የወንድሞቻችን ደም ምክንያት ኾኖ አንድነታችን ቢጸና… አንድ መኾን በቀል ነው

ethiopian and coptic christians

ግብጻውያን እና ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት (ሥዕል: ዘሪሁን ገብረ ወልድ)

‹‹የኢራቅ እና የሶርያ እስላማዊ መንግሥት›› (Islamic State in Iraq and Syria) የሚል መጠሪያ ለራሱ የሰጠው ታጣቂ ቡድን፣ ጸጥታቸው የደፈረሰ አገሮችን የወታደራዊ ኃይሉ እንዲኹም እስከ ኹለት ቢልዮን ዶላር የሚገመተው የገንዘብ እና የንብረት ሀብቱ ማጠናከርያ በማድረግ ወደ ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ አሸባሪነት እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡

‹‹የጥንቱን ገናና የእስልምና ሥርዐት›› በ፳፩ኛው ምእት ዳግም ለማስፈን የአምስት ዓመታት ግብ ያስቀመጠው ቡድኑ÷ መካከለኛው ምሥራቅን፣ እስያን እና አፍሪቃን በማካተት እገነባዋለኹ ያለውን ሙሉ በሙሉ በሱኒ አስተምህሮ ላይ የተመሠረተ እስላማዊ ከሊፋ የሚያሳይ ካርታም ይፋ አድርጓል፡፡ በአፍሪቃ ከምድር ወገብ በላይ ሦስት ንኡሳን ከሊፋዎችን የሠየመው ቡድኑ÷ ‹‹የሐበሻ ምድር›› በሚል ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሶማልያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማእከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክንና ካሜሩንን ያካተተ ሲኾን ግብጽ፣ ሰሜን ሱዳን፣ ቻድ እና ከፊል ሊቢያ ደግሞ ‹‹የአልካና ምድር›› በሚል አካትቷቸዋል፡፡

እስላማዊ ከሊፋውን የመገንባት የተስፋፊነት ሕልሙን እውን እናደርጋለን በሚል ለቡድኑ ርእዮት እና አስተዳደር ማደራቸውን ያወጁ በየሀገሩ የሸመቁ ጽንፈኞች እየበረከቱ ናቸው፤ ባለፉት ዐሥር ወራት ብቻ ከቡድኑ ጋራ ማበራቸውን ያወጁ እንደ ቦኮ ሃራም ያሉ ዐበይት ሸማቂዎች ከ30 በላይ ተቆጥረዋል፤ ዋነኞቹ የቡድኑ ታጣቂዎች ኢራቃውያን እና ሶርያውያን ሱኒዎች ቢኾኑም በድረ ገጽ በሚያካሒደው ቅስቀሳና ምልመላው ተነሣሥተው፣ ለመዋጋት እና ለመሞት ፈቅደው የተቀላቀሉት ኮብላይ ተሰላፊዎች(ጂሐዲስቶች) ከ80 በላይ አገሮች እንደተውጣጡና ከ12 ሺሕ በላይ መድረሳቸው ተነግሯል፡፡

በመንግሥት አልባዋ ሊቢያ የሚንቀሳቀሱትና ከቡድኑ ቀጥተኛ ትእዛዝ የሚደርሳቸው ታጣቂ ኃይሎች፣ ከሜዲትራኒያን ባሕር እና ከኤደን ባሕረ ሰላጤ ባሻገር የተዘረጉ የጥፋት እጆቹ ኾነዋል፡፡ ይኸው የጥፋት ጥምረትም ታጣቂዎቹ፣ የቡድኑን ስም በመጠቀምና የሽብር ተግባሮቹን በመቅዳት በግብጽ – ኮፕት እና በኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ላይ በፈጸሙት አረመኔያዊ ግድያ ተረጋግጧል፡፡

ወታደራዊ እና አስተዳደራዊ መዋቅር በዘረጋባቸው ይዞታዎቹ እስልምናን መቀበልን የመኖር እና ያለመኖር ጥያቄ ያደረገው ቡድኑ፣ በአንድ በኩል የሺዓ እስልምና ተከታዮችን ያለርኅራኄ ሲፈጅ፣ ክርስቲያኖችን ጨምሮ የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖች ደግሞ ለሌሎች አመለካከት ቦታ በማይሰጠው መሥመሩ እንዲሰልሙ አልያም የተገዥነት ግብር እንዲከፍሉ ያስገድዳል፡፡ ይህን ባልፈጸሙት ላይ ግን የሽብር በትሩን ይሰነዝራል፡፡ ሃይማኖታችንን አንክድም ያሉትን ግብጻውያንና ኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን በተመሳሳይ ቦታና አኳኋን በግፍ የገደሉት ባለጭምብል የከሊፋው ታጣቂዎች የተናገሩትም፡- ‹‹የመስቀሉ ተከታይ አገሮች መጣንባችኹ! የእኛን እምነት ካልተቀበላችኹ በሕልማችኹ እንኳ ዕረፍት አይኖራችኹም!›› የሚል ፉከራ ነበር፡፡

ከፌስ ቡክ ገጻቸው የተገኘው ተከታዩ የዲያቆን ዓባይነህ ጽሑፍ በአንጻሩ፣ የንጹሐንን ደም በማፍሰሳቸው የአእምሮ ዕረፍት አጥተው የሚቅበዘበዙት ገዳዮቹ ራሳቸው በመኾናቸው በዚኽ ረገድ ፍርድን እና በቀልን በእግዚአብሔር መንገድ መረዳት እንደሚገባ ያብራራል፡፡ ‹‹የወጣቶቹ ወንድሞቻችን ደም ለክርስቲያኖች የጽናት ማኅተም ነው፤›› ያሉት ጸሐፊው፣ ሰማዕትነትን በጥብዐት እና በጸጋ መቀበል ለገዳዮች የእግር እሳት እንደሚኾንባቸው ገልጸዋል፡፡

ይልቁንም የጥፋት ቡድኑ በሙስሊሞች ዘንድ ሳይቀር በተወገዘበት የተስፋፊነት ንቅናቄው ፊትና አገራችን ኢትዮጵያን በትልቁ ከሊፋው ማህቀፍ ዒላማ ውስጥ በከተተበት ኹኔታ፡- አንድነትን አጽንቶ፣ አንድ ኾኖ መገኘት እንደሚገባ ይመክራሉ፤ ሲኖዶሳዊ አንድነትን በመመለስ በኩልም ‹‹የድርሻችንን እንወጣ፤ ከእንባ ወዳለፈ ተግባርም እንሒድ›› ሲሉም ይማጠናሉ‹‹አንድነታችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የሚፈለግበት የጥሪ ደወል የተሰማበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ … የወንድሞቻችን ደም ምክንያት ኾኖ አንድነታችን ቢጸና፣ ከኹለት ሲኖዶስ ወደ አንድ ጠንካራ ሲኖዶስ ብንመጣ ይኽም ሌላ በቀል ይኾናል፡፡ ሞታቸው ምክንያት ይኹነንና እንስማማ፡፡››

*       *       *

Dn. Abayneh Kasse

ዲያቆን ዓባይነህ ካሴ

በተደጋጋሚ በማኅበረሰብ ብዙኀን መገናኛ /social media/ እየጎመዘዘን የተጎነጨነው እየወጋን የለቀምነው የዜጎቻችን ግፍ አኹንም ከኅጽነ ኅሊናችን አልጠፋም፡፡ በነጋ በጠባ እየተጉላላብን ይገኛል፡፡ ከበሻሻ እስከ ሊቢያ የደረሰ የንጹሐን ደም እየጮኸ ዕረፍት ነስቶናል፡፡ ሰማዕታቱ በቅድመ እግዚአብሔር፣ ‹‹በታላቅ ድምፅ እየጮኹ፤ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ÷ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?›› እያሉ ለመጮኻቸው ጥርጥር አይገባንም፡፡ ራእ. ፮፥፲።

በዚኽ ቃል ውስጥ ፍርድ እና በቀል የሚለው የብዙዎቻችንን ትኩረት እንደሚስብ አምናለኹ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንገድ እንደ እኛ አይደለምና ፍርድ እና በቀልን በእርሱ መንገድ ልንረዳው ይገባናል፡፡ እንደ ሰብአ ትካት ምድርን በንፍር ውኃ ሊያጠፋት ይችላል፡፡ እንደ ሰዶም እና ገሞራም ደግሞም ነቢዩ ኤልያስ እንዳደረገው የቁጣውን እሳት ሊያዘንብ ይችላል፡፡ እንደ ግብጽ ስደት ደግሞ በዓይነት በዓይነት እያፈራረቀ መዓቱን ሊያወርድ ይችላል፡፡ እንደ ሐናንያ እና ሰጲራ ‹‹ገንዘባችኹ ከእናንተ ጋር ይጥፋ›› ሊልም ይችላል፤ ደግሞም ‹‹የሚያደርጉትን አያውቁምና›› ሊልም ሥልጣኑ የእርሱ ነው፡፡

ነገር ግን እነዚያ በራእየ ዮሐንስ ላይ ልመና ያቀረቡት ሰማዕታት አንድ መልስ ተመልሶላቸዋል፡፡ ‹‹ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።” የሚል፡፡ ራእ. ፮፥፲፩።

የመጀመሪያው በቀል ነጭ ማልበስ ነው፡፡ ይኽም ክብረ ሰማዕታትን፣ አክሊለ ሰማዕታትን ማቀዳጀት ነው፡፡ እነዚኽ አንድ መቶ አርባ አራት ሺሕ ሕፃናት ስለ ክርስቶስ ፈንታ የተገደሉ ናቸውና ክብረ ሰማዕታትን ተቀዳጅተዋል፡፡ በአፍ ባይመሰክሩም ሞታቸው ስለ ክርስቶስ ስለኾነ አክሊለ ሰማዕታትን አግኝተዋል፡፡ ሰሞኑን ወንድሞቻችን ደግሞ ‹‹ሃይማኖት ካዱ ወይም ታረዱ›› ሲባሉ እንታረዳለን እንጂ እምነታችንን አንለውጥም፤ ክርስቶስን አምላክ ነው ብለን እንዳመንን እንሠዋለን በማለት ገድለ ሰማዕታትን ፈጽመዋል፡፡ የመከራዋን ጽዋ ያለማመንታት ፉት ብለዋታል፡፡ እንዲህ ነው ጥብዐት በሃይማኖት!

እነዚያ አቋማቸውን ለመግለጽ አቅም ያነሳቸው ሕፃናት ስለ ክርስቶስ ፈንታ በመሞታቸው አክሊለ ሰማዕታትን ከተቀዳጁ በአፋቸው የመሰከሩት እነዚኽማ እንዴት ክብረ ሰማዕታትን አያገኙ? ይኽን ሰማያዊ ክብር መቀዳጀታቸው የመጀመሪያው በቀል ነው፡፡ አጥፊውን እርር ኩምትር የሚያደርግ እሳት ነው፤ ምክንያቱም በመግደል እንደማያጠፋን አንገት በመቅላት እንደማይደመስሰን ያይበታልና፡፡

ኹለተኛው መቅበዝበዝ ነው፡፡ የአቤል ደም እየጮኸበት፣ በሚሔድበት ኹሉ እየተከተለው፣ ምድር አልቀበለው ያለችው ቃየን እንደተቅበዘበዘ ሞተ፡፡ እነዚኽም ከእንግዲኽ ዕረፍት አይሰማቸውም፡፡ በቀን ይቃዣሉ፡፡ በሌሊት በሕልም ይመጣባቸዋል፡፡ የንጹሐን ደም ይጮኽባቸዋል፡፡ ወንጀል ሲሠሩ አልተገኙም፡፡ ይኽ ሌላው በቀል ነው፡፡ ሀገርን አይወክሉምና በሀገር ላይ መዐት አንጠብቅም፡፡ ሽፍቶች ናቸውና በያሉበት ቅጣታቸውን ያገኛሉ፡፡ የሚጠጡት ደም ባጡ ጊዜ እንደ እብድ ያደርጋቸዋል፡፡ ለአእምሯቸው ዕረፍት ይነሳቸዋል፡፡ በሕልማቸው ያስደነግጣቸዋል፡፡ እንደተሠቃዩ ይሞታሉ፡፡

ሦስተኛው በቀል የደረሰባቸው ውግዘት ነው፡፡ ሕዝብ እና አሕዛብ አውግዟቸዋል፡፡ ዓለም ጠልቷቸዋል፡፡ ምድር ድርጊታቸውን ተጸይፋለች፡፡ ሙስሊሞች ‹‹ኢትዮጵያን አትንኩ ያለውን ትእዛዛችንን ጥሰዋል›› በሚል አንቅረው ተፍተዋቸዋል፡፡ ‹‹ክርስቲያንን በመግደል የሚገኝ ጽድቅ የለም›› በማለት በየመድረኩ ዐውጀዋል፡፡ መተርጒማኑ የጠቀሱት ገዳዮቹ የሚጠቅሱትን ያንኑ ቁርዓን ነው፡፡ በዚኽም የተነሣ ገዳዮቹ እና ሙስሊሞች ተለያይተዋል ማለት ነው፡፡ ስለኾነም ሙስሊሞችም አውግዘዋቸዋል፡፡

አራተኛው በቀል የሰማዕታቱ ደም ለክርስቲያኖች የጽናት ማኅተም መኾኑ ነው፤ ክርስቲያን እና ሚስማር ሲመቱት ይጠብቃል ይኾናልና፡፡ ለእኛ አይምሰለን እንጂ የእኛ ሰማዕትነትን በጸጋ መቀበል ለገዳዮቻችን እንደ እግር እሳት የሚፋጅ መልስ ነው፡፡ ይፈራሉ ብለው ሲጠብቁ እኛ ግን ግፍአ ሰማዕታትን በጸጋ የምንቀበል ኾንባቸው፡፡ አንድ ሲገድሉ እልፎች ይነሣሉ፡፡ ያረፉት በሰማይ፣ የተረፉት በምድር አንድ ይኾኑባቸዋል፡፡ ያጠፏቸው ሲመስላቸው ይበዙባቸዋል፡፡ በሰይፋቸው ስለት ያመነመኑን ሲመስላቸው እንበረክትባቸዋለን፡፡

አምስተኛው በቀል አንድ መኾን ነው፡፡ በጥቃቅን ጉዳዮች የተለያየን አንድ ብንኾን ይህ ሌላው በቀል ነው፡፡ አሁን አንድነታችን ከመቼውም ጊዜ በተሻለ የሚፈለግበት የጥሪ ደወል የተሰማበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ አልሰማንም ለማለትም የማንችልበት ወቅት ነው፡፡ ክርስትና ተሸንፎ የማሸነፍ ሕይወት የበለጸገበት ጎዳና ነው፡፡ ክርስቶስ ተሸንፎ አሸነፈን፡፡ በወርቀ ደሙ ገዛን፡፡ ለፍቅር በተከፈለ መሥዋዕትነት ረታን፡፡

ክርስትና አይደለም የወንድምን በደል ሞትን እንኳ እንዲኽ ያሥታግሳል፡፡ ታዲያ አባቶቻችን ወደ አንድነት ቢመጡልን እንዴት ያማረ በኾነ፡፡ የወንድሞቻችን ደም ምክንያት ኾኖ አንድነታችን ቢጸና ከኹለት ሲኖዶስ ወደ አንድ ጠንካራ ሲኖዶስ ብንመጣ ይኽም ሌላ በቀል ይኾናል፡፡ ሞታቸው ምክንያት ይኹነንና እንስማማ፡፡

ስድስተኛው በቀል በራእየ ዮሐንስ ላይ ለእነዚያ ሰማዕታት የተነገረው ነው፡፡ እርሱም ‹‹ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ›› የሚለው ነው፡፡ እርሱ አይቀርም፡፡ እግዚአብሔር ሥራውን የሚሠራበት የራሱ የጊዜ ሰሌዳ አለው፡፡ እርሱ ሲደርስ ያደርገዋል፡፡ ምን እንደሚኾን ለጊዜው አናውቀው ይኾናል እንጂ እርሱ ዝም አይልም፡፡ ‹‹ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም›› እንዲል፡፡ ት.ኢሳ. ፷፪፥፩።

እግዚአብሔር ዝም አይልም፡፡ እኛም ዝም አንልም፡፡ እናም ድርሻችንን እንወጣ፡፡ ከእንባ ወዳለፈ ተግባር እንሒድ፡፡

Advertisements

4 thoughts on “የወንድሞቻችን ደም ምክንያት ኾኖ አንድነታችን ቢጸና… አንድ መኾን በቀል ነው

 1. mana April 29, 2015 at 7:47 pm Reply

  በስመአብወወልድወመንፈስቅዱስአሐዱአምላክ፤
  ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ባለንበት ዘመን የአገልግሎት አድማሷን በተለያየመልኩ ለማስፋፋት እየሞከረችብት በትገኝምበት ሳዓት ፤የበግ ለምድ በመልበስ በውስጧ ተደራጅተው ታሪካዊነቷን ከዓለም መድረክ ለማስጠፋት ናቅርሶቿን የሚያጠፉበትን ናየሚበትኑበትን መንገድ ለማስፋት፤ ‹‹አባ ግዓመርዔት ››የተባሉም ዕመናኖቿን ከበረታቸው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ለመበተን ከምንምግዜ በላይ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ በመቃወም በርካታ ግለሰቦች በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡
  በጋምቤ ላከተማ በሚገኙአጥቢያዎች በተለይም በሐመረኖ ኅቅድስት ኪዳነምህረት ካቴድራልና በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እየተደረገ የነበረውና አሁንም መልኩን ቀይሮ እየተደረገ ያለው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ የሆነ ተግባር ናጸረ-ተዋህዶ እንቅስቃሴዎች እየጎሉ በመምጣታቸው በምዕመናን ላይ እየደረሰ ያለውን የአስተምህሮት ልዩነትና ብረዛበቸ ልታመታ ለፍ እንደሌ ለበትበ ማመን አስፋላጊውን ዕርምትና ክትትል እንዲወስዱ የሚከተሉትን ጥቆማዎች አቀርባለሁ፡፡
  የተከበሩአባታችን፡-
  በጸረ-ተዋህዶ ሰፊእንቅስቃሴ ላይ ዋና ተሳታፊ ነበሩ የተባሉ መነኮሳትን ማሰናበትዎ እጅግ አስመስጋኝና ኃላፊነት የተሞላበት ሥራ ቢሆንም መነኮሳቱ አሁንም በአንዳንድ የወረዳና አጥቢያዎች (በላሬ፣በዲማናበመታር) በአጎራባች ሀገረ ስብከት ወረዳዎች (ለምሳሌ በበደሌ) በአገልግሎት ላይ መሆናቸውን የሰሙየ ከተማችን ምዕመናንና ምዕመናት ለምን በሚል አግራሞትና ቁጣበመላው ሁኔታውን እያወሩ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም መነኮሳቱ አሁንም የኑፋቄ ትምህርታቸውን ከማስፋፋታቸው በፊት ከፍተኛ ክትትል ቢደረግባቸው መልካምነው፡፡ከዚህ ባሻገርግ ንእርስዎ ከወሰዱት እርምጃ በኋላ እንቅስቃሴያቸውን በድብቅ በማድረግራሳቸውን በመከለል በአባልነት በመለመሏቸው የሰንበትት ምህርትቤት አባላት የኑፋቄት ምህርታቸውን እየሰጡ ይገኛል፡፡ ይህም የተመረጡ ዲያቆናትና ዘማሪያንን በመጠቀምነዉ፡፡
  በተለይ ምወጣት ሌሊሴ የተባለቸው የሐመረኖኅ ቅ/ኪ/ም/ቤ/ሰ/ት ቤትአባል እና ዲ/ን ሃማኖት (አቡሽ)የተባለው የቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በጽሁፍና በድምጽ ለብዙወጣት የሰንበትት ምህርት ቤት አባላትና ሕጻናት በተደጋጋሚ የኑፋቄት ትምህርት ሲሰጡታ ይተወሳል፡፡
  ወጣት ሌሊሴ በምስክርነቷ ከጀርባ የሚያስተምሯት ግለሰቦች ሥራቸውን በግላጭ መሥራት እንደማይችሉ፤ እንዲሁምለዚህ ሥራ ወጣቶችን እንደሚመርጡ ነገርግን አስተምህሮቱን በተለይ የሚቀበሉትን እንደሚያሰለጥኑ ገልጻለች፡፡በተለይም እንደሚያስተምሩ የምትጠቅሳቸው ሰባኪያን(አባ ትቶ እና አባ ኃይለ ማርያም)እስከአሁን ከእርስዎ ጋር ቃለ እግዚአብሔርን በማስተማርና በማገልገል ላይየሚገኙ ሲሆኑ፤ሌሎችም መምህራን ያል ሆኑ ነገርግን ጉዳዩ ግልጽ እንዳይሆን በጥንቃቄ በሽፋን የሚንቀሳቀሱ ዲያቆናት(እንደነ ዲያቆንና ትናኤል ያሉት)በእርስዎ ተከል ለው የሚያገልግሉ ናቸው፡፡ሌላው ግለሰቧ በስም ያልጠቀሰቻቸው በምታስተምርበት ወቀት አዲስ የመጡና ጠየም (ጠቆር)ያሉሰባኪ መነኩሴ (አባ ኃይለ ማርያም መሆናቸው ተረጋግጧል) ይገኙበታል፡፡ እኚህ አባትም ተባረሩ ከተባሉት ሦስት መነኮሳት አንዱ መሆናቸውና በአሁኑ ወቅትም በመታር አካባቢ በማገልግል ላይ እንዳሉም ለመረዳት ተችሏል፡፡ለዚህዋቢ ግለሰቧ በጽሁፍና በድምፅ ያስተላለፈችው የኑፋቄ ትምህርት ነው፡፡
  በኑፋቄ ትምህርት የተሞላውና በቤተክርስቲያናችን እያገለገለ በአገልግሎቱ ላይ በድፍረት የጽርፈት ቃል የሚናገረው ዲ/ን ሃይማኖት ለአብዛኛው ወጣቶች በሚያስተላልፈው ትምህርት በግልጽ ጸረ-ተዋህዶመሆኑን ከመግለጹ ባሻገር እንደአቋም የሚከተሉትን ኑፋቄያት ያራምዳል፤
  – ቅድስት ድንግል ማርያም እንደማታማልድ፣
  – ቅዱሳት ሥዕላትን ማቃጥል ጽድቅ እንደሆነ፣
  – በቤተክርስቲያን ከነገረ-ክርስቶስ ሌላ ትምህርት (ነገረ-ማርም፣ ነገረ-ቅደሣን፣ ትምህርተ ቅዱሳን መላእክት ወዘተ) እንደማያስፈልግ ወዘተ… ይገልጻል፡፡
  ግለሰቡበዚህ አስተምህሮ ውስጥ ቀንደኛ ተዋናያን መሆናቸውን በመግለጽ ‹‹የገባቸው ናቸው ››ሲል በስም ከሚጠቅሳቸው ተሐድሶውያን መካከል፡-
  1. አባ ኃይለ ማርያም
  2. ዲ/ን ዮሐንስ (ጆን- በአሁኑ በመቀሌ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ)
  3. ዲ/ን ናትናኤል
  4. አባ ትቶ
  5. መምህር ጥላሁን ይገኙበታል፡፡
  ይህ በእንዲህ እንዳለ ዲ/ን ሃይማኖት የተባለውን ቀሳጢ ማግኘት ባልችልም በተሐድሶ አራማጆች መመልመሏንና በድፍረትም ‹‹እኔ ተሐድሶ ነኝ›› ብላ እንደምታ ስተምር በመስማቴ እኔም ሌሊሴን በአካል አግኝቼ አነጋግሬያታለሁ፡፡ ነገር ግን ተሐድሶ የሚባል ድርጅትና የተሐድሶ መምህራን እንደሌሉ፤ እርሷም አባል እንዳልሆነች፤ የቅዱሳንንም ምልጃ እንደምትቀበል ብትናገርም እውነቱ ግን ከዚህ እጅግ የራቀ ስለመሆኑ ከሚከተሉት ንግግሮቿ መረዳት ይቻላል፡፡
  • ለቅዱሳን በተሰጠው ቃል ኪዳን አለማመኗ (ለዚህም በገደለ አቡነ ተ/ሃይማኖት የተጠቀሰውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ ተ/ሃይማኖት ››ዝክርህን ለዘከረ በምልጃህ ለተማመነ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ››የሚል ቃል ኪዳን ገብቷል ብሎ ማመን የክርስቶስን ሥራ መሸፈን ነው ማለቷ፤
  • ‹‹ሥዕለ አድህኖ ተቀባይነት የለውም›› በማለት በቅዱሳን ሥዕላት እምነት እንደሌላት መግለጧ፤
  • ‹‹ መላእክት አይታዩም ሥዕል የላቸውም›› ብላ መቀለዷ፤
  • አቦ ትቶ እና አባ ኃይለ ማርያም ስለታቦት የተሳሳተ ትምህርት ማስተማሩን ማስተባበል ሞክራ ባይሳካላት ‹‹ በእርሱ አትፍረድ፤…የኮርሱ ወረቀት የተላከው ከአዲስ አባባ ነው፡፡ እንደ መጣ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን ነው የተሰጠው…. መጣ አባ ጋ ሄደ፤ እዚያ መምህራን ፈተሹት፣ ከዚያ እንዲያስተምር አደረጉት፡፡ ›› በማለት የሥልጠናው ዶክመንት ከአዲስ አባባ እንደሚመጣ (ከማን…?)፣ ለቤተ ክርስቲያን እንደሚሰጥ (በማን…?)፣ ተፈትሾ ለሥልጠና አገልግሎት እንደሚውል (መምህራኑ እንማን ናቸው…?) የተጠቀሰው የክህደት ትምህርትም በኮርስ መልክ እንደሚሰጥ መናገሯ፣ ወዘተ…
  በዚህ ጉዳይ ላይ አብዛኛው ምዕመን ዘንድ‹‹እመቤታችን ድንግል ማርያም ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይናት››የሚለውን ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ በመቃወም መስከረም 20/2004 ዓ.ም በአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን በዋዜማው የስብከት መርሐ ግብር ላይ ‹‹ትክክል አይደለም‹‹ ብሎ አስተምሯል በሚልስሙ በተደጋጋሚ እየተጠቀሰና መነጋገሪያ ሆኖ ያለውን መምህር ጥላሁ ሶሬሳ በጉዳዩ ምንም እጁ እንደሌ ለበትና እስከአሁንም ድረስ የቅድስትቤተ ክርስቲያን ልጅ እንደሆነ በዚህ አስተምህሮ ተሳታፊ የነበሩሰዎች ( አባ ኃለይ ማርያም ባለ ሁለት ስልጣን ባለቤት ናቸው ናሌሎችም ) እንደነበሩና‹ ‹ማርያም አታማልድም ››ብለው ሲያስተምሩ እንደሰማ፣በአሁን ሰዓት ግን እንደተባረሩ ገልጾልኛል፡፡ይሁንና የመምህራኑ ደቀመዛሙርት ግን እስከአሁን ምድረስ በቅጽረ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ እንዳሉ ይታመናል፡፡በእርግጥ መሰናበታቸውን በዕለተ ሰንበት ባደረጉልን መልዕክት ከእርስዎብን ረዳም በጥቅሉ የሃይማኖት ችግር እንዳለባቸው እንጂየአስተ ምህሮ ታቸው ኑፋቄነት ምን እንደሆነ አልተገለጸም፡፡ ምዕመናኑ ሰሞኑን እንደሚያወሱት መነኮሳቱ በወረዳ ላይ የሚገኙ ከሆነ ደግሞ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ቤተክርስቲያንን የድርጊቱ ተሳታፊ ሊያስብላት ወይም በምዕመናን ዘንድ ተዓማኒነት እንድታጣሊ ያደርጋት ስለሚችል ጉዳዩ ተጣርቶ ለሁሉ ምሊገለጽ ይገባል እላለሁ፡፡
  በተጨማሪም በእንቅስቃሴው ማዕከልነት ከፑኝውዶ አንስቶ ችግር ይፈጥሩ እንደነበሩና የተለያዩ መጻሕፍትን ከአባ ማቴዎስ ጋር ሆነው በስውር ያከፋፍሉ ነበር የተባሉት የአባ መልከ ጼዴቅ ጉዳይም መታለፍ የለበትም፡፡ እኚሁ ግለሰብ ከፑኝውዶ ወደ ጋምቤላ ከተዛወሩ በኋላም አላርፍ በማለት አገልጋይ ዲያቆናትን ኑፋቄ በማስተማር በጥርጥር ባህር እንዲጠልሙ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ ከዚህ ከተማ ጠፍተው ቢሄዱም በአሁኑ ሰዓትበዲማ ወረዳ አካባቢ የተለመደ ድርጊታቸውን እየቀጠሉበት መሆኑ ይነገራል፡፡ ግለሰቡ ከፑኝውዶ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ወስደውታል እየተባለ ያለው 16000ብር እና እንኛግ አማኑኤል ቤተ ክርሲቲያን 150,000 ጉዳይም መረሳት የለበትም መረጃው አስፈላፈጊ በሆነ ሳዓት ኢስካን በማድሬግ የሚንለጥፊ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ከጋምቤላ ቅድስ ኪዳነ ምረት ቤተ ክርሲቲያን ከሐፀደ ሕፃናት የሚገኘው ገቢ 1,800,000 ብር በሰቤካው ጉባኤ እጅ ሳሆን በሀገረ ስብከት መሆኑን፡፡
  የተሐድሶ እንቅስቃሴ በስውር የሚቀነባበርና ለመረጃ ዝግ የሆነ እንቅስቃሴ መሆኑ ባይካድም ችግር ፈጣሪዎቹ ስለተወገዱ በቂ መረጃ በሌለበት ይቆማል ብሎ ማሰብ የዋህነት ሊሆን ስለሚችል በጥልቀት ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ በቅርቡ እንኳን በእመቤታችን የአስተ ርዕዮ በዓል (ጥር 21/2004 ዓ.ም) በሐመረኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ካቴድራል የሰርክጸሎት ላይ የዕለቱ መምህር የነበሩት መምህርሰናይ‹‹… እመቤታችን ሞታለች፤ ሞታም ታማልዳለች ››የሚልፍጹም ትንሣኤዋን የካደ የኑፋቄትምህርት‹‹ አጨብጭቡ›› እያሉ ሲያስተምሩ ተደምጠዋል፡፡ እኚሁ ግለሰብም በተለያዩ ወረዳዎች (በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፑኝውዶ፣) በመዟዟር የተለያዩ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ድርጊቶችን እየፈጸሙ መቆየታቸው ያደባባይ ምሥጢር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡
  ሌላው በግልጽ መረጃያል ተገኘለት ናያልተ ረጋገጠው ጉዳይ በአብዛኛው በተሀድሶ እንቅስ ቃሴ ላይ ተሰማርተው የሚገኙትመነኮሳትና መምህራን እንዲሁም ዲያቆናት ከደቡብ ክልል ከጂንካ አካባቢ የመጡናቸው የሚባለው ነው፡፡ እነዚህም ከመጡበት አገልግሎት በተጓዳኝ በሀገረ ስብከቱና በሰበካ ጉባዔያቱ ምድብ ሥራ ስለሚሰጣቸው በመካከላቸው በነበረ የቀረበ ግንኙነት የተነሳ ጉዳዩን በቀላሉ በጥልቀትና በተግባቦት እንዳስፋፉት ይነገራል፡፡በመሆኑም እርስዎን በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም የሚያማክሩ በመምሰል የራሳቸውን ስው ርሴራሲያ ቀነባብሩ ኖረዋል፡፡ከዚህም አልፎም ቅድስትቤተክርስቲያን የማትቀበላቸውን የምንፍቅና መጻህፍት የእርስዎን የማዕረግ ማህተም (ቲተር) እያደረጉበት አሰራጭተዋል፡፡በዚህምም ክንያት የተከበረስምዎ‹‹የእነርሱ ደጋፊናቸው ››እየተባለ እንዲነሳ አድርገዋል፡፡
  ሌላው በቤተክርስቲያን የውስጥ አሰራር ላይ በወረዳዎች በአገልግሎት ላይ ችግር ወይ ምህጸጽ የነበራቸው ግለሰቦች በዝውውር ወደ ዚህ የመምጣታቸው ጉዳይነው፡፡ ከኢታንግ ወረዳ በዝሙት ምክንያት እጅ ከፈንጅ ተይዘው የተባረሩት አባ ኤርምያስ የተባሉ መነኩሴ ላጭር ጊዜም ቢሆን ወደ ጋምቤላ ተዛውረው እንዲሰሩ መደረጉ ቁጣ በማስነሳቱ እንዲባረሩ ቢደረግም በቅርቡ ተመልሰው በመምጣት በዚሁ ከተማ ያውም ክህነት እንዳለው አገልጋይ መታየታቸው ምእመናኑን ተስፋ በማስቆረጥ ለሌላ አደጋ እያነሳሳ መሆኑ ስጋት ውስጥ ይጥላል፡፡ በሰሙነ የካቲት ኪዳነምህረት ተባረዋል ከተባሉ በኋላ ተመልሰው እንደገና ወደ ሀገረ ስብከቱ የመጡት የሌሎች መነኮሳት ጉዳይም አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ከጋምቤላም በአገልግሎት ወደ መታር የተዛወረው የዲያቆን ቀለመወርቅ ጉዳይ ፈጽሞ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ መሆኑ አነጋጋሪሆኗል፡፡ ዲያቆኑ ከቤተክርስቲያን ዕውቅና ውጪ ልጅ መውለዱን፣ወላጅእናት ምሪፖርት ማድረጓ በመላ ጋምቤላ ከተማ ይነገራል፡፡ይሁን እንጂ ግለሰቡ ለክህነቱክ ብር ባለ መስጠቱ ከአገልግሎት መሰናበት ሲገባው ታሪኩን ወደ ማያውቁት ሕዝበ ክርስቲያን አካባቢ እንዲዛ ወር መደረጉ አጠያያቂ ሆኗል፡፡ይህና መሰል ድርጊቶች በተለያዩ ወረዳዎች ጉዳዩን በሚያውቁ ወይም የሰሙ የወረዳ አጥቢያም ዕመናንና ምዕመናት በእርስዎ ላይ ያላቸው እምነት እንዲሸረሸር ወይም ከእርስዎ እንዲሸሹእ ያደረገ ነዉ፡፡
  በሐመረኖ ኅቅድስት ኪዳነምህረት ካቴድራል በሥራ ላይ በተፈጠረ ችግር የሰበካ ጉባዔ አባላት ሪፖርት ሳያቀርቡ እንዲሰና በቱተ ደርጓል፡፡በምትካቸውም አዳዲስ አባላት እንዲመረጡ ሆኗል፡፡ይሁን እንጂ የተሰናበቱት ሰዎች በአግባቡ ርክክብ እንዳላደረጉና ተተኪዎቹ ምበ ቃለዓ ዋዲ ውመሠረት እንዳል ተመረጡ ይነገራል፡፡ ይህ ጉዳይ የተሐድሶ እንቅስቃሴውን ስለተቃወሙነው የታገዱት፤ ሰ/ትቤቱም ተመሳሳይ ዕጣ ነው የገጠመው፤ ምክንያቱም በዚህ እንቅስቃሴ ቀንደኛ ተቃዋሚዎች ነበሩ የተባሉት ወጣቶች የሚገኙት በዚህ ደብር ነው ወደሚል እጅግ አስጊ አስተሳሰብ ሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲገባና እንዲጠራጠር ያደረገው ስለሆነ እውነታው በግልጽ ቢነገር መልካም ነው እላለሁ፡፡አለበለዚያ በየካቲት 16 በዓለ ንግስ እንደተፈጠረው ጎራ ለለየ ኢ-ክርስቲያናዊ ድርጊትና ፀብ መነሾ ይሆናል፡፡
  አባታችን፡-
  እርስዎ በጋምቤላ ሀገረስብከ ትበሚገኙም ዕመናንና ምዕመናት ዘንድ ያገኙትን ተቀባይነት፣ሞገስና እምነት የሚሸራርፍና የሚያስጠልም ድርጊት ሲፈጸም እያየበ ዝምታ የሚያልፍ ሰው በእውነት በቅድስት ቤተክርስቲያን እድገት ዓይኑ ቀይ የለበሰ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር በእርስዎ አድሮበ አደረገው የአቢያተክርስቲያናት መስፋፋት የሚያዝን ናየሚተክዝ ሰይጣን ብቻ ነዉ፡፡ ባሉት ችግሮች፣በሥራ ላይ በሚያጋጥሙ እንቅፋቶች ዙ ሪያከ ሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ሊገኝ ይች ላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገሮች በእንዲህ ሁኔታ ቢቀጥሉ ውኃ ቅዳ… ከመሆን ያለፈ ጥቅም ይገኛል ብዬ አላምንም፡፡በመሆኑም በዙሪያዎ የሚያገለግሉ ሰዎችን (ዲያቆናትን፣ካህናትን፣መነኮሳትናመምህራንን፣ የሀ/ስብከትና የሰበካ ጉባኤ ሠራተኞችን) መልሰው በጥልቀት የሚያዩበት የሚገመ ግሙበት ጊዜ አሁን እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ስንዴው ከእንክርዳዱ ተለይቶ ምዕመናኑና ምዕመናቱ እውነቱን እንዲያውቁ ቢደረግ መልካም ነው እላለሁ፡፡
  እንዲሁም፡-
  1. በእርስዎ በኩል በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ ዲያቆናት፣ካህናት፣ መምህራንና ሌሎችም አገልጋዮች ጋር ጉባዔ ተደርጎ ካህናቱ የቅድስት ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የበለጠ እንዲያውቁ፣ኑፋቄ የሚዘሩትን አካላት በንቃት ተከታትለው በቀጥታለእርስዎ ጥቆማ በማድረግ እርምጃ እንዲወሰድ እንዲያ ስደርጉ፤እንዲሁም ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከጥፋት እንዲጠብቁ ቢደረግ፤ ለተፈጻሚነቱም ይረዳ ዘንድ ጉዳዩን ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሪፖርት ለማድረግ እንዲመች የጉባዔው ክንውን ቢቀረጽና ቢላክ፤
  2. በቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮዎችና በጸረ-ተሐድሶ እንቅስቃሴ ላይ ያነጣጠሩ የተለያዩ በራሪ ጽሁፎች ታትመው በየክብረ በዓላቱ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ቢሰራጭ መልካም ሲሆን፣ ለዚህም ተግባር የሀገረስብከቱን የህዝብ ግኑኝነት ማጠናከር አስፈላጊ ይመስለኛል፤
  3. ዋናውና በይበልጥ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ፡- ለከተማው ምዕመናንና ምዕመናት በተዋረድም ለወረዳ፣ ለአጥቢያዎች፣ ለሰ/ት/ቤቶች፣ ወዘተ… ጉባዔ ተዘጋጅቶ የተሀድሶምንነትና የአስተምህሮታቸው ኑፋቄነት፣በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እያደረጉ ስላሉት ስውርዘመቻ በግልጽ ለሕዝበ ክርስቲያን ቢብራራ፤በሂደትም በዚህእንቅስቃሴ ተሳታፊ የሆኑሰዎች አባቶችበ ጉባኤያ ደርጉ እንደነበረው ከኑፋቄያቸው የማይመለሱ ከሆነ በግልጽተወግዘው ጉዳዩ በደረጃ ለሀገረስብከ ቱሊቀጳጳስና ለጠቅላይቤተክህነት እንዲሁም ለቅዱስሲኖዶስ ቢገለጽ የሀገረስብከታችንን የስራእንቅስቃሴይበልጥ የሚያስመሰግን፣የእረኝነታችንም ምስክር፤እንዲሁም ከቅድስትቤተክርስቲያን የተጣለብንን አደራ የመወጣታችን ልዩ ማስረጃየሚሆንነው፡፡
  6. ሌላው ሊታሰብበት የሚገባው ጉዳይ ነባር ካህናት በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በሚገኙ የሥራ መደቦች ላይ ቦታ አለማግኘታቸውና ሙሉ በሙሉ የሥራ ዕድሉ ለአዳዲስ አገልጋዮች መሰጠቱ ብሎም ዘወትርእንደባለጉዳይ የመታየታቸው ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ድርጊት ካህናቱ ከእርስዎ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያሻክር፣ በጥርጣሬም እንዲታይ የሚያደርግ፤ ብሎም ታዛዥነታቸው ከልብ በፍቅር ሳይሆን በፍርሃት ለእንጀራ (ደመወዝ) ብቻ ስለሚያደርገው በሚፈጠሩ ችግሮችና አሉባልታዎች ከእርስዎ ጋር በመነጋገር መፍትሔ ከመሻት ይልቅ ከህብረተሰቡ ጋር አብረው በመወገን ሳያውቁት አመጸኛ ሆነው እንዲገኙ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ እነዚህንና እኔያል ዳሰስኳቸውን ሌሎች ጥቆማዎች በመቀበልና በጥልቅ በመርመር የከፋ አደጋ ከመከሰቱ በፊት አፋጣኝ መፍትሔና እርምጃ በመውሰድ እየተረበሸ ያለውን የሕዝበ ክርስቲያን ልብ በማረጋጋት አባታዊ ግዴታዎን ይወጡ ዘንድእምነቴጽኑዕነው፡፡ በዛሬ ዕለት ሚያዚያ 11/202007 ዓ/ት ዲ/ን ናትናኤል በጋምቤላ ሀገረ ስብከት በቆሞስ አቦ ተክለ ሀይማኖት ጠሳሸነት ሥዐተ ቤተ ክርስቲያን እየተጣሰ ዋለ ምከንያቱ ከላይ የተጠቀሰው አግብታ የፈታቸውን በሥዐተ ተክልል ስፈጸሙና ስያስፈጽሙ በጋምቤላ ክልል በጎደሬ ወረዳ መድንኃለም ገዳም ተፈጸመለት ግለስብ በጋምቤላ ሀገረ ስብከት ዋና ፃፍ ሆኖ የተቀጠረ ዲ/ን ነው፡፡

  እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቃት!
  አሜን!

  

  `
  `በጋምቤላ ሀገረ ስብከት በጎግ ወረዳ የተሰራ ተብሎ ሪፖርት የሚቀሪብት ቤተ ክርሰቲያን

 2. TIRSIT WUBIE April 30, 2015 at 1:39 pm Reply

  ቃለ ህይወት ያሰማልን

  በረከታቸው ይድረሰን

 3. Neth I Mins May 2, 2015 at 1:02 am Reply

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን። እኔ በጣም ታናሽ ነኝ በሀይማኖት።ግን እውነት መኖር ቢያቅተን መመስከር መቻል አለብን በተለይ በውጭ ሀገር የምትኖሩ ምእመናን መገዘት መልስ አይደለም። ግን ነገሮችን መለካት ያለብን በእግዚያብሄር ቃል ነው።ጳጳስ ሲመረጥ ሐዋርያት እንዳደረጉት በእጣ ነው መሆን ያለበት ከዚህ ውጪ የሆነ ለእኔ የነገስታቱ ምኞት ማስፈፀሚያ እንጂ የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ነው አልልም። እኔ ይሄ ጳጳስ ተጠራ ብዬ ከየትኛውም ቤተክርስትያን አልቀርም አንድነታቸውን ግን እናፍቃለሁ።ከምን በላይ በሰማይ አባታችን አባታችን ሆይ ብሎ ባስተማረን አንድ እንሁን።
  ወስብሐት ለእግዚያብሔር።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: