲያን ፀሎት እንጂ። ሊሰደብ ወደ ጫሂዎች ስብሰባ የሚመጣ ሰው የለም። ይህ ጉባኤ ከለባ ይሉሃል እንዲህ ነው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: