ቅዱስ ሲኖዶስ: ጸሎተ ምሕላ ያውጃል፤ በሊቢያ በግፍ ለተሠውት ክርስቲያኖች ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፤ የመታሰቢያ ሥያሜም ይሰጣል

terrorist kills Ethiopian 11

ሰማዕታተ ሊቢያ

 • በሊቢያ፣ በየመን እና በሌሎችም ክርስቲያኖች ለጥቃት በተጋለጡባቸውና የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ በሚገኙባቸው አገሮች ከተጨማሪ ጉዳት ለመታደግ የሚሠራ ኮሚቴ ተቋቁሟል
mother of Eyasu YekunoAmlak

በደቡባዊ ሊቢያ በርሓ ከተሠውት ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች አንዱ የኾነውና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ አጥቢያ የሚገኙት የኢያሱ ይኵኖ አምላክ ቤተ ሰዎች እና ወዳጆች

 • በአዲስ አበባ እና በአህጉረ ስብከት የሰማዕታት ቤተ ሰዎችን እያፈላለጉ የማጽናናት እና የመደገፍ መርሐ ግብር ይካሔዳል
Holy Synod on the excution of Eth Ortho christians in Libya

የቋሚ ሲኖዶስ አባላትና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የተገኙበት የትላንት ሚያዝያ ፲፪ ቀን መግለጫ

 • ከሊቢያው የግፍ ተግባር ጋራ በተያያዘ ባሉ ኹኔታዎች ላይ በየዕለቱ እየተሰበሰበ በመምከር መልእክት ለማስተላለፍ የወሰነው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬም መግለጫ ይሰጣል
Advertisements

2 thoughts on “ቅዱስ ሲኖዶስ: ጸሎተ ምሕላ ያውጃል፤ በሊቢያ በግፍ ለተሠውት ክርስቲያኖች ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፤ የመታሰቢያ ሥያሜም ይሰጣል

 1. Anonymous April 21, 2015 at 8:50 am Reply

  ኀዘኑን ለማዘን ሰብዓዊነት በቂ ነው፡፡ኀዘኑን በቅጡና በተቋማዊ መንገድ፣ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ተላብሶ መወጣት ግን ብልኅነትንና ቅንነትን ሳይጠይቅ አይቀርም፡፡
  አንዳንድ ወንድሞቻችን ቅ/ሲኖዶሱ ገና መግለጫ ሳይሰጥ “ይሄ ጉደኛ ሲኖዶስ ምን ሊል ይኾን?” በሚል ፍረጃ ሲያሟሙቁ ቆይተው፡-(1)መንግሥት እንኳ ለራሱ በተደናበረበት ሰዓት አባቶች በመንበረ – ፓትርያርክ የሰጡትን መግለጫ እየበለቱ ራስን ማጽደቅን፣(2)አስቀድሞ ገና አባት የለንም እያሉ ማሳቀልን፣(3)ብፁዐን ጳጳሳት አባትነታቸው ቢካድ እንኳ ኢትዮጵያዊ የዜግነት ተቆርቋሪነት የሌላቸው ይመስል ስለ ሰቆቃው አንዳች እንዳልተሰማቸው ማስመሰልን፣(4)በተለመደው የግብፅ ኮፕቲክ ሚዛን አባቶችን ለክቶ መቁረጥን ተያይዘውታል፡፡ነውር–ርኵሰት–ጥፋት ነው፡፡
  መጀመሪያ ዘመነ – ሰማዕታት ለኢኦተቤክ እንግዳ አይደለም፡፡ወደ ኢየሩሳሌም ሲደረጉ በነበሩ የሲና በረሃ መንፈሳዊ ጉዞዎች፣በኢየሩሳሌም የመስቀል ጦርነት ወቅትና እሱን ተከትሎ በነበረው ጊዜ በኢየሩሳሌም በነበሩ መነኮሳት፣በዮዲት፣በግራኝ፣በሱስንዮስ፣በመካከለኛው ዘመን ሰሎሞናዊ ነገሥታት፣በደርቡሽ፣በጣሊያን፣በደርግ፣በዘመነ – ኢህአዴግም በአክራሪ እስልምና በ1984/5 ዓ.ም እና በ1998/9 ዓ.ም የበዙ ውሉደ – ጥምቀት ስለ ፀናች ሃይማኖት ተሰይፈዋል፡፡እሱን ኀዘንና የሰማዕታቱን ምስክርነት የኢኦተቤክ በተግባርም በጽሑፍም ወደ ቋሚ ምስክርነት ስትቀይር ኖራለች፡፡ትኖራለች፡፡
  ስለዚህ አሁንም አጓጉል የግብፅ ሚዛንን ከፍ አድርጎ የራስን አባትና ተቋም ከማሳነስ ጎዳናችን ተመልሰን አባቶች የሚነግሩንን በጽሞና እየተከታተልን በአባትና ልጅ ሥርዓት መሄድ የቀናው ጎዳና ነው፡፡እናንተ ወንድሞቻችን(የሐራ ብሎግ አስተዳዳሪዎች) በዚህ ረገድ እያደረጋችሁት ያለው የቤ/ክ ድምጽ የመኾንና ኀዘኑን ላልተገባ አጀንዳ ማጀቢያ ማድረግን ሳይኾን ርቱዕ ኦርቶዶክሳዊነትንና ለኦርቶዶክሳዊነት የተከፈለን ዋጋ ከነ ክርስቲያናዊ ክብሩ፣አሸኛኘቱ፣ዝክሩ፣ቅ/ሲኖዶሳዊ ብያኔው…ለማቅረብ የጀመራችሁት መንገድ የጽድቅ መንገድ ነው፡፡ደስ ያሰኛል፡፡
  የሰማዕታቱ በረከት ይሕን በምታቀርቡ በእናንተ፣በምናነበው በኛ እንዲያድር አምላከ – ቅዱሳን ይርዳን፡፡ኀዘኑን የኀዘን ዳርቻ ያድርግልን፡፡አሜን፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: