የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን: በስደት ያሉ ተዘዋዋሪ ወገኖችን ለመመለስ እና ለማቋቋም የድጋፍ ትብብር ጥሪ አቀረበ

ethiopianorthodoxስለተሰደዱት ወገኖች አዘውትራ የምትማልደው ቤተ ክርስቲያናችን፣ የአይ ኤስ አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በፍልሰት በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ስለ ክርስቲያንነታቸው የፈጸመባቸውን አሠቃቂ ግድያ በጽኑ ከማውገዝ እና ከመቃወም በተጨማሪ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ ፈጣንና ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈለግ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በሰጠችው መግለጫዋ ጠይቃለች፡፡

የዜጎች ሕይወት በአሸባሪዎች እንዳይቀጠፍ መንግሥት ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እና ከየሀገሩ መንግሥታት ጋራ በመኾን ከእስከ አኹኑ በበለጠ የተጠናከረ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ያሳሰበችው ቤተ ክርስቲያናችን በመግለጫዋ አሳስባለች፤ በበኩሏም በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ ተዘዋዋሪ ወገኖችን እና ልጆቿን ከመሰል ጥቃት ለመታደግ አስፈላጊውን ኹሉ ለማድረግ ዝግጁ መኾኗን አረጋግጣለች፡፡

ይህንኑም ጉዳይ እንዲከታተል ከመንግሥት ጋራ በቅርበት የሚሠራ ዐቢይ ኮሚቴ በአስቸኳይ እንደምታቋቁም ከሚያዝያ ፳፯ – ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በተካሔደው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖናዊ ጉባኤዋ የገለጸች ሲኾን፣ የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንም ርዳታ ሰጪዎችን በማስተባበር ረገድ ሓላፊነቱን ወስዶ በንቃት እና በትጋት እንዲሠራ መወሰኑንም አስታውቃለች፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን በልዩ ልዩ ምክንያት ከአገራቸው የወጡ ኢትዮጵያውያን ፈላስያንና ተዘዋዋሪዎች (migrants) ወደ አገራቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ የምታደርገውን ጥረት በግንባር ቀደምነት የማስተባበር ሓላፊነት የተጣለበት የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንም ለለጋሽ አካላት እና በጎ አድራጊዎች ይፋዊ የርዳታ ትብብር ጥሪ አቅርቧል፡፡

ኮሚሽኑ “Response to Migrant Crisis” (ምላሽ ለስደተኛ ዜጎች ችግር እና ስጋት) በሚል በገጸ ድሩ (http://www.eotcdicac.org) ባስተላለፈው ጥሪ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በአፍሪቃ በከፍተኛ ሥቃይ እና ቀጣይ አደጋ ውስጥ የሚገኙ ፈላስያን ወገኖቻችንን ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ሥነ ልቡናዊ መፍቀዶች ለማሟላት አስቸኳይ የርዳታ ትብብር ጠይቋል፡፡

ከቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫም ቀደም ብሎ ለዓለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ለጋሽ አካላት እንዲኹም ለበጎ አድራጊ ግለሰቦች በተላለፈው የኮሚሽኑ ጥሪ÷ በሊቢያ የአይ ኤስ የሽብር ቡድን በክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው ዘግናኝ ግድያ ዓለም አቀፍ ውግዘት ቢገጥመውም ለቡድኑ ታማኝነታቸውን ያወጁ ጽንፈኛ ታጣቂዎች በሚቆጣጠሩት ክልል የሚገኙና በእጃቸው የወደቁ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም የሠቆቃ ኑሮ በመግፋት ላይ እንዳሉ መዘገቡን አውስቷል፡፡

አይ ኤስ ታማኝ ታጣቂዎች ከታገቱት እና ከሚታደኑት መካከል ሕፃናት እና ነፍሰ ጡር ሴቶች እንደሚገኙበት ኮሚሽኑ ጠቅሶ፣ እኒኽን ወገኖች ከረኀብ፣ ከሥቃይ፣ ከእንግልት እና ከመጠቃት አውጥቶ በሰላም እና ደኅንነት ወደብ በማሳረፍ ኑሯቸው ለመለወጥ ኢትዮጵያውያን እና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የተባበረ ጥረት እንዲያደርጉ ተማፅኗል፡፡

  • በኮሚሽኑ የዓለም አቀፍ ድጋፍ እና ርዳታ ጥሪ ሦስት የትብብር አግባቦች ተለይተዋል፤ እነርሱም፡-
  1. በስደት ያሉትን ወደ አገራቸው የመመለስ
  2. በኑሯቸው መልሶ ማቋቋም እና ወደ ቤተ ሰዎቻቸው መቀላቀል
  3. የምክር አገልግሎት እና ሥነ ልቡናዊ ድጋፍ መስጠት ናቸው፡፡
  • የርዳታ እና ድጋፉ ዐይነት፤

የትብብር ጥሪው÷ አብያተ ክርስቲያናትን፣ የረድኤት ድርጅቶችን፣ በጎ አድራጊ ግለሰቦችን እና አብያተ እምነትን የሚያካትት ሲኾን ርዳታው እና ድጋፉ በሞያ፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እና በመሣርያ መልክ በአጠቃላይ ኮሚሽኑ የተመላሽ ወገኖችን መሠረታዊ መፍቀዶች ለማሟላት የሚያስችሉት እገዛዎች ኹሉ እንደኾኑ ተመልክቷል፡፡

  • ልገሳቸውን በገንዘብ የሚያደርጉ አካላት እና በጎ አድራጊዎች የሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፤

COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
Selassie Branch
ACCOUNT No# 1000010883214
SWIFT CODE; CBETETAA
P.O.BOX215
TEL.251 11 551 50 04
FAX. 251 11 55 14 45/22
E-MAIL.CBECOMU@COMBANKETH.ET
ADDIS ABABA/ETHIOPIA

  • ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የድጋፍ ጥያቄዎች፤

EOTC DICAC
P.O.BOX 503
Addis Ababa/ETHIOPIA
TEL. 0111 55 35 66/0111 56 30 33
FAX. 0111 55 14 55
e-mail eoc.dicac@ethionet.et

ኮሚሽኑ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተጣለበትን ሓላፊነት በስደተኞች እና ተመላሾች ጉዳይ መምሪያ በኩል የሚያከናውን ሲኾን መምሪያው የማኅበራዊ አገልግሎት እና የትምህርት ዘርፎች ያሉት አንጋፋ አካል ነው፡፡ በስደትና በሌሎችም ምክንያቶች እንግልት የሚደርስባቸውን ወገኖች በመከባከብ የተለያዩ ሕይወት አድን ሥራዎች በመፈጸም ላይ የሚገኘው መምሪያው፣ ተመላሽ ፍልሰተኞች ከደረሰባቸው የአካል ጉዳት እንዲያገግሙ፣ ከሥነ ልቡና ድቀታቸው እንዲነሡ፣ በክህሎት ሥልጠናዎች ታግዘውም ከቤተ ሰዎቻቸው እና ከማኅበረሰቡ ጋራ እንዲቀላቀሉ የማድረግ ዓላማዎች አሉት፡፡

refugees eoc-dicac
መምሪያው ከታደጋቸው ተመላሽ ወገኖች አብዛኞቹ የጤና ችግር ያለባቸው እና የኑሮ ደረጃቸው ዝቅ ያለ ቢኾንም ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ ከፍ ያለ ርእይ የነበራቸው መኾናቸውን ጦማረ ልማት የተሰኘው የኮሚሽኑ ልሳን ገልጧል፡፡ በሔዱበት ያልተመቻቸውና የጠበቁትን ያላገኙ ተመላሾች መምሪያው በአዘጋጀላቸው መጠለያ ጣቢያዎች ገብተው በተደረገላቸው ድጋፍ እና ክብካቤ የአእምሯቸው ቁስል ደርቆ፣ የተሰበረ ልባቸው ተጠግኖ በትምህርት እና ሥልጠና ተሳትፏቸው ብሩህ ተስፋ ሰንቀዋል፡፡

3

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፤ የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ

የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከተለያዩ ክፍላተ ዓለም በተለይም ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመለሱ ወጣት ሴቶችን መልሶ የማቋቋም ሥራ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ በለጋሽ ድርጅቶች አጋዥነት የሚፈጸመው የኮሚሽኑ አገልግሎት ዜግነት እና ሃይማኖት የማይለይበት ነው፡፡ ለዚኽም በስደተኞች ጣቢያዎች ከኤርትራ፣ ከሶማልያ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከኮንጎ እና ከሌሎችም አገሮች ለመጡ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ እና ክብካቤ ተጠቃሽ እንደኾነ ብፁዕነታቸው ተናግረዋል፡፡

‹‹ኹሉም ኢትዮጵያዊ የተሻለ ኑሮ ተፈጥሮለት ማየት›› በሚል ርእይ በመንቀሳቀስ አራት ዐሥርት ዓመታትን ያስቆጠረው ኮሚሽኑ የቤተ ክርስቲያናችን የልማት እና በጎ አድራጎት ክንፍ ነው፡፡ በተለያዩ አደረጃጀቶች ተዋቅሮ ከለጋሾች ጋራ የፕሮጀክት ስምምነቶችን በመፈራረም÷ በምግብ ራስን የማስቻል፣ ግጭትን፣ ፆታዊ አድልዎን፣ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሥርጭትን የማስወገድ ምግባረ ሠናያትን በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
*******************************

eoc-dicac logoResponse to Migrant Crisis

This is intended to bring to the attention of international, national institutions, and individuals regarding the current migrant crisis affecting thousands of citizens across Africa, Asia and the middle East, and calls for urgent response to attend social, economic and psychological needs of migrants, whose lives are under constant danger and harassment due to illegal forced migration by means of persuasions and false promises.

1. The overall situation of migrant crises

In recent report by IOM and Migrant Rescue Operations under the auspices of EU and other European entities, about 2000 migrants were drowned in the Mediterranean Sea in 2015 alone. Most of the victims were Ethiopians, Eritreans, Somalis, Sudanese, Syrians and Iraqis. Prior to the arrival at the sea side, the migrants are exposed to hardships, torture, hunger and different forms of exploitation.

As evidenced by 30 Ethiopians who were savagely beheaded in Libya by ISIS, migrants are subjected to torture and deaths because of their religious convictions and consciousness of human dignity. The beheading of 30 Ethiopians has prompted international and national reactions and condemnation directed to ISIS.

It is recently reported that Ethiopians have been stranded in Libya and taken by the radical militants, ISIS group. The stranded group is composed of children, pregnant women in hideout ordeal against the hunt by the ISIS. Such a humanitarian tragedy will likely continue for the years to come.

Both the Ethiopian and International communities are urged to join hands to ameliorate the suffering and inhuman conditions of the migrants.

2. Urgent need for intervention

Realizing the urgency of the matter and understanding the death and live situation of the migrants, by both Ethiopians and others, the Ethiopian Orthodox Church Patriarch together with other religious leaders in the country and outside called for paying and exerting greater efforts to assist the migrants.

To this effect, the Ethiopian Orthodox Church Development and Inter Church Aid Commission together with other pertinent organizations of similar concerns has identified the following areas of interventions, aimed at the current and future migrants. These include:

1. Repatriation of migrants
2. Rehabilitation and integration of migrants with their home communities
3. Provision of psychosocial support.

3. Forms of assistance and collaboration

DICAC would like to appeal to faith based organizations, churches, humanitarian organization and individuals to extend their support in the form of finance, technical assistance, materials and equipment in order that DICAC could meet the critical needs of the migrants.

a. For financial donations, please refer to

COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
Selassie Branch
ACCOUNT No# 1000010883214
SWIFT CODE; CBETETAA
P.O.BOX215
TEL.251 11 551 50 04
FAX. 251 11 55 14 45/22
E-MAIL.CBECOMU@COMBANKETH.ET
ADDIS ABABA/ETHIOPIA

b. For information and other support please refer us;

EOTC DICAC
P.O.BOX 503
Addis Ababa/ETHIOPIA
TEL. 0111 55 35 66/0111 56 30 33
FAX. 0111 55 14 55
e-mail eoc.dicac@ethionet.et
Web site: http://www.eotcdicac.org

Advertisements

One thought on “የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን: በስደት ያሉ ተዘዋዋሪ ወገኖችን ለመመለስ እና ለማቋቋም የድጋፍ ትብብር ጥሪ አቀረበ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: