ፓትርያርኩ ዛሬ በሕግ አፍራሽነት ይጠየቃሉ፤ መመሪያቸው በአ/አበባ ሀ/ስብከት ዘለቄታዊ ሰላምና አንድነት ላይ ያሳደረው ስጋት ቋሚ ሲኖዶሱን አሳስቧል

His Grace gen secretary of the holy synod and His holiness aba mathias

 • ፓትርያርኩ ‹‹አልመራኹትም›› በሚል ያፈኑት የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ እና የዋና ሥራ አስኪያጁ ጥያቄ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አቅራቢነት ቋሚ ሲኖዶሱ ዛሬ ይወያይበታል
 • ረዳት ሊቀ ጳጳሱ፣ ፓትርያርኩ መመሪያቸውን ከቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ሕግና ከሀ/ስብከቱ ዘለቄታዊ ሰላም አንጻር መዝነው የእርምት ማስተካከያ እንዲያደርጉ በድጋሚ አሳስበዋቸዋል

A.A Diosces Head Office

 • የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት በወረራ መልክ በመቆጣጠር ስለ ሥዩማን ሥራ አስኪያጆቹ ምደባ ያብራሩት እነዘካርያስ ሓዲስ፡- ‹‹ወደ ቤታችን ገባን፤ ትክክለኛ ቦታችንን ይዘናል›› እያሉ ነው
 • በየአጥቢያው ኑፋቄንና ግብረ ሙስናን ለማጋለጥ የሚደረገውን ጥረት በማስተባበር አስተዋፅኦ ያለውን የሀገረ ስብከቱን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራር የማፍረስ ዕቅድ ተይዟል
 • ሰንበት ት/ቤቶች፣ አማሳኝ አለቆች እንዲገሠጹ ቅ/ሲኖዶስ ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲኾን መጠየቃቸውን ተከትሎ የአንድነቱ አመራሮች ‹‹ወፍ ዘራሾች›› በሚል በፓትርያርኩ ተዘልፈዋል
 • ውዝግቦችን በመፍጠርና በሽፋንነት በመጠቀም ከምዝበራ ተጠያቂነት ራሱን ለማዳን የሚላላጠው ቀንደኛው አማሳኝ ኃይሌ ኣብርሃ፡- ‹‹መንግሥት ሐራ ብሎግን እንዲዘጋልን›› ሲል ጠይቋል

*       *       *

 • ‹‹እርስዎ ሲያጠፉ የሚያርምዎ ይህ ጉባኤ ነው፤… የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለረዳት ሊቀ ጳጳሱ ነው፤ በሥራ አስኪያጁ ሥያሜ ረዳት ሊቀ ጳጳሱ ይኹንታውን ካልሰጠ እንዴት እና ከማን ጋራ ነው ተስማምተው የሚሠሩት?››

/ከትላንት በስቲያው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ‹‹እኔ ያልመራሑበትን አጀንዳ ልትነጋገሩበት አትችሉም›› በሚል ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ እና ከዋና ሥራ አስኪያጁ በተደጋጋሚ የቀረቡላቸውን ማሳሰቢያዎች እና ማስታወሻዎች ላፈኑት ለፓትርያርኩ ከጉባኤው አባላት የተሰነዘረ ምክርና ጥያቄ/

*       *       *

his grace abune Kelemntos

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ኹላችንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት በየደረጃው ተሰጥቶናል፤ የቆምንለት ዓላማ ለቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ታማኝ መኾንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ ነው፤ ቅዱስነትዎ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንደመኾንዎ መጠን ለሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መከበርና ማስከበር ግንባር ቀደም ሓላፊነት እንዳለብዎ አይዘነጋም፡፡ ነገር ግን በቅዱስነትዎ የተላለፈው መመሪያ ተቀራርቦና ተወያይቶ በመተማመን ቤተ ክርስቲያኒቱን የመምራትና የማስተዳደር መንፈስን የሚጋፋ ከመኾኑም በላይ የሕገ ቤተ ክርስቲያኑን አንቀጽ 53/8 እና በሥሩ ያሉትን ንዑሳን አናቅጽ በእጅጉ የሚፃረር ነው፡፡

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሚመደበው፣ በፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ተመርጦ ሊቀ ጳጳሱም በሕጉ መሠረት የመረጡትን ሥራ አስኪያጅ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ በማቅረብ ሲኾን በቀረበው ሥዩም ላይ ፓትርያርኩ ሲስማሙ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ፊርማ ይሾማል፤ ይላል፡፡ ይህም በቤተ ክርስቲያን አድሏዊ አሠራር እንዳይኖርና የጋራ ስምምነቱ ለሰላም ያለውን ሚና በመገንዘብና እርስ በርስ ያለውን መዋቅራዊ መከባበር የሚያሳይ ነው፡፡

የተላለፈው መመሪያና ትእዛዙ፡- መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን ሕግ፤ የሕግ የበላይነት የሚለውን ፅንሰ ሐሳብ፤ የሀገረ ስብከቱን፣ የሠራተኞችንና የምእመናንን አንድነትና በመንፈሳዊ ሕይወት ተከባብሮና ተፋቅሮ የመኖር ኹኔታን እንዲኹም ሰላምን የሚሸራርፍ በመኾኑ በአፈጻጸም ለመተግበር በእጅጉ እንቸገራለን፡፡ መመሪያውን ከቤተ ክርስቲያኗ መሠረታዊ ሕግ፣ ከሀገራችን ነባራዊ የሕግ ድንጋጌዎች አንጻርና ከሀገረ ስብከቱ ዘለቄታዊ ሰላምና የልማት አቅጣጫ አኳያ እንዲገመግሙትና የእርምት ማስተካከያ እንዲያደርጉ በድጋሚ አሳስባለኹ፡፡

/በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ ‹‹በተሰጠው መመሪያ ላይ ቅዱስነትዎ ከቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ሕግ፣ አሠራርና ሰላም አንጻር ማስተካከያ እንዲደረግበት ማሳሰብን ይመለከታል›› በሚል ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ለኹለተኛ ጊዜ ለፓትርያርኩ በአድራሻ ከጻፉት ማሳሰቢያ/

Advertisements

13 thoughts on “ፓትርያርኩ ዛሬ በሕግ አፍራሽነት ይጠየቃሉ፤ መመሪያቸው በአ/አበባ ሀ/ስብከት ዘለቄታዊ ሰላምና አንድነት ላይ ያሳደረው ስጋት ቋሚ ሲኖዶሱን አሳስቧል

 1. Anonymous March 27, 2015 at 6:07 am Reply

  your one-sided biased approach is playing its role to make things complex.I’m sick of your hate driven news.You are roaring day and night as if you are a soldier of EOTC, but things are always going in contrast of what you wish.Your idea is getting and getting defeat b/c you are moving with a bad motive. Be honest to yourselves,try to be independent,insert in your dictionary the word accommodation,avoid insults and defaming words.I dare to say you are the most divisive, hate agent, group-minded medium within our beloved EOTC.That is why you are not successful.You regularly try to incite Sunday School students against the institution and its leaders.not good approach.Be part of the solution than making things complex by being for one a prosecutor and for the other a defendant.

 2. nehmiashishay March 27, 2015 at 6:38 am Reply

  egxier yibarikachu ye hara tewahido azegajoch

 3. Kuba March 27, 2015 at 6:40 am Reply

  Oh My God

 4. Anonymous March 27, 2015 at 6:58 am Reply

  ካልደፈረሰ አይጠራም።ፓትርያርኩ እንዲህ ፈጽመው ማበዳቸው መልካም ነው ምን አልባት የኤልያስ ዲያብሎሳዊ ስራ እየቆየ ይገባቸው ይሆናል። ግን ፓትርያርኩ አእመረ መናፍቅ መሆኑን ዘንግተውት ነው? ንቡረ እድ አማሳኝ ዘራፊ ቀማኛ በምስኪን ካህናት እጅ መንሻ የከበረ ሌባ መሆኑን አጥተውት ነው ? አባ ቃለ ጽድቅስ ቢሆን ቤተክርስቲያኑንየከዳ እና መናፍቅ ሆኖ ሳለ ባልደከመባት በማያውቃት አና በማታውቀው ቤተክርስቲያን ውስጥ ቦታ ሊሰጠው ይገባ ነበር? ማርያምን ፓትርያርኩ አብደዋል። እኛስ ምን እናድርግ ? ቤተክርስቲያን የወንበዴዎች ዋሻ ስትሆን አይተን እንዳላየን ለምን ዝም እንላለን? ማኅበራት ነን የምንል ድምፃችንን ለምን አይሰማም? ሰበኪያንስ ለምን አንነሳም? ዘማር ያንስ ለምን አንጮህም? መንግስትም በቤተክርስቲያን ላይክንዱን ያከበደው የእኛን ፍዝነት አይቶ ይሆን? ነው ወይስ አያገባኝም ብለን ይሆን?ምእመናን እባካችሁ በአገኘነው አጋጣሚ ድምፃችንን አናሰማ ። ዘራፊና አማሳኝ ኤልያስን ሁለቱን መናፍቃን አእመረ እና አባ ቃለ ፅድቅን ካድሬው የማነን እንቃወማቸው አንቀበላችሁም እንበላቸው

 5. Alebel Atalel March 27, 2015 at 8:33 am Reply

  መረጃዎችን ለአንባቢያን ለማድረስ የምታርጉት ጥረት እጅግ የሚያበረታታ ነዉ በመሆኑም ህዝበ ክርሲቲያኑ እንዳያዉቀዉ ይፋ እንዳሆን የሚፈልጉ እና እንደ ይሁዳ በደዲናር እየተገዙ የሚኖሩ አማሳኞች የሐራ ተዋህዶ ብሎገ ለማዘጋትጅ ደፋ ቀና የሚሉ አሉ ነገር ግን እዉነት የሆነነን ነገር በእግዚአብሔር ይሆናል፡፡ እናም ሁሉን በእርሱ ላይ ጣሉት!

 6. […] Source:: haratewahido […]

  • Anonymous March 27, 2015 at 10:45 am Reply

   ደረጀ ነጋሽ ወይንዬ ተክለሃይማኖት የተሰኘ ሕገ-ወጥ ማኅበርህ በታላቁ አባት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ታግዶ ከደብረ – ብርሃን ሲወገድብህ ብሎግ ከፈትኩ ብለህ ደግሞ ማፋዘዝ ጀመርክ፡፡

 7. Anonymous March 27, 2015 at 12:59 pm Reply

  አይ እናነተ መሳደብ ነው አላመቹ?መለያየት ነው አላመቹ? ግበራቹ የሚሳየኝ ይህንኑ ነው፡፡

 8. yemane March 28, 2015 at 4:28 am Reply

  ” እርስ በእርስዋ የምትለያይ መንግስት አትፀናም ቤትም እርስ በአርሱ ከተለያየ አይቆምም”።

 9. nehmiashishay March 30, 2015 at 6:34 am Reply

  እና ምነው አቶ የማነ ቤተ ክርስትያን እኮ አልተለያየችም የተለያየው የሰው ሃሳብ ነው ይህም ሐወርያትም አጋጥማቸው ነበር መፅሐፍ ቅዱስ የምታንብ ከሆነ። ስለዚህ ግለ ሰዎች ቢለያዩ እንዲስማሙ በፀሎት እናስባለን ካልተስማሙ ግለ ሰዎች ብነጠሉ ምንም አይደለም ቤተ ክርስትያን ግን ከእገዚአብሔር ስለ ሆነቸ መሰረቷ ከአለት ነውና አትናወጥም ስለዚህ ከመንግስተ ዓለም የሚወግን ይጠፋል ከእገዚአብሔር መንግስት የሚወግን ይፀናል

 10. Anonymous April 13, 2015 at 5:08 pm Reply

  ዲቁና ቤተ ክርስቲያንችን የሥርዓት መጻሕፍት ከተደነገጉት የሥልጣነ ከህነት ደረጃው አንዱ ነው፡፡
  አንድ ሰው ዲንቁና ሲሆን ከሁሉ በፊት ቤተ ክርሲትያኑን በትጋት ለማገልገል ቤያዘው ስልጣን ምእመናን በጸሎቱና በዕወቀቱ ሊረዳ በነነፍሰም ከሚነጥቃቸው ከፋ ነገር ሁሉ ሊታደጋቸው፡፡ ነው ፍት
  እንደ በቴ ክርስቲያናን ሥርዓት አንድ ወጣት የዲቁናን ማዕረግ ለመቀበል የሚጠበቁበት መስፈርቶች አሉ ፡፡ በመጀመሪያ ደረጀ እድሜው ይሀንን ሐላፊነት ተረደቶ ቤተ ክርሲቲያን የምጠብቅበትን እንዲያሟላ ይረዳዋል ፡፡
  ሁለጠኛው መስፈ ት ደግሞ የዕጩ ዲያቆን ድንግልና ነው ፡፡ ተሿሚው ዲቁን ከመቀበል በፊት ከተቃሪያን ጾታ ጋር በግብር ሥጋ ያልተዋቀወቀ መሆን ይኖርበታል፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ስለ አምነቱ ያለው ቀናኢነት የተመሰከረለት መሆን አለበት፡፡
  አንድ ዕጪ ዲያቆን ይህ ሥልጠና ሲሰጠው እንደ ቀዳሜ ቅዱስ ስማዕት ቁዱስ እስጢፋኖስ ለተሾመላት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሲል ራሱን ለሞት አሳለፎ እስከመስጠት የሚደርስ ነው፡፡
  እንደ ቤተ ክርሲቲያን ሥርዓት አንድ ደያቆን ሥልጣነ ክህነቱን ከማግኘቱ በፊት ከቃል ንባቢ ጀምሮ ውዱሴ ማርያም አንቀጸ ብርሃንን ይዌድሰዋ መላክትን መልክዐ ማርያም፣ መልዕከ ኢየሲስን ሥርዓተ ቅዳሴን አጠናቆ ማወቅ አለበት፡፡
  ዲያቆናት ከማዕረጋቸው የሚሻሩበትም ሁኔታ አለ ሁለት ሴት ያገባ ወይም አግብታ የፈታቸውን ሴት ያገባ ሥልጣን ይሻራል ቤተ ክርሲታናችን ሥዕራት ላይ የተቀመጠ ሲሆን በጋምቤላ ሀገረ ስብከት በተላዩ ጊዜ ህግ ቤተ ክርሲቲያን በመጣስ አግብታ የፈታቹን ሴት ጋር ለማጋባት ጭራሽ የሚያሳዝኖ ነገር አብሮ አንድ ላይ በመኖር ላይ ያሉትን ሁለቱ ተጋብዎችን ማዕረጉን በመጥራት ለመጋባት እየመኮሩ መሆን እንዲሁም ሰው ብቻውን ይሆን ዘንደ መልካም አይደለም ዘፍ2፣18 ዲ/ን ናትናኤል አለምነህ እና የወ/ሪት ጥብ አርኮ በመላለት የአገረ ስብከቱ መለዕክት እየስተላለፈ ይገኛል ፡፡
  አንድኛ ከላይ ስሙ የተጠቀሰው ዲቁንኑ የአገረ ስብከቱበ ዋና ፀፍ ሲሆን በየወረዳው ቤተ ክርሲቲያን 150,000 ብር የተቀቤለ ሀገረ ስብከቱ ሁለት ባጃጅ በቴ ክረሲቲያነቱ የገዛ መሆኑን
  በአገረ ስበሰከቱ ስራካጅ በኩል ቁጥር ስፍር የላቸውን ታቦት ደብር ላይ በመስጋባት የሚታወቁ ጋምቤላ ከተማ ላይ ብቻ ያለው የታቦቱ ብዛት ማየይት በቅ ስለሆነ በገዳም ላይ ብቻ 12 ታቦት ጄበ ላይ 16 ታቦታት ቅድስት ኪዳኒ ምረት 9 ታቦት ቁዶዱስ ሚካኤል 5 ታቦታት ቅዱስ ገርብኤል 5 ጽላት ሥላሴ በቴ ክርሲታያን ደግሞ 3 የሚገኙ ሲሆን አብዛኛው ጽዕላት ትክክለኛ ስለመሆኑ ጠቅላይ በቴ ክነት አጣሪ ጉዳዩን በከታተል እንይላለን፡፡
  በሁለተኛ ደረጃ ታቦታት የቅድስት ኪዳኒ ምረት የአፀደ ሕፃናት ት/ቤ የሚሰበሰበው ገንዘብ በምን አገልግሎት እንዲውል ቢጠየቁልን
  ከመናፊቃን ድሪጅት ጋረ ያላቸውን ግንኙነት የነሱን መጽፍት በማስራጨት ጭምር የሚያደጉት ጉዳይ ቢጣሪልን
  ሚንባስ በመግዛት 2003 ላይ ወደ ጋምቤላ ካመጡ ብኋላ ወደ ሌላ ቦታ ማሸሽ ቸውን ቢጠየቁልን
  ስበካው ጉባኤ ምርጫን በየ ሦስት ዓመት የማደረግበት ምክንያት በጠየቁልን
  ሰበካው በቅድስ ከዳነ ምርት ላይ የተሰሩትን ሥራዎች በዝርዝር ለህዝብ ክርሲታኑ ሪፖርት የመያቀሩብት ምክናትና አቦ ተክለዓማኖት ባጎ ፍቃድ ብቻ ላይ የተመሰረት የሰበካው ጉባኤ ምርጫን የፈለጉትን ሰው እንዲቀጥል በማድሬግ የአሰራር ችግር አለብን ብሎ ጥያቄ የሚያቀርብ የሰበካ ጉባኤ አባላትን በመባረሪ የፈለጉትን ሰው ገቤቱ በመጥራት በራሳቸው ሃላፍነት ብቻ የሰብካው ጉባኤ አመራር በማድሬግ ቃለ አዋድ ውጭ በቀሳቀስ ጉዳይ በተመለከተ ቢጣራሊን
  የጋምቤላና ደቡብ ስዳን ሀጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሥዐተ ቤተ ክርሲቲያን ያልጠበቀ አሰራር የተሰራው ከመሆኑን የተነሳ በነፋሰ የተወሰደ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርሲቲያን 2005 ዓ.ም መሆኑን ይታወቃል፡፡ ጽዕላቱ የት እንዲምገኝ ቢጠየቁልን በመቀጠል ለጠቀላይ ቤተ ክነት የሚያቀረቡትን ሪፖረት በተመለከተ አጣሪ ኮሚተ ብላክልን፤
  በመናፍቃን ድርጅት የተዘጋጀውን መጽፍት እያሰራጩ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

  በጎግ ወረዳ በንፋስ የተወሰደ በቆመስ አባ ተክለ ሃይማኖት የተሰራ ቤተ ክርሲቲያን 2005 ዓ.ም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: