ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ወደ አኵስም ተዛወሩ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የዓዲ ግራት ሀገረ ስብከትን ደርበው ይመራሉ

?

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ

ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በደቡብ ትግራይ የማይጨው እና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ በክልል ትግራይ የምሥራቃዊ ዞን – ዓዲ ግራት ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተመደቡ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ ብፁዕነታቸውን የመደበው፣ ትላንት ያጠናቀቀውን ቀኖናዊ ጉባኤ አስመልክቶ ዛሬ ጠዋት መግለጫ ከመስጠቱ አስቀድሞ ባሳለፈው ውሳኔ ነው፡፡

የምሥራቃዊ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ደግሞ፣ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ – ሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ ወደ ትግራይ ማእከላዊ ዞን – አኵስም ሀገረ ስብከት እንዲዛወሩ ምልዓተ ጉባኤ መወሰኑ ታውቋል፡፡

ለኹለቱም ብፁዓን አባቶች መልካም የሥራ ዘመን እንመኝላቸዋለን፡፡

Advertisements

One thought on “ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ወደ አኵስም ተዛወሩ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የዓዲ ግራት ሀገረ ስብከትን ደርበው ይመራሉ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: