፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል

2004 eotc ssd gen assembly

  • ዓመታዊ ጉባኤው የሚካሔድበት ወቅት ‹‹የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን›› በሚል ተሠይሟል
  • በአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ ላይ አቋም እንደሚይዝ ይጠበቃል
  • ዋና ሓላፊው፣ ‹‹የአ/አበባዎችን ጥያቄ እንዳትቀበሉ›› በሚል ያደረጉት እንቅስቃሴ ተነቅቶበታል
  • የሀ/ስብከቱ ሥ/አስኪያጅ ለአንድነቱ ልኡካን የውክልና ደብዳቤ ባለመጻፍ በዓላማ ተባብረዋቸዋል

በዓለ ጰራቅሊጦስን ተንተርሶ በየዓመቱ የሚካሔደው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤአራተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ይጀምራል፡፡

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ከዛሬ ግንቦት ፳፩ እስከ ፳፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ለሦስት ቀናት በሚካሔደው ሀገር አቀፉ የሰንበት ት/ቤቶች ጠቅላላ ጉባኤ ከ52 አህጉረ ስብከት የተወከሉ ከ500 በላይ ልኡካን ይሳተፉበታል፡፡

እንደ መንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ኹሉ፣ አስፈላጊነቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ታምኖበት በጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም. በጸደቀው የውስጥ መመሪያ የተፈቀደው ዓመታዊው ሀገር አቀፍ አጠቃላይ የሰንበት ት/ቤቶች ጉባኤ÷ ኹሉንም ሰንበት ት/ቤቶች እኩል አድርጎ በአገልግሎት ለማሳተፍ እና ለመምራት በወጣው ስትራተጅያዊ ዕቅድ መመራታቸውን ለመከታተል፤ ወጥ የአገልግሎት ሥርዐት እንዲኖር ለማድረግ፣ ልምድ እና ተሞክሮን ለመለዋወጥ እንዲኹም ለጋራ ችግሮች መፍትሔ የሚቀየስበት የመመካከርያ ጉባኤ ነው፡፡

የሀገር አቀፍ አንድነቱ የመጨረሻ የሥራ አካል እና በማደራጃ መምሪያው የሚመራው ጠቅላላ ጉባኤው በዘንድሮው ዓመታዊ ስብሰባው፥ በማደራጃ መምሪያው እና በሥራ አመራር ጉባኤው ተመክሮበት በአምስት ዓመቱ ስትራተጅያዊ ዕቅድ ማህቀፍ የተከናወነውን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም እና የበጀት አጠቃቀም ሪፖርት እንዲኹም የአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤያትን የሥራና የበጀት ሪፖርቶች ይገመግማል፤ በቀጣይ ተግባራት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡

ስለ ሰንበት ት/ቤቶች የአስተዳደር ወጥነት እና የፋይናንስ ሥርዐት ዝርጋታ እንዲኹም በጸደቀው የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ አፈጻጸም የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ምን ዐይነት ለውጥ ሊያመጡ ይገባል በሚሉ አርእስተ ጉዳዮች ላይ በማደራጃ መምሪያው የተዘጋጁ ሥልጠናዎች እንደሚሰጡ ለስብሰባው በወጣው መርሐ ግብር ተመልክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር በሚገኙ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች መሠረትነት በአህጉረ ስብከት ተዋፅኦ የተዋቀረው ጠቅላላ ጉባኤው፣ ከ52 አህጉረ ስብከት ጠቅላላ ጉባኤያት ተመርጠው የሚላኩ ሦስት፣ ሦስት ልኡካን ይኖሩታል፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙት ሰንበት ት/ቤቶች በቁጥር ከፍተኛ በመኾናቸው እና ሰፊ እንቅሰቃሴ የሚከናወንበት በመኾኑ ከሀገረ ስብከቱ 160 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በተውጣጡ ኹለት፣ ኹለት አባላት የሚወከል ይኾናል፡፡

በጠቅላላ ጉባኤው መክፈቻ፥ የማደራጃ መምሪያው የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና የሚመለከታቸው ከፍተኛ ሓላፊዎች የሚገኙ ሲኾን የስብሰባው መዝጊያ በኾነው የበዓለ ጰራቅሊጦስ ቀን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል፡፡

በሌላ በኩል፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱን ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ በመወከል በዓመታዊ ስብሰባው መገኘት ለሚገባቸው ልኡካን ደብዳቤ ባለመጻፍ የጀመሩትን የሰንበት ት/ቤቶቹን የፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ የማዳከም ውጥን የገፉበት ሲኾን፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ደግሞ፣ ወደ አህጉረ ስብከት ስልክ በመደወል ‹‹አንድነቱ ተበትኗል፤ የአዲስ አበባዎችን ጥያቄ እንዳትቀበሉ›› በሚል የልኡካኑን ተቀባይነት የማሳጣት አሻጥር ሲፈጽሙ መሰንበታቸው ታውቋል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል

  1. Anonymous May 29, 2015 at 7:47 am Reply

    አይ ሐራ!ማኅበረቅዱሳንን በዚህ በዚያ ብላችሁ የወሬ ሱሳችኋን ስትወጡበት እንዳይሆን እንዳይሆን አድርጋችሁ ከቤተክሕነቱ አቃቃራችሁት፡፡አቡነ ማቴዎስንና አቡነ ቀሌምንጦስን በተሳካ መልኩ ከፓትርያርኩ አጋጫችሁ፡፡ግን ከሂደት አትማሩም፡፡አሁን ደግሞ ሰንበት ት/ቤቶችን መጠቀሚያ ለማድረግ ዘምታችኋል፡፡ሐራነታችሁ በአሳዳሚነትና የቤተክርስቲያንን አስተዳደራዎ ክፍተቶች አዘውትሮ በመግለጽ ብቻ የታጠረ መሆኑ ያስገርማል፡፡ደግነቱ በጊዜ አወቅናችሁ፡፡ ቤተክሕነታችንን ጨምሮ ሁላችሁንም እግዜር ይማራችሁ!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: