ሰበር ዜና – ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ ለተሠዉት ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የሰማዕትነት ሥያሜ ሰጠ

ethiopian Orthodox martyrs

 • ዝርዝር መግለጫው በይፋ የሚወጣው በቀጣዩ የጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ ነው
 • በስደት ያሉ የሚመለሱበትና በኑሯቸው የሚቋቋሙበት ጠንካራ ውሳኔ ተወስኗል
 • ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ጋራ የሚሠራ ኮሚቴ ይቋቋማል

በሊቢያ፣ ‹‹ሃይማኖታችን አንክድም፤ ማዕተባችንን አንበጥስም›› ብለው በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነታቸው በመጽናታቸው፣ ራሱን እስላማዊ መንግሥት(ISIS) ብሎ በሚጠራው ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን በሰይፍ ተቀልተው እና በጥይት ተደብድበው የተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች የሰማዕትነት ሥያሜ እንዲሰጣቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወሰነ፡፡

የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአረመኔያዊ አኳኋን የተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ሰማዕት እንዲባሉ የወሰነው፣ በዛሬው ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የመጀመሪያ ቀን የቀትር በኋላ ውሎው በጉዳዩ ላይ በስፋት ከመከረበት በኋላ ነው፡፡

በሊቢያ የሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ እና በረሓ በወሩ መጀመሪያ ስለ እምነታቸው መሠዋታቸው የታወቁት ኦርቶዶክሳውያን፣ ‹‹ወኩን መሃይምነ እስከ ለሞት ወእሁበከ አክሊለ ሕይወት = እስከ ሞት ድረስ የታመንኽ ኹን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለኹ›› /ራእይ ፪፥፲/ ያለውን የጌታችን ቃል ጠብቀው ሃይማኖታችንን አንክድም በማለት የሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃይማኖት መስተጋድላን እንደኾኑ የግድያው ዜና በተሰማበት ማግሥት በቋሚ ሲኖዶስ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በሚያዝያ ፲፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. መግለጫው በአይ.ኤስ አሸባሪ ቡድን በግፍ የተገደሉት ልጆቻችን ቤተ ሰዎች ኹሉ የሰማዕታቱን ስመ ክርስትና፣ ሥዕለ ገጽ(ፎቶ) እና ሙሉ አድራሻ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በተቻለ ፍጥነት እንዲያቀርቡ አሳስቦ ነበር፡፡

በሃይማኖታቸው ምክንያት ለተሠዉት ክርስቲያኖች ሊሰጥ የሚገባው የሰማዕትነት ክብር(ማዕርግ) መኾኑን በውሳኔው ያመለከተው ምልዓተ ጉባኤው፣ ስለ ሥያሜው እንዲኹም እያንዳንዳቸው ስለተሠየሙበት የሰማዕትነት ማዕርግ እና ክብር ዝርዝር መግለጫ የሚሰጠው በመጪው ዓመት ጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደሚኾን በውሳኔው ማመልከቱ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ምልዓተ ጉባኤው በዛሬው ውሎው፣ በስደት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖች እና የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሊቢያን ጨምሮ ለጥቃት ከተጋለጡባቸው አካባቢዎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ቤተ ክርስቲያን ጠንካራ ግፊት ከማሳደር ጀምሮ ተመላሾችን በማቋቋም ረገድ ፋይናንሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ ልቡናዊ ድጋፎችን ማድረግ እንደሚኖርባት የሚገልጽ ጠንካራ ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል፡፡

ውሳኔውን የሚያስፈጽም አካል የሚቋቋም ሲኾን፣ ይኸው አካል ተግባሩን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ጋራ በመተባበር እንደሚፈጽም ተጠቅሷል፡፡ የስደተኞች እና ተመላሾች ጉዳይን በመምሪያ ደረጃ አቋቁሞ በቀጥተኛ እና በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሠራው ኮሚሽኑ፣ ቀደም ሲል የገንዘብ አስተዋፅኦ የሚሰበሰብበት አካውንት በመክፈት ገባሬ ሠናይ አካላትን ማነጋገር መጀመሩ ተገልጧል፡፡

Advertisements

14 thoughts on “ሰበር ዜና – ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ ለተሠዉት ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የሰማዕትነት ሥያሜ ሰጠ

 1. efrem May 6, 2015 at 4:55 pm Reply

  We proud about them

 2. addotcomplex May 6, 2015 at 5:49 pm Reply

  good news !!!

 3. efrem May 7, 2015 at 4:55 am Reply

  Egziabher abatochachn ybarkln betam lib yemiyareka wsanie

 4. ርብቃ May 7, 2015 at 5:45 am Reply

  ይገባቸዋል!!!

 5. Anonymous May 7, 2015 at 6:30 am Reply

  let us give thanks to the synod

 6. Anonymous May 7, 2015 at 6:52 am Reply

  ይበል ነው

 7. Anonymous May 7, 2015 at 8:45 am Reply

  God gives us strength !!!

 8. Anonymous May 7, 2015 at 9:56 am Reply

  Ygebachewal! egziabher yabzan!

 9. burukdess1976 @gmail.com May 7, 2015 at 10:10 am Reply

  Kale Hiywet yasemalin

 10. Anonymous May 7, 2015 at 12:07 pm Reply

  በረከታቸው ይደርብን

 11. Yibeltal Demeke May 7, 2015 at 12:49 pm Reply

  ክርስትናን በቃል ሳይሆን በገቢር የመሰከሩ የዘመኑ ሰማእታት ይገባቸዋል

 12. Anonymous May 7, 2015 at 1:36 pm Reply

  Ameen beraketachew yedaribin

 13. Anonymous May 8, 2015 at 11:21 am Reply

  amen bereketachew yideresen

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: