የምርጫው ድባብ ያጠላበት ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ፤ በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ጥያቄዎች ዙሪያ ሰላማዊ ጥረቱ እና ምክክሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል

 • የኤጲስ ቆጶሳትን ሢመት ጨምሮ በርካታ አጀንዳዎች ለጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ ተላልፈዋል
 • የአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራሮችን ለማሳሰር በአማሳኞች አጋሮች ተሞክሮ ነበር
 • በሰንበት ት/ቤቶቹ ጥያቄ የተቆጡት ፓትርያርኩ፣ ረዳት ሊቀ ጳጳሱን በቀስቃሽነት ከሠዋል

የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት

ከስድስት ያልበለጡ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ትላንት የተጀመረው የ፳፻፯ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ማጠናቀቁ ተገለጸ፤ በነገው ዕለት ጠዋት መግለጫ እንደሚሰጥም ይጠበቃል፡፡

ወትሮ እንደሚያደርገው ኹሉ፣ በስብሰባው መጀመሪያ የአጀንዳዎች አዘጋጅ ኮሚቴ ያልሠየመው ምልዓተ ጉባኤው መነጋገሩን የቀጠለው በቋሚ ሲኖዶስ ተለይተው በቀረቡ የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ መኾኑ ተጠቅሷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው በስብሰባው መጀመሪያ፣ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን የመክፈቻ ንግግር እንዲኹም በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ የቀረበውን ዓመታዊ ሪፖርት አዳምጧል፡፡ ከመነጋገርያ ነጥቦቹ፣ ስለ ሰማዕታት ጉዳይ እና ከስደት ስለሚመለሱ ዜጎች በሚል የተያዙትና ውሳኔ ያሳለፋባቸው አጀንዳዎቹ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ለባሕር ዳር ከተማ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የመደበው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ለቀጣይ ሦስት ወራት በተለዋጭ የቋሚ ሲኖዶስ አባልነት የሚያገልግሉ አራት ብፁዓን አባቶችንም መርጧል፡፡ በዚኽም መሠረት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል መመረጣቸው ታውቋል፡፡

ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ አንድነት በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋራ የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በድጋሚ ያወሳው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ስለሚካሔደው ምርጫ ‹‹አገራችን ሰላም እንድትኾን እንጸልያለን፤ እንማልዳለን›› በሚል የቤተ ክርስቲያንን መልእክት እንደሚያስተላልፍም ተገልጧል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ቃለ ጉባኤዎችን በመናበብ እና በጸሎት መርሐ ግብር ኹለተኛ መደበኛ ዓመታዊ ስብሰባውን ዛሬ እንደሚያጠናቅቅ የሚጠበቅ ሲኾን ነገ ዓርብ፣ ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 መግለጫ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ ከጥቅምቱ ለአኹኑ ምልዓተ ጉባኤው ከአሳደራቸው ዐበይት አጀንዳዎች መካከል የተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት የሚገኝበት ቢኾንም ጊዜው ቤተ ክርስቲያን በግፍ ያጣቻቸውና በሰማዕታትነት ክብር ያከበረቻቸው ልጆቿ የሚዘከሩበት፣ በጭንቅ ላሉት ደኅንነት እና ሰላምም የበኩሏን ጥረት የምታደርግበት ወቅት በመኾኑ ለቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ መተላለፉ ታውቋል፡፡

እንደ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት ኹሉ አወያይ እና አወዛጋቢ ተብለው የተያዙ አጀንዳዎች በሙሉ ከግንቦቱ ምርጫው ጋራ በተያያዘ ባደሩበትና ስብሰባውም ያለወትሮው በኹለት ቀናት በተጠናቀቀበት ኹኔታ፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ገዳማት እና አድባራት ሰንበት ት/ቤቶች ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በአድራሻ ያቀረቧቸውና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለእያንዳንዳቸው ያደረሷቸው ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት አስተማማኝ ምላሽ እስከሚያገኙ ድረስ አግባብነት ያለው ቀጣይ እንቅስቃሴ እና ምክክር እንደሚደረግባቸው ተገልጧል፡፡

በሌላ በኩል በምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዐት ወቅት በቀረበው የመላው ሰንበት ት/ቤቶች ጥያቄ የተደናገጠው አማሳኝ ቡድን፣ የአንድነቱን አመራሮች ለማሳሰር ተጣጥሮ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰንበት ት/ቤቶቹ በራሳቸው ተነሣሽነት ያቀረቧቸውን የብዙኃን አገልጋዮች እና ምእመናን ጥያቄ፣ ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ ነው፤ የማኅበሩ እጅ አለበት›› በማለት የወነጀለው ቡድኑ፣ የወጣቶቹ ሰልፍ እና ጥያቄ ‹‹ከማደራጃ መምሪያው ዕውቅና ውጭ ነው፤ ሁከት ሊያስነሡ፣ ሰላም ሊያደፈርሱ ነው›› በሚል የአንድነቱን አመራሮች ለማሳሰር ያደረገው ሙከራ ሰላማዊነት እና ጥበብ በተመላበት የሰንበት ት/ቤቶቹ ቅድመ ዝግጅት እንዳልሠራለት ተገልጧል፡፡

the pat furious at his aidies failureበፓትርያርኩ በኩልም ቢኾን፣ ‹‹አባ ቀሌምንጦስ ማኅበሩንና ወጣቱን ቀስቅሰው ያደረጉት ነው፤ በየአጥቢያው ከተነሡ ችግር ውስጥ ነው የምንወድቀው፤ ሰላም ጠፋ ማለት ነው፤›› ማለታቸውስ አግባብ ነው? የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን ተፈጻሚነት ለማስከበር፣ ከገቢያቸው በላይ በሚኖሩና ሥራቸውን በአግባቡ በማይሠሩ አማሳኝ የአስተዳደር ሓላፊዎችና ሠራተኞች ላይ ምርመራ እንዲካሔድ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር በሰረጉና ማስረጃ በቀረበባቸው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞች ላይ ርምጃ እንዲወሰድ፤ በአጠቃላይ በየጊዜው ከሙስና እና መልካም አስተዳደር አኳያ ያወጁት ቃላቸው ከተግባራቸው እንዲስማማ መጠየቁ የሰላም ምንጭና ዋስትና ይኾናል እንጂ እንዴት ነው ሰላምን የሚያጠፋው? ሰላምን ያጠፋውስ፣ የሚያጠፋውስ የሰንበት ት/ቤቶቹን አካሔድ ‹‹እንቆጣጠረዋለን›› እያሉ በመፎከር ላይ ያሉትን አማሳኝ አማካሪዎቻቸውን በተለይም ልዩ ጸሐፊአቸውን ንቡረ እድ ኤልያስን መስማታቸው ነው፡፡

Advertisements

5 thoughts on “የምርጫው ድባብ ያጠላበት ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ፤ በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ጥያቄዎች ዙሪያ ሰላማዊ ጥረቱ እና ምክክሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል

 1. Anonymous May 7, 2015 at 12:25 pm Reply

  opsss.the misguided parrot and the most divisive weapon within EOTC, which is HARA, is going to bankruptcy thanks to quick summery of holy synod.chaw eske tikimt yewere gebeta.

 2. Anonymous May 7, 2015 at 4:20 pm Reply

  አቤቱ አምላክ ሆይ ኢትዮጵያንና ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በቸርነትህ ጠብቅ ያለአንተ እውነተኛ ጠባቂ የለምና።

  በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በሙስና የነቀዙ
  በተሐድሶ መንፈስ የረከሱ በሆዳምነት የነፈዙ
  ከገረገራዋ እስከመቅደሷ ድረስ ሰርገው ገብተዋልና አንተ በረቀቀው ሥልጣንህ አስወግዳቸው።

 3. Gashaw Assefa May 8, 2015 at 12:11 am Reply

  Long life to Orthodox

 4. endale May 8, 2015 at 6:47 am Reply

  abetu geta hoy aseben

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: