ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል: የቅ/ሲኖዶስ አባላት ራሳቸውን በመስጠትና ወቅቱን በዋጀ አካሔድ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያድኑ ጥሪ አቀረቡ፤ስለ አስተዳደራዊ ችግሮችና የወደፊት ስጋቶች ተናግረዋል

His Grace Abune Samuel, Archbishop of DICAC copy

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ፣ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር እና ልማት ድርጅት የበላይ ሓላፊ

 • እኛ ዘንድ ቀኖና እና ሥርዐት ሲጣስ ‘No’ ማለት የለም፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ማስፈጸም ከኹሉም የሥራ ሓላፊዎች የሚጠበቅ ኾኖ ሳለ በዝምታ ማየት ነው፡፡ ምእመናን ናቸው ሃይማኖታችን እያሉ የበለጠ መቆርቆር እያሳዩ ያሉት፡፡
 • መልካም አስተዳደር ባለመኖሩ በየጊዜው በሚፈጠረው ውዝግብ የተነሣ÷ የቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖናዊ ሥርዐት ይጣሳል፤ የእርስ በርስ ግጭት ይስፋፋል፤ ሙስናና ዝርፊያ ይንሰራፋል፤ ገጽታዋ ይዳከማል፤ ኢኮኖሚያዊ አቅሟ ይቀንሳል፤ የሕዝብ ድጋፍ እና የውጭ ዕውቅና ይጠፋል፤ የውስጥና የውጭ ጠላቶቿ ይበረታሉ፤ አንድነቷ ተናግቶ በየመንደሩ ልዩ ልዩ እምነቶች ይፈጠራሉ፤ በመጨረሻም መበታተን እና መከፋፈል ይከተላል፡፡
 • ልቅ ዝርፊያና ሙስና፣ መንፈሳዊነት እና ሰብአዊነት የሌለው መሥመር የለቀቀ ዘረኝነት፣ የፋይናንስ ሥርዐቱን እና የንብረት አያያዙን የሚያዘምን አስተዳደራዊ ሥርዐት እንዳይኖር ከሚቃወም የአመለካከትና የተግባር ድክመታችን መላቀቅ ይገባናል፡፡ ወቅቱን የዋጁ፣ በተግባር የሚተረጎሙ ሕገጋት እና ደንቦች ያስፈልጉናል፤ በረጅምና በአጭር ጊዜ ዕቅዶች መመራት ይኖርብናል፤ ዕውቀትን መሠረት ያደረገ፣ በተሰጠው ሓላፊነት የሚጠየቅ፣ በማያቋርጥ ሥልጠና አቅሙን የሚገነባ የሰው ኃይል ምደባና ሥምሪት ያስፈልገናል፡፡
 • በታሪካቸው ከእነሐርቫርድ የሚወዳደሩ እና የሚልቁ የአብነት ት/ቤቶቻችን ሥርዐተ ትምህርት ከወቅቱ አንጻር ማደራጀት እና በየክልሎቹ ማስፋፋት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችንን ምሩቃን እንደ የክህሎታቸው በሥልጠና ማብቃት፣ በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንት እና ምሁራን በአግባቡ ማሳተፍና መጠቀም ይጠበቅብናል፡፡

ብፁዕነታቸው፣ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር ማእከል ግብዣ፣ ‹‹ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች እና መፍትሔዎች›› በሚል ርእስ ትላንት ማምሻውን በመንፈሳዊ ኮሌጁ አዳራሽ በርካታ ተከታታዮች በተገኙበት ያቀረቡትን የውይይት መነሻ ሐሳብ (public lecture) ሙሉ ይዘት ይከታተሉ፡፡

Advertisements

24 thoughts on “ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል: የቅ/ሲኖዶስ አባላት ራሳቸውን በመስጠትና ወቅቱን በዋጀ አካሔድ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያድኑ ጥሪ አቀረቡ፤ስለ አስተዳደራዊ ችግሮችና የወደፊት ስጋቶች ተናግረዋል

 1. Anonymous April 2, 2015 at 6:12 am Reply

  ከአባቶቻችን ቸር ወሬ ያሰማን

 2. Anonymous April 2, 2015 at 6:42 am Reply

  አባታችን ቃለህይወት ያሰማልን እድሜና ጤና ይስጥልን እንዲህ ዘመኑን የዋጀ አስተሳሰብ ያላቸው አባቶችን ያብዛልን

 3. ቀፀላወርቅ ዓድማሱ April 2, 2015 at 6:51 am Reply

  አቡነ ሳሙኤል የዐላማ ሰው ናቸው፡፡በዘረኝነትም አይታሙም፡፡የቤተክሕነቱን ችግር አንጥሮ በመረዳት ተወዳዳሪ የላቸውም፡፡ለመፍትሔውም ባፍም በመጣፍም ደክመዋል፡፡ለአለቆችና ለሌሎች የቢሮ ሰራተኞች በአስተዳደር ዙሪያ የሚያጠናጠንና በይዘቱ ዓለማዊውን ከመንፈሳዊው የሚያስተናብር የ3 ወር ሥልጠና የተሰጠው በእሳቸው ጊዜ ነው፡፡በቤተክርስቲያን አስተዳደር ዙሪያ የጻፉት መጽሐፍም ግሩም ነው፡፡ሀገረስብከቱ ይሕን ያማረ ሕንጻ የገነባው፣አሁንም የልማት ኮሚሽኑ የበጎ አድራጎት ማኅበራት ሕግ ሳይቀፈድደው የበዛ ልማት የሚያለማው፣በመንገድ ላይ ያሉት ሜጋ የቤተክርስቲያን ፕሮጄክቶች ሂደት ውስጥ የአቡነ ሳሙኤል ድርሻ ትልቅ ነው፡፡በጅማ የክርሰቲያኖች ጭፍጨፋ ወቅት ያሳዩትን ቁርጠኝነትና “እውን በኢትዮጵያ መቻቻል አለን?” የሚል ዝምታ ሰባሪ መጽሐፋቸውን አንረሳውም፡፡በእሱ መጽሐፍ ከመንግሥት ጥርስ ተነክሶባቸው ነበር፡፡ሆኖም እምብዛም ሳይቆይ መንግሥት አቡኑ ያነሱትን አጀንዳ አጀንዳው አደረገው፡፡ትንቢታቸው ዐይኑ ስር ሲተረጎመው ዐየው፡፡ይሕ ሁሉ የትልቅነታቸው ማሳያ ነው፡፡

  ሰው ያለድክመት አይፈጠርም፡፡እናም እሳቸው ለአብነት መምሕራን ብዙም ቦታ ባለመስጠት፣ ለዋልድባ ሰዎች በተለየ መልኩ በማድላት(በዘር ስሜት ሳይሆን እሳቸውም በዚያ ስለመነኮሱ “የትም ተወለድ ዋልድባ መንኩስ” አይነት አቋም አላቸው እያልን እናማቸዋለን)፣ አንዴ ከተጣሉ ከተጣሉት ሰው ጋር የታየውን ሁሉ ቦታ በመንፈግ(ሲጣሉ ያስፈራሉ-አይጣል!)፣ ከአረጋዊ ጳጳሳት ባለመናበብ፣ ለሚዲያው ራሳቸውን ከሚገባው በላይ በማጋለጥ፣ የሚያነሷቸውን የተቀደሱ ክርስቲያናዊ ዐላማዎች ሌሎች ጠልፈው ላልተገባ ፖለቲካዊና ቡድናዊ ፍላጎት ሲጠቀሙባቸው አርምሞን መምረጥ ድክመቶቻቸው ይመስሉኛል፡፡

  የነዚህ ቡድኖች እጅ አቡነ ሳሙኤል በመንግሥት በጥርጣሬ እንዲታዩ፣ በሊቃነጳጳሳትም ለሲመት የተቻኮሉ እንዲመስሉ፣ በስደተኛው ሲኖዶስና በተከታዮቹ ሚዲያዎች(ዘ-ሐበሻ፣ ኢትዮጵያን ሪቪው፣ ኢሳት፣ወዘተ…) የሥም ማጥፋት ኢላማ እንዲሆኑና ያላቸውን አቅም በምልዐት ለቤተ ክርስቲያን እንዳያውሉ እክል ፈጣሪ የነበረ ይመስለኛል፡፡ የተሐድሶ ብሎጎችን የበሬ ወለድ ክስ በአቡነ ሳሙኤል ላይ ማንሳት ለእነሱ እውቅና መስጠት ስለሆነ ንቆ ማለፍ ነው፡፡

  በበኩሌ ስለቤተክርስቲያን ዘመኑን መዋጀት አስፈላጊነት የሚደክሙት ድካም በልቤ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ነው፡፡ስለሆነም ከቡድናዊ ፍላጎት ነጻነቱን ያስጠበቀና ቅድስት ተዋሕዶን እና ቅድስት ተዋሕዶን ብቻ ያማከለ ሀሳብ ይዘው ሲመጡ ማየት ምኞቴ ነው፡፡ፍላጎታቸውን በጉያቸው ሸሽገው ላይ-ላዩን የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ከሚመስሉ ባለ ብዙ ድብቅ አጀንዳ ግለሰቦችና ቡድኖች እንዳይጠለፉብኝ አምላኬን ከመማጸን አልቦዝንም፡፡በተለይ የእሳቸውን ዐላማ ደጋፊ መስለው የትሮይ ፈረስ ሊያደርጓቸው ከሚፈልጉ ሰዎች ባለቤቱ ጠባቂ መልአኩን ልኮ እንዲጠብቻው እጸልያለሁ፡፡

  • anonymous April 2, 2015 at 8:09 am Reply

   ወንድሜ ቀጸላወርቅ እኔም “ከአረጋውያን ጳጳሳት ባለመናበብ፣ ለሚዲያው ራሳቸውን ከሚገባው በላይ በማጋለጥ፣ የሚያነሷቸውን የተቀደሱ ክርስቲያናዊ ዐላማዎች ሌሎች ጠልፈው ላልተገባ ፖለቲካዊና ቡድናዊ ፍላጎት ሲጠቀሙባቸው አርምሞን መምረጥ” የለባቸውም እላለሁ፡፡ አስተያየትህን እጋራለሁ፡፡ ሆኖም አሁንም ብፁዕነታቸው በቡድን እና በግል እየተጠቀሙባቸው ያሉትን ያስተውሏቸው፡፡ እስከአሁን ሰንብተው ይህን ጥናት ለማቅረብ ይህንን ጊዜ የመረጡበት ምክንያትም እነኚሁ ቡድንተኞች የፈጠሩባቸው ተጽዕኖ ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ ከሁሉም የከፋውን በአረጋውያኑ አበው የሚታየውን ድክመትና የትውልድ ክፍተት በማጥበብ ትውልዶቹን ያናብቧቸው፡፡ ቀጥተኛነታቸው እንደ ደካማ ጎን ተጠቅመው ሊያጣሉዋቸው የሚሰሩትን ግለሰቦችና ቡድኖች ሊጠነቀቋቸው የሚገባ ይመስለኛል፡፡

 4. yared Abebe April 2, 2015 at 8:30 am Reply

  እግዚያብሄር አባት ሆይ እባክህ ደጋግ አባቶችን አብዛልን !
  ቸር ወሬም አሠማን !
  እባካችሁ አባቶች በወንድሞች መሃል ያለውን አለመግባባት ፈታችሁ ደጋግ ነገሮችን ቤተክርሥቲያናችን ላይ እንድንሠማ አድርጉን ?
  እኛ እኮ በጭንቀት አለቅን ግራም ተገባ እረ በመቤታችን መላ በሉ አባቶች ?
  እግዚያብሄር አምላካችን ሆይ ደግ ነገርን አሠማን ! ! !
  አሜን +
  አሜን +
  አሜን +

 5. Anonymous April 2, 2015 at 10:36 am Reply

  Egzeher yestelen abun samuel endhi nw abat

 6. Anonymous April 2, 2015 at 10:57 am Reply

  ልጅ ያሬድ አሁን እናት ቤተክርስቲያናችን የልጆቹዋን / ካህናትና ምእመናን/ ሁለንተናዊ ድጋፍ የምተፈልግበት ወቅት ሰለሆነ
  የበኩልዎን የልጅነትዎን ድርሻ ያበርክቱ እንጂ አይጨነቁ

  • Anonymous April 2, 2015 at 1:04 pm Reply

   እግዚአብሔር ደጋግ አባቶችን ያቆይልን ያብዛልን!!!!!!!!!!

 7. zakios April 2, 2015 at 12:30 pm Reply

  የቀንቋ አጠቃቀማቸው የቤተክርስቲያኗን ትውፊት የያዘ ባይሆንም መሠረታዊ ችግሩን በትክከል ብለውታል፡፡ ዋናው ቁምነገሩ መፍትሔው ምንድን ነው?
  1.የቀኖናው መጣስ የአመጣው ችግር ከላይ እስከታች ቤቸክርስቲያኗን እየናጣት 25 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ በአባቶች መካከል ዕርቀ ሠላም ጊዜ ሳይሰጠው መጀመር አለበት፡፡ የዕውነት ለቤተክርስቲያኗ የሚታሰብ ከሆነ፡፡ ይሔ ጉዳይ ከካሕናት አልፎ ሞዕመኑ ድረስ ዘልቆ በየአገሩ በየአጥቢያው መናቆር ከተያያዘ ቆይቷል፡፡
  2. ቤተክርስቲያኗ ምዕመናንና ሐብቷን በሥርዓት የሚያስተዴድር መመሪያ ሊኖር ይገባል፡፡ አሁን በሚተየው ከሆነ ከአበቶች ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ ሙስና ዘረኝነትና ቤተሰባዊነት በግልጽ የሚታይ ነው፡፡
  3. በአሁኑ ዘመን የሚታየው የአገልጋዮች የብቃት ማነስ ጎልቶ ይታያል፡፡ ክህነት በዝምድና በአገር ልጅነትና በዘር አድሏዊነት ይሰጣል፡፡
  የአሁኑ አካሔድ በአጭር ካልተቀጨ የቤተክርስቲያኗ የወደፊት ችግሯ ነው፡፡
  ዋናው መናገሩ ሳይሆን ደፍሮ እዚህ ላይ መቆም አለበት ብሎ ሲኖዶሱ አቋም ላወስድ ይገባል፡፡

 8. Anonymous April 2, 2015 at 1:14 pm Reply

  bereketewe yederebene yaberetawe

  • anonymous April 2, 2015 at 6:10 pm Reply

   Egna wusit andinetina metesaseb kelele eminetina betekirstianin kewuchi telat endet enitebikalen? Ewunet yehulachinim alama midirawi/sigawi bicha hone? Hulachinim nege yeminimot mehonachinin eyasebin bego begowun enisira. Lebetekirstian telatoch metekemia yehasabachew siket mesaria anihun.

 9. Tewodros Abebe Amare April 2, 2015 at 8:00 pm Reply

  እንደው እኝህን ታላቅ አባት ስወዳቸው። ሀገር ቤት እያለሁ ፅሁፋቸውንም እከታተል ነበር፣ እግዚአብሄር አምላክ ፀጋውን ያብዛሎት ብፁህ አባታችን። በአሜሪካን ሀገር ክርስትና አደጋ ውስጥ ነው እና ህዝቡ ፈጥኖ አባቶች ፈጥነው ሊታደጉ ይገባል

 10. genetemaryam April 3, 2015 at 3:27 am Reply

  ብጹዕ አባታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

 11. Anonymous April 3, 2015 at 1:39 pm Reply

  his holiness ABA Samuel may God z almighty boosts his Spirit up on you in order to save z historic Apostolic and Holy and our mother church.O our Spritual Mind u All prists decons and laities make daily preyar to come in to ur power in addis abeba hagere sibket.

 12. Anonymous April 3, 2015 at 2:05 pm Reply

  አባቴ፣ የቅዱስ ሺኖዳን አይነት መንፈስ ሁለት እጥፍ ፈጣሪ ይስጦት፡፡ በበኩሌ ስለቤተክርስቲያን ዘመኑን መዋጀት አስፈላጊነት የሚደክሙት ድካም በልቤ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ነው፡፡

 13. Anonymous April 3, 2015 at 9:09 pm Reply

  ብጹዕ አባታቺን ቃለ ሕይወት ያሰማልን ቤተክርስቲንን የሚያጠፉ ብዙ እደቃ የተቀመጡ እሉ/

 14. Anonymous April 4, 2015 at 12:14 pm Reply

  ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳሙኤል በቅርብ አውቃቸዋለሁ፤ በዋልድባ ገዳም ሥርዓተ አበውን ጠብቀው መጽሐፈ መነክሳትን ጠንቅቀው የተማሩ በገዳሙ የተልዕኮ ተግባር በተማኝነት አበው መነኮሳትን እየታዘዙ ያደጉ ናቸው። የመጽሐፍታት ቁንጮ የአምላክ ፍጹም ቃል መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ቃልነቱን እደጠበቀ የዘመኑ የሥልጣኔ አስተዳደር ጥበብ ቁንጮ ነው ብለው ያስተምራሉ፤ በዓለም ካለው እውቀት ሁሉ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተራቀቀችበት የኦርቶድክስ ተዋህዶ እምነት የሚያስንቅ ማንም የለም ብለው ያምናሉ። በአስተዳደር አዋቂነታቸው፣ ነገሮችን በቀላሉ የመረዳት ክህሎታቸው፣ የውሳኔ ሰጭነታቸውና ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት ብቃታቸው ከፍተኛ ነው። ብዙ ከመናገር ይልቅ ብዙ ማዳመጥን ይመርጣሉ፤ አነጋገራቸው ውሱንና በቁምነገር የታጠረ ነው። የአመኑበትን አቋማቸውን ለማስቀየር ከፍተኛ ጥንካሬን ይጠይቃል።

  የዘመኑን የአስተዳደር ጥበብ በመንፈሳዊ ስልት ቀምረውና ሞርደው ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር እንዲጠቅም የማድረግ ገና ተቀድቶ ያላለቅ ዕውቀት እንዳላቸው ምንም ጥርጥር የለኝም።

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን በማፍቀር እረገድ ተውዳዳሪ የላቸውም፤ ቤተ ክርስቲያንዋ ያሳለፈቸውን ውጣውረድ፣ ለሀገርና ለወገን ያደረገችውን ውለታ ሲናገሩ በፈጹም በስሜት ተውጠው ነው፤ በተረጋጋ የመናገር ችሎታቸው የአድማጭን ልቦና የመሳብ ችሎታቸው ልዮ ነው። አቡነሳሙኤል ቤተ ክርስቲያናችን አሁን በእኛ ዘመን ካፈራቻቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ቀዳሚ ተራ የሚሰጣቸው ናቸው።

  እርግጥ ነው ይህን ብቃታቸውን ለማደናቀፍ በዘመኑ የዘመኑን የመናገር በነጻነት ተጠቅመው እንደፈለጉ የሚናገሩ አፍ እንዳመጣ የሚዘባርቁበት በመሆኑ እንዳንድ ቅጥረኞች ከግለሰባዊ ጥላቻና ሰይጣናዊ ቅናት በመነሳት ብዙ ሊያወሩ ይችላሉ፤ አይገርመንም! አይደንቀንም! ለፈጣሪው የማይመለስ ጠማማ ትውልድ ለፍጡር ይመለሳል ብሎ ማሰብ ከሰውነት የአስተሳሰብ ተራ መውጣት ነው።

  ለብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳሙኤል እረጅም ዘመን እንዲሰጥል የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አምላክ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን።
  ከሀገረ እንግሊዝ ፤ለንደን ከተማ

 15. Anonymous April 5, 2015 at 9:57 am Reply

  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ኢሀዲግ ለ23 ዓመታት እየፈጸመ ያለው መሰሪ ተግባር፡-
  • እቺ ነፍጠኛ ቤተክርስቲያን
  • የድህነት ፊት አውራሪ
  • ማህተሙም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ይወልቃል! ይወልቃል!
  • ለህጻናት የሚሰጠው ቁርባን ለህጻናት የጤና ጠንቅ ነው፤
  • …..
  • …..

 16. ስምዓ ጽድቅ April 5, 2015 at 10:57 am Reply

  ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የሚጹፏቸው ምጻህፍት እና የሚያድርጓቸው ንግግሮች በሙሉ የቤተክርስቲያኗ መሰረታዊ የሆኑ ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ እና መጻኢ የቤተክርስቲያኗ ጉዞ ቀና እና ትክክለኛ እንዲሆን የሚያመላክቱ ናቸው።
  ይ ሁን እንጂ የቤተክርስቲያኗ እድገትዋን ሳይሆን ውድቀትዋን የሚመኙ ሰዎች እሳቸው በሚጹፏችው መጻህፍትና በሚያድርጓቸው ንግግሮች የጥፋት መርበባቸውን ከመዘርጋት ኣልቧዘኑም:: ስለሆነም ይህ ቀንና የሆነ ኣላማ ለግዚው የተዳከመ ቢመስልም ከጊዜ በኋላ ግን ግቡ መምታቱ ኣይቀርም ::
  እግዚኣብሔር ሀግራችን እና ቤተክርስቲያናችንን ይባርክ ለብጹዕ ኣባታችንም ረጅም ዘመን ይስጥልን ።

 17. Anonymous April 7, 2015 at 5:31 am Reply

  Abatache rejem zemen yestwot

 18. Anonymous June 27, 2015 at 7:43 pm Reply

  let ‘s GOD Help our respect father honarable aba samauel

 19. Anonymous June 27, 2015 at 8:30 pm Reply

  tadia be’atbiachin afrso yemikeds menekusie ele min yilalu ?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: