የመርሐ ግብር ማስተካከያ፡- የነገው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የጸሎተ ፍትሐት መርሐ ግብር ለኀሙስ ሚያዝያ 15 ጠዋት ተሸጋገረ

  • በነገው የአ/አበባ ነዋሪዎች የመስቀል ዐደባባይ ሰልፍ ቤተ ክርስቲያን መልእክቷን ታስላልፋለች
Holy Synod Miyaziya 13 Meglecha

የቋሚ ሲኖዶስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙበት የዛሬ ሚያዝያ 13 መግለጫ በተሰጠበት ወቅት

ራሱን አይ ኤስ እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን፣ በንጹሐን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ በፈጸመው ግፍ ለገደላቸው ወገኖቻችን በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት እና ጸሎተ ወንጌል ለማድረግነገ ከጠዋቱ 2፡30 – 4፡30 የወጣው መርሐ ግብር ለኀሙስ ጠዋት፣ ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. መተላለፉን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

መርሐ ግብሩ የተላለፈበት ምክንያት፣ በተመሳሳይ ሰዓት መላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሊቢያውን ግፍ በማውገዝ በመስቀል ዐደባባይ ሰልፍ ስለሚያካሒድ እና ቤተ ክርስቲያንም በዚኹ ሰልፍ ላይ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አማካይነት መልእክት ስለምታስተላልፍ እንደኾነ ከጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከሚካሔደው የመርሐ ግብር ማስተካከያ በቀር፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ባሉ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ለሰባት ቀናት የሚቆይ ጸሎተ ፍትሐት እና ጸሎተ ምሕላ እንዲካሔድ የተላለፈው ዐዋጅ፣ ቀደም ሲል በተገለጸው ማለትም ከነገ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚፈጸም ተመልክቷል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “የመርሐ ግብር ማስተካከያ፡- የነገው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የጸሎተ ፍትሐት መርሐ ግብር ለኀሙስ ሚያዝያ 15 ጠዋት ተሸጋገረ

  1. liku April 22, 2015 at 12:30 am Reply

    I hope ethiopians wherever they are and whatever religion they follow will unite at this difficult time . As an ethiopian want to express my condences to the victims family. RIP!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: