ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ: በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ አወገዘ፤ ‹‹በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ እና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት አስፈላጊውን ኹሉ እናደርጋለን››

terrorist kills Ethiopian 11

‹‹ሃይማኖታችንን አንለውጥም›› በማለታቸው በአይ ኤስ የግፍ ተግባር በሰሜናዊ ሊቢያ የሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ ለሰማዕትነት ክብር የበቁት ኢትዮጵያውያን እና ኦርቶዶክሳውያን ወገኖች፤ በረከታቸው ይድረሰን፡፡

Terrorist 2

‹‹ሃይማኖታችንን አንለውጥም›› በማለታቸው በአይ ኤስ የግፍ ተግባር በደቡባዊ ሊቢያ በረሓ ለሰማዕትነት ክብር የበቁት ኢትዮጵያውያን እና ኦርቶዶክሳውያን ወገኖች፤ በረከታቸው ይድረሰን፡፡

 • ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን አሠቃቂ ድርጊት በጽኑ ትቃወማለች፤ አጥብቃም ታወግዘዋለች
 • ጭካኔው የማንኛውም ሃይማኖት ተቋም እና እምነት የማይወክል የአሸባሪዎች ተግባር ነው
 • በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት አስፈላጊውን ኹሉ እናደርጋለን
 • ፓትርያርኩ የአርመን ክርስቲያኖች ዕልቂት ፻ኛ ዓመት ዝክር ጉዟቸውን ሰርዘዋል
 • የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ይታወጃል፤ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል
Holy Synod on the excution of Eth Ortho christians in Libya

መግለጫው ዛሬ፣ ሚያዝያ ፲፪ ቀን ረፋድ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተሰጠበት ወቅት

በስመ አብ ወወልድ መወንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን፡፡

ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ ሀገር በንጹሐን ወገኖች ላይ ስለተፈጸመው አሠቃቂ ግድያ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ከእኩለ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ የዜና ማሰራጫዎች በሰሜን አፍሪካ በሊቢያ የሜድትራኒያን ባሕር ዳርቻ አካባቢ አይ ኤስ በተባለ አሸባሪ ቡድን በንጹሐን ወገኖች ላይ አሠቃቂ ግድያ እንደተፈጸባቸው ዘግበዋል፡፡

በዘገባው፣ ከምኑም ከምኑ የሌሉበት ንጹሐን ክርስቲያን ወጣቶች በታጠቁና ፍጹም ሰብአዊነት በሌላቸው አሸባሪዎች ሲገደሉ የሚያሳየው ምስልም በመላው ዓለም እየታየ ይገኛል፡፡

አሠቃቂው ግድያ ስለተፈጸመባቸው ንጹሐን ወጣቶች ዜግነት እና ማንነት ግልጽ እና አስተማማኝ የኾነ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ቢኾንም እስከ አኹን ድረስ በበርካታ የዓለም የዜና ማሰራጫዎች ሲነገር እንደሚሰማው፣ የዚኽ የግፍ ወንጀል ሰለባዎች ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች መኾናቸውን የዜና ማሰራጫዎቹ አክለው እየገለጹ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፈጣሪ የተሰጠች የማንኛውም የሰው ልጅ ሕይወት ሓላፊነት በማይሰማቸው እና በእነርሱ ላይ ሊደረግ በማይፈቅዱ ምንም ዓይነት ሰብአዊ ርኅራኄ በሌላቸው እንድትቀጠፍ ስለማትፈቅድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን አሠቃቂ ድርጊት በጽኑ ትቃወማለች፤ አጥብቃም ታወግዘዋለች፡፡

ስለዚኽ፣ የዚኽ ግፍ ሰለባ የኾኑት ወገኖቻችን ማንነት ተረድተን፡-

 • በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ እና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት አስፈላጊውን ኹሉ የምናደርግ መኾኑን ሕዝበ ክርስቲያኑ መላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ተገንዝበው ኹኔታውን በትዕግሥት እንዲጠብቁ፤
 • እንደዚኹም የተፈጸመው የጭካኔ ተግባር የማንኛውም ሃይማኖት ተቋምና እምነት የማይወክል የአሸባሪዎች ተግባር መኾኑን ተገንዝበው ኢትዮጵያውያን የኾኑ ኹሉ እንደ ቀድሞው በአንድነት በማውገዝ የዚኽ ድርጊት ፈጻሚዎች ኪሳራ እንጂ ምንም ዓይነት ትርፍ የማያገኙ መኾናቸውን በተግባር እንዲያሳዩዋቸው እናሳስባለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ፤ አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
አዲስ አበባ

Advertisements

13 thoughts on “ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ: በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ አወገዘ፤ ‹‹በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ እና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት አስፈላጊውን ኹሉ እናደርጋለን››

 1. MINILIK SALSAWI April 20, 2015 at 9:47 am Reply

  Reblogged this on MINILIK SALSAWI (ምንሊክ ሳልሳዊ) and commented:
  ቅዱስ ሲኖዶስ: በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ አወገዘ

 2. Anonymous April 20, 2015 at 2:11 pm Reply

  please do not disseminate an expression which is not officially signed and sealed.

 3. Anonymous April 20, 2015 at 2:53 pm Reply

  Wosibhat leEgziabher woleWoladitu Dingil woleMeskelu kibur. Gena inbezalen, insefalen.

 4. meaza meles April 20, 2015 at 3:41 pm Reply

  በኢዮጵያ ኦርቶዶክስ ዋህዶ ቤተክርስቲያንየአዋጅ ጶም ይታዘዝል እናልቅስ እንፀልይ አትዘግዬ ውሳኔ ይሰጠን

 5. Anonymous April 20, 2015 at 5:34 pm Reply

  nefes yimar !!!

 6. zakios April 20, 2015 at 5:54 pm Reply

  አሳፋሪ መግለጫ የዘገየ መግለጫ፡፡ አለም የአወቀውን ቤተሰቦቻቸው በጥልቅ ሐዘን ወገኖቻቸው በዓለም ዙሪያ በጥልቅ ሐዘን ውስጥ በአሉበት እንዲህ ዓይነት ስሜት የሚነካ መግለጫ እጅግ ያስተዛዝባል፡፡
  መረጃ ፍለጋ ከ24 ሰዓት በኀላ ምን ለማግኜት? ምን ለመፍጠር? በዕውነት ሰሜት የጎደለው በእጅጉ አቁሳይ ነው፡፡ ለመሆኑ መታወቂያቸዉን ሟቾቹ ማቅረብ ነበረባቸው ይህንን መግለጫ ከዚህ የበለጠ እርምጃ ለመዉሰድ፡፡
  ሕዝብ እየታዘበ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗ ፍጹም አባታዊ በሆኑ እየተመራች አለመሆኑ ጊዜ ተቆጠረ፡፡ እባካችሁ ይሉኝታ ይያዛችሁ ማስመሠል ይቁም፡፡ እጅግ የቤተክርስቲያኗን ደረጃ ያልጠበቀ መሆኑን ማንም በትክክል ያውቀዋል፡፡
  ይብላኝ ለእናንተ እንጅ እነዚህ ልጆች የሰማዕት ሞት ነው፡፡

 7. Anonymous April 21, 2015 at 4:51 am Reply

  እግዚአብሄር ነፍሳቸው ይማር

 8. Anonymous April 21, 2015 at 6:36 am Reply

  ዜናው የተሰማው እሑድ እኩለ ቀን አካባቢ ነው፡፡ አባቶች ሰምተው ወዲያውኑ ተነጋግረው ፓትርያርኩ ጉዟቸውን ሰርዘው መግለጫ ለመስጠት ሚዲያ ጠሩ ፤ ጠዋት አንስተው ጠበቁ፤ ረፋዱ ላይ አቀረቡ፤ ሚዲያ ወስዶ ለምሳ ሰዓት ዜና ቀረበ፡፡ ወገኖቼ የቤታችን ሁኔታ እያወቃችሁና የግል የቴሌቭዥን ሚዲያ የሌለን መሆኑን እየተረዳችሁ፤ ከዚህ በላይ እንዴት ሊፈጥኑ ይችላሉ?፡፡ የግብጽ ቤተ ክርስቲያንም በባለፈው ጊዜ መግለጫ የሰጠችው ከአንድ ቀን በኋላ ነው፡፡ ይልቅስ ከዚህ በኋላ ማድረግ ያለባቸውን እንዲያከናውኑ የምንፈልገውን ብንጠቁም ይሻላል፡፡

 9. Anonymous April 21, 2015 at 9:16 am Reply

  ምን ሰው አለና ገና ነወው ጉዱ

 10. muluneh yohannes April 21, 2015 at 9:20 am Reply

  አዝነናል እንቃወማለን እናጣራለን…ዝባዝንኬ…የናንተም የመንግስታቹህም አንድ አይነት መግለጫ። መንግስትም አባቶችም የለሉት ሃገር እና ሕዝብ…የራሳችንን ውሳኔ በያለንበት እየተመካከርን እንውሰድ። የዚህን ስቃይ ዋና መንስኤ ከሥሩ እንንቀል። ስደትን የሚያስቆም ስራ እንስራ። ዘላቂ ለውጥ እናምጣ፣ እስከመቼ ይፈራል።

 11. Anonymous April 23, 2015 at 2:08 pm Reply

  we should have to work cooperatly to solve the problem from the scrach .the problem of un employment and we should have to creat socity that fights aginst terrism and love of peace and humanity,work with our countries resource
  .let us avoid acute angle and zero sum game with religious based
  poltics .

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: