ፓትርያርኩ በሕግ አፍራሽነታቸው ጸኑ፤ በአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ምርጫ ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጋራ እንዲግባቡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም

Aba Mathias

 • መመሪያቸው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶሱ ስብሰባ ያቀረበውን ስጋት አጣጥለውታል
 • በአ/አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ምርጫ እና ሥያሜ የፓትርያርኩን የአካሔድ ስሕተት ከማረም አንጻር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ እና መመሪያ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል

በሥራ አስኪያጅ ምርጫ እና ሥያሜ አለመግባባቱ አጋጣሚ፣ ፓትርያርኩ፡-

 • ረዳት ሊቀ ጳጳስ መርጦ ከማቅረብ ድርሻቸው በላይ በቅዱስ ሲኖዶሱ የሚወሰነው የመመደቡም ጉዳይ ከእርሳቸው ሓላፊነት ጋራ እንደሚያያዝ በመመሪያቸው ከመጥቀስ አልፎ፣ ‹‹እኔ[ሥራ አስኪያጅ] መድቤአለኹ፤ ሾሜአለኹ፤ የሚሠሩ ከኾነ ተስማምተው ይሥሩ›› በማለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱን ሚና ፋይዳ ቢስ ማድረጋቸው፤
 • በብፁዕ ዋና ጸሐፊው የሚመራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ የቋሚ ሲኖዶሱን መነጋገርያ ርእሰ ጉዳይ አዘጋጅቶ ለውይይት የማቅረብ ተግባሩ መሠረት፣ በትላንትናው ዕለት በአድራሻ የተጻፈለት የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጥያቄ በአጀንዳነት ተይዞ እንዲታይ ሲጠይቅ፣ ጉዳዩን ለውይይት ዝግ ከማድረግ አልፎ ብፁዕ ዋና ጸሐፊውን በአሳዳሚነት መውቀሳቸው

እንደ ቅዱስ ፓትርያርክ መጠን፣ ሕጉን ተገንዝቦ እና ጠብቆ ለቤተ ክርስቲያን ከአድልዎ የጸዳ አጠቃላይ አባታዊ አመራር በመስጠት ረገድ ያለባቸውን የታማኝነት ውስንነትና የአማሳኝ አማካሪዎቻቸውን በተለይም በተደጋጋሚ ሲጋለጥ የቆየውን የልዩ ጸሐፊአቸውን ተንኰል እና ክፋት በገሃድ ያረጋገጠኾኖ አልፏል፡፡

Advertisements

24 thoughts on “ፓትርያርኩ በሕግ አፍራሽነታቸው ጸኑ፤ በአ/አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ምርጫ ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጋራ እንዲግባቡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም

 1. Anonymous March 27, 2015 at 6:45 pm Reply

  ere ebakachihu yeselam negern bicha aqrbulen! Hul gize Abatochin bich mezlef eskemech new

  • Gebre tsadik Yihdego March 28, 2015 at 7:49 am Reply

   አሁንኮ ቤተ ክርስቲያኗ ፖትርያርክ የላትም እሳቸው የሌላ ተወካይ ናቸው፡፡ የሚያስፈጽሙት የሌላ አካል ተልእኮን እንጂ የቤተ ክርስቲያንን አይደለም፡፡ ይኸውም ከሥራቸው ይታወቃል የሚሠሩት የቤተ ክርስቲያንን ሥራ ሳይሆን የሌሎችን ጉይል ማስፈጸም ነው፡፡ እንዲህ የመናፍቃን መጫወቻ ትሁን ቤተ ክርስቲያናችን ይባስ ብለው የለየለት መናፍቅ አእመረን አዲስ አበባ ላይ ያስቀምጡት አረ ጉድ ነው ጉድ ነው ጉድ ነው፡፡ በቃ ይህች ቤተ ክርስቲያን ሰው የላትም ሀይ ባይ ጠፋ ማለት ነው፡፡ የሚመራን አባት ያስፈልገናል ድሮውኑ የተወገዙ ሰው አምጥተው ያስቀመጡብን ለዚህ አይደል፡፡ አረ አባት አባት… አልወጣልን አለ..

   እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
   ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
   ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
   ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡፡፡
   አበው ይናገሩ

   እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
   የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
   የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
   መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡

   እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
   ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
   ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
   ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡

   ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
   ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
   ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
   ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
   ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡

   ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ
   የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡
   ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
   እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡
   ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት?
   ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት?
   ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት?
   እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡

   ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
   ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
   እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
   ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
   የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
   በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
   ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው?

   ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው
   የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው?
   ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
   ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት?
   አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ
   ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ?
   ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ
   ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡

   የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች
   ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡
   የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት
   ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡
   እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
   የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ?
   የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ?
   መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡

   ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው
   በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው?
   ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና?

   በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ
   መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ
   የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ
   እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ?
   የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው
   የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው
   የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው
   የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?
   ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ
   ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ
   እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ
   ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡

   ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር
   መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር
   ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን
   ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን
   ልሳነ ጤዛ መናፍቅን
   ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡
   በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ
   ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡

   ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት
   እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት
   ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ
   ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡

   የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት
   ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት
   ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት
   የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት
   ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር
   የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

   ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ
   ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡
   ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ
   መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ
   ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ
   መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡

   እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት
   ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡

   እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
   ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
   ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ
   ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡

   ምንጭ፡- መለከት 1ኛ ዓመት ቁጥር 6

   • Anonymous March 28, 2015 at 10:30 am

    Selam bewestachu yelemena yeselamen neger maseb atchlum.

   • Anonymous March 28, 2015 at 10:36 am

    Ye amlaken sem eyeteru abatoch mesadeb jegnenet hone ende??? Man new endezi yastemarek??? Yasaznal !

 2. ኅይለ ገብርኤል March 27, 2015 at 8:08 pm Reply

  በዘረኝነት በወንዝ በመናፍቅነት(የቤተክርስቲያንን ሕግ መጣስ =መናፍቅነት ስለሆነ) የሰከሩ ፓትርያርክ:ልብ እንዳይሰጣቸው ልባቸውን ዝግ አድርገው በካድሬነት ሰክረዋል

 3. Anonymous March 27, 2015 at 8:25 pm Reply

  May lord protect our patriarch. Im concerned if in case MK is thinking of assassination of the patriach or people standing with the same idea. They wished it infront of the patriarch few months ago. From what I see on this blog, and from what their preachers are preaching on their web and blog. I really am concerned.

  • Anonymous March 28, 2015 at 7:31 am Reply

   Oh! Mk is a very peaceful christian community… We would never even think of such a thing… Egzer betekrstianin enditebik tselotachin new… Wendmachin atisasat

   • Anonymous March 28, 2015 at 10:23 am

    That’s not what I have seen and am seeing several times.

 4. Anonymous March 28, 2015 at 5:13 am Reply

  ohh abet ere bemeherethi gobgnen

 5. Anonymous March 28, 2015 at 5:21 am Reply

  Hara mereja akirabe enamesgenalen

 6. wud March 28, 2015 at 5:34 am Reply

  We’re going down
  Are these people really ours?
  It feels like a game for two…lol

 7. nehmiashishay March 28, 2015 at 5:40 am Reply

  aydelem metarem yalebet enditarem yegid megaletu yitekimal

 8. Yared March 28, 2015 at 8:35 am Reply

  Gudish new Group of blind extreemists.

 9. Anonymous March 29, 2015 at 4:15 pm Reply

  ከእባብ እንቁላል እርግብ እንጠብቅ ወይ?

  የእኚህ ፓትሪያርክ የሹመት ሂደት እኮ ገና ከምርጫ ሂደት ጀምሮ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ሥርዓት ያልጠበቀ ነው እኮ፡፡

  በየትኛውም የፕትርክና ምርጫም ይሁን በማንኛውም የቤተክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ሂደት የሚከናወነው (የሚካሄደው) እንደ ዘመኑ ፓለቲካ የቀበሌ ሊቀመንበር ምርጫ በካርድ ሳይሆን ዋና ዋና እጩዎችን (ወይም ተግባራትን..) በመስፈርቱ መሰረት ከተለዩ በኃላ የመጨረሻ ሂደቱ የሚወሰነው በእጣ ነው፣ በአደባባይ፣ በአውደ ምህረት በህጻናት ወይም በበቁ አባቶች አይናቸው በሻሽ ታስሮ የዕጩዎቹን ዝርዝር ከአንድ ሰሃን ውስጥ በጸሎት፣ በምህላ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡ ይህ ሥርዓት ከቀደምት ቅዱሳን ሀዋርያት ተጀምሮ እስከ አሁን አሃት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እየተገለገሉበት፣ እየተተገበረ ነው፡፡ የአባ ማቲያስ ምርጫ ሂደት ግን በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሽፈራው ተ/ማርያም እየተመራ በደህንነት ካድሬዎች የተከናወነ ነው፡፡

  ስለዚህ በዚህ ሂደት የመጣ ማንኛውም አካል ለቤተክርስቲያን፣ ለሀገር፣ ለምዕመን … ከቶ አይጠቅምም፣ አይበጅም፡፡ ስለዚህ እኚህ ግለሰብ የቤተክርስቲያኒቷ አደጋ እንጂ አገልጋይ እንዲሆኑ ማሳብ፤ ከእባብ እንቁላል እርግብ መጠበቅ ነውና ገና ብዙ ፈተናዎች ይጠብቁናል፡፡ …

  … ፍጹም አሳዛኝ፣ ፍጹም የክህደት ተግባር፣ የዘረኝነት፣ የዝርፊያ ተግባር … ፈጻሚ፣ ተባባሪና አስፈጻሚ ከመሆን የበለጠ ግን ምን እንደሚመጣ ሲታሰብ በጣም ከባድ ነው፡፡ ….

  • Anonymous March 29, 2015 at 11:31 pm Reply

   In most of Egyptian history, the patriarchs were selected by a vote. Why don’t you read? Le betekerestian mekorkor endante kehone, balkorekor yeteshale agzatalew. Ye awaki sew andebet endante kehone, alawaki mehonen emertalew. Menfesawinet endante kehone, be alem yeteshale ferdna tsedk ale.

 10. nehmiashishay March 30, 2015 at 5:37 am Reply

  አወ እኛ የምንለው ሃይማኖት እና ጎሳ እጅግ የተራራቁ ናቸው ስለዚህ እኛ ክርስትያኖች ግን ከ ጎሳ የበለጠ ዘር አለን እሱም የሥላሴ ልጅነት ነው የስላሴ ልጅነት የሚያደናቅፍ መሰናክል የሚሆን ሁሉ ቢሰደብ በነቀፍ ይገበዋል ኣባታችን እኮ ተሰሳቱ አልን እንጂ ሌላ ምን አልናቸው ስለዚ ሁለተኛ ሀሳብ ሰጪ ሰላም በውስጣችሁ የለምና ሰላም አትኖሩም ያልከው ግን ሰላም ከመንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶናል ሰይጣን ይፈትነን ዘንድ ግን የግድ ነው አንተ ግን ከአባትህ ከዲያብሎስ ስለ ሆንህ ሰይጣን አይፈትንህም ምክንያቱ ሰይጣን ሰይጣንን አይቃወምም አና

  • Anonymous March 31, 2015 at 7:38 am Reply

   Selam bewestek binor endezi atnagerm neber. Tefetgnalew kalk nesha abatkn agegne + tetemek. Fetari yerdak. Ayzok. Yabesacheken ena selamken yewesedewen guday kenesha abatek gar awrana miluken sema. Ayawkum ene negne mereja yalegne satel amlakachen besachew adro minegreken tekebel. Yane selamen tagegnal. Yewneten sew.

 11. Anonymous March 30, 2015 at 8:22 am Reply

  በዚህ ድርጊት ከንቡረዕድ ኤልያስ ይልቅ የበዙ ጳጳሳት በአካልና በስልክ ከፓትርያርኩ ተባባሪ እንደነበሩ ካልገባችሁ የወሬ ምንጫችሁን መፈተሽ ሊኖርባችሁ ነው፡፡ቢያንስ ሊቀ – አእላፍ በላይ ሊወርዱ እንደሚገባ አያሌ ጳጳሳት አቋም ይዘው ከፓትርያርኩ ጎን ተሰልፈዋል፡፡አዳዲሶቹን ተሹዋሚዎች በሚመለከትም በአዲሱ ሕገ – ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት መሆኑ በግልጽ ስለሰፈረ በረዳት ሊቀጳጳሱና በቅ/ፓትርያርኩ መሀል ሊፈታ የማይችል አለመግባባት ቢከሰት ፓትርያርኩ በሚሉት መሄድ እንደሚገባ ለመናገር የፍትሐ – ነገሥት ወይም የjurisprudence (ነገረ – ሕግ) ሊቅ መሆን አይጠይቅም፡፡

 12. Anonymous March 30, 2015 at 6:19 pm Reply

  ‹b> የዘመናችን የቤተክርስቲያን ፈተናዎች፡-
  1. በቤ/ክ ላይ የተሀድሶ መናፍቃን በውስጥና በውጭ የተቀናጀ ሴራ፣
  2. በቤ/ክ ውስጣዊ አስተዳደር ላይ የጸረ-ተዋህዶ ካድሬዎች ጣልቃ ገብነት፣
  3. የእናት ጡት ነካሽ ሙሰኞች፣ ዘረኞችና ማህይማን የቤተክህነት፣ የአድባራትና ገዳማት ሹማምንት የሙስና ተግባራት፣…
  4. የምዕመናን ግዴለሽነት፣ የዕውቀትና የምግባር ደካማነት፣ …
  5. የወጣቱ ትውልድ ለግሎባላይዜሽን መጥፎ ተጽዕኖዎች ተጋላጭ መሆን እና
  6. የእኛ የኃጥያት ውጤት፡፡

   መፍትሔውስ?
  ———————————————————————-
  </b

  • Anonymous March 31, 2015 at 6:47 am Reply

   ፈተናዎቹን ጥሩ ገልጸሀቸዋል፡፤ብቻ የዘለልከው አለ፡፡እኔ ልሙላው፡-
   7. ከኔ በላይ ኦርቶዶክሳዊነት ላሳር የሚል ገፊነት፣መታበይ፣ገደብ የለሽ ጣልቃገብነት፣ያልተቋረጠ የሐሜት ጎዳና፣ራስን መቆለል፣የገሰጹትን ሥም ለጥፎ ማሳደድ፣የቲፎዞና የእወደድባይነት ፈሊጥ
   8. ሐራን ጨምሮ በየብሎጎቹ የሚራመደው የሐሜት ጎዳና፣በአባቶች መሀል እርስበርስና እንዲሁም አባቶች ከምዕመናንን የሚገናኙበትን ድልድይ የሚያወድም አፍራሽ አካሄድ፣የአባቶች ደረጃ መዳቢ መሆን፣ተስፋ አስቆራጭ ዜናዎችን ብቻ ስራየ ብሎ በማሰራጨት ምዕመኑን ተስፋ ማስቆረጥ፣በቡድንተኛነተ የታጀበ አቀራረብ የሚል ጨምርበት፡፡

 13. Anonymous March 30, 2015 at 9:07 pm Reply

  libonuna yistachew.

 14. Anonymous April 1, 2015 at 2:50 pm Reply

  ራሄል ሥለልጆችዋ አለቀሠች መፅነናናትም አልወደደችም እዳለው መፅሀፍ ቅዱሥ እኛም የተዋህዶ ልጆች ሁሌ እንዳለቀሥን ነው የቤተክርሥቲያናችን አንባገነናዊ አሥተዳደር ሁሌም አንገት እያሥደፍን ነው እግዝአብሄር ሁሉም ቻይ ነው

 15. We can against why poletics in the church April 7, 2015 at 3:35 am Reply

  Why politics in church? We should listen to our fathers and mothers!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: