በስልጤ ዞን የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ክርስቲያኖች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፤ ሓላፊነት በማይሰማቸው ጽንፈኛ ባለሥልጣናት በደል ‹‹ወረዳው ሊቢያ ኾኖብናል፤ ለእኛም አልቅሱልን›› እያሉ ነው

Silte Kilto Orthodox Christians Plight

 • ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ተመርረው እና ተሠቃይተው ወረዳውን እንዲለቁ ከሥራ ማባረርን ጨምሮ እስራት፣ ያለበቂ ምክንያት የደመወዝ ቅጣት፣ ያልተገባ የሥራ ምደባ እና ዝውውር እንዲኹም ‹‹እናርዳችኋለን›› በሚል የግድያ ዛቻ ይደረግባቸዋል፤
 • የሚያስቀድሱበት እና የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ያገኙት በብዙ ውጣ ውረድ ነው፤ ይህም ኾኖ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ለመሥራት በኮሚቴ የተሰባሰቡ ምእመናን በአንድነት ባሉበት ቤት በምሽት ቤንዚን በማርከፍከፍ እሳት ተለቆባቸዋል
Kilto Gomoro St. Mary Church

የወረዳው ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን፣ የጽንፈኛ እና ዓምባገነን ባለሥልጣናትን በደል ተቋቁመው የሚያሠሯት የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን

 • እየተሠራ ባለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ላይ ‹‹ጉልላት ለምን አስቀመጣችኹ›› በሚል ሦስት ጊዜ የማቃጠል ሙከራ ተደርጓል፤ በዚኽ ሳቢያ በዞኑ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ተወቅሰዋል የሚባሉት የወረዳው አስተዳደርና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጉዳዩን በውይይት ስም እያድበሰበሱ ክርስቲያኖችን በማይመለከታቸው ጉዳይ በደመወዝ ከመቅጣት፣ ከሥራ ከማባረር እና ከመኖርያቸው ከማሳደድ ውጭ መፍትሔ ሰጭ የእርምት ርምጃ እየወሰዱ አይደለም፤
 • የሚደርስባቸውን በደል ለዞኑ ያሳወቁ እና በጠንካራ ሠራተኝነታቸው ከዐይን ያውጣችኹ የተባሉ የወረዳው ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ‹‹አስወቅሳችኹን›› ባሉ የወረዳው አስተዳደር እና የድርጅት ጉዳይ ሓላፊዎች፥ ያለበቂ ምክንያት ከሥራ ተባርረዋል፤ የትምህርት ዝግጅታቸውን እና የሞያ ልምዳቸውን በማይመጥን ቦታ በማዛወር ሞራላዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፤ ‹‹ሀገራችኹ ሥራ ቢኖር እዚኽ አትመጡም ነበር›› በሚል ተዘብቶባቸዋል
 • በዛሬው ዕለት ለሦስተኛ ጊዜ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ምስጉኑ የቂልጦ ኹለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት መምህር የማርያም ወርቅ ተሻገር በፖሊስ ጣቢያ እንግልት እና ድብደባ እየተፈጸመበት እንዳለ ተዘግቧል፡፡ የዋስ መብቱ ተጠብቆ ሊፈታ እንደማይችልም ከወረዳው ኢንስፔክተር መገለጹን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
 • ይህ መልእክት የደረሳችኹ ወገኖቻችን፤ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት አመራሮች እና መሥሪያ ቤቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ለሊቢያ ወንድሞቻችን ብቻ አይደለም ለእኛም አልቅሱ፤ እነርሱ ከአገር ወጥተው ነው፤ እኛ ግን በአገራችን ከአዲስ አበባ 220 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ነው የምንገኘው፡፡ ፍጹም መሮናል፤ ተሠቃይተናል፤ በጭንቀት እና በስጋት ላይ ነን፤ መቼ ምን እንደምንኾን አናውቅምና ድረሱልን ! ! !

  *        *        *

  የወረዳው ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን፥ ለወረዳ፣ ለዞን፣ ለክልል እና ለፌዴራል መንግሥት የአስተዳደር፣ የፍትሕ እና የጸጥታ አካላት እንዲኹም ለወረዳው ቤተ ክህነት እና ለሃዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤቶች ያሰራጩት የድረሱልን ጥሪ
  Silte Kilto Orthodox Christians PlightSilte Kilto Orthodox Christians Plight02Silte Kilto Orthodox Christians Plight03Silte Kilto Orthodox Christians Plight04Silte Kilto Orthodox Christians Plight05Silte Kilto Orthodox Christians Plight06

   

  Advertisements

11 thoughts on “በስልጤ ዞን የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ክርስቲያኖች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፤ ሓላፊነት በማይሰማቸው ጽንፈኛ ባለሥልጣናት በደል ‹‹ወረዳው ሊቢያ ኾኖብናል፤ ለእኛም አልቅሱልን›› እያሉ ነው

 1. Anonymous May 13, 2015 at 5:32 pm Reply

  የኢትዮጵያ አምላክ ተዋህዶ ኦርቶዶክስን ይጠብቅልን ሰው በሀገሩ መሸበር መንግስት የስልጤ ዞን በዝምታ ማየት ለምን መረጠ?ቤተ ክርስቲያን ከማቃጠል አልፎ አማኝን ማሰቃየት ምን ተልዕኮ ተይዞ ነው

 2. Anonymous May 13, 2015 at 6:11 pm Reply

  እንድረሥላቸው!!! በአሸባሪ እየተሠቃዩ ላሉ ወገኖቻችን የመንግሥትም አካል ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ቢሠጥ መልካም ነዉ

 3. Anonymous May 13, 2015 at 6:18 pm Reply

  ለዚህ ዞን ትኩረት ቢሠጥ መልካም ነው ጉዳዩ ለሀገርም የሚያሰጋ ነውና ዞኑን እኔ በደንብ ሥለማውቀው እባካቹ እንድረስላቸው!!!

 4. Anonymous May 14, 2015 at 3:35 am Reply

  እውነታችሁን ነው ከማልቀስ በቀር ምን እናደርጋለን…… አቤቱ ፊትህን መልስልን….ክርሰቲያኖችን አፅናልን….የአሃዛብን ልቦና መልስልን….

 5. Anonymous May 14, 2015 at 12:56 pm Reply

  ውድ ወገኖቻችን ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይጠብቃችሁ ፍርዱን ከእግዚአብሄር ነው መጠበቅ ፡፡ በአሁኑ ሰአት በየትኛው ቦታ መፍትሄ ሰጭ አካል የለም፡፡ እመቤታችን ትራዳችሁ ፡ በእናንተ ላይ ም ሆነ በቤተክርስቲያኗ ላይ የዘመቱትን መድህን አለም ክርስቶስ ያስታግሳቸው፡፡ ሰማችሁ ወገኖቸ በጸሎት ተግታችሁ የጀመራችሁትን ስራ አጠናክራችሁ ቀጥሉ ድል ታደርጋላችሁ፡፡ ለእኛ ስለሃይማኖታችን እግልትና ስቃይ መከራ መቀበል ሰማእትነት ስለሆነ አትሸበሩ፡፡ እድላችን ሆኖ በትንቢቱ መፈጸሚያ ጊዜ ላይ ስለደረስን ነው ፡፡ እባካችሁ የመንግስት ሰዎችም በየደረጃው የምታስቀምጧቸውን ባለስልጣናት በአግባቡ ብትፈትሷቸው ምንአልባት በአደባባይ እደምታወሩት አገሪቱን በአግባቡ ለመምራት ፍላጎቱ ካላችሁ፡፡ እባካችሁ ተከባብሮ የኖረውን የዋህ ህዝብ በሰፈር ፡ በብሄር በሃይማኖት በታትናችሁ አታተራምሱት፡፡ የመንግስት አካላት እግዚአብሄር አስተዋይ ልቦና ይሰጣችሁ፡፡ከጀርባችሁ የማያዳላ የሚዳኛችሁ ሞት አለና እሱን አስቡት መሞታችሁ አይቀርምና!

 6. […] Source- https://haratewahido.wordpress.com/2015/05/13/ […]

 7. Biruk May 21, 2015 at 10:24 am Reply

  Few weeks after we heard the ISIS barbaric act (slaughtering of Christians in Libya), the Silte Zone barbaric zonal officials & radical Silte Muslims are threatening to slaughter Christians in that part of the country. Where are we heading next? What is the role of the government before the danger occurs? Which one is better court verdict or saving life before the danger happens? Once (Eight years ago) I have been working in Silte zone as a medical staff and I observed certain radical/fundamental Muslims were agitating the peaceful Muslim followers to drive out Christian and non-Silte ethnics from the zone. If the federal government is not taking serious measure against these radicals who are hidden in the public, the danger will be more serious & worst than the Libya massacre.
  God Bless Ethiopia & its people

  Negash

 8. Anonymous May 28, 2015 at 9:27 am Reply

  Egzabher yerdan

 9. Lakew Woldemichael May 30, 2015 at 9:47 am Reply

  አኛ በስልጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የምንገኝ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች በሰላም ከህብረተሰቡ ጋር ተቻችለን እና ተሳስበን እንዲሁም ተከባብረን እየኖርን ነው ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰብንም ቤተክርስቲያኑዋም ተሰርታ ለምእመናን አገልግሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች ይህ ሁሉ ዘገባ ውሸት ነው

 10. Anonymous May 30, 2015 at 1:00 pm Reply

  ደደብ ኣሰተሳሰብ ካላቸዉ ሃይማኖት ኣልባ ህዝብ ኣምላክ ይሰዉረን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: