ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ ቋሚ ሲኖዶሱን በመተላለፍ በድጋሚ መመሪያ ሰጡ፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለከፍተኛ ውዝግብ እንደሚዳርግ በመግለጽ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ያገናዘበ ተለዋጭ መመሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል

Aba Mathiasብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፡-

 • ‹‹የአ/አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት ነው›› የሚለውን ድንጋጌ ተገን አድርገዋል
 • የወቅቱ ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዲዛወሩ አዝዘዋል
 • የሀ/ስብከቱ ብልሹ አሠራር የቀጠለው ሥዩማኖቹ ‹‹በወቅቱ ሥራ ባለመጀመራቸው ነው›› ብለዋል

His Grace Abune Mathewosብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ፡-

 • ተጠሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስም ለፓትርያርኩም የኾኑት ረዳት ሊቀ ጳጳሱ አልተስማሙበትም
 • የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ድርሻ ከሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት ተግባርና ሓላፊነት በተለየ አልተዘረዘረም
 • የአ/አ ሀ/ስብከትን ልዩ ኹኔታዎች ያገናዘበ የሥራ አስኪያጆች አሿሿም ዝርዝር አልወጣም
 • ፓትርያርኩንና የሀ/ስብከቱን ረዳት ሊቀ ጳጳስ የሚያስማማ ተለዋጭ መመሪያ ይሰጠኝ

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ከረዳት ሊቀ ጳጳሳቸው ስምምነት ውጭ በራሳቸው ቀጥተኛ ውሳኔ ለሠየሟቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች፣ በዛሬው ዕለት የምደባቸው ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ለኹለተኛ ጊዜ መመሪያ ሰጡ፡፡

‹‹ሕጋዊ አሠራርን በእጅጉ የሚፃረር ነው›› በሚል ከረዳት ሊቀ ጳጳሱ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠመውንና ከሕገ ቤተ ክርስቲያን አንጻር በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ የአፈጻጸም ጥያቄዎች የተነሡበትን ያለፈው ሳምንት የመጀመሪያ መመሪያቸውን ያስታወሱት ፓትርያርኩ፣ ‹‹የተሰጠው አመራር ባለመፈጸሙ በሀገረ ስብከቱ ያለው ብልሹ አሠራር እንዲቀጥል እየተደረገ ነው፤›› በማለት ነው መመሪያውን ለኹለተኛ ጊዜ የጻፉት፡፡

ፓትርያርኩ ከልዩ ጽ/ቤታቸው በቁጥር ል/ጽ/312/10/2007 በቀን 14/7/2007 ዓ.ም. በድጋሚ መመሪያ በሰጡበት በዛሬው ደብዳቤአቸው፣ የወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን እና ምክትል ሥራ አስኪያጁ መ/ር ኃይለ ማርያም ኣብርሃ ከሓላፊነታቸው መነሣታቸውንም አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ደረጃቸውን በጠበቀ ኹኔታ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ተዛውረው እንዲሠሩ›› እንዲደረግና ይኸው መመሪያም በዛሬው ዕለት ተፈጻሚ እንዲኾን በጥብቅ አስታውቀዋል፡፡

የፓትርያርኩ የሹመት መመሪያ ‹‹በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅራዊ ሒደት ያልተለመደ ነው›› ያሉት በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በበኩላቸው፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅም ኾነ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ተጠሪነት ለቅዱስ ፓትርያርኩ ኾኖ እንደማያውቅና መኾንም እንደማይችል ለቅዱስነታቸው በአድራሻ በጻፉት ደብዳቤ በማስታወስ፣ አካሔዱ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቃለ ዐዋዲ ደንቡ እና ከሀገሪቱ የሕግ አሠራር ጭምር ውጭ ኾኖ እንደተመለከቱት ገልጸዋል፡፡

የፓትርያርኩ አካሔድ የሕግ ድጋፍ የሚኖረው፣ የሀገረ ስብከቱ ረዳት ሊቀ ጳጳስ መርጦ አቅርቦ ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጋር ጭምር የጋራ ስምምነት ሲደረስበት እንደኾነ ብፁዕነታቸው አስገንዝበዋል፡፡ አሠራሩ እንደ አጠቃላይ ሲታይ ከትዝብት ላይ የሚጥል መኾኑን በመጥቀስም ‹‹ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላማዊ አሠራርና ለኹላችንም ሰላም›› ሲባል ፓትርያርኩ ውሳኔአቸውን እንደገና እንዲያጤኑ አሳስበዋቸዋል፡፡ የሹመት መመሪያውን እንዲሰሙት የተደረገው በግልባጭ ቢኾንም በተካሔደው የሥራ አስኪያጅ ምርጫ እንደማይስማሙና የመመሪያውን ተፈጻሚነት ለማስተናገድ እንደሚቸገሩም አስታውቀዋቸዋል፡፡

የፓትርያርኩ ተደጋጋሚ የሹመት መመሪያ በአድራሻ ሲጻፍላቸው፣ መመሪያው ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ደንብ አኳያ እንዲጤን የሚያሳስበው የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ደብዳቤ ደግሞ በግልባጭ የደረሳቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስም፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ የቋሚ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ወቅት፣ የቅዱስነታቸውን አባታዊ መመሪያ ለማስፈጸም ዝግጁ መኾናቸውን ነገር ግን አፈጻጸሙ አከራካሪ ሐሳቦችን ስለሚያስነሣ የሚያስከትለው ውዝግብና አለመግባባት አስቀድሞ በስፋት እንዲጤን ጠይቀው ነበር፡፡

ቋሚ ሲኖዶሱን በርእሰ መንበርነት የሚመሩት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሐሳብ በአጀንዳ ተይዞ እንዳይደመጥ ለማድረግ ‹‹ውሳኔ ነው፤ መታየት አይችልም›› በማለት ቢቃወሙም ቋሚ ሲኖዶሱ ብፁዕነታቸው አስተያየታቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ በመስጠት ለቀጣይ ስብሰባ እንዳሳደረው ተዘግቦ ነበር፡፡

በዚኽ ኹኔታ ውስጥ ነው እንግዲኽ፣ ፓትርያርኩ ሥዩማን ሥራ አስኪያጆቻቸው ሥራ የሚጀምሩበት የምደባው ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ‹‹በጥብቅ አስታውቃለኹ›› በማለት ለኹለተኛ ጊዜ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን በዛሬው ዕለት ያዘዟቸው፡፡

ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ በበኩላቸው፣ በዛሬው ዕለት በቁጥር 3156/357/2007 በቀን 14/7/07 ዓ.ም. ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጻፉት ማስታወሻ፣ ከመመሪያው አፈጻጸም በፊት ምላሽ ይሻሉ ያሏቸውን አከራካሪ ሓሳቦች በመዘርዘር ቅዱስነታቸውንና የሀገረ ስብከቱን ረዳት ሊቀ ጳጳስ የሚያግባባ ተለዋጭ መመሪያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ታውቋል፡፡

ብፁዕነታቸው በማስታወሻቸው በቀዳሚነት ያነሡት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን አወቃቀር ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ወር ፳፻፯ ዓ.ም. በአጸደቀው ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፶ ንኡስ አንቀጽ (፩) እና (፪) መሠረት÷ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት እንደኾነና ሀገረ ስብከቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ አቅራቢነት ተጠሪነቱ ለቅዱስ ፓትርያርኩ የኾነና በቅዱስ ሲኖዶስ የሚመደብ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እንደሚኖረው መደንገጉን ብፁዕነታቸው ዘርዝረዋል፡፡

በዚኹ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ(፫)፣ ሀገረ ስብከቱ የአገሪቱ ርእሰ ከተማ ስለኾነና ከሌሎች አህጉረ ስብከት የሚለይባቸው ልዩ ኹኔታዎች ስላሉ እኒኽን ኹኔታዎች ከግምት ያስገባ ለየት ያለ አደረጃጀት በቃለ ዐዋዲው እንዲኖረው ይደረጋል ማለቱን ያመለከቱት ብፁዕነታቸው፣ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሹመትን በተመለከተ ‹‹የሥራ ዝርዝር ያልወጣና ወደፊት በቃለ ዐዋዲ የሚወጣ መኾኑን ነው የሚጠቅሰው›› ብለዋል – ተጠሪነታቸው ለሊቃነ ጳጳሳት ከኾኑት የሌሎች አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች የተለየ አለመኾኑን በማመልከት፡፡

ከሕጉ አኳያ ምላሽ ማግኘት ይገባዋል በሚል በብፁዕነታቸው የተቀመጠው ተከታዩ አከራካሪ ሐሳብ፣ በሀገረ ስብከቱ የረዳት ሊቀ ጳጳሱ የሥራ ዝርዝር ተለይቶ አለመውጣቱን ነው፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ ፶፫ ንኡስ አንቀጽ ፰፣ ለሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ብቁ የኾነን ሰው መርጦ ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በማቅረብ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲስማማበት በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ ፊርማ እንዲሾም የማድረግ ተግባርና ሓላፊነት የሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት እንደኾነ ተደንግጓል፡፡ ይኹንና አዲስ አበባ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት እና ራሱን የቻለ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ያለው ሀገረ ስብከት እንደመኾኑ መጠን የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ተጠሪነት ለቅዱስ ሲኖዶስ እና ለቅዱስነታቸው ቢኾንም ለረዳት ሊቀ ጳጳሱ ከሌሎች አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት የተለየ የሥራ ዝርዝር አልወጣለትም፡፡

የሀገረ ስብከቱ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ባልተስማሙበት ኹኔታም ፓትርያርኩ በራሳቸው ብቸኛ ውሳኔ ለመደቧቸው ሥራ አስኪያጆች ‹‹አኹን እንዲሾሙ ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተብሎ የተሰጠውን መመሪያ መሠረት በማድረግ ቢጻፍ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለከፍተኛ ጭቅጭቅ እና ውዝግብ የሚዳርግ መኾኑን›› ፓትርያርኩ እንዲገነዘቡት ብፁዕነታቸው አሳስበዋል፡፡ ስለዚኽም በዝርዝር ያስቀመጧቸው ነጥቦች ምላሽ ሳያገኙ ከሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ውጭ የሥራ ስሕተቶች ተፈጽመው ቢገኙ ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመኾኑ ‹‹ቅዱስነትዎንና የሀገረ ስብከቱን ረዳት ሊቀ ጳጳስ የሚያግባባ ተለዋጭ መመሪያ እንዲሰጡኝ›› በማለት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ባቀረቡት አጭር ማስታወሻ ጠይቀዋል፡፡

ይኸው የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የጽሑፍ አስተያየት ከነገ በስቲያ በሚካሔደው የቋሚ ሲኖዶሱ ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባ ቀርቦ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረት ቋሚ ሲኖዶስ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ኾኖ በቅዱስ ሲኖዶሱ የጸደቁት ሕገጋት፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎች በሥራ ላይ መተርጎማቸውን የሚከታተልና የሚቆጣጠር አካል ነው፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መቅረብ በማያስፈልጋቸውና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሚሰጣቸው ውሳኔዎች ላይ የሚቀርቡ የይግባኝ(የቅሬታ) አቤቱታዎችንም መርምሮ የመወሰን ተግባርና ሓላፊነት አለው፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተመርጦ በፓትርያርኩ ፊርማ የሚሾመው ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ፣ የቤተ ክርስቲያንን የሥራ አስፈጻሚነትና የአስተዳደር ተግባር በከፍተኛ ደረጃ የማከናወን ሥልጣን ያለውን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሚመራ ሲኾን ተጠሪነቱም ለቅዱስ ሲኖዶስ እና ለቅዱስ ፓትርያርኩ እንደኾነ ተደንግጓል፡፡

Advertisements

27 thoughts on “ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ ቋሚ ሲኖዶሱን በመተላለፍ በድጋሚ መመሪያ ሰጡ፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለከፍተኛ ውዝግብ እንደሚዳርግ በመግለጽ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ያገናዘበ ተለዋጭ መመሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል

  • Mulumebet March 25, 2015 at 7:31 am Reply

   Let GOD protect our religion and our church leaders. We have no power except praying to Almighty GOD.

   We all request our Mother Sr. Mary to request Mercy from our Father for all of us.

 1. abera March 23, 2015 at 10:17 pm Reply

  MK, you are speaking non sence and trying to influence the pops and synod for ur will with all possible sensless reasons. University students first rose their hands on the king elected by God for Ethiopia, Haile Selasse. The result was death for 1 generation +a patriarch + separation of the ethiopian church synod. These days through MK, university students are raising their hand on their own patriarch. For sure the result is going to be double hard ! May God save my country and church from the savage political works of Mahbere Kidusan. Amen. What a sad story. Though everyone knows the inside work, people are still trying to hide a truth. Why do you have to fight for your name, power and money mahbere kidusan???

  • Dinku March 24, 2015 at 2:17 am Reply

   Abera – Just citing prominent names and writing what you simply think doesn’t make you smart. Before you write, read read read and read more, and write the reality not your emotions. See you, may be after you become old and smart enough to distinguish between your emotions and the reality you are trying to cover.
   Edeg😊!

   • abera March 24, 2015 at 11:22 am

    Hey, I read a lot. I research a lot. I don’t speak before prominent evidences. I’m not driven by a talk. I know ….i have worked with them. They fooled me after together we worked for a fund raising for a gedam. At the end they took all the money that belong to the gedam. For now, im not in addis ababa. Soon I will be there. I will post all their work online. I have the evidences. I’m not the one running for fame and money. I’m from gebi gubae….I was sera asfetsami. I know them all. I ve worked in their maekels. You dont know what the higer diakons do but the lowerlower’s dont know. I know it all. I know how they work polithically. I’m afraid that there may be a blood shadee due to this mahber. Ye heywet weyeyet eyetebale setesebesebu, wektawi ye bete kerestian huneta eyetebale haset sinegerachu hulum ewnet yemeslachwal. I ve workes with pops. I know how mk plays the game. The problem is not from the pops. I know brother. … I know. It’s not as you think I know. I don’t have chifen telacha or chefen degaf for mk. But what you now are doing will not have a good consequence. And u know it well. Kefreachu akachualew. Andebetachu abatoch lay endih sinager yelebachew kefat adebabay taytoal. Enes…..enes ke betekerestiane gar eseralew. Gezebwan endenesu shiche kise alagebam. Wendeme westun mech ayehew? Alawekewemna…..kefatenem….MENALBAT… alayehatmna alferdbhem. Ene gen haset sidereg ferd sizaba be adebabay siwash siserek mk hone a priest zem alelem. Lehuletum enageralew. Mk selemisetew gubo atakum….ene be ayne aychalew. Selemiasdebedbachew sewoch atakum…..ene be enba tekerakere bians anduan lej kedebdeba atrfeatalew. I know wedaje. I know. And im telling you the truth of what I know under God. Amlakachen seneleyay zem aybelben. Fetenawen kehulachnem yarek. Fiker yesten. Selamun yabzalen. Yebarken. Abatochachenem yebarkun. Lezelalem be andnet yauren. Fetro aytewen. Leneseha mot yabkan. Meleyayeten yarekelen. Haseten kelebachen yatfa. Tsedk enemola. Kekefu menged yetebken. Fekadu begna lay yehun. Lezelalemu Amen.

   • asnake March 24, 2015 at 12:56 pm

    @abera-u seem akadirea kkkkk why u hate mk???? before pointing ur finger on others go to ur inside and wash ur heart which is filled with dirty game called politics!!!!

   • abera March 25, 2015 at 12:47 am

    Is it my heart which is filled with politics? Are you sure?

  • Anonymous March 24, 2015 at 2:17 pm Reply

   oh! abera,u nailed it.ignore those brainwashed folks.they act as if they r masterminds of z church.we know their ill motive(save z good one).we r waiting for them till they cross z red-line.don’t cry.don’t bow-down for them.they fabricate accusations, disseminate it, count themselves as a witness, place themselves in court of the judge;then preach us about fairness&justice.what a FERISAWI generation.the saddest story is most of BISHOPS and beloved members r not aware of their leaders who r messing both z church and z country. soon or later they will pay for it.MK’s ledership biased,politicized, tribalist, self-centered approach,exploitation of communication gap of BETEKIHNET for its cult-led propaganda is costing EOTC as an institutions. they r eroding trusts b/n our Fathers.playing divisive role.labeling one as an enemy of EOTC, z other as a saint without a tangible parameter.their usual parameter is an attitude towards MK.whoever praised mk will be praised, whoever criticize mk will be prosecuted. we witnessed it for two decades.same principle resuming on Abune Mathias.NOTHING IS NEW!

  • Anonymous March 26, 2015 at 7:15 am Reply

   My freind Abera,
   We know MK and let’s see ur research and what you read before. I think you are a member of this zeregna and gubogna pop muday mitsiwat sebary.

 2. በር March 24, 2015 at 2:56 am Reply

  እግዚአብሔር መልካሙን ያሳስባቸው
  በማህበሩ ላይ ጭፍን ጥላቻ ያላችሁ በክንቱ አትድክሙ ስሚ የላችሁም

 3. Anonymous March 24, 2015 at 5:50 am Reply

  Abera – I can’t understand the relation between MK and the situation that took place in the Bete kihnet. can you explain please or you are trying to divert attention to.

 4. Anonymous March 24, 2015 at 6:36 am Reply

  Abera, do you live on earth or not? Because what you say is not on earth;It is a simple talk.Do you think that our pope is right?

 5. ለይኩን ልመንህ March 24, 2015 at 7:46 am Reply

  1. ተጠሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስም ለፓትርያርኩም የኾኑት ረዳት ሊቀ ጳጳሱ አልተስማሙበትም ስለተባለው፡- ሊቀ – ጳጳሱ ለፓትርያርኩ ተጠሪ መኾናቸው እስካልተካደ ድረስ የፓትርያርኩን ውሳኔ ተቀብሎ አንድ ወር የሞላ ጊዜ ላልቀረው ለግንቦቱ የርክበ – ካሕናት ቅ/ሲኖዶስ በፓትርያርኩ ውሳኔ ላይ ቅሬታን በአጀንዳነት ማስመዝገብ የተሻለ ነው፡፡ያ ካልኾነ ግን ፓትርያርኩ ከቅ/ሲኖዶስ በተጨማሪ ተጠሪነታቸው በሥም ለተጠቀሱት (ለስራ አስኪያጆቹ) ብፁዐን ሊቃነ – ጳጳሳት ሊመስል ነው፡፡ ረዳት ሊቀ – ጳጳሱ ለፓትርያርኩ ያላቸው ተጠሪነትም የይስሙላ መባሉ ነው፡፡ “ልዩ ሀ/ስብከት” የሚለው ቃልም ትርጉም ያጣል፡፡
  2. የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ድርሻ ከሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት ተግባርና ሓላፊነት በተለየ አልተዘረዘረም ስለተባለው፡- ካልተዘረዘረ ክፍተቱ ሊሞላ የሚችለው “ተጠሪ የኾኑላቸው ቅ/ፓትርያርኩ እና ቅ/ሲኖዶስ በሚሰጡዋቸው መመሪያ መሰረት” ተብሎ ነው፡፡ረዳት ሊቀ – ጳጳሱ በቅ/ሲኖዶስ ቢሾምም አቅራቢው “አዲስ አበባ ልዩ ሀ/ስብከታቸው ነው” ተብሎ በቃለ – ዓዋዲው የተደነገገላቸው ቅ/ፓትርያርኩ መኾናቸውን አንዘንጋ፡፡ስለዚህ የረዳት ሊቀ – ጳጳሱ ሥልጣን እና ኃላፊነት ስላልተዘረዘረ የፓትርያርኩን መመሪያ የመቀበል ግዴታ የለባቸውም ወደሚል መደምደሚያ እንዳንደርስ ብንጠነቀቅ አይከፋም፡፡በአ/አ/ሀ/ስብከት ላይ የሚሾም ሊቀ – ጳጳስ ያለው መዐርግ “የቅ/ፓትርያርክ ረዳት” የሚል መኾኑ፣ሀ/ስብከቱ ከገቢው 65 በመቶ ለጠ/ቤ/ክሕነት የሚገባ መሆኑ፣ረዳ ሊቀ – ጳጳሱ ቦታውን የሚይዘው ከሌላ ሀ/ስብከት ጋር ደርቦ ላልተወሰነ ጊዜ (በልማድ ፓትርያርኩ እስከተስማሙ ድረስ ) መኾኑ (የረዳት ሊቀ – ጳጳስ አስተዳደረዋ ነጻነት መጠበቅ ያለበት መኾኑ ሳይረሳ) ሥልጣኑ የቅ/ፓትርያርኩን ድርሻም ያገናዘበ መኾኑን ያሳያል፡፡ስለሆነም ካልተዘረዘረ ተዘርዝሮ እስኪደነገግ ድረስ በእሳቸው መመሪያ ክፍተቱ ይሞላል እንጅ ስላልተዘረዘረ ፓትርያርኩ የሚሰጡት መመሪያ መሰረት የለውም ማለት አይደለም፡፡
  3. የአ/አ ሀ/ስብከትን ልዩ ኹኔታዎች ያገናዘበ የሥራ አስኪያጆች አሿሿም ዝርዝር አልወጣም ስለተባለው፡- ዝኒ ከማሁ፡፡
  4. ይሕ ክስተት ፡- ወደፊት ግልጽ የኾነ እና ዝርዝር መመሪያ በቅ/ሲኖዶስ ሊወጣ እንደሚገባ ያሳየ ይመስለኛል፡፡ስለኾነም የአቡነ ማቴዎስን መከራከሪያዎች ባልስማማባቸውም አከብራቸዋለሁ፡፡ሁኔታውንም በቤ/ክ ያለውን የአባቶቻችንን ብስለትና ጥንቃቄ የሚያመላት አድርጌ ነው የማየው፡፡ይሕ ኹሉ የሚኾነው በራሳችን መመዘኛ ሲመዘን ቢደክምም ከሌሎች ሃይማኖቶች ሲነጻጸር ግን በተሻለ መልኩ የተማከለና የተደራጀ አስተዳደራዊ መዋቅር ስላለን ነው፡፡በሌሎቹ የሃይማት ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ ችግር የማንሰማው ችግሩ ስለሌለ ሳይሆን ችግሩ ሊደመጥበት የሚችል ማዕከላዊ ተቋም በቅጡ ስለሌለ ነው፡፡ስለዚህ አስተዳደራችን ቅድስት ቤ/ክንን የሚመጥን ሊኾን እንዲገባው በቅንነት መትጋቱን ሳንስት ባለን መጽናናቱን አንዘንጋ፡፡

 6. Anonymous March 24, 2015 at 9:05 am Reply

  የምናስታውልበትን ልቦና እግዚአብሄር አምላክ ይስጠን ሌላ ምን ይባላል! በሚፈጠረው ችግር ሁሉ እጃችንን ወደ ማኅበር ቅዱሳን የምንቀስር ለምንድን ነው?

  • abera March 25, 2015 at 1:05 am Reply

   Ye chigru tensash, aramajna back boan man honena?? Chegerun man lay betesete ye video asteyayet tejemerena??? Hara tewahdona abelak beman back tefereguna? Bemanes andebet tenageruna??? Information keyet agegnuna??? if u want to track, there is nothing as such hidden. Speculially when you know how to manipulate the internet in the expert way.

 7. yemane March 24, 2015 at 10:11 am Reply

  “ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ እግዚአብሔር ምክር ሰናይት ለኵሉ ዘይገብራ”

 8. yemane March 24, 2015 at 11:28 am Reply

  በአንድ ግቢ አብረው እየኖሩ በአንድ ማእድ አብረው እየተሳተፉ ተማክረው አለመስራተቻው ያሳዝናል።

 9. Me March 24, 2015 at 12:50 pm Reply

  የተለዋወጡባቸ ደብዳቤዎች እስቲ ለማስረጃ አቅርቡልን

 10. Anoni March 25, 2015 at 6:34 am Reply

  @ Abera- Min likifit new yeyazeh, kewotaw zena gar mahiberkidusanin letagenagenew yemetemokerew? Egziabher yemarih/rish? Anbebo meredat chegeroh kehonem qena lebuna yestih.

  • abera March 27, 2015 at 12:09 am Reply

   Amen. Yayehuten helinaye alkebel selale new. Ene yayehuten deg yalhone neger ayasayek. Bene yederese yehelina metawek aydresbek. Yanebebkuten bego yahone yemahberun cheger ayasnebebek. Balehbet tsentek tseley. Keriwen amlakachen mehon endalebet yadegewal. Enenem antenem fetro aytewenem. Ayzoh atfra.

 11. Yared March 25, 2015 at 9:32 am Reply

  ወይ እናት ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር ያስብሽ ያጽናናሽም፡፡
  የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ያልሆኑ አባቶች እንዳይሾሙ በመፍራት የጳጳሳት ሹመት እየተገፋ አኅጉረ ስብከት ካለ አባት ዘጠኝ ዓመት ሊሞላቸው ነው፡፡
  አሁንም በ አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት የማኅበረ ቅዱሳን ሰው ስላልተሾመ ነው አይደል ይህ ሁላ መንጫጫት፡፡
  በቃ! ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ ቀረና ማኅበርን መጠበቅ እንደ ጽድቅ ተቆጠረ፡፡
  ኪርያላይሶን!!!
  ኪርያላይሶን!!!
  ኪርያላይሶን!!!

  ገ/ሚካኤል

 12. Gemechu March 25, 2015 at 12:17 pm Reply

  This shows the strength of our church. There is no place for dictatorship in our church. Thank you God

 13. ገረመው March 25, 2015 at 2:52 pm Reply

  ይህን የምትጽፉ የሐራ አድሚኖች ዛሬ በላይ ሲንሳ ሊቃነ ጳጳሳትና እናንተ እንዲህ የምትሆኑት ግለሰቡ ከሳህለ ማርያም ወዳጆ ጋር በመቆራኘት በሙሰኝነት ተጨማልቀው አገልጋዮችን ሲበድሉ ለምን ዝም አላችሁ? የድሆቹ ለቅሶ አይሰማችሁም የአንድ ግለሰብ መነሳት ግን ያንገበግባችሁአል፡፡ አዝናለሁ ሁሌም በጥቅም ከተሳሰራችሁት ጋር ብቻ ነው የምትሰለፉት? እውነትንና የእውነትን አምላክ ፈሩ፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሐሰት ወሬ አትበጥብጧት

 14. Anonymous March 29, 2015 at 12:25 am Reply

  are gira tegabehulachihu wedimoche eski mulu mereja akirbachihu lemasamen mokiru MK kezih guday gar min ayayazew

  • Anonymous March 29, 2015 at 4:02 pm Reply

   Ene balegne moya yesebesebkutwnena mesebesbewen mereja le betekehnet lemasrrekeb asbealew. Be ketita adebabay mawetabet kenem ruk ayhonm. Zare bawetaw gen ke St. Mariam betekerestian be fird bet kereker bewesedachut meret lay beserachut hentsana bematasmeremerut lemat tekuamachu besebesebachut asazagne ye betekerestian mehon yeneberebet genzeb mereja yawetuten akalat selemetatefuna selemtasadedu lemengestena le betekihnet and mimeleketachew akalat kemasrekeb begele ejemralew. Kememeker yelek selemetatefubet legizew ene lenante alekem. Rasachunem kerasachu yewenjel sera endatetebku moyayen alnegrachum. Gen tegermalachu.

  • Anonymous March 29, 2015 at 4:12 pm Reply

   You always try to escape pointing on others after messing up everything. Smarter than EPRDF! I admire you. You still want to play political games. If you want to know the truth, go to eotcssd.org as a start up. Then as an amater, the internet is a wide source of information. Finally, as you worked with MK for free, work with church fathers for free and you will know the difference as well as the truth. You have nothing to lose for doing this.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: